YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ትናንት እንደገና ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ሳተርፊልድ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከተመድ ከፍተኛ ሃላፊዎች እና ከዓለማቀፍ ረድዔት ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ይመክራሉ ተብሏል። ሳተርፊልድ ትናንት በአዲስ አበባ ከአፍሪካ ኅብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ እና ከኅብረቱ ባለሥልጣናት ጋር በኢትዮጵያ እና ሱዳን ዙሪያ ተነጋግረዋል ተብሏል።

በሌላ ዜና በአፍሪካ ቀንድ የቻይናው ልዩ መልዕክተኛ ዢ ቢንግ ቻይና ለአፍሪካ ቀንድ አገራት መሃንዲሶችን እና ሳይንቲስቶችን እንጅ ጦር መሳሪያ አትልክም ሲሉ ለኢስት አፍሪካን ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ቻይና ለአፍሪቃ ቀንድ ያመጣቻቸው ምክረ ሃሳቦች በጸጥታ፣ ልማት እና መልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ መሆናቸውን የጠቆሙት ቢንግ ቻይና በቀጠናው ፍላጎቷ የልማትና ብልጽግና እንጅ ጅኦፖለቲካ እንዳልሆነ ገልጠዋል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ሐዲድ እና የናይሮቢ-ሞምባሳ ባቡር ሐዲዶች ባንድ ላይ ሊገጥሙ ወይም የቻይናው "ቤልት ኤንድ ሮድ" መሠረተ ልማት እቅድ አካል ሊሆኑ እንደሚችሉ ዢ ቢንግ ተናግረዋል። በልማት መስክ የቀይ ባሕር ዳርቻን እና የምሥራቅ አፍሪካ አገራትን የውቂያኖስ ዳርቻዎች ማልማት የቻይና አንዱ ትኩሩት እንደሆነ ልዩ መልዕክተኛው አውስተዋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ሩሲያ በሀገሯ የሚገኙትን የአሜሪካ አምባሳደር አምባሳደር ለማብራሪያ ጠራች!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዙሪያ አስተያየት መስጠታውን ተከትሎ ሩሲያ በሀገሯ የሚገኙትን የአሜሪካ አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠርታለች።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደሩን ጠርቶ ያናገረው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሩሲያው አቻቸው ላይ በሰነዘሩት ያልተገባ አስተያየት ዙሪያ መሆኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን፤ ቭላድሚር ፑቲንን የቶር ወንጀለኛ ናቸው ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሩሲያ የባይደን አስተያየት “ተቀባይነት እንደሌለው” የሚያስረዳ ደብዳቤ ለአምባሳደሩ መስጠቷን አስታውቃለች።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦኬሎ ኝጌሎ በ58 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

አቶ ኦኬሎ ከ1989 እስከ 1995 ዓ.ም ሶስተኛው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ማገልገላቸው የሚታወስ ሲሆን÷ ባደረባቸው ህመም ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ኦኬሎ ባለትዳር እና የ 3 ወንድ እና የአንድ ሴት ልጆች አባት የነበሩ ሲሆን÷ የቀብር ስነ ስርአታቸው ዛሬ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት እየተፈፀመ ነው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትላንትናው እለት ከተከሰከሰው የቦይንግ አውሮፕላን እስካሁን በህይወት የተረፉ ሰዎች አልተገኙም ተባለ!

በትላንትናው እለት 132 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው የቦይንግ አውሮፕላን ከተከሰከሰ በኋላ እስካሁን በተደረገ የነፍስ አድን ስራ በህይወት የተገኘ ሰው አለመኖሩ ተዘገበ።የእንግሊዙ ኢንዲፔንደንት ጋዜጣ የቻይናን መንግስታዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ በተራራማ ስፍራ የደረሰው አደጋው የነፍስ አድን ስራውን አስቸጋሪ ቢያደርገውም እስካሁን በህይወት ያለ ሰው ማግኘት አልተቻለም ብሏል።

ቦይንግ 737-800 የተሰኘው አውሮፕላን ከ30 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ መከስከሱን የዘገበው ጋዜጣው፤ በቻይና ከረጅም ጊዜ በኋላ የተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ መሆኑን ገልጿል።የነፍስ አድን ባለሙያዎች ከሰዎች ህይወት ፍለጋ በተጨማሪ የአውሮፕላን መረጃዎችን የሚመዘግበው ‘ብላክ ቦክስ’ን እየፈለጉ ሲሆን የመረጃው መገኘት የአደጋውን መንሳኤ ለማጣራት ባለሙያዎችን እንደሚያግዝ ተስፋ ተደርጎበታል።

በአሁኑ ወቅት በቻይና በርካታ በረራዎች እየተሰረዙ ነው ያለው የኢንዲፔንደንት ዘገባ፤ የተከሰከሰው አውሮፕላን ባለቤት ቻይና ኢስተርን አየር መንገድ የቦይንግን ተመሳሳይ አውሮፕላኖች በሙሉ ከበረራ ውጪ ማድረጉን ገልጿል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ መስጠታቸውም ተሰምቷል።

Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
የማዕድን ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሚገኘውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ ኔዘርላንድስ ስዌል እና አሶሼት ኢንክ ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር በዛሬው እለት ተፈርሟል።ኩባንያው በሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ 3 ሺህ 500 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የተሰሩ የፍለጋ እና የጥናት ውጤቶችን መነሻ በማድረግ በአካባቢው ያለውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መጠን የማሳወቅና ኢኮኖሚያዊ ግምገማን የሚያሳይ ጥናት ያካሂዳል ተብሏል።

በስምምነት ስነስርአቱ ላይ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ትሬሲ አን ጃኮብሰን የኩባንያው ተወካዮች እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ከኢትዮጵያ ህዝብ 5 በመቶ የሚሆነዉ ሲጋራ ያጨሳል ተባለ

ኢትዮጵያ ካላት የህዝብ ቁጥር ውስጥ አምስት በመቶ የሚሆነው ትንባሆ እንደሚያጨስ የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ይህ ቁጥር ከሌሎች ሀገራት ቁጥር አንፃር አነስተኛ ቢመስልም በኢትዮጵያ ካለው የህዝብ ቁጥር ሰባ በመቶ የሚሆነው ወጣት በመሆኑ ለትንባሆ በቀላሉ ሊጋለጥ እንደሚችል የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

እንደ ሄራ ገርባ ማብራሪያ በህገወጥ መንገድ የሚገቡት የተለያየ ፍሌቨር ያለዉ ትንባሆ መቆጣጠር ካልተቻለ ጣዕሙ የተለየ በመሆኑ ጀማሪ አጫሾች በቀላሉ ሊያማልሉ እና ሊጋብዝ እንደሚችል ስጋታቸዉን አስቀምጠዋል፡፡ በዓለም አቀፋ ደረጃ ትንባሆ የተከለከለ ሳይሆን ቁጥጥር ሊደረግበት የሚችል በመሆኑ ኢትዮጵያ ቁጥጥሯን አጠናክራ ከቀጠለች ለውጥ ይመጣል ሲሉ አክለዋል፡፡

የቁጥጥር ስራውን ለመስራት ግን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት እና ስነምግባር በተላበሰ መልኩ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ከዛሬ ጀምሮ አዲስ አበባ ከተፈቀደ ቦታዎች ውጪ ከትንባሆ ነጻ ለማድረግ መመሪያ ተግባራዊ የማድረግ እና የመቆጣጠር ስራ መጀመሩ ተነግራል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@Yenetube @Fikerassefa
በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 42 ኪሎ ግራም ኮኬይን ተያዘ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሸቱ 2፡30 ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ በቁጥጥር ስር አዋሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን 200 ሺ ሜቲሪክ ቶን ስኳር ለመግዛት በቅርቡ ያወጣው አለም አቀፍ ጨረታ አለመሳካቱን ተከትሎ ለተመረጡ የውጭ አቅራቢዎች በቀጥታ ዋጋ እንዲያቀርቡ ጥሪ አደረገ፡፡

ቀደም ሲል ተከፍቶ የነበረው ጨረታ ሶስት ተጫራቾችን የሳበ ሲሆን አንደኛው ተጫራች በቴክኒካል መመዘኛ ማለፍ ባለመቻሉ ሁለቱ ድርጅቶች ማለትም ሱክደን እና ኢዲ ኤንድ ኤፍ ማን ወደ ፋይናንስ ምዘና አልፈው ነበር፡፡ሆኖም ኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ሰነዱን ሳይከፍት በመቆየቱ እና የዋጋ መቆያ ግዜ (price validation) በጨረታው ሰነድ ላይ ተቀምጦ ከነበረው 8 የስራ ቀናት በተጨማሪ ተጫራቾች 5 ቀናት እንዲጨምሩ ጠይቆ አንደኛው ተጫራች ሳይቀበለው ቀርቷል ሁለተኛውም ሰነዱ እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ብቻ በማራዘሙ ጨረታው ሊሳካ እንዳልቻለ ባለሞያዎች ይገልፃሉ፡፡

በመሆኑም ባሳለፍነው ሳምንት ኮርፖሬሽኑ ለተመረጡ ወደ ስድስት ለሚጠጉ አለም አቀፍ አቅራቢዎች ለመግዛት ለተፈለገው 200 ሺ ሜቲሪክ ቶን ስኳር ዋጋ እንዲያቀርቡ መጠየቁ ተሰምቷል፡፡በዚህም መሰረት ኩባንያዎቹ እስከዛሬ ከሰአት ድረስ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡በአለምአቀፍ ደረጃ የሚታየው የዋጋ በከፍተኛ መዋዠቅ እንደ ስኳር ያሉ የፍጆታ እቃዎችን ግዥ በፍጥነት ለማከናወን አዳጋች እንደሆነ ባለሞያዎች እየገለጹ ነው፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
The Right Time,
The Right Moves!
Join The Global Education Expo Today.
www.backtoschoolafrica.com

List of Exhibitors:

Schools & Colleges/Universities
School Management Solution Providers
Software developers
App developers & Coders
Start-ups & TECH Entrepreneurs
Education Consultants
STEM Education Incubators,
Digital Service Providers
Education Material Producers & Suppliers
Digital Libraries
NGOs & related.

To Reserve Your Booth:
Call us:
+251 974 0820 36
+251 974 0820 37
👍1
ኢሰመጉ ታጣቂዎች በኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና አማራ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጽሟቸውን ጥቃቶች የፌደራል እና ክልል መንግሥታት ባስቸኳይ ማስቆም እና የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት ማረጋገጥ እንዳለባቸው ዛሬ በድጋሚ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። ኢሰመጉ በደቡብ ክልል በተለይ በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በርካታ ሰዎች ከሕግ ውጭ በእስር ላይ እንደሚገኙ እና በአማሮ ወረዳ እና ኮንሶ ዞኖች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆኑን በመጥቀስ፣ መንግሥት ለመብት ጥሰቶቹ መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቋል። ኢሰመጉ የሰሜኑ ግጭት ተፈናቃዮች በቂ ሰብዓዊ ዕርዳታ እያገኙ እንዳልሆነ በመጥቀስ፣ መንግሥት ያለ አድልዖ ለተፈናቃዮች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲያቀርብ እና መንግሥት በቂ ዕርዳታ የማቅረብ አቅም ከሌለው ደሞ ዓለማቀፍ ረድኤት ድርጅቶች ዕርዳታ የሚያቀርቡበትን ሁኔታ እንዲያመቻች አሳስቧል።

በተያያዘ ዜና መንግሥት በርካታ ተፈታኞች እና ወላጆች ቅሬታ እያነሱበት ያለውን የ2013 ዓ፣ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት እንደገና መርምሮ ለተማሪዎች አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። የተለያዩ አካላት በፈተናው ውጤት ዙሪያ የሚሰጧቸው ሃሳቦች ሕዝቡን ግራ እያጋቡ እና የተማሪዎችን ስነ ልቦና እየጎዱ መሆኑን ኢሰመጉ በመግለጫው አውስቷል። በመሆኑም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት በችግሩ ዙሪያ ግልጽ ማብራሪያ መስጠት እና ባስቸኳይ የእርምት ርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ኢሰመጉ ጨምሮ አሳስቧል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢዜማ “ለውጡ በጠበቅነው ልክ አልሄደም”ሲል መንግስትን ተቸ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት 2010 ዓ.ም በኋላ በኢትዮጵያ መጣ የተባው ፖለቲካዊ “ለውጥ” በተጠበቀው መልኩ እየቀጠለ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (አዜማ) ገለጸ።የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ “ለውጡ” በብዙ ኃይሎች ጥረት ዕውን ቢሆንም በተጠበቀው ልክ እየሄደ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ከዐልዐይን ያደረጉት ሙሉ ቆይታ:

https://am.al-ain.com/article/ezema-says-the-change-the-government-embarked-on-fails-to-keep-going-in-tempo-as-expected

@YeneTube @FikerAssefa
በካፋ ዞን የ12ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ከተቀበሉ 57 ትምህርት ቤቶች ዉስጥ የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ ከ21 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ብቻ መሆናቸው ቅሬታ አስነሳ፡፡

በደቡብ ምዕራብ ክልል በከፋ ዞን 57 ትምህርት ቤቶች ፈተናዉን የወሰዱ ቢሆንም የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ከ21 ትምህርት ቤቶች ብቻ የተወጣጡ በመሆናቸዉ ዞኑ የፈተና ውጤቱ በድጋሚ ይታይልኝ የሚል ጥያቄ ማንሳቱን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታወቋል፡፡ በማህበራዊ ሳይንስ እና በተፈጥሮ ሳይንስ በአጠቃላይ ከከፋ ዞን 4ሺህ 579 ተማሪዎች የ12ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መውሰዳቸውን የከፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፍቅረእየሱስ ሀብተጊዮርጊስ ለአሀዱ ገልጸዋል፡፡

ዞኑ ካስፈተናቸው ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ እና ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ በአጠቃላይ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች 7 መቶ 38 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውንም አክለዋል፡፡የከፋ ዞን አምና በነበረው አፈጻጸም 621 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት የተመዘገበበት ዞን መሆኑን እና ከአንድ ትምህርት ቤት በአማካኝ እስከ 88 በመቶ የሚያልፍበት እንደሆነ አስታዉሰዋል፡፡

የዘንድሮው አጠቃላይ ዉጤት ታይቶ የማይታወቅ በመሆኑ ዞኑ ያነሳውን የተማሪዎች የፈተና ውጤት በድጋሚ ይታይልኝ ጥያቄ የትምህርት ሚኒስቴር በአጽኖት እንዲመለከተው ጠይቀዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሳምንታት የቀሩት አለም አቀፍ የትምህርት ኤክስፖ
በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ
ላይ ይካሄዳል።

ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?

ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ

👉 ትምህርት ቤቶች
👉 ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች
👉 የሶፍትዌር ገንቢዎች
👉 ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች
👉 ት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣
👉 አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች
👉 ኢንኩቤተሮች
👉 የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች
👉 የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች
👉 ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና
👉 ተያያዥነት ያላቸው።

ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ👇!
www.backtoschoolafrica.com

☎️ : +251 974 08 2036
+251 974 08 2037
🖲ሴኩሪቲ ካሚራ ከነፃ ገጠማ ጋር...

📍በተጨማሪም በቻናላችን join በማለት እቃዎችን ማየት ይችላሉ👇👇

join :- @Dawitengineering

📍የፈለጉትን ይዘዙን እኛን ለማግኘት ከታች ባለው አድራሻ ያገኙናል።


ስልክ :- 0920757958
inbox :- @Dawit757985
https://tttttt.me/sabinaadvisor

የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week

👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
በ18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአንደኛነት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገባ!

በ18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአንደኛነት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርሩ ቱሉን ጨምሮ በርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከመጋቢት 9 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ በነበረው በ18ኛው የቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ከዓለም አንደኛ ሆና ማጠናቀቋ ይታወሳል።በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ አራት ወርቅ፣ ሶስት ብር፣ ሁለት ነሐስ በድምሩ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን በማግኘት አንደኛ በመሆን በበላይነት ጨርሳለች።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa