YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ!

አቶ ተወልደ ከኃላፊነታቸው በይፋዊ መንገድ የለቀቁት ከጤናቸው ሁኔታ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ታማኝ ምንጮች ለኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ ተናግረዋል፡፡

ከስድስት ወራት ላለፈ ጊዜም አቶ ተወልድ ህክምናቸውን በአሜሪካ እየተከታተሉ እንደሆነም ይታወቃል፡፡አቶ ተወልደ አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስፈፃሚ አሥፈፃሚነት የመሩ ሲሆን፤ ለ37 አመታትም አየር መንገዱን አገልግለዋል፡፡

ምንጭ- ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
@YeneTube @FikerAssefa
ትምህርት ሚኒስቴር የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታን ተቀብሎ እንዲፈታ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ!

ትምህርት ሚኒስቴር የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታን ተቀብሎ እንዲፈታ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ።የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን አስመልክቶ ከተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታ እንደቀረበለት ገልጿል።

ተቋሙ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን አስመልክቶ ለተቋሙ የቀረቡ ጥቆማዎች እና በተለያዩ ሚዲያዎች ጉዳዩን አስመልክቶ የቀረቡ ዘገባዎችን መነሻ በማድረግ ጉዳዩን መርምሬያለሁ ብሏል።

በተደረገው ምርመራ መሰረትም የፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተና እርማትን አስመልክቶ ተማሪዎች ያቀረቡትን ቅሬታ በመቀበል ምላሽ መስጠቱን የገለጸ ቢሆንም የተቋሙ መርመሪዎች ለምርመራ ስራ በኤጀንሲው በተገኙበት ወቅት በርካታ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለማቅረብ በኤጀንሲው ቢገኙም ወደ ውስጥ ገብቶ ቅሬታን ለማቅረብም ሆነ ቅሬታቸውን ተቀብሎ ሊያስተናግዳቸው አልቻለም ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
The Right Time,
The Right Moves!
Join The Global Education Expo Today.
www.backtoschoolafrica.com

List of Exhibitors:

Schools & Colleges/Universities
School Management Solution Providers
Software developers
App developers & Coders
Start-ups & TECH Entrepreneurs
Education Consultants
STEM Education Incubators,
Digital Service Providers
Education Material Producers & Suppliers
Digital Libraries
NGOs & related.

To Reserve Your Booth:
Call us:
+251 974 0820 36
+251 974 0820 37
⬆️⬆️
#NewsAlert

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንትና ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት የቀድሞው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ተነስተው በምትካቸው የአየር መንገዱ ቦርድ አባል የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ ተሹመዋል።አቶ ግርማ ዋቄ ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ መመደባቸውንም ምንጮቹ ገልጸዋል።

አቶ ግርማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመደቡት ለአንድ ዓመት ብቻ እንደሆነና ዋና ተልእኳቸውም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የተረጋጋ የማኔጅመንት ቡድን መገንባት እንደሆነ ታውቋል።በአዲሱ የድርጅቱ አወቃቀር መሠረት፣ ከፕሬዚዳንቱ ስር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈጻሚ ሊኖር እንደሚችል ምንጮቹ ገልጸዋል።

አቶ ግርማን የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አድርጎ የመደባቸው በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል።የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ማሞ ምህረቱ መረጃውን እንዲያረጋግጡ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የአቶ ግርማ ዋቄ ሹመት ከመሰማቱ አስቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን መዘገቡ ይታወሳል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ተወልደ በህክምና ላይ ባሉበት አሜሪካን አገረ ሆነው ለተቋሙ ማኔጅመንት በላኩት የኢሜል መልእክት፣ በገጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በኃላፊነት መቀጠል እንዳልቻሉ ጠቅሰው፣ በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው በጡረታ መገለላቸውን አሳውቀዋል።

አቶ ተወልደ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚነትን የተረከቡት ከአቶ ገርማ ዋቄ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በአየር መንገዱ በተለያዩ ኃላፊነቶች ለ37 ዓመታት አገልግለዋል፡፡በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ አባላት ስብሰባ ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ምንጮቹ ፣ በዚህ ስብሰባ ለአየር መንገዱ አዲስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ምደባ ሊወሰን እንደሚችል ጠቁመዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ በብላቴ ወንዝ ፏፏቴ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በድንገተኛ የደራሽ ውሃ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን ከከተማ አስተዳደሩ አሰታወቀ።

በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 4 ሰዓት አከባቢ በቁሊቶ ከተማ ገበያ ውለው ወደ ቤታቸው ለመመለስ ወንዙን በማቋረጥ ላይ ሳሉ ነው ድንገተኛ የደራሽ ውሃ አደጋው የተከሰተው።

ህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ ብያድርግም የደራሽ ውሃው ግፊት ከፍተኛ በመሆኑ አንድም ሰው በህይወት ማትረፍ አልተቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ለሟች ቤተሰቦቹ መፅናናትን እየተመኘ በቀጣይ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት መልዕክት ማስተላለፉን ከከተማ አስተዳደሩ መንግስት ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ቭላድሚር ፑቲን ጋዝ በሀገራቸው የመገበያያ ገንዘብ “ሩብል” እንዲሸጥ ወሰኑ!

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከዚህ በኋላ ጋዝ የምትሸጠው በራሷ የመገበያያ ገንዘብ “ሩብል” እንዲሆን መወሰናቸው አስታውቀዋል።ፕሬዝዳንቱ ወደ አውሮፓ የሚደረገው የጋዝ ሽያጭ በሩሲያ ገንዘብ እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፈዋል ነው የተባለው። የዚህ ውሳኔ ተግባራዊነትም በፍጥነት እንደሚከናወን ሞስኮ አስታውቃለች።

ሩሲያ ቱዴይ (አርቲ) የተባለው መገናኛ ብዙኃን እንደዘገበው ሞስኮ ከዚህ በኋላ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ጋር “በዩሮም ሆነ በዶላር የመገበያየት ስሜት የላትም” ብሏል።ቭላድሚር ፑቲን ዶላር የሚታመን የመገበያያ ገንዘብ እንዳልሆነ መናገራቸውን ሩሲያ ቱዴይ (አርቲ) ዘግቧል።የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ እና የካቢኔ አባላት ከአውሮፓ ጋር በሩብል የሚካሄደውን ግብይት በተመለከተ በአንድ ሳምንት ውስጥ ውሳኔ እንዲያስቀምጡ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብሏል።ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ምንም እንኳን የተለያዩ ሀገራት የሩሲያን ሀብት ቢያግዱም ሀገራቸው ግን በገባችው ውል መሰረት ነዳጅ ማቅረቧን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

Alain
@YeneTube @FikerAssefa
ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች ከአራት ሳምንታት በኋላ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ነገ አስቸኳይ ስብሰባ ሊቀመጥ ነው።

በዚሁ ስብሰባ ለመሳተፍ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የአውሮጳ ጉዟቸውን ጀምረዋል። የስብሰባቸው ዋነኛ ዓላማም የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ ጫና ማሳደር መሆኑን ከጉዟቸው ቀደም ሲል ዐስታውቀዋል።
«ከአጋሮቻችን እና ወዳጆቻችን ጋር የፑቲን የክሬምሊን ምጣኔ ሐብት ላይ ጫና ማሳደራችን እንቀጥላለን። በዓለም አቀፍ መድረክም እንዲገለል እናደርጋለን። ያ ነው ግባችን።»
ፕሬዚደንት ጆ ባይደን፦ ዩክሬናውያን ራሳቸውን እንዲከላከሉ የጦር መሣሪያ ድጋፍ ማድረጋችን ይቀጥላልም ብለዋል።

30 የኔቶ አባል ሃገራት ርእሰ-ብሔራን እና ጠቅላይ ሚንሥትሮች በሚሳተፉበት የነገው አስቸኳይ ስብሰባ የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በበይነ መረብ የቪዲዮ መልእክት ያስተላልፋሉ። ፕሬዚደንትቱ ዛሬ ለፈረንሳይ ምክር ቤት በኢንተርኔት ንግግር አሰምተዋል። ቀደም ሲል ጃፓን እና የእስያ ሃገራት ሩስያ ዩክሬንን በመውረሯ ማዕቀብ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ በኢንተርኔት ንግግር አሰምተዋል። በኔቶ የነገው አስቸኳይ ስብሰባ የአውሮጳ ኅብረት ምክር ቤት እና የቡድን 7 አባል ሃገራትም እንደሚካፈሉ ታውቋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
🖲ሴኩሪቲ ካሚራ ከነፃ ገጠማ ጋር...

📍በተጨማሪም በቻናላችን join በማለት እቃዎችን ማየት ይችላሉ👇👇

join :- @Dawitengineering

📍የፈለጉትን ይዘዙን እኛን ለማግኘት ከታች ባለው አድራሻ ያገኙናል።


ስልክ :- 0920757958
inbox :- @Dawit757985
https://tttttt.me/sabinaadvisor

የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week

👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ላይ ያካሄደውን አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥናት ሪፖርት ይፋ አደረገ፡፡

ኮሚሽኑ አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥናቱን ያካሄደው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በ2014 በጀት ዓመት 17 ሚሊዮን 809 ሺህ 388 የወባ መከላከያ አጎበር ግዥ ለመፈፀም በጨረታ ቁጥር Tender No: ICB/EPSA6/MOH-GF/LLINS/MS/23/21 አውጥቶት የነበረው የግዥ ጨረታ ህግን ተከትሎ የተፈፀመ አይደለም በሚል በቀረበ ጥቆማ መነሻነት ነው፡፡

አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥናቱ የተከናወነው በተቋማት በአካል በመገኘት ለጥናቱ የሚያስፈልጉ ሰነዶችና መረጃዎችን በማሰባሰብ እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ነው፡፡የጥናቱ ግኝት እንደሚያመለክተው በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ሰነድ ከገዙት 27 ተጫራቾች ውስጥ 8ቱ የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ያስገቡ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

በጨረታ ሂደቱ አሸናፊ ተደርጎ የተመረጠው "Fujian Yamei Industry and Trade Co. Ltd." የተባለው ድርጅት "DROGA, MAJIOR and ATMA" የተባሉ ሦስት ወኪሎች አሉት፡፡ ከነዚህ ውስጥ "DROGA" ለተባለው ወኪሉ የተሰጠው የምዝገባ ሰርተፊኬት ጋር በተያያዘ የኋላ ፋይሉ ሲታይ ህጋዊ አሠራርን ባልተከተለ መንገድ የወጣና በዚህ መሰረት ድርጅቱ እንደ ዋና ተጫራች ተደርጎ የተወሰደ መሆኑ ሲታይ የግዥ ሂደቱ የአሰራር ክፍተት የነበረበት ነው።"DROGA" የተባለው ወኪል የማጭበርበር ድርጊቱ ታውቆ በኢትዮጵያ መድኃኒትና ምግብ ባለስልጣን ከተሰረዘ በኋላ አሸናፊው ድርጅት "ATMA" በተባለው ሌላው ወኪሉ ጨረታውን እንዲሳተፍ መደረጉ የነፃ ገበያ ሂደትን የሚጎዳ መሆኑ፣ ግዥ እንዲፈፀምለት የጠየቀው የጤና ሚኒስቴር የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ከግብርና ሚኒስቴርና የዓለም የጤና ድርጅትን የብቃት ደረጃ ያሟላ ሆኖ እንዲወሰድለት ቢጠይቅም ከዚህ በተጨማሪ እንዲወሰድ መደረጉና የግብርና የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ እንደአማራጭ መታየቱ፣ ከፍቃድ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን መካከል የሀላፊነት ግልፅነት መጓደል መኖሩ በጥናት ግኝቱ ላይ ተመላክቷል፡፡

ከጥናቱ ግኝቱ በመነሳት ኮሚሽኑ የሚከተሉትን የውሳኔ ምክረ-ሀሳቦችን አቅርቧል፤

-በጨረታው አሸናፊ የተባለው ድርጅት ሶስት ወኪሎች አድርጎ በአንደኛ የተጭበረበረ የብቃት ሰርተፊኬት ማውጣቱ ሲታወቅ በጨረታው እንዳይወዳደር መደረግ የነበረበት መሆኑን፣

-አሸናፊ የተባለው ድርጅት “Droga” በተባለው የሀገር ውስጥ ወኪሉ አማካኝነት የተጭበረበረ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አውጥቶ የነበረ በመሆኑ በተመሳሳይ የግዥ ሂደቶች እንዳይሳተፍ ቢደረግ፤

-ጉዳዩ የሚመለከተው የኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የወባ አጎበር ለማቅረብ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አወሳሰድ ጋር ለተፈፀመው የማጭበርበር ድርጊት የበኩሉን የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ቢደረግ፣

-አንድ ተጫራች ከአንድ በላይ የሆነ ወኪል ይዞ በአንድ ጨረታ ለመሳተፍ ሲሞክር የነፃ የወድድር ሂደት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድርና ለብልሹ አሰራር ክፍተት ሊፈጥር የሚችል መሆኑን፣

-ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት በብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ግልፅ የሆነ አሰራር እንዲዘረጉና በታዩ የአሰራር ክፍተቶች ላይ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ቢደረግ፣

-በግዢ ሂደቱ ውስጥ የነበሩና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት በተጠቀሰው የግዥ ሂደት የታየውን የአሰራር ችግር እንዲፈቱ፣

ኮሚሽኑ ያካሄደውን አስቸኳይ የሙስና ጥናት ሪፖርት መነሻ በማድረግ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር፣ ለኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር፣ ለኢፌዲሪ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ለኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ሚኒስትሮች፣ ዋና ዳይሬክተሮችና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ባካሄደው የመውጫ ውይይት ስለጥናቱ ሂደትና ስለተገኙ ውጤቶች ግልፅነት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡

በአጠቃላይ ኮሚሽኑ ባደረገው የአስቸኳይ ጥናት መሰረት የወባ መከላከያ አጎበር ግዥው እና የብቃት ሰርተፊኬት አሰጣጥ ሂደቱ ግልፅነት የጎደለው እንደነበር ማየት የተቻለ ሲሆን የሂደቱን ጥራት የሚያጓድል ሆኖ በመገኘቱ በተሻሻለው የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ለማሻሻለው በወጣው አዋጅ ቁጥር 1236/2013 አንቀፅ 7 ንዑስ አንቀፅ 4 መሰረት ማሰተካከያ እንዲደረግ ምክረ-ሀሳብ ያቀረበ ሲሆን በጉዳዩ ላይም የቅርብ ክትትል እንደሚያደርግ ገልፆል፡፡ኮሚሽኑ ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር በሚቀርቡለት ጥቆማዎች መነሻ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጥናት ሪፖርትን በዚህ ሁኔታ ይፋ ማድረግ መደበኛ አሰራሩ መሆኑን እያስገነዘበ የተቋማት አመራሮች ለጥናቱ ሂደት ቀና ትብብር ምስጋና መቅረቡን ከፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙሰና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባዔው የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል ነው የተባለው።ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባዔ ምክር ቤቱ የስድሰተኛው አንደኛ መደበኛ ጉባዔን ቃለ ጉባዔ ያፀድቃል።

የበጀት ዓመቱን የስድስት ወር የመልካም አስተዳደርና የልማት እቅድ የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል።

ምክር ቤቱ በመልሶ ግንባታ ላይም ውይይት ካደረገ በኋላ የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም ተገልጿል።ጉባዔው የቋሚ ሰብሳቢዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅም ነው አሚኮ ያስነበበው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከባህር ዳር - ዳንግላ የኤሌክትሪክ አስተላለፊ መስመር ላይ የታወር ብረት ስርቆት የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች ተያዙ!

ከባህር ዳር - ዳንግላ በሚሄደው 66KV የኤሌክትሪክ አስተላለፊ መስመር ላይ የታወር ብረት ስርቆት የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች እየተያዙ መሆኑን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር 8ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የቴክኒክ ምርመራ ተወካይ ሳጅን ስጦታው ንጉሴ ገልፀዋል፡፡

ሳጅን ስጦታው እንደገለፁት ሁለት ተጠርጣሪዎች በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር አዲስ ኣለም ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ በአካባቢው አስተዳደርና የፀጥታ አካላት ቅንጅት መያዛቸውንና ያልተያዙ ተርጣሪዎችን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ  አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በቶጎ ሎሜ አስካይ አየር መንገድ  ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን እያገለገሉ ነበር።በዛሬው እለት አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል ።

ላለፉት 11 አመታት በዋና ስራ አስፈጻሚነት በአጠቃላይ በተለያዩ የስራ ክፍሎች ለ37 አመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያገለገሉት አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በትላንትናው እለት የስራ መልቀቂያ አስገብተው ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል።ትላንት አመሻሹን አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሬዚዳንት እና የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሹመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa