YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
የብሄራዊ ደኅንነትና መረጃ አገልግሎት ሠራተኞች የማናቸውም ፖለቲካ ፓርቲ አባላት እንዳይሆኑ የሚያዝ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን ዋዜማ ዘግባለች።

የሚንስትሮች ምክር ቤት መጋቢት ላይ የመራው ረቂቅ አዋጅ፣ የብሄራዊ ደኅንነትና መረጃ ተቋምን እንደገና ለማዋቀር የቀረበ ነው። ረቂቅ አዋጁ የተቋሙ ሠራተኞች በማንኛውም የፖለቲካ ቅስቀሳ እና ገቢ በሚያስገኝ ሌላ ተጨማሪ የሥራ መስክ እንዳይሰማሩ ጭምር ይከለክላል። የተቋሙ ሠራተኞች ከሥራው ባህሪ ጋር የሚመጣጠን በቂ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም እንዲከፈላቸው ለመንግሥት ጥያቄ እንደሚቀርብ የሚገልጠው ረቂቁ፣ የሠራተኛ ምልመላ፣ ቅጥር፣ ሙያዊ ስነ ምግባርና የስንብት ደንቦችን ጭምር አካቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከ300 በላይ ሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች በዚህ ሳምንት ወደ ትግራይ መግባታቸውን ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ተናገሩ።

ተሽከርካሪዎቹ የንጽህና መጠበቂያን ጨምሮ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ጭምር ወደ ትግራይ ማድረሳቸውን ፕሮፌሰር ክንደያ በመቐለ ለሚገኘው የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ተናግረዋል።ለህወሓት ታማኝ የሆኑ የትግራይ ኃይሎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና አጋሮቹ ጋር የሚያደርጉት ውጊያ "ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ" ተላልፎ ጋብ ያለው ባለፈው መጋቢት አጋማሽ ገደማ ነበር። ውጊያው እንደገና ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ሥጋት በሚሰማበት በዚህ ወቅት ወደ ትግራይ የሚደርሰው የሰብዓዊ ዕርዳታ ጭማሪ ማሳየቱን የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ተናግረዋል።

"ተኩስ ማቆም እንደ ስምምነት ካደረግን ጀምሮ የተወሰኑ ነገሮች መግባት ጀምረዋል። በዚህ ሳምንት ደግሞ ትንሽ ጨመር የማድረግ [አዝማሚያ̄] አለ። ከታኅሳስ ጀምሮ እስከ መጋቢት ምንም መኪና አልገባም ነበር። አሁን ደግሞ በዚህ ሳምንት ወደ 300 ከዚያ በላይም መኪኖች መጥተዋል። የምግብ ብቻ አይደለም። የንጽህና አገልግሎቶች ሌሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ የምንላቸው የገቡበት ሁኔታ አለ። ዋናው መልዕክት የትግራይ ሕዝብ ተዘግቶ እጁን እንዲሰጥ፤ በተለያዩ ጥረቶች ተከቦ እጁን እንዲሰጥ የተደረገበት አጋጣሚ ነው አሁን ያለንበት።ግን ደግሞ አሁን ያየንው በዚህ ሳምንት ትንሽ የመጨመር ሁኔታ የሚያሳየው ይቻል ነበር ነው" ሲሉ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እና ወደ አፋር ክልሎች በማምራት ላይ እንደሚገኙ ባለፈው እሁድ ገልጾ ነበር።ድርጅቱ በተረጋገጠ የትዊተር ገጹ ባሰፈረው አጭር ጽሁፍ 85 ከባድ ተሽከርካሪዎች ባለፈው ግንቦት 6 ቀን 2014 መቐለ ከተማ መድረሳቸውን አስታውቋል። በሌሎች 130 ተሽከርካሪዎች ደግሞ በጉዞ ላይ ነበሩ።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ በኢትዮጵያ ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ የተሰኘ አዲስ የልማት ፋይናንስ ተቋም እንደተቋቋመ ካፒታል ዘግቧል።

አዲሱ ተቋም ለመንግሥት እና ለግሉ ፋይናንስ ዘርፍ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፎችን የሚሰጥ ነው።ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያን በገንዘብ የሚደግፉት የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን እና የእንግሊዙ የውጭ የጋራ ብልጽግና አገሮች የልማት ቢሮ እንደሆኑ ተገልጧል።ትናንት ገንዘብ ሚንስቴር እና ተቀማጭነቱ ኬንያ የሆነው ኤፍኤስዲ አፍሪካ በትብብር የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ አክሲዮን ገበያ ለማቋቋም ስምምነት ላይ እንደደረሱ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
ፈንጂ 5 ሰዎችን ገደለ!

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ባቲ ከተማ ፈንጂ 5 ሰዎች መሞታቸውን የባቲ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሰኢድ ለዶይቼ ቬሌ ዛሬ እንደነገሩት በቅርቡ ከህወሓት ጋር በነበረ ጦርነት ቡድኑ ጥሎት የሄደን ፈንጂ ትናንት አግኝተው ሲነካኩ በመፈንዳቱ በአካባቢው የነበሩ ሠዎችን ጨምሮ 5 ሠዎች ህይወታቸው አልፏል።እንደ አቶ መሐመድ ሌሎች 5 ሠዎች ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ቆስለው በህክምና ላይ ናቸው።ጉዳቱ የደረሰባቸው ሠዎች ከህፃናት እስከ አዋቂ ያሉ እንደሆኑም ጨምረው ተናግረዋል።ሕብረተሰቡ ማነኛውንም ብረት ነገር ሲያገኝ ለፀጥታ አካላት ማሳየት እንጂ በራስ መነካካት ጉዳት ያመጣልም ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ዶይቸ ቬሌ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኦዴሳ


ፑቲን ኦዴሳ ከተማን ሳይቆጣጠር የዩክሬይን ዘመቻው ስኬታማ ሊሆንለት አይችልም። ኦዴሳን ከተቆጣጠረ ግን በአውሮፓ ትልልቅ ጂኦፖለቲካዊ ለውጦች ይጠበቃሉ። ለምን? ኦዴሳ ይህን ያህል ጥቅሟ ምንድነው?? ይህን አጭር ቪዲዮ ተከታተሉ

https://youtu.be/sW0rM_nr8Uo
አሳዛኝ ዜና!

ተወዳጁ ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሜድስታር ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው እለት ግንቦት 11, 2014 በተወለደ በ57 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ዶክሌ ላለፋት ሁለት አስርተ አመታት በኮሜዲው ዘርፍ አዝናኝ፣ አስተማሪ እና ቁምነገር አዘል የኮሜዲ ስራዎችን ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል። ዶክሌ ሀገራችን ካፈራቻቸው ብርቅዬና ግንባር ቀደም ኮሜዲያኖች ውስጥ አንዱ ሲሆን ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር።

@Yenetube @Fikerassefa
ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የመጀመሪያውን ቋሚ ድልድይ ሰራች

በደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የመጀመሪያውን ቋሚ ድልድይ በትላንትናው እለት በይፋ መመረቁን ተከትሎ በደስታ የተሞላው የሀገሬው ህዝብ በድልድዩ ላይ ደስታውን ሲገልፅ ውሏል። በዋና ከተማዋ ጁባ  የሚገኘውና 560 ሜትር ርዝመት ያለው የነጻነት ድልድይ የተገነባው ከጃፓን መንግስት በተገኘ እርዳታ ነው።

ግንባታው የጀመረው በ2013 ቢሆንም በእርስ በርስ ጦርነት እና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ግንባታው ሲስተጓጎል ቆይቷል።አስቀድሞ የነበረው ድልድይ  ሊንቀሳቀስ የሚችል በተለይ ለእግረኞች መሻገር አደገኛ ነበር።

በድልድዩ የምረቃ ስነስርዓት የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ እጩ እና የአፍሪካ ህብረት የመሠረተ ልማት ልዑክ ራይላ ኦዲንጋ እንዲሁም የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ኃላፊ ታናካ አኪሂኮ ተገኝተዋል። የነጻነት ድልድይ በጃፓን እና በደቡብ ሱዳን ህዝቦች መካከል የረጅም ጊዜ እና ዘላቂ ወዳጅነት ምልክት መሆኑን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በስነስርዓቱ ላይ ተናግረዋል።

ድልድዩ በጁባ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ከማቃለሉም በላይ የንግድ እንቅስቃሴውን ለማፋጠን ይረዳል ተብሎ ይጠበቃል።

Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
ሃገራቸውን እና ህዝባቸውን ያገለገሉ አካላት ላይ የሚደርስ መንግስታዊ እገታ እንዲቆም የፓርላማ የአብን አባላት አሳሰቡ!

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላት በሕግ ማስከበር ስም የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችንና ጠያቂዎችን የማጥፋትና ሕዝባችንን አንገት የማስደፋት እንቅስቃሴ አጥብቀን እንቃወማለን ሲሉ መግለጫ አወጡ።መንግስት በአማራ ክልል ህዝብ ላይ የሚፈፅመው ማዋከብ “የታወቀ ጠላት የሚያደርገው ዓይነት” ሲሆን ማዋከቡ በአስቸኳይ ካልቆመ ሀገርና ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀው የአገራዊ ምክክር ከወዲሁ እንዲጨናገፍ የሚያደርግ ውጤት እንደሚያስከትል አጥብቀን ለማሳሰብ እንወዳለን።

በፓርቲው አባላትና አመራሮች፣ በፋኖ አባላት፣ በሕጋዊ ታጣቂዎችና ወጣቶች እንዲሁም አገራቸውንና ሕዝባቸውን ያገለገሉ የጦር መኮንኖችንና የጸጥታ አመራሮች ላይ የሚፈጸመው መንግስታዊ እገታና ስወራ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዚህ ሰበብ በማንነታቸው ብቻ የታገቱ አካላትም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ ሲሉም ጠይቀዋል።

የአብን የፓርላማ አባላት በመግለጫቸው “መንግስት ትንሹን መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣና የህዝባችንን ደህንነት እንዲያረጋግጥ” በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ጆሮ አልሰጠንም።በእዚህም የተነሳ የክልሉ ህዝብ ማንነትን መሰረት ላደረገ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀልና ስደት ተዳርጓል ያሉት አባላቱ ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ መፈናቀል ከዓለም ቀዳሚ ለመሆኗ አንዱ ምክንያት ሆኗል።

ሕግ ማስከበርን ሰበብ በማድረግ የፌደራል የፀጥታ መዋቅር በሕገ መንግሥቱ ለክልልና ለፌዴራል ተለይቶ የተሰጠውን ኃላፊነት እና ሚና በደፈጠጠ መልኩ ክልሉን በሕገ-ወጥ መንገድ ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም እንዲሁም “የክልሉ መንግስት በፌደራል መንግስቱ ለሚፈጸመው።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
“ሊፍት ኢትዮጵያ” የትራንስፖርት ዘርፉን ተቀላቅያለሁ ብሏል፡፡

ሊፍት ኢትዮጵያ የታክሲ አገልግሎት በመዲናችን አዲስ አበባ አሁን ካለው የሜትር ታክሲ ክፍያ ከ25 እስከ 35 በመቶ ቅናሽ በማድረግ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንደሚሰጥ የሊፍት ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙኒብ አብዱልካፉር ተናግረዋል፡፡አገልግሎቱ በመዲናዋ ያሉ አነስተኛ እና መካከልኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍል የትራንስፖርት ፍላጎት ለሟሟላት መቋቋሙንም ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሙኒብ አገልግሎቱን የሚጠቀሙ ደንበኞች ክፍያውን የሚፈጽሙት በዲጂታል መሆኑ “ሊፍት ኢትዮጵያን” ለየት ያደርገዋል ብለዉናል፡፡ከዚህም በተጨማሪ አብረው መስራት የሚፈልጉ የተሸከርካሪ ባለንብረቶች፤ምንም ተቆራጭ( ኮሚሽን) የማይደረግባቸው ሲሆን፤በወር የ449 ብር ጥቅል በመሙላት ብቻ ያለገደብ መስራት እንደሚችሉ ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ 1 ሺ 800 መኪናዎች ከሊፍት ኢትዮጵያ ጋር አብረው እየሰሩ መሆናቸውን የነገሩን አቶ ሙኒብ፤ በሚቀጥለው ወር 10 ሺ መኪናዎችን ወደ ስራ ለማስገባት ማቀዳቸውንም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም “ሊፍት ተማሪ” የተባለ ለየት ያለ የተማሪዎች የወር ጥቅል የተዘጋጀም ሲሆን፤ተማሪዎች በጋራም ሆነ በግል በተመጣጣኝ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡አገልግሎት ፈላጎዎች “የሊፍት ኢትዮጵያን” መተግበሪያ ከጎግል በማውረድ አልያም በ9885 በነጻ የስልክ መስመር በመደወል መጠቀም ይችላሉ ተብሏል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋር ሀገሮች አምባሳደሮችና የልማት ድርጅቶች የስራ ኃላፊዎች ጋር በሀገሪቱ የዘጠኝ ወር የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ላይ ዛሬ ውይይት አድርጓል።

ለውይይቱ መነሻ የዘጠኝ ወር የማክሮ ኢኮኖሚውን አፈፃፀም ሪፖርት የፕላንና ልማት ሚንስትሯ ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ሲያቀርቡ እንዳሉት፣ ባላፉት ዘጠኝ ወራት ኢኮኖሚው በየዘርፉ ዕድገት በማስመዝገብ ላይ መሆኑን ጠቅሰው በተለይ በውጭ ቀጥተኛ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ወደ ሀገር ውስጥ በሚልኩት ዶላር ረገድ ጥሩ ዕድገት አለ ብለዋል።

በአጠቃላይ በ9 ወር ውስጥ ኢኮኖሚው 6 ነጥብ 6 በመቶ አድጓል ያሉት ዶ/ር ፍፁም፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ለ 1 ነጥብ 4 ሚለዮን ዜጎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረ፣ የመንግስት ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ7 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት እንደሳየ፤ እንዲሁም ባንኮች 1 ነጥብ 6 ትሪሊየን ብር ቁጠባ መሰብሰብ እንደቻሉ፣ በአጠቃላይ ከተሰራጨው ብድር ውስጥም 70 በመቶው ለግሉ ዘርፍ አገልግሎት ላይ እንደዋለ ተናግረዋል።

ውይይቱን የመሩት የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንዳሉት፣ ኢኮኖሚው በወጪ ንግድ፣ በውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ ፍሰትና በሌሎችም መመዘኛዎች ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ ተናግረው ነገር ግን ኢኮኖሚው በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት፣ ድርቅ፣ ኮቪድ 19 እና በሩስያ ዩክሬን ግጭት ምክንያት እየተፈተነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

መንግስት ኢኮኖሚው የገጠመውን ወቅታዊ ችግር ለመፍታት ቅድሚያ ትኩረት የሚሹ እንደ ድርቅ ፣ በጦርነቱ የደረሱ ጉዳቶችን ለማገገም፣ እንዲሁም መሰረታዊ የመገልገያ ሸቀጦችና መሰል ጉዳዮችን በመለየት እየሰራ እንደሚገኝም አስረድተዋል።

በቀጣይም መንግስት የሀገሪቱን ዜጎች በልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚደርገው ጥረት ከልማት አጋሮች አላማ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ግንኙነታችንን ይበልጥ በማጠናከር ልንሰራ ይገባል ሲሉ አቶ አህመድ ሽዴ መናገራቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት ከአራት ሺ በላይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ምርኮኞች ናቸው ያላቸውን እለቃለሁ ሲል መንግስት ደግሞ ከሰሞኑ መግለጫ እሰጥበታሉ አለ፡፡

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሽብርተና ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት ራሱን የትግራይ ክልል መንግስት ብሎ የሚጠራው ድርጅት ከፍተኛ አመራር ለአሜሪካ ድምፅ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም እንደተናገሩት የጦር ምርኮኞች ናቸው ያሏቸውን ለመልቀቅ ወስኗል፡፡

አሻም ይህን ለማጣራት የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገለግሎት ሚኒስቴርን ለማነጋገር የሞከረች ቢሆንም ሚኒስትር ዲኤታዋ ሰላማዊት ካሳ ከሰሞኑ መግለጫ ይሰጥበታል ከማለት ውጪ የተብራራ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ከጥቁት ሳምንታት ወዲህ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ሊቀስቀስ ይችላል የሚል ስጋት በብዙዎች በሚነገርበት ወቅት ከህወሓት በኩል ይህ ወሳኔ መሰማቱ ያልተጠበቀ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ታህሳስ 29 ቀን 2014 ዓ.ም የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ስበሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች ”ተጠርጣሪዎች ክስ በማቋረጥ” ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
ፍርድ ቤቱ በብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ላይ የ10 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ::

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀድሞው የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄ/ል ተፈራ ማሞ ላይ የ10 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

ዛሬ ጠዋት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብለው የነበሩት ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ዛሬ ከሰዓት መልስ መቅረባቸውን ጠበቃቸው አቶ ሸጋው አለበል ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል። ህገ መንገስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል በሚል ፍርድ ቤት መቅረባቸውንም ነው ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ለ14 ቀናት ታስረው እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ 10 ቀን ብቻ በመፍቀድ ለግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱንም አቶ ሸጋው ተናግረዋል። የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄ/ል ተፈራ ማሞ ባሳለፍነው ሰኞ በአዲስ አበባ ባልታወቁ ሰዎች መታፈናቸው መገለጹ ይታወሳል።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የፌደራል መንግስት ከህወሃት ጋር ባደረገው ጦርነት በፌደራል መንግስት ጦር እዝ ስር በመሆን ውጊያ ሲመሩ፣ ሲዋጉና ሲያዋጉ መቆየታቸው አይዘነጋም።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
“የመዲናዋ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ይቀባሉ" የሚል ዉሳኔ አልተላለፈም ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ህንፃዎች ሁሉ ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ አስታወቁ።የቢሮ ኃላፊው በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የህንፃ ስታንዳርድና የውጭ ማስታወቂያ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህን መነሻ አድርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች አዲስ ከተማ ግራጫ ቀለም ልትቀባ ነው በሚል በስፋት ሲዘዋወር የታየው መረጃ የተሳሳተ ነው፡፡

እስካሁን ድረስ የከተማዋ ህንጻዎች ቀለም ምን አይነት ይሁን የሚለው ጉዳይ ለውይይት ቀረበ እንጂ የከተማ አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳላሳለፈ አመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይም ከዚህ ቀደም ‹‹ከተማችን ቡራቡሬ ሆና ባለቤት አልባ መስላለች›› ማለታቸውን ያስታወሱት የቢሮ ኃላፊው፤ ይህን ችግር ማንኛውም የመዲናዋ ነዋሪም ሊታዘብ ይችላል። የከተማ አስተዳደሩም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል።ችግሩን ለመፍታት የውጭ ማስታወቂያውና የከተ ማዋ ቀለም ሁኔታ የሚመራበት ስታንዳርድ ዝግጅት ተደረገ እንጂ ውሳኔ ላይ አለመድረሱን ጠቁመዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=73364

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ጎንደር ዞን ስር ያሉ ሁሉም ያልተፈተኑና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በቀጣይ አመት እንደሚፈተኑ ተገለጸ።

ተማሪዎቹ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ሃገር አቀፍ ፈተናውን ያልወሰዱና ፈተናውንም ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በቀጣይ አመት በሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከክልል በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የቲቶሪያል ትምህርት በወረዳቸው ከሚገኘው አዲምህረት ትምህርት ቤት ከግንቦት ወር ጀምሮ እንደሚሰጡ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ አጸደ በሬ አሳውቀዋል።

በቀጣይ ሁለት የክረምት ወራቶች የማጠናከሪያ ትምህርት እንደሚሰጥ የገለጹት ወ/ሮ አጸደ በሬ በተለያዩ ምክንያት ከወረዳው ውጭ የሚገኙ ተማሪዎችንና ወደ ወረዳው መሄድ የማይችሉ ተማሪዎችን የተማሪ መታወቂያ አይዲ ካርድ ይዘው በደባርቅ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤት ከአዲ አርቃይ ከተማ ተማሪዎች ጋር መማር እንደሚችሉ አሳውቀዋል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በሰሜኑ የሃገሪቷ ክፍል በነበረው ጦርነት በተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተገንዝቦ በ2013 ዓ.ም ኦንላይን ተመዝግበው ሃገር አቀፍ የ 12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱና ፈተናውን ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች ከ 2014 ዓ.ም ተፈታኞች ጋር በድጋሚ ፈተናውን እንዲፈተኑ ከሃገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በጋራ መወሰናቸው የሚታወስ ነው።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በ12 አገራት ወደ 80 የሚጠጉ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ሞንኪፖክስ) መያዛቸው መረጋገጡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የአገራቱን ስም ሳይገልጽ ሌሎች 50 ተጠርጣሪዎችም በምርመራ ላይ መሆናቸውንም የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።መጀመሪያ በአውሮፓ መታየቱን ተከትሎ ቀደም ሲል በጣሊያን፣ በስዊድን፣ በስፔን፣ በፖርቱጋል፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በዩናይትድ ኪንግደም በሽታው መኖሩ ተረጋግጧል።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በብዛት በመካከለኛው እና በምዕራብ አፍሪካ አካባቢዎች በብዛት የሚከሰት ነው።

የእንግሊዝ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት እንደገለጸው፣ ይህ ያልተለመደ የቫይረስ ኢንፌክሽን አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ሲሆን ብዙዎች ላይም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚድን ነው።ቫይረሱ በሰዎች መካከል በቀላሉ የማይሰራጭ ሲሆን በሰፊው ሕዝብ ጤና ላይ የሚያስከትለው ስጋት በጣም ዝቅተኛ ነው ተብሏል።

ለዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተለየ ክትባት የለም። ከመደበኛው ፈንጣጣ ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው የፈንጣጣ ክትባት 85 በመቶ የመከላከል አቅም ይሰጣል።የዓለም ጤና ድርጅት አርብ ዕለት በሰጠው መግለጫ "በቅርብ ጊዜ በ11 አገሮች የተመዘገበው ወረርሽኞች ተላላፊ ባልሆኑ አገሮች ውስጥ መከሰቱ ያተለመደ ነው" ብሏል።

"ተጎጂዎችን ለማግኘት፣ ለመደገፍና የበሽታ ክትትልን ለማስፋፋት ከተጎዱት አገራት እና ከሌሎች ጋር እየሠራሁ ነው" ብሏል።በተጨማሪም ድርጅቱ በበሽታው ምክንያት ማግለል እንዳይኖር አስጠንቅቋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
“የመዲናዋ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ይቀባሉ" የሚል ዉሳኔ አልተላለፈም ተባለ፡፡ የአዲስ አበባ ህንፃዎች ሁሉ ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ አስታወቁ።የቢሮ ኃላፊው በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ…
#update

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕንጻዎችን ቀለም በተመለከተ ማብራሪያ ሰጠ!

አስተዳደሩ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እንድትሆን እና ዓለም አቀፍ ደረጃን የሚመጥን ገፅታ እንዲኖራት ከሚሠሩ ሥራዎች አንዱ የሕንጻዎችን ቀለምና ቁመት የሚወስን አሠራርን መተግባር መሆኑን አስታውቋል።

በእስካሁኑ ሂደት የከተማዋ ሕንጻዎች ያለምንም ቁጥጥርና ወጥነት በጎደለው መንገድ የሚቀቡ ቀለማት የከተማዋን መልክ ቡራቡሬና ዥንጉርጉር ከማድረጋቸውም በላይ÷ የሚገነቡ ሕንጻዎች ዲዛይን በዘፈቀደ መሠራቱ የከተማዋን ገፅታ በእጅጉ ጎድቶታልም ነው ያለው አስተዳደሩ፡፡

ስለሆነም ይህን ችግር መልክ ለማስያዝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከብዙ ዓለም አቀፍና አፍሪካዊ ከተሞች ተሞክሮ በመውሰድ÷ ለከተማዋ የሚስማማ የሕንጻ ቀለማት ደረጃን አጥንቶ ለውይይት አቅርቧል፡፡በመሆኑም በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች በተሳተፉበት ሁኔታ ዝርዝር ጥናት በማድረግ ለከተማዋ የሚስማሙ 13 ዓይነት ቀለማት መለየታቸውን ገልጿል።

በዚህ መሰረት በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ለከተማዋ በመለያነት ከተመረጡ ቀለማት መካከል የሕንጻ ባለንብረቶች የሚመርጡትን ወስደው የመጠቀም መብት ያላቸው ሲሆን÷ ይህ አሠራር በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች ተጀምሮ ወደ ትግበራ መገባቱንም ነው ያስታወቀው፡፡

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር ወጪ አዲስ ቤተ መንግሥት ሊገነባ መሆኑ ተነገረ!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር ወጪ አዲስ ቤተ መንግሥት ሊገነባ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ። ለቤተ መንግሥቱ ግንባታ የተያዘለት በጀት ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ በኋላ ከፍተኛ ወጪ የሚወጣበት የመንግስት ሜጋ ፕሮጀክት እንደሚሆን ዘገባው አመላክቷል።በየካ ክፍለ ከተማ የሚገነባው አዲስ ቤተ መንግስት ከሚያካትታቸው ግንባታዎች መካከል ልዩ ልዩ አዳራሾች፣ የመኖሪያ ቤቶች፣ ሦስት ሠው ሰራሽ ሐይቆችና መንገዶች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በመንግስት የ10 አመት ዕቅድ ውስጥ የተካተተው ይህ ፕሮጀክት በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ከይዞታቸው የሚያስለቅቅ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ ቤተመንግቱ የሚገነባበትን ስፍራ ደረጃ የሚመጥን ሆኖ ከተገኘ በቦታው ላይ ራሳቸው በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት ግንባታ እንዲያከናውኑ ዕድል ይሰጣቸዋል ተብሏል።ዘገባው የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች መንግስት የፕሮጀክቱን የተወሰነ ወጪ በድጋፍ መልክ እንደሚሸፍን ምንጮቼ ነግረውኛል ብሏል።

በቦታው 15 ቢሊዮን ብር ያወጣል ተብሎ የሚገመተውን የ20 ኪሜ የመንገድ ግንባታ ስራ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር መጀመሩ የታወቀ ሲሆን ወደ 9 ኪሜ የሚሆነውን ስራ ማጠናቀቁም ታውቋል።

ግንባታውን የሚያስተባብሩት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አካላት፣ አዲሱን የቤተ መንግሥት ግንባታ ፕሮጀክት 'ጫካ' ፕሮጀክት የሚል ሥያሜ ሰጥተውታል፡፡የአዲሱን ቤተ መንግስት ግንባታ ተከትሎ አሁን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መኖሪያ ሆኖ የሚያገለግለውን የምኒልክ ቤተ መንግሥት እንዲሁም የኢዮቤልዩ ቤተመንግስትን ብሔራዊ ሙዝየም የማድረግ እቅድ መያዙም ተጠቅሷል።

[Reporter/✍️ Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በአራት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተዘጋጅቶ በቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ነው፡፡የፌደራል አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አስፈጻሚ ተቋማት ከተሰጣቸው ስልጣንና ተግባራቸው ጋር የሚመጣጠን የሰው ሃይል እንዲኖራቸው የሚያስችል የአደረጃጀት ማሻሻያ ማድረጋቸውን ተከትሎ በቀጣይ ሊፈጸሙ ስለሚገባቸው አቅጣጫዎች በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው ስለኢንቨስትመንት ማበረታቻ በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ሲሆን የግሉ ዘርፍ ለአገር የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ ድርሻ ያለው በመሆኑ ዘርፉ ያለውን ሀብት መንግሥት ትኩረት በሚሰጣቸው የልማት መስኮች ላይ በማዋል ለኢኮኖሚ ዕድገት ተገቢውን አስተዋፅኦ ማድረግ እንዲችል የሚያበረታቱ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤ በተለይም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የውጭ ካፒታል ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት በአጠቃላይም ለማህበራዊ ኑሮ መሻሻል አስተዋፅኦ ማድረግ የሚችልበትን መሠረት መጣል የሚገባ መሆኑን ከግምት በማስገባት እንዲሁም የተሰጠው ማበረታቻ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ የሚያስችል የክትትል ሥርዓት የሚዘረጋ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ግብዓቶች በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በጉምሩክ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ የአገራችንን የወጪና የገቢ ንግድ ሥርዓት ከሚመሩ ሕጐች መካከል የጉምሩክ መጋዘን አስተዳደርን እና የጉምሩክ አስተላላፊዎችን በሚመለከት የወጡ ደንቦች ይገኙበታል፡፡ እነዚህን ደንቦች በአንድ በማጠቃለል ዓለም ዐቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ጋር የሚጣጣም፣ በአገራችን እያደገ የመጣውን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት የሚደግፍ እንዲሁም ሕጋዊ ንግድን እና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ፣ በስራ ላይ ካለው የጉምሩክ አዋጅ ጋር የሚጣጣም ደንብ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶች በማከል ከጸደቀበት ከዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

ቀጥሎ ምክር ቤቱ ውይይቱን ያደረገው የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን ስልጣንና ተግባር እና አደረጃጀት ለመወሰን በወጣው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የፌደራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 መሰረት የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ መብትና ግዴታዎች እንዲተላለፉለት የተደረገ በመሆኑና በተሻለ አቅም የቁጥጥር ስራውን እንዲመራ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶች በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

[PMOEthiopia]
@YeneTube @FikerAssefa