የአፍሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች ከሜዳዉ ዉጭ እንዲያደርግ ወሳኔ አሳልፏል፡፡
ከስድስት ወራት በፊት ኢትዮጵያ በሜዳዋ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል እና የካፍን ደረጃ የሚያሟላ ስታዲየም የለትም በሚል በሜዳዋ ማድረግ የሚገባትን ጨዋታዎች በገለልተኛ ሜዳ ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል።
ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላም በስታዲየሞቹ የተሻሻለ ነገር ባለመኖሩ ምክንያት ኢትዮጵያ በድጋሚ በሜዳዋ እንዳትጫወት ካፍ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በዚህ ወር መገባደጃ ላይ ለሚደረገዉ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳዉ እንዲጫወት እና የካፍ አመራሮችን ዝቅተኛ መስፈርት እንኳን ለማሟላት ርብርብ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካ መቅረቱ ታዉቋል።
በዚህም የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን(ካፍ) ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን በሜዳዋ እንድትጫወት ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን አሳውቋል፡፡
በውሳኔው መሰረትም እስከ ግንቦት 4 ድረስ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሜዳው ውጭ የሚጫወትበትን ሜዳ ይፋ እንዲያደርግ ካፍ በላከው ደብዳቤ ማስታወቁን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

በኦሮሚያ ክልል በእስር ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሰራተኞች ተለቀቁ!
በኦሮሚያ ክልል በእስር ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሰራተኞች መለቀቃቸው ተገለፀ።የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኦሮሚያ ክልል ያሉት ሰባት ቅርንጫፎቹ ከሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮመዘጋታቸውን እና ሰራተኞቹ መታሰራቸውን መግለጹ ይታወሳል።
የምርት ገበያው ገበያው የኮርፖሬት ኮሙንኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ነጻነት ተስፋዬ ለአል ዐይን አማርኛ ከአንድ ሳምንት በፊት “በጊንቢ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ በደሌ፣ ቡሌሆራ፣ ነቀምት እና መቱ ያሉ የምርት ገበያ ማዕከሎች ከሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ፖሊስ መታሸጋቸውን ገልጸው ነበር።እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ የምርት ገበያው መጋዝኖች ይሰሩ የነበሩ “58 አመራሮች እና ሰራተኞች በእስር ላይ ናቸው” ማለታቸውም ይታወሳል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:
https://am.al-ain.com/article/ethiopian-commodity-exchange-announces-release-of-detained-employees-of-branches-in-oromia

የጉህዴን ታጣቂዎች እጃቸውን ለመንግስት እየሰጡ በመሆናቸው በመተከል አንፃራዊ ሰላም መኖሩ ተገለፀ!
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የጉህዴን ታጣቂዎች እጃቸውን ለመንግስት እየሰጡ መሆናቸውን ተከትሎ በአካባቢው ሰላም እየሰፈነ መሆኑን በመተከል ዞን የድባጤ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ገልጿል።
በታጣቂዎች የተነሳ በዞኑ በተደጋጋሚ የፀጥታ ችግሮች ያጋጥሙ የነበረ ሲሆን በቅርቡ መንግስት ያደረገውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ታጣቂዎች እጃቸውን እየሰጡ እንደሚገኝ የድባጤ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አ/ ቶ አዳሙ ያረጋል ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ። ያለውን የሰላም ሁኔታ በተመለከተ የድባጤ ከተማ ነዋሪዎችን ይህንኑ ለብስራት ራዲዮ አረጋግጠዋል።
እንደ ነዋሪዎች ገለፃ በአሁኑ ወቅት ድባጤ ከተማ ሰላም ናት ። ከከተማ አቅራቢያ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ቢኖሩም መከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ ሀይሎች በመኖራቸው ስጋት የለብንም ብለዋል ። ነዋሪዎች አክለውም ከአከባቢው ተፈናቅለው በድባጤ ከተማ ተጠልለው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ተናግረዋል።
በአካባቢው ከመከላከያ ሰራዊት በተጨማሪ የፀጥታ ሀይሎች ሰላም የማስከበር ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ ።ከትናንት በስቲያ የተሀድሶ ስልጠና የጨረሱ 887 የጉህዴን ታጣቂዎች ወደ ልማት ሊገቡ እንደሆነ ተገልጿል።
Via Bisrat FM

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( ኢዜማ ) በመጪው ሰኔ 11 እና 12 ቀን፣ 2014 ዓ. ም አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን እንደሚያደርግ ዐስታወቀ።
ጉባኤው በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት የፖርቲውን መሪ እና ምክትል መሪ እንደሚሰይምም ፓርቲው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ለፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የሰጠው የሦስት ዓመታት የሥልጣን ጊዜ በመጠናቀቁ ሰኔ ላይ በሚደረገው አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ማንኛውም የፓርቲው አባል የመወዳደር እድል ክፍት ሆኖለት መሪዎቹን በምርጫ እንደሚሰይም ፓርቲው ይፋ አድርጓል።
የፓርቲው የመሪዎች አስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሥዩም መንገሻ የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች የምርጫ ሂደት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሠራር ውስጥ አዲስ በጎ ባህል የሚያለማምድ መሆኑን ተናግረዋል።"በኢትዮጵያ የፓርቲዎች ታሪክ ፓርቲዎች በውስጣቸው የሚያደርጉትን ምርጫ በተመለከተ በውድድር፣ ሀሳባቸውን ገልፀው ፣ የምርጫ ቅስቀሳ አድርገው እንዲመረጡ ያስፈልጋል። ይህን ልምምድ ፓርቲዎች በራሳቸው ውስጥ ሊያደርጉት ይገባል።
ማሸነፍ መሸነፍ፣ ኃላፊነት የመስጠትና የማስረከብ ልምምድ በፓርቲዎች ውስጥ ሊለመድ ይገባል።ኢዜማ ይህ በኢትዮጵያ ፓርቲዎች ውስጥ ባህል እንዲሆን ይፈልጋል" ብለዋል።የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሥርዓትን አሟልቶ መሪዎቹን እንደሚመርጥ የተናገረው ኢዜማ የፓርቲውን መሪ እና ምክትል መሪ ለመምረጥ ሁለት ችግሮች እንደገጠሙት ገልጿል።
[DW]

መንግሥት የአገሪቱን ወጪ ከገቢዋ ጋር ለማመጣጠን የንብረትና ኤክሳይስ ታክስን ተግባራዊ እንደሚያደርግ እና የተጨማሪ እሴት ታክስን እንደሚያሻሽል ዛሬ ባወጣው የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም መግለጫ አስታውቋል። ሃብት ለመቆጠብ ለሌላ ጊዜ የሚተላለፉ የመንግሥት ፕሮጀክቶች እንደሚኖሩም ተገልጧል። የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አሃዝ ለማውረድ የተደረገው ጥረት በአገራዊና ዓለማቀፋዊ ክስተቶች ሳቢያ እንዳልተሳካ የገለጠው መንግሥት፣ ወደፊትም ግሽበቱን ለመቆጣጠር ተጨማሪ ርምጃዎችን እወስዳለሁ ብሏል።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication

የቻይናና ኢትዮጵያ መንግሥትታት የኢንቨስትመንት ስምምነት ሊፈጽሙ ነው!
የኢትዮጵያና የቻይና መንግሥታት፣ የቻይና ባለሀብቶች በተለየ ሁኔታ በኢትዮጵያ መዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነት ሊፈራረሙ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ነገ ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በሁለቱ መንግሥታት መካከል ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ስምምነት፣ የቻይና መንግሥት ባለሀብቶቹ በኢትዮጵያ የተለያዩ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚገፋና ኢትዮጵያም ለእነዚህ ባለሀብቶች አማራጮችን እንድታቀርብ የሚያስገድድ ነው፡፡
የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ እንደ ኬብልና ብረት ብረት ምርት እንዲሁም ግብርና ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውን ለሪፖርተር የገለጹት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሔኖክ ሰሎሞን፣ ኢትዮጵያ ከአገሮች ጋር ‹‹ልዩ የሆነ›› የመግባቢያ ሰነድ ሲፈረም የመጀመሪያው ባይሆንም፣ ኢትዮጵያ የገባቻቸው እንዲህ ዓይነት ስምምነቶች ጥቂት ናቸው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ከሚገኝባቸው ቀዳሚ አገሮች መካከል ቻይና በመሆኗ በስምምነት የታገዘ የኢንቨስትመንት ሥራ መኖሩ በቻይና በኩል ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጠው እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://www.ethiopianreporter.com/article/25468

አንጋፋዋ የአልጀዚራ የፍልስጤም ወኪል ጋዜጠኛ ሺረን አቡ አክሌህ በእስራዔል የፀጥታ ሀይሎች መገደሏን የዜና አውታሩ አስታወቀ፡፡
የ51 አመቷ አክሌህ ዌስትባንክ በሚገኝ ጄኒን በተሰኘ የስደተኞች መጠሊያ ጣቢያ በቀረፃ ላይ በነበረችበት ወቅት በእስራዔል የፀጥታ ሀይሎች ተተኩሶ መገደሏን የፍልስጠየም ጤና ሚኒስቴር አረጋግጦልኛል ሲል አልጀዚራ አስታውቋል፡፡
የጋዜጠኛዋን ግድያ ባወጣው መግለጫ ያወገዘው አልጀዚራ ዓለም አቀፉ ማህረሰብም ይህን ድርጊት እንዲወግዝ ጠይቋል፡፡የግድያው ፈፃሚዎችም በህግ ይጠየቁልኝ ብሏል፡፡የአልጀዚራ መግለጫ አክሌህ ብቻ ሳትሆን ሌላም የጣቢው ባልደረባ(ፕሮዲዩሰር) አሊ አለ-ሳሙዲ ከጀርባው በጥይት መመታቱን ገልፆል፡፡
ይሁንና ሳሙዲ አሁን ህክምናውን በመከታተል ይገኛል፤ በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡የጋዜጠኛዋን ግድያ የፍልስጤም፣ የኳታር መንግስትም በፅኑ አውግዘውታል፡፡ምንም እንኳን አልጀዚራ ጋዜጠኛ አክሌህ በእስራዔል ወታደሮች መገደሏን ይዘግብ እንጂ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የእስራአየል መንግስት የሰጠው ምላሽ የለም፡፡
✍Asham

ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ክስ ላይ በቨርቹዋል ቴክኖሎጂ የመከላከያ ምስክርነታቸው እንዲሰማ ታዘው የነበሩት የቀድሞ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎችም ትክክለኛ የመኖሪያ አድራሻቸው ባለመታወቁ አድራሻቸው ተጣርቶ እንዲቀርብ ታዘዘ።
ትዛዙን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትጰልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
በመጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ/ም በነበረ የችሎት ቀጠሮ የቀድሞ የኢፌድሪ የብረታብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) ዋና ዳሪክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በተከሰሱበት የዕርሻ መሳሪያ ግዢና የመርከብ ግዢ የሙስና ክስ ላይ በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት የቀድሞ ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ: የቀድሞ የጀርመን አንባሳደር በአሁን ወቅት በአሜሪካ የሚገኙች ፍስሀ አስገዶም : የኢኮኖሚ ጉዳዮች ካውንስለር ካሳና የቀድሞ የፖላንድ አንባሳደርንም ጨምሮ ከዛሬ ግንቦት 3 ቀን እስከ ግንቦት 5 ቀን ድረስ ባሉበት ሀገር ሆነው በቨርቹዋል ቴክኖሎጂ የመከላከያ ምስክርነታቸው እንዲሰማ ትዛዝ ተሰቶ ነበር።
ሆኖም በዛሬው የችሎት ቀጠሮ በውጭ ሀገር የሚገኙት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎችም የመከላከያ ምስክሮች ትክክለኛ የመኖሪያ አድራሻቸው አለመመታወቁን ፍርድ ቤቱ ተገልጿል።
በጠበቃ ዘረሰናይ በኩል ግን የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አድራሻ ጀርመን ወይም አሜሪካ ሊሆን እንደሚችል በቃል ገልጿል።
በተጨማሪም ጠበቃ ዘረሰናይ የአቶ ኃይለማርያም ተወካይ በሀዋሳ እንደሚኖር በማብራራት አቶ ኃይለማርያም ለምስክርነት ዝግጁ እንዲሆኑ ለተወካያቸው እንደሚያሳውቀው አስተያየት ሰቷል።
በፍርድ ቤቱ በኩል ግን የምስክሮቹ ትክክለኛ መገኛ (የመኖሪያ) አድራሻ አለመገለጹ ተከትሎ ምስክርነታቸውን ለመስማት እንደሚያስቸግር በመጠቆም ባሉበት ቦታ የምስክሮቹን የቨርቹዋል ቴክኖሎጂያቸውን ክትትል ማን ያደርጋል የሚል ጥያቄ ተነስቷል።
ጠበቃ ዘረሰናይ በበኩሉ በፍርድ ቤቱ በኩል የኢንተርኔት ቴክኖሎጂው ከተመቻቸ ምስክሮቹ በማንኛውም ጊዜ በበየነ መረብ ስብሰባ እንደሚጠቀሙት ሁሉ የመከላከያ ምስክርነታቸው ሊሰማ እንደሚችል እና መገኛ አድራሻቸውንም ማጣራት እንደሚቻል ሀሳብ ተሰቷል።
ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በበኩላቸው ኢትዮጲያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የኢንተር ፖል ስምምነት እንዳላት በመጥቀስ በዚህ ስምምነት መሰረት ለፀረ ሽብር በማስረጃ የሚፈለጉ ሰዎች ተፈልገው እንዲሰጡ ይደረጋል ያሉ ሲሆን በዚህ መልኩ መገኛቸው ተፈልጎ እንዲሰጡ ቢደረግ የሚል ሀሳብ ሰንዝረዋል።
በዚህ ደረጃ ከፖሊስ ጋር የሚደረግ ስምምነት እንጂ ከፍርድ ቤት ጋር የተደረገ የኢንተርፖል ስምምነት አለመኖሩን የችሎቱ ዳኞች አብራርተዋል።
የመከላከያ ምስክሮቹ ምስክርነታቸው ሲጀመር ወደ አፈጻጻም ሲገባ ኢንተርኔት ቢቋረጥ: የሚጠየቁትን ጥያቄ ሳይመልሱ ትተው ቢሄዱ እንኳ የምስክር አሰማም ሂደቱን መቆጣጠር የሚያስችል እንዳይሆን ያደርጋል ሲሉ ስጋታቸውን በሀሳብ ደረጃ የችሎቱ ዳኞች ገልጸዋል።
ጠበቃ ዘረሰናይ የምስክሮቹን መገኛ አድራሻ እና ሰዓት አጣርተን እንቀርባለን ሲል ምላሽ ሰቷል።
ሆኖም የምስክር አሰማም በፍርድ ቤቱ በኩል ስርዓትና አካሔድ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን በዚህ አግባብ ሊኬድና ጥንቃቄ መደረግ ስላለበት እያንዳንዱ ምስክር መገኛ አድራሻቸው በምን አግባብ እና በየትኛው ሰዓት ይገኛሉ የሚለውን ግልጽ ሆኖ ተጣርቶ ትዛዝ መሰጠት እንዳለበት በችሎቱ ዳኞች ተብራርቷል።
በዚህም መሰረት በውጭ ሀገር የሚገኙት የሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው መከላከያ ምስክሮች ትክክለኛ አድራሻ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትዛዝ ሰተዋል።
በዚሁ መዝገብ በአካል ቀርበው ለመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩ በመከላከያ ሚኒስቴር ስር የሚገኙ አራት ምስክሮችን በተመለከተ ትዛዝ ወቶ በመከላከያ ሚኒስቴር በኩል ምንም አይነት ምላሽ ባለመቅረቡ ትዛዙ በድጋሚ ወጪ ተደርጎ በፌደራል ፖሊስ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ታዟል።
በቨርቹዋል ቴክኖሎጂ ቀርበው በመከላከያ ምስክርነታቸው እንዲሰማ ትክክለኛ መገኛ አድራሻቸው ተጣርቶ እንዲቀርብ የታዘዙ ምስክሮችን የአድራሻ ውጤት ለመጠባበቅ እንዲሁም በድጋሚ መጥሪያ ደርሷቸው በአካል እንዲቀርቡ የታዘዙ አራት ምስክሮችን የመከላከያ ምስክርነትታቸውን ቃል ለመስማት ከሰኔ 20 ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷል።
በሌላ በኩል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸው በጥር 23 ቀን ትዛዝ የወጣባቸው የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን በተመለከተ በምን አግባብ ይቀርባሉ የሚለውም በዚሁ ተመሳሳይ ቀጠሮ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትዛዝ ተሰቷል።
ትዛዙን ተከትሎ ጠበቃ ዘረሰናይ ከዶ/ር ወርቅነል ጋር አብረዋቸው በሚሰሩት በቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር በአቶ ሲራጅ ፈጌሳ በኩል አጣርቶ ምላሽ እንደሚያቀርብ ገልጿል።
በዚህ በዛሬው ቀጠሮ ከዓቃቢህግ በኩል የቀረበ ተወካይ አልነበረም።
Via Tarik Adugna

1005 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!
ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1005 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የተቻለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 51 ህጻናት 319 ሴቶችና 635 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡ እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 20,900 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከኢፌዴሪ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ አመልክቷል፡፡

Forwarded from YeneTube
ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቼ
መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**
የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም
👉የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል። 🍎
👉 የሪህ መድኀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
👉 ለመፍትሔ ሥራይ
👉 ፍቅር ለነሳው ለመስተፋቅር። 🍒
👉 ገንዘብ አልገባ ለሚለው ለሚበተንበት።
👉 ለአስም ለሳይነስ ።
👉 ለአይነጥላ ለገርጋሪ።
👉 ለስንፈተወሲብ ለሚቸኩልበት።
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ ።
👉 ለእራስ ሕመም።
👉እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶች እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱ እዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
የሚፈልጉትን መድኀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል። 🥒
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ ባህርዳር ፦ቀበሌ 11 🫑
☎️ 0917040506
📞 0912718883
ይደውሉ👍
መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
ለጤናወ መፍትሄ የሚፈልጉትን ለማግኔት
🌿 ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ 🌱
🩺
👇
https://tttttt.me/meritibe

ኢሰመኮ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በእጅጉ መባባሱን ለፓርላማው ባቀረበው የ9 ወራት ሪፖርት መግለጡን የዋዜማ ሪፖርተር ዘግቧል።
ጸጥታ ኃይሎች የሚፈጽሙት ከፍርድ ውጭ ግድያ፣ ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀም፣ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ የዘፈቀደ እስር፣ የተራዘመ የቅድመ-ክስ እስር፣ ባንዳንድ የእስር ቦታዎች ያለ ኢሰብዓዊ አያያዝ፣ የሕጻናት ሕገወጥ እስር እና ጋዜጠኞችን፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችንና የማኅበረሰብ አንቂዎችን አስገድዶ መሰወር ተደጋግሞ መከሰቱን ኮሚሽኑ ገልጧል። ከሰሜኑ ጦርነት፣ ከብሄር ማንነት፣ ራስን በራስ ከማስተዳደር፣ ከአስተዳደር ወሰንና ከሐይማኖት ጋር የተያያዙ ግጭቶች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማስከተላቸውን ኮሚሽኑ ጨምሮ ጠቅሷል።

የመመሪያ ጥሰት በፈጸሙ 106 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ።
እርምጃ የተወሰደባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር (በፎቶ)⬆️
@YeneTube @FikerAssefa
እርምጃ የተወሰደባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር (በፎቶ)⬆️
@YeneTube @FikerAssefa
በጦርነት እና እገዳ ከሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል በተገለለችዉ ትግራይ አለቅጥ የናረዉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ የሕዝቡን ኑሮ እያቃወሰዉ መሆኑ ተዘገበ።
ዶይቸ ቨለ እንደዘገበዉ መቀሌ ዉስጥ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 5 ብር ይሸጥ የነበረዉ 50 ግራም ዳቦ (ፉርኖ) ሰሞኑን 8 ብር ገብቷል።የፉርኖ ዱቄት፣የጤፍ፣ የበርበሬና የመሰል የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምር ማኮሮኒና ፓስታን የመሳሰሉ የፋብሪካ ምርቶችን ገበያ ላይ ማግኘት ሲበዛ ከባድ ነዉ።የዚያኑ ያክል እዚያዉ ትግራይ የሚመረቱ እንደ ሽንኩርትና ቲማቲም የመሳሰሉ ማጣፈጫዎች ዋጋ ብዙ ለዉጥ አላሳየም።የከብትና የስጋ ዋጋ ግን ቀንሷል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት ለግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች እና ሁኔታዎች ላይ ጥናት እንዲደረግ አሳሰበ፡፡
ቋሚ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት የሰላም ሚኒስቴርን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ ከተመለከተ በኋላ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ነገዎ ሰላም ሚኒስቴር ባለፉት 20 እና 30 ዓመታት የነበሩ ግጭቶች ምንጮቻቸውን እና የአፈታት ሥርዓታቸውን በማጥናት ላይ ትኩረቱን ማሳረፍ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡
በኢትዮጵያ የተለያዩ ባሕላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶች መኖራቸውን ጠቁመው ÷ የግጭት አፈታቶቹ ምን ያህል ውጤት አምጥተዋል በሚለው ላይም ጥናት ሊካሄድ ይገባል ብለዋል፡፡
ተቋሙ በዘመናዊ አደረጃጀት ተልዕኮውን ለመፈጸም በሚያስችል ቁመና ላይ እንዳለ የተረዳ መሆኑን የጠቆመው ቋሚ ኮሚቴው÷ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት የመከታተያ ዘዴ በቴክኖሎጂ መደገፉ የሚበረታታ መሆኑን አንስቷል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ በበኩላቸው÷በተቋሙ አዲስ የተሠራው አደረጃጀት ዕውቀትን መሠረት ያደረገ እንደሆነ መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት መከላከል የሚያስችሉ ሥርዓቶችን ዘርግቶ እየሠራ መሆኑን ያነሱት አቶ ታዬ÷በግጭት አፈታት ዙሪያ ከክልሎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
ቋሚ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት የሰላም ሚኒስቴርን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ ከተመለከተ በኋላ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ነገዎ ሰላም ሚኒስቴር ባለፉት 20 እና 30 ዓመታት የነበሩ ግጭቶች ምንጮቻቸውን እና የአፈታት ሥርዓታቸውን በማጥናት ላይ ትኩረቱን ማሳረፍ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡
በኢትዮጵያ የተለያዩ ባሕላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶች መኖራቸውን ጠቁመው ÷ የግጭት አፈታቶቹ ምን ያህል ውጤት አምጥተዋል በሚለው ላይም ጥናት ሊካሄድ ይገባል ብለዋል፡፡
ተቋሙ በዘመናዊ አደረጃጀት ተልዕኮውን ለመፈጸም በሚያስችል ቁመና ላይ እንዳለ የተረዳ መሆኑን የጠቆመው ቋሚ ኮሚቴው÷ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት የመከታተያ ዘዴ በቴክኖሎጂ መደገፉ የሚበረታታ መሆኑን አንስቷል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ በበኩላቸው÷በተቋሙ አዲስ የተሠራው አደረጃጀት ዕውቀትን መሠረት ያደረገ እንደሆነ መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት መከላከል የሚያስችሉ ሥርዓቶችን ዘርግቶ እየሠራ መሆኑን ያነሱት አቶ ታዬ÷በግጭት አፈታት ዙሪያ ከክልሎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማስገኘቱ ተሰማ!
የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ አስገኘ።የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን ለዚህ ታሪካዊ ላሉት ስኬት እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።የቡና ምርት ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ ከምታቀርባቸው የግብርና ምርቶች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ ቀጥሏል።ሀገሪቱ በተለይም ወደ ቻይና የምትልከው የቡና ምርት በከፍተኛ መጠን አድጓል።
በፈረንጆቹ 2021 ዓመተ ምህረት ላይ ቻይና ከኢትዮጵያ ያስገባቸው የቡና ምርት መጠን ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ196 በመቶ አድጓል።በቅርቡ የኢትዮጵያን የቡና ምርት በቻይና ገበያ የበለጠ ለማስተዋወቅ በተዘጋጀ መድረክ ላይ የሀገሪቱ የቡና ማህበር እንዳስታወቀው፥ በቻይና ከትላልቅ ከተሞች እስከ መለስተኛ ከተሞች የቡና ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ዕድገት ያሳየ ሲሆን፥ ይህም ለኢትዮጵያ ቡና አምራቾች እና ላኪዎች ሰፊ የገበያ ዕድል መፈጠሩ ተመልክቷል።ሚኒስትሩ ባለፉት የበጀት ዓመቱ ወራት የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ምን ያህል የቡና መጠን ወደ ውጭ ተልኮ እንደሆነ አልጠቆሙም።
[FBC]

የትግራይ ህዝብ “ለመጨረሻው ምዕራፍ ትግል” እንዲዘጋጅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥሪ አቀረቡ!
የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ከማዕከላዊው መንግስት ጋር ችግሮችን በዲፕሎማሲ ለመፍታት ሲደረግ የነበረው ጥረት “ባለመሳካቱና የሰላም መንገድ በመዘጋቱ የትግራይን ሕዝብ ነፃነት ለማረጋገጥ” የክልሉ ህዝብ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀረቡ።
ደብረፅዮን በመቀሌ ሌሎች የሕወሃት አመራሮች ደግሞ በተለያዩ የትግራይ ዞኖች ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የትግራይ ህዝብ አሁን ያለበት የከፋ ስቃይ እንዲቀለበስና የትግራይ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ብለዋል።
“ኹሉም የፖለቲካ ችግር በሰላምና በዲፕሎማሲ እንደማይፈታ ብናውቅም አሁን የገባንበት ጦርነት ከመጀመሩ አስቀድመን እንዲሁም በጦርነቱ ወቅት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተናል” ብለዋል ደብረፅዮን በመቀሌ ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ።
በአለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸማጋይነት ጊዚያዊ ሥምምነት ተደርጎ ወደ ክልሉ እህል መድሀኒትና ሌሎች ድጋፎች እንዲገቡ ጥረት ብናደርግም እስከ አሁን ድረስ የተገኘው ድጋፍ ችግሩን ለማቃለል በቂ አይደለም ብለዋል።
መላክ ያለበትን መልዕክት ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ባለን የመገናኛ መንገድ አድርሰናል ያሉት ደብረፅዮን የሚመለከታቸው ያሏቸውን አካላት አልዘረዘሩም።
መንግስት የተኩስ አቁም በሚል ሽፋን የመሳሪያና የሰራዊት ማሰባሰብ ስራ ላይ ነው ሲሉ የከሰሱት ርዕሰ መስተዳድሩ የትግራይ ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚረጋገጠው የኀይል የበላይነትን በመያዝ ብቻ መሆኑን ለተሰብሳቢዎች አስረድተዋል።
ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር(ሞንጀሪኖ)፣ አለም ገብረሐዋድና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ነዋሪዎችን ያወያዩ ሲሆን ሕዝቡ ለመጨረሻው ምዕራፍ ትግል እንዲዘጋጅ መጠየቃቸውን ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርስ ሁኔታዎችን ባመቻችም ሕወሃት ራሱ ዕርዳታ በማስተጓጎልና ተጎራባች ክልሎችን በመውረር እንቅፋት መፍጠሩን ይናገራል። የትግራይ አማፅያን በቅርቡ ይዘውት ከነበረው የአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ለቀው መውጣታቸውን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንት የምዕራብ ዕዝ የመከላከያ ሰራዊትን በቦታው ተገኝተው ያበረታቱ ሲሆን ወታደራዊ ብቃቱን የሚያሳይ ትርዒትም መመልከታቸው ይታወሳል።