የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት በቀጣዮቹ ዓመታት ጦርነት ቆሞ ሰላም እንደሚሰፍን ዘመኑም መልሶ ግንባታ ላይ ትኩረት የሚደረግበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የቀጣዩን አመት በጀት አስመልክቶ ባቀረቡት የበጀት መግለጫ እንደገለፁት ሰላም ሰፍኖ ኢኮኖሚው ከተግዳሮቶች የተላቀቀና ለቀጣይ የማክሮኢኮኖሚ መረጋጋት ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጠር ታሳቢ ተደርጓል ብለዋል።በዚህም ኢኮኖሚው ከነበረበት ችግሮች በማገገም በ2015 በ9.2 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ ግምት መያዙን ገልፀዋል።የፌደራል መንግስት አጠቃላይ የ2015 በጀት 786.6 ቢሊየን ሆኖ የቀረበ ሲሆን በጀቱ ከአምናው አንጻር የ16.6 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ተነግሯል።ከምክርቤቱ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ረቂቅ በጀቱ ለአንድ ወር ያህል የተለያዩ ውይይቶች ተደርገውበት በሰኔ 2014 መጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
@YeneTube @FikerAssefa

በአዲስ አበባ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ይገታል የተባለለት ምክር ቤት መመስረቱ ተገለጸ፡፡
በመዲናዋ የምክር ቤቱ ምስረታ የበርካታ የህገወጥ ሰዎች ዝውውር መነሻ እና መዳረሻ ናት በሚባለው አዲስ አበባ የተቀናጀ ስራ በመስራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ይገታል የተባለለት ምክር ቤት መመስረቱ ተገለጸ፡፡በመዲናዋ የምክር ቤቱ ምስረታ የበርካታ የህገወጥ ሰዎች ዝውውር መነሻ እና መዳረሻ ናት በሚባለው አዲስ አበባ የተቀናጀ ስራ በመስራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡በአዲስ አበባ ደረጃ የተመሰረተው ህገወት የሰዎች ዝውውርን የሚከላከለው ምክር ቤት የችግሩ መነሻ ከሚሆኑ ክልሎች ጋር በአብሮነት የሚሰራበት ቋት መኖሩም ነው የተነገረው፡፡ ወ/ሮ ጽዋዬ ሙልነህ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ኃላፊ ናቸው፡፡
ኃላፊዋ እንደሚሉት አሁን አሁን የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል ለሚባለው ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ከቢሮያቸው ባሻገር በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ለችግሩ እልባት ለመስጠት ቅንጅታዊ ስራ ማስፈለጉ ለምክር ቤቱ ምስረታ ዋናው ምክኒያት ነው ይላሉ፡፡አዲስ አበባ ከተማ በአገሪቱ ለበርካታ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ማስተላለፊያነት፣ መነሻ እና መድረሻነት ስሟ ይጠቀሳል፡፡ይሁንና በርካታ በሰላምና ፀጥታ እጦት ችግር የሚሰቃዩና ለአስከፊ ስደትም ዜጎች የተዳረጉባቸው አከባቢዎች መኖራቸው የምክር ቤቱ በአዲስ አበባ ብቻ መመስረትን እንዴት ችግሩን መፍታት ይቻለዋል የሚል ጥያቄም አንስተንላቸዋል፡፡
ዛሬ ሰኞ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የህገወጥ ሰዎች ዝውውር መቆጣጠሪያ ከተለያዩ ተቋማት በተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ሲመሰረት ለተሳታፊዎች ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህገወጥ ሰዎች ዝውውር መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ በበኩላቸው፡፡በምክር ቤቱ ምስረታ የተለያዩ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ሲንፀባረቁ፤ በተለይም የስዴት ፍልሰትን ለመግታት ዋናው ተግባር በኢኮኖሚውና ስራ እድል ፈጠራ ላይ በሰፊው መስራት እንደ መፍትሄ ሊቀርብ የሚችል ነው ተብሏል፡፡የሰዎች ዝውውርን ለመግታት የተቋቋመው አዲሱን ምክር ቤት በኃላፊነት የሚመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በዚሁ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።
[DW]

በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ በደረሰ የእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ!
በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ያጋጠሙ ሁለት የእሳት አደጋዎች በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡አንደኛው የእሳት አደጋ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ቦታ መኮንኖች ክበብ አካባቢ በአንድ መኖሪያ እና አንድ የንግድ ቤት ላይ ከሌሊቱ አምስት ሰዓት አካባቢ መድረሱን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
በእዚህ አደጋ ሳቢያ በመኖሪያው ቤት በእንቅልፍ ላይ የነበሩ እና እድሜያቸው የ40 ዓመት የተገመተ ጎልማሳ በእሳት ቃጠሎው ህይወታቸው ማለፉን ባለሙያው ገልጸዋል፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠር ሁለት የአደጋ ግዜ ተሸከርካሪ እና አስራ ስድስት የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ደርሰው አንድ ሰዓት በፈጀ ጊዜ አደጋው የከፋ ጉዳት በሰውም ሆነ በንብረትም ሳያደርስ መቆጣጠር እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡
ሁለተኛ አደጋ የደረሰው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው በርታ ኮንስትራክሽን ጀርባ በጋራዥ ውስጥ የደረሰ ሲሆን አደጋው የከፋ ጉዳት እንዳላደረሰ ተነግሯል፡፡በእዚህ ሁለተኛ የእሳት አደጋ ሀያ ሺብር የሚገመት ንብረት መውደሙን አቶ ንጋቱ ማሞ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
Via Bisrat FM

👍1
በአዲስ አበባ ክረምቱን ተከትሎ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ 141 ቦታዎች ተለይተዋል ተባለ፡፡
ክረምቱን ተከትሎ በመዲናዋ የጎርፍ አደጋ ይከሰትባቸዋል በተባሉት ቦታዎች የኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቋል፡፡
የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በአዲስ አባባ በተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋ የሚከሰትባቸው ቦታዎች ተለይተው የጥንቃቄ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡
በከተማዋ ከፍተኛ የጎርፍ ተጋላጭ ናቸው ተብለው ከተለዩት አካባቢዎች መካከል አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አንደኛው ሲሆን ኮልፌ ቀራኒዮም ከፍተኛ ተጋላጭ ተብለው ከተለዪ ቦታዎች ይገኝበታል፡፡
እንዲሁም ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ አራዳ እና ቦሌ ክፍለ ከተሞች ደግሞ በከፊል ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብሏል፡፡ህብረተሰቡ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሚያደርጉ የፈሳሽ ማጋጃች ቱቦዎች ባግባቡ እንዲጠቀምባቸው ባለሙያው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ባሳለፍነው 2013 ዓ.ም 11 ሰዎች በጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል፡፡
Via Ethio FM

ኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደሮች ድርጅት በኢትዮጵያ በአማራ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ የ145 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ!
ኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደሮች ድርጅት በኢትዮጵያ በአማራ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ የ145 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ፡፡
ድርጅቱ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር ተያይዞ በአማራ ክልል ባደረገው ጥናት በ145 ሚሊዮን ብር የአደጋ ጊዜ እርዳታ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን የኤስ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደሮች ድርጅት በኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ሳህለማሪያ አበበ ገልጸዋል።
ድርጁቱ በቀጣይ ጦርነቱ ጉዳት ባደረሰባቸው በትግራይ እና በአፋር ክልል ተመሳሳይ ጥናት በማድረግ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ፕሮጀክቶች ይፋ እንደሚያደርግም ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።
ፕሮጀክቱ ስኬታማ እንዲሆን ከመንግሥት ተቋማት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ሊደረግ እንደሚገባ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ገልጸዋል።
ለፕሮጀክቱ የሚሆን ፋይናንስ ድጋፍ ከጀርመን ኤስ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደሮች ድርጅት የተገኘ መሆኑም ተመላክቷል።በሁለት አመት ውስጥ በ4 ሚሊዮን ዩሮ 2 መቶ ሺህ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም ድርጅቱ አስታውቋል።

ሱዳን ብሔራዊ ምክክር ማድረግ ጀመረች!
ሱዳንን ከገጠማት ፖለቲካዊ ቀውስ እንደሚያወጣ ተስፋ የተጣለበት ብሔራዊ ምክክር ዛሬ በካርቱም ተጀመረ፡፡ምክክሩ በሌ/ጄ አል ቡርሃን የሚመራውን ወታደራዊ መንግስት ጨምሮ ሌሎችን ተቀናቃኝ አካላት የሚያሳትፍ ሲሆን ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣት ወደ ምርጫ ለማምራት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡
የምክክሩን መጀመር አስመልክተው ትናንት ማታ (ማክሰኞ) ለሱዳናውያን መልዕክትን ያስተላለፉት የሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሱዳናውያንን ህልም እውን ለማድረግ ከሁሉም አካላት ጋር በመተባበር እንሰራለን ብለዋል፡፡
ሱዳን ሽግግር ላይ መሆኗን ተከትሎ ስምምነት በመታጣቱ ብዙ ችግሮች ማጋጠማቸውን ያስታወሱት ቡርሃን የሚመሩት ጦር ሽግግሩ እንዲያበቃ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንና ለዚህም ከ2019 ጀምሮ (እ.ኤ.አ) ቃል ገብቶ እየሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡ጦሩ ለምክክሩ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል ለስኬታማነቱ እንደሚታገም ነው አዛዡ የተናገሩት፡፡
[Alain]

ፍርድ ቤቱ ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ ( ሻላዬ) ከ3ኛ ፎቅ ወድቃ ህይወቷ ካለፈው ከዶክተር ቤዛ ተዋበ ሞት ጋር በተያያዘ በተጠረጠረበት የግድያ ወንጀል ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ 12 ቀን ፈቀደ።
ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ ከጠበቃው ገመቹ ጋር በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ ጉዳዩ ታይቷል።
መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በግንቦት 19 ቀን በዋለው ችሎት በተሰጠው የ 12 ቀን የምርመራ ጊዜ የምስክር ቃል መቀበሉን ተናግሯል።የሟች ዶ/ር ቤዛ ተዋበ አስከሬን ምርመራ ውጤት የመጣ ቢሆንም ከሶስተኛ ፎቅ እራሷን አጥፍታነው ወይስ ተገፍትራ ነው የሚለውን ለማጣራት ሙያዊ ማብራሪያ እንደማጠይቅ ለችሎቱ ገልጿል።
ሟች ከተጠርጣሪው ጋር በስልክ ያደረገችውን የድምጽና የመልክት ልውውጥ ለማጣራት ኢትዮ ቴሌኮምን በደብዳቤ ጠንቆ ውጤት እየተጠባበቀ መሆኑን አስረድቷል።ለተጨማሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
የድምጻዊ አብርሀም ጠበቃ ገመቹ በበኩላቸው ለፖሊስ ከዚህ ቀደም በተሰጠ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት የደንበኛዬን ንጽህና ያረጋግጣለሰ ብለን ነበር።እራስን የማጥፋት እንጂ የግድያ ወንጀል ተፈጽሞ አለመሆኑ እየታወቀ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ እንኳ ይህን የሚያረጋግጥ ምርመራ ውጤት አላቀረበም ተከራክሯል።
ደንበኛዬ ቋሚ አዶራሻ ያላቸው ከመሆናቸው አንጻር እና መርማሪ ፖሊስ ያቀረበው ምክንያት በስነስርዓት ህጉ 63 መሰረት ዋስትናን የሚያስከለክል ባለመሆኑ የዋስ መብታቸው ይከበር ሲል ጠበቃው የዋስትና ጥያቄ አቅርቧል።
የችሎቱ ዳኛ በኩል ተጠርጣሪው ከግድያው ጋር ምን ትስስር አለው ተብሎ ለመርማሪ ጥያቄ ቀርቧል።
ሟች ከተጠርጣሪው ጋር የፍቅር ግንኙነት እንደነበረና ቀደም ብላ ተጣልተው ስለነበር ሟች ይቅርታ ልጠይቀው በመኖሪያ ቤቱ በሄደችበት ወቅት ከ3ኛ ፎቅ ላይ ወድቃ በጭቅላቷ እና በሰውነት አካሏ ላይ ስለታማ ግዑዝ ነገር ጉዳት እንደደረሰባት በአስከሬን ምርመራ ስለሚያሳይ ምናልባት በተጠርጣሪው ተገፍትራ ሊሆን ስለሚችል ለማጣራት የህክምና ማብራሪያ እንደጠይቃለን ሲል መርማሪ ፖሊስ ምላሽ ሰቷል።
በምስክር በኩል ሟች ከተጠርጣሪ አብርሀም መኖሪያ ቤት 3 ኛ ፎቅ እንደወደቀች እና ወዲያውኑ በሩ ላይ ተጠርጣሪውን መመልከታቸውን ገልጸውልናል ይህንንም እያጣራን ነው ሲል ፖሊስ አብራርቷል።
ጠበቃ ገመቹ በበኩሉ ሟች ከ3ኛ ፎቅ ወድቀው ስለመሞታቸው የካደ የለም ያለ ሲሆን የህክምና ማስረጃ ተገፍትረው ነው ወይስ አደለም የሚለውን ለመለየት ተብሎ በፖሊስ የተገለጸው በባለፈው ቀጠሮ የቀረበ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን ይመሕከትልን ሲሉ ጠይቀዋል።ፍርድቤቱም የፖሊስን የምርመራ መዝገብ ከተመለከተ በኋላ ለፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ 12 የምርመራ ቀናትን ፈቅዷል።
Via Tarik Adugna

ስራቸውን በአግባቡ በማይወጡ የሲሚንቶ አከፋፋዮችና አምራቾች ላይ እርምጃ እወስዳለው ሲል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስጠነቀቀ፡፡
የሚኒስቴር መ/ቤቱ የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ሃሰን ሙሃመድ ከ230 በላይ የሲሚንቶ አምራቾችና አከፋፋዮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የሲሚንቶ ጉዳይ ሃገራዊ ችግር እንደሆነና ለዚህም ችግር መከሰት የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትን ተከትሎ የግብይት ስርዓት ላይ የሚስተዋለው ውስብስብ ችግር የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡
መንግስት የሲሚንቶ ምርት ዋጋ ላይ የቁጥጥር ስርዓቱን ማንሳቱን ተከትሎ በፊት ሲሸጥ ከነበረበት ዋጋ ከእጥፍ በላይ ጭማሪ በማድረግ፣ በአሁኑ ወቅት ሲሚንቶ በገበያ ላይ እስከ 1200 ብር እየተሸጠ መሆኑን ሚንስትር ዴኤታዉ ገልጸዋል፡፡
ይህም ያልተገባ ድርጊት መንግስት ካሁን ቀደም በሲሚንቶ የግብይት ሂደት ውስጥ ያስቀረውን የዋጋ ቁጥጥር ስርዓት በድጋሜ እጁን እንዲያስገባ እያስገደደው እንደሚገኝና በነዚህ ህገ ወጥ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ መናገራቸዉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንት መርማሪ ፖሊስ በሦስት ጋዜጠኞች ላይ ባቀረበው ይግባኝ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሰጠ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ችሎቱ በይግባኙ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ ባዋለው ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠባቸው፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ሰለሞን ሹምዬ እና መዓዛ ሞሐመድ ናቸው። የስር ፍርድ ቤት ተጠርጣሪዎቹ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትናንት ወስኖ የነበረ ቢሆንም፣ መርማሪ ፖሊስ ግን ወዲያውኑ ይግባኝ በመጠየቁ ተጠርጣሪዎቹ በዕለቱ ሳይፈቱ እንደቀሩ ይታወሳል።
[ዋዜማ ራዲዮ]

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጃዋር መሀመድ የድርጅቱን ህጋዊ ባንዲራ ያለአግባብ እንዳይጠቀም አሳሰበ!
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር የሆነው አቶ ጃዋር መሀመድ ህጋዊ ባንዲራዬን ያለአግባብ እየተጠቀመበት ነው ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ገለፀ።ኦነግ ለኦፌኮ በፃፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው “በህግ እና በምርጫ ቦርድ የተመዘገበውን የኦነግ ባንዲራ አቶ ጃዋር መሀመድ ከህግና ስርዓት ውጪ እየተጠቀመው ስለሆነ እንድታስቆሙልን እንጠይቃለን” ብሏል።
በፓርቲዎቹ መካከል ያለውን ትብብር እንዲሁም የሀገሪቱን ህግ በማክበር ይህ ድርጊት ይቆማል ብለን ጠብቀን ነበር ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ድርጊቱ በመቀጠሉ ይህን ደብዳቤ ለመፃፍ ተገደናል ሲል አስታውቋል።
በመሆኑም ይህ ደብዳቤ ለኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከደረሰበት ቀን ጀምሮ አቶ ጃዋር መሀመድ የኦነግን ባንዲራ በተለያዩ መድረኮች ላይ እንዳይጠቀም እንድታሳስቡት እንጠይቃለን ብሏል።
[Addis Zeybe]

በሕገወጥ መንገድ የሚሠሩ የሜትርና ኤሌክትሮኒክ ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች በመኖራቸው፣ እንደገና ምዝገባ እንዲደረግ መወሰኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
የሜትርና የኤሌክትሮኒክ ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ማኅበራትና ድርጅቶችን ለመቆጣጠር በሚያስችል መንገድ ማሻሻያ መደረጉንና በዚህ መሠረት አገልግሎት ሰጪዎቹን እንደ አዲስ መመዝገብ ማስፈለጉን፣ በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብና ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች የስምሪት ዳይሬክተር አቶ አልዓዛር ይርዳው ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ 53 የሜትር ታክሲ ማኅበራት መኖራቸውን ገልጸው በእነዚህ ማኅበራት ውስጥም 2,800 ተሽከርካሪዎች ይገኛሉ ብለዋል። ከእነዚህ ውስጥም ፈቃዳቸውን በወቅቱ ያላደሱ በርካታ ማኅበራት በመኖራቸው ለቁጥጥር እንዲያመች በድጋሚ ምዝገባ ሊደረግ መሆኑን አክለዋል።
በተጨማሪም እስካሁን በቢሮው ዕውቅና ያገኙት የኤሌክትሮኒክ ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች 17 ብቻ መሆናቸውን፣ ከእነዚህ ውጪ ፈቃድ ሳያወጡ የሚሠሩ መኖራቸውን ገልጸዋል። ፈቃድ ካወጡት ውስጥም አብዛኞቹ በወቅቱ ሳያድሱ እየሠሩ በመሆናቸው እንደገና ምዝገባ ማድረግ አስፈልጓል ብለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://www.ethiopianreporter.com/article/25749
[Reporter]

በዛሬው እለት በሶስት ዙር 1 ሺህ 30 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ።
ከእነዚህ ውስጥ 209 ሴቶች 68 ህጻናትና 753 ወንዶች መሆናቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 34 ሺህ 328 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

ፌደራል መንግሥት ለቀጣዩ ዓመት ካዘጋጀው 786 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ውስጥ ለትግራይ ክልል 12 ቢሊዮን ብር መመደቡን ዋዜማ ዘግባለች። ለኦሮሚያ ክልል 71 ቢሊዮን ብር፣ ለአማራ ክልል 44 ቢሊዮን ብር፣ ለደቡብ ክልል 26.5 ቢሊዮን ብር፣ ለሱማሌ ክልል 20.5 ቢሊዮን ብር፣ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 6.4 ቢሊዮን ብር፣ ለአፋር ክልል 6.2 ቢሊዮን ብር፣ ለቤንሻንጉል ክልል 3.7 ቢሊዮን ብር፣ ለሐረሬ ክልል 1.5 ቢሊዮን ብር፣ ለጋምቤላ ክልል 2.4 ቢሊዮን ብር እና ለሲዳማ ክልል ደሞ 8.4 ቢሊዮን ብር ድጎማ ተመድቦላቸዋል። በጀቱ የ234 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንደሚገጥመው እና ዘንድሮ ይመዘገባል ተብሎ የተጠበቀው የ8.7 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት እንደማይሳካ ገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ትናንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ እና አፋር በጦርነት ወቅት የተፈጸሙ ወንጀሎች የመረመረው የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ሪፖርቱን ይፋ ሊያደርግ ነው!
በሰሜኑ ጦርነት በአማራ እና አፋር ክልሎች የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚመረምረው የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል፤ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የምርመራ ሪፖርቱን ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ። ግብረ ኃይሉ በምርመራው በሁለቱ ክልሎች ብቻ በሺህዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን መገደላቸውን አረጋግጧል ተብሏል።
የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ያቋቋመውን ጽህፈት ቤት በኃላፊነት የሚመሩት ዶ/ር ታደሰ ካሳ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 1፤ 2014 ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ የምርመራ ሪፖርቱን ይፋ ለማድረግ ዝግጅት መጀመሩን ተናግረዋል። የምርመራ ሪፖርቱ “በቁጥርም፤ በአካባቢም ዝርዝር መረጃዎችን” ይዞ እንደሚወጣም ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።
ለሪፖርቱ ግብዓት የሆኑ “አስፈላጊ” መረጃዎች የተሰበሰቡት፤ የሚኒስትሮች ግብረ ኃይሉ ከሶስት ወራት ገደማ በፊት ባሰማራቸው የምርመራ ቡድኖች ነው። በአማራ እና አፋር ክልል በሚገኙ ዘጠኝ አካባቢዎች የተሰማሩት ቡድኖች 158 አባላት ያሏቸው ናቸው።
ግብረ ኃይሉ ባሰማራቸው የምርመራ ቡድኖች አማካኝነት ሲያሰባስባቸው የቆያቸውን መረጃዎች የመተንተን ሂደት፤ በቀረው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚከናወን መሆኑን ዶ/ር ታደሰ አስረድተዋል። ትንተናውን ተከትሎም ግብረ ኃይሉ “የትኛው ማስረጃ የትኛውን ወንጀል ነው የሚደግፈው እና የሚያስረዳው” የሚለውን እንደሚወስን የጽህፈት ቤት ኃላፊው ገልጸዋል።
Via Ethiopia Insider

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ነን በማለት ጦር መሣሪያና ሐሰተኛ መታወቂያ በመጠቀም ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪ ግለሰቦችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ልዩ የክትትል አባላት ነን በማለት ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያና ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ተደራጅተው የዝርፊያ ወንጀል ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ፖሊስ ባደረገው ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ በመታጠቅ እና ሐሰተኛ የፖሊስ መታወቂያ በመያዝ ፖሊስ መስለው ወንጀል የሚፈፅሙ ሲሆን ለአብነት የሚጠቀሙባቸው ስሞች ባይሳ ገመቹ እና መርጋ ጋሩማ በሚሉና ትክክለኛ ባልሆኑ መታወቂያዎች አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው መርካቶ ይርጋ ኃይሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የወንጀል ድርጊት ሲፈፅሙ ፖሊስ ደርሶባቸው በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል የግለሰቦቹ የወንጀል አፈፃፀም ዘዴ ህብረተሰቡ ለማደናገር በቀድሞ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሠራዊት ሬንጀር የደንብ ልብስ ለብሰው በተነሱት ፎቶግራፎች የተዘጋጀ ሐሰተኛ መታወቂያ በመጠቀምና እንዲያሳዩ ሲጠየቁ እንዳይታወቅባቸው በርቀት በማሳየትና በያዙት የጦር መሳሪያ በማስፈራራት ተጨማሪ የወንጀል ተግባር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ፖሊስ ደርሶባቸዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የሚፈጽሙት የፌደራል ፖሊስ ልዩ ክትትል አባላት ነን በማለት በተለያዩ የንግድ ቦታዎች ተሰማርተው በነጋዴው ማህበረሰብ ላይ ጫና በመፍጠር ለዚህ እኩይ ዓላማ ማስፈፀሚያ በሚገለገሉበት ህገወጥ መታወቂያና የጦር መሣሪያ በማስፈራራት የተለያዩ ገንዘቦችንና ሞባይሎችን ሰርቀው ሲሰወሩ እንደነበር ፖሊስ ከህዝብ ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የሚጠቀሙበት መታወቂያ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሚገለገልበት መታወቂያ ጋር በእጅጉ የሚለይ ሲሆን ይዘውት የተገኘው የጦር መሣሪያና ህገ-ወጥ ገንዘብ በተመለከተ ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፖሊስ ምርመራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ይህንን ድርጊት የሚፈፅሙት በተደራጀ መልኩ መሆኑንና ግብረአበሮች እንዳላቸው አመላካች መረጃ በመገኘቱ ምርመራው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላካልና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤ ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት አካላት ጋር በመሆን ጥብቅ ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ እንደሚቀጥል ያረጋግጣል፡፡
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አደረጃጀት ውስጥ ልዩ የክትትል ፖሊስ የሚል ስያሜ አለመኖሩን ህብረተሰቡ እንዲያውቅና ከፀጥታ አከላት ጋር ሆኖ ከነዚህ ዓይነቱ አጭበርባሪዎች ራሱን እንዲከላከል ፖሊስ ያሳስበባል።
በመሆኑም ህዝቡ ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ሲያጋጥመው ትክክለኛውን የፖሊስ የደንብ ልብስና መታወቂያ መሆኑን ማረጋገጥ፤ የሚያጠራጥር ሁኔታ ሲኖር በአፋጣኝ በስልክ ቁጥሮች
+251115-52-63-03፣ +251115-52-40-77፣ +251115-54-36-78 እና +251115-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች በመጠቀም ጥቆማ በመስጠት ወይም በአካባቢው ለሚገኝ የፀጥታ ኃይል መረጃውን በአካል በማድረስ የተለመደ ድጋፍና ትብብሩን እንዲያደርግ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላልፋል።

በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን ቱርክ ገባ!
በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ቱርክ ገብቷል፡፡ልዑካኑ የቱርክ መንግሥት ባዘጋጀው ኢ ኤፍ ኢ ኤስ 2022 በተሰኘው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ለመሳተፍ ነው ቱርክ የገቡት፡፡
ከዝግጅቱ ጎን ለጎን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከቱርክ አቻቸው ጄነራል ያሳር ጉለር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ከዚህ ባለፈም በአቅም ግንባታና ወታደራዊ ድጋፎች ላይ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጠቅሶ ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ እስካሁን 2 ሺህ 100 ሚሳዔሎችን ወደ ዩክሬን አስወንጭፋለች ተባለ
ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ባለፉት 3 ወራት ውስጥ 2 ሸህ 100 ሚሳዔሎችን ወደ ዩክሬን ማስወንጨፏ ተገለፀ።
ከእነዚህም ውስጥ 600 ሚሳዔሎች ከቤላሩስ ወደ ዩክሬን የተተኮሱ መሆኑንም ቪስጋርድ የተባለ ተቋም ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
ቪስጋርድ የተባለው ተቋም ቼክ ሪፐብሊክ፣ ሁንጋሪ፣ ፖላንድ እና ስሎቫኪያ በጋራ የመሰረቱት የባህል እና የፖለቲካ ማዕከል ነው።
@Yenetube @Fikerassefa

አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ
በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ
የነበሩት አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ።
አምባሳደር ተስፋዬ ከሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙትን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን በመተካት ነው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታነት የተሾሙት።
አምባሳደር ሬድዋን የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ/ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጻፈ ደብዳቤ መሾማቸው ይታወሳል።

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በተጠረጠረበት ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት ወንጀል ጉዳይ መታየት ያለበት በብሮድካስት አዋጅን ነው ወይስ በፍርድ ቤቱት ጊዜ ቀጠሮ ነው የሚለውን መርምሮ ብይን ለመስጠት በይደር ተቀጠረ።
በዩቱዩብ ማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፈው የአልፋ ቴሌቢዥን መስራች ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ከጠበቃው ታደለ ገ/መድህን ጋር በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ ጉዳዩን ተከታትሏል።
የምርመራ መዝገቡን የያዙት ሁለት መርማሪ ፖሊሶች ከዚህ በፊት በተሰጣቸው የምርመራ ጊዜ ውስጥ የሰሩትን የምርመራ ሪፖርት ለችሎቱ አቅርበዋል።
በዚህም በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በሚሰሩ አካላት የተደረገ የገንዘብ ስለመኖሩ ማስረጃ መሰብሰባቸውን ለችሎቱ ገልጸዋል።
ከቀሪ ባንኮች የተደረገ የገንዘብ ድጋፍ ውጤት እና በጋዜጠኛው እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ ምርመራ ውጤት እየጠበቁ መሆናቸውን እንዲሁም ተጨማሪ ማስረጃ ከመንግስት ተቋማት ማምጣት እንደሚቀራቸው ለችሎቱ አስረድተዋል።
ከወንጀሉ ውስብስብነት አንጻር ድርጊቱ በሀገር ውስጥ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ አባሪ ለመያዝ እና ቀሪ ማስረጃ ለመሰብሰብ ለተጨማሪ ማጣሪያ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድላቸው ችሎቱን ጠይቀዋል።
የጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ጠበቃ ታደለ ገ/መድህን በበኩላቸው ደንበኛዬ የተጠረጠረው በሚዲያ በሰራው ስራ በመሆኑ ጉዳዩ ሊታይ የሚገባው በመገናኛ ብዙሀን አዋጅ1238/2013 መሰረት ነው ሲሉ ተከራክረዋል።
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 86 ድንጋጌ የብሮድ ካስት የወንጀል ድርጊት በጊዜ ቀጠሮ የሚያሰጥ እንዳልሆነ የገለጹት ጠበቃ ታደለ በዘፈቀደ እስር መታሰሩ አግባብ አደለም በማለት ተከራክረዋል።
ከዚህ በፊት ለፖሊስ በተሰጠው በቂ ጊዜ የምርመራ ስራቸውን በትጋት ባልሰሩበት ሁኔታ ተመሳሳይ ይዘትና ጥያቄ አሁንም ማቅረባቸው በደንበኛዬ ላይ የሰባዊ መብት ጥሰት የሚያስከትል ነው ብለዋል ጠበቃ ታደለ።
ይህም በፖሊስ የቀረበው የተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ሀገራችን በአለም አቀፍ ደረጃ የተስማማችበት የሰባዊ መብት ህግጋትን የሚጥስ ነው ሲሉ ተቃውመዋል።
በተጨማሪም ጠበቃው ቀሪ ማስረጃዎች ከመንግስት መስሪያ ቤት የሚመጣ በመሆኑ ደንበኛዬ ደግሞ ሰነዶችን ሊያጠፋ ወይም ሊደልዝ በማይችልበት ሁኔታ ላይ ታስሮ የሚቆይበት የህግ አግባብ የለም ብለዋል።
ደንበኛዬ ፖሊስ የሚያዙ ቀሪ አባዎች አሉ ብሎ የገለጻቸውን አያውቅም ስለዚህ እንደመያዣ ሆኖ በስር የሚቆይበት አግባብ ስለሌለ የፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ ውድቅ ይደረግልን እና ዋስትና ይፈቀድል ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
መርማሪ ፖሊሶች የዋስትና ጥያቄውን ተቃውመዋል።
እኛ የያዝነው በመገናኛ ብዙሀን ስራው ሳይሆን ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ወንጀል ተጠርጥሮ ነው ሲሉ ማብራሪያ ሰተዋል።
በዚህ በተሰጠን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ በርካታ ስራ ሰርተናል ያሉት መርማሪ ፖሊሶች በሰራነው ዝርዝር ስራ ደግሞ በሀገር ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ ድጋፍ ከሚያደርጉ አካላት በባንክ በዶላርና በኢትዮጲያ ገንዘብ ያስገቡት ገቢን የሚመለከት ማስረጃ እየመጣ ነው ተጨማሪ የሚመጣም አለ ሲል ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷል።
የችሎቱ ዳኛ በግንቦት 29 ቀን በነበረ የችሎት ቀጠሮ ጋዜጠኛው የተጠረጠረበት ወንጀል የሚሸፈነው በብሮድካስት ህግ ነው ወይስ በፍርድ ቤት ጊዜ ቀጠሮ ነው በሚለው ጉዳይ ላይ ፖሊስ አጣርቶ እንዲቀርብ መታዘዙን አስታውሰዋል።
በዚህ ትዛዝ መሰረት መርማሪ ፖሊሶቹ ማጣራትና አላማጣራታቸውን የማረጋገጫ ጥያቄ ዳኛው ያቀረቡ ቢሆንም ፖሊስ አለማጣራቱን መልስ ሰቷል።
በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ የብሮድካስት አዋጅ ለመመልከት በጠባቃ በኩል እንዲቀርብ ታዟል።
ጋዜጠኛ በቃሉ የተጠረጠረበት ወንጀል የሚታየው በብሮድካስት አዋጅ ነው ወይስ በፍርድ ቤት ጊዜ ቀጠሮ የሚለውን አጣርቶ ብይን ለመስጠት በይደር ቀጥሯል።