YeneTube
120K subscribers
31.2K photos
480 videos
79 files
3.82K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የዊክሊክስ መስራች የሆነዉ ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ መንግስት ተላልፎ እንዲሰጥ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

አዉስትራሊያዊዉ ኤዲተር፣ ጸሀፊ እና አክቲቪስት ጁሊያን አሳንጅ እ.ኤ.አ በ2010 በአሜሪካ የጦር ሃይሎች መረጃ ተንታኝ ቼልሲማኒንግ አማካኝነት ባገኘዉ እና ባሰራጨዉ ሾልኮ የወጣ መረጃ ምክንያት አለምአቀፋዊ ትኩረትን አግኝቶ ነበር፡፡

የለንደን ፍርድ ቤት አሳንጅ ለአሜሪካ መንግስት ተላልፎ ይሰጥ የሚለዉን የርክክብ ትዕዛዝ ለእንግሊዝ መንግስት ከላከ በኋላ ፣ እዛዉ አሜሪካ ዉስጥ በስለላ ህግ እንደሚዳኝ ተገልጿል፡፡

በ 2010 ዊክሊክስ ባሳተመዉ በሺዎች የሚቆጠሩ ምስጢራዊ ፋይሎች እና ዲፕሎማቲክ ግንኙነቶች ላይ ያተኮረ ጽሁፍ አሳንጅ በአሜሪካ መንግስት በ18 የወንጀል ክሶች የሚፈለግ ሲሆን፣ በዚህ ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 175 አመታት የሚደርስ የእስር ፍርድ እንደሚጠብቀዉም አልጄዚራ ዘግቧል።

Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በቅርስነት ከየተመዘገበው አንበሳ መድኃኒት ቤት በር ተሰብሮ ዕቃዎች እንዲወጡ ተደረገ!

(በዶይቸ ቨለ)

አዲስ አበባ ከተማ ፒያሳ የሚገኘው እድሜ ጠገቡ አንበሳ መድኃኒት ቤት ለረጅም ዐመታት ከነበረበትና በቅርስነት ከተመዘገበው ቤት ዛሬ ማለዳ ዕቃዎቹ እንዲወጡ ተደረገ። የመድኃኒት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፀጋዬ ታደሰ በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት፦ ዛሬ ማለዳ «ከ12 ሰዓት ጀምሮ የድርጅቱ የጥበቃ ሠራተኞች የመድኃኒት ቤቱ መግቢያ በር እየተሰበረ መሆኑን እንደነገሯቸውና ቦታው ላይ ሲደርሱ በር ተሰብሮ ዕቃዎች እየተጫኑ እንዳገኟቸው» ተናግረዋል።

ይህንን ድርጊት የፈፀሙት እነማን እንደሆኑ ተጠይቀው ሲመልሱ «ማን እንደሆኑ አናውቅም፣ ከክፍለ ከተማ ታዘን ነው የሚሉ ናቸው» ብለዋል። የአዲስ አበባ መስተዳድር ፖሊሶች ነበሩ የሚሉት ወይዘሮ ፀጋዬ ወደ ሥፍራው ስንደርስ «እኛም ለሰላሳ ደቂቃ እንዳንገባ ተከልክለን ቆይተን መታወቂያችን እየታየ ነው የገባነው» ብለዋል።

ዶይቼ ቬለ በሥፍራው ተገኝቶ ባደረገው ምልከታ ከመድኃኒት ቤቱ ውስጥ ዕቃዎች «አይሱዙ» ተብለው በሚጠሩት የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ እየተጫኑ ተሽከርካሪዎቹም የጫኑትን እየያዙ ሽቅብ ወደ ጣይቱ ሆቴል በሚወስደው መንገድ ሲጓዙ ተመልክቷል።

መድኃኒት ቤቱ በሚገኝበት መስመር ቁልቁል ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ የሚወስደው መንገድ እስከ ረፋዱ 4 ሰዓት ለተሽከርካሪዎች ዝግ ሆኖ፣ አሽከርካሪዎች በዚያ መስመር ማለፍ እንደማይችሉ በፖሊሶች እየተገለፀላቸው ሲመለሱ እንደነበርም ታዝቧል። የዜናው ዘጋቢም የመድኃኒት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ገብቶ ቀረፃ ለማድረግ ፈቃድ አላገኘም።

ዕቃው ወዴት እየተጫነ እየተወሰደ ነው? ያልናቸው ሥራ አስኪያጇ «የመድሃኒት ቤቱ ንብረት የሆኑ አነስተኛ ተሽከርካሪዎችን ተጠቅመን በየ ዘመድ ቤት እየጫንን ነው» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ከመንግሥት በኩል የተዘጋጀ ምትክ ቤት ወይም ቦታ ስለመኖሩም ጠይቀናቸው «የለም» ብለው መልሰዋል።አክለው እንደነገሩንም የመድኃኒት ቤቱ ሠራተኞች ወደ ቤቱ ገብተው ዕቃዎችን በመጫን ሲያግዙ ውለዋል።

በጉዳዩ ላይ የተጠየቀው በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ አንክ ዶንኮህ ጉዳዩ እጅግ እንዳሳሰባቸው ገልፀው «ክስተቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ እና መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ በሚያደረጉ የጀርመን ባለሀብቶች ላይ ትልቅ ተፅእኖ ይሮረዋል» ብለዋል።

አንበሳ መድኃኒት ቤት ላለፉት ስምንት ዐሥርት ዐመታት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መድኃኒት የሚያቀርብ ጥንታዊ የጀርመን ድርጅት መሆኑንም ተናግረዋል።ፒያሳ የሚገኘዉ እና በቅርስነት የተመዘገበዉ የአንበሳ መድሐኒት ቤት ባለቤት ጀርመናዊዉ ካርል ሂልደብራንት በንጉሱ ዘመን አባታቸዉ ኩርት ሂልደብራንድት የመሰረቱትን መድሐኒት ቤት በማስቀጠል የቆየ መሆኑ ይታወቃል።ድርጅቱ የመድሃኒት ሽያጭ አገልግሎት፣ የቅመማ እና የሕክምና ቁሳቁስ ማስምጣት ላይ የተሰማራ ነው።

የቤቱ ባለቤት የሆነው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ «አንበሳ ፋርማሲ እና ኒዮን አዲስ የተባሉ ድርጅቶች በኪራይ ሲገለገሉበት የነበሩበት እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ንብረት የሆኑ ቤቶች፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቅርስነት ይዘታቸው ሳይቀየር፣ ባሉበት ምንም ዓይነት የቅርጽና የይዘት ለውጥ ሳይደርግባቸው በአካባቢው ከሚገነባው አዲስ ግንባታ ጋር ለአልሚው ባለሀብት እንዲተላለፉ ተደርጓል» ብሏል።

በቅርሶቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማይደርስባቸው በኮርፖሬሽኑ እና በከተማ አስተዳደሩ መካከል ሥምምነት ላይ መደረሱንም ዐስታውቋል።«ቅርሶችን በመጠበቅ እና በመንከባከብ፤ ቅርስ ጥበቃ እና ልማት ሚዛኑን አስጠብቆ እንዲሔድ ማድረግ ሌላኛው ከድህነት መውጫ መንገድ ሊሆን ይገባል» ያለው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን «በእርጅና ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን እና ቤቶችን ደግሞ ለኹላችን ጥቅምና እድገት በሚያስገኝ መልኩ ማልማትም ተገቢ ነው» ብሎ እንደሚያምንም ዐስታውቆ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።


አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።

መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ

ለጤናወ መፍትሄ👇

https://tttttt.me/meritibe
የሱዳን ተቃዋሚዎች በተመድ እና በአፍሪካ ህብረት የቀረበውን የ‘እናደራድራችሁ’ ጥያቄ ሳይቀበሉ ቀሩ!

ተቃዋሚዎቹ ከድርድሩ በፊት ጦሩ ስልጣን እንዲያስረክብ ጠይቀዋል

የሱዳን ተቃዋሚዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በአፍሪካ ህብረት የቀረበላቸውን የየ‘እናደራድራችሁ’ ጥያቄ ሳይቀበሉ ቀሩ፡፡
ተቃዋሚዎቹ ከድርድሩ በፊት ሊተገበሩ ይገባል ያሏቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አስቀምጠዋል፡፡

ከቅደመ ሁኔታዎቹ አንዱ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ይመራ የነበረውን የሲቪሊያን አስተዳደር ከሽግግር መንግስቱ አስወግዶ ስልጣን የያዘው የሃገሪቱ ጦር ስልጣኑን ያስረክብ የሚል ነው፡፡

በሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራው የሃገሪቱ ጦር ባሳለፍነው ወርሃ ጥቅምት መጨረሻ "የእርምት ነው" በሚል በወሰደው እርምጃ የሃምዶክን አስተዳደር በአዲስ መተካቱ ይታወሳል፡፡

Via Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
የሳተላይ ምስሎች ታጣቂዎች ዶግ አመድ ያደረጓትን የኦሮሚያ አንስተኛ ከተማ አሳዩ!

ሰኞ ጥር 16/2014 ያጋጠመው ክስተት የአንዲት መንደር ነዋሪ አርሶ አደሮችን ሕይወት እስከ ወዲያኛው የቀየረ ክስተት ነበር።በዕለቱ በምዕራብ ኦሮሚያ በምትገኘው እና ፊጤ በቆ ወደ ምትሰኘው መንደር ታጣቂዎች ዘልቀው ገብተው፤ ተኩስ ከፈቱ፤ መኖሪያ ቤቶች ላይ እሳት ለኮሱ፣ የሰው ሕይወት ቀጠፉ።ከጥቃቱ ያመለጡ የመንደሯ ነዋሪዎች ሕይወታቸውን ለማዳን እግሬ አውጪኝ ብለው ቀያቸውን ጥለው ተሰደዱ። ይህ ዘገባ እስከ ተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የፊጤ በቆ ነዋሪዎች ወደ መንደሯ አልተመለሱም።

ፊጤ በቆ የምትገኘው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ገሊላ ወረዳ ውስጥ ነው።ቢቢሲ የሳተላይት ምስሎችን በመጠቀም፣ በአካባቢው የተነሱ ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በመመርመር እንዲሁም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ እና ቤታቸው የተቃጠለባቸው ሰዎችን በማነጋገር በመንደሯ የተፈጠረው ምን እንደሆነ ማረጋገጥ ችሏል።በተለያዩ የወለጋ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ለሚከሰተው ግድያ፣ ማፈናቀል፣ መኖሪያ ቤት እና እህል የማቃጠል ተግባራት ሶስት ቡድኖችን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር (መንግሥት ሸኔ) የሚለው ቡድን፣ የአማራ ታጣቂዎችን እንዲሁም የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ናቸው በነዋሪዎች በጥፋት የሚወነጀሉት።ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ የ54 ዓመት አዛውንት ተወልደው ካደጉባት መንደር ተፈናቅለው ከስምንት የቤተሰብ አባላታቸው ጋር ተደብቀው ይገኛሉ።

"ከባድ መሳሪያዎች የታጠቁ ናቸው። የግንቦት 7 የሚባለውን ባንዲራ ነው የሚይዙት። ዱላ ይይዛሉ እንዲሁም ባንዲራውን ግንባራቸው ላይ አስረው ነው የሚንቀሳቀሱት።"

በመንደሯ የሆነውን አይቻለሁ የሚሉት እኚህ አዛውንት "የአማራ ታጣቂዎች ናቸው" የሚሏቸው ቡድኖች በመንደሯ ላይ ሰኞ ጥር 16/2014 አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ የጀመሩት ጥቃት እስከ ምሽት 3 ሰዓት መዝለቁን ያስረዳሉ።

"እስከ ሶስት ሰዓት ድረስ እዛው ነበሩ። ሲዘፍኑ ነበር። የሚያቃጥሉትን አቃጥለው የሚወስዱትን ወስደው [ሄዱ] . . . የተመቻቸውን ነው የወሰዱት፤ የቀረውን ደግሞ በመጥረቢያ ነው የፈለጡት።" በማለት የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል።

እኚህ አዛውንት መኖሪያ ቤታቸው መቃጠሉን እና በገንዘብ "ይህ ነው" ብለው መገመት ያልቻሉት ንብረት እንደወደመባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"ከሶስት ሄክታር መሬት ተሰብስቦ የነበረው በቆሎ እዛው ተቃጥሏል። ሞተር ወስደውብኛል። ቤቴ ከነ ሙሉ ንብረቱ ተቃጥሏል። ሕይወታችን ብቻ ነው የተረፈው. . . ።" ይላሉ

ዘገባው የቢቢሲ ነው ሙሉውን ለማንበብ:

https://www.bbc.com/amharic/news-61153195?at_custom2=facebook_page&at_medium=custom7&at_custom3=BBC+News+Amharic&at_campaign=64&at_custom4=BA3DBCAA-C132-11EC-AA64-17B096E8478F&at_custom1=%5Bpost+type%5D

@YeneTube @FikerAssefa
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በእስር ላይ የነበሩት አመራሮቹና ልዑካን ፣ ከእስር መፈታታቸው አሳውቋል።

በአሁን ሰዓት አመራሮቹ እና ልዑካኑ ጉዟቸውን ለማድረግ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ሄደዋል ሲል አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጦርነቱ ጉዳት ከደረሰባቸው 42 ሆስፒታሎቹ መካከል 36 ወደ ስራ ገቡ!

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የህወኃት ቡድን በተቆጣጠራቸው የአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ ከሶስት ሺ በላይ የጤና ተቋማት ውድመት እና ዝርፊያ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ውድመት ከደረሰባቸው የጤና ተቋማት ውስጥ 42ቱ ሆስፒታሎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 532 ያህል ጤና ጣቢያዎችና የጤና ኬላዎች ናቸው።

ጉዳት ከደረሰባቸው 42 ሆስፒታሎች መካከል 40 የሚሆኑት በአማራ ክልል ሲሆኑ ቀሪ ሁለት ሆስፒታሎች በአፋር ክልል ናቸው።የጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች እና በአዲስ አበባ እና ሌሎች ክልሎች ከሚገኙ ሆስፒታሎች በተደረገ ድጋፍ እና ጥራት 36 ሆስፒታሎች ወደ ስራ እንዲገቡ እና አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ዶክተር ተሾመ ጨምረው ተናግረዋል።

ዳግም ወደስራ ከገቡት 36 ሆስፒታሎች ውስጥ 35ቱ በአማራ ክልል ሲሆን አንድ ሆስፒታል ደግሞ በአፋር ሲሆን በአማራ ክልል አምስት በአፋር አንድ ሆስፒታል ባለው የፀጥታ ችግር ወደ ስራ ማስገባት አለመቻሉን ዶክተር ተሾመ አንስተዋል። 26 የሚሆኑት ሆስፒታሎች አገልግሎት እንዲሰጡ የተደረገው በአዲስ አበባ እና ሌሎች ክልሎች ከሚገኙ ሆስፒታሎች በተደረገ ድጋፋ ሲሆን አስሩ ሆስፒታሎች በጤና ሚኒስቴር አጋር አካላትን በማስተባበር የህክምና ግብዓት በማቅረብ እና ጥገና በማድረግ ወደስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የጸሎተ ሐሙስ የተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓቶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እየተካሄደ ይገኛል።

በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንም ከማለዳው አንስቶ የተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከናወኑ ነው።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጻጻሳት፣ ካህናት እና ምዕመናን ተገኝተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
"ትክክለኛው ተወካይ ወደ መድረኩ እንዲመጣ እንሰራለን" - አገራዊ የምክክር ኮሚሽን

11 ኮሚሽነሮች ያሉት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና ሀላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።በመድረኩ ኮሚሽኑ የውይይት ሂደቱ ካቀፋቸው አራት ምዕራፎች (ቅድመ-ዝግጅት፣ ዝግጅት፣ ሂደትና አተገባበር) መካከል በቀዳሚው ሰራሁ ያላቸውን ተግባራት አብራርቷል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ " የኮሚሽኑ አባላት እርስ በእርስ ትውውቅ እንዲያደርጉ፣ የምክክር ፅንሰ ሀሳብ ላይ ውይይት በማድረግ ኮሚሽነሮቹ ተቀራራቢ አረዳድ እንዲኖራቸው ተጥሯል።" ብለዋል።በዚሁ ቀዳሚ ምዕራፍ "አመቺ የስራ ከባቢን መፍጠር፣ ሎጂስቲክ ማሟላት" ሌላኛው የተከናወነ ስራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከመድረኩ " ኮሚሽኑ የታችኛው የህብረተሰብ ክፍልን የሚያገኝበት መንገድ እንዴት ያለ ነው?፤ በቀደመው የግንኙነት ሰንሰለት ከሆነ "በካድሬዎች ሊጠለፍ ይችላል" የሚል አስተያየት ተሰንዝሯል።

ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ዋና ኮሚሽነሩ "ትክክለኛውን ተወካይ ለማግኘት ኮሚሽኑ የራሱን "ሜካኒዝም" ይከተላል፤ ትክክለኛውን ወኪል ለማግኘትም እንሰራለን።" ብለዋል።ኮሚሽኑ ከመገናኛ ብዙሃን ሃላፊና ባለሙያዎች ጋር ከመምከሩ አስቀድሞ ከሀይማኖት አባቶችና ሀገር ሽማግሌዎች ጋር መወያየቱም ተነግሯል።

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ባንክ በጦርነቱ የተከሰተው የምግብ ቀውስ 'ሰብአዊ ጥፋት' ያስከትላል ሲል አስጠነቀቀ!

ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ በተከሰተው የምግብ ቀውስ ዓለም "የሰብዓዊ ጥፋት" እያጋጠማት ነው ሲሉ የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ገለጹ።በዓለም አቀፍ ደረጃ ድህነትን ለማቃለል የተቋቋመውን ተቋም የሚመሩት ማልፓስ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ቀውሱ ከቀጠለ የምግብ ዋጋ ንረት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ወደ ድህነት እንደሚገፋና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል።

"ይህ የሰብዓዊ ጥፋት ነው። የተመጣጠነ ምግብ እየቀነሰ ይሄዳል። ምንም ማድረግ ለማይችሉ መንግስታት የፖለቲካ ፈተና ይሆናል። መንስኤ ባይሆንም የዋጋ መናር ያጋጥማቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

የዓለም ባንክ የምግብ ዋጋ በ37 በመቶ ሊጨምር እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል።፣ ይህም "ለድሆች ከፍተኛ የሚባል" ሲሆን "ትንሽ እንዲመገቡ እና እንደ ትምህርት ቤት ላሉት የሚኖራቸውን ወጪ ያሳንሳል። በእውነቱ ይህ ፍትሃዊ ያልሆነ ቀውስ ነው። በጣም ድሃ የሆኑት ላይ የበለጠ ጫናው ያርፋል። ይህ በኮቪድ ወቅት ተመሳሳይ ነበር ።

ተጨማሪ ለማንበብ:

https://www.bbc.com/amharic/news-61172475

@YeneTube @FikerAssega
የሩሲያ ጦር ከቧት የነበረችውን የዩክሬኗን ማሪዎፖል ከተማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ!

የሩሲያ ጦር የማሪዎፖልን ከተማ ዶምባስ ግዛት ለመቀንቀሳቀስ የሚያችል ስትራቴጅካዊ ቦታ መሆኑን ሩሲያ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡የሩሲያ መከላከያ አሁንም በማሪዎፖል የመሸጉ የዩክሬን ወታደሮች መኖራቸውን ገልጿል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአፋር ጨው ማምረቻ ድርጅት ፈቃድ እንዳይታደስ የአፋር ክልል መንግሥት ጠየቀ!

በኢትዮጵያ የማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን 83 በመቶ ድርሻ የተመሠረተው የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማኅበር፣ በአፋር ክልል አፍዴራ የተሰጠው የጨው ማምረት ፈቃድ እንዳይታደስ የአፋር ክልላዊ መንግሥት ጠየቀ።

ጥያቄውን ያቀረቡት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አወል አርባ እንደሆኑ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አወል ጥያቄውን ያቀረቡት ለማዕድን ሚኒስቴር መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማኅበር ላለፉት ሃያ ዓመታት በአፋር ክልል ጨው ለማምረት ሲጠቀምበት የነበረው የማዕድን ፈቃድ በመጪው ሰኔ 2014 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅ በማመልከት፣ የማዕድን ሚኒስቴር የማኅበሩን ፈቃድ ለተጨማሪ ጊዜ እንዳያድስ መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

ለአክስሲዮን ማኅበሩ የተሰጠው የማዕድን ፈቃድ ጊዜ ሲጠናቀቅ ይዞታው ለክልሉ እንዲመለስ፣ በይዞታው ላይ ጨው የማምረት አዲስ የማዕድን ፈቃድ ለአፋር ልማት ድርጅት እንዲሰጥ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

የፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው የኢትዮጵያ የማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን በአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማኅበር ላይ 83 በመቶ ድርሻ በመያዝ ወሳኝ ባለድርሻ ሲሆን፣ ቀሪው 17 በመቶ የሕወሓት ኢንዶውመንት የሆነው ኢፈርትና ሌሎች ባለድርሻዎች የተያዘ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
**ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።


አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።

መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ

ለጤናወ መፍትሄ👇

https://tttttt.me/meritibe
ማንችስተር ዩናይትድ ኤሪክ ቴን ሃግን ቀጣዩ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ፡፡

በዚህም ሃግ ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የማንቸስተር ዩናይትድ አለቃ ሆነው ያገለግላሉ ተብለዋል፡፡

ኢሪክ ቴን ሃግ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ እስከሆኑበት ጊዜ የሆላንዱ አያክስ አምስተርዳም ሲያሰለጥኑ ቆይቷል፡፡ ሃግ 12ኛው የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ መሆናቸው ነው፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
**ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።


አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።

መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ

ለጤናወ መፍትሄ👇

https://tttttt.me/meritibe
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከምደባ ውጪ ባሉ መርሃግብሮች የሚቀበሏቸውን የተማሪዎች የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን እንዲያረጋግጡ ጠየቀ፡፡

ባለስልጣኑ ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ ትምህርት ተቋማቱ ከመንግስት ምደባ ውጪ በማታ እና በርቀት ትምህርት በራሳቸው መልምለው እንዲሁም የተለያዩ መስሪያ ቤቶች በአቅም ግንባታ ሲባል የሚልኳቸውን ተማሪዎችን እንደሚቀበሉ አስታውሷል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በሁዋላ በሚኖር የተማሪዎች ቅበላ ወቅት ሶስት ጉዳዮችን ልዩትኩረት ሰጥቶ መመዝገብ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
በተጨማሪም ፡-
- በግሉ አልያም በመስሪያ ቤት ለድህረ ምረቃ ለመመዝገብ የሚቀርቡ ማመልከቻዎች ከባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ ህጋዊነት እና ትክክለኛነት የተረጋገጠ መሆኑን ማጣራት

- በማንኛውም ደረጃ ከውጭ የተገኙ የትምህርት ማስረጃዎች በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአቻ ግመታ የተሰጣቸው መሆን እና
- የቴክኒክ እና ሙያ የትምህርት ማስረጃዎችም በሚመለከተው አካል ህጋዊነታቸው የተረጋገጠ መሆን እንደሚገባው አሳስቧል፡፡

አያይዞም የሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተበራክተዋል ተብሎ ስለሚታመን፤ በትምህርት ተቋማቱ የሚሰሩ ሰራተኞችን የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን እንዲያረጋግጡ ይሁን ሲል አሳስቧል፡፡

ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልእኮ ያለ ትምህርት ተቋማቱ ማሳካት እንደማይችል ያስታወሰ ሲሆን ዩኒቨርስቲዎች እያበረከቱ ላለውም አስተዋፅኦ እውቅናን እንደሰጠ የላከው መረጃ ያመለክታል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የኤርትራ ዜጎች ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ አለመከልከሉን መንግስት አስታወቀ!

የኤርትራ ዜጎች ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ መንግስት አለመከልከሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ ላይ “የኤርትራ ዜጎች ከኢትዮጵያ እንዳይጡ ይከለከላሉ” በሚል ለቀርበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህም አምባሳደር ዲና፤ መንግስት ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ ተከልክለዋል ስለተባሉትና የኤርትራ ፓስፖርት የያዙ የውጭ ሀገር ቪዛ ያላቸውን ጉዳይ በጥንቃቄ ይመረምራል ሲሉ ተናግረዋል።
በኤርትራውያን በኩል የሚነሳ ቅሬታ ሚኒሰቴር መስሪያ ቤታቸው በተለያየ መልኩ እንደሚሰማ ያነሱት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ “ጉዳዩ በዋናነት ከህግ፣ ከሰነድ እንዲሁም ከደህንነት ጋር የሚያያዝ በመሆኑ መንግስት ነገሮችን በተጠና መልክ ለመስራት እየጣረ ነው” ሲሉ ብለዋል።

የሀገሪቱ ህግ እና ሂደቶች በሚጣረስ መልኩ ኢትዮጵያን ለቆ ለመውጣትና የመቻኮል (እዚህ ሀገር ካልሄድን ወዘተረፈ የሚሉ) ሁኔታዎች ቢኖሩም፤ ሁሉም ነገር ግን በህጉ መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናልም ብለዋል ቃል አቀበዩ።

የ1951ዱን የስደተኞች ኮንቬንሽንና የ1967ቱን ፕሮቶኮልም የፈረመችው ኢትዮጵያ ፣ ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን /ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር/ እና ሌሎች ባለድርሻ አካለት ጋር በመሆን ዓለም አቀፋዊ ኃላፊነቷን በመወጣት ላይ ናት።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት በአስቸኳይ እንዲመሰረት ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኅብር ኢትዮጵያ) ጠየቀ።

ፓርቲው ዛሬ በሰጠው መግለጫ «ኢትዮጵያ በታሪኳ ገጥሟት ከማያውቅ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ክስረት፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ በተለይም የሠላምና መረጋጋት ቀውስ ውስጥ ወድቃለች» ብሏል። የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ የሕግ የበላይነት አለመከበር «መንግሥት አለ ወይ?» ብሎ ከማስጠየቅ አልፎ ሕዝብ ተስፋ ቆርጦ ለመሰደድ የተገደደበት ሁኔታ በአራቱም የአገሪቱ አቅጣጫ እየተስተዋለ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ተመስርቶ ለአጠቃላይ ችግሮች የጋራ መፍትኄ እንዲዘጋጅ መንግሥት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ሊይዝ ይገባልም ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
🌟 ምርቶን ያስተዋውቁ🌟
🌟በ Facebook በ Instagram🌟 በማስተዋወቅ አዳዲስ ደንበኛ ያግኙ
☎️ 0954742475
ከ1000 ብር ጀምሮ በመክፈል ሱቆን | ክሊኒክ | የሚሸጥ መኪና | የሚሸጥ ቤቶን | የሚሰጡትን አገልግሎት እና ምርት | ከየትኛውም ቦታ ሆነው ለአለም ተደራሽ ይሁኑ በአሉን በማስመልከት 15% ቅናሽ ይጠቀሙ

ለመደወል ☎️ 0954742475
ወይም ☎️ 0973071680

ይጠቀሙ
©ቁንጮ ዲጂታል ላብ
የብሪታኒያን ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድ ሂዉማን ራይትስ ዎች ተቸ

ብሪታንያ ተገን ጠያቂ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመመለስ የያዘችውን ዕቅድ ሂዉማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብዓዊ መብት ድርጅት ነቀፈ።ድርጅቱ ስደተኞችን የሰብዓዊ መብት ወደ ማይከበርባት ሩዋንዳ መላክ ተገቢ አይደለም ሲል ዕቅዱን ተችቷል።

@Yenetube @Fikerassefa