YeneTube
120K subscribers
31.2K photos
480 videos
79 files
3.82K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቀድሞው የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ሞሐመድ ኡመር ክስ የዛሬውን የምስክር መስማት ሂደት ወደ ዓርብ ማስተላለፉን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

ችሎቱ የዛሬውን ቀጠሮ ያዛወረው፣ ለተከሳሹ አስተርጓሚ ሆነው የተመደቡት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ አብዱላሂ ረሚ ችሎት ሳይቀርቡ በመቅረታቸው ነው። ችሎቱ አስተርጓሚው በ24 ሰዓት ውስጥ ታስረው እንዲቀርቡ አዟል። ተከሳሾቹ የክሳቸው ሂደት እየተጓተተ መሆኑን በመጥቀስ፣ ችሎቱ ከሌላ መንግሥት መስሪያ ቤት ተተኪ አስተርጓሚ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ፤ ሱዳን ያልከፈለቻትን ውዝፍ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ እንድትከፍላት መጠየቋን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የ2014 ስድስት ወራት አፈጻጸሙን ለገንዘብ ሚኒስቴር ባስገመገመበት ወቅት፤ ሱዳን ውስጥ ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት አገሪቱ ለኢትዮጵያ መክፈል የነበረባትን የስድስት ወራት ክፍያ መፈጸም አለመቻሏን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሞገስ መኮንን ለአል ዐይን አማርኛ እንደገለጹት፤ ሱዳን ያልከፈለችው የኤሌክትሪክ ክፍያ መኖሩን ገልጸው፤ ይህ ግን ከዚህ ቀደምም የሚያጋጥም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ከዚህ በፊትም ሱዳን የተጠቀመችውን የኤሌክትሪክ ውዝፍ ክፍያ ትከፍል እንደነበር የገለጹት ሞገስ የአሁኑም ከቀደመው ጊዜ የተለየ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል፡፡ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተገኘው መረጃ መሰረት፤ ኢትዮጵያ ለሱዳንና ጂቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች ትገኛለች፡፡ሁለቱም አገራት ውዝፍ ክፍያ ቢኖርባቸውም ቀደም ሲል ባለው አሰራር መሰረት ውዝፍ ክፍያውን እንደሚከፍሉ ተገልጿል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ተጨማሪ ጥቃት ሳትከፍትብን ድረሱልን ሲሉ ለአውሮጳ ሃገራት ጥሪ አቀቡ።

ለኢስቶኒያ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር አውሮጳ ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ርምጃ እንዲወስድ የተማጸኑት ፕሬዝደንት ዘለንስኪ አውሮጳ ርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ጊዜ የሚያጠፋ ከሆነ ሩሲያ የጦርነት ቀጣናውን ወደሌሎች ሃገራትም ታስፋፋዋለች በማለት አስጠንቅቀዋል። የዘለንስኪ ጥሪ የተሰማው የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ውጤት ከሌለው ያሰቡትን እስኪያሳኩ ወታደራዊ ዘመቻውን እንደሚገፉበት ከተናገሩ በኋላ ነው።

የሩሲያ ኃይሎችም የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ወታደራዊ ዘመቻውን እያጠናከረች ነው ያላት ኪየቭ የሰላም ንግግሩን እያጓተተች ነው በሚል ከሷል። የሩሲያ ኃይሎች ትናንት ምሽቱን ማሪዎፖል ከተማን መደብደባቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት መግለጻቸው ተዘግቧል። ይኽ በእንዲህ እንዳለም የብሪታንያ ፍርድ ቤት የሩሲያዊውን ባለሃብት ሮማን አብራሞቪችን 7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረት ማገዱን ሮይተርስ ከሎንደን ዘግቧል።

አብራሞቪች ከሰሞኑ በብሪታንያ እና በአውሮጳ ሕብረት ማዕቀብ ውስጥ ከተካተቱ የሩሲያ ባለጸጎች አንዱ ነው። እስካሁንም የአውሮጳ እና የብሪታንያ መንግሥታት የሩሲያውያናኑን ባለሀብቶች መርከቦች እና የተቀናጡ ሌሎች ንብረቶችን እያገዱ ነው። በተያያዘ ዜናም ዩክሬን ላይ በከፈተችው በዚህ አውዳሚ ጦርነት ሩሲያን ማውገዝ ያቃታቸው ሃገራት ማስተዋል የጎደላቸው ናቸው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የሊን ተቹ።ሚኒስትሯ አክለውም የምዕራባውያንን ማዕቀብ ችላ የሚሉ ከሆነም መዘዝ ይከተላቸዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ለኢትዮ ከቴሌኮምና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ
ከስምምነት ላይ ደረሱ!


እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሰረተ ልማት መጋራት እና ትስስር ላይ ያደጉት ዘርፈ ብዙ ድርድሮች በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃቸውን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።ኩባንያዎቹ በቅርቡ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
"አንበሳ ፋርማሲ እና ኒዮን አዲስ እንዲፈርሱ ተወሰነ ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ፍጹም ከእውነታው የራቀ ነው"፦ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

አንበሳ ፋርማሲ እና ኒዮን አዲስ እንዲፈርሱ ተወሰነ ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ፍጹም ከእውነታው የራቀና መሰረተ ቢስ መረጃ ነው ሲል የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አስታወቀ።ኮርፖሬሽኑ የቅርስ ቤቶቹ ይዘታቸው እና ቅርጻቸው ሳይቀየር፤ ባሉበት ሳይነኩ አካባቢው እንዲለማ ተደረገ እንጂ፤ እንዲፈርሱ አልተወሰነም ብሏል።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በትላንትናው ዕለት የቅርስ ቤቶቹን መፍረስ አስመልክቶ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሲናፈስ ስለነበረው መረጃ ማብራሪያ ሰጥቷል።በማብራሪያውም አንበሳ ፋርማሲ እና ኒዮን አዲስ የተባሉ ድርጅቶች በኪራይ ሲገለገሉበት የነበሩበት እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ንብረት የሆኑ ቤቶች፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቅርስነት ይዘታቸው ሳይቀየር፣ ባሉበት ምንም ዓይነት የቅርጽና የይዘት ለውጥ ሳይደርግባቸው በአካባቢው ከሚገነባው አዲስ ግንባታ ጋር ለአልሚው ባለሀብት እንዲተላለፉ መደረጉን ገልጿል።

በዚህም በቅርሶቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማይደርስባቸው በኮርፖሬሽኑ እና በከተማ አስተዳደሩ መካከል ሥምምነት ላይ መደረሱንም አስታውቋል፡፡በተለይ ከቅርብ ዓመታት በፊት ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸው በርካታ ቤቶቹ እና የቅርስ ቤቶች በልማት ምክንያት በከተማ አስተዳደሩ መፍረሳቸውን ተከትሎ፤ የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታትና የቤቶችን ደህንነት በጋራ በመጠበቅ እንዲሁም ከተማዋን በጋራ ለማልማት ኹለቱ አካለት ሥምምነት ላይ በመድረሳቸው፤ ከአሁን በፊት በተለየ ሁኔታ ልዩ ትኩረት ለቅርስ ቤቶች ደህንነት እንደተሰጠም ገልጿል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያሉንን ቅርሶች በመጠበቅ እና በመንከባከብ፤ ቅርስ ጥበቃ እና ልማት ሚዛኑን አስጠብቆ እንዲሔድ ማድረግ ሌላኛው ከድህነት መውጫ መንገድ ሊሆን እንደሚገባ ገልጿል፡፡ሆኖም በእርጅና ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን እና ቤቶችን ደግሞ ለኹላችን ጥቅምና እድገት በሚያስገኝ መልኩ ማልማትም ተጊቢ ነው ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል፡፡

በዚህም ልማት እና ቅርስ ጥበቃ ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲሔዱ ማድረግ ተጊቢ እንደሆነ ህብረተሰቡ በውል እንዲረዳ ያሳሰበው ኮርፖሬሽኑ፤ ከዚህ አውድ ውጭ ሌላ ትርጉም ሰጥተው ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት የተሳሳተ መረጃ እየሰጡ መሆኑንም ገልጿል፡፡የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ እና በድሬደዋ ከተማ የሚገኙ የፌደራል መንግስት ቤቶችንና ይዞታዎችን የሚያስተዳድር እንዲሁም በቤት ልማት ዘርፍ የተሰማራ የመንግስት የልማት ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሦስት ወረዳዎች የአቮካዶ ምርትን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ውጤታማነታቸው መረጋገጡን ማኅበሩ አስታወቀ!

ጥራት ያለው የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ሦስት አካባቢዎች ውጤታማነታቸው በተግባር መረጋገጡን የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማኅበር አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማኅበር የፕሮጀክት ማናጀር አቶ ዋለ ጌታነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ፤ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ቡታጂራ አካባቢና በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ጥራት ያለው የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ውጤታማነታቸው በተግባር ተረጋግጧል።

እስካሁን በተከናወኑ ሥራዎች በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ለወጪ ንግድ የሚውሉ ጥራት ያላቸው የአቮካዶ ምርቶችን ማዘጋጀት ቢቻልም በኢትዮጵያ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥራት ያለው የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም መኖሩን ጠቁመዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
"ብልፅግና፣ ብሔር ተኮር ፓርቲ መሆኑን አረጋግጧል" - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ሚያዚያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም በአምስት አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት ይመስገን መሳፍንት "ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ህብረ ብሔራዊ ነኝ ይበል እንጂ ብሔር ተኮር ፓርቲ መሆኑን አረጋግጧል።" ብለዋል።

የፓርቲው አመራሮች እርስ በእርሳቸው አውራ ለመሆን የሚፎካከር መሆኑን ያነሱት ይመስገን፤ "የራሱ የብልፅግና ሰዎች የሀገሪቱ ስጋት ሆነዋል።" ሲሉ ገልፀዋቸዋል።"ለእያንዳንዱ ድርጊታቸው ተጠያቂ እንደሚሆኑ ሊያወቁ ይገባል።" ሲሉ አሳስበዋል።

በኑሮ ውድነት፣ የመሬት ወረራ፣ በተለይ በደቡብ ክልል ያሉት "የፀጥታ ችግሮች"፣ ሀይማኖት ነክ ጉዳዮችና በመንግስት መካከል ያሉት የእርስ በእርስ እሰጣ ገባዎች የሚሉት አምስቱ ኢዜማ ትኩረት ሰጥቶ መግለጫ የሰጠባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ለወራት ታስረው የነበሩ ከአንድ ሺህ በላይ የትግራይ ተወላጆች መፈታታቸው ተነገረ!

በደቡብ ክልል ሃድያ ዞን ሾኔ በተሰኘች ከተማ ለወራት ታስረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች መፈታታቸውን ቢቢሲ ከተፈቱ ግለሰቦች ሰምቷል።ወደ 1 ሺህ 300 የሚሆኑ እስረኞች በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ በአውቶብስ ተጭነው አዲስ አበባ መድረሳቸውን መረሳና አይናለም የተሰኙና በስፍራው ታስረው እንደነበር የገለጹ የትግራይ ተወላጆች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ለዘጠኝ ወራት ያህል ክስ ሳይመሰረትባቸውና የተጠረጠሩበት ወንጀል ሳይነገራቸው እንደቆዩ የሚናገሩት መረሳና አይናለም ሲለቀቁም ምንም መረጃ እንዳልተሰጣቸው ለቢቢሲ አስረድተዋል።ከትናንት በስቲያ ከነበሩበት እስር ቤት ውጡ እንደተባሉና በየእያንዳንዱ አውቶብስ ሁለት ፖሊሶች ተመድቦ እንደመጡና በአዲስ አበባ ቃሊቲ እንዳወረዷቸውም መረሳ ተናግሯል።"የት እንደሚወስዱን፣ ወደ የት እንደምንሄድ አናውቅም። ብንጠይቅም፣ አናውቅም የሚል ምላሽ ተሰጠን" ሲለ መረሳ ያስረዳል።

በእስር ላይ ያሉ የትግራይ ተወላጆችን ቢቢሲ ከሰሞኑ ባናገራቸው ወቅት በብሔራቸው ምክንያት በቂ የምግብ፣ የውሃና የመድኃኒት አቅርቦት በሌለበት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ታስረናል ሲሉ ተናግረው ነበር።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ 47 የጭነት ተሸከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እየተጓዙ ነው!

እየተጓጓዘ ያለው የሰብዓዊ ዕርዳታም ምግብ፣ ዓልሚ ምግቦችን እና ሌሎች ሕይወት አድን ቁሳቁሶችን እንዳካተተ ነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያስታወቀው።ከምግብ እና መሰል አቅርቦቶች በተጨማሪ 3 የነዳጅ ቦቴዎች በማጓጓዝ ሂደቱ ለተሸከርካሪዎቹ ለጥቅም እንዲውሉ ታስቦ አብረው ወደ ትግራይ ክልል እየተንቀሳቀሱ እንደሆነም ነው ድርጅቱ በትዊተር ገጹ ያመላከተው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ ግንባታውን በጨረታ አሸንፈው የተረከቡት የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች አስጠንቅቀዋል።

300 አባላት ያሉት የአማራ ክልል የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማኅበር እንዳስታወቀው የማኅበሩ አባላት የሆኑ ተቋራጮች ከመንግሥት በጨረታ የተረከቧቸውን የግንባታ ፕሮጀክቶች ማከናወን አለመቻላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለአማራ ክልል ር/መስተዳደር እንዲሁም ለሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት ማለትም ለአማራ ክልል ማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ፣ ለገንዘብ ቢሮ፣ ለከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ ለፍትሕ ቢሮ እና ለአማራ ብልፅግና ጉዳዩን የሚያብራራ እና ምላሽ እንዲሰጥበት የሚጠይቅ ደብዳቤ አስገብተዋል።

የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮቹ እንደሚሉት የግንባታ ቁሳቁሶች ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን በመናሩ ቀድሞ በጨረታ አሸንፈው ስራውን በተረከቡበት ዋጋ ግንባታውን ማከናወን እንዳይችሉ እንቅፋት ሆኗል። በመሆኑም የዋጋ ማሻሻያ የማይደረግ ከሆነ ስራቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዲያቋርጡ ይገደዳሉ።

ሙሉውን ያንብቡ
https://bit.ly/3EgJ8O5

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጥሏል፡፡

ወቅቱ የፋሲካ በዓል በመሆኑ ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ስለሚኖር፣ ግርግር እና ስርቆት እንዳይፈጠር በማሰብ፤ አዲሱ ጥናት ተጠናቆ እስኪጠናቀቅ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግ እገዳ ተጥሏል፡፡

በዚህም እርምጃ እንዲወሰድ ቢሮው ለሚመለከተው አካል የስራ ትዕዛዝ ማስተላለፉም ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ አፍሪካ የዩክሬን አምባሳደር ከዲፕሎማሲያዊ መስመር ዉጪ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎዛን ለማነጋገር መሞከራቸዉን ደቡብ አፍሪቃ አወገዘች።

የዩክሬኗ አምባሳደር ሊዩቦቭ አብራቪቶቫ ፕሬዝደንቱን ለማነጋገር የፈለጉት ሐገራቸዉ ከሩሲያ ጋር ስለገጠመችዉ ጦርነት ለማስረዳት ነበር።ይሁንና አምባሳደሯ መደበኛዉን የዲፕሎማሲ መስመር ጥሰዉ በትዊተር ቀጠሮ መጠየቃቸዉ የደቡብ አፍሪቃ ባለስልጣናትን አስቆጥቷል።አምባሳደር አብራቪቶቫ በትዊተር ቀጠሮ እንዲሰጣቸዉ የጠየቁት ራማፎዛንና ሌሎች ባለልስጣናት ለመነጋገር «በተደጋጋሚ ያቀረብኩትን ጥያቄ የደቡብ አፍሪቃ ባለስልጣናት ባለመቀበላቸዉ ነዉ» ይላሉ።

የደቡብ አፍሪቃ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ክሌይሰን ሞንዬላ ግን የአምባሳደሯን ወቀሳ አጣጥለዉታል።ሞንዬላ እንደሚሉት አምባሳደሯ ከተለያዩ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረዋል።ፕሬዝደንት ራማፎዛ የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ለማነጋገር ለቀረበዉ ጥያቄም አምባሳደሯ መልስ አልሰጡም። በሩሲያና በምዕራባዉያን መንግስታት በምትደገፈዉ ዩክሬን መካከል በሚደረገዉ ጦርነት ደቡብ አፍሪቃ ገለልተኛ አቋም መያዝዋ የኪየቭና የረዳቶችዋን መንግስታት አስቀይሟል።

ሩሲያ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት አባልነት እንድትወጣ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ድምፅ ሲሰጥ ደቡብ አፍሪቃ ድምፅዋን አቅባለች።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ አካባቢን የኤሌክትሪክ ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት አለመቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል!

ቀጦርነቱ ምክንያት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ኃይል ከተቋረጠ ከአንድ ዓመት በላይ ሲሆን፤ የላሊበላ እና የዋግ ኽምራ ዞን በርካታ አካባቢዎችም ለወራት የኤሌክትሪክ ኃይል እያገኙ አይደለም፡፡

ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሑመራ አካባቢዎች ኃይል ያገኙ የነበረው በሽብር ቡድኑ በተያዙ አካባቢዎች ከሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ከተዘረጉ መሥመሮች እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡በመሆኑም የተቋረጡትን መሥመሮች ለመጠገንና አካባቢዎቹ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ተቋሙ መቸገሩን አስታውቋል፡፡

ሆኖም ላሊበላና አካባቢው በሌሎች አማራጮች ኃይል ለመስጠት ተቋሙ እያጠኔ መሆኑን የገለፀ ሲሆን፤ ለወልቃይት ጠገዴ አካባቢ መፍትሔ ለመስጠት ከጎንደር ወይም ከመተማ ኃይል ለመዘርጋት ረጅም ጊዜ እንደሚጠይቅ ጠቅሷል፡፡

በወልቃይት ጠገዴ ያለው ችግር ከሌሎች አካባቢዎች በተለየ ከዓመት በላይ የቆየው በአካባቢው አማራጭ መስመር ባለመኖሩና የአዲስ መስመር ዝርጋታው ትልቅ ኢንቨስትመንት ከመጠየቁ በተጨማሪ ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ እንደሆነም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገልጿል፡፡

ከዚህ በፊት ላሊበላን በጄኔሬተር ኤሌክትሪክ ለመስጠት የተደረገው ሙከራ በነዳጅ አቅርቦት ምክንያት መስተጓጎሉ ተቋሙ አስታውቋል፡፡ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ደንበኞች ይህንን ተገንዝበው የተፈጠረው ችግር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ተጠይቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ 247 የሚሆኑ የጉህዴን ታጣቂ ዎች እጅ መስጠታቸውን የዳንጉር ወረዳ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ፡፡

የወረዳው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሻለቃ ደምስ ዳኘ÷ በወረዳው የአሸባሪውን ህውሓት ተልዕኮ ተቀብለው የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) በሚል ስም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 247 ታጣቂዎች ለፀጥታ ኃይሉ በሰላማዊ መንገድ እጅ መስጠታቸውን ገልጸው÷ ከነዚህም ውስጥ በዛሬው ዕለት 57 ሽፍቶች ከነትጥቃቸው መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

የጥፋት ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ከቀረበላቸው የሰላም ጥሪ ባለፈ÷ በመከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት ቅንጅት ሕግን ለማስከበር እየተወሰደ ባለው የኦፕሬሽን ሥራ ብዙዎች እጅ እየሰጡ መሆኑንም ጨምረው መግለጻቸውን ከመተከል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የ10 ዓመት ታዳጊን የኩላሊት ሕመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!

የ10 ዓመት ታዳጊን የኩላሊት ሕመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ 11 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ ታዳጊውን የኩላሊት ሕመምተኛ በማስመሰል እና የሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ገንዘብ ሲያሰባስቡ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ ገልጸዋል።

እንደ አቶ ጌታሁን መግለጫ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በ3 ክፍለ ከተሞች ስም የተዘጋጁ ሐሰተኛ ሰነድ እንዲሁም የሐኪም ማስረጃዎችን ከሚለምኑባቸው 2 ሚኒባስ መኪኖች ጋር በኅብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማ እና በፀጥታ አካላት ክትትል በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል።

በተደረገው የክትትል ሥራ ለሕገ-ወጥ ሥራው የተዘጋጁ ሐሰተኛ ሰነዶችን፣ ታርጋ ቁጥር 58456 እና 79169 ኮድ 3 ኦሮሚያ የሆኑ ሚኒባስ ታክሲዎችን እንዲሁም 9 ሴት እና 2 ወንዶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል ብለዋል።

አሁን ላይ በከተማዋ የተለያዩ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማዘጋጀት እና ያልታመመ ሰውን ታመመ በማለት የሚመለከተው የሕክምና ተቋም ማረጋገጫ ሳይሰጥ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚካሄዱ ልመናዎች መብዛታቸውን የጠቆሙት ኃላፊው ኅብረተሰቡም ከአጭበርባሪ ወንጀለኞች ራሱን እና ንብረቱን እንዲጠብቅ ሲሉ ጥሪያቸውን ማስተላለፋቸውን ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በመረጃ ክልከላ፣ በመገናኛ ብዙሃን እና ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት መፍታት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ መንግስት መገናኛ ብዙሃን የሚጠበቅባቸውን የምርመራ ስራዎች እና መረጃዎችን ተደራሽ እንዲያደርጉ ቁርጠኝነት ቢኖረውም የመረጃ ፍሰቱ ላይ ከትናንት የተረከብናቸው ከፍተኛ ችግሮች አሉ ብለዋል።

የስራ ሃላፊዎች እና ተቋማት በአብዛኛው ለቦታው አዲስ ነኝ፤አይመለከተኝም እና ሌሎች ምክንያት በማቅረብ ለመገናኛ ብዙሃኑ ተግበራት ማነቆ ይሆናሉ ነው ያሉት።ይህን በአገሪቱ በስፋት የሚስተዋልን ችግር ለመቅረፍ የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ውይይት ተደርጎበት ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

መመሪያው ከፌደራል ጀምሮ እስከ ታችኛው የኮሙኒኬሽን እርከን የግንኙነት አሰራር የሚፈጥር ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎች ተቋማቸውን የሚያስተዋውቁበት እንዲሁም ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ያላቸው ግንኙነት የሚጠናክሩበትን እድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡በተጨማሪም የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎችን በስልጠናዎች የማገዝ፣ የአቅም ግንባታ ስራዎች እና ሌሎች ተግባራትም በቀጣይ በትኩረት የሚሰራባቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
-200,000 ብር

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ሰንጋ በሞርትና ጅሩ ወረዳ የሆሳዕና ገበያ በ200,000 ብር መሸጡን የወረዳው ኮምኒኬሽን ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮ ቴሌኮም ለሚከራያቸው የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ኪራዩን በኢትዮጵያ ብር እና በአሜሪካ ዶላር ለመክፈል መስማማቱን ሪፖርተር ዘግቧል።

በስምምነቱ መሠረት ሳፋሪኮም ላንዳንድ መሠረተ ልማቶች በ70/30፣ ለሌሎች ደሞ በ40/60 ስሌት በብር እና ዶላት ይከፍላል። ኩባንያዎቹ በመርህ ደረጃ ለደረሱበት ስምምነት በቅርቡ ሕጋዊ ውል እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል። ኢትዮ ቴሌኮም ኪራዩ በዶላር እንዲሆንለት ሲጠይቅ ሳፋሪኮም ደሞ ብርን በመምረጡ የተፈጠረው ልዩነት የተቀረፈው፣ በኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን አደራዳሪነት ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የቅዱስ ላልይበላ ገዳም ካህናትና አገልጋዮችን ለመደገፍ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ 8 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ!

የቅዱስ ላልይበላ ገዳም ካህናትና አገልጋዮችን ለመደገፍ "ወደ ቅዱስ ላልይበላ ተመልክቱ!" በሚል ጥሪ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር 8 ሚሊዮን ብር ያህል መሰብሰቡ ተገለፀ።

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ ላይ እንደተገለጸው፤ በመንፈሳዊ አገልግሎቱ ኢትዮጵያን ከዘመን ዘመን ሲያሻግር የኖረውና ለአገሪቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ሆኖ ያገለገለው የቅዱስ ላልይበላ ቅርስ ጠባቂዎች በጥልቅ የመኖር አለመኖር ፈተና ውስጥ ወድቀዋል። በመሆኑም የቅርሱ ጠባቂዎች የህልውና ጥያቄ በቅርሱ ደህንነት ላይ ተጨማሪ ጫና ፈጥሯል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን (ከሚሴ ) አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመርሐግብሩ ላይ እንደተናገሩት፤ "በረዥም ዕድሜ ሳቢያ እንክብካቤ ለሚፈልገው ቅርስ በመንግሥት እገዛ ከፈረንሳይ መንግሥት ድጋፍ የተገኘ ቢሆንም፤ የቅርሱን ጉዳትና ደህንነት በቅርብ የሚያውቁትና የሚከታተሉት የቅዱስ ላልይበላ ካህናትና ነዋሪዎች ግን አስታዋሽ አላገኙም" ብለዋል።

በአካባቢው ባለፉት አሥር ወራት የመብራት አገልግሎት ከመቋረጡ ጋር ተያይዞ የውሃ፣ የህክምና፣ የወፍጮና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን ብፁዕነታቸው አመልክተዋል። በአካባቢው በነበረው ጦርነት 4 ሺህ 322 ንፁሀን ወገኖች መሞታቸውንም ጠቅሰዋል።

ደብሩ በዚህ የከፋ ሁኔታ ውስጥ ላሉት ካህናት፣ የቅርሱ ጠባቂዎችና ነዋሪዎች ያለውን ጥሪት ቆጥቦና ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ተበድሮ ህዝቡን ለመመገብ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም ብፁዕነታቸው አያይዘው ገልጸዋል።

ሆኖም ግን፤ ያለው አቅም ሁሉ በመሟጠጡ መንግሥትና በመላው ዓለም የሚገኙ የቅርሱ ቤተሰቦች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪው መተላለፉን ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አብራርተዋል።

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ባህል ሚኒስትር ዲኤታ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው "የአገር ውስጥና የውጭ አገር ቱሪስቶችን ወደ ሥፍራው ለጉብኝት ለመሳብ ሰፊ ጥረት ቢደረግም በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ጦርነት ትልቅ ጫና ፈጥሯል። ይህም በቅርሱ ዙሪያ ባሉ ነዋሪዎች ሕይወት ላይ ትልቅ ፈተና ሆኗል" ብለዋል።

በኢኦተቤ በሰሜን ወሎ አገረ ስብከት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ ገዳም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን ባዘጋጀው የገቢ ማስገኛ መርሐ ግብር 8 ሚሊዮን ብር ያህል ተሰብስቧል።

በመርሐግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ ብፁዕ አቡነ ሰላማ በሰሜን አሜሪካ የኦሃዮና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፤ ስጦታው ጅምር መሆኑን ጠቅሰው በመላው ዓለም የሚገኙ የቅዱስ ላልይበላ ቤተሰቦች በሀሳብ በጸሎትና በገንዘብ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማስተላለፉቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሀን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
348 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!

ዛሬ በተደረገው የመጀመሪያው በረራ 348 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ተመላሾች ሁሉም ወንዶች መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa