YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው አሰራጭተዋል ብሎ የተጠረጠራቸውን የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር ጨምሮ 4 አባላቱን አገደ፡፡

በፓርቲው የሥራ ኃላፊዎችና በአባላቱ ላይ እግድ የጣለው የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ነው፡፡ግለሰቦቹ የሳምንት ሥራ መከታተያ ቅፅ በሚል ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው ግንቦት 2፣ 2014 በብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የዋትስ አፕ ግሩፕ ላይ በመላክ ተጠናክረው መታገዳቸው ሸገር ከፓርቲው ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴውም ከትናንት በስትያ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በጉዳዩ ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ሰነዱ ፍፁም ስህተት እና የፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሂደት ዲሞክራሲያዊነትን የሚያቀጭጭ ብሎታል በውሳኔው፡፡በመሆኑም ሰነዱን አዘጋጅተዋል ተብለው የተጠረጠሩት 4 የፓርቲው አባላት በሰነዱ ላይ ያላቸውን ተሳትፎና የህግ ጥሰታቸው ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለፓርቲው ህገ ደንብ ትርጉምና ዲሲፕሊን ኮሚቴ ተመርቷል ተብሏል፡፡

ጉዳዩ በኮሚቴው ተመርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስም ፡-

• የኢዜማ የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊው አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ
• የፋይናንስ መምሪያ ሀላፊው አቶ አንድነት ሽፈራሁ
• የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደና
• አባል የሆኑት አቶ ኢዮብ መሳፍንት ከሀላፊነታቸው ለጊዜው እንዲታገዱ መወሰኑን ሸገር ራዲዮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የዩኤኢ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ!

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡የአቡ ዳቢው ልዑል አልጋ ወራሽ፤ ወንድማቸው ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ ትናንት አርብ ማረፋቸውን ተከትሎ ነው የዩኤኢ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት፡፡የሃገሪቱ ጠቅላይ ምክር ቤት ነው ሼክ መሃመድን ፕሬዝዳንት አድርጎ የመረጠው፡፡ ሼክ መሃመድ ምክር ቤቱ እምነት አድሮበት ለሰጣቸው ትልቅ ኃላፊነት አመስግነዋል፡፡ሼክ መሃመድ የዩኤኢ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ አዛዥ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቼ

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል። 🍎
👉 የሪህ መድኀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
👉 ለመፍትሔ ሥራይ
👉 ፍቅር ለነሳው ለመስተፋቅር። 🍒
👉 ገንዘብ አልገባ ለሚለው ለሚበተንበት።
👉 ለአስም ለሳይነስ ።
👉 ለአይነጥላ ለገርጋሪ።
👉 ለስንፈተወሲብ ለሚቸኩልበት።
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ ።
👉 ለእራስ ሕመም።
👉እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶች እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱ እዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
የሚፈልጉትን መድኀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል። 🥒

ለበለጠ መረጃ

አድራሻ ባህርዳር ፦ቀበሌ 11 🫑
☎️ 0917040506
📞 0912718883
ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
ለጤናወ መፍትሄ የሚፈልጉትን ለማግኔት
🌿 ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ 🌱
🩺
👇
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት እና ለሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ የክብር ዶክትሬት ሰጠ!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና እና ለጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ የክብር ዶክትሬት ሰጠ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፤ በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደው መርሃ ግብር ለተሸላሚቹ የክብር ዶክትሬቱን አበርክተዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት ዶክተር አኪንውሚ አዴሲና በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ በልማትና ሌሎችም ተግባራት የላቀ ሚና የተወጡ ናቸው።እንደ ኢዜአ ዘገባ የአፍሪካ ልማት ባንክ 8ኛው ፕሬዚዳንት በመሆን እየመሩ ያሉት አዴሲና በአህጉሪቷ የድህነት ቅናሳ፣ የትምህርት መስፋፋት፣ የስራ ፈጠራ እና ሌሎችም ተግባራት ላይ ውጤታማ ስራ ማከናወናቸው ይታወቃል።በመሆኑም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለእኒህ ታላቅ ባለውለታ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲቪል ስራዎች ግንባታ ስኬታማነት ሃላፊነታቸውን በብቃት የተወጡ ናቸው።በግድቡ ግንባታ ስኬት የላቀ ሚና ለነበራቸው ለእኒህ ታላቅ ባለውለታ ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት ለውጭ አገር ዜጎች ዲጂታል መታወቂያ ሊሰጥ እንደሆነ ሪፖርተር ዘግቧል። የውጭ ዜጎች ዲጂታል መታወቂያ መያዛቸው ግን ዜጎች የሚያገኟቸውን አገልግሎቶች ሁሉ እንዲያገኙ እንደማያስችላቸው የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተናግሯል። መንግሥት ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት የሚያስችለውን ሕግ ያረቀቀ ሲሆን፣ ሕጉ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አገልግሎት ሲሰጡ ተገልጋዮች ዲጂታል መታወቂያ ያላቸው መሆኑን እንዲያረጋግጡ ያስገድዳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የመንግሥት የፕሮፎርማ ግዥ ከመጪው በጀት ዓመት አንስቶ በግዥ ካርድ ሊሆን ነው!

የፌዴራል በጀት ተጠቃሚ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከመጪው በጀት ዓመት አንስቶ የፕሮፎርማ ግዥ የሚፈጽሙት፣ መንግሥት ባዘጋጀው የግዥ ካርድ ሊሆን ነው፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ከሰኔ ወር ጀምሮ የግዥ ካርዱን ወደ ሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ማሠራጨት የሚጀምር ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዕቃ አቅራቢዎች የክፍያ መሣሪያ (POS Machine) በነፃ ያቀርባል፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጋራ ያዘጋጁት የመንግሥት ግዥ ካርድ፣ ባንኩ በመሥሪያ ቤቱ ስም የሚያዘጋጀውና በፕሮፎርማ ለሚፈጸሙ ወይም ሌሎች ጥቃቅን ግዥዎች የሚውል ነው፡፡ ይህ ካርድ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር ሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች የፕሮፎርማ ግዥዎችን የሚፈጽሙት በግዥ ካርድ ብቻ እንደሚሆን፣ በገንዘብ ሚኒስቴር የትሬዠሪ ዳይሬክተር ወ/ሮ ነጠሩ ወንድወሰን ተናግረዋል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢሰመኮ በሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበው ገለጸ!

በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግሥት ኃይሎች መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም አልፎ አልፎም ግጭቶች ሪፖርት መደረጋቸው እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።የነዚህ ውጥረቶች መባባስና ይህንንም የሚያጋግሉ ትርክቶች በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋትን ደቅኗል ብሏል ኢሰመኮ በዛሬው ዕለት ግንቦት 7፣ 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ።

በተለይም አገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ ሌላ ጦርነትም ሆነ ግጭት መሸከም እንደማትችል አፅንኦት ሰጥቷል።ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጣው የዋጋ ግሽበት ፣ የመሠረታዊ አቅርቦቶች እጥረትና ከሰሜን ኢትዮጵያ ሰፊ አካባቢዎች የሚደረጉ የምርት እንቅስቃሴዎች መቋረጣቸው፣ እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው ሰብዓዊ ፍላጎቶችም የሃገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን በእጅጉ ጎድተውታል ብሏል።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ቀጣይ ግጭት እና ጦርነት የሚያስከፍለው በዋጋ የማይገመት ነው ያለው መግለጫው ሲቪል ህዝቦችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳ እና ተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊ ህግ ጥሰቶችን እንደሚያስከትልም አጽንኦት ሰጥቷል።

በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ ኃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ለአስራ ስምንት ወራት የዘለቀው ጦርነት መቋጫ ሊሆን ይችላል የሚል ተስፋን ዘርቶ የነበረ ቢሆንም ከሰሞኑ ዳግም ጦርነት ይከሰት ይሆን የሚሉ ፍንጮች ጥያቄ ፈጥረዋል።

ሙሉ ዘገባው: https://bbc.in/3woveHL

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በደስታ መግለጫቸው፥ ከፕሬዚዳንት ሞሀመድ ጋር ለኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ በሆኑ ሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

በሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሰፊ የድምፅ ልዩነት ያሸነፉት ሀሰን ሼክ መሃመድ ምርጫው በተጠናቀቀ ጥቂት ሰአታት ውስጥ 10ኛው የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

ለሁለት ዓመታት የተራዘመው የሶማሊያ ምርጫ በትላንትናው እለት ተካሂዶ አገሪቱን ለቀጣይ 4 አመታት የሚመሩት ሀሰን ሼክ መሃመድ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በ3ኛው ዙር 328 ድምፅ ያለው የሶማሊያ ፓርላማ ባደረገው ምርጫ ሀሰን ሼክ መሃመድ በስልጣን ላይ ያሉትን መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆን ካጠቃላዩ ድምፅ የ214ቱን በማግኘት ነው ለማሸነፍ የበቁት።

የሶማሊያው ተመራጭ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ ከዚህ ከቀም በፈረንጆቹ ከ2012 እስከ 2017 ሶማሊያን በፕሬዝዳንትነት መርተው እንደነበረ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው÷በትግራይ እና አፋር ክልሎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚሰራጨው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት የሰብዓዊ እርዳታ የያዙ ተጨማሪ 85 የጭነት ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን ነው የገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 130 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እያቀኑ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ይህም በተያዘነው የፈረንጆቹ ዓመት ወደ መቀሌ ከተጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳታ በመጠን ትልቁ መሆኑ ተመላክቷል፡፡በተመሳሳይ በሰሜን አፋር አካባቢዎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች በሚቀጥሉት ቀናት በዓለም የምግብ ፕሮግም የተዘጋጀው የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚሰራጭ ተጠቁሟል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ አሽከርካሪዎች በራሳቸው ፈቃድ ከግማሽ በላይ ዋጋ ጨምረዋል!

ሰሞኑን የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ አሽከርካሪዎች በራሳቸው ፈቃድ ከፍተኛ የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ አድርገዋል።

የተደረገው ጭማሪ በመንግሥት የተደረገ ሳይሆን አሽከርካሪዎች በራሳቸው ያደረጉት ሲሆን፣ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን በሙሉ ለከፍተኛና አላስፈላጊ ወጪ እንዲሁም እንግልት የሚዳርግ ስለመሆኑ አዲስ ማለዳ ከተጓዦች ሰምቻለሁ ብላለች።

@Yenetube @Fikerassefa
አርቲስት አብርሃም በላይነህ በሴት ጓደኛው ሞት ተጠርጥሮ መታሰሩን ፊደል ፖስት ሰምቷል።

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ቦሌ ሚካአል ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ የጤና ባለሙያ የሆነችው ከ 26 አስከ 28 እድሜዋ የሚገመተወ የሴት ጓደኛው ራሷን ከፎቅ ጥላ ሒወቷን በማጥፋቷ ሻለየ በሚለው ዘፈኑ የሚታወቀው አርቲስት አብርሃም በላይነህ ፖሊስ ለምርመራ እንዳሰረው ፊደል ፖስት ሰምቷል።

Via Fidel Post
@Yenetube @Fikerassefa
የአማራ ክልል ዜጎች የጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቀረበ!

ከግንቦት 9/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው በሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት በመገኘት እንዲያስመዘግብ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አሳስቧል።

የቢሮው ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው፤ የጦር መሳሪያ ምዝገባው የአማራን ሕዝብ ደኅንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል፡፡

አሸባሪው ትሕነግ የጥፋት መንገድ ተጋሪዎች የአማራን ሕዝብ አንድነት ለመሸርሸር በብሔርና በሃይማኖት ሽፋን የተለያዩ አጀንዳዎችን እየዘረጉ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው የሽብር ቡድኑ አሁንም ወደ ዳግም ጦርነት ለመግባት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ በተጨባጭ እያሳየ ነው ብለዋል።

የጥፋት ኃይሉን ዓላማ ለማክሸፍ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይል በተጨማሪ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ያለው ምዝገባ ካካሔደ በኋላ የተደራጀ ሥልጠና እንዲወስድም ይደረጋል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ባደረጉት ክትትል በአንድ የእንጨት ስራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ከ3 ሺህ በላይ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሁለቱ ተቋማት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አዲሱ ገበያ ቀለበት መንገድ አካባቢ በሚገኝ አንድ የእንጨት ስራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ጥይት ስለመኖሩ ከህዝብ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ሲከታተሉ ቆይተው ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ/ም በህግ አግባብ በድርጅቱ ውስጥ ባደረጉት ብርበራ በ4 ማዳበሪያ ተጠቅልሎ በድብቅ የተቀመጠ 1ሺህ 98 የብሬን እና 2ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተይዟል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ሊያስከትል የሚችለውን ሃገራዊ ጉዳት ተገንዝቦ የዚህ ህገ ወጥ ተግባር ተሳታፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ እየሰጠ ያለውን ጥቆማ እና መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ም/ኢንስፔክተር እመቤት ሃብታሙ አ/አ ፖሊስ
@Yenetube @Fikerassefa
የሩሲያው ፕሬዝዳንት የስዊድን እና የፊንላንድ ኔቶን መቀላቀል "ስጋታችን አይደለም" አሉ!

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፒቲን ስዊድን እና ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ)ን ቢቀላቀሉም ለሀገራቸው ስጋት እንደማይሆን አስታወቁ፡፡ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት ከሰሞኑ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ካሳወቁ በኋላ ነው፡፡

ከሰሞኑ የፊንላንድ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሀገራቸው ኔቶን መቀላቀል እንዳለባት ድጋፍ መስጠታቸውን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሃሳቦች እየተሰነዘሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡እስካሁን በፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን የመቀላቀል ሂደት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የሩሲያ እና የቱርክ ፕሬዝዳንቶች ናቸው፡፡

ቭላድሚር ፑቲን ሁለቱ ሀገራት ድርጅቱን መቀላቀላቸው ለሩሲያ ስጋት ባይሆንም ምላሽ ሊያሰጥ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡የፖለቲካ ሰዎች የስዊድን እና ፊንላንድ ኔቶን መቀላቀል አሁን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ወደ ሌሎች ሀገራት ሊያዛምተው እንደሚችል እየተነበዩ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ ግን የሩሲያው ፕሬዝዳንት የሀገራቱን ወደ ኔቶ አባልነት የመቅረብ ሂደት በቀጥታ አልተቃወሙም፡፡

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
1
በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ ዓረቢያ የመመለስ ስራ 1 ሺህ 40 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመለሾች ውስጥም 303 ሴቶች ሲሆኑ÷ 90 የሚሆኑት ደግሞ ህጻናትና መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጁላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 23 ሺህ 640 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👉 ለጤናው ቅድሚያ እንሰጣለን


መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን
በተሰጠንና ባገኘነው ልምድና ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሔወችን እንሰጣለን።፦

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉 የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው
ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላሳይነካ
ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛ እንዳይተካ አድርጎ የፈውሳል።
👉 የእሪህ መድአኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉 ገብያ ለገረገረው ለገብያ
👉 ለመፍትሔ ስራይ
👉 ለአይነ ጥላ (ለገርጋሪ)
👉 ለስንፈተ ወሲቢ ለሚቸኩልበት
👉 የአስም (የሳይነስ)
👉 ለማይስማሙ (ለመስተፋቅር)
👉 ገንዘብ ለሚበተንበት
👉 ስራ አልሳካለት ላለ
👉 ለቡዳ
👉 ለሚጥል በሽታ
👉 ለማህጸን እንፌክሽን
👉 ህይወቱ ለሚመሰቃቀልበት
👉 ለአዕምሮ ጭንቀት
👉 ሌሊት ለሚሸና
👉 ለነገረ በትን
👉 ለሆድ ሀህመም
👉 ለስኳር መቀነሻ
👉 ለነርብ
👉 እራሱን ለሚያመው

እነዚህንና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን

መዳኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈጽማሉ

አድራሻ
ባህርዳር ቀበሌ 11
ዲያስፖራ በኮብሉ

ለበለጠ መረጃ
☎️ 0917040506
📞 0912718883

ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
የሚፈልጉትን ለማግኔት ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ
🩺
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe👇
👇
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
የአሜሪካ ወታደሮች በሶማሊያ እንዲሰማሩ ጆ ባይደን ወሰኑ!

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሳቸው በፊት በነበሩት ዶናልድ ትራምፕ የተወሰነዉን ውሳኔ በመቀልበስ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቅደዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ሊመለሱ ይችላሉ ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ በአልሸባብ የታጣቂ ቡድን መሪዎች ላይ ዒላማ ለማድረግ ከፔንታጎን የቀረበላቸዉን ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸዉን በፊርማቸውን አኑረዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ የሆነችዉ አድሪያን ዋትሰን እንደተናገሩት "እንደገና ለማስጀመር የወሰነው የኃይላችንን ደህንነት እና ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ ብሎም ለአጋሮቻችን ቀልጣፋ ድጋፍ ለመስጠት ነው" ብለዋል።

አክለዉም "በአልሸባብ ላይ የበለጠ ውጤታማ ትግል" ለማድረግ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡አሜሪካ ይህንን ዉሳኔ ያሳለፈችዉ የሶማሊያ የፓርላማ አባላት እሁድ እለት አዲሱን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድን መምረጣቸዉን ተከትሎ ነዉ፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በሕወሃት ኩባንያዎች በኢፈርት፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኡንጂነሪንግና ትራንስ ኢትዮጵያ ላይ የመሠረተው ክስ ዛሬ በችሎት ለተከሳሾቹ እንደተነበበ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ክሱ ኩባንያዎቹ ሕወሃት ፌደራል መንግሥቱን ከሥልጣን አስወግዳለሁ ብሎ የተነሳለትን ዓላማ ለማስፈጸም በከባድ ተሽከርካሪዎቻቸው ለትግራይ ወታደራዊ ዕዝ የሰው ኃይል፣ ነዳጅ፣ ጦር መሳሪያ እና ስንቅ እንዳጓጓዙ ይገልጣል። ዓቃቤ ሕግ የኩባንያዎቹን የተናጥል ወንጀሎች ጭምር ዘርዝሮ አቅርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa