YeneTube
120K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
53 አባላት ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዓመታዊ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ ያቀረበው ሪፖርት የሰሜኑን ጦርነት እና የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ባግባቡ ያልዳሰሰ ነው ተብሎ እንደተተቸ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ሪፖርቱ የእምናው አገር ዓቀፍ ምርጫ ሰላማዊ ነበር ማለቱን በተለይ ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ የቤንሻንጉል እና የወላይታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ክፉኛ ተችተውታል። ሆኖም ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ እንዳልነበር ሪፖርቱ ገልጧል። ምክር ቤቱ በ40 የድጋፍ ድምጽ ሪፖርቱን አጽድቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት ይሰጣል!

በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ይሰጣል፡፡

የክትባት ዘመቻው ከዛሬ ሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2014 የሚቆይ ሲሆን፤ ቤት ለቤት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ወላጀች ወይም አሳዳጊዎች ህጻናትን በማስከትብ ከሚደርስባችው የአካል ጉዳትና የጤና ችግር በመታደግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መጠየቁን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም በዓለማችን የመጨረሻውን የሞባይል ኔትዎርክ 5ተኛ ትውልድ (5ጂ) አገልግሎቱን ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ያስጀምራል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በቀጣዩ ወር በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያጋጥም እንደሚችል ተገለፀ!

በቀጣዩ ግንቦት ወር ከባድ ዝናብ በሚከሰትባቸው የአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያጋጥም ስለሚችል ሰብሎች እንዳይጎዱ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ የግንቦት ወር ዝናብ ሰጪ የሜትሮሎጂ ገጽታዎች በተለያዩ የአገሪቱ ሥፍራዎች ላይ አንጻራዊ ጥንካሬያቸውን ይዘው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎቹን ይጠቁማሉ ብሏል።ይህንም ተከትሎ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ እንደሚኖር ትንበያ አስቀምጧል።

በደቡብ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና  በጋምቤላ አካባቢ ጥቂት ሥፍራዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ የማስከተል አቅም ያለው ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችልም ተጠቁሟል። በግንቦት ወር ከምስራቅ ሃረርጌ ምስራቅ ዞኖች በስተቀር በኹሉም የኦሮሚያ ክልል ዞኖች ላይ፣ በቤንሼንጉል፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ክልል፣ በሲዳማ ክልል በኹሉም ዞኖች እንዲሁም በአማራ ክልል በአዊ፣ በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ላይ ከመደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይጠበቃል።አልፎ አልፎ ከሚፈጠሩ የደመና ክምችቶች በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የትንበያ መረጃው ያመለክተል።

በተጨማሪ በጎንደር ኹሉም ዞኖች በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣  ከአፋር ክልል፣ በምስራቅ ሀረርጌ፣ በምስራቅ ባሌ፣ ከሱማሌ ክልል በዳዋ፣ በሊበንና አፍዴራ ዞኖች ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል ተብሏል።በተቀሩት የአገሪቱ አከባቢዎች ደረቃማ ሆነው እንደሚሰነብቱ የአየር ትንበያው መረጃ አመላክቷል።ከቀላል እስከ ከባድ የሚጠበቀው የዝናብ መጠን በአብኛዛው የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ለረጅም ጊዜ ሰብሎችና ለቋሚ ተክሎች የውኃ ፍላጎት መሻሻል ትልቅ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

የሚገኘውን ውኃ አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ የተለያዩ የውኃ ማቆያ ዘዴዎችን አጠናክሮ በመጠቀል ዝናበ አጠር አካባቢዎች ለሚያጋጥማቸው የእርጥበት እጥረት ለማቃለል እንደሚረዳ ተገልጿል። በአገሪቱ አብዛኛው አካባቢዎች የሚጠበቀውን የግንቦት ወር ዝናብ በአግባቡ ለመጠቀምና ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባውም ነው ኢንስቲትዩት ያሳሰበው።በተጨማሪም የእርጥበት መብዛት ጋር የጸረ-ሰብል ተባይና የአረም መከሰት ሊኖረ ሰለሚችል ለዚህም ጥንቃቀቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ተጠቅሷል።

በሌላ በኩል ከክረምት እርጥበት መጠናከር ጋር ተያይዞ በደቡብ ምዕራብና በምዕራቡ የአገሪቱ የውኃ አካሎች ላይ የእርጥበት መጠኑ እንደሚጨምርም ተመላክቷል። ይህንንም የእርጥበት መጠን ጥቅም ላይ ለማዋልና የሚያስከትለውን አሉታዊ ጎን ለመከላከል ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ኢንስቲትዩቲ በመግለጫው ጠቁሟል።

@YeneTube @FikerAssefa
16 አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች መቐለ መድረሳቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

በሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ 64 አስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ መቐለ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም መግለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቼ

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል። 🍎
👉 የሪህ መድኀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
👉 ለመፍትሔ ሥራይ
👉 ፍቅር ለነሳው ለመስተፋቅር። 🍒
👉 ገንዘብ አልገባ ለሚለው ለሚበተንበት።
👉 ለአስም ለሳይነስ ።
👉 ለአይነጥላ ለገርጋሪ።
👉 ለስንፈተወሲብ ለሚቸኩልበት።
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ ።
👉 ለእራስ ሕመም።
👉እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶች እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱ እዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
የሚፈልጉትን መድኀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል። 🥒

ለበለጠ መረጃ

አድራሻ ባህርዳር ፦ቀበሌ 11 🫑
☎️ 0917040506
📞 0912718883
ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
ለጤናወ መፍትሄ የሚፈልጉትን ለማግኔት
🌿 ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ 🌱
🩺
👇
👇
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ የሚያዝያ ወር 2014 ዓ/ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 36.6 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ምግብና ምግብ-ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች በሁለት ትልልቅ የሃይማኖት በዓላት ምክንያት በያዝነው ወር ወቅታዊ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡የምግብ ዋጋ ግሽበት የሚያዝያ ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ42.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በያዝነውም ወር በተደራራቢ የሃይማኖት በዓላት መከበር ምክንያት በእህሎች የዋጋ ጭማሪ የታየ ሲሆን የአትክልት ዋጋም ላይ መጠነኛ ጭማሪ ታይቷል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ኅብረት ዓመታዊውን የፖለቲካ ውይይት ዛሬ ማድረጋቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

ከውይይቱ አጀንዳዎች መካከል፣ በኢትዮጵያ ስላሉ ሰብዓዊ ጉዳዮች፣ ለሰሜኑ ጦርነት ተጠያቂነትን ስለማስፈን እና የአገሪቱ ሁኔታ ለውጭ ኢንቨስትመንት ያለው ምቹነት ይገኙበታል። ደመቀ እና ፍትህ ሚንስትር ጌዲዮን መንግሥት የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የወሰዳቸውን ርምጃዎች ለኅብረቱ ልዑክ አብራርተዋል። ውይይቱ የተካሄደው፣ በኅብረቱ እና አፍሪካ የኮንቶኑ የጋራ ትብብር ማዕቀፍ ስር ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከአንድ ሳምንት በፊት ጎንደር ከተማ ውስጥ የተፈጸመውን ግጭት እና ግድያ በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ዐስታወቀ።

ኮሚሽኑ የምርመራው ውጤቱንም በቅርብ ጊዜ ይፋ ለማድረግ እየሠራበት መሆኑን በተለይም ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግሯል። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር መስከረም ገስጥ የሃይማኖት ግጭት የሚፈጥሩ አካሄዶች ለሰብአዊ መብቶችም አሳሳቢ መሆኑናቸውን በመረዳት ኮሚሽኑ አጽንእኖት ሰጥቶ እየተከታተለ ነው ብለዋል።

«እንዴት ነው ነገሮች፤ ያላቸው ሁኔታ ምንድን ነው የሚለውን [በቅርበት እየተከታተልን ነው]። የምርመራ ቡድን ልከን እያጣራን ነው የምንልበት ሁኔታ ላይም አይደለንም።ግን ያው የተፈጠረው ነገር አሳዛኝም ነገር ነው፤ …ለሰብአዊ መብት ጥሰት ሊያጋልጡ የሚችሉ፤ ሰብአዊ መብት ጥሰትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ግጭቶች መነሳታቸው አሳሳቢ መሆኑን [ግንዛቤ ወስደናል]። እና በአሳሳቢነት ደረጃ ላይ ይዘናል። ይኼ ደግሞ ምንድን ማለት ነው የሚለውን [በቅርበት ክትትል እያደረግንበት] ነው።»
የኮሚሽኑ ባለስልጣናት እስካሁን የደረሰውን የጉዳት መጠን «በዋናነት መለየት» መቻላቸውን ለዶይቼ ቬለ ዐሳውቀዋል።

«በሒደቱ ውስጥ መንግሥት ኃላፊነቱን በሚገባ ተወጥቷል ወይንስ አልተወጣም የሚለውን ለመለየት» ግን ኮሚሽኑ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጠዋል።በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ የምርመራ እና ክትትል ዳይሬክተር ይበቃል ግዛው ይህንኑ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

«በቀጣይ ክትትል እያደረግን ነው፤ አላቋረጥንም፤ ግጭቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ማለት ነው።ይፋ መውጣት ያለበት አስፈላጊ ነገር ሲኖር በእኛ በኩል ያንን እናደርጋለን።ለጊዜው ግን እያደረግን ያለነው በመንግሥትም በኩል ሆነ በግጭቱ ተሳታፊ የነበሩ በሁለቱም በኩል የነበሩት የነበራቸው ሚና ምድንድን ነው? መነሻው ምንድን ነው የሚሉትን ነገሮች የመለየትና የመከታተል ሥራ ነው እየሠራን ያለነው።»

በሌላ በኩል በአንድ ታዳጊ ላይ የጸጥታ አካላት የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች ሰብዓዊ መብትን የጣሰ ድርጊት ሲፈጽሙ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መታየቱን በተመለከተም ኮሚሽኑ የድርጊቱን ተጨባጭነት ጨምሮ ምርመራዎችን እያደረገ መሆኑን የዶይቸ ቨሌ ዘገባ ይጠቁማል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
Forwarded from YeneTube
ለረጅም አመታት ደምበኞችን በትጋት ሲያገለግል የቆየው እና አንቱታን ያተረፈው አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ እቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ ዘመኑ ባፈራቸው ዘመናዊ በረቀቁ ማሽኖች እና በዘርፉ አንቱታን ባተረፍ ባለሞያዎቻችን በመታገዝ ለመኖሪያ ቤቶው እና ለቢሮ አዳዳስ ምርቶችን ውበትን በተላበሱ ዲዛይኖች እና በበርካታ አማራጮች ይዞላችሁ ቀርቧል።

ለቤትዎ ግርማሞገስ የሚሆኑ ለአይን ዕይታ ማራኪ የሆኑ በሌዘር እና በጨርቅ የተሰሩ ዘመናዊ ሶፍዎች! ቀን በስራ ሲደክም የዋለ ሰውነቶን እፎይ የሚሉባቸው ቅንጡ አልጋዎች በፈለጉት ዲዛይኖች !

የምግብ ወንበር እና ጠረጴዛዎች ! እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት እና ህንፆዎች የሚያገለግሉ በአይነታቸው ልዩ የሆኑ ፈርኒቸሮችን ጥራታቸውን እና ጥንካሬዎቻቸውን ጠብቀው እርሶ እኛ ዘንድ ያገኛሉ !

እርሶ ብቻ ያሻዎትን ይዘዙን ከድርጅታችን የተለያዩ እቃዎችን ሲገዙ ማጓጓዣ እና የሰራተኛ አቅርቦት ከኛ መሆኑ ወጪዎን ይቀንስሎታል የፈለጉትን ዕቃ ያለቀጠሮ መግዛት በመቻሎ ! እና ያዘዟቸውን እቃዎች በቀጠሮ ቀን ማድረስ በመቻሎ ከሌሎች ልዩ ያደርገናል አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ አድራሻ

#ቁ 1 ሀዋሳ ሞቢል ከድሮ ሸዋበር ሆቴል ፊትለፊት

#ቁ2 ሀዋሳ መናሀርያ ዙፍን ህንጳ ስር እንገኛለን

#ቁ3 ሀዋሳ መናሀርያ ኖክ ማደያ ውስጥ እንገኛለን
#ቀ4 ሀዋሳ ወልደ አማኑኤል ዱባለ አደባባይ አለፍ ብሎ 300ሜ ላይ ባለው አጠና ተራ ፊት ለፈት እንገኛለን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥራችን
0966464646
0916107676
0916581884 ሀሎ ይበሉን

አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ እቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ
ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቼ

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል። 🍎
👉 የሪህ መድኀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
👉 ለመፍትሔ ሥራይ
👉 ፍቅር ለነሳው ለመስተፋቅር። 🍒
👉 ገንዘብ አልገባ ለሚለው ለሚበተንበት።
👉 ለአስም ለሳይነስ ።
👉 ለአይነጥላ ለገርጋሪ።
👉 ለስንፈተወሲብ ለሚቸኩልበት።
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ ።
👉 ለእራስ ሕመም።
👉እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶች እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱ እዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
የሚፈልጉትን መድኀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል። 🥒

ለበለጠ መረጃ

አድራሻ ባህርዳር ፦ቀበሌ 11 🫑
☎️ 0917040506
📞 0912718883
ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
ለጤናወ መፍትሄ የሚፈልጉትን ለማግኔት
🌿 ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ 🌱
🩺
👇
👇
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe
የሶማሊያ ምርጫ ግንቦት 15 እንዲካሄድ ተወሰነ፡፡

ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረዉ የሶማሊያ ምርጫ ግንቦት 15 በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ እንዲካሄድ ቀን ተቆርጦለታል፡፡


የፕሬዝዳንታዊ ምርጫዉን እያስተባበረ የሚገኘዉ የፓርላማዉ ኮሚቴ እንደገለጸዉ፣ ከላይኛዉ ምክርቤት ወይም ከሴኔቱ 54 እንዲሁም ከታችኛዉ ምክርቤት ደግሞ 275 በአጠቃላይ 329 ህግ አዉጭዎች 10ኛዉን የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ይመርጣሉ ብሏል፡፡


እጩዎቹ ተመራጮች በግንቦት 11 እና 12 በፓርላማዉ ተገኝተዉ ከምርጫዉ በፊት ስለ ፖሊሲያቸዉ ገለጻ እንደሚያደርጉ ኮሚቴዉ አክሎ ገልጿል፡፡

ከታቀደለት የጊዜ ገደብ በ15 ወራት የዘገየዉ የ2022 የሶማሊያ ምርጫ በባህሪዉም ሆነ በዉጤቱ በአፍሪካ ቀንድ አከባቢ ባሉ ሀገራት መካከል ያለዉ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነት ላይ እንደ ማዕበል ከፍ ያለ ከባድ ተጽዕኖ ያሳድራል ተብሏል፡፡

የምርጫዉ ዕለት እ.ኤ.አ በግንቦት 15፣ 1943 በ13 ወጣት የማህበረሰብ አንቂዎች ነጻ እና የተባበረች ሶማሊያን ለመፍጠር ታስቦ የተመሰረተዉ የሶማሊያ ወጣቶች ሊግ 79ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ታሪካዊ ቀን ላይ እንደሚዉልም ተነግሯል፡፡

ሲጂቲኤን አፍሪካ
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ 400 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለደቡብ ሱዳን ልትሸጥ ነው

በኃይል ሽያጭ ሥምምነቱ በመጀመሪያ ዙር 100 ሜጋ ዋት ኃይል ለደቡብ ሱዳን ይቀርባል

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር መፍጠር የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮጵያ በኩል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሱልጣን ወሊ ሲሆኑ፤ በደቡብ ሱዳን በኩል በኢነርጂና ግድብ ሚኒስትርቶም ረሚስ ጆን ናቸው።
@Yenetube @Fikerassefa
ሮማን አብራሆሞቪች የቼልሲ እግር ኳስ ክለብን በ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ለመሸጥ ተስማሙ

ሩሲያዊው ቢሊየነር እና የቼልሲ ባለቤት ሮማን አብርሃሞቪች ክለባቸውን በመሸጥ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ለተጎዱ ሰዎች በበጎ አድራጎትነት እንደሚሰጡ ቃል ገብተው ነበር።

ይህን ተከትሎም ላለፉት ሳምንታት ቼልሲን የሚገዙ የተለያዩ ሀገራት ኩባንያዎች በህብረት እና በተናጥል የግዢ ፍላጎታቸውን ሲያቀርቡ ቆይተው ነበር።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ በአሜሪካው ዶጀርስ በተሰኘው ኩባንያ መሪነት ቼልሲን ለመግዛት ከክለቡ ጋር ተስማምተዋል። ቶድ ቦኤህሊ የአሜሪካው ካሊፎርኒያ ዶጀርስ ቅርጫት ኳስ ክለብ ባለቤት ሲሆኑ በቼልሲ እግር ኳስ ክለብ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል።

አሜሪካዊ ማርክ ዋልተር እና ስዊዘርላነዳዊው ቢሊዬነር ሀንስጆርግ ከቶድ ቦኤህሊ ጋር ቼልሲ ክለብን የገዙ ባለሀብቶች ናው።

Via :- Al Ain
@Yenetube @Fikerassefa
ይህ ቻናል በኢትዮጲያ መንፈሳዊ ፤ ማህበራዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ በአርቲስት ሮቤል ግርማ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ የዩቱዩብ ፕሮግራም ነው ። በ ቴሌቭዥን እና በዩትዩብ ቻናላችን ይከታተሉ፡፡ ሊንኩን ተጭነው ሙሉ ቪድዮውን ይመልከቱ
📸ሼር
ላይክ
🔔ሰብክራይብ ያድርጉ

https://www.youtube.com/channel/UCvkF_ngaWgoyWaZCLI04PWA
YeneTube
Photo
ታይዋን፤ ቻይና ልትወረኝ ትችላለች ስትል ስጋቷን ገልጻለች

ቻይና ለሁለተኛ ጊዜ 18 የጦር አውሮፕላኖችን ወደ ታይዋን ላከች
ታይዋን የግዛቴ አንድ አካል ናት የምትለው ቻይና 18 ተዋጊ አና ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች መላኳ ተገልጿል።

የታይዋን አየር መከላከያ ክልል እንደተናገረው የቻይና ተዋጊ አውሮፕላኖች የታይዋንን የአየር ክልል ጥሰው እንደገቡ አስታውቋል።
ቻይና የታይዋንን የአየር ክልል ጥሳ ስትገባ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው የተባለ ሲሆን ታይዋን የዩክሬን እጣ ሊደርሳት እንደሚችል ስጋት እንደገባት ገልጻለች።

ከቻይና የወረራ ስጋት ያለባት ታይዋን ጦርነት ለመቋቋም የሚያስችል መመሪያ አዘጋጀች
አሜሪካንን ጨምሮ የዓለም ሀገራት አንድ ቻይና እንዲያከብር በማሳሰብ ላይ ብትሆንም ምዕራባዊያን ሀገራት ግን ታይዋን የቻይና አንድ አካል አይደለችም ሲሉ ይደመጣሉ።
ቻይና በአንጻሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት ታይዋን የግዛቷ አንድ አካል መሆኗን ገልጻ የውጊያ አውሮፕላኖችም ወደ ታይዋን ቢገቡ ወደራሳቸው ግዛት ገቡ እንጂ የማንንም የአየር ክልል አለመጣሷን ከዚህ በፊት አሳውቃለች።
ታይዋን ባቀረበችው የዛሬው የአየር ክልሌ ተጣሰ ክስ ዙሪያ እስካሁን ምላሽ ያልሰጠችው ቻይና ሉዓላዊነቷን በሚዳፈር ሀገርም ይሁን ተቋም ላይ ከባድ እርምጃ እንደምትወስድ ከዚህ በፊት ማስጠንቀቋ ይታወሳል።
የዓለም ትኩረት ሁሉ በሩሲያ-ዩክሬን ላይ በመሆኑ ቻይና ታይዋንን ልትወር ትችላለች የሚል ስጋት መኖሩን የታይዋን ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ባሳለፍነው ጥር ወር የቻይና ተዋጊ አውሮፕላኖች የታይዋንን የአየር ክልል ጥሰው እንደገቡ ዓለም አቀፉ የአየር መከላከያ ልየታ ቀጠና ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ቻይና፤ የአሜሪካ ም/ ቤት አፈጉባዔ ታይዋንን ከጎበኙ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል አስጠነቀቀች

ከቀናት በፊት አውሮፓን የጎበኙት የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ በእንግሊዟ መዲና ለንደን ላይ ባሰሙት ንግግራቸው ዓለም ለሩቅ ምስራቅ ትኩረት ካላደረገ የምስራቅ አውሮፓው ክስተት በምስራቅ እስያም ሊደገም ይችላል ብለዋል።

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሳለፍነው ዓርብ ባወጣው መግለጫ ጃፓን ከጸብ አጫሪነቷ እንድትታቀብ አስጠንቅቋል።

ሚኒስቴሩ አክሎም ጃፓን በእስያ እና በዓለም ሰላም እንዲመጣ ከፈለገች በዓለማችን ሀያላን ሀገራት መካከል ገብታ ጸብ ከምታጭር ሀገራትን ወደ ጦርነት እንዲገቡ ከመተንኮስ ትታቀብ ሲልም አሳስቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ግልጽና ኅቡዕ ጥቃቶች እንዲቆሙ ሲል ማኅበሩ አሳሰበ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ማኅበር በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ግልጽና ኅቡዕ ጥቃቶች እንዲቆሙ ሲል አሳሰበ።

ማኅበሩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ መንግሥት ጋዜጠኞች ሥራቸውን በማከናወናቸው ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግበትን ምስጢራዊ አሠራሩን ሊፈትሽ ይገባል ብሏል። እንዲህ ያለው ድርጊት ለመንግሥትም ሆነ በጠቅላላው ለአገር የሚፈይደው ነገር እንደማይኖር ይልቁንም መንግሥት እዘረጋዋለሁ ብሎ ከሚያምነው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓተ ማኅበር ውጥኑ የሚቃረን መሆኑንም ማስታወስ እንደሚገባ ጠቅሷል።

@Yenetube @Fikerassefa
ተመድ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በአፍሪካ ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ሲል አስጠነቀቀ!

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ተከትሎ በተከሰተው የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ መወደድ በአፍሪካ 'ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ' ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ።

በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ጦርነት እና ምእራባውያን በሞስኮ ላይ እየጣሉት ያለው መጠነ ሰፊ ማዕቀብ ስንዴ እና ማዳበሪያን ጨምሮ የሌሎች ምርቶች አቅርቦትን እያስተጓጎለ ነው ያለው ተመድ፤ ይህም በአፍሪካ ላይ ተጨማሪ አደጋ መደቀኑን ነው ያስታወቀው።

የጠመደ የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ኃላፊ ራይመንድ ግሊፒን በትናትናው እለት በስጡት አስተያየት፤ የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት በአፍሪካ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።

ኃላፊው ራይመንድ ግሊፒን፤ አሁን እያጋጠሙ ያሉ የኢኮኖሚ ችግሮች በአህጉሪቱ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ቀውስችን እያስከተሉ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በከተሞች አካባቢ ያለው ውጥረት ከፍተኛ ነው ያሉት ግሊፒን፤ ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች አሁን ያለው ቀውስ ወደ አምጽ እና ግጭት እንዲያመሩ ሊያስገድዳቸው እንደሚችል ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

በተለይም በዘንድሮው ዓመት እና በቀጣይ ዓመት ምርጫን የሚያደርጉ ሀገራት ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዘው ለሚቀሰቀሱ አመጾች ተጋላጭ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የስንዴ ላኪ ሀገራት በሆኑት ከዩክሬን እና ከሩሲያ በሚገቡ ምግቦች እና ማዳበሪያ ላይ ጥገኛ መሆናቸው ይታወቃል።

በተለይም በርከት ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ከሚያስፈልጋቸው የስንዴ ፍጆታ ውስጥ 80 በመቶውን ከሩሲያ እና ከዩክሬን እንደሚገዙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ጦርነቱ ከምግብ ፍጆታ በተጨማሪም ያስከተለው የዓለም የነዳጅ ዋጋ ግሽበት በአፍሪካ ሀገራትም የናፍጣ እና የቤንዚን መሸጫ ዋጋ ከፍ እንዲል አድርጎታል።
የምግብ ዋጋ መናር እና ዝቅተኛ የኢኮኖሚ እድገት በአፍሪካ አህጉርን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ደሃ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን አደጋ ውስጥ እንደጣለም ይነገራል።

Via Al Ain
@Yenetube @Fikerassefa