YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጉራጌ ዞን ቆሴ ከተማ ያለው ችግር ምንድን ነው?

ቆሴ በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ወደከተማ አስተዳደርነት ለማደግ እንቅስቃሴ ላይ ያለች መለስተኛ ከተማ ናት።አካባቢው ሁለት የጉራጌ እና የሃድያ ብሔረሰቦች የሚዋሰኑበት ነው። በዚህ አካባቢ  ከዚህ ቀደም ግጭት ተከስቶ ነበር። አካባቢው በህዝበ ውሳኔ ወደ ጉራጌ ዞን ተጠቃሎ ከቆየ ከረዥም ዓመታት በኋላ አሁን ደግሞ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶይቸ ቬለ እንደገለፁት ግጭት እንደ አዲስ ተነስቷል። » ለውጡ ከመጣ በኋላ በሀዲያ ዞን የሚኖሩ ወጣቶች ከተማው ለኛ ይገባል በሚል መነሳሳት ውዝግብ ተነስቷል።

እና አሁንም ድረስ ከፍተኛ የሆነ የአካል ጉድለት እና የንብረት ጉድለት እየተፈፀ ነው። ብዙ ቤቶች ተቃጥለዋል። »እንደ የአካባቢው ነዋሪ ከሆነ ችግሩ በውይይት ተፈታ በተባለ እለትም ቤቶች ተቃጥለዋል ንብረትም ወድሟል። « እስከዛሬ ድረስ ውጥረት ላይ ነው ያለው። ምንም መፍትሄ አላገኘም። ከተማዋ ላይ ትልቅ ገበያ ነበር። ግን እየተካሄደበት አይደለም» እናም ከመንግሥት አካላት መፍትሄ እንፈልጋለን ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች። ጉዳዩን አስመልክቶ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሃመድ ጀማል በመሠረተ ልማቶች ላይ በተደራጀ መልኩ ጥቃት የሚፈፅሙ ሰዎች እንደነበሩ ገልፀው «ዘግይተንም ቢሆን» በቅርቡ ችግሩን ለመፍታት ችለናል ይላሉ።

  ባለፉት ሁለት ወራት በአካባቢው አንፃራዊ ሰላም ይታያል ያሉን የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሁንም ግን አንዳንድ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱና በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ተጠርጣሪ ሰዎች መኖራቸውን ገልፀዋል።ቆሴ ከ 16 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች አብረው የሚኖሩበት ከተማ እንደሆነች የገለፁልን የድቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዴ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምክንያት አለመግባባቶች የነበሩ ቢሆንም እነዚህ ጥያቄዎች አሁን በምክክር እና በውይይት ተፈተዋል ይላሉ። ይሁንና አሁንም የህዝቡን እንድነት ለመሸርሸር የሚሞክሩ ውስን ግለሰቦች አሉ ብለዋል። አቶ አለማየሁ አክለውም እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎችን ህዝቡ ጠይቀዋል። ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙ ሰዎችም በህግ እንደሚጠየቁ ገልጸዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
https://tttttt.me/sabinaadvisor

የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week

👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
#ወደ_ሀብት_ጉዞ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች በሚለውና #አስበህ_ሐብታም_ሁን በሚል በተተረጎመው መጽሐፉ የምናውቀው የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ።

#ወደ_ሀብት_ጉዞ

ይህ ወደ ሀብት ጉዞ የተሰኘው መጽሐፍ እያንዳንዱን ሕልማችንንና ዓላማችንን ለማሳካት ያግዘናል፡፡

ብልፅግና በገንዘብና ዝና ብቻ የተገደበ ትርጉም እንደሌለው ያሳየናል፡፡ እውነተኛ ባለጸጋ ለመሆን በሁሉም የሕይወት ዘርፎች መበልፀግ ያስፈልጋል- በአካል፣ በመንፈስ፣ በገንዘብ፡፡

ለዚህም ደግሞ ከ25 ሺ በላይ ሰዎች የውድቀት ምክንያት፣ ከ500 በላይ ስኬታማ ሰዎች ምስጢርና የሀያ አምስት አመታት የምርምር ውጤት... ወደ #ሀብት_ጉዞ መጽሐፍን ፈጥሯል።

ከ60 ሚሊየን ኮፒ በላይ ከተሸጠው አስበህ ሀብታም ሁን መጽሐፍ ቀጥሎ ከፍተኛ ሽያጭን የተቀዳጀ መጽሐፍ።

እነሆ በሁሉም መልክ ወደ ሀብት ጉዞ!!
የናፖሊዮን ሂልን መጽሐፍ ይዞ!!!

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
በእስራኤል ከሚፈጸሙ ዘር ተኮር ጥቃቶች አብዛኞቹ ቤተ-እስራኤላውያን ላይ እንደሚያነጣጥሩ ሪፖርት ጠቆመ!

እስራኤል ውስጥ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ከተመዘገቡት የዘረኝነት ጥቃቶች ግማሽ ያህሉ ቤተ-እስራኤላውያን እንዲሁም አረቦች ላይ ያነጣጠሩ እንደነበሩ በመንግሥት የወጣ ሪፖርት አመለከተ።የእስራኤል የፍትሕ ሚኒስቴር ባወጣውን ሪፖርት መሠረት እንደ አውሮፓውያኑ በ2021 እስራኤል ውስጥ ከተፈጸሙ 458 ዘር ተኮር ጥቃቶች መካከል 48 በመቶው ያህሉ የደረሱት ከኢትዮጵያ በሄዱ ቤተ-እስራኤላውያን እና በአረቦች ላይ ነው።

በእስራኤል የፍትሕ ሚኒስቴር ሥር የሚገኘው የዘር ተኮር ጥቃቶች መከላከል ክፍል እንዳለው እነዚህ ጥቃቶች በአገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋል መድልዎ፣ የሥራ ቅጥር መድልዎ፣ ዘረኛ ንግግሮች እና ዘረኛ ማስታወቂያዎችን ያካትታሉ።አምና ለእስራኤል የፍትሕ ሚኒስቴር በደረሱ ጥቆማዎች መሠረት ኢትዮጵያዊ የዘር ሐረግ ያላቸው እስራኤላውያን ዘረኛ መድልዎ ይደርስባቸዋል፣ ይገለላሉም።

በመሥሪያ ቤቱ ከተመዘገቡ ዘረኛ ጥቃቶች መካከል 24 በመቶው በቀጥታ ቤተ-እስራኤላውያን ላይ ሲያነጣጥሩ፣ ቀሪው 24 በመቶ አረቦች፣ 10 በመቶው ደግሞ የመካከለኛው ምሥራቅ የዘር ግንድ ያላቸው አይሁዳውያን ላይ የተቃጡ ናቸው።የእስራኤል የፍትሕ ሚኒስቴር ባወጣውን ሪፖርት መሠረት፤ እአአ በ2019፤ 497 ዘር ተኮር ጥቃቶች ተመዝግበዋል። በ2020 ደግሞ 506 እንዲሁም አምና የተመዘገቡት 458 ጥቃቶች ናቸው።እነዚህ ጥቃቶች በፍትሕ ሚኒስቴር የተመዘገቡ ብቻ ሲሆኑ፣ በመላው አገሪቱ ያለው እውነታ ከዚህ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል አስተዳደር በተናጥል ግጭት ማቆማቸውን ባለፈው ሳምንት ካሳወቁ ወዲህ ወደ ትግራይ ዕርዳታ አልገባም በማለት የሕወሃት ባለሥልጣናት አማረዋል። የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሠ ቱሉ ግን ሕወሃት ታጣቂዎቹን ከአፋር ክልል ካላስወጣ ዕርዳታውን ለማጓጓዝ እንደማይቻል ለቪኦኤ ተናግረዋል። ባሁኑ ወቅት 43 ዕርዳታ የጫኑ ካሚዮኖች በሠመራ ከተማ ዝግጁ ሆነው የታጣቂዎችን መልቀቅ እየተጠባበቁ እንደሆነ ለገሠ ገልጸዋል። ሕወሃት ግን ግጭት የማቆም ቃሌን የማከብረው ዕርዳታ ከገባ ብቻ ነው ይላል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በቤንች ሸኮ ዞን የጉራ ፈርዳ ወረዳ የጸጥታ ችግሮች ከዞኑ አቅም በላይ መሆናቸው ተገለጸ!

በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ እና በአጎራባች አካባቢዎች በየወቅቱ የሚከሠቱ የጸጥታ መደፍረሶች ከዞኑ አቅም በላይ መሆናቸውን የቤንች ሸኮ ዞን መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ደቡብ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ቤንች ሸኮ ወረዳ፣ ሸካ ወረዳ፣ ጉራ ፈርዳ ወረዳ እና በአጎራባች ቦታዎች በየወቅቱ የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ለመቆጣጠር የጸጥታ ግብረ ኃይል እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም፣ ከዞኑ አቅም በላይ መሆኑን ተከትሎ በአከባቢው ያለውን የፀጥታ ችግር ሙሉ ለሙሉ ለማጥራት መቸገሩን የዞን ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ተስፋየ ጊታር ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በሀገር ውስጥ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ!

ከዚህ ቀደም ወደ ዉጭ ሀገር በመላክ ይሰጥ የነበረዉን አገልግሎት በሀገር ዉስጥ ለመስጠት ያስችላል የተባለለት ለወንጀል ምርመራ የሚያግዝ የዘረ-መል (ዲ ኤን ኤ) ምርመራ በሀገር ዉስጥ ለመጀመር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።አገልግሎቱ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ስለሚጀምረዉ ቴክኖሎጂው አተገባበር እና ስለሙከራው ውጤታማነት በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ለህዝብ መረጃ እንደሚሰጥ የፌደራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄላን ኢብራሂም ተናግረዋል።

ለወንጀል ምርመራ ስራ የሚያግዙ አዳዲስ የፎረንሲክ ምርመራ ማሽኖችን ወደ ሀገር አስገብቶ ጥቅም ላይ እያዋለ መሆኑን የገለጸዉ ፖሊስ ሌሎች አሰራሮቹንም በቴክኖሎጂ እያዘመነ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪም የአቪየሽን ፖሊስ፣ የምድር ባቡር ፖሊስ፣ የዩኒቨርሲቲ ደህንነት ፖሊስ እንዲሁም በኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርጎ የሚከታተል የፖሊስ ክፍሎች በአዲስ መልክ ተደራጅተዋል ነዉ የተባለው።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ዘመን ባንክ የማስተር ካርድ የክፍያ ሲስተምን መተግበር የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ!

ዘመን ባንክ ኤም ፒ ጂ ኤስ የተባለ የማስተር ካርድ ሲስተምን በማስጀመር ክፍያዎችን በቀጥታ መክፈል የሚያስችል ቴክኖሎጂን አስተዋውቋል።ይህንን ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀው ከማስተር ካርድ ጋር በመሆን ነው።ይህ የክፍያ ሲስተም ለአየር መንገድ እንዲሁም ለሆቴሎች ቅድሚያ አገልግሎት ክፍያ መፈጸም የሚያስችል ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም የኦንላየን ግብይቶችን በቀጥታ መክፈል የሚያስችል ነው።ይህ የክፍያ ሲስተም በኢትዮጵያ ብርም መገበያየት የሚያስችልና የቀጥታ ክፍያ ንክኪን የሚቀንስ ነው።ኢኮሜርስ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ የመጣ ከመሆኑ አንጻር እንዲህ አይነት ቴክኖሎጂ ግብይቱን በአንድ ቦታ በመጨረስ እንዲቀላጠፍ ያደርጋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በ2014 የሙያ ብቃት ምዘና ከወሰዱ መምራን መካከል 1,600ዎቹ ማለፋቸው ተነገረ፡፡

ምዘናው ሁለት ዓይነት እንደሆነ የከተማዋ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዛሬ ባዘጋጀው መርኃ ግብር ላይ ሲነገር ተሰምቷል።የመጀመሪያው የጽሑፍ ምዘና ሲሆን ይህን ምዘና 1,835 መምህራን በዚህ ዓመት ወስደዋል ተብሏል።

የጽሑፍ ፈተናውን ከወሰዱ 1,835 መምህራን መካከል 1,600ዎቹ ለማህደረ ተግባር ፈተና መቅረባቸው ተጠቅሷል።እነዚህ በሙሉ የማህደረ ተግባር ፈተናውን አልፈው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት ማግኘታቸው ተነግሯል።የማህደረ ተግባር ምዘና የመምህሩን አጠቃላይ የተግባር እንቅስቃሴ የሚያሳይ ስርዓት እንደሆነ ተሰምቷል።

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ቢሊየነሩ አብራሞቪች በኢስታንቡል የሰላም ንግግር ላይ ተገኝተዋል

ሮማን አብራሞቪች ተመርዘዋል የሚለዉ መረጃ ዉድቅ አድርጓል


ሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች በቱርክ አሸማጋይነት በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በተደረገው የሰላም ድርድር ላይ ታይተዋል።በኢስታንቡል በተደረገው ውይይት ላይ ሽምግልና ላይ ከሚገኙት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር ሲነጋገሩ ታይተዋል።

አብራሞቪች እና ሁለት የዩክሬን ተደራዳሪዎች በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ካካሄዱት ድርድር በኋላ የመመረዝ ምልክት ታይቆባቸዋል የሚል ሪፖርት ከወጣ ከሰዓታት በኋላ ነው የቢሊየነሩ ምስል ይፋ ተደርጓል፡፡ አብራሞቪች በሞስኮ እና በኪየቭ መካከል በሽምግልና ሚና ላይ ሳምንታት እንዳሳለፉ ይታወቃል።

የቼልሲው የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት የዓይን እና የቆዳ ህመም አጋጥሟቸው ነበር ቢባልም አሁን ግን አገግመዋል የሚል መረጃ ይፋ ሆኗል፡፡በዎል ስትሪት ጆርናል ዘገባ መሰረት ሮማን አብራሞቪች እና የዩክሬን ተደራዳሪዎች በሩሲያ አማካይነት ተመርዘዋል ቢልም የዩክሬን ፕሬዝዳንት ባለስልጣን ግን ሁለቱ ዩክሬናውያን ደህና እንደሆኑ እና መረጃዉ የውሸት ነው ብሏል።

ሆኖም ግን የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከውይይቱ ከሰዓታት በፊት በብሔራዊ ቲቪ እንደተናገሩት ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ የሚገኙ ባልደረቦቻቸው ምንም ነገር እንዳይበሉ እና እንዳይጠጡ መክረዋል።የኢስታንቡል ውይይት ማክሰኞ እለት በንግግር የከፈቱት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የተኩስ ማቆም እና የሰላም ጥሪ በማቅረብ "ግጭቱን ማራዘም ለማንም አይጠቅምም" ሲሉ ለሁለቱ ልዑካን ቡድን በዶልማባቼ ቤተ መንግስት ተናግረዋል፡፡

[ ዳጉ ጆርናል ]
@Yenetube @Fikerassefa
በኮንሶ ዞንና አሌ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ህይወት መጥፋቱና ንብረት መውደሙ ተገለጸ!

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ በሚገኙት የኮንሶ ዞንና አሌ ልዩ ወረዳ ከሰሞኑ በተከሰተ ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን፣ ቤቶች መቃጠላቸውንና ንብረት መውደሙን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ።መጋቢት 09/2014 ዓ.ም በተነሳውና እስከ ትናንት በስቲያ በቀጠለውም ግጭት በኮንሶ በኩል አስካሁን ቁጥሩ በትክክል ያልታወቀ የሰዎች ህይወት ማለፉን፣ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን እንዲሁም በሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን አቶ ሠራዊት ዲባባ በኮንሶ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

"የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ንብረት ወድሟል፣ የአካል ጉዳት ተመዝግቧል። ይህ ጉዳት ደግሞ የሁላችንም ህመም ነው። እጅግ በጣም አሳዝኖናል" ብለዋል አቶ ሠራዊት።በአሌ ወረዳ በኩልም እንዲሁ በተመሳሳይ የሰው ህይወት መጥፋትን ጨምሮ፣ የአካል ጉዳትና ከፍተኛ የንብረት ውድመት እንዳጋጠመ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የአሌ ልዩ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ገሚሶ ገሳቶ ያስረዳሉ።

ለግጭቱ መነሻ የሆነው በኮንሶ ዞንና አሌ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች ባለ የኩታ ገጠም እርሻ መሬት የይገባኛል ጥያቄ እንደሆነም ሁለቱም ባለሥልጣናት ይናገራሉ።የሰሞኑ ግጭት ከእርሻና ግጦሽ መሬት ጋር በተያያዘ የይገባኛል እንዲሁም የከብት ዝርፊያዎችና በሰዎች ላይ በደረሰ ጥቃት ግጭቱ ማገርሸቱንም ያስረዳሉ።ከሰሞኑም በኮንሶ በኩል የኮልሜ ክላስተር እንዲሁም በአሌ በኩል ደግሞ ገዋዳ ክላስተር የሚባሉ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ በሚገኙ አርሶ አደሮች መካከል የተፈጠረው ግጭት መባባሱን የጠቆሙት አቶ ገሚሶ "የግጭቱ መነሻ በግለሰቦች መካከል የነበረ ቢሆንም ወደ ማኅበረሰቡ መስፋፋቱን" አመልክተዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መጋቢት 16 ያሳለፈው ውሳኔ ገቢራዊ ይሆን ዘንድ ህወሓት ከተቆጣጠራቸው ስድስት የአፋር ክልል ወረዳዎች ለቅቆ መውጣት ይገባዋል አለ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ” ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማስቆም ስለመወሰኑ ” መጋቢት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ” በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ ” አስታውቋል፡፡

በዚህም” የሰብዓዊ አቅርቦቶች ወደትግራይ በበቂ ሁኔታ መድረስ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማሳካት የተቻለውን ጥረት ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን” መግለፁም አይዘነጋም፡፡ይሁንና ከተጠቀሰው ጊዜ አንስቶ ወደትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታዎች ወደትግራይ ክልል እየገቡ እንደማይገኝ መንግስት ገልጿል፡፡

ከአሻም ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሠ ቱሉ(ዶ/ር) ”ህወሓት ከያዛቸው ስድስት አፋር ክልል ወረዳዎች እስካለቀቀ ድረስ ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ መላክ እንደማይቻል” ተናግረዋል፡፡ምክንያታቸውን ሲያስቀምጡም ”ሰብዓዊ እርዳታዎቹ የሚተላለፉበትን የአስፓልት መንገድ ይዟል፤ ግጭትም አላቆመም” ሲሉ ከስሰዋል፡፡ምንም እንኳን በአፋር ክልል በኩል በየብስ ሰብዓዊ አቅርቦቶች ወደ ትግራይ ክልል ለማጓጓዝ አስቸጋሪ ይሁን እንጂ በአውሮፕላን በየቀኑ በሚደረገው በረራ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ ስለመሆኑ ለአሻም ነግረዋታል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
#ወርቃማ_ሕጎች
የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

#አእምሮህ_ማግኔት_ነው!

ሁልጊዜም አእምሮህ ማግኔት መሆኑን አስታውስ፡፡ አንተን የተቆጣጠሩህን ሃሳቦች እና በውስጥ የሰረፁትን እምነቶች የሚያምኑ እና የሚያስቡ ሌሎች ሰዎች ወዳንተ እንደሚያቀርብም ልብ በል፡፡

በትክክለኛ መንገድ የስበት ህግ (law of attraction) ብለን የምንጠራው አንድ ህግ አለ፡፡ ውሃ ከፍታውን የሚፈልግበት፣ በህዋ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ የየራሳቸውን አምሳያ የሚፈልጉበት ህግ፡፡ ፕላኔቶችን በትክክለኛ ቦታቸው ጠብቆ እንደሚያቆየው የስበት ህግ፡፡

ይህ ህግ የሚለዋወጥ ቢሆን ኖሮ የማንጎ ፍሬ ከአበባው ውስጥ በርራ በፓፓያ አበባ ውስጥ በመግባት በከፊል ማንጎ፣ በከፊል ደግሞ ፓፓያ የሆነ ዛፍ ይፈጥሩ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ግን ሰምተን አናውቅም፡፡ ይሄንን የስበት ህግ ትንሽ በመከተል በሴቶች እና በወንዶች መካከል እንዴት እንደሚሰራ ማየት እንችላለን፡፡

ውጤታማና ሃብታም ወንዶች የሚፈልጓት ሴት የእነሱኑ አይነት ሴት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለ ወንድም እንደዚያው፡፡ ይህ የሚሆነው በተፈጥሮ ነው - ልክ ውሃ ወደ ታች እንደሚፈሰው፡፡

“ሁሉም አምሳያውን ይስባል” የሚለው አባባል የማይገሰስ ሀቅ ነው፡፡ አንድ ወንድ የሚፈልጋት ሴት በብዙ መልኩ እሱን የምትመስለውን ሴት መሆኑ እውነት ከሆነ፣ የምትፈልጋቸውን ሰዎች ለማሰብ የእነዚህን ሰዎች ሀሳቦች እና እምነቶች በመቆጣጠር እና በማዳበር ማግኔት የመስራትን ጥቅም ማየት አትችልም?

#ወርቃማው_ሕግ መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና አዟሪዎች እጅ ይገኛል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun
👍1
ምርጫ ቦርድ በ2014 ዓ.ም 50 ሚሊዮን ብር ለፓርቲዎች አከፋፍላለሁ አለ!

ቦርዱ ለ35 አገር አቀፍ እና ክልላዊ ፓርቲዎች ገንዘቡን የሚያከፋፍል ሲሆን፤ ከእነዚህም ብልጽግና 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር፣ ኢዜማ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር፣ ኦብነግ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ ኦነግ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ ተብሏል።

ቦርዱ ከምርጫ ቁሳቁስ ሕትመት የተረፈውን 50 ሚሊዮን ብር ነዉ ለፓርቲዎች ድጎማ እንደመደበ የተናገረው።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ለፓለቲካ ፓርቲዎች ድጎማ የጠየቀውን የ230 ሚሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ ቢያቀርብም እንዳልተቀበለው ካስታወቀ በኋላ ነው ይህን አማራጭ የተጠቀመው። ቦርዱ ዛሬ ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ፣ አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ገንዘብ ሚንስቴር ገንዘቡን መመደብ እንደማይችል እንዳሳወቀ ገልጧል።የፓርቲዎች የድጎማ ቀመር፣ ፓርቲዎቹ በምርጫ ያገኙትን መቀመጫ፣ የሴት እና የአካል ጉዳተኛ አባላት ብዛት እና ያሰባሰቡትን የገንዘብ አቅም መሠረት ያደረገ እንደሆነ ዋዜማ ዘግባለች።

@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤት ዛሬ የአሶሴትድ ፕሬስ ዘጋቢዎች አሚር አማን እና ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው በ60 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል።

ሆኖም ችሎቱ ዘጋቢዎቹ ከአገር እንዳይወጡ እገዳ ጥሎባቸዋል። ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት ቢጠይቅም፣ ችሎቱ ግን የእስካሁኑ ምርመራ ለውጥ አላሳየም በማለት ነው የገንዘብ ዋስትናውን የፈቀደው። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ባለፈው ኅዳር ያሰራቸው፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮችን እና ታጣቂዎችን መስክ ወርደው በማነጋገር እና በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽ ወደ ውጭ አገር መረጃዎችን ልከዋል በማለት ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa