YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተለያዩ ለሴት እና ለወንድ እንዲሁም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን የሚያገኙበት ድረ-ገጽ 👇
shein.com SHEIN.COM shein.com

ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን (SHEIN.COM)

Contact @kiru04
☎️ 0931607806

Join 👇👇👇
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሳምንታት የቀሩት አለም አቀፍ የትምህርት ኤክስፖ
በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ
ላይ ይካሄዳል።

ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?

ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ

👉 ትምህርት ቤቶች
👉 ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች
👉 የሶፍትዌር ገንቢዎች
👉 ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች
👉 ት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣
👉 አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች
👉 ኢንኩቤተሮች
👉 የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች
👉 የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች
👉 ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና
👉 ተያያዥነት ያላቸው።

ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ👇!
www.backtoschoolafrica.com

☎️ : +251 974 08 2036
+251 974 08 2037
ማስታወቂያ!

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ባስመዘገባችሁት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችል ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳችሁ ይታወቃል።

ሆኖም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንድታደርጉ ሲል አሳስቧል።

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለፀ ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰበ በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ የተቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ወደ ሪያድ ሊጓዝ እንደሆነ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ብሄራዊ ኮሚቴው ዜጎችን ለመመለስ የመጨረሻው ጫፍ ላይ መድረሱን እና ባሁኑ ወቅት ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ፍልሰተኞችን የመመዝገብ እና የማጣራት ሥራ እየሠሩ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል። ኮሚቴው ፍልሰተኞቹን ለመመለስ እና መልሶ ለማቋቋም የሚያስችለውን የትግበራ መርሃ ግብር ቀደም ሲል ማዘጋጀቱ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
እናት ፓርቲ ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል የገቡትን ጨምሮ የመዋቅራዊ ጥቃት ሰለባ ሆነዋል ያላቸው ተፈናቃዮችን ህዝቡ እንዲታደጋቸው ጥሪ አቀረበ!

ፓርቲው መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ” የመዋቅራዊ ጥቃትና ጦርነቱ ሰላባ የሆኑ” ያላቸው ”ተፈናቃይ ወገኖች ህዝቡ በአፋጣኝ ይድረስላቸው”ሲል ጠይቋል፡፡ፓርቲው”በሀገራችን ሞትን እየተለማመድን፣ የሞተው ሰው ቁጥርና የአሟሟቱ የዘግናኝነት መጠን ያነጋግር ካልሆነ እንጂ የጅምላ ፍጅትና ዕልቂት የሚስገርም አልሆነም፡፡” ሲል ወቅሷል፡፡

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የተከሰቱትን ዘግናኝ ወንጀሎችን በመግለጫው ያስታወሰው ፓርቲው ድርጊቶቹ”ዝም በመባላቸው ዛሬ ሰው ከነህይወቱ እያገላበጥን መጥበስ ላይ ተደርሷል” ሲል ኮንኗል፡፡ አክሎም ”ይህም ዝም ስለሚባል ነገ ምን እንደሚደረግ መገመት አያዳግትም፡፡” ብሏል፡፡

ፓርቲው በመግለጫው”በቅርቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ መድረሻ ያጡ ምስኪን ኢትዮጵዊን አንገት ማስገቢያ ጎጆ አጥተው እንደ ኳስ ከቦታ ቦታ ሲላጉ እያየን ሃይ ባይ ስላጣን መቶሺዎች በመዋቅራዊ ጥቃት ሰበብ አማራ ክልል፣ ፍኖተ ሰላም አካባቢውን አጥልቅቀዋል፡፡” ሲል አመለክቷል፡፡

እናት ፓርቲ ” ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ሁኔታ” በህወሓት በፓርቲው አገላለፅ ትህነግ፣ አማካይነት ወደምድራዊ ሲዖል በመቀየሩ፣ ማህበረሰቡ እግሩ ወዳደረሰው በገፍ በመሰደድ በመጀመሩ አንዱ መዳረሻ ወደሆነው ቆቦና ሰቆጣ ሆኗል ሲል ገልፆል፡፡

ስለዚህም በመቶሺዎች የሚቆጠሩ በአማራ አፋር ክልል፣ አንዲሁም ከትግራይ ክልል እየገቡ ላሉት ” ተፈናቃዮች ” የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲድረስላቸውና እንዲታደጋቸው በመግለጫው ጠይቋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
‘ኦብነግ’ ከ25 ዓመታት በኋላ 2ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደ ነው! በአሸባሪነት ተፈርጆ ለ25 ዓመታት ከሐገር ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በማካሄድ ላይ የነበረው፣ በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ምክርቤት 2 መቀመጫ ያለው፣ እኤአ በ1984 ዓ.ም. የተመሰረተው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/ ድርጅታዊ ጉባኤውን በጅግጅጋ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል። አዘጋጅ ኮሚቴው ጉባኤው ከመጋቢት 7 እስከ መጋቢት…
በትላንትናው ዕለት ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የኦብነግ ድርጅታዊ ጉባኤ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ!

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) በጅግጅጋ ከተማ ሊያካሂደው ቀጠሮ የያዘለትን ድርጅታዊ ጉባኤ ማራዘሙን አስታወቀ።የግንባሩ የድርጅት ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ እና የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሁሴን ኑር ትላንት ምሽት በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግንባሩ እቅድ የያዘለትን 5ኛውን ድርጅታዊ ጉባኤ እንደማያካሂድ አሳውቀዋል።

አቶ ሁሴን በመግለጫቸው “ኦብነግ ጉባኤውን ያራዘመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተወካዮች ልኮ ስብሰባውን ለመታደም ባለመቻሉ ነው” ብለዋል።የምርጫ ቦርድ ጥያቄ በኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ማዕከላዊ ኮሚቴ ተቀባይነት በማግኘቱ ጉባኤው መራዘሙን ተናግረዋል።አመራሮች እና አባላት በአካል ተገኝተው በድርጅታዊ እና ሐገራዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ቀጠሮ የተያዘለት የኦብነግ ጠቅላላ ድርጅታዊ ጉባኤ መቼ እንደሚካሄድ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ፍ/ቤት ታስሬ እንድቀርብ ማዘዙ አግባብ አደለም ሲሉ አቤቱታ በጽሁፍ አቀረቡ!

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ፍ/ቤት ታስሬ እንድቀርብ ማዘዙ አግባብ አደለም ሲሉ አቤቱታቸውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጽሁፍ አቀረቡ።የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከዚህ በፊት እንዲቀርቡ መታዘዙ እንደማያውቁና መጥሪያ እንዳልደረሳቸው ገልጸው፤ መጥርያ ተረክቤ እንቢ ባላለኩበት ሁኔታ ታስሬ እንድቀርብ በፍ/ቤት መታዘዙን አግባብ አደለም ሲሉም አቤቱታቸውን አቅርበዋል።

በጥር 30 ቀን 2014 ታስሬ እንድቀርብ መታዘዙን ማህበራዊ ሚዲያ ነው የሰማሁት ሲሉ በጽሁፍ ለፍርድ ቤቱ በላኩት አቤቱታ አብራርተዋል።በደረሳቸው አገራዊ ጥሪ መሰረት ለአገር እና ለህዝብ ጥቅም እየሰሩ መሆናቸውን ተከትሎ ለሥራ በውጭ አገር እንደሚገኙ ጠቅሰው በማንኛውም ሰዓት ለመቅረብ ታዛዥ መሆናቸውን ገልጸዋል።ሆኖም ካላቸው የሥራ ሁኔታ አንጻር በአካል ለመገኘት እንደሚቸገሩ ገልጸው፤ ነገር ግን ምስክርነቱን ባሉበት ቦታ ሆነው በቨርቹዋል ቴክኖሎጂ ጥያቄውኝ ማስተናገድ እንደሚችሉ ፍርድ ቤቱ በላኩት ምላሽ አብራርተዋል።

የእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ጠበቃ ሀፍቶም ከሰተ በበኩላቸው፤ ሀይለማርያም ደሳለኝ መጥሪያ መላኩን አላውቅም ፈርሜ አልተቀበልኩም ማለታቸው እንደማይቀበለው ገልጿል።በተደጋጋሚ መጥሪያ እንዲደርሳቸው መታዘዙን ተከትሎ ለሮማንና ሀይለማርያም ፋውንዴሽን ድርጅት ጸሀፊ መሰጠቱንና ጸሀፊዋ በኢሜል ለሀይለማርያም እንደላከላቸው መግለጿንም ጠበቃ ሀፍቶም አብራርቷል።አገር ውስጥ መሆናቸውን በሚዲያ ከመመልከት ውጪ የሚኖሩበት አድራሻን እንደማያውቁና በቀድሞ ጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት በኩል ምላሽ ተሰቶ እንደነበር አስታዋሷል።

ሀይለ ማርያም እንደሚፈለጉ አውቀዋል ይህ በሆነበት ሁኔታ ትዛዙን አያውቁም ለማለት አይቻልም ሲል ምላሽ የሰጠው ጠበቃው፤ ነገር ግን በችሎት ለመቅረብ የሚቸገሩ ከሆነ በቨርቹዋል ቴክኖሎጂ ባሉበት ሆነው ምስክርነታቸው ቢሰማ አንቃወምም ብሏል።ከሳሽ ዓቃቢህግ ሀይለማርያምም ሆኑ የቀድሞ የጀርመን አንባሳደር ፍስሀ አስገዶም ካውንስለር ካሳን ጨምሮ ሌሎችም ካላቸው ሥራ ጫና አኳያ ባሉበት ሆነው ምስክርነታቸው ቢሰማ እንደማይቃወም አስተያየት መስጠቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።

@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ የተሾሙ አምባሳደሮች የተመደቡባቸው ሀገራት ዝርዝር ይፋ አደረገ!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው ሳምንታዊ መግለጫቸው ጥር 18 ቀን 2014 ዓ.ም ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገሮች ለሚወክሉ አምባሳደሮች የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት እና የአምባሳደርነት ሹመት መስጠታቸውን አስታዉሰዉ ፤በዚህም መሰረት ፤

1. አምባሳደር ተፈራ ደርበው ---ጃፓን
2. አምባሳደር ደሴ ዳልኬ---ደቡብ ኮሪያ
3. አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ---አሜሪካ
4. አምባሳደር ባጫ ደበሌ__ኬንያ
5. አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም--ግብፅ
6. አምባሳደር ዳባ ደበሌ --ሩዋንዳ
7. አምባሳደር ጀማል በከር--ፖኪሲታን
8. አምባሳደር ፈይሰል አሊይ__ኳታር
9. አምባሳደር ኢሳያስ ጎታ---ሞሮኮ
10. አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው--አውስትራሊያ
11. አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ---ስዊዲን
12. አምባሳደር ፍቃዱ በየነ--ኤርትራ

ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ሆኖ በተለያዩ ሀገሮች የተሾሙ አምባሳደሮች፦
13. አምባሳደር ጣፋ ቱሉ--ብራዚል
14. አምባሳደር ዶ/ር ገነት ተሾመ--ኩባ
15. አምባሳደር ሽታዬ ምናለ-- ኮትዲቯር
16. እምባሳደር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ-ኢንዶኔዥያ
17. አምባሳደር ረሻድ መሀመድ-- ዝምባብዌ

በቆንስል ጅነራልነት የተመደቡ:
18. አምባሳደር አንተነህ ታሪኩን -ገዳሪፍ
19. አምባሳደርአክሊሉ ከበደ--ዱባይ
20. አምባሳደር ሰይድ መሐመድ-ሀርጌሳ
21. አምባሳደር አወል ወግሪስ--ባህሬን

በምክትል የሚሲዮን መሪነት፦
22. አምባሳደር አሳየ አለማየሁ--ጋና
23. አምባሳደር ኃይላይ ብርሃነ--ጀርመን
24. አምባሳደር ብዙነሽ መሠረት--ህንድ
25. አምባሳደር ዮሴፍ ካሳዬ--ኒው ዮርክ
26. አምባሳደር ዘላለም ብርሃን--ዋሽንግተን
27. አምባሳደር ፍርቱና ዲባኮ-- ቤልጅየም
28. አምባሳደር ወርቃለማሁ ደሰታ --ኬንያ
29. አምባሳደር ውብሸት ደምሴ--እንግሊዝ
30. አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል--ፓኪስታን ተመድበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዲሲፕሊን ምክንያት 146 አመራሮችንና አባላትን ማሰናበቱን አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ የዲሲፕሊን ጥፋት የተገኘባቸውን 146 የፖሊስ አመራሮችንና አባሎችን በፖሊስ ማባረሩን ዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ፡፡

አመራሮቹና አባለቱ የተሰናበቱት በሰራዊቱ ህግና ደንብ መሰረት መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ ኮሚሽኑ፣ ይሄንን አይነት እርምጃ ሊወስድ የቻለው በስነምግባርና በአቅም ከተማዋን የሚመጥን የፖሊስ ሀይል ለማደራጀት መሆኑን ገልጿል፡፡

ፖሊስ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም በተለያየ ደረጃ የፖሊስ አባል የነበሩና በአስተዳደር ችግሮች ሳቢያ ከሰራዊቱ ወጥተው የነበሩ ከ400 በላይ የቀድሞ አባላትን፣ በድጋሚ ወደ ሠራዊቱ መቀላቀሉን አስታውቋል፡፡ ወደ ስራ ገበታቸው የተመለሱት የቀድሞ የፖሊስ አባላት፣ በሰራዊቱ ውስጥ የነበረው አሰራር ቅሬታ ስላሳደረባቸው “መስራት አንፈልግም” በማለት ወጥተው የነበሩ መሆናቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ መቐለን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ከሁለት ዓመት በኃላ በከፊል ትምህርት መጀመሩ ተገለፀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለዶቼቬለ እንደገለፀው በመቐለ እና ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች የቅድመ መደበኛ የህፃናት ትምህርት እና እስከ ስድስተኛ ክፍል ያሉ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ተመልሰዋል።የተማሪ ወላጆች ግን መቋጫ ካላገኘው ጦርነት ጋር ተያይዞ ጥቃቶች ሊፈፀሙ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልፀዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ትምህርት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱ የትግራይ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ 88 በመቶ የሚሆኑ በትግራይ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተለያየ ደረጃ ውድመት የደረሰባቸው ሲሆን፤235 መምህራን መገደላቸውን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግስት የዓለም አቀፉን የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር መግለጫ ነቀፈ በተለይ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም «ሆን ብለው የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ»ነው በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ወቅሷል።

የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሀላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከጀኔቭ ስዊዘር ላንድ ትናትንት በሰጡት መግለጫ በትግራይ ከፍተኛ የህክምና ቁሳቁስ እጥረትና የጤና ቀውስ መኖሩን ገልፀዋል።ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደገለፁት ፤የዓለም የጤና ድርጅት «ህክምና ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል እንዳላደርስ በመንግስት ተከልክያለሁ»ማለቱ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል።

የህወሃት ታጣቂዎች መንገድ በመዝጋት የህክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች እርዳታዎች ወደ ትግራይ እንዳይደርስ እያደረጉ ነው።ያሉት ሀላፊው።እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ መንግስትን ተወቃሽ ማድረግ ትክክል አለመሆኑን ገልፀዋል።

በተለይ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም «ሆን ብለው የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ»ነው በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ወቅሷል።የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀደምም የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር «የድርጀቱን መርሆችና እሴቶችን የጣሰ አካሄድ እየተከተሉ» ነው የሚል ቅሬታ ለድርጅቱ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሳውዲ አረቢያ በእሥር እና በተለያየ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል ሰላሳ አምስት ሺህ ያህሉ ወደ አገራቸው ለመመለስ መመዝገባቸው ተገለፀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው 100 ሺህ ዜጎችን ከሳውዲ ለምምለስ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በእሥር ላይ የሚገኙም ሆነ በውጪ ያሉት እንዲመለሱ ይደረጋል።የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው መግለጫቸው የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ስላለው የጤና አገልግሎት ችግር መናገራቸው ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ዳይሬክተሩ ችግሩ በአማራም፣በአፋርም መኖሩን ቢናገሩ ተገቢ ነበር የሚል መልስ ሰጥተዋል።ኢትዮጵያ አውዳሚ ጦርነት ውስጥ የገቡት ሩሲያ እና ዩክሬን ድጋፍ ለማሰባሰብ በሚያደርጉት ጥረት ገለልተኛ አቋም ስለመያዟ እና ሁለቱ አገሮች ልዩነታቸውን በሰላማዊ መንገድ ቢፈቱ ይሻላል፣ ለዓለምም የሚበጀው ይህ ነው በሚል አቋሟን በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ግልጽ ማድረጓ በመግለጫው ተጠቅሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሁለት የትምህርት ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ ተወሰደ!

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ ሁለት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰዱን አሰታውቋል።የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የደረሱትን የኅብረተሰብ ጥቆማዎች መነሻ በማድረግ ሰቭን ስታር ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ (ደብረ ብርሃን ካምፓስ) እና ራዳ ኮሌጅ (ደብረሲና ካምፓስ) ላይ የእርምት እርምጃ ተወሰዶባቸዋል፡፡ባለስልጣኑ በአጠቃላይ በ8 የትምህርት ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተለያዩ ለሴት እና ለወንድ እንዲሁም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን የሚያገኙበት ድረ-ገጽ 👇
shein.com SHEIN.COM shein.com

ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን (SHEIN.COM)

Contact @kiru04
☎️ 0931607806

Join 👇👇👇
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሳምንታት የቀሩት አለም አቀፍ የትምህርት ኤክስፖ
በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ
ላይ ይካሄዳል።

ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?

ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ

👉 ትምህርት ቤቶች
👉 ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች
👉 የሶፍትዌር ገንቢዎች
👉 ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች
👉 ት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣
👉 አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች
👉 ኢንኩቤተሮች
👉 የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች
👉 የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች
👉 ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና
👉 ተያያዥነት ያላቸው።

ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ👇!
www.backtoschoolafrica.com

☎️ : +251 974 08 2036
+251 974 08 2037
በቤላ ተራራ ላይ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ወደ ሌላ እንዳይዛመት እየተሰራ ነው!

በዋግ ኸምራ ዞን በቤላ ተራራ ላይ የተከሰተውና አምስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል የአካባቢ የደን እና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ሰደድ እሳቱን ለመከላከል እና ቃጠሎው ወደ ሌላ እንዳይዛመትና ከፍተኛ ውድመት እንዳያስከትል በአካባቢው ማህበረሰብና በባለድርሻ አካላት የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው፡፡በተጨማሪም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፌደራል ደን ኮሚሽን ጋር ችግሩን ሙሉ በሙሉ ለማስቆም ጥረት እንዲደረግና አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሠጥ ጥያቄዎች ቀርበው ኮሚሽኑ ችግሩን ለመፍታት የድርሻውን እንዲወጣ መግባባት ተችሏል ነው የተባለው።

ሰደድ እሳቱ ከተከሰተ ቀን ጀምሮ ከ100 ሔክታር በላይ የሚሸፍን ብዝሐ ህይወት እና የተፈጥሮ ጥብቅ ደን መውደሙን የዞኑ የአካባቢና ደን ጥበቃ አስታውቀዋል፡፡የቤላ ተራራ የብሌን ብሔረሰብ እትብት የማንነት አሻራን አቅፎ የያዘ ፤ በሰሜን የዳህላ ተፋሰስ ፣ የቤላ ፣ የወለህና ዲባ ወንዝ ፣ በምስራቅ የአሏቅ ወንዝ ፣ በምዕራብ የተላ ባርግባ ወንዝ ፤ እንዲሁም በደቡብ የተራራው አቅጣጫ የጅውና ገብርኤል ፣ የአግጣ ጊዮርጊስና የወይላ ወንዝ መነሻ ምንጭ በመሆን የሚያገለግል የውሀ ጋን በመባል የሚታወቅ ተፈጥሯዊ ተራራ መሆኑ ይታወቃል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa