YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ከሥራ ተቋራጩ ጋር ድርድር እየተደረገ ነው!

የተቋረጠውን የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ከሥራ ተቋራጩ ያፒ መርከዚ ጋር ድርድር እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር አብዱልከሪም መሐመድ፣ የፕሮጀክቱ ሥራ ተቋራጭ በጦርነቱ በደረሰበት ውደመት የሥራ ውሉን አቋርጦ ወደ አገሩ መመለሱን ጠቅሰው፣ አሁን ላይ ተመልሶ ወደ ሥራ እንዲገባ ድርድር እየተደረገ ነው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከቆቃ ኃይል ማምንጫ ጣቢያ ወደ ሞጆ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋው 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈጸመ ስርቆት ምክንያት በአከባቢው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጧል፡፡

የስርቆት ወንጀሉ ለጊዜው ባልታወቁ ግለሰቦች የተፈፀመ ሲሆን፤ በመስመር ተሸካሚ ማማዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጠቁሟል፡፡

በዚህም ሞጆና አከባቢው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችና አንዳንድ ድርጅቶች ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸዋል፡፡

ሆኖም በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቴክኒክ ሠራተኞች ችግሩን ለመቅረፍ የጥገና ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

[EEU]
@YeneTube @FikerAssefa
ከደራ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ከታገቱ ዜጎች ውስጥ 360 መለቀቃቸው ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘው የደራ ወረዳ አስተዳደር በአዲስ አበባ ፍቼ ደራ መስመር የፌዴራል የጸጥታ ኃይል እንዲሰማራ ጠየቀ።የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ ውብሸት አበራ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ የደራ ፍቼ አዲስ አበባ መስመር ላለፉት ስምንት ወራት ተዘግቶ መቆየቱን ገልጸዋል።ዋና አስተዳዳሪው የመኪና መንገዱ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ቢጀምርም ትናንት ሰዎች ግን መታገታቸውን ገልጸዋል።

ትናንትና አራት የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችና አንድ የጭነት መኪና መታገታቸውን ለአል ዐይን አማርኛ የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው አሁን ላይ የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ በኣባቢው እንዲሰማራ ጠይቀዋል።ዋና አስተዳዳሪው የፌዴራል ሰራዊት እንዲሰማራ በተደጋጋሚ ለሰላም ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን እና ምላሽ እንዳላገኙ ልጸዋል።

ከደራ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ከታገቱ ዜጎች መካከል እስካሁን 360 ዎቹ የክልሉ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሰሩት ስራ መለቀቃቸውን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው፤ አጋቾቹ ደግሞ በራሳቸው አንድ ወንድ እና አንድ ሴት መልቀቃቸውን ገልጸዋል።አሁንም 10 ሰዎች መታገታቸውን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው አጋቾቹ ብር እንደሚፈልጉም ገልጸዋል። ትናንት በስፍራው ከታገቱት ዜጎች ውስጥ ሁለት የደራ ባለሀብቶች እንዳሉበትም ተገልጿል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የባቡር የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት የሰረቁ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!

ለአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቶች ላይ የስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የተገኙ 6 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ።ስርቆቱ የተፈፀመው ከሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ መሆኑን በአገልግሎቱ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ማስተባበሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢልቱማ ቂጣታ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ የአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን እንድትለቁ መባላቸው እንዳሳሰባቸው ለየኔቲዩብ ተናገሩ!

ትግራይ ክልልን ጨምሮ የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢ የመጡና ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ የማይችሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እስካሁን ድረስ በጊቢው እንዲቆዩ ተፈቅዶላቸው የነበረ ቢሆንም ዩኒቨርስቲው ሰኔ 15፣ 2014 ዓ/ም ባወጣው ማስታወቂያ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ አሳውቋል። ይህንንም ተከትሎ ተማሪዎቹ ባለው የፀጥታ ስጋት የተነሳ ወደ ቤተሰቦቻችን መመለስ ስለማንችል ዩኒቨርስቲው ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው ሲሉ ተማፅነዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራሉ መንግስትና ህወሓት በቅርቡ የፊት ለፊት ድርድር ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለመሆኑ የፌዴራሉ መንግስት ምን ሰጥቶ ምን ለመቀበል ተዘጋጅቷል? የህወሓት ቀይና አረንጓዴ የድርድር ነጥቦችስ ምንድናቸው? ድርድሩ የመሳካት ዕድል ምን ያህል ነው? የሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ የተዘጋጀችውን ዘገባ ያዳምጡ!!

ቻናሉን ሰብስክራይብ ማድረግ አይዘንጉ!!
https://youtu.be/_eQA5xVzWjk
ዳግም በተቀሰቀሰ ጦርነት ሕወሓት ሦስት የቆቦ ወረዳ ቀበሌዎችን መቆጣጠሩ ተነገረ!

በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል ዳግም በተቀሰቀሰ ጦርነት ሕወሓት ሦስት የቆቦ ወረዳ ቀበሌዎችን መቆጣጠሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።

በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳ የሚገኙ ስሚዛ ጊዮርጊስ፣ መቀነት ጋሪያ፣ ጃን አሞራ የተባሉት ቀበሌዎችን ሕወሓት መቆጣጠሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና በአካባቢው ያሉ ሚሊሻዎች ታጣቂ ቡድኑ የሚሰነዝረውን ጥቃት ለመመከት ቢሞክሩም ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ለጥቃት ምቹ የሆኑ ስትራቴጅክ ቦታዎች በሕወሓት ቁጥጥር ስር ናቸው ተብሏል።

Via Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
በጉጂ ዞን ከኦነግ ሸኔ ቡድን ነጻ ወጥተው የነበሩ ሁለት ወረዳዎች በድጋሚ በቡድን መያዛቸው ስጋት ፈጥሯል ተባለ!

በጉጂ ዞን ከሚገኙ 18 ወረዳዎች ውስጥ በ5 ወረዳዎች የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ቡድን የጸጥታ ችግር ማስከተሉ ይታወቃል።

በዚህም በርካቶች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፣ ለረሃብ የተጋለጡ ሲሆን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዲረቁ ተገደዋል።

ነጻ ወጥተው ከነበሩ አምስቱ ወረዳዎች ውስጥ በሁለቱ ማለትም ሰባቦሩ እና ዋደራ ወረዳዎች ላይ የኦነግ ሸኔ ቡድን በድጋሚ መግባቱን ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮች ዳግም እንዲያገረሸምሹ ያደርገዋል የሚል ስጋት ነግሷል።

በመሆኑም የሚመለከተው አካል አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ካልቻለ በዞኑ ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮች እንደ አዲስ ሊከሰቱ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ በዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ ዮሀንስ ወርቁ ተናግረዋል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የወልድያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን በተለይ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን ጅምላ ጭፍጨፋ በመቃወም ትናንት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ተማሪዎቹ በግቢያቸው ውስጥ ተሰባስበው፣ መንግሥት ጭፍጨፋውን የፈጸሙ አካላትን ለሕግ እንዲያቀርብ እና ከጭፍጨፋው ለተረፉት የደኅንነት ዋስትና እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የወልድያ ከተማ ኮምንኬሽን ቢሮ ተማሪዎቹ ለአመጽ እንደወጡ ተደርጎ በአንዳንድ ማኅበራዊ ትስስር ዘዴዎች የተሠራጨው መረጃ ሐሰት ነው ሲል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጧል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ቭላድሚር ፑቲን የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት አካል የነበሩ ሁለት ሃገራትን ሊጎበኙ ነው!

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት አካል የነበሩ ሁለት ሃገራትን ሊጎበኙ ነው፡፡ሃገራቱ በማዕከላዊ እስያ የሚገኙ ሲሆን ታጂኪስታን እና ቱርክሜኒስታን ናቸው፡፡ፑቲን በዩክሬን ልዩ ዘመቻ እንዲካሄድ ጦራቸውን ካዘዙበት ከዛሬ 4 ወራት በኋላ ለመጀመሪያ የሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት ነው፡፡በዚህ ሳምንት እንደሚሆን ከሚጠበቀው ከማዕከላዊ እስያ ጉብኝታቸው መልስ በሞስኮው ከኢንዶኔዥያው ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶን ጋር እንደሚወያዩም ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 11 ወራት በአዲስ አበባ 23 ሰዎች ከሕንፃ ላይ ወድቀው መሞታቸው ተገለጸ!

በአዲስ አበባ በ11 ወራት 23 ሰዎች የግንባታ ሥራ እየሠሩ በነበረበት ወቅት ከሕንፃ ላይ ወድቀው መሞታቸውን የአዲስ አበባ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሙሉጌታ ሊክዲ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ ሰዎች በግንባታ ሥራ ላይ በቀን ሠራተኝነት፣ በግንበኝነት እና በሌሎች የሙያ ዘርፎች ተቀጥረው በሚሠሩበት ወቅት ተገቢውን የደኅንነት መጠበቂያ ተጠቅመው መሥራት ባለመቻላቸው እና በሌሎች ምክንያቶች ከሕንፃዎች ላይ ወድቀው የሞትና አካል ጉዳት ያጋጥማቸዋል ብለዋል።

ለተጨማሪ ለማንበብ: https://bit.ly/3xWH37p

@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት በኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች ”የጅምላ ግድያ” የፈፀሙት ለፍርድ እንዲያቀርብ የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠየቀ፡፡

ምክር ቤቱ ይህን የጠየቀው ”በንፁሃን ዜጎች ላይ በአሸባሪዎች እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ አጥበቀን እናወግዛለን!” ሲል ሰይሞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ላይ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ”በንፁሃን ላይ የሚደርሰውን ዘግናኝ የሰብዓዊ ቀውስ በፅኑ አውግዞ” ፤ ” በጥቃቱ ለተጎዱ ወገኖች፣ ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እመኛለሁ” ብሏል፡፡

ሀዘንና መፅናናቱን የገለፀው ምክር ቤቱ ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫውንም ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም ” ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል፣ ወለጋ ውስጥ፣ በቶሌና ሌሎችም ቀበሌዎች ውስጥ እንዲሁም በጋምቤላ በሌሎችም አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግድያ፣ አካላዊ ጉዳት ማድረስ፣ ማሳደድና ማፈናቀል፣ ማሸበር፣ አጥብቄ አወግዛለሁ፡፡” ሲል ድርጊቱን ኮንኗል፡፡

” ሠላማዊ ዜጎችን፣ መኖሪያቸው ድረስ እየሄዱ መግደል፣ መጉዳት፣ ማሳደድ ነውርም፣ ሃጢያትም፣ ወንጀልም ሰልሆነ” ያለው ምክር ቤቱ ” መንግስት ይህንን ተግባር የማስቆምና ፈፃሚዎችንም ለፍርድ የማቅረብ ግዴታውን እንዲወጣ” አጥብቆ ጠይቋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን በኢትዮጵያ የተገደሉባትን ወታደሮች አስመልክታ “ለፀጥታው ምክር ቤት ላመለክት ነው” አለች!

ሱዳን በኢትዮጵያ የተገደሉባትን ወታደሮች አስመልክታ ለጸጥታው ምክር ቤት እንደምታመለክት ገለጸች።የሱዳን መከላከያ ቃል አቀባይ በትናንቱ መግለጫ እንዳለው “ሰባት የሀገሪቱ ጦር አባላት በኢትዮጰያ እንደተገደሉ እና የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ” መናገራቸው ይታወሳል።

ሄንን ተከትሎም የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጉዳዩን አስመልክቶ ለመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እንደሚያመለክት አስታውቋል።ከዚህ በተጨማሪም ሚኒስቴሩ ለሌሎች ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ክፍለ አህጉራዊ ተቋማት እንደሚያመለክትም ገልጿል።

እንዲሁም በካርቱም ያለውን የኢትዮጰያን አምባሳደር ለምን የሱዳን ጦር በኢትዮያ እንደተገደሉ ተጨማሪ ማብራሪያ እንደሚቀበልም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ሱዳን የዓለም አቀፍ ህግን በጣሰ መንገድ ምርኮኞችን በማሰቃይት እና በመግደል የከሰሰች ሲሆን የኢትዮጰያ ጦር የሱዳን ጦር ምርኮኞችን በመግደል፣ ንጹሃንን በማገት እና የሱዳንን ሉዓላዊ ግዛት ጥሳለች በሚል ክስ አቅርባለች።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የሰሜኑ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ አቅጣጫ ማስቀመጡን ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ!

የብልጽግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ እና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አቅጣጫ ማስቀመጡን የፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ።

የሰላም ሂደቱ መርሆ ሕጋዊነትን እና ሕገ መንግስታዊነትን የጠበቀ እንዲሁም የሀገርን መሠረታዊ ጥቅም የሚያስከብር ሊሆን እንደሚገባው አጽንኦት መሰጠቱም ተገልጿል።

የሰላም ሂደቱ በአንድ ወገን ብቻ ውጤታማ ስለማይሆን ሂደቱ ካልተሳካ አስፈላጊውን መልስ የሚሰጥ የጸጥታ ኃይል እንዲዘጋጅም አቅጣጫ መቀመጡን ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናግረዋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ በሱዳን ወታደሮች እና የአካባቢ ሚሊሻዎች ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘኑን ገለፀ!

የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ በሱዳን ወታደሮች እና የአካባቢ ሚሊሻዎች ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘኑን ገለፀ፡፡በአሸባሪው ህወሃት ቡድን ድጋፍ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በገቡ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል።

ሚኒስቴሩ መግለጫው፡- በኢትየጵያ እና ሱዳን አዋሳኝ ድንበር መካከል የተከሰተውን አሳዛኝ ክስተት የኢትዮጵያ መንግስት መገንዘቡን አንስቷል፡

ድርጊቱ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የተፈጸመው በአሸባሪው የህወሓት አባላት የሚደገፈው የሱዳን መደበኛ ጦር ሰራዊት የኢትዮጰያን መሬት ከወረረ በኋላ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ጦር እና በአካባቢው ባለው ሚሊሻ መካከል በተፈጠረ ግጭት በጠፋው የሰው ህይወት ማዘኑን የገለፀ ሲሆን÷ በቅርቡም በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚካሄድ ማስገንዘቡን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከሳኡዲ አረቢያ አንድ ሺህ 85 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!

በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ አንድ ሺህ 85 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።ከተመላሾቹ 17 ሴቶች፣ 19 ህጻናትና 1049 ወንዶች ናቸው ተብሏል።

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 43 ሺህ 175 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በንጹሃን ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ለ20 ቀናት ወደ አዲስ አበባ መመለስ ሳይችሉ እንደቆዩ ቤተሰቦቻቸው ለዋዜማ ተናግረዋል። ከተለያዩ መገናኛ ብዙኀን የተውጣጡት ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች በደንቢዶሎ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ላይ ለመገኘት ወደ ደምቢዶሎ ከተማ የሄዱ ናቸው። ጋዜጠኞቹ እና የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎቹ ከ20 ቀናት በኋላ ወደ አዲስ አበባ መመለስ የቻሉት ባለፈው ቅዳሜ ነው።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን የሀገሪቷ ክፍል ያለውን ችግር ለመፍታት በፌዴራል መንግሥት በኩል የሰላም ተደራዳሪ ቡድን ተሠየመ!

በሰሜኑ የሀገሪቷ ክፍል ያለውን ችግር ለመፍታት የሚከተለው የሰላም አማራጭ ሀገራዊ ጥቅምን በሚያስከብር እና በአፍሪካ ኅብረት አመቻችነት እንዲካሄድ መወሰኑን የብልጽግና ፓርቲ አስታውቋል።

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ እንደ ብልጽግና ችግሩን ለመፍታት ፓርቲው የሚከተላቸው የሰላም አማራጮች ህገ መንግስታዊነትን ባከበረ፣ ሀገራዊ ጥቅምን በሚያስከብር መልኩ በአፍሪካ ህብረት አመቻችነት እንዲካሄድ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቅጣጫ አስቀምጧል ብለዋል።

በዚህም መሠረት በፌዴራል መንግሥት በኩል የሰላም ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን ለዋልታ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የቡድኑ አባላትም የሚከተሉት ናቸው፤

1ኛ. አቶ ደመቀ መኮንን........ሰብሳቢ
2ኛ. ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ.....አባል
3ኛ. አቶ ተመስገን ጥሩነህ......አባል
4ኛ. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር....አባል
5ኛ. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን.....አባል
6ኛ. ሌ/ል ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ....አባል
7ኛ. ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር.........አባል

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
የጌትሩምስ የጥሪ ማዕከል ስራ መጀመሩን በማስመልከት
ቁጥሩን ቀድመው ይገምቱ ይሸለሙ ??

በፌስቡክ ፔጃችን ላይ መልሶትን ይፃፉልን።
https://www.facebook.com/108758434826262/posts/202668268768611/

መተግበሪያውን ያውርዱ
ለአንድሮይድ ስልክ- https://cutt.ly/2PMOhFY
ለአይፎን ስልክ - https://cutt.ly/PPMOYZb.

#GetRooms #Hotels #Resort #Guesthouse #Hotelapartment #GetFee #CBE #Eaglelion #Hospitality #HotelRooms #Booking #Reserve #Bidding #System #callcenter #Ethiopia #Hotels