YeneTube
120K subscribers
31.2K photos
480 videos
79 files
3.82K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጦርነትና በግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በዚህ አመት ይፈተናሉ – ትምህርት ሚኒስቴር

በጦርነት እና በግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ያላመጡ በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የትምህርት ሚኒስቴር፣ ሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በጋራ መግለጫ እየሰጡ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ ለተማሪዎች አዲስ ውሳኔ መተላለፉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ!

በአማራ ክልል በ2013 የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ ለክልሉ ተማሪዎች አዲስ ውሳኔ መተላለፉን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የ2013 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ጉዳይ ከዚህ ቀጥሎ በተገለፁት ኹለት ውሳኔዎች የሚፈፀም ይሆናል ሲል ቢሮው ገልጿል፡፡

የመጀመሪያው ውሳኔ ከዚህ በፊት በተላለፈው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ከቻሉት የክልሉ ተማሪዎች በተጨማሪ 4 ሺህ 339 ተማሪዎች በመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ቅበላ የሚያገኙ ይሆናል ተብሏል።

እንዲሁም በ2013 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ ነጥብ ያላሟሉ የአማራ ክልል ኹሉም ዞኖች ተማሪዎች በ2014 በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመደበኛ ተማሪነት መፈተን እንዲችሉ መወሰኑን ቢሮው በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መረጃ አስታውቋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከተፈጠረው ችግር አኳያ ውሳኔው ያላረካቸው አካላት ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገመታል ያለ ሲሆን፤ የክልሉ ተማሪዎች በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እድሉን በድጋሜ ማግኘታቸውን እንደ ትልቅ አጋጣሚ አድርገው ለውጤታማነት እንዲጠቀሙበት አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ያሳለፍነው ወር የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ34.7 ከመቶ ጭማሪ አሳየ!

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ የመጋቢት ወር 2014 ዓ/ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ34.7 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት የመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ43.4 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ከየካቲት ወር 2014 ጋር ሲነጻጸር በ1.5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በያዝነውም ወር በአብዛኛው በእህሎች የዋጋ ጭማሪ የታየ ሲሆን የአትክልት ዋጋም ላይ መጠነኛ ጭማሪ ታይቷል፡፡

ሩዝ፣ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንቡራና ምሥር በአብዛኛው የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡በተጨማሪም ወተት፣ አይብና ዕንቁላል፣ ቅመማ ቅመም (በዋናነት ጨውና በርበሬ) ጭማሪ አሳይተዋል፡፡ የምግብ ዘይትና ቅቤ ዋጋ በፍጥነት የጨመረ ሲሆን ቡናና ለስለሳ መጠጦች ተከታታይ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ሩሲያ ኢትዮጵያውያን ወዶ ዘማቾችን እየመለመለች ነው መባሉን አስተባበለች!

የሩሲያ ኤምባሲ በር ላይ ኢትዮጵያዊያኑ ለምን ተሰለፉ ለሚለው ኤምባሲው አል-ዐይን አማርኛ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ መግቢያ በር ላይ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለሩሲያ ዩክሬንን ለመውጋት ለመመዝገብ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው የሚል ምስል በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ በመሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡

አል ዐይን አማርኛ ጉዳዩን በሚመለከት በአዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ጠይቋል።

የኤምባሲው ፕረስ አታቼ ማሪያ ቸርኑኪና ለአል ዐይን እንዳሉት “ሩሲያ ለዩክሬን ጦርነት ኢትዮጵያዊያንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አላወጣችም፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃም ሀሰተኛ ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል።

ይሁንና ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት “በርካታ ኢትዮጵያዊያን በኢሜይል እና በአካል ከሩሲያ ጎን መሆናቸውን እያሳወቁን ነው ለዚህ እናመሰግናለን” ሲሉም አክለዋል።

ኢትዮጵያዊያን ይሄንን እያደረጉ ያለው ረጅም እና ታሪካዊ በሆነው የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ወዳጅነት ላይ ስለሚተማመኑ እንደሆነም ኤምባሲው ተገልጿል።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ሽዋ በተቀሰቀሰ ግጭት ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚወስደው መንገድ መዘጋቱን ነዋሪዎቸ ገለጹ!

ግጭቱ ከአንድ ሳምንት በፊት ተከስቶ በውይይት የተፈታ ቢሆንም ከትናንት ጀምሮ ዳግም ማገርሸቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡በግጭቱ እስካሁን የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉንም ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ገንዘብ ሚንስቴር በግል ባንኮች ሒሳብ የከፈቱ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ሒሳባቸውን ባስቸኳይ እንዲዘጉ ማዘዙን የኢትዮጵያ የባንክ ባለሙያዎች ማኅበር እንደተቃወመው ካፒታል ዘግቧል።

የግል እና የመንግሥት ባንኮች ፕሬዝዳንቶች ዓርብ'ለት ባደረጉት የማኅበሩ ስብሰባ፣ የግል ባንኮች ቅሬታ ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርብ ተወስኗል። ብሄራዊ ባንክ የመንግሥት ተቋማት ገንዘብ እንዲያስቀምጡበት ውክልና የሰጠው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንደሆነ በቅርቡ በደብዳቤ አስታውቆ ነበር። የግል ባንኮች ውሳኔውን የተቃወሙት፣ አድሏዊ እና ነጻ እና ፍትሃዊ የገበያ ውድድርን የሚገድብ መሆኑን በመግለጽ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
🥳መልካም የትንሳኤ በአል እያልን የበአል ልዩ ቅናሽ ይዘን መጥተናል🥳
https://tttttt.me/getitonlinee
የወንድም የሴትም
🎯ኦርጂናል ጥሩ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች
🎯የስጦታ ጥቅሎች(package)🎁
🎯ኦርጂናል ሰአቶች
🎯 ቦርሳዎች እና የውበት መጠበቂያዎች
🎯 አልባሳት እና ጫማዎች

🎯ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ በ0929011031

🎯አድራሻ፣ ቦሌ መድሀኒያለም
ያሉበት ቦታ ድረስ በነጻ እናደርሳለን
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ ይሁኑ https://tttttt.me/getitonlinee
በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ ተካተው ከ3 ዓመት በላይ በእስር ላይ የነበሩ ግለሰቦች ከእስር እንዲፈቱ ታዘዘ!

የቀድሞ የደህንነት ቢሮ ዳይሬክተር በነበሩት በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ ተካተው ከ3 ዓመት በላይ በእስር ላይ የነበሩ ግለሰቦች ከእስር እንዲፈቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ትዕዛዝ አስተላለፈ።አዲሱ በዳሳ፣ ሳሙኤል ጊዲሳና ደርሶ አየነው የተባሉ ተከሳሾች በትናንትናው ዕለት በፍርድ ቤት ከተወሰነባቸው የቅጣት ውሳኔ በላይ በእስር በማሳለፋቸው (የእስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው) ነው ከእስር እንዲፈቱ የታዘዘው።

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ከተከሰሱት በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ ተካተው የነበሩት 17ኛ ተከሳሽ አዲሱ በዳሳ 18ኛ ሳሙኤል ጊዲሳ እና 24ኛ ተከሳሽ ደርሶ አየነው ከጥቅምት ወር 2011 ጀምሮ በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።እነዚሁ ሦስቱ ተከሳሾች በየካቲት 25 ቀን 2014 በነበረ የችሎት ቀጠሮ "ባልሰራንበት ወንጀል አራት ዓመት ታስረናል፤ የተፋጠነ ፍትህ ለማግኘት እንድንችል የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ አንፈልግም።" በማለት ጉዳያቸው ተነጥሎ ፍርድ እንዲሰጣቸው ጠይቀው እንደነበረም ይታወሳል።

በተለይም 24ኛ ተከሳሽ ደርሶ አየነው ያለጥፋቱ አራት ዓመት መታሰሩን ጠቅሶ በእያንዳንዷ ቀናት ቤተሰቦቹ ከቀለብ ጀምሮ መቸገራቸውን ገልጾ ነበር።ፍርድ ቤቱ የፈለገውን ፍርድ ይፍረድብን እና እንረፍ ሲሉ የተፋጠነ ፍትህ እንዲያገኙ እንደሚፈልጉ መግለጻቸው ይታወሳል።

በዚሁ የካቲት 25 ቀን 17ኛና 18ኛ ተከሳሽ የነበሩት አዲሱና ሳሙኤል የቅጣት ማቅለያ አስተያየት አያይዘው በጽሁፍ አቅርበው ነበር።ፍርድ ቤቱም ከክስ መዝገቡን የሦስቱን ተከሳሾች ጉዳይ ነጥሎ መርምሯል።

በዚህም ተከሳሾቹ የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውና ለአገር ልማት ያደረጉትን አስተዋጾ አክለው ያቀረቡትን 5 የቅጣት ማቅለያ ፍርድ ቤቱ ይዞላቸዋል።በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ትላንት ከሰዓት በኋላ በዋለው የችሎት ቀጠሮ፤ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከሉ በተባሉበት አንቀጽ አዱሱ በዳሳና ሳሙኤል ጊዲሳን እያንዳንዳቸውን የ3 ዓመት እስራትና የ3 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን፤ 24ኛ ተከሳሽ ደርሶ አየነውን በተመለከተ ደግሞ በኹለት ዓመት እስራትና በ1 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት አዲሱ በዳሳና ደርሶ አየነው ከታሰሩበት ከጥቅምት ወር 2011 ጀምሮ ታሳቢ ሲደረግ፤ ከቅጣቱ በላይ በመታሰራቸውና የእስር ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ከትላንት ጀምሮ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ መሰጠቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።ሳሙኤል ጊዲሳን በተመለከተም እስካሁን የታሰረበት ጊዜ በመዝገቡ ላይ ያልተካተተ ቢሆንም፤ የታሰረበት የጊዜ መጠን ተጣርቶ በተመሳሳይ ከእስር የሚፈታ ይሆናል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በቪዛ ፖሊሲዋ ላይ አዳዲስ ማሻሻያ ማድረጓን አስታወቀች!

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በቪዛ ፖሊሲዋ ላይ የተለያዩ ለውጦችን ማድረጓን ያስታወቀች ሲሆን የሃገሪቱ ምክር ቤት የውጭ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃዳቸው ከተሰረዘ ወይም ካለቀ በኋላ እስከ ስድስት ወር ድረስ በአገር ውስጥ እንዲቆዩ የሚያስችል ረጅም የእፎይታ ጊዜ ፈቅዷል።

ይሁን እንጂ ይህ በሁሉም የቪዛ ዓይነቶች ላይ ተፈፃሚ መሆን አለመሆኑ እስካሁን አልተገለፀም። የሀገሪቱ መንግስት አዲስ የመኖሪያ እና የቪዛ ስርዓት መዘርጋቱን ኻሊጅ ታይምስ ዘግቧል። አዲሱ ስርዓት የኤምሬትስ ዜጎች እድሜያቸው እስከ 25 ለሆኑ ህፃናትና ወጣቶች የጉዞ ቪዛ ስፖንሰር መሆን ይችላሉ። የተባበሩት ኤምሬትስ ነዋሪዎች ያላገቡ ሴቶችን ያለእድሜ ገደብ ቪዛ እንዲያገኙ ማስደረግ እንዲችሉም ተፈቅዷል።

ከዚህ ቀደም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የቪዛ መመሪያ መሰረት የቪዛ ስፖንሰርሺፕ እድሜያቸው እስከ 18 ለሆኑ ታዳጊዎች ብቻ የተገደበ ነበር።ካቢኔው በቪዛ ማሻሻያው ላይ ለአምስት ዓመት ከሚያገለግል የአረንጓዴ ቪዛ እና ለ10 ዓመት የሚቆይ ወርቃማ ቪዛ ምድቦችን አስተዋውቋል።

እንደ ኻሊጅ ታይምስ ዘገባ በአዲሱ አሰራር ነዋሪዎች የትዳር ጓደኛ እና ልጆችን ጨምሮ ለቤተሰብ አባላት የመኖሪያ ፈቃድ በቀላሉ ሊያስገኙ ይችላሉ። አረንጓዴ የመኖሪያ ቪዛ ያላቸውም ለቅርብ የስጋ ዘመዶቻቸው የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያሰጡ ተፈቅዶላቸዋል።በተጨማሪም ማሻሻያዎቹ ለወርቃማ ቪዛ ያዢዎች የቤተሰብ አባላትን፣ የትዳር ጓደኛ፣ ልጆችን ጨምሮ የቤት ውስጥ ሰራተኞችን ስፖንሰር እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በሁሉም ዩኒየኖችና ሸማቾች በኩል ከ 30 ሺ በላይ የእርድ እንስሳት ሊቀርቡ ነው፡፡

ለመጪው የፋሲካ እና ለኢድ አልፈጥር በዓላት በሸማች ሱቆችና ፤በዩኒየኖች በኩል የሚቀርቡ የእርድ እንስሳት ግዢን እየፈጸምኩ ነው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኤጀንሲ ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል።

ከ 500 በላይ ለቅርጫ የሚሆኑ የእርድ እንስሳትን በአሁኑ ሰዓት ግዢያቸው የተፈፀመ ሲሆን በአጠቃላይ ለመጪው የፋሲካ እና ለኢድ አልፈጥር በዓላት ከ 3 ሺ በላይ የሉካንዳ ከብቶች ግዢ በአማራና በኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ የግዢው ሂደት እየተፈፀመ መሆኑን በኤጀንሲው የግብይት ዳይሬክተር ወይዘሮ ደብሪቱ ለአለም ተናግረዋል፡፡

እንደ ፤ዱቄት ፤ዘይት፤በተለይ የድጎማ ዘይት፤በ148 የሸማች ህብረት ስራ ማህበራትና በሁሉም ዩኒየኖች በኩል እየገባ መሆኑን የነገሩን ወ/ሮ ደብሪቱ በአነስተኛ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰበ ክፍሎችን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማገልገል ፤መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን እያስገባን ነው ብለዋል፡፡

እነዚህን ምርቶች የሚሰራጩት በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ባዛሮችንም በማዘጋጀት፤ ለበአሉ አስፈላጊ የሚባሉ ምርቶቸን ለህረተሰቡ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማቅረብ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በሸዋሮቢት በተፈጠረው ግጭት የተነሳ ከ2ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው ወደ ደብረሲና ከተማ መግባታቸው ተሰማ!

በትላንትናው እለት በሸዋሮቢት ከተማ በተከሰተው ግጭት ምክንያት የሸዋሮቢት አካባቢ ነዋሪዎች ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት አካባቢ ጀምሮ 2ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ወደ ደብረሲና ከተማ መግባታቸዉን የከተማዋ ከንቲባ የሆኑት አቶ መክብብ ከበደ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡በአሁኑ ሰዓት ተፈናቃዮቹ በደብረሲና ከተማ በሚገኙ ሁለት ቤተክርስትያኖች ዉስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በትላንትናው ዕለት በሸዋሮቢት ከተማ ሞላሌ በሚባል በአካባቢ በሽብርተኛዉ ቡድን ኦነግ ሸኔ በከፈተዉ ጥቃት የተጎዱ ሰዎች ሲኖሩ እስካሁን ባለው መረጃ ሶስት ሰዎች መገደላቸዉን ገልጸዋል፡፡ሆኖም ግን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል እና በዛሬው እለት የአማራ ልዩ ሃይል አባለት በሸዋሮቢት ከተማ መግባታቸውን እና ከተማውም መረጋጋቱን አቶ መክብብ ከበደ ጨምረውም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡የልዩ ሀይሉ ወደ ሸዋሮቢት መግባቱን ተከትሎ ከተማዋ ሙሉ ለሙሉ ሰላም መሆኗ ስትረጋገጥ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት የመመለስ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የዩክሬን ኤምባሲ ሩሲያ ኢትዮጵያውያንን ለመመልመል ጥረት እያደረገች ነው አለ!

ሩሲያ አሁን ላይ ከኢትዮጵያ ወጣቶችን ለመመልመል ሙከራ እያደረገች ትገኛለችም ብሏል ኤምባሲው፡፡የኤምባሲው የሚሽን ሃላፊ አሌክሳንደር ከሰሞኑ አንድ የሩሲያን ወታደራዊ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) የለበሰ ሰው አዲስ አበባ ገብቷል ሲሉ ነው ለአል ዐይን የተናገሩት፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:

https://am.al-ain.com/article/ukraine-s-embassy-says-russia-is-trying-to-recruit-ethiopians

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ከሚያዚያ 20 ጀምሮ ባሉ 10 የስራ ቀናት የ"ይዞታ ይረጋገጥልኝ" ማመልከቻ መቅረብ አለባቸው አለ፡፡

ኤጀንሲው ከሚያዚያ 5 እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ ባሉት አምስት ወራት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 25 ቀጠናዎች ውስጥ የሚገኙ 21,436 ይዞታዎችንና 40,625 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በመስክና በሰነድ አረጋግጨ በህጋዊ ካዳስተር ሲስተም ለመመዝገብ ተዘጋጅቻለሁ ብሏል።

የኤጀንሲው የይዞታ ማረጋገጥና አድራሻ ዝርጋታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬከተሩ ጀማል ሀጅ በሰጡት መግለጫ ለይዞታ ማረጋገጥ የተመረጡ ወረዳ፣ ቀበሌና ሰፈሮች የትኞቹ እንደሆኑ በዝርዝር የሚያሳይ መረጃ ከሚያዚያ 5 እስከ ሚያዚያ 10 በወጣው የአዲስ ልሳን ጋዜጣ እትም፣ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና በተቋሙ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መለቀቁን ገልፀዋል።

ኤጀንሲው አረጋግጦ ላልመዘገበው ይዞታ ምንም ዓይነት ሕጋዊ ዋስትናና ከለላ የማይሰጥ ስለሆነም ባለይዞታዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ከሚያዚያ 20 ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅ/ጽ/ቤቶች በሚያወጡት ፕሮግራም መሰረት "የይዞታ ይረጋገጥልኝ" ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ሲሉ አሳስበዋል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ በተመረጡት 25 ቀጠናዎች ውስጥ ብቻ የመረጃ ልዩነት እንዳይፈጠር ሲባል ለአምስት ወራት ያክል ምንም አይነት የስም ዝውውር አይከናወንም ብለዋል።ኤጀንሲው ባለፉት 9 ዓመታት ለ4 ጊዜያት ባከናወንሁት የማረጋገጥ ስራ ከ288 ሺህ በላይ ይዞታዎችንና የጋራ መኖሪያ ቤቶችን አረጋግጨ በሕጋዊ ካዳስተር ሲስተም በመመዝገብ አገልግሎት እየሰጠሁ መሆኔ ይታወቅልኝ ብሏል።

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።


አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።

መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ

ለጤናወ መፍትሄ👇

https://tttttt.me/meritibe
በአዳማ ከተማ መናሀሪያ ውስጥ የዝርፊያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 19 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በአዳማ ከተማ መስተዳድር ሉጎ ክፍለ ከተማ በፒኮክ መናሀሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የዝርፊያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የከተማው ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት እና ከፍተኛ ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ለበዓል የተለያዩ ቦታዎች ላይ ለመሄድ በመናሀሪያ ውስጥ የሚገኙ ህብረተሰቡን ሲያጉላሉ የነበሩት 19 ተጠርጣሪዎች ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ተጠርጣሪዎቹ ከታሪፍ በላይ በማስከፈል፣ተጓዦች ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ንብረት በመንጠቅ እና በማታለል ፣ሰልፍ የሌለው ቦታ እንውሰዳችሁ በማለት መንገድ በማስቀየስ የያዙትን ንብረት በመዝረፍ ተግባር ተሰማርተዉ ቆይተዋል፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለው የክስ መዝገባቸው በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ተገልፆል፡፡በቀጣይ የበዓል ወቅት በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲመለክት አቅራቢያ በሚገኙ የፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@Yenetube @Fikerassefa
ተመድ በጸጥታው ምክር ቤት ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸውን ሀገራት ስልጣን ሊገድብ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመክረው ከአሜሪካ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ሲሆን ምክክሩ የሚካሄደው የተመድ አባል ሀገራት በተገኙበት መሆኑም ተገልጿል፡፡
አሜሪካ ቻይና፣ ሩሲያ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ ሲሆኑ አምስቱም አባል አገራት በማንኛውም ጉዳይ ላይ ውሳኔዎችን የመሻር መብት አላቸው፡፡

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤም የነዚህን ሀገራት ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣን በተወሰነ ደረጃ መገደብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡

ደምጽን በድምጽ የመሻር መብት ካላቸው አምስት ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደችው ያለው ጦርነት ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ መጠራት ምክንያት ሆኗልም ተብሏል፡፡

የዓለምን ጸጥታ ለመጠበቅ እንደተቋቋመ የሚነገረው የጸጥታው ምክር ቤትም የሩሲያን እና ዩክሬንን ጦርነት ሊያስቆም ባለመቻሉ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላት ሩሲያን ስልጣን ለመገደብ እንደሚወያይም ይጠበቃልም ተብሏል፡፡

የዛሬው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አሜሪካንን ጨምሮ በ50 ሀገራት ድጋፍ የተጠራ ሲሆን ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው አራቱ ቀሪ ሀገራት ድጋፍ እንዳልቸሩ የተመድ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተመሰረተው የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት አምስት ቋሚ እና ሁለት ዓመቱ የሚቀያየሩ 10 ቋሚ ያልሆኑ ሀገራትን ይዟል፡፡

Via Al Ain
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ምድባቸውን አውቀዋል!

በ2023 በአይቮሪኮስት አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከደቂቃዎች በፊት ይፋ በተደረገው የምድብ ድልድል እጣ ማዉጣት ላይ ዋልያዎቹ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል።

ዋልያዎቹ በምድብ አራት ከግብፅ ፣ ማላዊ እና ጊኒ ጋር መደልደላቸው ይፋ ተደርጓል። ከየምድቡ አንደኛ እና ሁለተኛ ሁነዉ የሚያጠናቅቁ ብሔራዊ ቡድኖች ወደ ኮትዲቯር የአፍሪካ ዋንጫ የሚያመሩ ይሆናል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም አስጀመረ!

የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ማስጀመሩን አስታወቀ፡፡የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሙ በዘጠኝ ወረዳዎች በ67 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 35 ሺህ 350 ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙክታር ሳሊ÷ የፕሮግራሙ መጀመር በምግብ እጥረት ምክንያት የሚታየውን የተማሪዎች ማቋረጥና የመድገም ምጣኔን ለመቀነስ እና ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመሳብ እንደሚጠቅም ተናግረዋል፡፡አያይዘውም የፕሮግራሙ መጀመር 600 ለሚሆኑ ወገኖች የስራ ዕድልን እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ለሩሲያ መዋጋት እንፈልጋለን ስላሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሩስያ ኤምባሲ ምላሽ

አዲስ አበባ የሚገኘው የሩስያ ኤምባሲ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ኤምባሲው «የሩስያ ጦር ሠራዊት ውስጥ ለመቀጠር ማንኛውንም ማመልከቻ አይቀበልም ሲል ጻፈ

በርካታ ኢትዮጵያውያን ለሩስያ ተሰልፈው ለመዋጋት ማመልከቻቸውን ይዘው እስከ ትናንት ድረስ አዲስ አበባ የሚገኘው የሩስያ ኤምባሲ መታየታቸውን ዶይቸ ቬለ (DW) በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል።

ዩክሬን ውስጥ ጦርነት ለገጠመችው ሩሲያ «መዋጋት እንፈልጋለን» ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለምዝገባ አዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ፊት ለፊት እንደተሰለፉ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ትናንት ተመልክቶ በቦታው የተሰለፉትን ኢትዮጵያውያን አነጋግሯቸውም ነበር።ዶይቸ ቬለ ካነጋገራቸው ወጣቶች መካከል አንዱ፦ «ከመከላከያ የተሰናበተበትን» መረጃ ይዞ በሥፍራው በመገኘት መመዝገቡን ገልጧል።

ለመመዝገብ ወደ ኤምባሲው አቅንቶ ሳይሳካለት እንደቀረ ለዶይቸ ቬለ የተናገረ አንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሦስተኛ ዓመት የአካውንቲንግ ተማሪ ወጣት ከዚህ ቀደም በውትድርና ሞያ የሰለጠነበት ማስረጃ ስለሌለው ምዝገባው ሳይሳካለት በመቅረቱ እንደሚቆጨው ገልጧል።

አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ ባለስልጣናት ለሩሲያ የሚዋጉ ወታደሮችን ከኢትዮጵያ እየመለመሉ አለመሆኑን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። ሩስያ ለሚጓዙ ግን እንደ ሁልጊዜው የቪዛ አገልግሎት እንደሚሰጡ አክለዋል።

Via DW
@Yenetube @Fikerassefa
በ2014 የትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ያደረጉ የግል ትምህርት ቤቶች በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ ተነገረ፡፡

የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2015 የትምህርት ዘመንን የክፍያ ጭማሪ አስመልክቶ ከትምህርት ቤቶቹ ጋር ባደረገው ምክክር በ2014 አ.ም ጭማሪ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች በ2015 የትምህርት ዘመን ምንም አይንት ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ህይወት ጉግሳ ተናገረዋል፡፡

ነገር ግን ላለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት ጭማሪ ሳያደርጉ የቆዩ ትምህርት ቤቶች በሚያቀርቡት ፕሮፖዛል እና ከወላጅ ጋር በሚያደርጉት መግባባት መሰረት ጭማሪ ማድረግ እንደሚችሉም ተነግሯል፡፡ ከመደበኛ የአገልግሎት ክፍያ ውጭ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ትምህርት ቤቶች ክፍያ መጠየቅ አይችሉም ያሉት የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ከዚህ ቀደም ያለ አግባብ ጭማሪ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች እርምት እንዲወስዱ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፎቻቸውን ጨምሮ 2 ሺህ ገደማ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ እነዚህ ትምህርት ቤቶች 400ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን እንደሚያስተናግዱ የገለጸው የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ይህም ከአጠቃላይ የአዲስ አበባ የተማሪ ሽፋን 43 በመቶውን ይይዛል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa