YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የመከላከያ ሰራዊት ከትናንት ጀምሮ መውሰድ በጀመረው ጠንካራ እርምጃ አስተማሪ ሥራ እየሰራ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ!

የመከላከያ ሰራዊት ከትናንት ጀምሮ መውሰድ በጀመረው ጠንካራ እርምጃ የጠላት ተላላኪዎችን ሊያስተምር የሚችል ሥራ እየሰራ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ከሰሞኑ ሽብርተኛው የኦነግ ሸኔ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በንፁሃን ላይ የፈፀመውን ጥቃት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትላንትናው እለት ማውገዛቸው አይዘነጋም፡፡

በጥቃቱ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች በሽብርተኛው ቡድን መገደላቸውን እና በሺሕዎች የሚቆጠሩ ደግሞ አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት አራተኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ የእጽዋት ማዕከል ዛሬ በይፋ ሲያጀምሩ ነው፡፡

በመርኃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ከኢትጵያውያን የሚጠበቀው ሀገራችንን መንከባከብ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንከባከብ ሲባል ሀገር ምድር ብቻም ሳይሆን ሰውንም ጭምር ነው ብለዋል፡፡

ዛሬ ከወታደር እና ከፖሊስ ጋር በቀጥታ መግጠም የማይችሉ ተላላኪ ባንዳዎች ንፁሃን ኢትዮጵውያንን ይጨፈጭፋሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ጸያፍ ድርጊት ለማስቆም ሁሉም ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው በአፅንዖት ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በግብዓት እጥረት ተቋርጦ የነበረው የተሽከርካሪ ሰሌዳ ከነገ ጀምሮ ይሰጣል!

በአዲስ አበባ በግብዓት እጥረት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኮድ- 2 ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ አገልግሎት ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ የከተማ አስተዳደሩ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የኮድ -2 አ.አ ሰሌዳ በግብዓት እጥረት ምክንያት አትሞ እያስረከበ ስላልሆነ የሰሌዳ እጥረት ያጋጠመ መሆኑን ግንቦት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ስለሆነም የነበረው የሰሌዳ ምርት እጥረት በመፈታቱ የኮድ -2 አ.አ ሰሌዳ ፈላጊዎች ከነገ ጀምሮ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

በዚህም ተገልጋዮች ወይም የኮድ 2 ሰሌዳ ፈላጊዎች በሙሉ መሟላት ያለባቸውን መረጃዎች በማሟላት በ11ዱም ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በመኖሪያ አድራሻቸው ብቻ መስተናገድ እንደሚችሉ የባለስልጣኑ መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከአውሮፓ የቀውስ ሥራ አመራር ኮሚሽነር ጄኔዝ ሌናርሲች ጋር መወያየታቸው ተገለፀ!

የሕወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከአውሮፓ የቀውስ ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔዝ ሌናርሲች ጋር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ገለፁ።

ቃል አቀባዩ በቲውተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፤ በውይይቱ የተለያዩ የጋራ ጉዳዮች መነሳታቸውን ገልፀዋል። ኮሚሽነር ጄኔዝ ሌናርሲች ቀደም ብለው በመቀለ ከተማ የሚገኘውን የአይደር ሆስፒታል መጎብኘታቸውንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በሙስና፣ መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ክስ የቀረበባቸው ከ300 በላይ የፌደራል ዳኞች በሥራቸው እንደቀጠሉ መሆኑን የፍትህና ሕግ ጥናት ኢንስቲትዩት ባደረገው አንድ የዳሰሳ ጥናት አመልክቷል።

በዳኞቹ ላይ የቀረቡት የክስ ጥቆማዎች፣ ጉቦ መጠየቅ፣ ሙስና፣ የመዝገቦች መሰወር፣ የዳኝነት ሃላፊነትን ያላግባብ መጠቀም፣ ደንበኞችን መበደል፣ ገለልተኛ አለመሆን እና በዳኝነት ላይ የግል አስተያየቶችን መስጠት ናቸው። በዳኞቹ ጉዳይ ላይ እስካሁን የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ውሳኔ አልሰጠም።ኢንስቲትዩቱ ይህን የገለጸው፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ በፌደራል ፍትህ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለ5 ወራት ያጠናውን ጥናት ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ዘንድሮ የሦስት ሕጻናት ሕይወት በጎርፍ አደጋ የተቀጠፈባት አዲስ አበባ ከተማ በ161 ቦታዎች ለተጨማሪ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ መሆኗ ተገለጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዐሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የጎርፍ አደጋ ስጋት ያለባቸውን አካባቢዎችን በጥናት መለየቱን ዐስታውቋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰለሞን ፍሰሀ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ተብለው ከተለዩት ቦታዎች አስቸኳይ መፍትኄ የሚሹ ያሉባቸው መሆናቸውን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

«ወደ መቶ ስድሳ አንድ አካባቢ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን ነው የለየነው።ከዚህ ውስጥ ስድሳ አንዱ አስቸኳይ መፍትኄ የሚያስፈልገው በሚል ነው የወሰድነው።ከዚስ ስድሳ አንዱ ደግሞ በዐሥራ ስምንቱ ገንዘብ የሚፈልግ የተለዩ ተጨማሪ ሥራ የሚፈልግ ኾኖ ነው የተገኘው።» ጊዜ የማይሰጡ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ስጋት ያለባቸው የተባሉ ካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ወደ ተዘጋጀላቸው ስፍራ የመዘዋወር ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አክለው ተናግረዋል።

ምን ያህል ሰው ወደ ተዘጋጀለት ስፍራ እንደተወሰደ ግን አልተጠቀሰም።ኮሚሽነሩ በመግባት ላይ ካለው የክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ በርካታ ችግሮች ሊፈጥሩ እንሚችል በመግለፅ ወላጆች እና ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ግን አስጠንቅቀዋል።በአዲስ አበባ ከተማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዐሥር በተለምዶ ቀይ አፈር በሚባለው አካባቢ ኲዋስ በመጫወት ላይ ከነበሩ ልጆች መካከል ሁለት ታዳጊዎች ባለፈው እሁድ በጎርፍ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል።

ልጆቹ ሰኔ 12 ቀን፣ 2014 በአቅራቢያው ከነበረ ወንዝ ኳስ ለማወጣት ሲሞክሩ ሕይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዐስታውቋል። ከሁለት ሳምንት በፊት ከትምህርት ቤት ሲወጣ በጎርፍ ተወስዶ ሕይወቱን ያጣውን ታዳጊ ልጅ ጨምሮ ከተማይቱ ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ ሊወገድ በሚችል አደጋ ሦስት ሕፃናትን አጥታለች።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ የተፈፀመው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጠየቀ!

በወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ጥሪ አቀረበ።ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ “የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በገጠር የሚገኙ ታጣቂዎችን በማፈላለግ ሰበብ ላለፉት ሁለት አመታት ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎችን በውጊያ እንዲሳተፉ እያስገደዱ መሆኑን በርካታ የተረጋገጡ መረጃዎች ያመለክታሉ” ብሏል። የአካባቢው ሚሊሻዎችም ቢሆኑ ከታጣቂዎች ጋር በሚያደርጉት ውጊያ ንፁሃን ዜጎችን ውስጥ ይመሽጋሉ ተብሏል።

ኦነግ “መንግስት በተደጋጋሚ ለሚደርሱ የንፁሀን ዜጎች ጥቃት እጁ እንደሌለበት” መግለፁ የተለመደ ነው ያለ ሲሆን በሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ብዙኀን አማካኝነት መንግስት የህብረተሰቡን ስሜት ለመቃኘት መሞከሩ የከፋ ደም አፋሳሽ ችግር ይፈጥራል” ብሏል።በመሆኑም በቅርቡ በጊምቢ ወረዳ ለደረሰው እና ሌሎችም ንፁሃን ዜጎች ተጠቂ የሆኑባቸው ክስተቶች በገለልተኛ አካል መጣራት ይገባቸዋል ሲል አሳስቧል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በተለምዶ "ሿሿ" የተባለውን የስርቆት ወንጀል ፈፅመው ሊሰወሩ የነበሩ 8 ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ ገለጸ!

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ እና ተሳፋሪ በመምሰል በተለምዶ "ሿሿ" የተባለውን የስርቆት ወንጀል ፈፅመው ሊሰወሩ የነበሩ 8 ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ቅድስት ማርያም አካባቢ መሆኑ ተመላክቷል።

ከ6 ኪሎ አቅጣጫ የመጣ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-36245 አ/አ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ነጠላ እና ፎጣ የተከናነቡ 4 ሴቶች እና 4 ወንዶችን ተሳፋሪ በማስመሰል በግብራበርነት የሚሳተፉ ግለሰቦችን ጭኖ ወንጀል ለመፈፀም እየተንቀሳቀሰ ነበርም ብሏል፡፡

ቅድስት ማርያም አካባቢ ሲደርሱ ትራንስፖርት በመጠባበቅ ላይ የነበረችውን የግል ተበዳይ ወዴት እንደምትሄድ ከጠየቋትና ወደ ሜክሲኮ እንደምትሄድ ከነገረቻቸው በኋላ ግቢ ብለው በማስገባት ከሹፌሩ ኋላ ባለው ወንበር ላይ እንድትቀመጥ ያደርጓታል።

ከጎኗ የተቀመጠችው ሌላኛዋ ተጠርጣሪ ስልክ የምታወራ በማስመሰል እና የግል ተበዳይ ምን ዓይነት ስልክ እንደያዘች ለማረጋገጥ ስልክ ቁጥር ያዢልኝ ብላ ስልኳን ከተመለከተች በኋላ ወንበር ቀይሪ ሌላ ተሳፋሪ ልንጭን ነው በማለት ወደ ጋቢና ያስገቧታል።

ጋቢና ከገባች በኋላ አሽከርካሪው በተራው የትራፊክ ፖሊስ እንዳይቀጣኝ ቀበቶ ማሰር አለብሽ ብሎ ራሱ ሊያስርላት በመሞከር እና በሩም በደንብ አልተዘጋም ልዝጋው በማለት ካዋከቧት በኋላ ከቦርሳዋ ውስጥ የዋጋ ግምቱ 7 ሺህ ብር የሚያወጣ የሞባይል ስልክ በመውሰድ ገፍትረው ከተሽከርካሪው ማስወረዳቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘገኘው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ብሔራዊ ባንክ ከዓለም ዐቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት ወሰነ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታት ከዓለም ዐቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት መወሰኑን አስታወቀ።የባንኩ የከረንሲ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አበበ ሰንበቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታትና የኮንትሮባንድ ንግዱን ለመቆጣጠር ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከዓለም ዐቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ እንደ ወርቁ ብዛት ከ10 በመቶ እስከ 29 በመቶ ጭማሪ በማድረግ ይገዛ እንደነበር አስታውሰዋል።በዚህም ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በነበሩት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ የሆነ የወርቅ አቅርቦት መገኘቱን ገልጸዋል።በእነዚህ ዓመታት ባንኩ ከወርቅ ግብይት አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር አግኝቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ በጊምቢ ወረዳ፣ ቶሌ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሰኔ 11ዱ ጥቃት የተረፉ ነዋሪዎች አስፈላጊውን የምግብ እርዳታ ስላላገኙ መቸገራቸውን ለቢቢሲ ገለጹ።

ነዋሪዎቹ ቤት ንብረታቸው ከመውደሙ ባሻገር ንግዳቸው እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻቸው ስለተዘረፉ የምግብ ችግር እንደገጠማቸው እየተናገሩ ነው።ቢቢሲ ረቡዕ ሰኔ 15 ቀን 2014 ማለዳ ያናገራቸው ነዋሪዎች እንዳሉት፣ በአካባቢው አሁን ላይ የፀጥታ ስጋት ባይኖርም በቂ ምግብ የላቸውም።ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው ሰዎች ዘመዶቻቸው ጋር ተጠልለው እንደሚውሉና የተወኑት ምሽት ላይ በመስጅዶች ውስጥ እንደሚጠለሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

በቶሌ ቀበሌ በሚገኙት ጉቱ፣ ጨቆርሳ፣ ስልሳው፣ በገኔ፣ ጫካ ሰፈር እና ሀያው በተባሉ መንደሮች (ጎጦች) ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ. ም. በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ከ300 የሚልቁ ንጹሀን ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናግረዋል።ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ ይፋዊ ቁጥር በመንግሥት በኩል ባይነገርም፣ የዐይን እማኞች እንዲሁም የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሟቾችን ቁጥር ከ300 በላይ አድርሰውታል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአገራቸው ጦር አዲስ ስሪቶቹን ታላላቅ የጦር መሳሪያዎች ይታጠቃል አሉ፡፡

ፑቲን በቅርቡ ሰራዊታቸው ይታጠቃቸዋል ካሏቸው ዘመን አፈራሽ የጦር መሳሪያዎች መካከል S-500 የሚሳየል መከላከያ ጋሻ አንዱ እንደሆነ B 92 የወሬ ድረ ገፅ ፅፏል፡፡

S-500 የሚሳየል መከላከያ ጋሻ አሁን በአገልግሎት ላይ ከሚገኙት S-300 እና S-400 የሚሳየል መከላከያ ጋሻዎች በእጅጉ የላቀ ነው ተብሏል፡፡

የሩሲያ ጦር ይታጠቃቸዋል ከተባሉት ዘመን አፈራሾች መካከል ሳርማት አህጉር አቋራጭ ሚሳየል እንደሚገኝበት በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ሳርማት በቅርቡ ሙከራው እጅግ በተሳካ ሁኔታ እንደተከናወነ ዘገባው አስታውሷል፡፡

ሚሳየሉ በዓለማችን አሁን ካሉት ሚሳየሎች ሁሉ አቻ የለሽ እንደሆነ ፑቲን ተናግረውታል፡፡

[Sheger]
@YeneTube @FikerAssefa
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው ተሾሙ!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከሀላፊነታቸው በመነሳት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው ተሹመዋል።

በምትካቸውም በኬንያ ለሦስት ዓመት የኢትዮጵያ በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ያገለገሉት  መለስ ዓለም ሚኒስቴሩ  በቅርቡ ባካሄደው ማሻሻያ እንደ አዲስ የተዋቀረውን ይህን ዳይሬክተር ጄኔራል እንዲመሩ ተሹመዋል።

አምባሳደርነት መለስ ዓለም በምክትል ጠቅላይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተፈረመ የሹመት ደብዳቤ እንደደረሳቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች ሰምቻለሁ ስትል አሻም ዘግባለች።

ምንጮቹ አክለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወቅቱ ቃልአቀባይ  አምባሳደር  ዲና ሙፍቱ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው መሾማቸውን ተናግረዋል።

አምባሳደር መለሰ በኬንያ፣ ማላዊ ሲሸልስ እና ኮሞሮስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ከመመደባቸው በፊት የውጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ሰርተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት ህወሃት የእርዳታ አውሮፕላኖች መቀሌ ኤርፖርት እንዳያርፉ መከልከሉን አስታወቀ!

የህወሃት ቡድን የእርዳታ አውሮፕላኖች መቀሌ ኤርፖርት እንዳያርፉ መከልከሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

መንግስት በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች አስፈላጊው ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርሳቸው ለማድረግ ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል።

ከተለያዩ አለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበርም አስፈላጊ መሰረታዊ ድጋፎች በየብስም በአየርም ሲያጓጉዝ ቆይቷል።

በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን ይህንን የመንግስትን ጥረት ጥላሸት ለመቀባትና የሃሰት ፕሮፖጋንዳውን ለመንዛት ሲል ወደ ክልሉ የሚገቡ ሰብአዊ ድጋፎች የሚገቡበትን ሂደት ለማስተጓጎል በተደጋጋሚ መሞከሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።

በየብስ የሚገቡትን ሰብአዊ ድጋፎች ለትግራይ ህዝብ እንዳይደርሱ መንገድ በመዝጋትና የእርዳታ ማስተላልፊያ ኮሪደሮች አካባቢ ትንኮሳ በመፈጸም ከራሱ የፕሮፖጋንዳ ስሌት ባሻገር ለትግራይ ህዝብ ግድ አንደሌለው በተግባር እያሳየ መምጣቱን ነው መንግስት የገለፀው።

መንግስት በቡድኑ በኩል የሚመጡ እንቅፋቶችን በመቋቋም አስፈላጊውን ያልተቋረጠ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርስ ማድረጉ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ እውቅና የተሰጠው መሆኑ ገልጿል።

ሆኖም አሁን መንግስት ያመቻቸውና በየቀኑ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች እንዲሁም የህጻናት አልሚ ምግቦች የሚላክበትን የአየር በረራ የሽብር ቡድኑ መከልከሉና ከትናንት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የእርዳታ አውሮፕላኖች መቀሌ ኤርፖርት እንዳያርፉ ማድረጉ ታውቋል።

መንግስት ይህ የህወሃት ቡድን እርምጃ ቡድኑ የትግራይን ህዝብ የሃሰት ፕሮፖጋንዳው መሳሪያ ከማድረግ ውጪ ሌላ አላማ እንደሌለው ዳግም በተግባር የሚያረጋግጥ ነው ብሏል።

ይህንን የቡድኑን ውሳኔ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያወግዘው የክልከላውንም ምክንያት እንዲያጣራም መልዕክቱን አስተላልፋል።

በተጨማሪም መንግስት እስካሁን ሲያደርግ እንደቆየው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉ የትግራይ ክልል ዜጎች አስፈላጊው ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርሳቸው የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የተቋረጡ መሰረተ ልማቶችን መመለስ የድርድሩ ቅድመ ሁኔታ እንጂ የድርድር አካል አይደለም ሲል ህወሓት ገለፀ!

በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ በትግራይ ክልል የተቋረጡ የቴሌኮም፣ መብራት፣ የባንክ እና የትራንስፖርት አገልግሎት ማስጀመር የድርድሩ ቅድመ ሁኔታ እንጂ የመደራደሪያ ነጥብ አይሆንም ሲል ህወሓት አስታውቋል።

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ትላንት ሰኔ 15 ቀን 2014 በሰጡት መግለጫ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጉዳይ ለድርድሩ መሳካት ትልቅ ሚና የሚኖረው በመሆኑ ከድርድሩ በፊት ችግሮቹ ይፈታሉ ብለን እናምናለን ብለዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል ስለ ድርድሩ ውይይት እየተደረገ እንጂ ገና ድርድር አልተጀመረም ብለዋል።

ፖላቲካዊ ችግሩ በሰላም እንዲፈታ ዝግጁ ነን ያሉት ጌታቸው ረዳ፤ ይሁን እንጂ የታየውን የድርድር ተስፋ ለማደናቀፍ “በሻዕቢያ መንግስት እና የእሱ ተላላኪ በሆኑ የአማራ ተስፋፊዎች” ትንኮሳ እየፈፀሙ ነው በማለት ወቀሳ ሰንዝረዋል።

ቃል አቀባዩ እየተፈፀሙ ላሉት ትንኮሳዎች ተመጣጣኝ እርምጃ ከመውሰድ ውጪ እንደቀደመው ወደለየለት ጦርነት ላለመግባት ጥረት እያደረግን ነው ብሏል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ ውድቅ አደረገች!

ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስታወቀች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መግለጫ ሰጥተዋል።ቃል አቀባዩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ከሰሞኑ የአውሮፓ ህብረት እና ግብጽ በጋራ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ባወጡት መግለጫ ዙሪያ አስተያየት ሰጥተዋል።

አውሮፓ ህብረት በእስካሁኑ የህዳሴው ግድብ የሦስትዮሽ ውይይቱ ላይ ታዛቢ ነበር ያሉት አምባሳደር ዲና፤ የሰሞኑ አስተያየት ግን ውግንናውን ለግብጽ በሚመስል መንገድ መግለጫ ሰጥቷል ብለዋል።የአውሮፓ ህብረት ከግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመሆን የግብጽ ታሪካዊ የውሃ ድርሻ ሊነካ አይገባም ብሏል።ይህ አስተያየት ከአንድ የድርድሩ ታዛቢ አካል መሰጠቱ ውግንናው ላይ ጥያቄ እንድናነሳ አስገድዶናል ያሉት አምባሳደር ዲና፤ ህብረቱ ከግብጽ ጎን ወግኖ የሰጠውን አስተያየት መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለንም ማለታቸውን አል አይን ዘግቧል።

በኢትዮጵያውያን እና መንግስት ወጪ እየተገነባ ያለው ታላቁ የህዳሴው ግድብ ግንባታ 84 በመቶ መጠናቀቁ ይታወሳል።ግንባታው በዚህ ደረጃ ላይ እያለም ከግድቡ ኹለት ተርባይኖች 700 ሜጋ ዋት ሀይል እንዲያመነጩ ለማድረግ በተደረገው ጥረት ከሦስት ወራት በፊት አንዱን ተርባይን ወደ ሥራ በማስገባት 350 ሜጋ ዋት ሀይል ማመንጨት መጀመሩም አይዘነጋም።ሦስተኛው የህዳሴው ግድብ ውሀ ሙሌት በሚቀጥለው ወር እንደሚጀመር መንግስት ከዚህ በፊት በሰጣቸው መግለጫ መናገሩ ይታወቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
ተመድ ምዕራብ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸመውን «አሰቃቂ» የጅምላ ግድያ ላይ ባለሥልጣናት ፈጣን፣ ገለልተኛ እና ጥልቅ ምርመራ እንዲያካሂዱ ጠየቀ።

«በቶሌ መንደር የተፈጸመው የጭካኔ ግድያ እና የነዋሪዎች በጥቃቱ ምክንያት ተገድዶ መፈናቀል ዘግንኖኛል» ያሉት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ኃላፊ ሚሼል ባችሌት ቅዳሜ ዕለት ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት እማኝን ባልደረባቸው እንዳነጋገሩ እና ወደ መንደሩ የገቡት ታጣቂዎች በነሲብ ተኩስ ከፍተው ብዙዎችን እንደገደሉ መረዳታቸውን ገልጸዋል።ከሟቾቹ አብዛኞቹ ሴቶች እና ሕጻናት መሆናቸውን እንዲሁም ቢያንስ 2000 ሰዎች ከአካባቢው ለመሸሽ መገደዳቸውንም አመልክተዋል።

አራት ሰዓት በፈጀው ጥቃትም ታጣቂዎቹ በርካታ ቤቶችን ማቃጠላቸውንም የኃላፊዋ መግለጫ ዘርዝሯል።ከጥቃቱ የተረፉት በጥቃቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ጎሳ ተወላጆች መገደላቸውን አስከሬን አሁንም በመንገዶች ላይ ወድቀው ሊገኙ እንደሚችሉ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል።የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ጥቃቱ በኦሮሞ ነጻነት ጦር፤ መንግሥት አሸባሪ ባለው ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መፈጸሙን ይናገራሉ።

የታጣቂው ቡድን ቃል አቀባይ በበኩሉ በመንግሥት ደጋፊ ሚሊሻዎች ነው የተፈጸመው በሚል በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጥሪ ማቅረቡ ተዘግቧል። ባችሌትም በመግለጫቸው ባለሥልጣናት «ጥቃቱ በአፋጣኝ መጣራቱን፤ ሰለባዎች እና ቤተሰቦቻቸው እውነት፣ ፍትህ እና ካሣ የማግኘት መብታቸውን እንዲሁም አጥፊዎችን በተጠያቂነት መያዛቸውን እንዲያረጋግጡ» ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች በጥቃቱ ወቅት መታገታቸውን እና ያሉበት እንደማይታወቅም አጽንኦት በመስጠት ባለሥልጣናት የታገቱት ነጻነታቸውን እንዲያገኙ አስፈላጊ እና ሕጋዊ ርምጃዎችን እንዲወስዱም አሳስበዋል።

[DW]
@YeneTube
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከሰሞኑ የደረሰውን የንጹሃን ግድያ አወገዙ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በወለጋና በጋምቤላ በደረሰውን አሰቃቂ የንጹሃን ግድያ ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ብፁዕነታቸው በመልዕክታቸው በወለጋና በጋምቤላ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ያወገዙ ሲሆን መንግሥትና ሕዝብ ግፍን በተግባር ማውገዝ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን ስለ ሰላም አስፈላጊነት ማስተማር ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን ከኢኦቴቪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ 85 ተማሪዎች በጎርፍ ተከበው ለ25 ደቂቃ መቆየታቸው ተነገረ!

ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታዊ ፊጋ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ባለዉ ኒዉ ፖራዳይ መዋለ ህጻናት ትምህርት ቤት ዉስጥ ከዋናዉ መንገድ ጥሶ የገባዉ ጎርፍ በክፍል ዉስጥ የነበሩ እድሜያቸዉ ከ4 እስከ 7 የሆኑ 85 ተማሪዎች በጎርፉ መከበባቸው ተሰምቷል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር 85ቱንም ተማሪዎች ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባቸዉ በጎርፍ ከተያዙበት ክፍል ዉስጥ ማዉጣት ተችሏል ብለዋል።

በዚህ ሂደት የኒዉ ፖራዳይ ትምህርት ቤት መምህራንና የአስተዳደር አካላት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እስኪደርሱ ተማሪዎቹን በማረጋጋትና የቻሉትን ሁሉ በማድረጋቸዉ ኮሚሽን መ/ ቤታችን ምስጋናዉን ያቀርባል ሲሉ አክለዋል።

ቀጣዩ የክረምት ጊዜ የሚበረታ በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ከኮሚሽን መስሪያ ቤቱ እና ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በተከታታይ የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa