YeneTube
120K subscribers
31.2K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጎንደር በተከሰተው የፀጥታ ችግር ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ 373 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል - የአማራ ክልል ሰላም ግንባታ እና የሕዝብ ደህንነት ቢሮ

በጎንደር በተከሰተው የፀጥታ ችግር ከፍተኛ ሚና የነበራቸው 373 ግለሰቦች በፀጥታ መዋቅሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአማራ ክልል ሰላም ግንባታ እና የሕዝብ ደህንነት ቢሮ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በቡድን በመንቀሳቀስ ለዝርፊያ እና ለቃጠሎ ተሰማርተው በመገኘት እና የግጭቱ ፊትአውራሪ በመሆን ለተፈጠረው ግጭት ምክንያት መሆናቸውን የቢሮው ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገልጸዋል።

[AMC]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በስልጤ ዞን በቤተክርስቲያናት እና በቤተአምልኮዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት ጉባኤው አወገዘ!

መንግስት ሕግና ስርአትን ለማስፈፀም ቀደም ብሎ ያወጣቸውን ህጎችን ሁሉ ተፈፃሚ ሊያደርግ ብሏል የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናት እና በፕሮቴስታንት ቤተ አምልኮዎች ላይ ተፈጽሟል ያለውን የወንጅል ድርጊት አውግዟል፡፡

ጉባኤው ወንጀልን በሌላ ወንጀል ለማረም መሞከር ሕገ ወጥነት ብሏል፡፡ተግባሩ በየትኛውም ሃይማኖት ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም በላይ ደረቅ ወንጀልና በህግ ሊያስጠይቅ የሚገባው ተግባር ነው ብሎ በጽኑ ያምናልም ብሏል ጉባኤው፡፡

ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ የተፈፀመወን አስነዋሪ ተግባርን አስመልክቶ ተግባሩን የሚያወግዝ መግለጫ መውጣቱን ያስታወሰው ጉበኤው፤ ትናንት በወራቤ በሆነው እጅጉን እንዳዘነም ገልጿል፡፡

“ሁሉም ሃይማኖቶች ሰላምን የሚሰብኩ፣ ትህትናን የሚስተምሩና ለሌሎች ስለመኖርና መስዋዕት ስለመክፈል የሚገዳቸው እንደሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም በሃይማኖት ስምና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚፈፀመው ሁሉ ሕገ ወጥና ደረቅ ወንጀል እንደሆነ ታውቆ መንግስት ሕግና ስርኣትን እንዲያስጠበቅ ጉባኤያችን አበክሮ ይጠይቃል”ም ብለዋል ጉባኤው፡፡መንግስት ሕግና ስርአትን ለማስፈፀም እንዲችል ቀደም ብሎ ያወጣቸውን ህጎችን ሁሉ ተፈፃሚ ሊያደርግ ይገባል ሲልም አክሏል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
Forwarded from YeneTube
**ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።


አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።

መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ

ለጤናወ መፍትሄ👇

https://tttttt.me/meritibe
ላልተወሰነ ጊዜ አዲስ መታወቂያ መስጠት ማቆሙን የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ!

ላልተወሰነ ጊዜ አዲስ መታወቂያ የመስጠት አገልግሎት ማቆሙን የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የመታወቂያ፣ የልደት፣ የጋብቻ እና የሞት ማስረጃዎችን ይመዘግባል፤ ዜጎች በሚፈልጉበት ወቅትም አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡

በአገልግሎት አሰጣቱ ውስጥ በተለይም የመታወቂያ አገልግሎቱ ላይ በተቋሙ ውስጥ እና ከተቋሙ ውጭ ባሉ ሃሰተኛ ማስረጃን በሚያድሉ ግለሰቦች የተነሳ ለማይገባቸው ሰዎች መታወቂያ አላግግባብ እየተሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክትር ዶክተር ታከለ ነጫ ገልጸዋል፡፡

ህገ ወጥ ድርጊቱን ሲፈጽሙ የተያዙ ግለሰቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡የነዋሪነት መታወቂያ ለማግኘት ሲባል ህገወጥነት እየተባባሰ በመምጣቱ ችግሩን በሚገባ ለማጥራት እንዲቻል በከተማ አስተዳደሩ ደረጃ በተላለፈ ውሳኔ መሰረት አዲስ መታወቂያ እንዳይሰጥ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱን ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ታከለ ገልጸዋል፡፡

አገልግሎቱ ላልተወሰነ ጊዜ ታግዶ የሚቆይ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሪክተሩ፤ በህወጥ ድርጊቱ ውስጥ የተሳተፉ አካላትን ወደ ህግ የማቅረብ እና ተቋሙ ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥነቶችን የማጥራት ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡የመታወቂያ እድሳትም ሆነ ሌሎች የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶች ባሉበት ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ዛሬ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው!

በአዲስ አበባ ዛሬ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው። የአዲስ አበባን የአውራ ጎዳና መንገዶችን ተከትሎ እየተካሄደ ባለው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተሳተፉበት ነው።

የተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ታላላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር ሲያዘጋጁ ቆይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ኢድን በአገር ቤት እናክብር በማለት “ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ የገቡ እንግዶችም በዛሬው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ እየተሳተፉ መሆኑም ተገልጿል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን የምርመራ ጋዜጠኝነትን በሥርዓት የሚመራ መመሪያ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት እንደተናገረ የዋዜማ ሪፖርተር ዘግቧል።

የምርመራ ጋዜጠኝነት በስነ ምግባር ካልተመራ፣ ማኅበራዊ ፍትህን በማስፈን ፋንታ የግለሰብ ጥቅሞች አስከባሪ እንደሚሆን ባለሥልጣኑ ተናግሯል። መመሪያውን የሚያዘጋጀው ከባለሥልጣኑ፣ ከስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን እና ከእንባ ጠባቂ ተቋም የተውጣጣ ኮሚቴ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን በቅርቡ የምርመራ ጋዜጠኝነት እንደሚጀምሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረው ነበር።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
የሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር አሰራጭተዋል የተባሉ ስድስት መገናኛ ብዙኃን በፌደራል ፖሊስ ምርመራ ሊደረግባቸው ነው!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር አሰራጭተዋል ባላቸው ስድስት መገናኛ ብዙኃን ላይ ምርመራ እንዲካሄድባቸው ሰነዶች አደራጅቶ ለፌደራል ፖሊስ መላኩን አስታወቀ። ባለሥልጣኑ ምዝገባ ሳያከናውኑ በበይነ መረብ አማካኝነት በህገወጥ መልክ የሚዲያ ስርጭት ላይ የተሰማሩ 25 ድርጅቶችን በህግ ተጠያቂ የማድረግ ሂደት መጀመሩንም ገልጿል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ይህን ያስታወቀው ዛሬ አርብ ሚያዝያ 21፤ 2014 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለህግ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ነው። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ እንዳሉት፤ መስሪያ ቤታቸው ባለፈው ዘጠኝ ወር ባከናወነው የሞኒተሪንግ ስራ በስድስት መገናኛ ብዙሃን በተሰራጩ 10 ፕሮግራሞች ላይ የህግ ጥሰቶች ተስተውለዋል።

“ከሐሰተኛ [መረጃ] እና ጥላቻ [ንግግር] ጋር ተያይዞ አስር ፕሮግራሞች ላይ የህግ ጥሰት በመስተዋሉ ፋይሉን አደራጅተን ለህግ አስፈጻሚ አካላት፣ ለፌደራል ፖሊስ ጥቆማ አቅርበናል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የህግ አስፈጻሚ አካላት በሚያደርጓቸው ምርመራዎች ላይ የተቋሙን ሙያዊ ድጋፍ በሚፈልጉበት [ጊዜ] ሁሉንም የጠየቁትን ጥያቄ በህጉ እና በህጉ ብቻ መሰረት አድርገን ሙያዊ ድጋፍ ሰጥተናል” ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ አስረድተዋል።

አቶ መሐመድ የመገናኛ ብዙኃኑን ማንነት በስም ከመጥቀስ ቢቆጠቡም፤ በንግድ መገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የተሰማሩ እንደሆኑ ግን በሪፖርታቸው ላይ አመልክተዋል። እነዚህ መገናኛ ብዙኃን “ሚዛናዊነት የጎደላቸው እና የአንድ ወገን ሀሳብና ፍላጎትን የሚያንጸባርቁ አድሏዊ ዘገባዎችን በማቅረብ” የህግ ጥሰቶችን መፈጸማቸውንም ጠቁመዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🥳መልካም የትንሳኤ በአል እያልን የበአል ልዩ ቅናሽ ይዘን መጥተናል🥳
https://tttttt.me/getitonlinee
የወንድም የሴትም
🎯ኦርጂናል ጥሩ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች
🎯የስጦታ ጥቅሎች(package)🎁
🎯ኦርጂናል ሰአቶች
🎯 ቦርሳዎች እና የውበት መጠበቂያዎች
🎯 አልባሳት እና ጫማዎች

🎯ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ በ0929011031

🎯አድራሻ፣ ቦሌ መድሀኒያለም
ያሉበት ቦታ ድረስ በነጻ እናደርሳለን
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ ይሁኑ https://tttttt.me/getitonlinee
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
133ኛው የላብ አደሮች ቀን በአዲስ አበባ በመከበር ላይ ነው!

በዓለም ለ133ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ47ኛ ጊዜ የሚከበረውን የላብ አደሮች ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም በተለያዩ ሁነቶች በመከበር ላይ ይገኛል።የኢትዮጵያ ሠራተኛና ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ሠራተኛ ጋር በመሆን እየታሰበ ነው የሚገኘው።

በከተማው የሚገኙ የመንግስትና የግል ሠራተኞች መብት አለመጠበቅ፣ የኑሮ ውድነትና የሚያገኙት ደሞዝ አለመጣጣም፣ ከጊዜ ወደጊዜ ግጭቶች መከሰት፣ ዲሞክራሲ በፈተና ውስጥ መግባትና ሌሎች ችግሮች እንዲቀረፉላቸው መጠየቃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።በየዓመቱ እ.ኤ.አ ግንቦት 1 ቀን የሚከበረው የላብ አደሮች ቀን (ሜይ ዴይ) የሰራተኞችን መብት ማስከበር ዋነኛ አላማው ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መጪውን የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በወልድያ የሚገኙትን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዕዞች ጎበኙ!

መጪውን የኢድ አልፈጥር በአል ምክንያት በማድረግ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና ከፍተኛ የመንግሥት እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር በመሆን፣ በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ የሚገኙትን የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የደቡብ፣ ምሥራቅ፣ 6ኛ እና 8ኛ ዕዞችን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለመኮንኖች ባደረጉት ንግግር ዝግጁነታቸውን አጠናክረው በመቀጠል 1) የማሸነፍ ዕድላቸውን እንዲያሰፉ፣ 2) ድል አድራጊ ሰብዕናን እንዲገነቡ እና 3) ለስጋት ተጋላጭነትን እንዲቀንሱ አበረታተዋል።

ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ማፍራት እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ መንገዱን መጥረግ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።

-PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በጋራ ባደረጉት ክትትል በቦሌ ክፍለ ከተማ ከመኖሪያ ቤት ጀርባ በማገዶ እንጨት ተሸፍኖ በድብቅ የተቀመጠ 10 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ተያዘ።

ከህብረተሰቡ በተገኘው ጥቆማ መነሻነት በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር የዋለው 7 ባለሰደፍ እና 3 ታጣፊ ክላሽን-ኮቭ ጠመንጃዎች መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው የጦር መሳሪያው የተያዘው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አቦ መሻገሪያ መቃብር ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኙ መኖሪያ ቤቶች በአንዱ ከቤቱ ጀርባ በሚገኝ የማገዶ ማስቀመጫ ስፍራ ላይ በሸራ ተጠቅልሎ በእንጨት ተሸፍኖ በድብቅ በተቀመጠበት ነው።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ ሲሆን፥ ህብረተሰቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በህዝብ እና በሃገር ላይ የሚያመጣውን የደህንነት አደጋ ተገንዝቦ ወንጀሉን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ጥቆማ እና መረጃ በመስጠት እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አሊባባ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ አገልግሎት የመጀመር አላማ እንደሌለው አስታወቀ!

የቻይናው ግዙፍ የኢኮሜርስ ኩባንያ አሊባባ ከኢትዮጵያዊው ስራ ፈጣሪ ኤርሚያስ አመልጋ ጋር በኢትዮጵያ የበይነ መረብ ግብይት አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምሩ ሲገለጽ ቢቆይም የኩባንያው አለማቀፍ ግኑኝነት ሃላፊ ሉይካ ማክ እና የአውሮጳ፣ መካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ ማጃ ሃዉክ በኢትዮጵያ ስራ ለመጀመር ስምምነት እንደሌላቸው ለሪፖርተር የእንግሊዘኛው እትም ተናግርዋል።

ሙሉ ዘገባውን ማንበብ ከፈለጉ:
https://www.thereporterethiopia.com/article/alibaba-refutes-ermias-amelgas-ecommerce-partnership-claims

@YeneTube @FikerAssefa
1443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ሰኞ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አስታወቀ!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት 1443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የሸዋል ወር ጨረቃ ዛሬ ማምሻውን ባለመታየቷ ሰኞ ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚከበር አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በዋጋ ንረት ምክንያት ግንባታቸው ላልተጠናቀቁ መንግሥታዊ የግንባታ ፕሮጀክቶች የውል ማሻሻያ ሊደረግ ነው!

በዓለም አቀፍና አገራዊ ምክንያቶች የተነሳ በኮንስትራክሽን ግብዓቶች ላይ የተፈጠረን የዋጋ ንረት ለማስተካከል ሲባል፣ ውላቸው ላይ የዋጋ ማስተካከያን ያላካተቱ የመንግሥት የግንባታ ፕሮጀክቶች፣ ከኮንትራክተሮች ጋር ያላቸው ውል ማሻሻያና ዕድሳት ሊደረግለት መሆኑ ተገለጸ፡፡

መንግሥት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ለወራት ሲያደርገው በቆየው ጥናት ላይ ተመሥርቶ ሲሆን፣ ውሳኔው በማክሮ ኢኮኖሚክ ኮሚቴ ስምምነት ተደርሶበት ከገንዘብ ሚኒስቴር የመጨረሻ ፊርማ እየተጠበቀ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ግንባታ ፕሮጀክቶች የዋጋ ጭማሪ ማስተካከያን በተመለከተ ለአምስት ወራት ገደማ ጥናትና ውይይት ሲደረግ መቆየቱን ለሪፖርተር የተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ (ኢንጂነር) ናቸው፡፡ በውሳኔው ማሳለፍ ሒደት ውስጥ የገንዘብ፣ የፍትሕ፣ የፕላንና ልማት፣ የከተማና የመሠረተ ልማት ሚኒስቴሮች፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር መሳተፋቸውን አስረድተዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ!

ኢድ ሙባረክ!