YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢዜማ መንግሥት በአድዋ ድል አከባበር ጋር በተያያዘ ያሠራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንዲፈታ በድረገጹ ባወጣው መግለጫ ገልጧል። በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦች ካሉ የፍርድ ሂደታቸው በነጻና ገለልተኛ አግባብ እንዲታይ ፓርቲው ጠይቋል። መንግሥት ስለ በዓሉ ባወጣቸው የተለያዩ መግለጫዎችን የጠብ አጫሪነት አዝማሚያ በማሳየቱ የተቃውሞ ድምጾች እንደተሰሙ ኢዜማ አስታውሷል። ኢዜማ ጨምሮም፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ አባላትን ከክልሎች እመለምላለሁ ማለቱን በመቃወም የፖሊስ ምልመላ ከከተማው ነዋሪ መካከል መሆን አለበት ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ አገራት በዩክሬኑ ጦርነት ገለልተኛ መሆን የለባቸውም ስትል ወቀሰች፡፡

በመንግስታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪን ፊልድ የአፍሪካ አገራት በጦርነቱ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያሳዩ ለመጠቆም ሞክረዋል፡፡ቀደም ሲል በነበረው በሩሲያ ላይ ጫና የመፍጠር ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ወቅት አፍሪካውያን ችላ ማለታቸውን በዋቢነት አምባሳደሯ አንስተዋል፡፡

አስራ ሰባት አገራት ድምጸ ተአቅቦ ፤ስምንት አገራት ከናካቴው ድምጽ ያልሰጡበት አጋጣሚም ተጠቃሽ ነው፡፡በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት በምዕራባውያን እና በሩሲያ መካከል የተፈጠረ የቀዝቃዛው ጦርነት እሰጥ አገባ አልያም ውድድር አይደለም ብለዋል፡፡

ዝም የሚያስብል ጉዳይ የለም ይላሉ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪን ፊልድ፡፡ዩናይትድ ስቴትስ ከሩሲያ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት አማራጭ ምንጭ እየተጠቀምኩ ነው ባይ ናት፡በተጨማሪም ዋሽንግተን በዩክሬኑ እና በሩሲያው ጦርነት ደቡብ አፍሪካ ለማሸማገል ያቀረበችውን ጥያቄ እንደምትደግፍ አሳውቃለች ፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
በአንድ የዲሽ ሳህን እስከ 64 ቤቶችን እንሰራለን

ለአፓርትመንቶች
ለሪልስቴቶች
ለሆቴሎች
ለገስት ሀውስ
ለኮዶሚንየሞች

📍በተጨማሪም በቻናላችን join በማለት እቃዎችን ማየት ይችላሉ👇👇

join :- @Dawitengineering

📍የፈለጉትን ይዘዙን እኛን ለማግኘት ከታች ባለው አድራሻ ያገኙናል።


ስልክ :- 0920757958
inbox :- @Dawit757985
በሰሜን ወሎ ዞን በስድስት ትምህርት ቤት የተፈተኑ ሁሉም ተማሪዎች የዪኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አለማምጣታቸውን ተገለጸ

በሰሜን ወሎ ዞን ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ካስፈተኑ 42 ትምህርት ቤቶች መካከል በስድስት ትምህርት ቤቶች የተፈተኑ ሁሉም ተማሪዎች ለዪኒቨርሲቲ መግቢያ የሚያበቃቸዉን ውጤት እንዳላመጡ የዞኑ ኮሙኒኬሽን አስታወቀ።ጦርነቱ በሰሜን ወሎ ዞን የመማር ማስተማር ሂደት ላይ በፈጠረው ችግር ተማሪዎች ትምህርታቸውን በምቹ ሁኔታና መማር የሚገባቸውን ትምህርት ባለመማራቸው በዪኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ መፍጠሩን የዞኑ መምሪያ ገልጿል።

የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ባለሙያ ወይዘሮ ሙሉ አዳነ በዞኑ በ42 ትምህርት ቤቶች ከተፈተኑት 9 ሺህ 710 ተማሪዎች መካከል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡት 37 በመቶ ማለትም 3 ሺህ 657 ብቻ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ከ42ቱ ትምህርት ቤቶች ውስጥም በስድስቱ ማለትም ጊራና፣ ቃሊም፣ ኩልመስክ፣ ጉርጉራ፣ ክበበው እና ሀና መኳት በተባሉ ትምህርት ቤቶች የተፈተኑ 679 ተማሪዎች የዮኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ሁሉም ውጤት አለማምጣታቸዉ ታዉቋል፡፡

“የትምህርት ሚኒስቴር በወራሪውና ዘራፊው የትግራይ ቡድን ዋጋ እየከፈሉ ያሉ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ ሊያይ ይገባል፡፡” ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጠይቋል።ከሰሞኑ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዉጤት ይፋ መደረጉን ተከትሎ ጦርነት በነበረባቸዉ አካባቢዎች የነበሩ ተማሪዎች ዝቅተኛ ዉጤት ማምጣታቸው እየተገለጸ ይገኛል። በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያዎች እነዚህ ተማሪዎች በተለየ ሁኔታ እንዲታዩ ሲጠይቁ ቆይተዋል።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በባሌ ዞን 13 ህጻናትን እያንዳንዳቸውን በሶስት ሺህ ብር ለመሸጥ ሲሞክሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በባሌ ዞን ሲናና ወረዳ 13 ህጻናትን ለጉልበት ብዝበዛ በሚል በ ሶስት ሺህ ብር ለመሸጥ ሲሞክሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዉለዋል።የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት ኮማንደር ናስር ዑመር በተለይ ለብስራት ራዲዮ እንደገለፁት ተጠርጣሪዎቹ ህጻናቱን ከምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ ወረዳ በማምጣት ባሌ ዞን ሲናና ወረዳ ላይ ለመሸጥ ሲሞክሩ እንደተያዙ ተናግረዋል።በማከልም በአንድ ህጻን ላይ በተፈጠረ የዋጋ አለመግባባት ምክኒያት ህብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ ተጠርጣሪዎቹ ሊያዙ መቻላቸዉን ጨምረዉ ተናግረዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ከባህርዳር-ዳንግላ በሚሄድ 66 ኪሎ ቮልት አስተላለፊ መስመር በተፈጸመ ስርቆት የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋረጠ!

በታወር ብረት ላይ በተፈፀመ ስርቆት ምክንያት ዳንግላ፣ ዱርቤቴ፣ መራዊ ፣ ኮሶበር፣ ግምጃ ቤት፣ ቻግኒ እና በአካባቢያቸው ባሉ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተገለጸ፡፡ከባህር ዳር እስከ ዳንግላ በሚሄድ 66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ አስተላለፊ መስመር የብረት ታወር ላይ በተለምዶ ቆጥቆጥማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተፈፀመ ስርቆት ምሰሶዎች በመውደቃቸው ከዳንግላ እና ፓዊ ማከፋፈያ ጣቢያ ኤሌክትሪክ የሚያገኙ ከተሞች ኃይል ተቋርጦባቸዋል፡፡

በተፈፀመው ስርቆት ምክንያት አራት የብረት ታወሮች የወደቁ ሲሆን÷ የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የእንጨት ምሰሶዎችን በመቀየር አገልግሎቱን ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ ያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡በብረት ታወሮች እና በአጠቃላይ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ስርቆት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባበሰ የመጣ በመሆኑ÷ በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ከፍተኛ ተግዳሮት ፈጥሮብናል ብሏል አገልግሎቱ፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡና በየደረጃው የሚገኝ የፀጥታ አካል በአካባቢው የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በንቃት እንዲጠብቅና ከዚሁ ጋር በተያያዘ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት ለሚመለከተው የፀጥታ አካልና ለተቋሙ እንዲጠቁም አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
“በተማሪዎች ውጤት እና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበናል” የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶ መረጃ መረጃ አጋርቷል።የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለቱም ዙር በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጥ የሚፈለግብንን ሁሉ አድርገናል ብሏል።

የአንደኛው ዙር ፈተና እንደተጠናቀቀ ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በወቅቱ ፈተና ተሰርቋል እየተባለ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ በነበረው የተለያየ መረጃ ምክንያት የፈተና ውጤት ትንተናው በጥንቃቄ እንዲታይ በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረቡን ገልጿል።

ውጤት ከተገለፀ በኋላም የቀረቡ ቅሬታዎችን መሠረት በማድረግ ፈተናቸው ድጋሜ እንዲታይላቸው የጠየቁ ተማሪዎችን ውጤታቸው እንዲፈተሽላቸው ሁኔታዎችን ከማመቻቸት በተጨማሪ አጠቃላይ በውጤቱ እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበናል ነው ያለው ቢሮው።

ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ዛሬ ገልጾልናል ነው ያለው ቢሮው።በሚኒስቴሩ በኩል አስፈላጊው ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ በትምህርት ቢሮው በኩል የሚፈለጉ መረጃዎች ካሉ ከሕዝቡ የሚደብቀው መረጃ እንደማይኖር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።የተማሪዎች ውጤት ለዞኖች፣ ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች በግልፅ የተላለፈ ስለኾነ ለመሸፋፈን የሚፈልግ አካልም የለም፤ መሸፋፈንም አይቻልም ብሏል ትምህርት ቢሮ።

@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል የማዛወር ሂደት እንዲራዘም መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ባካሄደው የአገር ውስጥ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዛወር የሚያስችል ማዕቀፎችን ማውጣቱ የሚታወስ ነው።ይህም የግሉ ዘርፍ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ሚና ለማስፋት፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማነት ለማሻሻል፣ ተወዳዳሪነታቸውን ለማጎልበት፣ የካፒታል ተደራሽነታቸውን ለማሳደግ እና የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ተገልጿል።

በዚህ ፕሮግራም መሰረት የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ በመሸጥ ከፊል ወደ ግል ለማዛወር ሀሳብ አቅርቧል።ባሳለፍነው ዓመት መስከረም ወር ላይም የኢትዮጵያ መንግስት በኦፕሬሽን፣ በመሰረተ ልማት አስተዳደር እና በቀጣይ ትውልድ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በማምጣት ለኩባንያው እሴት ሊጨምሩ የሚችሉ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮችን ለመጋበዝ የፕሮፖዛል ጥያቄ አቅርቧል። በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ ተጫራቾች ጋር ውይይት ማድረጉ ይታወሳል።

ቢሆንም ግን የገንዘብ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በአገር ደረጃ እየታዩ ያሉትን ፈጣን የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጦችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቋሙን በከፊል ወደ ግል የማዛወር ሂደቱን ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ መወሰኑን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤቱ የደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማርዎችን አግተዋል ተብለው የተከሰሱ 3 ተከሳሾችን በነጻ እንዲሰናበቱ ብይን ሰጠ!

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ ሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በአማራ ክልል የደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማርዎችን አግተዋል ተብለው የተከሰሱ 3 ተከሳሾችን በነጻ እንዲሰናበቱ ብይን ሰጠ።ቀሪዎቹ 1ኛ ተከሳሽ ከሊፋ አብዱራሀማን እና ዮሴፍ ጃረታን ጨምሮ 5 ተከሳሾች ደግሞ በተከሰሱበት የወንጀል ህግ አንቀጽ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቷል።

ከሳሽ ዓቃቢህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ ተከሳሾቹ የኦነግ ሸኔ የፖለቲካ ርዕዮተ አለም አላማን ለማራመድ፣ ህብረተሰቡን ለማሸበርና መንግስትን ለማስገደድ በማሰብ የደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ለማገት ከኦነግ ሸኔ አመራሮችና ከአባላት ጋር ከህዳር 22 ቀን 2012 ጀምሮ ሥምምነት መፈጸማቸው አመላክቷል።ረሱቅ አብደላ የተባለው 16ኛ ተከሳሽ በሚያሽከረክረውና ሀምዲ አረብሴ በረዳትነት በሚሰራበት ኮድ 3 ታርጋ ቁ._34629 ኦሮ በቀይ ዶልፊን መኪና፤ የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑት ተማሪ ሞንሙን በላይ፣ ተማሪ ጤናለም ሙላቴ፣ ተማሪ ሳምራዊት ቀሬ፣ ተማሪ አስቤ አያሌው እና የአካባቢው ኗሪ የሆነችው ተማሪ ትግስት መሳይን እንዲሁም በውል ያልተለዩ ሌሎች ሴቶችንም በደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተከስቶ የነበረውን የተማሪዎች ግጭት በመፍራት በህዳር 24 ቀን 2012 በመኪና ተሳፍረው እንደነበር ዓቃቢህግ በክሱ ዘርዝሯል።

ተማሪዎቹ የተሳፈሩበትን መኪና 1ኛ ተከሳሽ ከሊፋ አብዱራሀማን፣ አብዲ ኢብራሂም፣ ናስር መሀመድ፣ ዮሴፍ ጀረታ፣ አወሉ ጅብሪል፣ ነብዩ ባቤሰር፣ ጋዲሳ ገለቱ የተባሉ ተከሳሾች ካልተያዙ ከሌሎች ግብረአበሮቻቸው ጋር በመሆን ዱላና የጦር መሳሪያ በመያዝ መኪናውን በማስቆም አማረኛ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎችን ብቻ በመለየት ከመኪናው አስወርደው በመውሰድ በጫካ ውስጥ ማገታቸውን ዓቃቢህግ በክሱ ገልጿል።

የመኪናው ሹፌርና ረዳትም ጉዳዩን ለጸጥታ አካል ሳያሳውቁ መቅረታቸውን በክሱ አመላክቶ ነበር።ተከሳሾቹንም በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በሐምሌ 10 ቀን 2012 በ1996 የወጣውን ወንጀል ህግ አንቀጽ 32 1ሀ እና አንቀጽ 35:38 እንዲሁም የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3/3 ድንጋጌን በመተላለፍ ክስ ቀርቦባቸዋል።

ተከሳሾቹ ወንጀሉን አለመፈጸማቸውን የዕምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ፤ ዓቃቢህግ ወንጀሉ መፈጸማቸውን ያስረዳልኛል ያለውን የሰነድና የሰው ምስክር አቅርቦ ማሰማቱ ይታወሳል።ፍርድ ቤቱም ዓቃቢህግ ያቀረበውን የሰነድና የሰው ምስክሮችን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ በሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት
ችሎቱ ተሰይሟል።

ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ማስረጃ መርምሮ በተከሰሱበት አንቀጽ 1ኛ ከሊፋ አብዱረሀማን፣ ዮሴፍ ጃረታ፣ ጋዲሳ ገለቱ፣ ነብዩ በባከር እና ናስር መሀመድ የተባሉ 5ተ ከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ሰቷል።ሌሎች ሦስት ማለትም ጌታቸው ዮናስ፣ አብደሳ ፋፋ እና ተፈሪ ኒካ የተባሉ ተከሳሾችን ደግሞ በተከሰሱበት ክስ ወንጀሉን ስለመፈጸማቸው በበቂ ማስረጃ አልቀረበባቸውም ሲል ፍርድ ቤቱ በነጻ ማሰናበቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው የአምስት ተከሳሾችን የመከላከያ ማስረጃ ውጤት ለመጠባበቅ ለሚያዚያ 3 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
The Right Time,
The Right Moves!
Join The Global Education Expo Today.
www.backtoschoolafrica.com

List of Exhibitors:

Schools & Colleges/Universities
School Management Solution Providers
Software developers
App developers & Coders
Start-ups & TECH Entrepreneurs
Education Consultants
STEM Education Incubators,
Digital Service Providers
Education Material Producers & Suppliers
Digital Libraries
NGOs & related.

To Reserve Your Booth:
Call us:
+251 974 0820 36
+251 974 0820 37
በኢትዮጵያ ካሉ የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች 65 በመቶ ማንበብ እንደማይችሉ፤ የሚያስተምሩትን ትምህርት ከተፈተኑ መምህራን 85 በመቶ የሚሆኑት ብቁ አለመሆናቸው ተገለጸ።

ለትምህርት ስርዓቱ ውድቀትና ማነቆ ናቸው በተባሉ ተግዳሮች ላይ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጅማ ዩኒቨርሲቲ መክረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታዉ ዶክተር ፋንታ በላይ ዛሬ የጅማ ዩኒቨርሲቲን በጎበኙበት ወቅት የትምህርት ስርዓቱ በኢትዮጵያ ያለበትን ደረጃ በግልፅ አስቀምጠዋል።

የትምህርት ስርዓቱን ከውድቀት ለመታደግና ሀገር ከሚገጥማት ተግዳሮት ሊታደግ የሚችል ትውልድ ለመፍጠር ችግሮች ላይ ግልፅ ውይይት ማድረግና ለመፍትሄ ማስቀመጥ ወሳኝ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ካሉ የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች 65 በመቶ ማንበብ እንደማይችሉ፣ የሚያስተምሩትን ትምህርት ከተፈተኑ መምህራን 85 በመቶ የሚሆኑት ብቁ አለመሆናቸው ፣ ላለፋት ሰባት ዓመታት በየጊዜው የሀገር አቀፍ ፈተና መሰረቁም በመረጃ የተደገፈ ድክመት ሲሆን ፥ በተጨማሪ ትምህርት ቤቶችም 99 በመቶ አስፈላጊውን መስፈርት እንደማያሟሉ ተጠቁሟል ።

ለስርዓቱ ድቀት መነሻና ማነቆዎች የትምህርት ስርዓቱን ከፖለቲካው ጋር በመለየት ዩኒቨርሲቲዎች ከክልላዊና ብሄር ተኮር እሳቤ በማላቀቅ ተማሪን ማብቃት ግባቸው ሊሆን እንደሚገባ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን የኤፍቢሲ ዘገባ ያሳያል።

ዩኒቨርሲቲዎችም የሚያከናውኑት የህንፃ ግንባታ ተማሪን ከማብቃት ግብ ጋር ሲነፃፀር የላቀ በመሆኑ የሚያስተቻቸው ስለመሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ፥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተጣረሰ አሰራር መውጣትና ከፖለቲካ መነጠል የትምህርት ስርዓቱን ከውድቀት ይታደገዋል ተብሏል።በቀጣይም ምክክሩ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እንደሚቀጥል ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መተሐራ "አልጌ" አካባቢ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ!

በመተሐራ "አልጌ" ተብላ በምትጠራ አካባቢ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት የ10 ሰላማዊ ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።‹‹አልጌ›› የተባለችው የመኖርያ መንደር በምትገኝበት ቀበሌ ስር ባሉ ሦስት ቀጠናዎች በተመሳሳይ ሰዓት በደረሰው ጥቃት የ8 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ አንድ ሰው ከቆይታ በኋላ ህይወቱ አልፏል።ሌላ ተጨማሪ አንድ ሰውም ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ህይወቱ ማለፉ ተነግሯል።በጥቃቱ ከሞት የተረፉ 6 ግለሰቦችም ወደ አዳማ ጀነራል ሆስፒታል ተልከው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ከታካሚዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሆስፒታሉ በህክምና ላይ ከሚገኙ ተጠቂዎች መካከልም ህይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ ያለ ይገኙበታል ተብሏል።ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት 2 ሰዓት ላይ እንደሆነ የዓይን እማኞች ለአዲስ ዘይቤ አሳውቀዋል።በጥቃቱ ሰዓት ወዲያው ህይወታቸው ያለፈው 8 ሰዎች የቀብር ስነስርዓት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አልጌ በሚገኝ መስጊድ እና ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር የሚያስችል ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ።

ድርቁ በክልሉ ከአንድ ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቋረጥ አስገድዷል።  በሶማሌ ክልል ድርቅ ጉዳት ባስከተለባቸው አካባቢዎች ለሚኖረው ማኅበረሰብ የምግብ ፣ የውሀ እና ሌሎች ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑንም የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። በዚህ መሀልም በክልሉ የተለያዩ ዞኖችን ለችግር ለዳረገው ድርቅ በቅርቡ የሚጠበቀው የበልግ ዝናብ መፍትሄ ያመጣል በሚል ተስፋ ተደርጓል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈጸመውን ሰውን አቃጥሎ የመግደል ድርጊት የሚመረምር ቡድን ወደ አካባቢው ተሰማራ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈጸመውን ሰውን አቃጥሎ የመግደል ድርጊት የሚመረምር የወንጀል ምርመራ ቡድን ድርጊቱ ወደተፈጸመበት መተከል ዞን አቀና። ከፍትህ ሚኒስቴር እና ፌደራል ፖሊስ በተውጣጡ መርማሪዎች የተዋቀረው የምርመራ ቡድን ወደ መተከል ዞን የተጓዘው ከትላንት በስቲያ ረቡዕ መጋቢት 7፤ 2014 ነው።አምስት አባላት ባሉት በዚህ የምርመራ ቡድን ውስጥ ከፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሶስት ባለሙያዎች መካተታቸውን የሚኒስቴሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ አወል ሱልጣን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ቀሪ ሁለቱ አባላት ደግሞ ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የተወከሉ ናቸው።የወንጀል ምርመራው በሁለቱ የፌደራል ተቋማት የሚከናወን መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የገለጹት የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ፤ የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት የአጋዥነት ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል።“የኮማንድ ፖስቱ ስራ የአካባቢውን ጸጥታ ማስጠበቅ እና ተጠርጣሪዎች መያዝ ነው” ሲሉም ምክትል ኃላፊው የኮማንድ ፖስቱን ኃላፊነት አብራርተዋል።

ከመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ትላንት ሐሙስ መጋቢት 8፤ 2014 ውይይት ያደረገው የምርመራ ቡድኑ፤ “ያለውን ነገር አቅዶ ወደ ምርመራ ለመግባት” ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አቶ ሙሊሳ ተናግረዋል።“ምርመራውን ለመጀመር የሚያስችል በቂ ኃይል አለን። ትንሽ የሚያስቸግረን በአካባቢው ያለው የጸጥታ ችግር ነው። [ጸጥታው] አስተማማኝ አይደለም” ሲሉም በመተከል ዞን የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ለምርመራ ቡድኑ ስራ እንቅፋት ሊፈጥር እንደሚችል ጠቁመዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሳምንታት የቀሩት አለም አቀፍ የትምህርት ኤክስፖ
በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ
ላይ ይካሄዳል።

ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?

ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ

👉 ትምህርት ቤቶች
👉 ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች
👉 የሶፍትዌር ገንቢዎች
👉 ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች
👉 ት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣
👉 አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች
👉 ኢንኩቤተሮች
👉 የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች
👉 የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች
👉 ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና
👉 ተያያዥነት ያላቸው።

ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ👇!
www.backtoschoolafrica.com

☎️ : +251 974 08 2036
+251 974 08 2037
🎈ለልጆችዋ ደህንነት እና ለቢሮ ለሱቅ...

↪️እንዲሁም ለእርስዎ ደህንነት መጠበቂያ ካሜራ ቻርጀር የሚመስሉ እና ሰአት የሚመስሉ ድብቅ ካሜራዎች አሉን።

↪️እንዲሁም ለ24ሰዓት መብራት ባይኖር ድምፅ እና ምስል ይቀርፃሉ።

📍በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርበናል ይደውሉ...

📍በተጨማሪም በቻናላችን join በማለት እቃዎችን ማየት ይችላሉ👇👇

join :- @Dawitengineering

📍የፈለጉትን ይዘዙን እኛን ለማግኘት ከታች ባለው አድራሻ ያገኙናል።

ስልክ :- 0920757958
inbox :- @Dawit757985
መንግሥት 8 የቀድሞ የትግራይ ክልል ባለሥልጣናትን እንዳሰረ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዳንዔል በቀለን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል። ከታሰሩት መካከል የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሃላፊዎች እንደሚገኙበት ዘገባው ገልጧል። ጉዳዩን የሚከታተሉ ሌሎች ጠበቆች እና ምንጮች ደሞ 12 የክልሉ የቀድሞ ኃላፊዎች፣ አንድ የመብት ተሟጋች እና አንድ ሌላ ሰው እንደታሰሩ እና በጊዜያዊው አስተዳደሩ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት እበራ ንጉስ፣ የአንድ ዞን አስተዳደሪ እና የትግራይ ቴሌቪዥን ምክትል ዳይሬክተር እንደሚገኙበት ተናግረዋል። ኮሚሽነር ዳንኤል አንዳንዶቹ እስረኞች ወደ አፋር ክልል ተወስደዋል ማለታቸውን እና የእስሩን ምክንያት ግን እንዳልጠቀሱ ዘገባው አመልክቷል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባዔያቸውን ለማካሄድ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አስታወቁ!

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱን ተከትሎ እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ጉባኤ እንዲያካሂድ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ (ኦፌኮ)፣ ኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፣ እና ኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ (ኦነን) በቅርቡ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።

ትግራይ ዴሞክራቲ ፓርቲ (ትዴፓ) ጉባኤውን ማካሄድ እንደማይችል ገልጿል፡፡

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጡሩና ገምታ ድርጅታቸው ኦፌኮ መጋቢት 17 እና 18 ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚያካሂድ ገልጸዋል።አቶ ጡሩና እንዳሉትም ጉባዔው የፓርቲውን የውስጥ ጉዳዮች ተወያይቶ አቅጣጫ ያስቀምጣል።እንደ ፖለቲካ ፓርቲ በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa