YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የጎንደር የገበያ ማዕከላት ዛሬ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል!

በጎንደር ከተማ ሰሞኑን በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የገበያ ማዕከላት ተዘግተው የሰነበቱ ሲሆን በዛሬው እለት ማዕከላቱ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ታውቋል።በከተማዋ በተፈጠረው ችግር ምክንያት የገበያ ማዕከላት በመዘጋታቸው ታይቶ የማይታወቅ የሸቀጦች ዋጋ ንረት ተከስቶ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በሁኔታው የተለያዩ ሸቀጦች በከፍተኛ ዋጋ ለገበያ ይቀርቡ የነበረ ሲሆን ለማሳያም ያክል አንዳንድ ነጋዴዎች የ አንድ ኪሎ ሽንኩርት ዋጋ ከ 60 ብር በላይ እየሸጡ እንደነበርና ህዝቡም አማራጭ በማጣቱ በቀረበለት የዋጋ ተመን ገዝቶ እየተጠቀመ መቆየቱን መረዳት ተችሏል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባቸሌት በኢትዮጵያ በቅርቡ በሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች ግጭት በትንሹ 30 ሰዎች በመሞታቸው ከልብ አዝኛለሁ ሲሉ ዛሬ በድርጅታቸው ድረ ገጽ በኩል ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በክስተቱ ላይ ገለልተኛ፣ ግልጽ እና ጥልቅ ምርመራ እንዲያደርግ የጠየቁት ባቸሌት፣ መንግሥት ጥፋተኞችን ለሕግ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል። ኮሚሽነር ባቸሌት ከክስተቱ ጋር በተያያዘ እስር ያሉ ተጠርጣሪዎች ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙም አሳስበዋል። ባቸሌት ጨምረውም፣ ወደፊት በሐይማኖቶች መካከል ተመሳሳይ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ፣ መንግሥት ተጎጅዎችን ማኅበረሰቦች እና ከግጭቱ በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ባካተተ መንገድ ለችግሩ ስረ መሠረት ተገቢውን መፍትሄ መስጠት አለበት ብለዋል።

ከሳምንት በፊት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ባንድ የሙስሊሞች መቃብር ላይ የተፈጠረ ሁከት፣ ሐይማኖታዊ ገጽታ ወዳለው ግጭት እና ጥቃት አምርቶ ከ20 በላይ ሙስሊሞች እንደሞቱ መዘገቡ ይታወሳል። የክልሉ መንግሥት በዕለቱ ሁከት በማስነሳት፣ በቀብር ስነ ሥርዓቱ ላይ በታደሙ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት በመፈጸም እና ግጭቱን ተከትሎ በከተማዋ በርካታ ንብረት በማውደም የጠረጠራቸውን ከ75 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ከቀናት በፊት መግለጡ ይታወሳል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰማ!

መንግስት በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ አድርጓል ተባለ። ዋዜማ ሬዲዮ አገኘሁት ባለችው መረጃ መሰረት ቤንዚን በሊትር 5 ብር ጨምሯል።በሊትር ከ31፡71 ሳንቲም ወደ 36፡82 ሳንቲም ገብቷል። ይሁን እንጂ መንግስት አሁንም ለቤንዚን 85 በመቶ ድጎማ እያደረገ እንደሚገኝ ዘገባው ጠቅሷል።

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
ለረጅም አመታት ደምበኞችን በትጋት ሲያገለግል የቆየው እና አንቱታን ያተረፈው አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ እቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ ዘመኑ ባፈራቸው ዘመናዊ በረቀቁ ማሽኖች እና በዘርፉ አንቱታን ባተረፍ ባለሞያዎቻችን በመታገዝ ለመኖሪያ ቤቶው እና ለቢሮ አዳዳስ ምርቶችን ውበትን በተላበሱ ዲዛይኖች እና በበርካታ አማራጮች ይዞላችሁ ቀርቧል።

ለቤትዎ ግርማሞገስ የሚሆኑ ለአይን ዕይታ ማራኪ የሆኑ በሌዘር እና በጨርቅ የተሰሩ ዘመናዊ ሶፍዎች! ቀን በስራ ሲደክም የዋለ ሰውነቶን እፎይ የሚሉባቸው ቅንጡ አልጋዎች በፈለጉት ዲዛይኖች !

የምግብ ወንበር እና ጠረጴዛዎች ! እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት እና ህንፆዎች የሚያገለግሉ በአይነታቸው ልዩ የሆኑ ፈርኒቸሮችን ጥራታቸውን እና ጥንካሬዎቻቸውን ጠብቀው እርሶ እኛ ዘንድ ያገኛሉ !

እርሶ ብቻ ያሻዎትን ይዘዙን ከድርጅታችን የተለያዩ እቃዎችን ሲገዙ ማጓጓዣ እና የሰራተኛ አቅርቦት ከኛ መሆኑ ወጪዎን ይቀንስሎታል የፈለጉትን ዕቃ ያለቀጠሮ መግዛት በመቻሎ ! እና ያዘዟቸውን እቃዎች በቀጠሮ ቀን ማድረስ በመቻሎ ከሌሎች ልዩ ያደርገናል አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ አድራሻ

#ቁ 1 ሀዋሳ ሞቢል ከድሮ ሸዋበር ሆቴል ፊትለፊት

#ቁ2 ሀዋሳ መናሀርያ ዙፍን ህንጳ ስር እንገኛለን

#ቁ3 ሀዋሳ መናሀርያ ኖክ ማደያ ውስጥ እንገኛለን
#ቀ4 ሀዋሳ ወልደ አማኑኤል ዱባለ አደባባይ አለፍ ብሎ 300ሜ ላይ ባለው አጠና ተራ ፊት ለፈት እንገኛለን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥራችን
0966464646
0916107676
0916581884 ሀሎ ይበሉን

አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ እቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ
ያልተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ሰኔ 30 ተጠናቀው እንደሚተላለፉ ተገለጸ!

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ከ19 ሺሕ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. አጠናቆ ለባለ ዕድለኞች እንደሚያስተላልፍ አስታወቀ፡፡

በቅርቡ ከባንኩ በተገኘ 2.5 ቢሊዮን ብር ብድር ለባለ ዕድለኞች ተላልፈው ያልተጠናቀቁ ቤቶችን ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙን በኮርፖሬሽኑ የግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶማስ ደበሌ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው እንዳስረዱት፣ የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ካለበት 54 ቢሊዮን ብር ዕዳ ውስጥ፣ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የመክፈል አቅም እንዳለው በጥናት አረጋግጧል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ : http://bit.ly/3smWhR1

@YeneTube @FikerAssefa
64 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወርቅ በህገ-ወጥ መንገድ ደብቆ ኬላ ጥሶ ለማለፍ የሞከረው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋለ!

64 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወርቅ በህገ-ወጥ መንገድ ደብቆ ኬላ ጥሶ ለማለፍ የሞከረው አሽከርካሪ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፤ የጉምሩክ እና በአካባቢው በነበሩ የኦሮሚያ ክልል የሚሊሻ ኃይል ባደረጉት ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ በ11:30 በኦሮሚያ ክልል ነጌሌ ቦረና ከተማ ዶሎ በር ኬላ ሰሌደ ቁጥሩ ኮድ-3-ኢት AA 03775 የሆነ ትዮታ ደብል ፒክአፕ ላንድ ክሩዘር ከነጋሌ ከተማ ወደ ሶማሌ ክልል ለመሄድ ቀጥታ በጉምሩክ ኬላ በኩል መጥቶ ለፍተሻ ሲያስቆሙት ፊቃደኛ ባለመሆን በኬላው ጎን ባለው የእግረኛ መንገድ በመጠቀም ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር ለማስቆም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ጥይት ቢተኩሱም ሳይቆም በማምለጥ ላይ እያለ የጉምሩክና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ለነበረው ኮማንድ ፖስት መረጃውን በፍጥነት ማስተላለፉን ገልጿል፡፡

በዚህም ዶሎ በር አካባቢ በሚገኘው የእርዳታ እህል ማራገፊያ አየር ማረፊያ አካባቢ የኦሮሚያ የሚሊሻ ኃይል ባደረጉት ብርቱ ክትትል ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ሲፈተሽ 16 ኪ.ግ ወርቅ የተገኘ ሲሆን አሁን በገበያ ላይ ባለው ዋጋ በብር ሲተመን 64,000,000.00 ብር (ስልሳ አራት ሚሊዮን ብር) የሚያወጣ መሆኑ ተረጋግጧል።

ከነአሽከርካሪው በቁጥጥር ስር የዋለው ወርቅም በኦሮሚያ ክልል ነጌሌ ከተማ በሚገኘው የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ መጋዘን ገቢ እንደተደረገ ታውቋል::

[ፌደራል ፖሊስ]
@YeneTube @FikerAssefa
አብን ለአቶ ክርስቲያን ታደለ የመጨረሻ ያለውን ማስጠንቀቂያ ሰጠ!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የንቅናቄውን ህግ ጥሰዋል በሚል 10 አባላቱን ከአባልነት አገደ፡፡አብን ባወጣው መግለጫ ከድርጅት ህገ-ደንብ እና አሰራር ውጭ በመሆን አፍራሽ ድርጊቶችንና የዲሲፕሊን ጥሰቶችን በፈፀሙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰኑን ገልጿል፡፡

የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም አደረኩት ባለው አስቸኳይ ስብሰባ በፓርቲው መዋቅር የተለያዩ የሃላፊነት እርከኖች ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ የዲሲፕሊን እና ድርጅታዊ መርህ ጥሰቶችን በፈጸሙ አባላቱ ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ የንቅናቄው ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሳለ አፍራሽ ተልዕኮን ሲያረራምዱ ተገኝተዋል በሚል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡

አቶ ክርስቲያን የተጣለባቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው በተለያዩ አፍራሽ ድርጊቶች ላይ የተሳተፉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ሁለት ጊዜ የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ አቶ ክርስቲያን በንቅናቄው ሥራ አስፈፃሚነታቸውም ሆነ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው በጋራ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዥ ባለመሆን እና ንቅናቄውን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ አንጃዎች ጋር ሕብረት ፈጥረው ንቅናቄው የሃሳብና የተግባር አንድነት እንዳይኖረው በሚያደርጉ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ስለተገኙ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ተወስኗል ብሏል ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ጋር አዋሳኝ በሆኑት አካባቢዎች ላይ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከፍተው ለአጭር ጊዜ የቆየ ወታደራዊ ግጭት መካሄዱን ታማኝ ምንጭ ለቢቢሲ አረጋገጡ።

ጥቃቱ ተፈጸመ የተባለው እሁድ ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም. ሲሆን በራማ እና ባድመ አካባቢ ባለው የኤርትራ ጦር ላይ ሲሆን፣ ጥቃቱን ተከትሎ በትግራይ ኃይሎችን በኤርትራ ጦር መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገልጿል።መቀለ የሚገኙ የቢቢሲ ምንጮች እንዲሁ ክልሉ ከኤርትራ ጋር በሚዋሰንበት ድንበር አካባቢ ግጭት ተቀስቅሶ እንደነበር ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የከባድ መሳሪያ ጥቃቱ ከትግራይ ኃይሎች በኩል መከፈቱን ተከትሎ በስፍራው "ውጊያ ተካሂዷል" ብለዋል።ነገር ግን የተኩስ ልውውጡ ለአጭር ጊዜ የቆየ መሆኑን እና ከፍተኛ ቁጥር ያለው እግረኛን ያላካተተ በከባድ መሳሪያ የተደረገ እንደነበር ምንጩ ጨምረው ገልጸዋል።

የከባድ መሳሪያ ጥቃቱን ተከትሎ ለአጭር ጊዜ በተደረገው የተኩስ "የትግራይ ኃይሎች ወደ ኋላ አፈግፍገው ውጊያውም ቆሟል'' ሲሉ ተናግረዋል።ጨምረውም ይህ ጥቃት "የህወሓትን ተንኳሽ ባሕሪይ የሚያሳይ ነው" ሲሉም አክለዋል።ቢቢሲ ተፈጸመ ስለተባለው ጥቃት ከኤርትራ መንግሥት በኩል ይፋዊ ምላሽ ለማግኘት ሙከራ ቢያደርግም እስካሁን አልተሳካለትም።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከሳኡዲ አረቢያ 1 ሺህ 33 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!

በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1ሺህ 33 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ከእነዚህ ውስጥ ስምንት ሕጻናት እንደሚገኙበት እና አጠቃላይ ከተመለሱት 1 ሺህ 25ቱ ወንዶች መሆናቸውን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ከ19 ሺህ 900 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
ቢቢሲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአማራ ክልል ጸጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር በምዕራብ ትግራይ የተገደሉ የትግራይ ተወላጆችን አስከሬኖች በዘዴ አስወግዷል በማለት ያወጣው ዘገባ "የተሳሳተ እና ሆነ ብሎ የዩኒቨርሲቲውን ስም የማጠልሸት ድርጊት ነው" ሲል ዩኒቨርሲቲው ለቢቢሲ የምሥራቅ አፍሪካ ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ከሷል።

ዩኒቨርስቲው ቢቢሲ ዘገባውን እንዲያስተባብል፣ ዘጋቢውን ሉሲ ካሳን እንዲመረምር፣ የምንጮቹን ተዓማኒነት እንደገና እንዲያጣራና ለዘገባው የተከተለውን አካሄድ እንዲፈትሽ ጠይቋል። ዩኒቨርስቲው ቢቢሲ በሐሰት ሊያጠለሽ የፈለገው፣ በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት ሕወሃት በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎችን ለዓመታት እየገደለ በጅምላ እንደቀበረ በሳይንሳዊ ጥናት የደረስኩበትን መረጃ ነው ብሏል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ-ቴሌኮም 5G ኔትወርክን በይፋ አስተዋወቀ!

ኢትዮ-ቴሌኮም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአምስተኛው ትውልድ የግንኘነት መረብ ወይም 5G ኔትወርክን በአዲስ አበባ አስተዋውቋል።

አዳዲስ ቴክኖሎጂዋችን በማስተዋወቅ ላይ የሚገኘው ኢትዮ-ቴሌኮም ይህን ለኢትዮጵያ አዲስ የሆነውን የ5G ኔትወርክ በማስተዋወቅ አዲስ የቴክኖሎጂ እመርታን ለደንበኞቹ በዛሬው ዕለት ማስተዋወቅ ችሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቼ

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል። 🍎
👉 የሪህ መድኀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
👉 ለመፍትሔ ሥራይ
👉 ፍቅር ለነሳው ለመስተፋቅር። 🍒
👉 ገንዘብ አልገባ ለሚለው ለሚበተንበት።
👉 ለአስም ለሳይነስ ።
👉 ለአይነጥላ ለገርጋሪ።
👉 ለስንፈተወሲብ ለሚቸኩልበት።
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ ።
👉 ለእራስ ሕመም።
👉እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶች እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱ እዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
የሚፈልጉትን መድኀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል። 🥒

ለበለጠ መረጃ

አድራሻ ባህርዳር ፦ቀበሌ 11 🫑
☎️ 0917040506
📞 0912718883
ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
ለጤናወ መፍትሄ የሚፈልጉትን ለማግኔት
🌿 ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ 🌱
🩺
👇
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe
በስልጤ የተጀመረው የሐይማኖት ተቋማት መልሶ ግንባታ ተጀመረ!

በስልጤ ዞን በቅርቡ ቃጠሎ ደርሶባችው የነበሩ የእምነት ተቋማትን መልሶ የመገንባት ሥራ መጀመሩን የዞኑ መስተዳድር አሰታወቀ፡፡በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ግን ወደ ዞኑ እንዳልገባ በመከለከሌ መልሰው ይገነባሉ ሥለተባሉ ቤተ ክርስቲያናት መረጃው የለኝም እያሉ ነው፡፡

ከሳምንታት በፊት በጎንደር የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ላይ ደርሷል የተባለውን ጥቃት ተከትሎ በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማና በሳንኩራ ወረዳ በሚገኙ ቤተ እምነቶች ላይ ጥቃት መፈፀሙ ይታወሳል፡፡ በየአካባቢዎች የተጀመሩ የተቃውሞ ሠልፎች ወደ ሁከት በማምራታቸው በአንድ የኘሮቴስታንትና በአራት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት ላይ በሙሉና በከፊል ጉዳት ደርሶ እንደነበር የጠቀሰው የሥልጤ ዞን መስተዳድር አሁን ቤተ እምነቶቹን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በዞኑ መስተዳድር ሰብሳቢነት በተቋቋመው የመልሶ ግንባታ ኮሚቴ አማካኝነት የጥሬ ገንዘብና የቁሳቁስ ሀብቶችን የማሰባሰብ ሥራዎችን በማከናወን ወደ ሥራ መገባቱን የዞኑ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ከድር አብደላ ለዶቼ ቬሌ ገልፀዋል፡፡

የስልጤ ዞን የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ኘሬዝዳንትና የዞኑ የሃይማኖቶች ህብረት ሰብሳቢ ሀጂ መሀመድ ከሊል በበኩላቸው መጥፎ ነገርን በመጥፎ መመለስ ሥህተት እንደነበር በመጥቀስ የጠፋውን ንብረት ወደ ቦታው በመመለስ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

በሥልጤ ዞን የወደሙ ቤተክርስቲያናትን መልሶ ለመገንባት በተጀመረው እንቅስቃሴ ዙሪያ ዶቼ ቬሌ DW ያነጋገራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሀድያና የስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መላከ ሕይወት ቄሲስ ንጉሴ ባወቀ በበኩላቸው ወደ ዞኑ እንዳልገባ በመከልከሌ መልሰው ይገነባሉ ስለተባሉት ቤተ ክርስቲያናት መረጃው የለኝም ብለዋል፡፡

የአገረ ስብከት ሥራ አስኪያጁ ባቀረቡት ቅሬታ ዙሪያ የተጠየቁት የሥልጤ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ከድር አብደላ ‹‹ ሥራ አስኪያጁ ወደ ዞኑ እንዳይገቡ የከለከላቸው አካል የለም ፤ ቅሬታዎች ካሉም ዞኑ ተቀራርቦ በመወያየት ሊፈቱ የሚችሉ ናቸው ›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ላለፉት 8 ቀናት ማንነታቸው ባልታወቀ የፀጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤቱ ታፍኖ የተወሰደው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከደቂቃዎች በፊት ተለቆ ወደ ቤቱ መግባቱን ተሰምቷል።

ጎበዜ ስለሁኔታው በሰጠን ማብራሪያ በመጀመሪያ የተያዘበት ሁኔታ ፍፁም ኢ-መደበኛ መሆኑንና አጋቾቹ ሲቪል ብቻ ሳይሆን የማይገመት ተራ አለባበስ ያላቸው ግን ደግሞ የታጠቁ ግለሰቦች በአጥር ዘለው ገብተው ለጥያቄ ትፈለጋለህ በሚል ይዘውት ወጥተዋል።ከተወሰደም በኋላ የት እንደነበረ መለየት እንዳልቻለና ብቻውን በአንድ ቤት ውስጥ መቆየቱን በአቅራቢያው የቤተ ክርስቲያን ድምፅ ይሰማ እንደነበር ብቻ ገልጿል።

ከአጋቾቹ የቀረበለትን ጥያቄ በተመለከተ "የአብን እና የፋኖ አባል ነህ ወይ?" የሚል ጥያቄ ቀርቦለት እንደነበርና በቆይታው ምንም አይነት አካላዊ ድብደባ ወይም ጉዳት እንዳልደረሰበት እና ምግብ በአግባቡ ይቀርብለት እንደነበር አብራርቷል።በመጨረሻም አይኑን በጨርቅ ሸፍነው ወደቤቱ መግቢያ በር እንዳደረሱት እና ጥለውት እንደሄዱ በተለይ ለዋዜማ በሰጠው መረጃ ገልጿል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
Forwarded from YeneTube
ለረጅም አመታት ደምበኞችን በትጋት ሲያገለግል የቆየው እና አንቱታን ያተረፈው አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ እቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ ዘመኑ ባፈራቸው ዘመናዊ በረቀቁ ማሽኖች እና በዘርፉ አንቱታን ባተረፍ ባለሞያዎቻችን በመታገዝ ለመኖሪያ ቤቶው እና ለቢሮ አዳዳስ ምርቶችን ውበትን በተላበሱ ዲዛይኖች እና በበርካታ አማራጮች ይዞላችሁ ቀርቧል።

ለቤትዎ ግርማሞገስ የሚሆኑ ለአይን ዕይታ ማራኪ የሆኑ በሌዘር እና በጨርቅ የተሰሩ ዘመናዊ ሶፍዎች! ቀን በስራ ሲደክም የዋለ ሰውነቶን እፎይ የሚሉባቸው ቅንጡ አልጋዎች በፈለጉት ዲዛይኖች !

የምግብ ወንበር እና ጠረጴዛዎች ! እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት እና ህንፆዎች የሚያገለግሉ በአይነታቸው ልዩ የሆኑ ፈርኒቸሮችን ጥራታቸውን እና ጥንካሬዎቻቸውን ጠብቀው እርሶ እኛ ዘንድ ያገኛሉ !

እርሶ ብቻ ያሻዎትን ይዘዙን ከድርጅታችን የተለያዩ እቃዎችን ሲገዙ ማጓጓዣ እና የሰራተኛ አቅርቦት ከኛ መሆኑ ወጪዎን ይቀንስሎታል የፈለጉትን ዕቃ ያለቀጠሮ መግዛት በመቻሎ ! እና ያዘዟቸውን እቃዎች በቀጠሮ ቀን ማድረስ በመቻሎ ከሌሎች ልዩ ያደርገናል አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ አድራሻ

#ቁ 1 ሀዋሳ ሞቢል ከድሮ ሸዋበር ሆቴል ፊትለፊት

#ቁ2 ሀዋሳ መናሀርያ ዙፍን ህንጳ ስር እንገኛለን

#ቁ3 ሀዋሳ መናሀርያ ኖክ ማደያ ውስጥ እንገኛለን
#ቀ4 ሀዋሳ ወልደ አማኑኤል ዱባለ አደባባይ አለፍ ብሎ 300ሜ ላይ ባለው አጠና ተራ ፊት ለፈት እንገኛለን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥራችን
0966464646
0916107676
0916581884 ሀሎ ይበሉን

አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ እቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ
የሲሚንቶ ፋብሪካዎች አከፋፋይ ወኪሎቻቸውን ከግብይት ሥርዓቱ እንዲያስወጡ ታዘዙ!

ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርቶቻቸውን የሚያከፋፍሉላቸውን ወኪሎች (ኤጀንት) ከገበያ ሥርዓት ውስጥ አስወጥተው ምርታቸው በቀጥታ እንዲሸጡ አዘዘ፡፡ ሚኒስቴሩ ለአሥር የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በጻፈው ደብዳቤ ፋብሪካዎቹ ያስወጧቸውን የሲሚንቶ አከፋፋይ ኤጀንቶች ብዛትና ስም ዝርዝር በደብዳቤ እንዲያሳውቁትም አሳስቧል፡፡

ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሚያዝያ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጻፈውና በሚኒስትር ደኤታው ሐሰን ሙሐመድ የተፈረመው ደብዳቤ፣ ‹‹በሲሚንቶ ፋብሪካዎች በኤጀንትነት ተመልምለናል›› የሚሉና የጅምላ ንግድ ፈቃድ የያዙ ነጋዴዎች ሲሚንቶውን ለሌሎች ጅምላ ነጋዴዎች እየሸጡ ስለመሆናቸው መታወቁን ያስረዳል፡፡ ይኼም ጅምላ ከጅምላ የሚደረግን የጎንዮሽ ንግድ የሚከለክለውን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 እንደሚጥስ በደብዳቤው ላይ ተገልጿል፡፡ ስለሆነም ፋብሪካዎቹ ደብዳቤው ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ የሲሚንቶ አከፋፋይ ኤጀንቶችን አስወጥተው ለሚኒስቴሩ እንዲያሳውቁ ታዘዋል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ደኤታው አቶ ሐሰን፣ ሚኒስቴሩ ሲሚንቶ ላይ ያለውን የግብይት ሰንሰለት ለማሳጠር እየሠራ መሆኑን ገልጸው ኤጀንቶች የግብይት ስንሰለቱን ከሚያራዝሙት አንዱና በሕግም የማይደገፉ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ አክለውም ከአሁን በኋላ ሲሚንቶን ለማከፋፈል ኤጀንቶችን የሚጠቀም የሲሚንቶ ፋብሪካ ከተገኘ ጥብቅ የሆነ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ሰባት የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረጋቸው ተገለፀ!

ሰባት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረጋቸውን የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ።

የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሰጠኝ ገላን ለአዲስ ማለዳ እንደገለፁት፣ የተለያዩ የግዥ ስርዓትን ለማዘመን በአሁን ወቅት የመንግሥት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ ለትግበራ ከተመረጡ ተቋማት ዘጠኙ የተቋማቸውን አደረጃጀት እና ዕቅድ ወደ ስርዓቱ ማስገባት ችለዋል ብለዋል። ከነዛም መካከል ሰባት መሥሪያ ቤቶች ተግባራዊ አድርገው መጠቀም እንደቻሉ እና ኹለቱ መሥሪያ ቤቶች ደግሞ በሂደት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

ኃላፊው አክለውም ስርዓቱ ከንግድ ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከባንኮች ጋር የተናበበ እንዲሆን፤ መደበኛ የጨረታ ሠነዶችን በሲስተሙ ላይ የማዋቀር ተግባር እንደተጠናቀቀ ባንኮች ሲስተሙን ተጠቅመው ለተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪዎችን እንዲያስይዙ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የወባ በሽታ መከሰቱ ተገለፀ!

በክልሉ ውስጥ ባሉ ዞኖች ውስጥ በሶስት ዞኖች በዋናነት በሽታው እየታ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኃይሌ ዘውዴ ገልፀዋል፡፡በተለይ በቤንች ሸኮ ዞን የበሽታው የመያዝ ምጣኔ ጭማሪ ማሳየቱን ሀላፊው ይገልፃሉ፡፡

በሽታው ሊስፋፋ የቻለው በአካባቢው ላለፉት ሰባት አመታት ታይቶ ስለማይታወቅ በአመራሩና በአካባቢው ነዋሪ ዘንድ መዘናጋት ስለተፈጠረ ነው እንዲህ ሊስፋፋ የቻለው በማለት አቶ ኃይሌ ተናግረዋል፡፡

ክልሉ በአሁኑ ነሰዓት በሽታውን ለመከላከል እየሰራ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የአጎበር እና የኬሚካል እጥረት እንደገጠማቸው ተናግረዋል፡፡ህብረተሰቡ ክረምት ከመሆኑጋር ተያይዞ ለወባ መራቢያ አመቺ የሚሆኑ ስፍራዎችን ማፅዳት አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa