🖲ሴኩሪቲ ካሚራ ከነፃ ገጠማ ጋር...
📍በተጨማሪም በቻናላችን join በማለት እቃዎችን ማየት ይችላሉ👇👇
join :- @Dawitengineering
📍የፈለጉትን ይዘዙን እኛን ለማግኘት ከታች ባለው አድራሻ ያገኙናል።
ስልክ :- 0920757958
inbox :- @Dawit757985

👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሳምንታት የቀሩት አለም አቀፍ የትምህርት ኤክስፖ
በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ
ላይ ይካሄዳል።
ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?
ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ
👉 ትምህርት ቤቶች
👉 ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች
👉 የሶፍትዌር ገንቢዎች
👉 ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች
👉 ት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣
👉 አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች
👉 ኢንኩቤተሮች
👉 የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች
👉 የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች
👉 ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና
👉 ተያያዥነት ያላቸው።
ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ👇!
www.backtoschoolafrica.com
☎️ : +251 974 08 2036
+251 974 08 2037
በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ
ላይ ይካሄዳል።
ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?
ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ
👉 ትምህርት ቤቶች
👉 ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች
👉 የሶፍትዌር ገንቢዎች
👉 ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች
👉 ት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣
👉 አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች
👉 ኢንኩቤተሮች
👉 የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች
👉 የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች
👉 ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና
👉 ተያያዥነት ያላቸው።
ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ👇!
www.backtoschoolafrica.com
☎️ : +251 974 08 2036
+251 974 08 2037
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡
በዚህ መሰረትም፡- አቶ ፀጋ አራጌ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።
እንዲሁም ዶክተር ንጉሴ ምትኩ የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
@YeneTube @FikerAssefa

የጦላይ ማሰልጠኛ ት/ቤት የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ያጠናቀቁ ወታደሮችን በማስመረቅ ላይ ነው!
የጦላይ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኞች ማሰልጠኛ ት/ቤት የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ያጠናቀቁ ወታደሮችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የመከላከያ ጄነራል ኢንስፔክተር ኃላፊ ሌተና ጄነራል ድሪባ መኮንን በክብር እንግድነት መገኘታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የውጤት አያያዝ እና የማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሁለት ዙር መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን÷ የውጤት አያያዝ እና የማለፊያ ነጥብም እንደየዙሩ የተለያየ ነው።
በዚህ መሠረትም በመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች የሲቪክስ ትምህርት ፈተና ውጤት ያልተያዘ ሲሆን÷ ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ መሆኑን ተመላክቷል፡፡
ለመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 600፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 500፣ ለአይነ ስውራን ተፈታኞች ከ 400 ተይዟል፡፡
ለሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ደግሞ ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 700፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 600፣ ለአይነ ስውራን ተፈታኞች ከ 500 ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት መያዙ ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ በሁለት ዙር በተሰጠው ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ የውጤት አያያዝ እና የማለፍያ ነጥብን ከተያያዘው ምስል ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

ከዩክሬን መውጣት ያልቻሉ ኢትዮጵያዊያን ወደ ፖላንድ እዲገቡ ሊደረግ ነዉ ተባለ!
አዲስ አበባ የሚገኘው የዩክሬን ኤምባሲ ዩክሬን ውስጥ ባለ አንድ ካምፕ ተዘግቶባቸው ያሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ፖላንድ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀምሯል ተብሏል።ከኢትዮጵያዊያን ዜጎች የደረሰውን ጥቆማ በመቀበል ኤምባሲው ይህንን ስራ ጀምሯል።
ኤምባሲው ዜጎቻችንን ከካምፑ በማውጣት ወደ ፖላንድ ድንበር ሊወስዱ ንግግር እንደጀመሩ እንዳሳወቀው ጋዜጠኛ ኤልያሰ መሠረት የዘገበ ሲሆን ፣ የካምፑ ሀላፊ ስልክ ተደውሎለት ይህን እንዲያስፈፅም ታዟል ተብሏል።

ዋሽንግተን ለግብፅ F-15 ጄቶች ልታቀርብ ነው!
የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ የአሜሪካ ጦር ጄኔራል ዩናይትድ ስቴትስ ለግብፅ ኤፍ-15 አውሮፕላኖችን እንደምትሰጥ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡የዩናይትድ ስቴትስ የማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ ጄኔራል ፍራንክ ማኬንዚ በኮንግረሱ ላይ ‘‘ረጅም ጠንካራ እና ኢላማውን በአግባቡ የሚመታ F-15 ልንሰጣቸው መሆኑ መልካም ዜና ነው'' ማለታቸው ተሰምቷል ፡፡
ማክኬንዚ በምን ያህል ጊዜ ወይም በቁጥር ስንት F-15 አውሮፕላኖች እንደሚሰጡ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።ባለፈው ወር የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለሀገሪቱ የሚሰጠውን 130 ሚሊዮን ዶላር በሰብአዊ መብት ስጋት ምክንያት ማቋጡን ማናገሩ የሚታወስ ነው፡፡
ማክኬንዚ በግብፅ ጎብኝት ማድረጋቸው ተከትሉ ግን ለግብፅ “በጣም ጠንካራ” ወታደራዊ እርዳታን እንዲሰጥ አፅንዖት በመስጠት ሲናገሩ ተደምጧል።በሕዝብ ብዛት የምትታወቀው ግብፅ በአረብ ሀገራት ወሳኝ አጋር እና ቁልፍ ድምጽ ነች።የአሜሪካ የጦር መርከቦች በስዊዝ ካናል በኩል እንዲያልፉ እና ለአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ያለገደብ በረራ በመስጠትም ግብፅ ሚናዋ ከፍተኛ መሆነን የዋሽንግተን ወታደራዊ ባለስልጣናት ሲናገሩ ቆይተዋል።
✍️Ethio FM

በጋምቤላ ክልል ባለዉ ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ የመንግስት የስራ መግቢያ እና መዉጫ ሰዓት ተቀየረ!
በጋምቤላ ክልል ባለዉ ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ለውጥ የተደረገበት የመንግስት የስራ መግቢያ እና መዉጫ ሰዓት ለዉጥ እስከ ግንቦት 30 እንደሚቆይ የክልሉ ፕሬስ ሴክረታሪያት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል። ዉሳኔዉ ከ የካቲት 1 ጀምሮ መተግበር መጀመሩን የተናገሩት አቶ ኡገቱ በክልሉ ባለዉ ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ የስራ ሰዓት ለዉጡን ማድረግ እንዳስፈለገ ተናግረዋል።
በመሆኑም የስራ ሰዓት መግቢያ ጠዋት 1 ሰዓት እስከ 5:30 ከሰዓት መግቢያ 10 ሰዓት እንዲሁም ከስራ መዉጫ 12 ሰዓት ከ 30 እንደሆነ ተናግረዋል። አክለዉም ቅዳሜ እና እሁድ የእረፍት ቀናት እንደሆኑም ገልጸዋል።
ሆኖም የስራ ሰዓት ለዉጡ በስራ ሂደት ላይ ጫናን እየፈጠረ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊዉ የስራ ሰዓቱን በማያከብሩ ሰራተኞች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝም የጋምቤላ ክልል ፕረስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ አክለዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።በክልሉ በያዝነዉ ሳምንት እስከ 41° ሴንቲግሬድ የሚደርስ ሙቀት ሊኖር እንደሚችል ተሰምቷል።
Via Bisrat FM

የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ ታዩ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ መታየታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገለጹ።ቢቢሲ አቶ ዳውድ ዛሬ ረፋድ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ስብሰባ ለመቀመጥ ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አምርተው እንደነበር ከታማኝ ምንጮች ተረድቷል።ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት የኦነግ የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደቆዩ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገልጾ ነበር።
ይህም ድርጊት ከሕግ ውጪ መሆኑን በመጥቀስ በሊቀ መንበሩ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአፋጣኝ እንዲነሳ ቦርዱ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን እና ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን በደብዳቤ መጠየቁ ይታወሳል።ከአቶ ዳውድ የቁም እስር በተጨማሪ በርካታ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በእስር ላይ ይገኛሉ።የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ሚካኤል ቦረን እና አብዲ ረጋሳን ጨምሮ ኬነሳ አያና፣ ኮሎኔል ገመቹ አያና፣ ዳዊት አብደታ እና ለሚ ቤኛ በእስር ላይ ይገኛሉ።
የኦነግ ቃል አቀባይ በቴ ኡርጌሳ ደግሞ ከጥቂት ቀናት በፊት ከእስር ቢለቀቁም፤ በእስር ላይ ሳሉ ያጋጠማቸውን የጤና መታወክ ተከትሎ በጤና ተቋም ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።የፖለቲከኞቹ ጠበቆች ደንበኞቻችን በፍርድ ቤት በነጻ ቢለቀቁም ፖሊስ ነጻ ለማሰናበት ፍቃደኛ አይደለም ሲሉ ከዚህ በፊት ለቢቢሲ ተናግረዋል።የአቶ ዳውድ ኢብሳን ከቁም እስር መለቀቅ በተመለከተ ፓርቲያቸው እስካሁን ያለው ነገር የለም።
BBC
@Yenetube @Fikerassefa

12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጂቡቲ ከሚገኝ አምራች ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አስታወቁ!
ሰሞኑን የተከሰተውን የዘይት አቅርቦትና ዋጋ መወደድ ዙሪያ መንግስት ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ገበያዉን ለማረጋጋት 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጂቡቲ ከሚገኝ አምራች ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አስታወቁ። ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር አገር ውስጥ የገባ ገብቶ እየተከፋፈለ መሆኑን ጠቁመዋል። ቀሪዉ 7 ነጥብ 7 ሚሊየን ሊትሩ እየተጓጓዘ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም በየወሩ 50 ሚሊየን ሊትር በሶስት ወራት 150 ሚሊዮን ሊትር በተከታታይ ግዢ ይፈጸማል ብለዋል።ባለፈው አመት 1ነጥብ 1 ቢሊየን ሊትር ወደ አገር ውስጥ መግባቱንና በቀጣይ ገበያዉን ለማረጋጋት የተለያዩ ውሳኔዎች መተላለፋቸዉንና ወደ ትግበራ መገባቱንም ገልጸዋል።መንግስት በዘይት ላይ የሚያደርገውን ድጎማ በሌሎች ዘርፎች ላይ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።በየወሩ 50 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ አገር ውስጥ ውሳኔ ላይ መደረሱን ገልፀዋል።
Via EBC/EPA

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ቦሌ ድልድይ አከባቢ ረፋድ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
አደጋዉ የደረሰዉ በሲኖ ትራክ እና የቤት መኪና መሃል በተፈጠረ ግጭት ሲሆን ፣ መብራት ይዞት ቆሞ የነበረ የቤት መኪና ላይ ከፍጥነት ገደብ በላይ እያሽከረከረ የነበረ ሲኖ ትራክ መብራት ጥሶ በማለፍ መኪናዉን ገጭቶ አደጋው እንደደረሰ የቦሌ ክፍለከተማ ቡድን መሪ ዋና ሳጅን ወንድሙ አሻግሬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል፡፡
በዚህም በቤት መኪናዉ ዉስጥ ከነበሩ 4 ሰዎች መካከል ሁለቱ በዕድሜ ገፋ ያሉ ወንድ እና ሴት ወዲያዉ ህይወታቸዉ ሲያልፍ ፣ ሹፌሩ እና ከጀርባ የነበረች ሌላ ሴት ደግሞ ወደ ህክምና መወሰዳቸውን ዋና ሳጅን ወንድሙ ተናግረዋል፡፡ዋና ሳጅን ወንድሙ አሻግሬ እንደገለጹት በመኪናዉ ዉስጥ ከነበሩት 4 ሰዎች መካከል ሹፌሩን ጨምሮ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባል እናት፣ አክስት እና ልጅ ሲሆኑ ሌላዉ አንድ ግለሰብ ግን ያለዉ ዝምድና እየተጣራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ዋና ሳጅኑ እንደገለጹት በመብራት ዙሪያ ያለ ሁኔታን በጣም በጥንቃቄ መተግበር እንዳለበት እና መብራት ጥሶ ማለፍ ለብዙ ጉዳቶች የሚያጋልጥ በመሆኑ ሁሉም አሽከርካሪ በጥንቃቄ እንዲያሽከረክር መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
Via Ethio FM

YeneTube
12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጂቡቲ ከሚገኝ አምራች ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አስታወቁ! ሰሞኑን የተከሰተውን የዘይት አቅርቦትና ዋጋ መወደድ ዙሪያ መንግስት ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ገበያዉን ለማረጋጋት 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጂቡቲ ከሚገኝ አምራች ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አስታወቁ። ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር አገር ውስጥ የገባ ገብቶ እየተከፋፈለ…
4 ሚሊዮን 316 ሺሕ ሊትር የምግብ ዘይት በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፡፡
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ሳርቃ ለዋልታ እንደገለጹት ባቡር በመጠቀም በአንድ ቀን 4 ሚሊዮን 316 ሺሕ ሊትር ዘይት ገብቷል፡፡ባቡሩ በአንድ ዙር 2 ሚሊዮን ሊትር እንደሚያጓጉዝ ገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው አሁንም ተጨማሪ ዘይት በባቡር በመጓጓዝ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን የምግብ ዘይት በአስቸኳይ ሁኔታ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ እንደሆነ ማሳወቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ተጨማሪ እገዛ እንዲደረግላቸው የዩናይትድ ስቴትስን ኮንግረስ ጠየቁ፡፡
ዋሽንግተን በጦርነቱ እገዛ እያደረገችላቸው እንደሆነ ያስረዱት ዜሌንስኪ ነገር ግን ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልገናል ባይ ናቸው፡፡የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በግላቸው በጦርነቱ ውስጥ እያደረጉት ስላለው ተሳትፎ እውቅና ሰጥተዋል፡፡በዕርግጥ ሞስኮ በጉዳዬ ላይ ጣልቃ ገባችሁብኝ የሚል ስም ትሰጠዋለች፡፡
ዋሽንግተን ለኪዬቭ የተለያዩ እርዳታዎችን እና እገዛዎችን ስለማደረጓም ፕሬዚዳንቱ አልደበቁም፡፡ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ ማዕቀቦችን እንድትጥልም ለኮንግረሱ ጥሪ አቅረበዋል ፡፡
በሩሲያ ፌደሬሽን ውስጥ ያሉ ሁሉም ፖለቲከኞች ማዕቀብ እንዲጣልባቸው ምክረ ሀሳብ ያቀረቡት ዜሌንስኪ ዩክሬናውያንን አልታደጓቸውም በሚል ትችት ይሰነዘርባቸዋል፡፡ሁሉም የዩናይትድ ስቴትስ ኩባንያዎች ከሩሲያ ገበያ በአፋጣኝ መውጣት አለባቸውም ይላሉ፡፡ፕሬዚደንት ዜሌንስኪ የዩናይትድ ሰቴትሱ አቻቸው ጆ ባይደን የሰላም መሪ እንዲሆኑም ለማስገንዘብ ሞክረዋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው

አሜሪካ 840 ሺሕ 60 ዶዝ ፋይዘር የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓን ገለፀች።
ድጋፉ አሜሪካ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል።አሜሪካ እስካአሁን ለኢትዮጵያ ያደረገቸው የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ በጥቅሉ 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶዝ እንደደረሰም ተነግሯል።ክትባቱ በያዝነው ሳምንት በኮቫክስ ጥምረት አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ አንደገባም በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

‘ኦብነግ’ ከ25 ዓመታት በኋላ 2ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደ ነው!
በአሸባሪነት ተፈርጆ ለ25 ዓመታት ከሐገር ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በማካሄድ ላይ የነበረው፣ በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ምክርቤት 2 መቀመጫ ያለው፣ እኤአ በ1984 ዓ.ም. የተመሰረተው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/ ድርጅታዊ ጉባኤውን በጅግጅጋ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል። አዘጋጅ ኮሚቴው ጉባኤው ከመጋቢት 7 እስከ መጋቢት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
የኦብነግ የፓርቲ ጉዳዮች ኃላፊና የግንባሩ የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሁሴን መሀመድ ኑር ለሁሉም የፓርቲው አባላት ክፍት እንደሚሆን በሚጠበቀው ጉባኤ ላይ “የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ይገኛሉ” ብለዋል። ከአጀንዳዎቹ መካከልም የግንባሩ ውስጣዊ ችግሮች ላይ መወያየትና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ማስቀመጥ እንዲሁም በወቅታዊ እና ሐገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት እንደሚገኙበት አቶ ሁሴን አብራርተዋል።
Via Addis Zeybe

የዝቋላ አቦ ገዳም በሚገኝበት ደናማ ተራራ ላይ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ተነስቶ ለአምስት ቀናት ያህል የቆየው የእሳት አደጋ ትናንት ሌሊት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ።
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሊበን ጩቃላ ወረዳ በተከሰተው በእዚህ የእሳት አደጋ ምክንያት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉንም የአከባቢው ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።የሊበን ወረዳ አከባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ኃላፊ አቶ ገመዳ ቢራ እንዳሉት፦ ባለፈው ሰኞ የዝቋላ አቦ ዓመታዊ ክብረ በዓል ለማክበር ከአዲስ አበባ ወደ ስፍራው እያቀኑ ከነበሩ ምእመን አንዱ ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ሲያደርግ ወደ ገደል ወድቆ ሕወይቱ ማለፉን ገልጸዋል።
ከመጋቢት 1 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ሲነድ የነበረውን አንድ ሺህ ሄክታር ገደማ ደናማ የዝቋላ ተራራን ለመታደግ የጸጥታ ኃይላት እና የመንግስት ሠራተኞች ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውንም ተናግረዋል። «እኛ አቅቶን ስንመለስ ማታ ኅብረተሰቡ በእድር በጥሩምባ ተጠራርቶ እሳቱን ለመቆጣጠር አመቺ ነው በተባለው ሌሊት ላይ ማጥፋት ችለዋል።
ኅብረተሰቡ ከዚህ በፊትም ልምድ ስላለው እሳቱን ለመቆጣጠር ተችሏል።»በወረዳ ደረጃ እሳቱን ለመቆጣጠር አቅም እንዳልነበራቸው የገለጹት ኃላፊው ለበላይ አካል ቢያሳውቁም አፋጣኝ ምላሽ ባለማግኘታቸው እሳቱ ለቀናት መስፋፋቱን አብራርተዋል።እሳቱ የተነሳው ዶዶቲ ከሚባል የደኑ ጠረፍ አከባቢ መሆኑ ተገልጧል። መንስዔው በውል ዐልታወቀም። በሰደድ እሳቱ በርካታ አገር በቀል እፅዋት እና የዱር እንስሳት መጎዳታቸውንም አቶ ገመዳ አመልክተዋል።እሳቱ በተራራው አናት ላይ ከሚገኘው የዝቋላ አቦ ቤተክርስቲያን እና የአከባቢው ማኅበረሰብ መኖሪያ ቤቶች እሩቅ በመሆኑ ጉዳት አለማድረሱን ዘጋቢችን ሥዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል። የዝቋላ ደናማ ተራራ 13 ሺህ 700 ሄክታር ገደማ ስፋት እንዳለው ይነገራል።
Via DW

በአንድ የዲሽ ሳህን እስከ 64 ቤቶችን እንሰራለን
ለአፓርትመንቶች
ለሪልስቴቶች
ለሆቴሎች
ለገስት ሀውስ
ለኮዶሚንየሞች
📍በተጨማሪም በቻናላችን join በማለት እቃዎችን ማየት ይችላሉ👇👇
join :- @Dawitengineering
📍የፈለጉትን ይዘዙን እኛን ለማግኘት ከታች ባለው አድራሻ ያገኙናል።
ስልክ :- 0920757958
inbox :- @Dawit757985
ለአፓርትመንቶች
ለሪልስቴቶች
ለሆቴሎች
ለገስት ሀውስ
ለኮዶሚንየሞች
📍በተጨማሪም በቻናላችን join በማለት እቃዎችን ማየት ይችላሉ👇👇
join :- @Dawitengineering
📍የፈለጉትን ይዘዙን እኛን ለማግኘት ከታች ባለው አድራሻ ያገኙናል።
ስልክ :- 0920757958
inbox :- @Dawit757985
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication