ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሶማሊያ ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም ሞቃዲሹ ገቡ
በአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ በዓለ ሲመት በዛሬው እለት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት የሶማሊያዋ መዲና ሞቃዲሹ ገብተዋል።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪም የጅቡቲ፣ የኬንያ፣ የቱርክ፣ የባህሬን፣ የዐረብ ሊግ፣ የሕንድ፣ የኢንዶኔዥያ እና የኦማን ተወካዮች ሞቃዲሾ መግባታቸውን የሶማሊያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በዓለ ሲመቱ ዛሬ በሞቃዲሾ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዓሉ ከአልሸባብ ጥቃት በጸዳ መልኩ እንዲከበር ሰፊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa

የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚነት ምዝገባ በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት መጀመሩ ተገለፀ
ኢትዮ ቴሌኮም በሂደት ላይ የሚገኘውን የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በቴክኖሎጂ በማገዝ ተግባራዊ ለማድረግ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየሠራን እንደሚገኝ አስታውቋል።
በዚህም መሠረት በድጎማው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለዩ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አገልግሎቱ የሚሰጠው በቴሌብር አማካኝነት መሆኑን ገልጿል።
ስለሆነም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በኢትዮ ቴሌኮም የሸያጭ ማዕከላት ዋና ወይም ቅጂ ሊብሬ እንዲሁም የታደሰ መታወቂያ በመያዝ የተሸከርካሪውን ባለቤት የስልክ ቁጥር በማሳወቅ የቴሌብር አገልግሎት ምዝገባ ከወዲሁ እንዲያከናውኑ፤ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያሟሉ ኢትዮ ቴሌኮም ጠይቋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አዲስ የስራ አመራር ቦርድ አባላትን መድበዋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የስራና ክህሎት ሚስንቴር ሚንስትር---ሰብሳቢ
2. ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር---አባል
3. ዶ/ር በለጠ ሞላ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር----አባል
4. አቶ ተስፋዬ ዳባ-----የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚንስትር ዴኤታ---አባል
5. ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር----አባል
6. ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር----አባል
እንዲሁም
7. ዶ/ር አንዱአለም አድማሴ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር---ጸሃፊና አባል ሆነዉ ተመድበዋል፡፡

የብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ የችሎት ውሎ፦
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል።
በዚህም ፤ የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራየን ጨርሸ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቢ ህግ ለመላክ በዝግጅት ላይ ነኝ ያለ ሲሆን፣ የክልል ዐቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ አዎ ምርመራው አልቋል የክስ መመስረቻ ጊዜ 15 ቀናት ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል።
የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው ምርመራ ካለቀ ደንበኛችን የተከሰሱበት ጉዳይ ዋስትና የሚያስከለክል ባለመሆኑ እና ተጠርጣሪው ደንበኛችን ታዋቂ ሠው በመሆናቸው ሊጠፉ ስለማይችሉ የደንበኛችን የዋስትና መብት ይከበርላቸው ሲሉ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም ሲሰጥ የነበረው የጊዜ ቀጠሮ ምርመራው ያለቀ በመሆኑ የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ ዘግቷል።
በመቀጠል የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ዐቃቤ ህግ አስተያየት እንዲሰጥበት አድርጓል።
ዐቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሰሱበት ጉዳይ የሽብር ወንጀል ስለሆነ በተጨማሪም ከሚዲያ ጋር በተያያዙ ሌሎች ተጨማሪ ክሶች ሊቀርቡ ስለሚችሉ ዋስትና ሊፈቀድላቸው አይገባም ሲል ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም የተጠርጣሪ የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ለሰኔ 3/2014 ዓ/ም ቀጠሮ መስጠቱን ከአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Via :- Ethio FM

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሊያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ጅቡቲ ሲደርሱ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በቆይታቸውም በኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሊያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ጅቡቲ ሲደርሱ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በቆይታቸውም በኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ ላይ ያላትን የ19 በመቶ ድርሻ ማጣቷ ተገለፀ
ኢትዮጵያ የሶማሌላንድ መንግስት በበርበራ ወደብ ላይ የባለቤትነት መብትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ባለመቻሏ በበርበራ ወደብ ላይ ያላትን የ19 በመቶ ድርሻዋን ማጣቷ ተገልጿል።
የሶማሌላንድ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ማሟላት የነበረበትን የባለቤትነት መስፈርቶች በጊዜው ባለሟሟላቱ ባለቤትነቱን ተነጥቋል።
ሚኒስትሩ እንዳመለከቱት ከቅድመ-ሁኔታዎች አንዱ ለወደቡ ግንባታ የገንዘብ መዋጮ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ይህን ማድረግ ሳትችል ቀርታለች መባሉን ካፒታል ዘግቧል።

በኢትዮጵያ አዲስ የግል አየርመንገድ ተቋቋመ
አርብ ሰኔ 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ኤር ኤክስፕረስ አፍሪካ የግል የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሆኖ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ተመዝግቧል፡፡
ተቋሙ ምዝገባውን በስኬት ያጠናቀቀው አለም አቀፍ አሰራርን ተከትሎ የተቀመጠውንና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንም የሚተገበሩትን አምስት ደረጃዎችን በስኬት አጠናቆ በመገኘቱ መሆኑም ለመረዳት ተችሏል፡፡
ኤር ኤክስፕረስ አፍሪካ በዛሬው ዕለት ሰኔ 3 ቀን 2014 በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የተፈረመበትን ሰርትፊኬት በይፋ ተቀብሏል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በተካሄደው የሰርቲፊኬት ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግስቴ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ተግዳሮቶች ያሉበት መሆኑን ተረድታችሁ፤ ተስፋ ሳትቆርጡ በትጋት በመስራት ለስኬት እንድትበቁ እመኛለሁ ሲሉ መልዕታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የኤር ኤክስፕረስ አፍሪካ መስራችና ባለቤት ካፒቴይን ነስሩ ከማል በበኩላቸው፤ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ኢንስፔክተሮች ሳይሰለቹ በመስራት ለዚህ ውጤት ስላበቁን አመሰግናለሁ ሲሉ ደስታቸውን መግለፃቸውን ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡
ካፒቴይን ነስሩ ከማል ለረዥም ዓመታት በአውሮፕላን አብራሪነት ሙያ ላይ ተሰማርተው ሲያገለግሉ የነበሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡
በአሁን ሰዓት ኤር ኤክስፕረስ አፍሪካን ጨምሮ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ተመዝግበው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት ተቋማት 12 መድረሳቸውን ከባለስልጣኑ የተኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
___
#አዲስ_ማለዳ

በመንግሥት በኩል ለሰላም የሚደረጉ ጥረቶች ቢጠናከሩም ህወሓት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ አለመሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተዉን ቀዉስ በሚመለከት ለሰላም የሚደረጉ ጥረቶች አሁንም እንደቀጠሉ ናቸዉ። በቅርቡ መንግስት ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት አመቺነት ያደረገዉን የተኩስ አቁም ዉሳኔ ለዚህ አንድ ማሳያ ነዉ ያሉት አምባሳደሩ መንግስት ዘላቂ የሰላም ሁኔታ ለመፍጠር ጥረት እያደረገ ቢሆንም ፤ ህወሓት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ አለመሆኑን ገልጸዋል።
አምባሳደሩ በመግለጫቸዉ ከህወሓት ጋር እየተደረገ ያለ ድርድር አለ ባይሉም በመንግስት በኩል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለአለማቀፍ ተቋማት እና መንግስታት ገለጻ እንደተደረገላቸዉና እዉቅና እየሰጡት መሆኑንም አንስተዋል። የሰብዓዊ አቅርቦቱም አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እና መድሀኒትን ጨምሮ አየደረሰ ነዉም ብለዋል።
ብስራት ራዲዮ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽንን ዋቢ አድርጎ ከ 1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ትግራይ መላኩንም መዘገቡ ይታወሳል ።
ሆኖም የህወሓት ታጣቂ ሀይሎች በቅርቡ በኤርትራ ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ጨምሮ ለሰላም የሚደረጉ ጥረቶች ላይ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ አይደለም ሲሉ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።
አያይዘዉም በየትኛዉም አካል ሰላም ለመፍጠር የሚመጡ ወገኖችንም ኢትዮጵያ እንደምትቀበል አስታዉቀዋል።
Via:- #ዳጉ_ጆርናል

ዘመን ባንክ አክሲዮን ማህበር የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከልን ለመገንባት ስምምነት ተፈራረመ!
ዘመን ባንክ አክሲዮን ማህበርና የከተማ አስተዳደሩ ለአቅመ ደካሞች መመገቢያ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከልን በጋራ ለመገንባት የስምምነት ፊርማቸዉን አኑረዋል፡፡የምገባ ማዕከሉ ግንባታ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባ ነው። የግንባታው ወጪ ሙሉ በሙሉ በዘመን ባንክ የሚሸፈን ነው ተብሏል።ከተማ አስተዳደሩ ለሚሰራቸዉ ስራዎች ባንኩ ከጎኑ እንደሚቆም የዘመን ባንክ አ.ማ ስራ አስፈፃሚና ፕሬዝዳንት አቶ ደረጀ ዘበነ ተናግረዋል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ፣ ከተማ አስተዳደሩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የከተማዉን ህዝብ በተለየ ሁኔታ ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።ስራዉን ለማሳካት የባለሃብቶችና ተቋማት እገዛ ከፍተኛ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡የዘመን ባንክ አ.ማ አመራርና ቦርድ ለዚህ በጎ ጥሪ በጎ ምላሽ በመስጠታቸ ምስጋና አቅርበዋል።
(ኢ ፕ ድ)
@YeneTube @FikerAssefa

"የሱዳን እና የኢትዮጵያ ግጭት የውጭ አካላት የፈጠሩት ነው " ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ!
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃለ አቀባይ አምባሳደር ዲና ዛሬ በፖለቲካ ዲፕሎማሲ ፣ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እንዲሁም በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ረገድ ማብራሪያን ሰጥተዋል።ማብራሪያውን የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃለ አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ካነሱዋቸው ነጥቦች መካከል የሱዳን ጉዳይን በሚመልከት ሱዳን ያለ አግባብ የተወሰኑ ቦታዎች ይዛ ለመውቀስ ሞክራለች ነገር ግን ኢትዮጵያ ብልጠት በተሞላበት መልኩ ምላሽ ስትሰጥ መቆየቱን አንስተዋል።
"ጉርብትናችን ላይ እንስራ እያልን በየጊዜው ጦርነት አንፈልግም ግጭት አንሻም እያልን ስንገልጽ ነበር አሁን ላይ ከሞላ ጎደል ለማስተካከል እና ጦርነት ላለመቀስቀስ ሰርተናል ውጤታማ ሆነን ግጭቶችን ቀንሰናል" ብለዋል።እንዲሁም ደግሞ ከአረብ ሃገራት ጋር ያለው ግንኙነት ሻክሯል ወይ በሚል ለቀረበው ጥያቄ ከአረብ ሃጋራት ጋር የጂኦግራፊ ቅርበታችን ይህንን እንድናደርግ አይፈቅድልንም ትክክልም አይደለም ሲሉ አምባሳደር ዲና ምላሽ ሰጥተዋል።የውጭ አካላትም የህዳሴ ግድብ ጉዳይንም በተመለከተ የተጠማዘዘ ትክክለኛ ያልሆነ ሃሳብ ለሃገራቱ ስለማይነግሩዋቸው ከኛ ጋር ሊያጋጩ ይሞክራሉ ይህንን እኛ አንቀበለውም ብለዋል።
በስተመጨረም ወደ ትግራይ የሚሄደው ድጋፍ እስከሚያስፈልገው ድረስ ይቀጥላል ያሉት አምባሳደሩ ድጋፉ አይቆምም የትግራይ ዜጎች የኛ ዜጎች ናቸው ለዚህ ህዝብ ከማንኛውም ሰብአዊ ተሟጋች በላይ የሚቀርበው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ነው ስለዚህ የሚያስፈልገውን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉም ጨምረው መናገራቸውን ተሰምቷል።
[Bisrat FM]

ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነ፡፡
የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 3 ቀን 2014 በዋለው ችሎት የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የቀድሞ አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ አዟል።
በትላንትናው ዕለት በዋለው ችሎት ላይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራ መጨረሱን ገልፆ መዝገቡን ለክልሉ አቃቤ ህግ ሊልክ መሆኑን አስታውቆ የነበረ ሲሆን፤ የክልሉ አቃቤ ህግም ምርመራው በማለቁ የክስ መመስረቻ የ15 ቀናት ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር።
የተከሳሽ ጠበቃም ምርመራው ካለቀ ዋስትና የሚያስከለክል ክስ ባለመኖሩ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱ ዋስትና የሚከለክል ሆኖ ስላላገኘው በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ አዟል ሲል የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታዉቋል።

ተከስክሶ መኖሪያ ቤት ላይ ያረፈው የቻይና ተዋጊ ጄት ሰው ገደለ
በአደጋው በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የነበሩ ሁለት ሰዎች መጎዳታቸውም ተነግሯል
በአደጋው በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የነበሩ ሁለት ሰዎች መጎዳታቸውም ተነግሯል፡፡
ተዋጊ ጄቱ ዛሬ ጠዋት በማዕከላዊ ቻይና ሁቤይ ግዛት ከሚገኝ አንድ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ መከስከሱን የዘገበው ሲሲቲቪ አብራሪው የከፋ ጉዳት ሳይደርስበት ከአደጋው ተርፏል ብሏል፡፡
ተዋጊ ጄቱ በሶቪዬት ህብረት ዘመን ከተመረቱ የሚግ-23 ተዋጊ አውሮፕላኖች መካከል መሆኑ ተነግሯል፡፡ ይህም ጄቱ የአገልግሎት ዘመኑ ማብቂያ ላይ ይገኝ እንደነበር የሚያሳይ ነው እንደ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ፡፡
በቻይና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ተደጋጋሚ የአውሮፕላን አደጋዎች እያጋጠሙ ነው፡፡ በቅርቡ አንድ የኢስተርን ላይንስ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከስክሶ ጭኗቸው የነበሩ 132 ሰዎች በሙሉ ሞተዋል፡፡
ከወር በፊት በደቡብ ምዕራባዊ ቻይና ቾንግኪንግ ከተማ የተነሳና 122 ሰዎችን የጫነ የቲቤት አየር መንገድ አውሮፕላን የእሳት አደጋ ደርሶበት እንደነበር ይታወሳል፤ ምንም እነኳን በአደጋው የደረሰ ሰብዓዊ ጉዳት ባይኖርም፡፡
ቻይና “ሉዓላዊነቴን እና ደህንነቴን አደጋ ላይ የሚጥል እቅስቃሴ እያደረገች ነው” በሚል ከሰሞኑ ወደ አየርና የውሃ ክልሏ የቀረቡ የአውስትራሊያ የጦር አውሮፕላኖችን በረራ ማቋረጧ ይታወሳል፡፡

👍1
ጄ/ል ተፈራ ማሞ ከእስር ተለቀቁ!
"ህገ መንገስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል" ተጠርጥረው በአማራ ክልል በእስር ላይ የነበሩት የቀድሞው የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከእስር መለቀቃቸውን ባለቤታቸው ለአል ዐይን አረጋግጠዋል፡፡
አል ዐይን ቀደም ሲል የአማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ30 ሺ ብር ዋስ እንዲለቀቁ መወሰኑን መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን የተምች ወረርሽኝ ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የፌደራል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን የተምች ወረርሽኝ ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የፌደራል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የሚኒስቴሩ አንድ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊ ዛሬ ለዶቼ ቬለ እንደገለጹት በስድስት ክልሎች የተከሰተውን ወረርሽኝ ለመከላከል የፀረ ተባይ ኬሚካልና የመርጫ መሣሪያዎች አቅርቦትን ጨምሮ በቅንጅት እየተሠራ ይገኛል፡፡ የመከላከል ሥራው ሰብል አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች በወረርሽኙ ምክንያት ሊያጋጥም የሚችለውን የምርት መቀነስ ለማስቀረት ያስችላል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ በአብዛኞቹ አካባቢዎች የተከሰተው የተምች ወረርሽኝ ወትሮም እንደነገሩ በሆነው የአገሪቱ የግብርና ምርት ላይ ስጋት መደቀኑ አልቀረም፡፡መነሻውን ደቡባዊውን የኢትዮጵያ ክፍል ያደረገው ወረርሽኝ በቡቃያ ላይ የሚገኙ ሰብሎችንና በግጦሽ ሳሮች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚል ሥጋት እንዳደረባቸው በተለይ በደቡብና በሲዳማ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች እየገለፁ ይገኛሉ፡፡
በፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር የእጽዋት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ንጉሴ አሁን ባለው ሁኔታ የተምች ወረርሽኙ በስድስት ክልሎች ውስጥ መታየቱን ነው ለዶቼ ቬሌ DW የገለፁት ፡፡ ወረርሽኙ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ሥር ለማዋል አስቀድሞ ዝግጅት መደረጉን የሚናገሩት አቶ በላይነህ ለዚህም ለክልሎች የፀረ ተባይ ኬሚካልና የመርጫ መሳሪያዎች ሥርጭት ተደርጓል ብለዋል፡፡
[DW]

ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለድርድር ፍላጎት እንዳላት ተገለፀ
⚡️የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ አምባሳደር ስለሺን ጠቅሰው እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሶስትዮሽ ድርድር እንደገና ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላት አጉልቶ ያሳያል ብለዋል።
⚡️ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ፣ በግብፅ እና በሱዳን መካከል የተካሄዱት በርካታ ድርድሮች ሳይሳኩ መቅረታቸው ይታወሳል። ይህም የግድቡ በፍጥነት መሞላት ከአባይ ወንዝ ልታገኝ የምትችለውን የውሃ ድርሻ ይቀንሳል ብላ የምታምነው ግብፅ ወደፊት ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶችን ለመቅረፍ አስገዳጅ ስምምነት ቀድሞ እንዲፈፀም በመፈለጓ ነው።
⚡️አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ሦስተኛው የግድቡ ሙሌት ዘንድሮ በተያዘለት መርሃ ግብር እንደሚከናወን በመግለፅ "የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የሶስትዮሽ ውይይት እንደሚቀጥል ስንናገር ቆይተናል" በማለት አክለዋል።

እውቁ ካናዳዊ አቀንቃኝ ግማሽ ፊቱ ፖራላይዝ አንደሆነ ተናገረ
እውቁ የዘፈን ደራሲና አቀንቃኝ ጀስቲን ቢበር ከፊል ፊቱ ፓራላይዝድ እንደሆነ ተናግሯል።
ጀስቲን 240 ሚሊዮን ተከታዮች ባሉት ኢንስታግራሙ ላይ በለቀቀው ቪድዮ “እንደምታዩት ይህኛው ዓይኔ አልገለጥ ብሏል፤ በዚህኛው የፊቴ ክፍል ፈገግ ማለት አልችልም፤ ያኛው የፊቴ ክፍል ደግሞ ሙሉ በሙሉ ፓራላይዝድ ሆኗል” ሲል ተደምጧል።
በዚህም ‘ጀስቲስ ወርልድ ቱር’ በሚል በተለያዩ ሀገራት ኮንሰርት ሲያርባቸው ከነበሩ ኮንሰርቶች ስስቱን ሰርዞ ለሌላ ጊዜ ማሸጋገሩን ዘ-ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
ይሁን እንጂ ለማገገም የተቻለውን የአካል እንቅስቃሴ እንደረገ መሆኑ ጀስቲን ቢበር ለአድናቂዎቹ መልእክት አስተላልፏል፡፡
Via :- alian

በቀን 6 መቶ ቶን ፌሮ ማምረት የሚችል የብረታ ብረት ፋብሪካ በዱከም ተመረቀ
በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
በዱከም ከተማ አቅራቢያ በ50 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈው ''ታዳሽ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ'' 5 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ካፒታል እንደወጣበት ተገልጿል።
ፋብሪካው በቀን 450 ቶን ብረት የማቅለጥ አቅም እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፣ ለ7 መቶ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ይፈጥራል።
ሀገሪቱ ለብረት ምርት የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት ፋብሪካው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።
የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ዘመናዊ መሳሪያዎች እንደተገጠሙለት ተገልጿል።
(አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ.ም)

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያስገነባው የረገ ኤያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ያስገነባው የረገ ኤያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ሽማግሌዎች እና የሐይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
ትምህርት ቤቱ በውስጡ 10 መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ -ሙከራ፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ የተማሪ ክሊኒክ ፣የአስተዳደር ሕንጻና የስብሰባ አዳራሽ ያካተተ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከዚህ ቀደም በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ማመዴ ቀበሌ ሁለተኛውን ትምህርት ቤት አስገንብቶ ማስመረቁ የሚታወስ ነው።

አዲስ አበባ ግዙፍ መንትያ ህንፃዎች ልትገነባ ነው።
በQuara manufacturing plc እና በቻይናው ኮንትራክተር CCECC መሀል ባለ ግርማ ሞገስ ህንፃ በካዛንቺስ አከባቢ 13 ቢሊየን ብር በጀት ለመገንባት ውል ተፈርሟል ሲል ሪፖርተር ዘግቧል።
በ5,743 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚንሰራፋው መንታ ህንፃ ባለ 44 ፎቅ እና 30 ፎቅ ህንፃዎች ይኖሩታል። 219 ሜትር ከፍታ ያለው ይህ 44+4 ፎቅ ህንጻ ለንግድ ስራ የሚውል ሲሆን ቁመቱ 209 ሜትር ከሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት የሚበልጥ ይሆናል።
ባለ 30 ፎቅ ህንጻ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ሲሆን፥ ባለ ሶስት እና አራት መኝታ ቤቶች ያሉት ይሆናል። ከቻይናው ኩባንያ ጋር የተፈራረመው ውል አካል ባይሆንም የመንታ ግንብ ፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲጠናቀቅ ሌላ ሕንጻ ለፓርኪንግ ቦታ ይገነባል።
የውብሸት ዝካለ (ፒኤችዲ) ባለቤትነት እና አስተዳደር የሆነው የየክስቃ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት የፕሮጀክቱ ዋና አማካሪ ሆኖ ውል ገብቷል።
በመዲናዋ ልዩ ዲዛይን ያለውና በመንታ ማማ መካከል አረንጓዴ ቦታ ያሉት በመዲናዋ ውስጥ ካሉት ረጅሙ ሕንፃ ይሆናል ተብሏል። የህንፃው ግንባታ ስድስት ዓመታት ይፈጃል ተብሎ ይጠበቃል።
Via:- ሪፖርተር