YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቻይና በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ በ25 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

ደቡብ ምዕራብ ቻይና ቾንግኪንግ፤ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመነሳት ላይ እያለ ከመንደርደሪያው በመውጣቱ 25 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ።

አደጋው ከደረሰ በኋላ፤ መንግደኞቹን ሙሉ በሙሉ ከአውሮፕላን የማስወጣት ስራ የተሰራ ሲሆን፤ ጉዳት የደረሰባቸው ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጿል።

ንብረትነቱ የቲቤት አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላን በውስጡ 113 መንገደኞችን እና 9 የበረራ አባላትን አሳፍሮ ነበር ተብሏል።

Via Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
በሶማሌ ክልል በባህላዊ የምርጫ ሥነ ሥርዓት ላይ በፀጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ግድያ ኢሰመኮ ኮነነ!

በሶማሌ ክልል ቦምባስ ከተማ በባህላዊ ሥነ ሥርዓት የጎሳ መሪ ለመምረጥ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በፀጥታ ኃይሎችና በታጠቁ ግለሰቦች በተፈጸሙ ጥቃቶች የ11 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮነነ።በሶማሌ ክልል ከሚገኙት የሶማሌ ጎሳዎች መካከል የሆኑት የአኪሾ ጎሳ አባላት መጋቢት 11 እና 12 ቀን 2014 ዓ.ም. የጎሳ መሪያቸውን ለመምረጥ በተሰበሰቡበት ዕለት ከግድያ በተጨማሪ 33 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ማረጋገጡን ኢሰመኮ ዛሬ ግንቦት 04/2014 ዓ.ም. ባወጣው የምርመራ ሪፖርቱ አስታውቋል።

ኢሰመኮ በስፍራው ተገኝቶ ባደረገውም ምርመራ የክልሉ መንግሥት የፀጥታ አካላት ከመጠን ያለፈ የኃይል አጠቃቀም ለሞትና ለአካል ጉዳት ምክንያት ሆኗል ብሏል።ኢሰመኮ በሁለቱ ቀናት ስለተፈጸሙ ግድያዎችና የአካል ጉዳቶች የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ በቦታው በመገኘት የዓይን ምስክሮችን፣ ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የአገር ሽማግሌዎችን ማናገሩን አስታውቋል።

በተጨማሪም ከሆስፒታል ምንጮች መረጃ በማሰባሰብ እንዲሁም ፈቃደኛ የሆኑ የክልሉ ኃላፊዎችን በማነጋገር የምርመራውን ሪፖርት አጠናቅሯል።በተጨማሪም ቦምባስ ከተማ የሚገኝ የጥቃቱ ሰለባዎች የተቀበሩበትን መካነ መቃብር መጎብኘቱን ገልጾ በዚህም በመጀመሪያው ቀን የተገደሉ ሰዎች የተቀበሩበትን የጅምላ መቃብር እንዲሁም በሁለተኛው ቀን የተገደለች ሴት ተቀብራበታለች የተባለ መካነ መቃብር መመልከቱንም በዚሁ የምርመራ ሪፖርቱ አካቷል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://bbc.in/39h6k3i

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የ8ተኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል ተባለ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከተማ አቀፍ የሆነው የ8ተኛ ክፍል (ሚኒስትሪ) ፈተናን ከ71 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 2014 ድረስ ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

በአጠቃላይ 71 ሺህ 661 የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለማስፈተን ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን በትምህርት ቢሮ ፈተና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የፈተና ዝግጅቱ ተጠናቆ የህትመት ሥራዉ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በዕለቱ የማሰራጨት ሥራ ብቻ እንደሚቀርም ገልጸዋል፡፡የፈተናዉን ምዝገባ በተመለከተ የተማሪዎች የአድሚሽ ካርድ በሚቀጥለው ሳምንት በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚላክ እና ለተማሪዎቹም እንደሚተላለፍ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስምንተኛ ክፍል ፈተና 211 የመፈተኛ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ሲሆን፤ ጣቢያዎቹን ምቹ ናቸው የሚለውን ምልከታ እየተደረገ መሆኑን በማንሳት ቁጥሩ ከፍ አልያም ዝቅ ሊደረግ እንደሚችል ዳይሬክተሩ ለሬዲዮ ጣቢያው አብራርተዋል።ፈተናው በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚሰጥም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በአዲስ አበባ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ ነገ እንደሚጠናቀቅ ኤጀንሲው ገለፀ!

በአዲስ አበባ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ በተሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲያቀርቡ የከተማዋ የመሬት ይዞታ፣ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ጀማል ሀጅ እንደገለፁት፥ ለይዞታ ማርጋገጫ በተመረጡ 25 ቀጠናዎች እና 112 ሰፈሮች የሚገኙ የመሬት ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እያቀረቡ ነው፡፡

ኤጅንሲው የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ ሀሙስ ሚያዚያ 20 መቀበል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባሉት 6 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ11 ሺህ 300 በላይ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመለከቻዎችን ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡

የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ የመቀበል ሂደቱ እስከ ግንቦት 5 ብቻ የሚቆይ በመሆኑ በተመረጡ ቀጠናዎች እና ሰፈሮች ውስጥ የሚገኙ ባለይዞታዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድና አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት የክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤቶች ባዘጋጁት ቦታ በመገኘት ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ አስተላልዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ባለ ይዞታዎች ኤጀንሲው አረጋግጦ ላልመዘገበው ይዞታ ምንም ዓይነት ህጋዊ ዋስትናና ከለላ የማይሰጥ መሆኑን ተገንዝበው ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ሃላፊው አሳስበዋል፡፡የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ አቀራረቡንና አመዘጋገቡን ሂደት የሚታዘቡ ከህብረተሰቡ የተመረጡ 336 ታዛቢዎች እየተሳተፉ መሆናቸው ኤጅንሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በህገ- ወጥ መንገድ ሰባት ሕፃናትን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በቤንች ሸኮ ዞን የዘረፋና ወንብድና ልዩ ልዩ ወንጀል ማስተባበሪያ ኃላፊ ም/ኢ/ር ወንዳየሁ ገ/ሚካኤል፣ ተጠርጣሪው ሸኮ ወረዳ ጉፊቃ ቀበሌ ግንቦት አንድ ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 በተሽከርካሪ ይዞ በመጓዝ ላይ እንዳለ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ ከካፋ ዞን ጨና ወረዳ ባላ ሻሻ ቀበሌ ከአስር ዓመት በታች የሆኑ ሰባት ሕፃናትን ከሚኖሩበት ቤተሰብ ከብቶችን ትጠብቃላችሁ በማለት ለጉልበት ብዝበዛ ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ይዞ መጓዙን ገልጸዋል።

በህገ_ወጥ መንገድ ከቦታ ወደቦታ እያዘዋወሩ የጉልበት ብዝበዛ የሚዳርጉ ግለሰቦችን ህብረተሰቡ ለህግ አካላት አሳልፈዉ መስጠት እንዳለበት ፖሊስ ማሳሰቡን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቼ

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል። 🍎
👉 የሪህ መድኀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
👉 ለመፍትሔ ሥራይ
👉 ፍቅር ለነሳው ለመስተፋቅር። 🍒
👉 ገንዘብ አልገባ ለሚለው ለሚበተንበት።
👉 ለአስም ለሳይነስ ።
👉 ለአይነጥላ ለገርጋሪ።
👉 ለስንፈተወሲብ ለሚቸኩልበት።
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ ።
👉 ለእራስ ሕመም።
👉እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶች እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱ እዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
የሚፈልጉትን መድኀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል። 🥒

ለበለጠ መረጃ

አድራሻ ባህርዳር ፦ቀበሌ 11 🫑
☎️ 0917040506
📞 0912718883
ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
ለጤናወ መፍትሄ የሚፈልጉትን ለማግኔት
🌿 ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ 🌱
🩺
👇
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe
ኦፌኮ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ባለፉት ጥቂት ወራት በኦሮሚያ ክልል 297 ሰዎችን ገድለዋል ሲል ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መናገሩን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። በክልሉ መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር በገባበት ግጭት ከግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተፈናቅሏል በማለት ኦፌኮ በመግለጫው ጨምሮ ገልጧል። የፓርቲው መግለጫ ትኩረት ተባብሰው ቀጥለዋል ባላቸው የርስበርስ ግጭት፣ የፖለቲካ ውድቀትና የኢኮኖሚ ቀውስ ላይ ነው። አገሪቱ ከቀውስ የምትወጣው፣ ግጭቶችን አቁሞ ወደ ፖለቲካዊ ድርድር በመመለስ እንደሆነ ፓርቲው ገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ ሲሰራ የነበረው ሁዋጂያን ግሩፕ የተሰኘው የቻይና ኩባንያ በአለም አቀፍ ወረርሽኝ ምክንያት ስራውን ካቆመ ከአንድ አመት በኋላ የተከራየውን ሼዶች በሙሉ አስረክቦ ፓርኩን ለቆ መውጣቱን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳንዶካን ደበበ ተናግረዋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ዓሳ የማርባት ሥራ ተፈቀደ!

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የዓሳ ማርባት ሥራ መፈቀዱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የዓሳ ሀብት ልማት ዕድሎችና ተግዳሮቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከዘርፉ ባለድርሻዎች ጋር ማክሰኞ ግንቦት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ምክክር ያደረገ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዓሳ ሀብት ያላት ቢሆንም በተገቢው መንገድ ያልተያዘና ጥቅም ላይ ያልዋለ መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት የህዳሴ ግድብን ሳይጨምር በተደረጉ ጥናቶች ኢትዮጵያ በዓመት 94,500 ቶን ዓሳ የማምረት አቅም እንዳላት፣ በግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት አስቻለው ላቀው (ዶ/ር) ገልጸዋል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት እየተመረተ የሚገኘው በዓመት ከ60 ሺሕ ቶን ያልበለጠ ዓሳ መሆኑን አክለዋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 200 ያህል የዓሳ ዝርያዎች መኖራቸውንና 40 የሚሆኑት በኢትዮጵያ ብቻ እንደሚገኙ ገልጸው፣ ከእነዚህም ውስጥ ስድስቱ ዝርያዎች አሁን ባለው ገበያ ተፈላጊ ናቸው ብለዋል። ነገር ግን ዓመታዊ ምርቱ በቂ ባለመሆኑ የአንድ ሰው ዓመታዊ የዓሳ ፍጆታ ግማሽ ኪሎ ግራም በታች መሆኑን ጠቁመው፣ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች የአንድ ሰው ዓመታዊ የዓሳ ፍጆታ እስከ 12 ኪሎ ግራም መድረሱን ተናግረዋል። በመሆኑም ያሉትን ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ የውኃ ሀብቶች በመጠቀም የተሻለ የቁጥጥር ሥርዓት ሊኖር እንደሚገባ አክለዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በማላዊ ስታዲየም ይገጥማል!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ አቻው ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም እንዲካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወስኗል።

ቀደም ሲል ለኢንተርናሽናል ጨዋታዎች የተመረጠው የባህርዳር ስታዲየም የካፍ ደረጃን ባለማሟላቱ ካፍ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምታደርገውን ጨዋታ በሌላ ሀገር ስታዲየም እንድታደርግ መወሰኑ የሚታወስ ነው።

በመሆኑም ካፍ ኢትዮጵያ የማጣሪያ ጨዋታዋን የምታደርግበትን ስታዲየም እንድታሳውቅ መጠየቁን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከግብፅ አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የሚጫወትበትን ስታዲም አሳውቋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በቀድሞው የማላዊ ፕሬዝዳንት ቢንጉ ዋ ሙታሪካ ስም በተሰየመው ቢንጉ ስታዲየም ጨዋታውን እንደሚያደርግ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የዘኢኮኖሚስት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር የስራ ፈቃድ ተሰረዘ!

የዘ ኢኮኖሚስት መጽሔት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር በኢትዮጵያ የነበረው የሥራ ፈቃድ መሰረዙን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታውቋል።ባለስልጣኑ ለጋዜጠኛው በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንዳስታወቀው፤ ጋዜጠኛው ከሙያ ስነ ምግባር ውጭ በተደጋጋሚ ሲሰራ በመገኘቱ ተደጋጋሚ የቃል እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል።

በተጨማሪም ከጋዜጠኛው ጋር ውይይት በማድረግ ከስህተቱ እንዲታቀብ ለማድረግ ጥረት መደረጉን ባላስልጣኑ ገልጿል።

ይሁን እንጂ ቶም ጋርድነር የሙያውን ስነ ምግባር በማክበር ለመስራት ባለመቻሉ ከዛሬ ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ የነበረው የጋዜጠኝነት የስራ ፈቃድ መሰረዙንና ከዚህ በኋላ በጋዜጠኝነት ስራ በኢትዮጵያ ውስጥ መስራት እንደማይችል ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ዘ ኪኮኖሚስት በዚህ ጋዜጠኛ ምትክ ሌላ የሙያውን ሥነ ምግባር አክብሮና ገለልተኛ ሆኖ መስራት የሚችል ሰው መድቦ ማሰራት እንደሚችልም ባለስልጣኑ በዚሁ ደብዳቤ ላይ ገልጿል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
የዩኤኢው ፕሬዚዳንት ሼህ ካሊፋ ቢን ዛይድ አረፉ!

የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ፕረዚዳንት ሼህ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የኤሚሬትስ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
‹‹አሁን ያለዉ መንግስት በስልጣን የመቀጠል ያለመቀጠል ዕጣ ፋንታዉ የሚወሰነዉ እየፈታ ባለዉ የህዝብ ችግሮች መጠን ነዉ››
-የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

አሁን ያለዉ መንግስት በስልጣን የመቀጠል ያለመቀጠል ዕጣ ፋንታዉ የሚወሰነዉ እየፈታ ባለዉ የህዝብ ችግሮች መጠን ነዉ ሲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሃይሌ ተናግረዋል፡፡

መንግስት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በሚፈጽሙ የመንግስት ሰራተኞችም ሆነ ሃላፊዎችን ተጠያቂ በማድረጉም ሆነ ባለማድረጉ ፣ ከህዝብ የበለጠ ተጎጂ ስለሆነ ተጥያቂነት ማንበር እንደሚገባው በአፅንኦት ተናግረዋል።

ሃላፊው ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ተገኝተው ለህግ ፣ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ 10 ወራት የስራ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት፡፡

ዋና ዕንባ ጠባቂው ከቋሚ ኮሚቴዉ አባላት ከተጠያቂነት አንጻር ለተነሳላቸዉ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ መመረጥ እና በስልጣን ላይ መቆየት የሚፈልግ ከሆነ ጥሰቶችን በሚፈጽሙ ሰራተኞች እና ሃላፊዎች ላይ እርምጃ መዉሰድ እንደሚገባውና ጠቀሜታው ለራሱ እንደሆነ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

በተያያዘም ዶ/ር እንዳለ " እኛ እንደ አንድ ዴሞክራሲ ተቋም እንዲሁም የተከበረዉ ምክርቤት ማድረግ የሚችለዉ ነገር ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል ህግ እና ደንብ እንዲሁም ስርዓት፣ መመሪያ ወይም አዋጆችን ማዉጣት ነዉ፤ ከዛ ባለፈ የወጡ አዋጆችን ወይም ደንቦችን የመፈጸም ሃላፊነት ያለበት ግን የመንግስት አስፈጻሚ አካል ነዉ "ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በነዚህ ምክረሃሳቦች ላይ መግባባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን በማንሳት መግባባት ከሌለ ግን ምክር ቤቱ ብዙ ህግ ቢያወጣ ፤ የዴሞክራሲ ተቋማት ምክረሃሳቦችን ቢሰጡ እና መፈጸም ባይችሉ ፤ መንግስት ተጎጂ እሆናለዉ ብሎ በማሰብ የበለጠ ቢሰራ የተሻለ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ!

ከሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ በነዳጅ ጭማሪ ምክንያት በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በዚህም መሠረት ነባር ታሪፍ በደረጃ አንድ ተሽርካሪ በአስፋልት መንገድ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 493 የነበረው በአዲሱ ታሪፍ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በሰው በኪሎ ሜትር ብር 0 ነጥብ 532 ሆኗል፡፡

ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎ ሜትር ታሪፍ 0 ነጥብ 548 የነበረው ወደ 0 ነጥብ 596 ከፍ ብሏል፡፡ በሌላ በኩል በደረጃ ሁለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 457 የነበረው በአዲሱ ታሪፍ በኪሎ ሜትር የ0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 496 መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በደረጃ ሁለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 505 የነበረው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በአዲሱ በኪሎ ሜትር 0. ነጥብ 554 መደረጉ፤ደረጃ ሦስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 416 ይከፈልበት የነበረው 0 ነጥብ 039 በኪሎሜትር ጭማሪ በማድረግ 0 ነጥብ 455 በኪሎሜትር እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ደረጃ ሦስት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 471 የበነረው በኪሎ ሜትር የ0 ነጥብ 049 ጭማሪ በማድረግ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 520 ሆኗል፡፡ የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ በደረጃ አንድ ተሽርካሪ ለአንድ ሰው በነባር ታሪፉ በአስፋልት መንገድ ብር 49 ነጥብ 29 ይከፈል የነበረው በአዲሱ ብር 53 ነጥብ 16 ሆኗል፡፡ ይህም በ100 ኪሎ ሜትር ጭማሪ ያደረገው የብር 3 ነጥብ 87 ነው፡፡በደረጃ ሁለት ተሽከርካሪዎች ለአንድ ሰው በነባር ታሪፍ በ100 ኪሎ ሜትር 45 ነጥብ 70 ያስከፍል የነበረው በ100 በኪሎ ሜትር ብር 3 ነጥብ 87 በመጨመር 49 ነጥብ 58 በ100 ኪሎ ሜትር ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ በደረጃ ሦስት ተሸርካሪ በ100 ኪሎ ሜትር ለአንድ ሰው ብር 41 ነጥብ 61 ያስከፍል የነበረው በ100 ኪሎ ሜትር የ3 ነጥብ 88 ጭማሪ በማድረግ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 45 ነጥብ 49 መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአገሪቱ ምዕራብና የደቡብ ምዕራብ ተፋሰሶች ላይ የተሻለ የዝናብ ሁኔታ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ በአገሪቱ የምዕራብ አጋማሽ አካባቢዎች እየተስፋፋ ይሄዳል ብሏል።እነዚሁ አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ እንደሚያገኙም የሚቲዎሮሎጂ ትንበያዎች ያመለክታሉ ነው ያለው።የዝናቡ ሁኔታ በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ደግሞ ከሞላ ጎደል ቀጣይነት እንደሚኖረውም አመልክቷል።

በእነዚሁ ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች ቀጣይነት እንደሚኖራቸውም ተጠቁሟል።ይህም በተለያየ የዕድገት ደረጃዎች ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎችና ለቋሚ ተክሎች የውሃ ፍላጎትን ለማሟላት ይረዳልም ተብሏል።

በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ለግጦሽና ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት መሻሻል የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ነው የገለጸው።በተጨማሪም ለመኸር ግብርና ዝግጅት መልካም አጋጣሚን እንደሚፈጥርም ኢንስቲትዩቱ አመላክቷል::

@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት ለአምራች ኢንደስትሪው የመሬት ፖሊሲውን ቀየረ!

በዚህም መሰረት ለአዳዲስ አምራች ኢንደስትሪዎች የተመቻቸ መሰረተ ልማት ባላቸው የኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ ቦታ ይመቻቻል ተብሏል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዳሉት አሁን ላይ ለሚታየው ምቹ የቢሮክራሲ ጥያቄ እና ብልሹ አሰራር የመሬት ጉዳይ ዋነኛው ነው፡፡

በመሆኑም ይህን ችግር ለመቅረፍ ከዚህ በኋላ በኢንደስትሪው ዘርፍ ለመሰማራት ለሚፈልግ ኢንቨስተር በከፍተኛ ሃብት በተገነቡ ግን በበቂ ባልተያዙ የኢንደስትሪ ፓርኮች ቦታይመቻቻል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባም ሆነ በክልሎች ለኢንደስትሪው ዘርፍ መሬት አይቀርብም፤ ለብልሹ አሰራር በር አይከፈትም ብለዋል፡፡ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ 13 የኢንደስትሪ ፓርኮች እና ሶስት የግብርና ማቀነባበሪያዎች የተገነቡ ቢሆንም በባለሃብቶች ሙሉ ለሙሉ አልተያዙም፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
"ሕዝባችን ዳግም ለወያኔ ወረራ እና ጥቃት እንዳይዳረግ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደወትሮው ሁሉ የፀጥታ መዋቅሩ እና ደጀኑ ሕዝብ የራሱን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ ይሁን" - የአማራ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት



የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል።

የምክር ቤቱ መሉ መግለጫ ቀጥሎ ቀርቧል:-

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፀጥታው ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ በዝርዝር ገምግሟል፡፡

የወያኔ ወራሪ ቡድን በየቀኑ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ የትግራይን ሕዝብ ለጦርነት እያነሳሳ በአማራ ክልል ላይ ዳግም ጦርነት አውጇል፡፡

ይህን አደገኛ ቅዠቱን ለመመከትና ለመቀልበስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ምክር ቤት በአንክሮ ተወያይቶበታል፡፡ የጸጥታ ምክር ቤቱ በየደረጃው ያለው የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ መሆን እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል በየደረጃው በተደረጉ ሕዝባዊ ውይይቶች ላይ ጎልተው ከወጡ ወሳኝ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሕግ ማስከበር ሥራ መላላት ተጠቃሽ መሆኑን የጸጥታ ምክር ቤቱ በጥልቀት አንስቷል፡፡

በቅርብ ጊዜ ደግሞ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የአማራን የውስጥ አንድነት ለማዳከም፣ ሕዝብ ከሕዝብ በማጋጨትና በማጋደል ላይ ተሰማርተው ለጠላት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየሠሩ ያሉ የተደራጁና ያልተደራጁ ኃይሎች እየተበራከቱ መምጣታቸው ተጨባጭ የፀጥታ ስጋት እየፈጠሩ መሆኑን በዝርዝር ተወያይቶበታል፡፡

እነዚህ ኃይሎች በእምነት፣ በፖለቲካ፣ በብሔር ሕዝባችን እየከፋፈሉ የአማራን የውስጥ አንድነት በማዳከም ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርጉት ሙከራ በአጭር ካልተቀጨ በሕዝባችንና በክልላችን ሰላምና ደኅንነት ላይ ዘላቂ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡

የሕገ-ወጥ ንግድን በማስፋፋት ካለው ሀገራዊ የምርት እጥረት በተጨማሪ ሰው ሠራሽ የምርት እጥረት በመፍጠር የኑሮ ውድነት የሚያባብሱ፣ ምርትን ለጠላት በኮንትሮባንድ አሳልፈው የሚልኩ፣ የሕዝብን ሃብት የሚዘርፉ፣ የዜጎችን ነጻ እንቅስቃሴ የሚገድቡ ድርጊቶች በየአካባቢው እያቆጠቆጡ መጥተው ለክልሉ የፀጥታ ስጋት መሆናቸውን ጸጥታ ምክርቤቱ ለይቷል፡፡ ከዚህም በላይ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እየተስፋፋ የመጣው ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ስጋት ውስጥ እየጣለ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም መሳሪያን ለመሞከር በሚል በሐዘንና በደስታ ላይ በግዴለሽነት በሚተኮስ ጥይት የንጹሐንን ህይወት እየቀጨ እና የሕዝባችን የፀጥታ ስጋትና የሐዘን ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ጸጥታ ምክር ቤቱ በአንክሮ ተመልክቷል፡፡

ሕገ-ወጥነትና ሥርዓት አልበኝነት ሥር እየሰደደ በመምጣቱ ሕገ-ወጥ ታጣቂዎች በሚያደርጉት ያልተገባ እንቅስቃሴ የክልሉን ልማቶች እያዳከመ፤ የዜጎችን ነጻ እንቅስቃሴ እየገደበ ፤ የኢንቨስትመንት እድሎችን እየዘጋ፣ የተፈጠረውን የሥራ ዕድል እያጠፋ፣ ለቀጣይ ልማትም እንቅፋት በመሆንና በአጠቃላይ የአማራን ክልል ልማት በአደገኛ ሁኔታ እየተፈታተነ እንደሚገኝ አጽንኦት ሰጥቶ ተመልክቷል፡፡

እነዚህ ሕገ-ወጥ ተግባራት በከተማም ሆነ በገጠር በአጭር ጊዜ ማረም ካልተቻለ የአማራ ክልል ልማት የሚያስቀጥል ሳይሆን የነበረውንም የሚያመክን የሕገ-ወጥነትና የሥርዓት አልበኝነት መናኸሪያ የሚያደርግ መሆኑን በመረዳት ለሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ሲባል መልክ መያዝ እንዳለባቸው ታምኖበታል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው የሚገኙ ወገኖቻችንም በአግባቡ ምግብ እንዲያገኙ አድርጎ ወደ ቀያቸው ጊዜ መመለስ ካልተቻለ የፀጥታና ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ፀጥታ ምክር ቤቱ ተወያይቶበታል፡፡

ከዚህ አንጻር መንግሥት በየደረጃው ሕግ የማስከበር ሥራውን በጥብቅ በመፈጸም የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት ማስከበር አለበት በማለት ሕዝቡ በተለያዩ መድረኮች ያነሳቸውን ጥያቄዎች መርምሮ ትክክለኛ ጥያቄ መሆኑን አስምሮበታል፡፡

ስለሆነም የክልሉ ጸጥታ ምክር ቤት የአማራ ክልል ያለበትን የፀጥታ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም የወያኔን ዳግም ወረራ ለመቀልበስና ለመከላከል የውስጥ አንድነትን ማጠናከር፣ ሰላምና ደኅንነትን መጠበቅ ቁልፍ ጉዳይ ነው ብሎ ያምናል።

ሕዝባችን ዳግም ለወያኔ ወረራ ለጥቃት እንዳይዳረግ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደወትሮው ሁሉ የፀጥታ መዋቅሩ፣ ደጀኑ ሕዝብ የራሱን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በመሆኑም በአንድ በኩል ከፌደራል የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ከወያኔ የሚሰነዘርብንን ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅና በዝግጁነት መቆም፤ በሌላ በኩል ደግሞ በውስጣችን ለወያኔ ሴራ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩትን ሕገ-ወጦችንና ሥርዓት አልበኞችን በመቆጣጠር የክልላችን ሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ ግንባር ቀደም የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆኑ ወስኗል፡፡

ስለሆነም የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት በየደረጃው የጸጥታ ግብረ ኃይል አቋቁሞ ሕገወጥነትን ለመቆጣጠርና ሕግን ለማስከበር ተገቢ ነው ያላቸውን ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በመሆኑም የክልላችን ሕዝብ፣ ወጣቶች፣ የገጠርና የከተማ ነዋሪዎች ሰላምና ደኅንነታችን ለመጠበቅ እና የውስጥ አንድነታችን ለማጠናከር የፀጥታ መዋቅሩ በሚወስደው እርምጃ ሁሉ ተባባሪ እንድትሆኑ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፀጥታ ምክር ቤት

ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም

ባሕር ዳር

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተከናወነ ያለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ውጤታማ በመሆኑ በአብዛኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች አንጻራዊ ሰላም እየሰፈነ መምጣቱን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች፣ በሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እና በመደበኛ የመንግስት የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ መግለጫ እየሰጡ ነው፡፡የሰላም እና የደህንነት ሁኔታዎችን በተመለከተ በተሰጠው መግለጫ ጽንፈኝነትና ፖለቲካዊ ገጽታ ባላቸው መገፋፋቶች ምክንያት የሚፈጠሩ ግጭቶችን የሰው ሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት የህብረተሰቡን ደህንነት እና ሁለንተናዊ ሀገራዊ አንድነትን ለማስከበር እየተወሰደ ያለው ህብረተሰብን ያሳተፈ የተቀናጀ እርምጃ በሁሉም ክልሎች ሊባል በሚችል መልኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት፡፡

በህብረተሰብ ንቅናቄ እና ድጋፍ ታጅቦ እየተካሄደ የሚገኘው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ውጤታማ እየሆነ በመምጣቱ በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም እየሰፈነ መምጣቱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።እየተደረጉ ባሉ ሥራዎች በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

በጎንደር በቀብር ስፍራ በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል በተከሰተ አለመግባባት የተፈጠረውን ግጭት ለማስፋፋት የተደረገው ሙከራ በሰላም ወዳዱ የህብረተሰብ ክፍል እና የጸጥታ ኃይሎች የተቀናጀ ርብርብ መለስተኛ ጉዳት ቢያስከትልም ሴራው ግን ከሽፏ ብለዋል፡፡በኦሮሚያ ክልል በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለው የተቀናጀ ዘመቻም ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው ያመለከቱት።ዘመቻው በፀረ ሽብርና በፀረ ሽብር ዘመቻ ኮማንዶ የታገዘ በመሆኑ ከፍተኛ ውጤት እየመጣ ነው ብለዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa