YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ በግፍ ለተጨፈጨፉት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብሄራዊ የሐዘን ቀን እንዲያውጅ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መጠየቁን ዋዜማ ዘግቧል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያውጀው የሐዘን ቀን በኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ደቡብ ክልሎች በተለያዩ ጊዜያት ለተገደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን መታሰቢያ እንዲሆን ምክር ቤቱ ጠይቋል። ማንነትን መሠረት ያደረጉ ኢሰብዓዊ የጅምላ ግድያዎች ባስቸኳይ እንዲቆሙ የጠየቀው ምክር ቤቱ፣ ሁኔታው ወደ ርስበርስ እልቂት ከማምራቱ በፊት ባስቸኳይ መፍትሄ እንዲበጅለት አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጋምቤላ እና ምዕራብ ወለጋ ዞን በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አጣርቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጠ!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ÷የምክር ቤቱ አባላት ከመራጭ ህዝብ ጋር በተወያዩበት ወቅት ህዝቡ መንግስት የዜጎችን ሠላም፣ ደህንነት እና የየአካባቢውን ፀጥታ እንዲያስከብር ጥያቄ በከፍተኛ ደረጃ ሲያቀርብ መቆየቱን አንስቷል፡፡የህዝቡን ጥያቄ መነሻ በማድረግም መንግሥት ህግ የማስከበር ህገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት አስፈላጊውን እያደረገ ይገኛል ነው ያለው፡፡

በህግ የማስከበር ዘመቻ ላይ የተለያዩ ቅሬታዎች መነሳታቸውን መነሻ በማድረግም የህግ ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ያለአግባብ በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች አሉ በሚል የቀረበውን ቅሬታ መነሻ በማድረግ በአስቸኳይ ማጣራት አደርጎ ለምክር ቤቱ እንዲያቀርብ ተልዕኮ ተሰጥቶት ሥራ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል ሰሞኑን በጋምቤላ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች በአሸባሪውና ተላላኪው ሸኔ በንፁሃን ዜጎች ላይ እጅግ አሰቃቂ፣ አሳዛኝና በሰው ልጆች ላይ መፈፀም የሌለበት ግፍ መፈጸሙን ምክር ቤቱ በመግለጫው አመላክቷል፡፡ምክር ቤቱ የተፈጸመውን ግፍ ሂደት ማጣራትና ተገቢውን ድጋፍ መስጠት አስፈላጊ ነው ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም ምክር ቤቱ በሂደቱ የደረሰው ጉዳት መጠን እና የሚያስፈልገው አስቸኳይ ድጋፍ በቋሚ ኮሚቴው በኩል ተጣርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡የሚቀርበውን የጉዳት መጠን መረጃ መነሻ በማድረግም የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ተከታትሎ አስፈላጊውን ድጋፍ በአስቸኳይ ለዜጎች እንዲያቀርብ መመሪያ ሰጥቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሂደቱ ከሰብዓዊ መብት ጋር ተያይዞ የተፈጸሙ ጉዳዮችን አጣርቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡መረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እና ምላሽ መስጠት ይቻል ዘንድም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎ ከምክር ቤት አባላት የተውጣጡ ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚያጣሩ ሁለት ቡድኖችን በማቋቋም ስምሪት መስጠታቸው ታውቋል፡፡ ቡድኖቹ ሥራቸውን እንደጨረሱ ውጤቱን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ እና አስፈላጊ አቅጣጫ እንደሚሰጥበትም አፈ ጉባዔው አስታውቀዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል መንግሥት ሕግ ማስከበር ባለው ዘመቻ በአንዳንድ የማቆያ ጣቢያዎችና ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ተጠርጣሪዎች አያያዝ የከፋ እንደሆነ የኢፌድሪ ተወካዮች ምክርቤት አስታወቀ።

በምክር ቤቱ የሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግሥቱ በክልሉ የማረሚያ እና ማቆያ ቦታ ጉብኝት ማጠቃለያ ባቀረቡበት ወቅት መልካም የሚባሉ ሥራዎች ቢኖሩም በአንዳንዶቹ ግን ለመናገር የሚያስቸግሩ ጉድለቶች እንዳሉ ገልጸዋል።ለተጠርጣሪዎች የተመደበው የቀን ባጀትም በእጅጉ አነስተኛ እንደሆነ ገልጠዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባል ወ/ሮ ሉባባ ኢብራሂም በበኩላቸው አንዳንድ ተጠርጣሪዎች በሚያዙበት ወቅት ያልተገባና ስርዓት የጎደለው ሁኔታ እንደነበረ አስረድተዋል።ቋሚ ኮሚቴው ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ዋና ዋና ተጠርጣሪዎች አልተያዙም፣ የሕግ ማስከበሩ እፎይታን ፈጥሮልናል፣ «ወደ ኋላ እንዳይመለስብን» ማለታቸውን ዶይቸቬለ ዘግቧል።

በፋኖ ስም የሚነግዱ፣ ጥይት የሚተኩሱ እና ህዝብን የሚረብሹ አካላት መኖራቸውን ያስረዱት ነዋሪዎቹ፣ ትክክለኛ ፋኖዎች ግን በዱር በገደሉ በግንባር «ጠላት» ያሉትን ኃይል እየተፋለሙ ነው ብለዋል።የአማራ ፖሊስ ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር በሚውሉበት ወቅት ኢሰብአዊ ድርጊት የፈፀመ አካል ተጣርቶ ተጠያቂ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

ሁሉም ፋኖ አይጠየቅም፣ በፋኖ ስም ተደብቆ ወንጀል የሚሠራና ተመክሮ የማይመለስ ከሆነ ግን ተጠያቂ እንደሚሆን ተናግረዋል።የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ም/ኮሚሽነር አቶ ውቤ ወንዴ የተነሱ ችግሮች እንዲስተካከሉ ይደረጋል ብለዋል።የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ ሕግ በማስከበሩ ከ12,400 በላይ በቁጥጥር ስር ውለው ነበር። 5ሺህ 600 ያህሉ ተለቅቀዋል።

[DW]
@YeneTube
የሶማሊያ ሁለተኛው ትልቁ ወንዝ በቀጠናው በተከሰተው ድርቅ ምክንያት እየደረቀ መሆኑ ተሰማ!

በሶማሊያ ሁለተኛው ትልቁ ወንዝ ሻበሌ በሀገሪቱ ብሎም በምስራቅ አፍሪካ በተከሰተው ከፍተኛ ድርቅ ምክንያት እየደረቀ መሆኑን አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል። በዚሁ ምክንያት ሚሊዮኖች ለከፋ ረሀብ ሊጋለጡ ይችላሉ በሚል ተሰግቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ወለጋው ጥቃት ወቅት ታግተው የተወሰዱ ሰዎች እንዳሉ ተገለጸ!

በምዕራብ ወለጋው ጥቃት ወቅት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች በታጣቂዎቹ ታግተው መወሰዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን አመለከተ።ኮሚሽኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት አስመልከቶ ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በርካታ ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውንና የት እናዳሉ እንደማይታወቅ ገልጿል።በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ፣ ቶሌ ቀበሌ ቅዳሜ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም ታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥርን በተመለከተ የተለያዩ አሃዞች እየወጡ ቢሆንም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውና በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለመፈናቀል መዳረጋቸው ተዘግቧል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው!

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በሚኖሩ ንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ በማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

በሰልፉ ላይ የተለያዩ የተቃውሞ ድምፆች ተሰምተዋል። ከነዚህም መካከል "ብሔር ተኮር ግጭት ይብቃ" ፣ "የአማራ ጭፍጨፋ በቃ"፣ " ሰላም እንፈልጋለን" እና የመሳሰሉ ድምፃች ይጠቀሳሉ።

በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ ሰኔ 11፣ 2014 ዓ. ም. በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ንጹሀን ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች መናገራቸው ይታወሳል።መንግሥት እስካሁን ድረስ የሟቾቹን ቁጥር ይፋ ያላደረገ ሲሆን፤ ለደረሰው ጥቃት ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራውን እና በመንግስት ‘ሸኔ’ በመባል የሚታወቀውን ታጣቂ ኃይል ተጠያቂ አድርጓል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምክር ቤቱ የአብን ተወካይ ከትናንት ወዲያ በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ያሳዩት አካሄድ ከምክር ቤቱ ደንብ ጋር ይጻረራል ሲል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጧል። ምክር ቤቱ ስብሰባዎች የውይይት መድረክ እንጅ የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሪያ አይደሉም ብሏል። በደንቡ መሠረት የምክር ቤት አባላት ከስብሰባ በፊት አጀንዳ ለአማካሪ ምክር ቤቱ፣ ለመንግሥት ተጠሪ ወይም ለአፈ ጉባዔ ማቅረብ እንደሚችሉ የጠቀሰው ምክር ቤቱ፣ የአብን ተወካይ ግን ይህን አካሄድ እንዳልተከተሉ አውስቷል። የአብን ተወካይ ደሳለኝ ጫኔ ማስያዝ የፈለጉት አጀንዳ፣ ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ክልል ለተጨፈጨፉ አማራዎች የሐዘን ቀን እንዲታወጅ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የልጆቿን ደም በየጊዜው የምትጠጣ መሆን የለባትም ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሀገሪቱ አሁናዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ባደረጉት ንግግር፣ የሰላም እጦት ብዙዎችን አሳጥቶናል፣ የጭካኔ ጥግ እንድናይ አድርጎናል ብለዋል፡፡የሰላም ጉዳይ ጦርነት ስላበቃ ብቻ ማውራት የለብንም፣ ሰላም ባለበት ወቅትም ቢሆን መነጋገር ይገባናል ነዉ ያሉት ፕሬዝዳንቷ፡፡

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ ላይ የተፈጠረው ክስተት መሆን የሌለበት እና መፈጠር የሌለበት ጉዳይ ነበር ብለዋል፡፡የሰላም እጦት እርስ በርሳቸውን እንዳንተማመን አድርጎናል፣ አፋጅቶናል ከዛ በላይ ደግሞ ሀገሪቷን ትልቅ ዋጋ አስክፍሏታል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ግዚያት በተከሰቱ ጥቃቶች የተነሳም ህጻናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን የጥቃቱ ዋነኛ ሰለባ መሆናቸውንም ነው ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተናገሩት፡፡በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ እና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ፣ የተደፈሩ ሴቶች አደባባይ ወጥተው ሰቆቃቸውን የተናገሩበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፣ ይህ ደግሞ የሚያሳየው ጥቃቱ ምን ያህል አስከፊ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ ግጭት በተከሰተባቸው ቦታዎች ተዘዋውረው መጎብኝታቸውን ገልጸዉ፣ በአብዛኛው በሁሉም አካባቢዎች ሴቶች እና ህጻናት ሰው ሰራሽ በሆኑ ጥቃቶች ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በምዕራብ ወለጋና በጋምቤላ የተፈፀሙትን ግድያዎች አወገዘች፡፡

ቤተክርስቲያኗ በመግለጫ እንዳመለከተችው በምዕራብ ወለጋና በጋምቤላና የተፈፀሙትን በአብዛኛው ሴቶች እና ህፃናት ሰለባ የሆኑበትን የንፁሃን ወገኖች ግድያ በፅኑ አውግዛለች፡፡ሰው በማንነቱና በሃይማኖቱ መገደል የለበትም ስትል ድርጊን ኮንናለች፡፡

መንግስትና አካባቢያዊ አስተዳደሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ዜጎች በሙሉ እንዲህ መሰል እኩይ ተግባራት በአጭሩ እንዲቀጩ፣ የቆየውና በመላው ዓለም የምንታወቅበት የህዝባችን ተከባባሮና ተደጋግፎ የመኖር ልማድ እንዲመለስ ለማድረግ ተግተው እንዲሰሩ አሳስባለች፡፡

ከዚህ ቀደም በየአካባቢው የሚፈፀሙ ዜጎችን ለሞት፣ ለመፈናቀል እና ለንብረት መውደም የሚዳርጉ ሁኔታዎችን በተለያዩ ጊዚያት ስታወግዝ እንደቆዮች ያስታወሰው መግለጫው ለጥቃቱ ሰለባ ቤሰቦች መፅናናትን ተመኝታለች፡፡

ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም መግለጫ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ይህንኑ ጥቃት ሰኔ 16 ባወጡት መግለቻ ማወገዛቸው ይታወሳል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
ከደራ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ያሉ የሕዝብና የጭነት ተሸከርካሪዎች ከነ ተሳፋሪዎቻቸው መታገታቸው ተገለጸ!

ከኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ የነበሩ አራት የሕዝብ ማመላለሻና አንድ የጭነት ተሸከርካሪዎች መታገታቸው ተሰማ።
ተሳፋሪዎቹ ከደራ ወረዳ ጉንዶ መስቀል ከተማ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳሉ መታገታቸው ነው የተገለጸው።ተሳፋሪዎቹ የታገቱት ደራ ወረዳን አልፈው ሂደቡአቦቴ ወረዳ ኤጀሬ ከተማ ሊገቡ ሲሉ ጥቂት ሲቀራቸው እንደሆነም የዐይን እማኞች ገልጸዋል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ600 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ!

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ600 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።ከ600 ሚሊየን ዶላር ውስጥም 200 ሚሊየን ዶላሩ በድጋፍ መልክ የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

400 ሚሊየን ዶላሩ በብድር መልክ የተገኘ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡ገንዘቡ በሀገሪቱ የምግብ ሥርዓትን ለማሻሻል እንደሚውል ተጠቁሟል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ኮረደም ልዩ ስሙ ገላል ውኃ በተባለ አካባቢ የሱዳን ታጣቂዎች በአካባቢው ኢትዮጵያውያን የግብርና ባለሀብቶች ላይ ጥቃት ከፍተው በአርሶ አደሮች ተሸንፈው መሄዳቸውን አንድ የዐይን እማኝ ለዶይቼ ቬሌ ተናገሩ።

በግጭቱ የወንዳማቸውን ልጅ ያጡት አቶ ሲሳይ አሸብር የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ባለፈው ረቡዕ አነጋግ ላይ የሱዳን ታጣቂዎችና “ጁንታው” ያሏቸው ኃይሎች ከበባ በመፈፀም ዘረፋ ለማከናወን ተኩስ መክፈታቸውን ተናግረዋል።በኢትዮጵያ በኩል የወንድማቸው ልጅ መገደሉን፤ በሱዳን ታጣቂዎች በኩል ደግሞ 16 ተገድለው መሸሻቸውን ገልጠዋል።

የአከባቢው አርሶ አደሮች ታጣቂዎቹን በተኩስ አሸንፈው ካካባቢው አንዳስወጧቸው ተናገሩት አቶ ሲሳይ ከዚያ በኋላ የመንግስት ኃይሎችም ወደ ቦታው መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።«መላ 200 ኃይል አፍኖን አድሮ ጥይት (ተኩስ) ተጀምሮ ብዙ ነገሮች፣ ቦንባችንም ያለውን ነገር ጨርሰን የጠላት መሣሪያ እየማረክን ያው ውጊያውን አካሄደን ብዙውን ሙት እየተሸከሙ፣ ብዙ ቁስለኛም እተሸከሙ ይዘው ሄዱ። እኛ 16 ነው ሙት ያደረግነው እኛ።»ከሱዳን ታጣቂዎች ጋር ኢትዮጵያውያን ወታደራዊ አመራሮች እንደነበሩና እንደተገደሉ የዐይን እማኙ አስረድተዋል።

«ሰባቶችን አመራሮች ባለስልጣን 50 አለቃ፣ 10 አለቃ መታወቂያቸው ያለውን ነገር ስናይ የትግራይ ተወላጅ ተልዕኮውን ለመፈፀም የተላከውን ኃይል በየቀየው በመጣበት አዋርደን ወደዚያ ወደ ቦታው ከሞተበት ወስደን እንዲቀበር አድረገረነ፣ እነዚያ አመራሮችን፡፡»ዶይቼ ቬሌ ስለጉዳዩ ከምዕራብ ጎንደር አስተዳደርና ከአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ተጨማሪ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ተገደሉ ስለተባሉት አካላትም ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጫ ማግኘት አልተቻለም።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ግብርና ሚንስቴር በቅርቡ በኢትዮጵያ የተከሰተው ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ሥርጭቱ እና ጉዳቱ እየቀነሰ እንደመጣ መናገሩን ሪፖርተር ዘግቧል።

ሚንስቴሩ ይህን የገለጸው፣ 50 ያህል ዶሮ አርቢዎች እና እንቁላል ሻጭ ድርጅቶች ዶሮ እና እንቁላል ለገበያ እንዳይቀርብ መንግሥት ከ15 ቀናት በፊት በጣለው እገዳ ላይ ቅሬታቸውን ለመግለጽ ዛሬ በሚንስቴሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቃውሞ ባሰሙበት ወቅት ነው። ቅሬታ አቅራቢዎቹን በአካል ያነጋገሩት የሚንስቴሩ የሥራ ሃላፊዎች፣ በቅርቡ የተከሰተው የዶሮ በሽታ እየቀነሰ እንደመጣ ገልጸዋል። ሚንስቴሩ ችግሩን እንዴት ማስተናገድ እንደሚቻል አዲስ መመሪያ እንዳዘጋጀ እና በመመሪያው ላይ ዛሬ ውሳኔ እንደሚሰጥ ሃላፊዎቹ ጨምረው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሕወሃት ታጣቂዎች ሰሞኑን በራያ ቆቦ አንዳንድ አካባቢዎች ከአማራ ክልል ፋኖ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

በሁለቱ ወገኖች ውጊያ የሕወሃት ታጣቂዎች አራት የገጠር ጎጦችን መቆጣጥፕራቸውን የአካባቢው እማኞች ተናግረዋል። ተኩስ ልውውጡን ተከትሎ፣ ከ160 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቀያቸው እንደተፈናቀሉ ዘገባው ገልጧል። ከሕወሃትም ሆነ የአማራ ክልል መንግሥት በራያ ቆቦ ተካሄደ ስለተባለው የተኩስ ልውውጥ ያሉት ነገር የለም።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪዎችን እያስመረቀ ነው!

የኢትዮጵያ አየር ኃይል "ነብሮች 2014" በሚል መሪ ቃል ያሰለጠናቸውን አብራሪዎች ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና የመንግሥት ከፍተኛ የሲቪልና ወታደራዊ አመራሮች በተገኙበት እያስመረቀ ይገኛል።

ተመራቂ አብራሪዎቹ በተለያዩ አውሮፕላን አይነቶች በጀማሪነትና ተጨማሪ አብራሪነት ስልጠና የወሰዱ መሆናቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ በአየር ኃይል አካዳሚ ለ4 ዓመታት ያህል ስልጠና የተከታተሉ ሲሆን በተዋጊ አውሮፕላን፣ በትራንስፖርት አውሮፕላን፣ በትራንስፖርት ሂሎኮፕተር፣ ቪ አይፒ ሂሎኮፕተር እና በመጀመሪያ ደረጃ በረራ ማሰልጠኛ አውሮፕላን አብራሪነት የሰለጠኑ መሆናቸው ታውቋል።

ስልጠናው የአየር ኃይል አካዳሚ የጀግና አብራሪዎችና የብቁ ቴክኒሻኖች ማፍሪያ ማዕከል ሆኖ እንዲቀጥል አቅም የሚፈጥር መሆኑም ተገልጿል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ሚኒስትሮች፣ የመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች እና የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ታድመውታል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
ተቃውሞ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ድብደባ ደረሰባቸው።

ዛሬ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ከጠዋት ጀምሮ በኦሮምያ ክልል በወለጋ የአማራ ብሄር መሰረት አድርጎ የተፈፅመውን የጅምላ ግድያ ሲያወግዙ ነበር።

@Yenetube @Fikerassefa
አብን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ተወላጆች ላይ በደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ተሳልቋል አለ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ በቶሌ ቀበሌና አጎራባች ቀበሌዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል አስመልክቶ የወሰደው አቋም የተጣለበትን ኃላፊነት የማይመጥን መሳለቅም በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ነው ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አሳሰበ፡፡

አብን እንደገለጸው፣ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌና አጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪ በሆኑ የአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተከትሎ የፓርቲው አመራርና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)፣ ምክር ቤቱ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ አጀንዳነት ይዞ ውይይት እንዲያደረግ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

ነገር ግን ምክር ቤቱ በአጀንዳነት ከተያዙ ጉዳዮች ውጭ ያሉ አሰቸኳይ ጉዳዮችን ለማስተናገድ የሚያስችል አሰራር በሕግ ተፈቅዶለታል። አስቸኳይ ጉዳዮችን በተመለከተ በሕግ ያልተገደበና ሙሉ ሥልጣን የተሰጠው የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ሲፈቅድ ጥያቄውን ማስተናገድ እንደሚቻልም በግልጽ ተደንግጓል፡፡በክቡር ደሳለኝ (ዶር) እና በክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ መካከል የተደረገው የንግግር ምልልስ ቪዲዮ ላይ በግልጽ እንደሚታየው፣ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የምክር ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ ጥሰው “በአጀንዳ ባልተያዘ ጉዳይ ላይ አንወያየም” በማለት፣ በአስቸኳይ ጉዳይነት እንዲያዝ የተጠየቀውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ጉዳይ ውድቅ አድርገውታል፡፡

በደሳለኝ (ዶ/ር) የቀረበው ጥያቄ፣ ምክር ቤቱ የሚመራበትን ደንብና ሥርአት መሰረት አድርጎ የቀረበ አስቸኳይ ጉዳይ ቢሆንም ፣ ምክር ቤቱ ግን በይፋዊ ማኅበራዊ ድረገጹ ባወጣው አጭር መግለጫ ግን “ምክር ቤቱ የውይይትና የምክክር እንጅ የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሪያ መሆን የለበትም” በማለት የዘር ማጥፋት ወንጀልን በሚመለከት የቀረበን አጀንዳ ተራ የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሪያ ነው ሲል መሳለቁን ጠቅሷል፡፡

አፈጉባኤው በአጀንዳነት ያልተያዘ አስቸኳይ ጉዳይን የማስተናገድ በሕግ የተፈቀደና ያልተገደበ ሙሉ ሥልጣን እያላቸው ፣ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ፣ ምክር ቤቱ ባወጣው አጭር መግለጫ፣ የብሔራዊ ደኅንነት ከፍተኛ ስጋት የሆነውንና ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ወደ ለየለት ቀውስ ውስጥ የሚከትን የዘር ማጥፋት ወንጀልን የሚመለከት ጉዳይ “ተራ የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሪያ” ሲል መሳለቁ ፣ (አብን)ን ፣ የአማራን ሕዝብና መላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውንን ያሳዘነ፣ የተጣለበትን አደራ ያጎደለ ተግባር ሆኖ እንዳገኘው አብን በመግለጫው አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa