YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢድ አልፈጥር በዓል ላይ አስለቃሽ ጭስ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተጠረጠረው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በዕለቱ በደረሰብኝ ድብደባ ግራ አይኔ እና ኩላሊቴ ላይ ጉዳት ደርሷብኛል ሲል ለፍርድ ቤት አስታወቀ!

የኢዳልፈጥር በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ አካባቢ አስለቃጭ ጭስ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተጠረጠረው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በዕለቱ በደረሰብኝ ድብደባ ግራ አይኔ እና ኩላሊቴ ላይ ጉዳት ደርሷብኛል ሲል ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አድማ ብተና ዘርፍ ባልደረባ የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ባሳለፍነው ሚያዚያ 24 ቀን በተከበረው የኢዳል ፈጥር ባአል በአ/አ ከተማ በመስቀል ሰማታት መታሰቢያ ሙዚዬም አካባቢ በተመደበበት የወንጀል መከላከል ስራ ላይ ኦያለ ከፈነዳው አስለቃሽ ጭስ ቦንብ ጋር ተያይዞ ተጠርጥሮ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ካለጠበቃ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

ተጠርጣሪው ኢድ አልፈጥር በዓል በተመደበበት ሥራ ላይ በአጋጣሚ ሳላውቅ የፈነዳብኝ አስለቃጭ ጭስ ቦንብ ሲፈነዳብኝ ጭሱ ወደ ህዝቡ እንዳሄድ ወዲያው ሸገር ባስ ውስጥ ወርውሬ ከትቻለሁ፤ በአካባቢው የነበሩት ሰዎች ግን የፌደራል ፖሊስ ልብስ ለብሼ ሳለሁ አንገቴን አንቀው ባደረሱብኝ ድብደባ የግራ አይኔና ኩላሊቴ ላይ ጉዳት አድርሰውብኛል ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

ተጠርጣሪውን ያቀረቡት ሁለት መርማሪ ፖሊሶች ባሳለፍነው ሚያዚያ 26 ቀን ጀምሮ ለተጨማሪ ምርመራ በተሰጣቸው የ10 ቀን ጊዜ ውስጥ የሰሩትን የምርመራ ውጤት ለችሎቱ አቅርበዋል።በዚህም የሦስት ሰዎች ምስክርነት ቃል መቀበላቸውንና የሥራ ሀላፊዎችን ቃል መውሰዳቸውን፣ የተጠርጣሪው የግል ስልክ ምርመራ እንዲደረግ ለብሔራዊ መረጃ ደህንነትና ለኢትዮ ቴሌኮም ደብዳቤ መጻፋቸውን አብራርተዋል።

የፋይናንስ ድጋፍ እንዳለውና እና እንደሌለው ለማጣራት ለባንኮች ደብዳቤ መጻፋቸውን ተናግረዋል።ግብረአበሮችን ተከታትሎ የመያዝ ሥራ ለመስራትና ምርመራ አጠናቀው ለሚመለከተው ዓቃቢህግ ለመስጠት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።በፍርድ ቤቱ በኩል ግብረአበር ለመያዝ ማለት ምን ለማለት እንደሆነ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

ከፍንዳታው በፊት ከአንዲት ሴት በአካል ማዋራቱን እና በወቅቱ ስልክ ተደውሎለት ሲያወራ እንደነበር ጠቁመው ይህን ተከትሎ ግብረአበር ካለ የመያዝ ሥራ እንደሚሰራ አብራርተዋል።ተጠርጣሪው በበኩሉ “የፈነዳው ቦንብ አውቄ አደለም ባጋጣሚ እንጂ ምንም አይነት ወንጀል እኔ አልሰራሁም በኔ የደረሰ ችግር የለም”ሲል ምላሽ ሰጥቷል።ከደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ለሥራ መምጣቱን ገልጾ፤ ጠያቂ ዘመድ እንደሌለው ወላጆቹን በሞት በማጣቱ ትንሽ ወንደሰሙን በሱ እርዳታ እንደሚያስተምር በመግለጽ ዋስትና እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

መርማሪዎቹ በበኩላቸው በዕለቱ አንድ የጭስ ቦንብ ሳይሆን 3 የጭስ ቦንብ ነው የፈነዳው ያሉ ሲሆን፤ ተጠርጣሪው ከተመደበበት የሥራ ምድብ ውጪ በህዝብ መሀል ሆኖ ነበር ያሉ ብለዋል። ሲጀመር አስለቃሽ ጭስ ቦንብ ይዞ ህዝብ መሀል መቆም አይፈቀድም ይሁንና እንዲወጣ ታዞ ሳይወጣ ቀርቷል ኹከትና ብጥብጡም በዚህ መነሻ ነው የተነሳው ሲሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህ መነሻ በመንግስትና በግል ድርጅቶች ላይ የደረሰው የንብረት ጉዳት ፍርድ ቤቱ እንዲረዳላቸውና ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀን እንዲፈቅድላቸው ጠይቀዋል።ጉዳዩን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሪ ምርመራ ማድረግ እንደማያስፈልግ በመግለጽ ለተጨማሪ ምርመራ 13 ቀናትን በመፍቀድ የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለግንቦት23 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠጹን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት ጉዳይ የኡጋንዳን አምባሳደር ጠርቶ ማወያየቱን ገለጸ!

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኡጋንዳ በህወሃት ላይ ያላትን አቋም ለማወቅ የኡጋንዳን አምባሳደር ጠርተው ማነጋገራቸውን ገልጸል፡፡ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በትናንትናው እለት ኡጋንዳ ለህወሓት ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን እና ይህን የኢትዮጵያ መንግስት እንዴት እያየው ነው በሚል ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ነው፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኡጋንዳ ካምፓላ ያሉት የኢትዮጵያ አምባሳደርም ይፋዊ መልእክት ለኡጋንዳ መንግስት ማቅረባቸውን እና ማብራሪያ መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡በቅርቡ በኢትዮጵያ በተካሄደው የወታደራዊ ኦፊሰሮች ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ከኡጋንዳ መከላከያ ሚኒስቴር ጋር መወያየቷን የገለጹት ሚኒስትሩ ጉዳዮ “በቀላሉ የሚያይ እና የሚተው አይደለም” ብለዋል፡፡

ጉዳዩ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዝርዝር መገምገሙን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
“እንዳንዴ የሚሉት ምንድነው፣ ይሄ በራሳቸው የሚኖሩና እና ራሳቸው የሚጠየቁበት ነው፤ እኛ ይሄን አንደግፍም ይላሉ፡፡”ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት አንድ የኡጋንዳ ከፍተኛ ባለስልጣን በአንድ ሀገር ጉዳይ ላይ አቋም ከወሰደ፣ የመንግስት አቋም አድርገን ነው የምንወስደው ብለዋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፡፡ሚኒስትሩ ኡጋንዳ ግልጽ አቋሟን እንድታሳውቀን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ሱዳንንም ህወሓትን ትደግፋለች በሚል ከሷል፡፡

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክትል ዋና ጸሐፊ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው!

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክትል ዋና ጸሐፊ ኢሊዝ ብራንድስ ኬሪስ ኢትዮጵያን እና ደቡብ ሱዳንን ሊጎበኙ ነው፡፡

ምክትል ዋና ጸሐፊዋ ጉብኝታቸውን ዛሬ በደቡብ ሱዳን የጀምሩ ሲሆን ከቀጣዩ አርብ ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

ኬሪስ በደቡብ ሱዳን ቆይታቸው ከአገሪቱ የፌደራል እና የየአካባቢው ባለስልጣናት፣ ከኅብረተሰብ ተወካዮች፣ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና በአገሪቱ ከሚገኙ ዓለም ዐቀፍ እና ቀጣናዊ አጋር አካላት ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በጁባ እና ዬኢ ከተሞች የሚገኙ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ካምፕ እንደሚጎበኙ ተገልጿል፡፡

የደቡብ ሱዳን ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት የአፍሪካ ኅብረት፣ የአውሮፓ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት በትብብር የሚያከናውኑት የአፍሪካ ኅብረትን አሰራር ማሻሻያ ፕሮጀክት ይፋ በሚደረግበት መርኃ ግብር ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

ይህ ትብብር የአፍሪካ ኅብረት በሰላም ዙሪያ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለመደገፍ እና አሰራሩም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ደንብን የተከተለ እንዲሆን የሚያስችል መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የፑሽኪን አደባባይ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ይሆናል ተባለ!

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በስራ ተቋራጭ እያስገነባው የሚገኘው የፑሽኪን አደባባይ - ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ግንባታ ስራ በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ያደርጋል፡፡

ከፑሽኪን አደባባይ እስከ ጎተራ ማሳለጫ ያለው ዋና መንገድ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ተደርጓል።

አሁን ላይ በተለምዶ ጎፋ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው የቄራ አካባቢ ከቂርቆስ አቅጣጫ ወደ ጎፋና ላፍቶ የሚወስደው ተሻጋሪ ድልድይ የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

መንገዱን በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ሙሉ ለሙሉ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
1ሺህ 22 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!

ዛሬ ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺህ 22 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የተቻለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 108 ሴቶች 9 ህጻናትና 905 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡ እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 24,660 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
ለመሆኑ ቅጥረኛ ወታደሮች በወር ምን ያህል ይከፈላቸዋል???
============
ከሰሞኑ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በዩክሬይኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ለመዋጋት ተሰልፈው ታይቷል። ወዶ መዝመት ከጥንት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ የወጣቱን ልብ ያሸፈተው የርዕዮተ ዓለም ፍቅር አይደለም። አማላይ ክፍያው እንጂ። ለመሆኑ ቅጥረኛ ወታደሮች ምን ያህል ይከፈላቸዋል??? የሚሰጣቸው ስልጠና እና ዋነኛ ስራቸው ምንድነው? ይህን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ። ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ!!!

https://youtu.be/Q0Uj40oaOho
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ የክልሉ ጸጥታ ኃይሎች በሰሜኑ ክፍል የሕወሃት ተላላኪ አካላትን እየተፋለሙ መሆኑን ዛሬ ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ይልቃል ክልሉን ለማዳከም የሚንቀሳቀሱ የውስጥ "ጠላቶች" እንዳሉ በጥናት ደርሰንበታል ብለዋል። "የሕወሃት ተላላኪ" ያሏቸውን አካላት ማንነት ግን ይልቃል አላብራሩም። መንግሥታቸው በሕግ ማስከበር እንቅስቃሴው እንደሚገፋበት የገለጹት ይልቃል፣ ጦር መሳሪያ ከመመዝገብ ውጭ ትጥቅ የማስፈታት እና የፋኖ አደረጃጀትን የመበተን ዓላማ እንደሌለው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሰኞ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በድንገት የተሰወሩት የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ እስካሁን የት እንደደረሱ የተገኘ መረጃ የለም።

ባለቤታቸው ዛሬ ለሪፖርተር በሰጡት ቃል፣ ብ/ጀኔራል ተፈራ ከቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂ ጥናት ኢንስቲትዩት ሃላፊ ዮሃንስ ቧያሌው ጋር በአካል ለመገናኘት ከወጡ በኋላ እንዳልተመለሱ ተናግረዋል። ባለቤታቸው ጨምረውም፣ ብ/ጀኔራል ተፈራ አዲሶቹ የአማራ ክልል አመራሮች ብቃት የላቸውም በማለት በቅርቡ ለኢሳት እና ናሁ ቴሌቪዥኖች የሰጡት ቃለ ምልልስ በክልሉ አመራሮች ዘንድ እንዳልተወደደ ጠቁመዋል። ፌደራል ፖሊስ ስለ ግለሰቡ አድራሻ መረጃ እንደሌለው ገልጦ ሁኔታውን አጣራለሁ ብሏል።

[Reporter/Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
#update

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባሕር ዳር እንደሚገኙ እንደተነገራቸው ባለቤታቸው ገለጹ!

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከሁለት ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ባለቤታቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው ረፋድ ላይ ከወጡ በኋላ የደረሱበት ሳይታወቅ እስከ ረቡዕ አመሻሽ ድረስ ቆይተዋል።

ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ረቡዕ ምሽት ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የጄነራል ተፈራ ጠበቃና የሚያውቋቸው ሰዎች ባለቤታቸው ባሕር ዳር ውስጥ በሚገኘው ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሉ ገልጸዋል።

ወ/ሮ መነን ባለቤታቸው በላኩት መልዕክት ደህና መሆናቸውን እና አሁን ያሉበት ቦታ በመግለጽ ቤተሰባቸው እንዲረጋጋ መልዕክት ልከዋል ብለዋል።ቢቢሲ ይህንኑ በተመለከተ ከአማራ ክልል የፀጥታና ደኅንነት እንዲሁም ፖሊስ ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በነኮሎኔል ገመቹ አያና እስር ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር ኮሎኔል ገመቹ አያና እስር እና ሰብኣዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ላይ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊዎች ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት ከሌሎች በመዝገቡ ከተጠቀሱት ተከሳሾች ጋር በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተብለው የነበሩት ኮሎኔል ገመቹ አያና ለአንድ ዓመት ያህል “በህገወጥ እስር” ላይ እንደነበሩ ጠበቆቻቸው ይገልጻሉ፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ያስቻለው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ተከሳሹ ኮሎኔሉ እና ከሳሽ አቃቤ ህግ በቀረቡበት ቀሪ ተከሳሾች እና የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲቀርቡ በማለት መዝገቡን በይደር ይዟል፡፡

ሙሉ ዘገባው: https://p.dw.com/p/4BTgX?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

@YeneTube @FikerAssefa
👉 ለጤናው ቅድሚያ እንሰጣለን


መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን
በተሰጠንና ባገኘነው ልምድና ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሔወችን እንሰጣለን።፦

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉 የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው
ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላሳይነካ
ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛ እንዳይተካ አድርጎ የፈውሳል።
👉 የእሪህ መድአኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉 ገብያ ለገረገረው ለገብያ
👉 ለመፍትሔ ስራይ
👉 ለአይነ ጥላ (ለገርጋሪ)
👉 ለስንፈተ ወሲቢ ለሚቸኩልበት
👉 የአስም (የሳይነስ)
👉 ለማይስማሙ (ለመስተፋቅር)
👉 ገንዘብ ለሚበተንበት
👉 ስራ አልሳካለት ላለ
👉 ለቡዳ
👉 ለሚጥል በሽታ
👉 ለማህጸን እንፌክሽን
👉 ህይወቱ ለሚመሰቃቀልበት
👉 ለአዕምሮ ጭንቀት
👉 ሌሊት ለሚሸና
👉 ለነገረ በትን
👉 ለሆድ ሀህመም
👉 ለስኳር መቀነሻ
👉 ለነርብ
👉 እራሱን ለሚያመው

እነዚህንና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን

መዳኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈጽማሉ

አድራሻ
ባህርዳር ቀበሌ 11
ዲያስፖራ በኮብሉ

ለበለጠ መረጃ
☎️ 0917040506
📞 0912718883

ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
የሚፈልጉትን ለማግኔት ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ
🩺
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe👇
👇
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
ግንባታቸው የተጠናቀቁ 528 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለሰራዊት አባላት የማስተላለፍ መርሃግብር እየተካሄደ ነው!

ግንባታቸው የተጠናቀቁ 528 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ተመዝግበው ለቆጠቡ ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን አባላትና ለተቋሙ የሲቪል ሰራተኞች በእጣ የማስተላለፍ መርሃግብር እየተካሄደ ነው።

ዕጣው በግዳጅ ላይ ያሉ የሰራዊት አባላት፣ በክብር የተሰናበቱ የሰራዊት አባላትን ያካተተ ነው። ሴት የሰራዊት አባላትን በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተፕራይዝ እየተገነቡ ካሉት የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል በአዲስ አበባ በሰሚት ቁጥር ሁለት ግንባታቸው የተጠናቀቁ 528 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ተመዝግበው ለቆጠቡ የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን አባላትና የተቋሙ ቋሚ የሲቪል ሰራተኞች በእጣ የማስተላለፍ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየገነባ ሲሆን በቅርቡም ግንባታቸው የተጠናቀቁ ቤቶችን ለሰራዊቱና ለቋሚ ሰራተኞች ያስተልፋል ተብሏል።

የተገነቡ ቤቶች በእጣ ለባለእድለኞች በሚተላለፍበት መርሃግብር ላይ የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብራሃም በላይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕይዝ በኢትዮጵያ ካሉ ታላላቅ የግንባታ ኩባንያዎች አንዱ ሲሆን የኢንፎርሜሽን ደህንነት ዋና መስሪያ ቤት፣ የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻን ጨምሮ በርካታ አገራዊ ፕሮጀክቶችን ገንብቷል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አስር ወራት 360 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 282 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተነገረ፡፡

ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥም 168 ነጥብ 7 ቢሊየን ብሩ ከአገር ውስጥ ገቢ ታክስ የተገኘ ሲሆን፥ 113 ነጥብ 8 ቢሊየን ብሩ ደግሞ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ የተገኘ ገቢ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ጠቁመዋል፡፡

በዚህም የእቅዱን 93 ነጥብ 1 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው አቶ ላቀ በሪፖርታቸው ያመላከቱት፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት እያካሄደ በሚገኘው 8ኛ መደበኛ ጉባዔ የገቢዎች ሚኒስቴርን እና የተጠሪ ተቋማቱን የ2014 በጀት ዓመት የ10 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እያዳመጠ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢሰመኮ ከሕግ አግባብ ውጪ በእስር ላይ የሚገኙ የኦነግ አባላት በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቁ ጠየቀ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ለተራዘመ ጊዜ ከሕግ አግባብ ውጭ ታስረው የሚገኙ በመሆኑ በአፋጣኝ ከእስር ሊለቀቁ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ፡፡የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) አመራሮቹ ከእስር ከመለቀቅም ባለፈ ለደረሰባችው ጉዳት ሊካሱ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የፍርድ ቤትና የዐቃቤ ሕግ ውሳኔዎች በተደጋጋሚ እየተጣሰ፣ እስረኞቹ ከሕግ ውጪ ለተራዘመ እስር መዳረጋቸው ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም መሆኑንም ነው ኮሚሽሩ የገለጹት፡፡የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አፋጣኝ ማጣራት አካሂዶ ተገቢውን እርምጃ ሊወሰድበት እንደሚገባም ኮሚሽነሩ ማሳሰባቸውን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ኢሰመኮ በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች በእስር ላይ ያሉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባሎች የእስር ሁኔታን በተመለከተ ክትትል ማድረጉን ገልጿል፡፡

ኢሰመኮ፤ ከመጋቢት 1 እስከ 10 ቀን 2014 ዓ.ም በቡራዩ ፣ በገላንና በሰበታ ፖሊስ መምሪያዎች በመሄድ እስረኞችን፣ የፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎችን፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተወካዮችን በማነጋገር ምርመራ መደረጉንም አስታውቋል።

ሙሉ ዜናውን ለማንበብ: https://am.al-ain.com/article/ehrc-urges-government-to-release-members-of-olf

@YeneTube @FikerAssefa
ኦዴሳ


ፑቲን ኦዴሳ ከተማን ሳይቆጣጠር የዩክሬይን ዘመቻው ስኬታማ ሊሆንለት አይችልም። ኦዴሳን ከተቆጣጠረ ግን በአውሮፓ ትልልቅ ጂኦፖለቲካዊ ለውጦች ይጠበቃሉ። ለምን? ኦዴሳ ይህን ያህል ጥቅሟ ምንድነው?? ይህን አጭር ቪዲዮ ተከታተሉ

https://youtu.be/sW0rM_nr8Uo
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር አደረገ።

የከተማ አስተዳደሩ ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ በመተባበር ከተማውን ለማልማት በሚያስችለው መንገድ ዙርያ በዛሬው እለት ውይይት አካሂዷል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ት ያስሚን ዉሀቢረቢ የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጃቸውን አማራጭ የቤት ልማት ሞዳሊቶችን ለውይይት መነሻ ይሆን ዘንድ ለሪል እስቴት አልሚ ድርጅቶች ተወክለው ለመጡ ተሰብሳቢዎች አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

ከንቲባ አዳነች በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር በመተባበር ፣የሚችሉ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግና ሌሎችም በአቅማቸው ልክ ቤቶቹ ተገንብተው በተመጣጣኝ ዋጋ ተከራይተው የሚኖሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከተማ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር የላቀ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀዋል፡፡

ባለሀብቶች የልማት አጋር እንደመሆናችሁ መጠን የተዘጋጁ ሞዳሊቲዎችን በዝርዝር በመመልከት ለተግባራዊነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅንጅት ለመስራት እንቅስቃሴ ልታደርጉ ይገባል ብለዋል
አያይዘውም የከተማ አስተዳደሩ ፤የነዋሪዎችን የቤት ፍላጎት በሂደት ለመቅረፍ አምስት የቤት ግንባታ ሞዳሊቲዎችን በዝርዝር አዘጋጅቶ ለተግባራዊነቱ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ አጋርነታችሁን እየተጠባበቀ የሚገኝ በመሆኑ እናንተም በነፍስ ወከፍ በአጭር ግዜ ግንባታ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማምጣት የየድርሻችሁን አሻራ ለማኖርና የታሪክ ተከፋይ ለመሆን ልትሰወስኑ ይገባል ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የውጭ አገር አልሚዎችን የአዋጭነት ደረጃን በመፈተሽ እንዲሳተፉ ለማድረግ ይሰራልም ብለዋል ከንቲባዋ

የቤት አቅርቦትን በሚፈለገው መልኩ ተደራሽ ለማድረግ በዓመት 200,000 ሺና ከዚያ በላይ ቤቶችን መገንባት ያስፈልጋል ያሉት በምክትል ከንቲባ መዓረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ት ያስሚን አሁን ያለው ወቅታዊ ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ አልሚዎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ የተዘረጉ ሞዳሊትዎችን መሠረት በማድረግ ልትሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የግሉ ዘርፉ በተለይ የቤት ልማትን በሚመለከት የፌደራል መንግስትና ከተማ አስተዳደሩ የጀመሩትን በርካታ የማክሮ ኢኮኖሚ የለውጥ ስራዎች መሠረት በማድረግ በሽርክናና በሌሎችም ተስማሚ አማራጮች ዘርፉን የማነቃቃት ሥራ መስራት ከአልሚዎች ይጠበቃል ሲሉ አስታውቀዋል ኃላፊዋ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ በቅርበት የሚሰራ ግብርሃይል በውይይቱ መጨረሻ ተቋቁሟል
በውይይቱ ማጠቃለያ ተሳታፊዎቹ የማዘጋጃ ቤትን እድሳት ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡

Via:- አ/አ ኮምኒኬሽን
@Yenetube @Fikerassefa
ዚምቧብዌ የቀድሞው ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሀይለማሪያምን ደብቅሻል መባሌ አግባብ አይደለም አለች፡፡

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ፍሬድሪክ ሻቫ ” በዘር ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱት፣ ጥፋተኛ ተብለው በ2000 በሌሉቡት የሞት ብይን የተሰጠባቸው የቀድሞ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሀይለማሪያምን እንዱደበቁ አድርገዋል የሚሉት ሪፖረቶች ትክክል አይደለም” ሲሉ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራችው የተናጠል ቆይታ ተናግረዋል፡፡

ይህ የዚምቧብዌ ወቅታዊ አቋም ”ትልቅ ፖሊሲ ሽፍት ነው” ሲል የገለፀው ዘገባው የቀድሞው የሀገሪቱን አቋም የማስታወቂያ ሚኒስትሩን ንግግር ጠቅሶ ፅፏል፡፡

የቀድሞው የማስታወቂያ ሚኒስትር ቲቾና ጃኮንያ ለአውሮፓዊያኑ 2009 ለአሜሪካ ድምፅ እንደነገሩት ”መንግስቱ ሀይለማሪያምን አሳልፈን አንሰጥም” ብለው ነበር፡፡

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም ከ17 ዓመት የመሪነት ዘመን በኋላ ከኢትዮጵያ የወጡት ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም ነበር፡፡

ከሀገራቸው ከወጡ 31ኛ ዓመታቸውን የፊታችን ቅዳሜ ይደፍናሉ፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ከዓለም በርካታ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ያሉባት አገር ሆነች!

ኢንተርናል ዲስፕለስመንት ሞኒተሪንግ ሴንተር የተባለው ተቋም የአውሮፓውያኑ 2021 ማብቂያ ላይ በመላው ዓለም የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር 59.1 ሚሊዮን መድረሱን ገልጿል።እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ አፍጋኒስታን፣ ሶሪያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ያሉ አገራት ደግሞ በርካታ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸው አገራት ናቸው።በዓለም ላይ በርካታ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙት ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ብቻ የተመዘገበው 5 ሚሊዮን የተፈናቃይ ሕዝብ ቁጥር በአንድ አገር የተመዘገበ ትልቁ አሃዝ ሆኗል ብሏል ድርጅቱ።

በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ አጎራባች ወደሆኑት አማራ እና አፋር ክልሎች ተሸጋግሮ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉ ይታወቃል።ይህንን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተናቀሉ ሰዎች ቁጥር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ገልጾ ነበር።ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት ከግጭት ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 11.6 ሚሊዮን ሕዝብ ሲሆን ከተፈጥሮ አደጋ ጋር በተያያዘ ደግሞ 2.6 ሚሊዮን ሕዝብ ቀየውን ጥሎ ለመሰደድ ተገዷል።

ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣አፍጋኒስታን እና ሚያንማር እአአ 2021 ላይ ከፍተኛ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በመመዝገባቸውን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ቁጥርን የሚከታተለው ማዕከል ገልጿል።ምንም እንኳ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሰሜን አፍሪካ በሚገኙ አገራት የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር በ10 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢቀንስም፤ አሁንም በቀጠናው ተፈናቅለው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ ነው ተብሏል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa