YeneTube
120K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለረጅም አመታት ደምበኞችን በትጋት ሲያገለግል የቆየው እና አንቱታን ያተረፈው አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ እቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ ዘመኑ ባፈራቸው ዘመናዊ በረቀቁ ማሽኖች እና በዘርፉ አንቱታን ባተረፍ ባለሞያዎቻችን በመታገዝ ለመኖሪያ ቤቶው እና ለቢሮ አዳዳስ ምርቶችን ውበትን በተላበሱ ዲዛይኖች እና በበርካታ አማራጮች ይዞላችሁ ቀርቧል።

ለቤትዎ ግርማሞገስ የሚሆኑ ለአይን ዕይታ ማራኪ የሆኑ በሌዘር እና በጨርቅ የተሰሩ ዘመናዊ ሶፍዎች! ቀን በስራ ሲደክም የዋለ ሰውነቶን እፎይ የሚሉባቸው ቅንጡ አልጋዎች በፈለጉት ዲዛይኖች !

የምግብ ወንበር እና ጠረጴዛዎች ! እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት እና ህንፆዎች የሚያገለግሉ በአይነታቸው ልዩ የሆኑ ፈርኒቸሮችን ጥራታቸውን እና ጥንካሬዎቻቸውን ጠብቀው እርሶ እኛ ዘንድ ያገኛሉ !

እርሶ ብቻ ያሻዎትን ይዘዙን ከድርጅታችን የተለያዩ እቃዎችን ሲገዙ ማጓጓዣ እና የሰራተኛ አቅርቦት ከኛ መሆኑ ወጪዎን ይቀንስሎታል የፈለጉትን ዕቃ ያለቀጠሮ መግዛት በመቻሎ ! እና ያዘዟቸውን እቃዎች በቀጠሮ ቀን ማድረስ በመቻሎ ከሌሎች ልዩ ያደርገናል አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ አድራሻ

#ቁ 1 ሀዋሳ ሞቢል ከድሮ ሸዋበር ሆቴል ፊትለፊት

#ቁ2 ሀዋሳ መናሀርያ ዙፍን ህንጳ ስር እንገኛለን

#ቁ3 ሀዋሳ መናሀርያ ኖክ ማደያ ውስጥ እንገኛለን
#ቀ4 ሀዋሳ ወልደ አማኑኤል ዱባለ አደባባይ አለፍ ብሎ 300ሜ ላይ ባለው አጠና ተራ ፊት ለፈት እንገኛለን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥራችን
0966464646
0916107676
0916581884 ሀሎ ይበሉን

አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ እቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ
Forwarded from YeneTube
🥳መልካም የትንሳኤ በአል እያልን የበአል ልዩ ቅናሽ ይዘን መጥተናል🥳
https://tttttt.me/getitonlinee
የወንድም የሴትም
🎯ኦርጂናል ጥሩ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች
🎯የስጦታ ጥቅሎች(package)🎁
🎯ኦርጂናል ሰአቶች
🎯 ቦርሳዎች እና የውበት መጠበቂያዎች
🎯 አልባሳት እና ጫማዎች

🎯ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ በ0929011031

🎯አድራሻ፣ ቦሌ መድሀኒያለም
ያሉበት ቦታ ድረስ በነጻ እናደርሳለን
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ ይሁኑ https://tttttt.me/getitonlinee
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
የወለድ አልባ ባንክ አገልግሎት ከስምንት ዓመት በፊት አንስቶ በመሰጠት ላይ ይገኛል

እስላሚክ ባንክ በዓለማችን ካሉ የባንክ አገልግሎቶች መካከል አንዱ ሲሆን አገልግሎቱ ተመሳሳይ ቢሆንም ስያሜው ግን ከሀገር ሀገር ይለያያል፡፡

ይህ የባንክ አገልግሎት በእንግሊዝ እስላሚክ ባንክ፣ ኢቲካል ባንክ የሚሉ ስያዌሞች ሲኖሩት በአሜሪካ ላሪባ ባንክ ሲባል በኢትዮጵያ ደግሞ ወለድ አልባ ባንክ ተብሎ እንዲጠራ የኢትዮጰያ ብሄራዊ ባንክ ደንግጓል፡፡

https://am.al-ain.com/article/what-is-islamic-banking
ለመጀመሪያ ጊዜ በሚተገበረው የመንግስት እና የግል አጋርነት 270 ሺህ ቤቶች ሊገነቡ ነው

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የመኖሪያ ቤት ችግርን ለማቃለል ለመጀመሪያ ጊዜ በሚተገበረው በመንግስት እና በግል አጋርነት በቀጣይ 5 ዓመታት 270 ሺህ ቤቶች ሊገነቡ መሆኑን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ፕሮጀክቱ ወደ ስራ ለማስገባት በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የመንግስት እና የግል አጋርነት አዋጅ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን በሚኒስቴሩ የቤቶች ልማት አስተዳደር ኃላፊ አቶ ታደሰ ከበበ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ አዋጆች በኢነርጂ፣ በመንገድ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ተግባራዊ መደረጋቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

በመንግስት እና በግል አጋርነት የሚገነቡ ቤቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የአዋጭነት ጥናት ተሰርቶ አዋጭነቱ በመረጋገጡ በመንግስት ይሁንታ ተሰጥቶት ወደ ስራ መገባቱን ነው አቶ ታደሰ የገለጹት፡፡

በመንግስት እና በግል ባለሃብቱ አጋርነት የሚገነቡ ቤቶች በግለሰቦች፣ በማህበራት፣ በባለሃብት ሪልስቴት አልሚዎች እንዲሁም በጆይንት ቬንቸር ከሚገነቡ ቤቶች በተጨማሪ የሚገነቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

መንግስት እስካሁን ድረስ ከ400 ሺህ በላይ ኮንዶሚኒየሞች መገንባቱን የገለጹት አቶ ታደሰ፣ ከፍተኛ የቤት ፍላጎት በመኖሩ በመንግስት ብቻ ችግሩን መቅረፍ እንደማይቻል መንግስት ተረድቷል ብለዋል፡፡

እስከ አሁን ያለው የቤት ፈላጊዎች ቁጥር፣ ወደፊት የሚጨምረው የቤት ፈላጊ ቁጥር፣ እንዲሁም በከተሞች የሚገኙ ለመኖሪያ የማይመጥኑ ቤቶችን ታሳቢ በማድረግ በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ 6 ሚሊዮን ቤቶችን መገንባት እንደሚያስፈልግ በሚኒስቴሩ የተሰራው ጥናት ያመለክታል፡፡

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ትናንት ለክርስትና እምነት አባቶች የምሳ ግብዣ አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ በትናንትናው ዕለት ለክርስትና እምነት አባቶች የምሳ ግብዣ አድርገዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና ለመፍታት መንግሥትና የሃይማኖት አባቶች በጋራ እንዴት መሥራት እንዳለባቸው እግረ መንገድ ውይይት መደረጉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ከኢድ ሰላት ምዕመኑ ተረጋግቶ ወደ መጣበት እየተመለሰ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የኢድ ሰላት ከመሰገዱ በፊት በሰማዕታት ሀውልት አካባቢ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል።

ምዕመኑ አሁን ተረጋግቶ ወደ መጣበት እየተመለሰ ስለሆነ ህብረተሰቡ በመረጋጋት ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በቀጣይ የረብሻውን መነሻና ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች ጉዳዮችን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ መግለጹን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ታሰረ።

በትናንትናው ዕለት 4 ስዓት አካባቢ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከመኖሪያ ቤቱ ከ ሃያት አካባቢ በፀጥታ ሃይሎች መወሰዱን ጠበቃው አዲሱ አልጋው ለየኔታ ሚዲያ ገልፀዋል እስካሁን ለምን እንደታሰረ እና በየትኛው ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰረ ማወቅ እንዳልቻሉ ጠበቃው አክለው ገልፀዋል

@Yenetube @Fikerassefa
የሰማዕታት ሃውልት፣ መስቀል አደባባይና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ህንጻን ጨምሮ በ28 ተቋማት ላይ ጉዳት ደረሰ!

በኢድ ሶላት ላይ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በሰማዕታት ሃውልት፣ መስቀል አደባባይና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ህንጻን ጨምሮ በ28 ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡ጽ/ቤቱ እንዳስታወቀው የረመዳን ፆም መጠናቀቁን ተከትሎ ህዝበ ሙስሊሙ በሰላማዊና ሀይማኖቱ በሚፈቅደው መንገድ በአዲስ አበባ ስቴዲየም በዓሉን እያከበረና ለፈጣሪው ምስጋናውን እያቀረበ ባለበት ሰዓት ላይ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል።

ችግር ፈጣሪዎቹ ስቴዲየም ውስጥ እና በዙሪያዋ ያሉ 28 ተቋማት ላይ ካደረሱት ጉዳት በተጨማሪ መስቀል አደባባይ የመኪና ማቆሚያ መግቢያና መውጫ መስታወቶች ላይ መጠነኛ ጉዳት አደርሰዋል፡፡በሰማዕታት ሀውልትና አጠገቡ ያለው የመፀሀፋት መደብር እና ካፍቴሪ እንዲሁም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቢሮ ላይ ጉዳት መድረሱን የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፋ አቶ ታዬ ሽፈራው በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ታዬ ማብራሪያም በከተማዋ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራን ባለበት በዚህ ወቅት ጥቂት ሰላማችን የሚያማቸው የውስጥ ጠላቶቻችን ከውጭዎቹ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ በመፈፀም ሀገሪቱን ለማተራመስ እየሰሩ ነዉ ብለዋል፡፡በተወሰኑ አካባቢዎች የተፈጠሩ አለመግባባቶችን መነሻ በማድረግ አብዛኛው አካባቢ ችግር ለመፍጠር መሞከር እንዲሁም ችግሩን ከወንድማማችነት እሴትና ከሀይማኖት አስተምህሮት ውጭ ለመፍታት መሞከር ውጤቱ የከፋ ይሆናል፤ኢትዮጵያውያን ሁሌም የመቻቻል እሴታችን መሰረት ላይ መቆም ይገባናል ሲሉ አክለዋል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
**ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።


አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።

መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ

ለጤናወ መፍትሄ👇

https://tttttt.me/meritibe
👍1
 በሁከትና ብጥብጥ በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ 76 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።
 
1 ሺህ 443ኛ የኢድ አልፈጥር በዓል በአዲስ አበባ በሰፊ ፕሮግራም ታጅቦ በሰላማዊ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን ነገር ግን ጥቂት ከሀይማኖታዊ ሥርዓቱ ውጭ ሌላ የሁከትና ብጥብጥ ዓላማ ያላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ለብጥብጥ መነሻ በማይሆን ምክንያት ከስታዲየም ውጭ በተለምዶ የቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም አጠገብ ሆነው ባስነሱት ረብሻና ብጥብጥ በጸጥታ ኃይሎችና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን 76 ግንባር ቀደም ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።
 
የጋራ ግብረ ኃይሉ የኢድ አልፈጥርን በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስምሪት መግባቱ ይታወቃል፡፡
 
በዓሉን ለማክበር ከወትሮው በተለየ መልኩ ህዝበ ሙስሊሙ በነቂስ ወደ በዓሉ ስፍራ በመሄድ የስግደት ስነ ስርዓቱ እንደ ተጀመረ ሁከትና ግርግር የተፈጠረ ሲሆን የፀጥታና ደህንነት ግብረ ሀይሉ መንስኤውን እያጣራ እንደሚገኝና ውጤቱንም ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡
 
የጋራ ግብረ ኃይሉ ባደረገው ክትትልና ግምገማ አብዛኛው የበዓሉ ታዳሚ ስግደቱን ፈፅሞ የበዓሉን በረከት በመቋደስ ወደ ቤቱ ለመመለስ አስቦ የመጣ ቢሆንም፥ አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች በቀልና ጥላቻን ቋጥረው እንዲሁም ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቻችን ስውር ተልዕኮ ወስደው ሀገራችን የምትታወቅበትን የሀይማኖት መቻቻል በመናድ ህዝቡን በሀይማኖት በመከፋፈልና በመለያየት ሀገራችንን ለማፍረስ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ግጭት በማባባስ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።
 
እነዚህ ፀረ-ሰላም ግለሰቦችና ቡድኖች ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ ተደራጅተው በአንዳንድ አካባቢዎች ስለታማ ነገሮችን፣ የውጭ ሀገር አክራሪዎችን አርማና የተለያዩ ግጭት ቀስቃሽ ጽሁፎችን በመያዝ ጥቃትና በቀል ለመፈፀም ወደ በዓሉ ስፍራ መምጣታቸውን ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ፀረ-ሰላም ኃይሎች እጅ መያዙን ገልጿል።
 
የፈጠሩትን ሁከትና ግርግር ተጠቅመው ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቻችን የተቀበሉትን ስውር ተልዕኮ ለመፈፀም ጥረት አድርገዋልም ብሏል ግብረ ኃይሉ።
 
በዚህ የተነሳ የጸጥታ አካላት ላይ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በህዝብና በመንግስት  ተቋማት ላይም ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
 
ይህንን እኩይ ተግባር ሲፈፅሙ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ሁከቱን በትዕግስት በመከታተልና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በህዝበ ሙስሊሙ በተለይም በሴቶች፣ ህፃናትና በሰላማዊ የሀይማኖቱ ተከታዮች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ብርቱ ጥረትና ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጓልም ነው ያለው፡፡
 
ከዚህ ሁከትና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ 76 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን በቀጣይም ጉዳዩን በማጣራት ሌሎች የድርጊቱ ተሳታፊዎችን አድኖ በመያዝ ለህግ እንደሚያቀርብ ግብረ ኃይሉ አስታውቋል።
 
ግብረ ኃይሉ ክቡር የሰው ልጅ ህይወት እንዳይጠፋና የአካል ጉዳት እንዳይደርስ ከሰላም ወዳዱ የሙስሊም ህብረተሰብ ጋር በመሆን ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎ መቆጣጠር የቻለ ሲሆን በበዓሉ ታዳሚዎች ላይ የሞትም  ሆነ የአካል ጉዳት እንዳልደረሰ አረጋግጧል።
 
ይህ ደግሞ የሀገራችን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ጥንካሬና ብቃት እንዲሁም ለህዝቡ ያለውን ወገንተኝነት ያረጋገጠ ነው ሲል ግብረ ኃይሉ ገልጿል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
"በዒድ ሰላት ወቅት የተከሰተው ክስተት በክርስቲያኑና በሙስሊሙም መካከል የተፈጠረ አይደለም።"

- የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት


"አንዳንድ አካላት ችግሩን ከመንግስት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውም የተሳሳተ መሆኑን አረጋግጠናል።

በዒድ ሰላት ወቅት የተፈጠረው ችግር ምን እንደሆነ በስፍራው ከነበሩ በጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎቻችን ደርሶናል። በአንድ ፌደራል ፖሊስ ድንገት (ባርቆብኝ ነው ብሏል) በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ ምክንያት የተፈጠረ ግርግር ነበር። የአስለቃሽ ጭሱ እንደተተኮሰ በቦታው የነበሩ የበአሉ ታዳሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ተደናግጠዋል።ወደ ፌደራል ፖሊሱ በማቅናት ይዘውታል።ፖሊሱም ድንገት ባርቆበት እንደሆነ ተናግራል። ሆኖም ህዝቡ ከፍተኛ የሆነ መረበሽ ውስጥ ስለገባ ለመግባባት አልተቻለም።

በመጨረሻም የፌደራል ፖሊሱ በኤግዚቢሽን ማዕከል አካባቢ ወደ ሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ካንፕ እንዲገባ ተደርጓል።ይህን ተከትሎ ሌሎች ፖሊሶች ከካምፑ ሲወጡ ተኩስ የፈጠረው ግርግር ባለመረጋጋቱ ችግሩ ሊባባስ ችሏል።

ከዚህ በተረፈ ከእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ጋር ችግሩን የሚያይዘው ነገር አለመኖሩ ተረጋግጧል። በመንግስት በኩልም ሆነ ተብሎ የተፈጠረ ችግር አለመኖሩን አረጋግጠናል።በመሆኑም ህዝቡ እንዲረጋጋ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።"

የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
🥳መልካም የትንሳኤ በአል እያልን የበአል ልዩ ቅናሽ ይዘን መጥተናል🥳
https://tttttt.me/getitonlinee
የወንድም የሴትም
🎯ኦርጂናል ጥሩ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች
🎯የስጦታ ጥቅሎች(package)🎁
🎯ኦርጂናል ሰአቶች
🎯 ቦርሳዎች እና የውበት መጠበቂያዎች
🎯 አልባሳት እና ጫማዎች

🎯ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ በ0929011031

🎯አድራሻ፣ ቦሌ መድሀኒያለም
ያሉበት ቦታ ድረስ በነጻ እናደርሳለን
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ ይሁኑ https://tttttt.me/getitonlinee
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
“በህዳሴው ግድብና በፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች ከሽፈዋል”

– የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

በህዳሴው ግድብና በከፍተኛ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች መክሸፋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ገለፀ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያን መልካም ነገር ማየት በማይፈልጉ የውስጥና የውጪ ኃይሎች የሚደገፉ አካላት ህዳሴው ግድብ ላይ በተቀናጀ መልኩ የሳይበር ጦርነት ከፍተው ነበር። ጥቃቶቹ ምንም ጉዳት ሳያደርሱ እንዲመክኑ ተደርጓል።

በተመሳሳይም በኢትዮጵያ ከፍተኛ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ በርካታ የሳይበር ጥቃቶች በባለሙያዎች ጥረት እንዲከሽፉ ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል።

የሃገሪቱን ሰላምና ዕድገት በማይፈልጉ ሃገራት የሚደገፍ ድርጅት የህዳሴው ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል በማቀድ ‘ብላክ ፒራሚድ ወር’ በሚል ስያሜ የሳይበር ጦርነት ከፍቷል። ይሁንና የጥፋት አላማ አቅደው ሲያሴሩ የነበሩት ሁሉ እንዳሰቡት ሕልማቸው ሳይሳካ ተጨናግፏል ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳስታወቁት፤ ከህዳሴው ግድብ ውኃ ሙሌት ጋር በተያያዘ ብላክ ፒራሚድ ወር የሚባል የኮምፒውተር ቫይረስ ተሠርቶ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ተደርጓል። በተለይም የፋይናንስ ተቋማት የሚጠቀሙባቸውና እርስ በእርሳቸው የተሳሰሩ 37 ሺህ ኮምፒውተሮችን ላይ ጥቃት በመፈጸም...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=72108

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ሀዘንን ለመግለጽ በቀብር ስነ ስርዓት ላይ በተተኮሰ ጥይት የአስር ልጆች እናትን ጨምሮ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ!

በሰሜን ሸዋ ዞን ጅዳ ወረዳ ለሀዘን መግለጫ በሚል በተተኮሰ ጥይት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡በክስተቱ ህይወታቸዉን ያጡት የመጀመሪያ ሟች የ55 ዓመት እድሜ ያላቸውና የአስር ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ሎሚ ሎሜታ ሲባሉ ሁለተኛዋ ሟች ወጣት ዲቃ ዘውዴ የሁለት ልጆች እናት ነበሩ፡፡

ሁለቱም ግለሰቦች የሰሜን ሸዋ ዞን ጅዳ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ አደጋው ባለፈው ሳምንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ የሟቾች ዘመድ በሆኑት በአቶ እሸቱ ገለልቻ የቀብር ስነስርዓት ላይ በተገኙበት ወቅት በአካባቢው የቆየ ጥይት የመተኮስ ባህል መሰረት በቀብር ስነስርዓቱ ላይ በአቶ ሽፈራው ገለልቻ በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል፡፡

አቶ ሽፈራው ገለልቻ በባህሉ መሰረት ሀዘናቸውን ለመግለጽ በአካባቢው ከነበሩት የቅርብ ጎደኛቸው ከሆኑት አቶ ዳኜ አበራ መሳሪያ በመዋስ ፈረስ ላይ በመሆን በተኮሱት ጥይት ፈረሱ በመደንበሩ እና መሳሪያው አውቶማቲክ በመሆኑ ምክንያት በመባረቁ ህይወታቸዉን ካጡት ሰዎች በተጨማሪ አንድ ሰው ላይ ቀላል የሚባል ጉዳት እንደደረሰበት በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ፖስ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ኮማንደር ታዲዮስ ዘውገ ተናግረዋል፡፡

በቀብር ስነስርዓቱ ላይ በተከሰው ያልተጠበቀ አደጋ ምክንያት የቀብር ስነስርዓቱ ለሰዓታት የተራዘመ ሲሆን የመሳሪያው ባለቤት የሆኑት አቶ ዳኜ አበራ እስካሁን ያሉበት አለመታወቁን ነገር ግን ጥይቱን የተኮሱት አቶ ሽፈራው ገለልቻ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ታዲዮስ ዘውገ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa