የጀጎል ግንብ አደጋ እንደተጋረጠበት የሐረሪ ክልል የባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ!
በሐረሪ ክልል የሚገኘው የጀጎል ግንብ እና በዙሪያው ያሉ በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ላይ አደጋ እንደተጋረጠ የሐረሪ ክልል የባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።
በዓለም ዐቀፍ የሳይንስ የትምህርት እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው እና አምስት መቶ ዓመት ገደማ ዕድሜ ያስቆጠረው የጀጎል ግንብ እና በዙሪያው የሚገኙ ቤቶች፣ በክረምት ወራት እንዲሁም በየወቅቱ በሚጥል ዝናብ ሳቢያ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው። እንዲሁም በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች በየወቅቱ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በሚያደርሱት ጉዳት ምክንያት ቅርሶቹ አደጋ እንደተጋረጠባቸው የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ተወለዳ ሀዱሽ ገልጸዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ:
https://bit.ly/3K5xBU3
@YeneTube @FikerAssefa

የፓኪስታኑን ፕሬዝዳንት ኢምራን ካሃንን ከስልጣን ለማንሳት የቀረበውን የመተማመኛ ድምጽ ማጣት (Vote of no confidence) ፓርላማው ውድቅ አድርጐታል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️
በኤሊያስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል!
ቃሊቲ ኢንዱስትሪ መንደር በኤሊያስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ትናንት ምሽት 3:15 ሰአት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታዉ ቃሊቲ ኢንዱስትሪ መንደር በኤሊያስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል።
“ከባለንብረቶቹ በደረሰን መረጃ መሰረት 350 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ላይ ወድመት ደርሷል” ብለዋል።
በፋብሪካዉ ያሉት የጨርቅ ማቅለሚያ ኬሚካሎችና በመጋዘን ዉስጥ የሚገኙ ጥሬ እቃዎች እሳቱ ፈጥኖ እንዲስፋፋ ከማድረጋቸዉም በላይ በፋብሪካዉ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ለመግባት አመቺ አለመሆኑ እንዲሁም ፋብሪካዉ ህንጻ ላይ መሆኑ እሳቱን በቀላሉ መቆጣጠር እንዳይቻል አድርጎታል ብለዋል።
በተከናወነው የአደጋ መቆጣጠር ርብርብ ከሌሊቱ 7 ሰዓት እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል።
የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር 15 የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች 6 ውሃ የጫኑ ቦቴዎች እንዲሁም 154 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተዋል፤ እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋትም 500 ሺህ ሊትር ውሃና 7 ሺህ 800 ሊትር ኬሚካል ፎም ጥቅም ላይ ውሏልም ብለዋል።
የእሳት አደጋዉ በአካባቢዉ ባሉ ሌሎች ፋብሪካዎች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል በዚህ ሂደትም 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን መቻሉን ገልጸዋል።
አቶ ንጋቱ እንዳሉት፤ በአደጋ መቆጣጠሩ ሂደት የአየር መንገድና የደብረዘይት እሳት አደጋ ባለሙያዎች እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ የአዲስ አበባ መንገዶችና ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን 6 የውሃ ቦቴ በማቅረብ ተባብረዋል።
በሌላ በኩልም የጸጥታ አካላት አስፈላጊዉን ትብብር ማድረጋቸውን ገልጸው፤ በስራ ላይ በነበሩ ሦስት የፋብሪካዉ ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ መሆኑን ገልጸዋል።
Via EPA

ከአዋሽ 2 ወደ አሰላ የተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በተፈፀመበት ዝርፊያ የኤሌክትሪክ ኃይል በከፊል ተቋርጧል።
በዶዶታ ወረዳ እና ጌራ ከተማ አቅራቢያ በተፈፀመው የምሰሶ አካላት ዝርፊያ ሁለት ምሰሶዎች በመውደቃቸው አሰላ ከተማን ጨምሮ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች በከፊል ኤሌክትሪክ የኃይል ተቋርጧል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጥገና ቡድን ዝርፊያ ወደተፈፀመበት አካባቢ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ጥገናውን በፍጥነት ለመጀመር የሚያስችል አሰሳ እያካሄደ ነው፡፡ ጥገናው ከሳምንት ያላነሰ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተገምቷል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ዝርፊያ እየተደጋገመ ሲሆን ይህም ለኃይል መቋረጥ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል።

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቁምቢ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ።
የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጐሹ እንደገለጹት፥ ዛሬ ረፋድ አራት ሰዓት አካባቢ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 -75091 ኦሮ የጭነት አይሱዙ የጭነት መኪና ከጎሎኦዳ ወረዳ ወደ ቁምቢ ወረዳ የተለያዩ ሸቀጦች እና 20 ሰዎችን ጭኖ ሲሄድ ተገልብጧል፣በአደጋው የስድስት ሰዎች ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ በ12 ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ለተጨማሪ ከፍተኛ ሕክምና ወደ በደኖ ሆስፒታል ተወስደዋል ብለዋል።አደጋው ከአቅም በላይ በመጫን እና በከፍተኛ ፍጥነት ምክንያት መድረሱንም ተናግረዋል።አሽከርካሪው ለጊዜው ከአባባቢው መሰወሩንና በወረዳው ፖሊስ አባላት ክትትል እየተደረገበት መሆኑን ገለፀዋል።
[FBC]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ‘‘ያሬድ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው’’ በሚል የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም የተሳሳተ መሆኑን አስታወቀ፡፡
አስተዳደሩ በማህበራዊ በትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፥ አንዳንድ ወገኖች የተሳሳቱ መረጃዎችን በተደጋጋሚ በመልቀቅ ህብረተሰቡን ወደ ውዥንብር ለመክተት ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡
በዚህ ሰሞን ‘‘አንጋፋው የሙዚቃ ትምህርት ተቋም የሆነው ያሬድ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው’’ የሚል መረጃ በማሰራጨት በህዝቡ ውስጥ ውዥንብር ለመፍጠር የሞከሩ መሆኑን ያስታወቀው አስተዳደሩ ፥ ነገር ግን በአስተዳደሩም በኩል ይሁን በትምህርት ቤቱ በኩል ምንም የተለየ ነገር የሌለና ይህ መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ እንደዚህ በተደጋጋሚ የሃሰት የበሬ ወለደ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላትን በማጋለጥ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

#ወደ_ሀብት_ጉዞ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች በሚለውና #አስበህ_ሐብታም_ሁን በሚል በተተረጎመው መጽሐፉ የምናውቀው የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ።
#ወደ_ሀብት_ጉዞ
ይህ ወደ ሀብት ጉዞ የተሰኘው መጽሐፍ እያንዳንዱን ሕልማችንንና ዓላማችንን ለማሳካት ያግዘናል፡፡
ብልፅግና በገንዘብና ዝና ብቻ የተገደበ ትርጉም እንደሌለው ያሳየናል፡፡ እውነተኛ ባለጸጋ ለመሆን በሁሉም የሕይወት ዘርፎች መበልፀግ ያስፈልጋል- በአካል፣ በመንፈስ፣ በገንዘብ፡፡
ለዚህም ደግሞ ከ25 ሺ በላይ ሰዎች የውድቀት ምክንያት፣ ከ500 በላይ ስኬታማ ሰዎች ምስጢርና የሀያ አምስት አመታት የምርምር ውጤት... ወደ #ሀብት_ጉዞ መጽሐፍን ፈጥሯል።
ከ60 ሚሊየን ኮፒ በላይ ከተሸጠው አስበህ ሀብታም ሁን መጽሐፍ ቀጥሎ ከፍተኛ ሽያጭን የተቀዳጀ መጽሐፍ።
እነሆ በሁሉም መልክ ወደ ሀብት ጉዞ!!
የናፖሊዮን ሂልን መጽሐፍ ይዞ!!!
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun

👉 ዋጋችን ከ 300 እስከ 1,000 ብር ብቻ!!!
😱 3 ልብስ ለገዛ 1 በነፃ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ ቅናሽ።
ሰላም ውድ ደንበኞቻችን ጥራት ያላቸውን አልባሳት እና ጫማዎችን እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።
👉የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ምርጥ ምርጥ ልብሶችን በቅናሽ ዋጋ ይግዙ።
https://tttttt.me/CITYFASHION321
📞ስ.ቁ
0975798585
አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ(New day) ኒው ዴይ ሆቴል አጠገብ ባማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ሱቅ ቁጥር 108 ላይ ያገኙናል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የጨመረው የነዳጅ ዋጋ ኢትዮጵያን አሥር ቢሊዮን ብር እንዳከሰራት ተገለጸ!
በሩሲያና በዩክሬን መካከል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የጨመረው የነዳጅ ዋጋ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያን አሥር ቢሊዮን ብር እንዳከሰራት ተገለጸ፡፡
ከኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ይሸጥበት ከነበረው 60 እና 70 ዶላር ወደ 140 ዶላር ማሻቀቡ፣ ኢትዮጵያ አሥር ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ እንዳስወጣት ወይም እንዳከሰራት አመልክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለሪፖተር እንደገለጹት እንደ ሌሎቹ አገሮች ሁሉ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ኢትዮጵያንም ዋጋ እያስከፈላት ሲሆን፣ በአንድ ወር ብቻ አሥር ቢሊዮ ብር እንድታጣ ምክንያት መሆኑ ትልቅ ጉዳት መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ በወርኃዊ የነዳጅ ወጪዋም ወደ 250 ሚሊዮ ዶላር ከፍ እንዲል አስገድዷል፡፡ ይህም መንግሥት ይህንን ልዩነት በመሸፈን በዓለም ዝቅተኛ በተባለ ዋጋ ነዳጅ እየተሸጠ የሚገኝ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመር የበለፀጉ አገሮችን ጭምር እየፈተነ የሚገኝ ሲሆን፣ እንደ ፈረንሣይ ያሉ አገሮች በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ በማድረግ ኅብረተሰቡ ነዳጅን ቆጥቦ እንዲጠቀም ሁሉ ማወጃቸውን አቶ ታደሰ አስታውሰው፣ በኢትዮጵያ ነዳጅ ጭማሪ ባይደረግም ኅብረተሰቡ በቁጠባ የመጠቀም ባህሉን ማዳበር አለበት ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ አሁን ነዳጅ በምታስገባበት ዋጋ መሠረት ለገበያ ቢቀርብ የአንድ ሌትር የቤንዚን ዋጋ 76 ብር መሸጥ የነበረበት መሆኑንም ከአቶ ታደሰ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ አሁን ላይ ግን የአንድ ሌትር ቤንዚን ዋጋ 31 ብር ከ74 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል፡፡
Via Reporter

ፓኪስታን በጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሃን ጥያቄ ፓርላማዋን በተነች!
የፓኪስታን ፕሬዝዳንት በጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሃን ጥያቄ የሃገሪቱን ፓርላማ በተኑ፡፡የፓርላማው መበተን በቶሎ ምርጫ ለማድረግ በማሰብ የተደረገ ነው ተብሏል፡፡የኢምራን ካሃን መንግስት ተቃዋሚ የፓርላማ አባላት ህግ አውጭው የሃገሪቱ ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ መተማመኛ ድምጽ እንዲሰጥ ጠይቀው ነበር፡፡
ተቃዋሚዎቹ የቀድሞው የክሪኬት ኮኮብ ከስልጣን ለማስወገድ ከ342ቱ የምክር ቤቱ አባላት የ172ቱን ድጋፍ ማግኘት ብቻ ነበር የሚጠበቅባቸው፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲ አጣማሪ ሆኖ ወደ ምክር ቤቱ የገባው ፓርቲ የተቃዋሚዎቹን ጥያቄ መደገፉም ለጥያቄው አቅራቢዎች የልብ ልብ የሰጠ ነበር፡፡ሆኖም የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ ጥያቄው የአገዛዝ ለውጥ ለማድረግ በማሰብ የቀረበ ነው በሚል ወድቅ አድርገውታል፡፡
ይህ ሲሆን ከሰሞኑ በሩሲያ ጉብኝት ላይ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሃን በፓርላማው አልነበሩም፡፡ሆኖም በሃገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ፕሬዝዳንት አሪፍ አልቪ ምክር ቤቱን እንዲበትኑ እንደሚጠይቁ ተናግረው ነበር፡፡መንግስታቸውን ለመገልበጥ የተሸረበው ሴራ መክሸፉን በማሳወቅም ፓኪስታናውያን ለምርጫ እንዲዘጋጁም ካሃን ጠይቀዋል፡፡
ተቃዋሚዎቼ ሊገለብጡኝ ከአሜሪካ ጋር እያሴሩ ነው የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥያቄ የተቀበሉት ፕሬዝዳንት አሪፍም ትናንት እሁድ ምክር ቤቱ መበተኑን አሳውቀዋል፡፡
https://am.al-ain.com/article/pakistan-dissolves-parliament

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር 200 ቶን የሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል በየብስ ማጓጓዙን አስታወቀ።
ማህበሩ ወደ ትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ከትናንት በስቲያ በየብስ ዳግም ሟጓጓዝ ጀምሯል።በዚህም 200 ቶን ምግብ፣ የሕክምናና የውሃ ማከሚያ ግብአቶችን የያዙ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር እርዳታ ጫኝ መኪናዎች ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን የተቋሙ የኢትዮጵያ ቃል አቀባይ ፋቲማ ሳቶር ለኢዜአ ገልጸዋል።
ማህበሩ ወደ ክልሉ በየብስ እርዳታ ማጓጓዝ የጀመረው ከስድስት ወራት በኋላ እንደሆነና በቀጣይ በመደበኛነት ሰብአዊ እርዳታ ማድረሱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።ተቋሙ ወደ ትግራይ ክልል የየብስ አርዳታ ከማድረሱ በፊት በአየር በረራ ሕይወት አድን መድሐኒቶችና የሕክምና ግብአቶችን ሲያጓጉዝ ቆይቷል ብለዋል።
የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር የመንግስትን የሰብአዊ ተኩስ አቁም ውሳኔ በመልካም ጎኑ እንደሚያየውና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትና ተደራሽነቱን ለማሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው ቃል አቀባይዋ የገለጹት።ማህበሩ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነቱ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ለተጎዱ ወገኖች በዋናነት የምግብና የጤና ግብአቶች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም 13 እርዳታ ጫኝ መኪኖች ባለፈው ሳምንት 500 ሜትሪክ ቶን የምግብ ድጋፍ ትግራይ ክልል ማድረሱን መግለጹ አይዘነጋም።የኢትዮጵያ መንግስት መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነት ለማሳለጥ ሲል የሰብአዊ ተኩስ አቁም ውሳኔ እንዳደረገ መግለጹ የሚታወስ ነው።መንግስት ከመጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ዓለም አቀፍ የእርዳታ አቅራቢ ተቋማት ወደ ትግራይ ክልል በሳምንት ሁለት ጊዜ ያደረጉት የነበረውን የአየር በረራ በየቀኑ እንዲያደርጉ ፈቃድ ሰጥቷል።
ከሐምሌ 14 ቀን 2013 እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2014 ድረስ ወደ ትግራይ ክልል በአጋር አካላት አማካኝነት 51 ሺህ 497 ሜትሪክ ቶን ምግብና ቁሳቁሶች ለተረጂዎች መጓጓዙን ኢዜአ ከአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ቀይ መስቀል ተጠልለው የነበሩ የሕወሓት ታጣቂዎች ለዳግም ጦርነት እንዲሰለፉ እየተገደዱ ነው ተባለ!
ወደ ሱዳንና ካርቱም ሸሽተው የነበሩና ትጥቃቸውን ለሱዳን መከላከያ ሠራዊት አስረክበው ወደ ቀይ መስቀል የተጠጉ የቀድሞ የሕወሓት አባሎች፣ በሕወሓት ታጣቂዎች ተገደው ወደ ጦርነት እንዲሰለፉ እየተደረጉ መሆኑን በሁመራ ወረዳ የሚገኙ ታማኝ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
አለው፣ ዲማ እና ልበዲ በተባሉት አካባቢዎች ከመጋቢት 12 ጀምሮ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ የጠቆሙት የአዲስ ማለዳ ምንጮች፣ ሠሞኑን ከሱዳን የመጡና የሕወሓት አባላትን የሚያስተባብሩ ሰዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።
እነዚህ ከሱዳን የተለያዩ አካባቢዎችና ከካርቱም የመጡ ታጣቂዎች፣ ከዚህ በፊት የሕወሓት አባል የነበሩና ወደ ሱዳን ሸሽተው ትጥቃቸውን ለሱዳን መከላከያ በመስጠት ወደ ቀይ መስቀል የተጠጉ ሰዎችን እንደገና አስገድደው ወደ ጦር ግንባር የማሰለፍ ሙከራ እያደረጉ መሆናቸውን ነው ምንጮቹ አያይዘው የገለጹት።
ተጨማሪ ለማንበብ:
https://bit.ly/36QwIAg

በሃርጌሳ የገበያ ሥፍራ በደረሰው የእሳት አደጋ በቢሊየን ዶላር የሚገመት ውድመት ደርሷል ተባለ!
ባለፈው አርብ ራስ ገዝ አስተዳደር በሆነችው ሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሃርጌሳ በገበያ ስፍራ በተከሰተ የእሳት አደጋ በቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረት ሳይወድም እንዳልቀረ ተገለጸ።በአደጋው ለተጎዱት ከአጎራባች አገራት ዕርዳታ መግባት መጀመሩን ተከትሎ በአካባቢው አስተዳደር የተቋቋመው ኮሚሽን፣ የእሳት አደጋው ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱ ንብረቶችን ሳያወድም እንዳልቀረ አስታውቋል።በእሳት አደጋው ምክንያት ከደረሰው ከፍተኛ ውድመት በኋላ የተቀረፁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተጋርተዋል።
አርብ አመሻሽ ላይ የተነሳው እሳት በአጠቃላይ የገበያውን ሥፍራ አውድሞታል። በሃርጌሳ የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ቤተሰቦችን ሜዳ ላይ ያስቀረውን ይህንን እሳት ለማጥፋትም ሰዓታት ፈጅቷል።በሶማሊላንድ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ የተዋቀረውና በአደጋው የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራው ኮሚሽን በአደጋው ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ ውድመት ሳይደርስ እንዳልቀረ አመልክቷል።"እንደ የመጀመሪያ ደረጃው ሪፖርት ከሆነ በእሳት አደጋው የደረሰው የጉዳት መጠን ከ1.5 እስከ 2 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይገመታል" ሲሉ የሃርጌሳ ከተማ ከንቲባ አብዲካሪን አሕመድ ሞጌ ተናግረዋል።
Via BBC

በዛሬው ዕለት ከሳኡዲ አረቢያ፣ ጂዳ በተደረጉ ሦስት በረራዎች 269 ህጻናትን ጨምሮ 1 ሺህ270 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
በሳውዲ አረቢያ፣ በሪያድ እና የጅዳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ተግባር መቀጠሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ተመላሾች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች እና ማዕከላት ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ አገር ቤት ማምጣቱ፤ በሳምንት ለሦስት ቀናት በቀን ሦስት ግዜ በሚደረግ በረራ የመመለሱ ሥራ እንደሚቀጥልም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።