YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በራስ_መተማመን
4ተኛው ዕትም በገበያ ላይ

ይህ A Guide to confident Living የተባለው መጽሐፍ በራስ መተማመንን እርካታን መቀዳጀት እንችል ዘንድ ያስችላል።

ቀላል ለማንም ሰው ሊገባ በሚችል ቋንቋ የተጠቀመው
ዶ/ር ፒል በሕይወታችን ትልቅ መታደስ ማግኘት እንችል ዘንድ አዲስ የሆነ የኃይል መንገድን ይጠቁመናል።

ከሚለግሰን ምክሮች መካከል እንደ፤

* ውስጣዊኃ ይሎቻችንን ነጻ ማውጣት
* ችግሮቻችንን አውጥተን መናገር
* የበታችነት ኮምፕሌክሳችንን መውደድ
* ለሕይወታችን የተረጋጋ ማዕከልን ማግኘት
* የጸሎትን ኃይል መለማመድ
* ከፍርሃትና ሃዘን ነፃነትን ማግኘት
* የትዳር፣ ሙያዊ እና ግለሰባዊ ደስታን ማግኘት ያሉት ይጠቀሳሉ።

ኖርማን ቪንሰንት ፒል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሽያጭ ያስገኘለት The Power of Positive Thinkingን ጨምሮ የ46 ያህል መጽሐፎች ደራሲ ነው።

በኖረበት ዘመን ትልቅ ከተባሉ የሃይማኖት ሰዎች አንዱ የነበረው ዶ/ር ፒል ምንም እንኳ ሕይወቱ ቢያልፍም በስሙ በተከፈተው Peal Center For Chrisitian Living በተባለው ፋውንዴሽን አማካይነት ውርሱ ለመላው ዓለም እየተዳረሰ ይገኛል።

አሳታሚና አከፋፋይ- ዘላለም
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
የሚያዚያ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል!

የሚያዚያ ወር የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
ነገር ግን የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ቀላል ጥቁር ናፍጣ የመሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ የመጣው ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሱን ሚኒስቴሩ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአማራ ብሄር ስም የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች ያላቸው ታጣቂዎች ወደ ክልሉ ዘልቀው በመግባት በሰላማዊ ሰዎች እና በክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ላይ የፈጸሙት ጥቃት የክልሉን ሕዝብ ክፉኛ አስቆጥቷል በማለት ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

መግለጫው ጨምሮም፣ መንግሥታዊው የአማራ ክልል መገናኛ ብዙኀን እና ሌሎች መገናኛ አውታሮች ሰሞኑን የግጭት ነጋሪት ሲጎስሙ እና ጥላቻን ሲሰብኩ ቆይተዋል ሲል የከሰሰው የክልሉ መንግሥት፣ ድርጊቱን በዝምታ መመልከት ተገቢ አይደለም ብሏል። ጽንፈኝነት የሚወክለው ብሄርም ሆነ ኃይማኖት እንደሌለው ያወሳው መግለጫው፣ ሌላ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጠም።

@YeneTube @FikerAssefa
ተቋሙ የጤና መድህን አገልግሎቱ ለ43 ሚሊየን ዜጎች ተደራሽ መሆኑን ገለጸ!

በአገር አቀፍ ደረጃ ለ43 ሚሊየን ዜጎች የጤና መድህን አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት አስታወቀ።በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን አዋጅ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።
 
በዚህም በረቂቅ አዋጁ ላይ መካተት ያለባቸውን ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል።የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ÷በአገር አቀፉ ደረጃ የማህበረሰብ ጤና መድህን ተግባራዊ ከሆነ አንስቶ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል።በኢትዮጵያ ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል 78 በመቶ በሚሆኑት ላይ አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰው÷ በዚህም 43 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡

በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሲዳማና በደቡብ ክልሎች የተሻለ አፈጻጸም እንዳለ ጠቁመው÷ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያለውን አነስተኛ አፈፃጸም ለማሻሻልም ቀጣይነት ያለው ስራ ይከናወናል ብለዋል።የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሰሀረላ አብዱላሂ በበኩላቸው÷ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አዋጅ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል የጎላ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በጋራ ለሚጠቀሟቸው መሠረተ ልማቶች የኪራይ ተመን አውጥቸላቸዋለሁ ማለቱን ካፒታል ዘግቧል።ሁለቱ ኩባንያዎች የባለሥልጣኑን የኪራይ ተመን የሚጠቀመት ግን ልዩነታቸውን በድርድር ካልፈቱ ብቻ እንደሆነ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ረባ ተናግረዋል። ሆኖም እስካሁን ሁለቱም ኩባንያዎች የኪራይ ተመኑን ባለሥልጣኑ እንዲወስንላቸው አልጠየቁም። ኢትዮ ቴሌኮም ለሳፋሪኮም በሚያከራያቸው መሠረተ ልማቶች የኪራይ ዋጋ ተመን እና ኪራዩ በሚከፈልበት የገንዘብ ዓይነት ዙሪያ ሁለቱ ኩባንያዎች ገና ከስምምነት አልደረሱም።

[Capital/Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
#ችግሮችን_እንደ_ካርታ_ጨዋታ

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ትክክለኛ አስተሳሰብ ያለው ሰው ችግር አያስጨንቀውም፡፡ ምክንያቱም በቀላሉ መፍትሄ ከመሻቱም በዘለለ ለሕይወቱ ጣዕም ይጨምርለታል፡፡ ካርታ በምትጫወትበት ወቅት የማይረቡ ካርታዎች ቢደርሱህ እድል ከእኔ ጋር አይደለችም ብለህ በራስህ ማዘን አትጀምርም፡፡

አዎ አታስብም!

እንደ ፈተና አይተኸው ካርታዎቹን በሚገባቸው ቦታ እየሰካካህ ለማሸነፍ ትጥራለህ፡፡ ስታሸንፍ ከፍተኛ ደስታ ይሰማሃል፡፡ችግሮችን በድል ትወጣ ዘንድ የዚህ ዓይነት ብሩህ አመለካከት ይኑርህ፡፡

ለራስህም ይህን በል፦

"ከራሴም ይሁን ከዓለም ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ፡፡ የሚያጋጥሙኝ ችግሮች ያለኝን እውቀትና ኃይል ስለሚፈትኑት መጥፎ አይደሉም፡፡ በተገቢው ጊዜ ተገቢ ነገር ለመስራት እንቀሳቀሳለሁ፡፡"

አዎ ይህንንም አሁኑኑ ማድረግ ትችላለህ!

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
👉 ዋጋችን ከ 300 እስከ 1,000 ብር ብቻ!!!

😱 3 ልብስ ለገዛ 1 በነፃ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ ቅናሽ።

ሰላም ውድ ደንበኞቻችን ጥራት ያላቸውን አልባሳት እና ጫማዎችን እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።

👉የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ምርጥ ምርጥ ልብሶችን በቅናሽ ዋጋ ይግዙ።

https://tttttt.me/CITYFASHION321

📞ስ.ቁ
0975798585

አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ(New day) ኒው ዴይ ሆቴል አጠገብ ባማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ሱቅ ቁጥር 108 ላይ ያገኙናል።
ሽሮሜዳ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሽሮሜዳ አምባ ትምህርት ቤት አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን የማቾች ቁጥር ስድስት መድረሱ ተነግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት፣ የማቾች ቁጥር ከዘህም ከፍ ሊል የሚችልበት አጋጣሚ አለ ብለዋል፡፡

አደጋው የደረሰው የታክሲ አገልግሎት በሚሰጥ በተለምዶ ሚኒባስ ተብሎ የሚጠራው ተሸከርካሪ ላይ ነው ብለዋል፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ በቦታው ተገኝተው የነፍስ አድን ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ሲሉ ኢንስፔክተር ማርቆስ ተናግረዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የበልግ ዝናብ የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቆመ!

ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ሕብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ አስታወቀ።የዝናብ መጠኑ የተለያየ ቢሆንም ድርቅ በተከሰተባቸው ዞኖች የበልግ ዝናብ መዝነቡን አመልክቷል።

የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ሃላፍ ኮሚሽነር ሙስጠፋ ከድር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፡ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች በበልግ ዝናብ ወቅት ሊከሰት ከሚችል የጎርፍ አደጋ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት።

ጎርፍ የሞቱ የእንስሳት አካላትን ጠርጎ ወደ ውሃ ምንጮች በመቀላቀል ለተላላፊ በሽታዎች ሕብረተሰቡን ማገለጥ ስለሚችል ተገቢው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ገልጸው ተያያዥ ችግሮች ከተከሰቱ ሕብረተሰቡ በአካባቢው በሚገኙት ጤና ተቋማት ማሳወቅ እንዳለባቸው መክረዋል።

በስምንት ዞኖች ስር በሚገኙ በ56 ወረዳዎች የድርቅ አደጋ አስከፊ ችግሮችን ማስከተሉን አመልክተው በአሁኑ ጊዜ በእነዚህ አካባቢዎች የበልግ ዝናብ እየዘነበ በመሆኑ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርበት አሳስበዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የካማሺ ዞን ማረሚያ ቤት አዛዥ ተወካይን ጨምሮ ሦስት የማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች በታጣቂዎች መታገታቸው ተገለፀ!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ማረሚያ ቤት ተወካይን ጨምሮ ሶስት የማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች፤ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ በታጣቂዎች መታገታቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

እገታውን የፈጸሙት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው የሚል ግምት እንዳለ የኮሚሽኑ ምክትል ኃላፊ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።  

በማረሚያ ቤት ፖሊሶቹ ላይ እገታው የተፈጸመው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ አካባቢ ባሳለፍነው ሳምንት ሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2014 መሆኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው እንጅፋታ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

ፖሊሶቹ በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱት፤ ከአሶሳ ከተማ ወደ ካማሺ ዞን በህዝብ ማመለሻ አውቶብስ ተሳፍረው በመመለስ ላይ እንዳሉ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው አስታውቀዋል።

እገታው በተፈጸመበት ዕለት እኩለ ቀን ገደማ፤ ታጣቂዎች የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱን በመንገድ ላይ ካስቆሙ በኋላ በተሸከርካሪው ውስጥ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል ሶስቱን የማረሚያ ቤት ሰራተኞች ብቻ ለይተው መውሰዳቸውን ከዓይን እማኞች መረዳታቸውን የፖሊስ ኃላፊው ተናግረዋል።

በታጣቂዎቹ ተመርጠው ወዳልታወቀ ቦታ የተወሰዱት ፖሊሶች፤ የካማሺ ዞን ማረሚያ ቤቱ አዛዥ ተወካይ ኮማንደር ጉተማ ደላላ እንዲሁም የማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች ኮማንደር አብዱራሂም ዑመር እና ኢንስፔክተር በካ ጊቼሌ መሆናቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

ሦስቱ የማረሚያ ቤት ፖሊሶች ከአንድ ሳምንት በፊት ወደ ክልሉ ዋና ከተማ አሶሳ በተጓዙበት ወቅት በጸጥታ ኃይሎች ታጅበው እንደነበር የሚያስታውሱት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ በመልስ ጉዟቸው ግን “ለማንም ሳያሳውቁ በራሳቸው ጊዜ” የህዝብ ትራንስፖርት መጠቀማቸውን አስረድተዋል።

“ያለ እጀባ መሄዳቸውን እኛም እንደ ስህተት ነው የምንወስደው” ሲሉም የፖሊሶቹ የመልስ ጉዞ በተለመደው መልኩ በጸጥታ ኃይሎች አጀብ መከናወን እንደነበረበት አብራርተዋል። 

የአጋቾቹን ማንነት በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላቸው ኮሚሽነር ምስጋናው፤ “እሱን እርግጠኛ መሆን አንችልም። [ነገር ግን] እዚያ አካባቢ በስፋት የሚንቀሳቀሰው ኦነግ ሸኔ ነው። እርሱ ይሆናል የሚል ግምት አለን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ኹለት የካማሺ ዞን ነዋሪዎችም፤ በአካባቢው የ“ኦነግ ሸኔ” ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱ አረጋግጠዋል። የኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሚዋሰኑበት አካባቢ ያለውን ሁኔታም “በጣም ስጋት ያለበት” ሲሉ ገልጸውታል። 

ሦስቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊሶች ያገቷቸው “የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” የሚለውን ግምት ታሳቢ በማድረግ፤ የክልሉ መንግስት ታጋቾቹን በሽምግልና ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው ተናግረዋል።

“እስከ ትላንት ማታ ድረስ ታጋቾቹ ደህና መሆናቸውን አረጋግጠናል” የሚሉት ኮሚሽነር ምስጋናው፤ ታጋቾቹ ለቤተሰቦቻቸው ስልክ ደውለው “በህይወት አለን አትስጉ” ማለታቸውን እንደሰሙም አመልክተዋል። “የት እንዳሉ፣ ለምን ምክንያት እንደታገቱ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። በህይወት እንዳሉ ብቻ ነው መረጃ ያለን” ሲሉም አክለዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በ50,000 ብር ዋስ እንዲፈታ ተወሰነ!

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ታምራት ነገራን ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ50,000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ መወሰኑን አዲስ ዘይቤ ከቅርብ ቤተሰቦቹ አረጋግጣለች።

ጋዜጠኛው ከታሰረ ዛሬ 117 ቀናት የሆነው ሲሆን ክስ ሳይመሰረትበትና የዋስ ይግባኝ ጥያቄውም በጊዜ ቀጠሮ እየተላለፈ ዉሳኔ ሳያገኝ እስከ ዛሬ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በገላን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት፣ ፍርድ ቤቱ ባስተላለፈው ውሳኔ አቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ጋዜጠኛው ላይ ክስ እንዲመሰርት ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ጋዜጠኛው በጠበቃው በኩል መጋቢት 02 ቀን 2014 ዓ.ም በዋስ እንዲለቀቅ የሚጠይቅ የዋስ መዝገብ ከፍቶ ነበር።

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዋስ መዝገቡን ከተመለከተ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥ ቆይቶ ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጋዜጠኛው የዋስትና መብት እንዲከበርለት ውሳኔ አሳልፏል።

በመሆኑም በአሁን ሰዓት ቤተሰቦቹ የተጠየቀውን የዋስትና ገንዘብ ለሚመለከተው ክፍል በማስተላለፍ ላይ እንደሚገኙ እና ቀጣዩን ሂደት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

Via @AddisZeybe
@YeneTube @FikerAssefa
ባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል አስተላላፊ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በተፈፀመ ዝርፊያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል!

መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በዶዶታ ወረዳ እና ጌራ ከተማ አቅራቢያ ከአዋሽ 2 ወደ አሰላ በተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል አስተላላፊ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በተፈፀመ ዝርፊያ ሁለት ምሰሶዎች ወድቀዋል፡፡

ይህን ተከትሎ አሰላ ከተማና አካባቢው እንዲሁም በምዕራብ አርሲ፤ ሻሻመኔ፣ አርሲ ነጌሌ፣ ጉልጆታ፣ ኮፈሌ፣ አጄ፣ ሽሬ፣ ቆሬ፣ ወንዶ ገነት ከተሞችና አከባያቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

ይህን ተከትሎ አሰላ ከተማና አካባባው እንዲሁም በምዕራብ አርሲ ሻሻመኔ፣ አርሲ ነጌሌ፣ ጉልጆታ፣ ኮፈሌ፣ አጄ፣ ሽሬ፣ ቆሬ፣ ወንዶ ግነት ከተሞችና አከባያቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በዚህ ስርቆት ምክንያት በሮቤ ኃይል ማከፋፋያ ጣቢያ ላይ ጫና ፈጥሯል፡፡በዚህም የተነሳ ኃይል ከጣቢያው የሚያገኙት ሮቤ፣ አጋርፋ፣ ጋሰራ፣ ጎባ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው ላይም የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር ፈጥሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከቡታጅራ፣ አዳሜ ቱሉ እና ቡኢ የኃይል ማከፋፋያ ጣቢያዎች ላይ ጫና በመፈጠሩ ምክንያት በወራቤ፣ ቡታጅራ፣ ዳሎቻ፣ ቡኢ እና ጦራ አካባቢዎች የአገልግሎት አሰጣጥ መቆራረጥ ተከስቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጥገና ቡድን ዝርፊያ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ በስፍራው በመገኘት ጥገናውን በፍጥነት እያካሄደ ቢሆንም፤ መስመሩ ከፍታኛ ኃይል ተሸካሚ ስለሆነ ጥገናው ከሳምንት ያላነሰ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል አሳውቋል፡፡

በመሆኑም ደንበኞች ይህንን ተገንዝበው የጥገና ሥራው እስከሚያጠናቅቅ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥሪ አቅርቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል እና በሲዳማ ክልል አዋሳኝ የድንበር ወረዳዎች ላይ ተቀስቅሶ በነበረው ግጭት በአጠቃላይ የስምንት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ጎዳት እንደደረሰባቸው ተረጋግጧል፡፡

የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ‹‹ ግጭት የተቀሰቀሰው በሲዳማ ክልል ፣ ጪሪ ወረዳ ፣ ሀሌላ ቀበሌ ነዋሪዎች ዘንድ ታዋቂ የሆኑ የሀገር ሽማግሌ መገደላቸውን ተከትሎ ነው›› ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም በስልክ ያናገራቸው የምዕራብ አርሲ ዞን የመስተዳዳር እና ጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ ኮማንደር ጌታቸው ታዬን ከዚህ በፊት ተመሳሳይ የድንበር እና የወሰን ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚከሰቱ ተናግረው በዚህ ዓመት ግን ይህ የመጀመሪያው መሆኑን አንስተዋል፡፡

የወሰን እና የድንበር ጥያቄዎች ያሉባቸውን ስፍራዎች በመለየት ክልሎቹ እርስ በእርስ እንዲሁም እስከ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ድርስ በማድረስ እንዲፈቱ ብርቱ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት ችግሩ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡የአሁኑ ግጭት ግን ከዚህ ጋር እንደማይገናኝ ገልጸዋል፡፡

ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች አንድ አባት ተገድለው መገኘታቸውን ተከትሎ በተነሳ ግጭት ከምዕራብ አርሲ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ዘጠኝ ያህል ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ኮማንደር ተናግረዋል፡፡

የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በሰጡት መግለጫ እንዳሳወቁት በግጭቱ እስካሁን ከሲዳማ በኩል የሀገር ሽማግሌውን ጨምሮ ቢያንስ 2 ሰዎች ሲገደሉ ፤ ከቦናና በዳዬ ሆስፒታል በተገኘው መረጃ 15 ሰዎች በጥይት ቆስለዋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን የመስተዳዳር እና ጽጥታ ዘርፍ ሀላፊ ኮማንደር ጌታቸው ታዬ ችግሩ የተከሰተበት ስፍራ ራቅ ያለ በመሆኑ በእኛም በሲዳማ ክልልም በኩል መከላከያን ሰራዊት ይዘን በስፍራው ለመድረስ ከሁለት ሰአታት በላይ ፈጅቷል ፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰውም ለዚህ ነው በማለት ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ ገልጸዋል ፡፡አካባቢው ላይ አሁን መከላከያን ጨምሮ የሁለቱም ክልሎች ልዩ ሀይል ፖሊሶች የማረጋጋት ስራ እየሰሩ ነው ፤ ጉዳዩንም ማጣራት ተጀምሯል ብለዋል፡፡

Via Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
በኩርሙክ ወረዳ ድንገት በተከሰተ አውሎ ነፋስ በመኖሪያ ቤቶችና በተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

ትናንት ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ገደማ ድንገት በተነሳ አውሎ ነፋስ በወረዳው 7 ቀበሌዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።አውሎ ነፋሱ በኩርሙክ ወረዳ አሸሽሬ፣ ዱልሆደ፣ አደንግዝ፣ ቤለሁጅብላ፣ ዱልሸታሎ፣ ኦገንዱ፣ አቀንደዩና ሳሊማ ቀበሌዎች በሰዎች፣ በመኖሪያ ቤቶች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በመብራት ፖሎች፣ በእንስሳት ጤና ኬላዎች፣ በንግድ ሱቆች፣ የሃይማኖት ተቋማትና በቤት እንስሳት ላይ ሙሉ ለሙሉና በከፊል ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ የደረሰውን የጉዳት መጠን በወረዳ ደረጃ አጣሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ በማጣራት ላይ ይገኛል።በአደጋው የደረሰው የጉዳት መጠን ተጣርቶ እንደሚገለጽም ከወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#በራስ_መተማመን
4ተኛው ዕትም በገበያ ላይ

ይህ A Guide to confident Living የተባለው መጽሐፍ በራስ መተማመንን እርካታን መቀዳጀት እንችል ዘንድ ያስችላል።

ቀላል ለማንም ሰው ሊገባ በሚችል ቋንቋ የተጠቀመው
ዶ/ር ፒል በሕይወታችን ትልቅ መታደስ ማግኘት እንችል ዘንድ አዲስ የሆነ የኃይል መንገድን ይጠቁመናል።

ከሚለግሰን ምክሮች መካከል እንደ፤

* ውስጣዊኃ ይሎቻችንን ነጻ ማውጣት
* ችግሮቻችንን አውጥተን መናገር
* የበታችነት ኮምፕሌክሳችንን መውደድ
* ለሕይወታችን የተረጋጋ ማዕከልን ማግኘት
* የጸሎትን ኃይል መለማመድ
* ከፍርሃትና ሃዘን ነፃነትን ማግኘት
* የትዳር፣ ሙያዊ እና ግለሰባዊ ደስታን ማግኘት ያሉት ይጠቀሳሉ።

ኖርማን ቪንሰንት ፒል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሽያጭ ያስገኘለት The Power of Positive Thinkingን ጨምሮ የ46 ያህል መጽሐፎች ደራሲ ነው።

በኖረበት ዘመን ትልቅ ከተባሉ የሃይማኖት ሰዎች አንዱ የነበረው ዶ/ር ፒል ምንም እንኳ ሕይወቱ ቢያልፍም በስሙ በተከፈተው Peal Center For Chrisitian Living በተባለው ፋውንዴሽን አማካይነት ውርሱ ለመላው ዓለም እየተዳረሰ ይገኛል።

አሳታሚና አከፋፋይ- ዘላለም
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/

Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
አብን ገዥው ብልጽግና ፓርቲ ውስጣዊ ልዩነቶቹን ወደ ሕዝብ ግጭት ለማውረድ ኃላፊነት የጎደለው ሙከራ እያደረገ ነው ሲል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ ከሷል።

ገዥው ፓርቲ ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ፣ አሞራ ቤት ቀበሌ የተፈጠረውን ግጭት ወደ ሕዝብ ለማውረድ መሞከሩ የፖለቲካ ኃላፊነትን መዘንጋት ወይም የፖለቲካ ሸፍጥ ነው ያለው አብን፣ ሙከራው ገዥውን ፓርቲ በሕግም ሆነ በታሪክ ተጠያቂ ያደርገዋል በማለት አስጠንቅቋል። አብን ጨምሮም፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአማራ ክልል ስር የሚገኝን አስተዳደራዊ አካባቢ ሌላ ስያሜ በመስጠት በኦሮሚያ ክልል ስር የሚገኝ አስመስሎ ማቅረቡን በአስቸኳይ እንዲያቆም ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በአምላክ ተሰማ የኳታር የዓለም ዋንጫን ከሚዳኙ ስምንት አፍሪቃውያን ዳኞች ውስጥ አንዱ ሆኑ።

የኳታር የአለም ዋንጫ በቀጣይ አመት ከህዳር 12 እስከ ታህሳስ 9 ድረስ ሲካሄድ በዳኝነት በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ አርቢትሮች መካከል ስምንቱ አፍሪካውያን መሆናቸውን ፊፋ አሳውቋል። በዚህም ባለፈው የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘው ኢትዮጵያዊው አርቢትር ባምላክ ተሰማ ፊፋ የአለም ዋንጫውን ይዳኛሉ ብሎ ዝርዝራቸውን ይፋ ካደረገው አፍሪካውያን ዳኞች አንዱ በመሆን የኳታርን ትኬት መቁረጡን አረጋግጧል። ከባምላክ በተጨማሪም በአለም ዋንጫው ላይ የሚዳኙ አፍሪካውያን ሙስጠፋ ጎርባል ከአልጄሪያ፣ሬዱያኔ ጅያድ ከሞሮኮ፣ፓፓ ባካሪ ጋሳማ ከጋምቢያ፣ቪክተር ጎሜዝ ከደቡብ አፍሪካ፣ጃኒ ሲካዝዌ ከዛምቢያ፣ማጉኤቴ ንዲያዬ ከሴኔጋል፣ጃኩኤስ ንዳላ ከኮንጎ መሆናቸው ተረጋግጧል።

@YeneTube @FikerAssefa