በመጀመሪያው የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ ለፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተመረጡ አባላት ስም ዝርዝር!
1. ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
2. አቶ አደም ፋራህ
3. አቶ ደመቀ መኮንን
4. አቶ ደስታ ሌዳሞ
5. ዶ/ር ፍጹም አሰፋ
6. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
7. አቶ አሻድሊ ሀሰን
8. አቶ ጌታሁን አብዲሳ
9. አቶ ኡሙድ ኡጁሉ
10. አቶ ተንኳይ ጆክ
11. አቶ ኦርዲን በድሪ
12. አቶ አሪፍ መሃመድ
13. ዶ/ር አብርሃም በላይ
14. ዶ/ር ሊያ ታደሰ
15. ሀጂ አወል አርባ
16. ሀጅሊሴ አደም
17. አቶ ኤሌማ አቡበከር
18. ወ/ሮ ሀሊማ ሀሰን
19. አቶ ሙስጠፌ መሀመድ
20. አቶ አህመድ ሽዴ
21. ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ
22. አቶ ፀጋዬ ማሞ
23. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
24. አቶ ተስፋዬ በልጅጌ
25. አቶ ርስቱ ይርዳው
26. አቶ ተስፋዬ ይገዙ
27. አቶ ሞገስ ባልቻ
28. አቶ ጥላሁን ከበደ
29. አቶ መለሰ ዓለሙ
30. አቶ ሽመልስ አብዲሳ
31. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
32. ዶ/ር አለሙ ስሜ
33. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
34. አቶ አወሉ አብዲ
35. አቶ ሳዳት ነሻ
36. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
37. ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ
38. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ
39. ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ
40. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
41. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
42. አቶ መላኩ አለበል
43. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
44. ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ
45. አቶ ግርማ የሺጥላ ናቸው።
@YeneTube @FikerAssefa
1. ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
2. አቶ አደም ፋራህ
3. አቶ ደመቀ መኮንን
4. አቶ ደስታ ሌዳሞ
5. ዶ/ር ፍጹም አሰፋ
6. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
7. አቶ አሻድሊ ሀሰን
8. አቶ ጌታሁን አብዲሳ
9. አቶ ኡሙድ ኡጁሉ
10. አቶ ተንኳይ ጆክ
11. አቶ ኦርዲን በድሪ
12. አቶ አሪፍ መሃመድ
13. ዶ/ር አብርሃም በላይ
14. ዶ/ር ሊያ ታደሰ
15. ሀጂ አወል አርባ
16. ሀጅሊሴ አደም
17. አቶ ኤሌማ አቡበከር
18. ወ/ሮ ሀሊማ ሀሰን
19. አቶ ሙስጠፌ መሀመድ
20. አቶ አህመድ ሽዴ
21. ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ
22. አቶ ፀጋዬ ማሞ
23. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
24. አቶ ተስፋዬ በልጅጌ
25. አቶ ርስቱ ይርዳው
26. አቶ ተስፋዬ ይገዙ
27. አቶ ሞገስ ባልቻ
28. አቶ ጥላሁን ከበደ
29. አቶ መለሰ ዓለሙ
30. አቶ ሽመልስ አብዲሳ
31. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
32. ዶ/ር አለሙ ስሜ
33. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
34. አቶ አወሉ አብዲ
35. አቶ ሳዳት ነሻ
36. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
37. ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ
38. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ
39. ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ
40. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
41. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
42. አቶ መላኩ አለበል
43. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
44. ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ
45. አቶ ግርማ የሺጥላ ናቸው።
@YeneTube @FikerAssefa
❤1
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ!
በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከፍተኛ ውድመት ተፈፅሞበት ተዘግቶ የቆየው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተማሪዎቹን መቀበል መጀመሩን አስታውቋል።
ተማሪዎቹ ከጧት ጀምረው ወደ ግቢ በመግባት ላይ መሆናቸውን የጠቀሰው ዩኒቨርሲቲው የተቋሙ የጥበቃና ደህንነት ሰራተኞችም በግቢው በር ላይ አስፈላጊውን የፍተሻ ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጿል።
ቀደም ሲል ተማሪዎች መጋቢት 5 እና 6 ቀን 2014 ዓ.ም በቅጥር ግቢው በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪ ያደረገው ዩኒቨርሲቲው በተጠቀሱት ቀናት ወልድያ ከተማ ለሚገቡ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ያመቻቸ መሆኑን ገልጿል።
ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ከጧቱ 2:30 ጀምሮ በመናኸሪያ፣ በፒያሳ፣ በአዳጎና ጎንደርበር ፌርማታዎች ላይ በመገኘት አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል።
Via EPA

ቻይና ለሩሲያ ወታደራዊ ድጋፍ የምትሰጥ ከሆነ ከባድ መዘዝ እንደሚጠብቃት አሜሪካ አስጠነቀቀች!
ሩሲያ በዩክሬን በምታካሂደው ወታደርዊ ዘመቻ ላይ ቻይና ድጋፍ የምትሰጥ ከሆነ ከባድ መዘዝ እንደሚጠብቃት የአሜሪካ ባለስልጣናትን በመጥቀስ የዩናይትድ ስቴትስ መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ይገኛሉ።ሩሲያ ዩክሬን ላይ ጦርነት ከጀመረች በኋላ ቻይና ወታደራዊ እርዳታ እንድትሰጣት ሩሲያ ጥያቄ ማቅረቧን ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ ባለስልጣናት መናገራቸው ተዘግቧል።
በዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በጉዳዩ ላይ መንም አይነት መርጃ እንደሌለው አስታውቋል።አሜሪካ ማስጠንቀቄያውን የሰጠችው በዛሬው ዕለት በጣልያን ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባ በፊት ነው።
የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቤጂንግ የረዥም ጊዜ አጋሯ ለሆነችው ሞስኮ ምንም አይነት ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ እንዳደረገች በይፋ የታወቀ ነገር የለም።የአሜሪካ ባለስልጣናትን በመጥቀስ ሩሲያ ከቅርብ ቀናት ወዲህ በተለይም የሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጨምሮ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ቻይና ድጋፍ እንድታደርግላት መጠየቋን እየተዘገበ ይገኛል።ለነዚህ የሩሲያ ጥያቄዎች ግን የቻይና ምላሽ ምን እንደሆነ እስከ አሁን የታወቀ ነገር የለም።
✍Asham

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊሶችን ቁጥር 50 ሺሕ ለማድረስ ታቀደ!
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማ ውስጥ ያለውን የነዋሪ ቁጥርና የፖሊስ ኃይል ምጥጥን ለማስተካከል፣ የከተማዋን ፖሊስ ቁጥር ወደ 50 ሺሕ ለማሳደግ መታቀዱን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ የፖሊስ ኃይሉን ቁጥር ለማሳደግ ተከታታይ ምልመላ እንደሚያደርግ አስታውቆ፣ በዚህ ዓመትም ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መልማዮችን መላኩን ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ የነዋሪዎቿ ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረና አሁን ላይ 6.8 ሚሊዮን ነዋሪዎች እንደሚገኙባት አስታውቋል፡፡ ይሁንና በከተማ ውስጥ ያለው የፖሊስ ኃይል ይህንን የሕዝብ ቁጥር የማይመጥንና የብዙዎቹን የከተማዋን አከባቢዎች የማይሸፍን መሆኑን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
የከተማ አስተደዳሩ ያደረገው ጥናት እንደሚያመላክተው፣ በከተማዋ ውስጥ ያለው የፖሊስ ቁጥር በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለው ምጣኔ በሁለት እጥፍ ያነሰ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ አንድ የፖሊስ አባል እየሸፈነ ያለው ቢያንስ የአራት ፖሊሶችን ተግባርና ኃላፊነት ነው፡፡
እንደ ኮማንደር ፋሲካ ገለጻ፣ የፖሊስ ቁጥሩ ከነዋሪው ብዛት ጋር ካለመመጣጠኑም ባሻገር፣ በከተማዋ 11 ክፍላተ ከተማዎች ከሚገኙ 121 ወረዳዎች ውስጥ፣ የፖሊስ ጣቢያዎች ያሉት በ72 ያህሉ ብቻ ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በቀሪዎቹ ወረዳዎች ላይ አዳዲስ የፖሊስ ጣቢያዎችን ለመክፈት እየተሠራ መሆኑን ተናግረው፣ ጣቢያዎቹን ለመክፈት የሰው ኃይል፣ የቢሮና የቁሳቁስ ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
ኮማንደር ፋሲካ የከተማዋ ስፋትና የነዋሪው ብዛት በፍጥነት እየጨመረ መሆኑንና ችግሩን ለመቅረፍ፣ “አንድ ፖሊስ ስንት ሰዎችን መጠበቅ አለበት?” የሚለው ሳይንሳዊና ዓለም አቀፋዊ ደረጃዎችን መሠረት በማድረግ እየተሠራበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በዚህ መሠረት ኮሚሽኑ ቢያንስ በአምስት ዓመት ውስጥ የአዲስ አበባ ፖሊስን ቁጥር 50 ሺሕ ለማድረስ ማቀዱን አስታውቀዋል፡፡
ሙሉ ዘገባ : http://bit.ly/3CF5UOV

በአዲስ አበባ ወደ ውጪ ሀገር ጉዞ የምታደርግ ግለሰብን ለመሸት የወጡ ሰባት ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጡ!
በአዲስ አበባ ከተማ ቅዳሜ ምሽት 3ሰዓት ከ30 ደቂቃ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታዉ ሀና ማርያም ቀለበት መንገድ ላይ ባጋጠመ የትራፊክ አደጋ ወደዉጪ ሀገር ጉዞዋን የምታደርግ ግለሰብን ጨምሮ ለመሸኘት የወጣ ቤተሰብ በአደጋውን ህይወታቸውን አጥተዋል።
በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 -35609 ዶልፊን ተሽከርካሪ ዉስጥ ከነበሩት 11 ተሳፋሪዎች ዉስጥ ሰባቱ ወዲያዉ ህይወታቸዉ ሲያልፍ አራት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል። ከሟቾቹ ዉስጥም የምትሸኘዋ ተጓዥና እሷን ለመሸኘት ከኤርትራ የመጡ እናቷ ይገኙበታል ሲሉ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ቀሪዎቹ አምስት ሰዎች ቤተሰብና ጎረቤቶች ሲሆኑ ከአደጋዉ የተረፉት ከእናታቸዉ ጋር የሚጓዙ የ4 አመት እና የ6 አመት ህጻናት አንዲሁም አሽከርካሪዉ ናቸዉ ። ሟቾቹ ሁሉም ሴቶች ሲሆኑ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ተጎጂዎችን ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ህክምና ቦታ እንዲደርሱ መደረጉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ጨምረው ተናግረዋል።
[Bisrat FM]

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ተማሪዎች እና በግቢው ግጭት ለመፍጠር የሞከሩ አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና÷ የጸጥታ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ከከተማው የጸጥታ ሃ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ተማሪዎች እና በግቢው ግጭት ለመፍጠር የሞከሩ አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ጠቁመዋል፡፡
አሁን ላይም ዩኒቨርሲቲው መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባሩ እንደቀጠለ መግለጻቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዲጂታል መታወቂያ በአምስት ክፍለ ከተሞች መሠጠት ተጀመረ!
በመዲናዋ ሕገ ወጥ የመታወቂያ ሥርጭትን ይከላከላል ተብሎ የታመነበት የዲጂታል መታወቂያ፣ በአምስት ክፍለ ከተሞች መሠጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።
በአዲስ አበባ በአራዳ፣ በቦሌ፣ በየካ፣ በጉለሌ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሕገ ወጥ የመታወቂያ ሥርጭትን እና አሠራርን ይቀርፋል ተብሎ ዕምነት የተጣለበት የዲጂታል መታወቂያ ማተሚያ ማሽን እና መታወቂያ የመሥጠት ሥራ በቅርንጫፎቹ በኩል ሙሉ ለሙሉ መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ከፍተኛ አማካሪ መላክ መኮንን ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።
ይህ ዲጂታል መታወቂያ በክፍለ ከተሞቹ ታትሞ ለነዋሪዎች መሰጠቱ ሕገ ወጥነትን ከመከላከል ጎን ለጎን፣ ደንበኞችን በፍጥነት ለማስተናገድ እንደሚረዳ እና በከተማዋ ነዋሪዎች መስተንግዶ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል።
Via Addis Maleda

ክፍት የስራ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ዴሊቨሪ ሀዋሳ ከስር በተዘረዘረው ክፍት የስራ ቦታ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
መስፈርቶች
የስራው ዘርፍ፥ ፡ ሴልስ
ደመወዝ፥ ፡ ከ2000፡ 3000 እንዲሁም ጥቅማ ጥቅም ያለው።
የትምህርት ደረጃ፥ ፡ 10 ክፍል ያጠናቀቀች
አድራሻ፥ ፡ ሀዋሳ አዋሽ ህንፃ ላይ አራተኛ ፎቆ R12
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈቶች የምታሟሉ አመልካቾች በአካል በመክረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ፩፭ ተከታታይ ቀናት በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።
Check our @Deliveryhawassa

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።
በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።
በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።
በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።
ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

The dates are getting closer to witness one of Largest Global Hybrid Expo, which shall be taking place at the newly built state of the art library, Abrehot Library.
Exhibitors can take part either Onsite or Virtual, form any part of the globe.
List of Exhibitors:
Schools & Colleges/Universities
School Management Solution Providers
Software developers
App developers & Coders
Start-ups & TECH Entrepreneurs
Education Consultants
STEM Education Incubators,
Digital Service Providers
Education Material Producers & Suppliers
Digital Libraries
NGOs & related.
To Reserve Your Booth:
Call us:
+251 974 0820 36
+251 974 0820 37
Book online via:
www.backtoschoolafrica.com

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያሳልጡና የሚያዘምኑ ስምምነቶችን ከቻይና ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያሳልጡና የሚያዘምኑ ሁለት ስምምነቶችን በዛሬው እለት ከቻይና ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአለም ባንክ በተገኘ የ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ በዛሬው እለት የተፈረመው ውል ስምምነት የመጀመርያው ለከተማዋ የሚመጥኑ ዘመናዊና ለአገልግሎት ተስማሚ የሆኑ 110 ባሶችን ከቻይናው ዩቶንግ ባስ ካምፓኒ ጋር ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ግዥ ለመፈፀም ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ኩባንያው ባሶቹን በ8 ወራት ውስጥ የሚያቀርብ ይሆናል ተብሏል፡፡
ሁለተኛው ስምምነት ደግሞ የአንበሳ አውቶብስን አቅም የሚያዘምነውና የሚያሳድገው በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን የታገዘው የብልህ ትራንስፖርት ስርዓት (intelligent transport system) ከቻይናው ሺንዶ ሂሰንስ ትራንስ ቴክ ኩባንያ ጋር የተፈፀመ ውል መሆኑ ተገልጿል፡፡ይህ ውል ከ14 ሚሊዮን ዶላር በላይ እና በሃገር ውስጥ በተጨማሪ 9 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚደረግ ሲሆን አጠቃላይ ድርጅቱን አለም ከደረሰበት የትራንስፖርት መሰረተ ልማት እድገት ጋር የሚያቀራርብና ከወረቀት ነፃ የሆነ አገልግሎት ለደንበኞች በየተርሚናሉና የጉዞ ዲጂታል መረጃ አቀረርቦትም እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
በስምምነት ስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት በ2013 ዓ.ም ምርጫ ላይ ለህዝቡ ለመፍታት ቃል ከገባናቸው ጉዳዮች አንዱ የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎትን ማሻሻል ነበር ብለዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ከ1.9 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን መንገዶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን በማስታወስ ዛሬ ደግሞ የትራንስፖርት አገልግሎቱን የሚያቀላጥፉና የሚያዘምኑ ስምምነቶችን መፈጸማቸው አስታውቀዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ለከተማ ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ኪራይ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደጉም የገለፁት ከንቲባዋ የትራንስፖርት አገልግሎትን መንግስት ብቻውን የሚፈታው አይደለም በማለት የግሉ ሴክተርን አስተዋፅኦ ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ስምምነቶቹ የእውቀት ሽግግር እና ዘመናዊነትን አለም የደረሰበትን ቀልጣፋ የአይሲቲ አገልግሎትን ያካተተ መሰረታዊ የትራንስፖርት የለውጥ ስራ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የመመሪያ ጥሰት በፈጸሙ 7 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማስተካከያ እርምጃ ተወሰደ!
የመመሪያ ጥሰት በፈጸሙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰዱን የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ የኅብረተሰቡን ጥቆማዎች መነሻ በማድረግ ተቋማት ላይ ባካሄደው ድንገተኛ ጉብኝት በሰባት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶች ላይ የእርምት እርምጃዎችን መውሰዱን ገልጿል፡፡
የማስተካከያ እርምጃው የተወሰደባቸው ተቋማት (ካምፓሶች) ቢኤስቲ ኮሌጅ ጊንጪ ካምፓስ፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ሆሳዕና ካምፓስ፣ ግሬት ቪዥን ኮሌጅ ሆሳዕና ካምፓስ፣ ዛክቦን ኮሌጅ ሻሽመኔ ካምፓስ፣ ብርሃን ኮሌጅ ደብረ ብርሃን ካምፓስ፣ ዮም የድህረ ምረቃ ኮሌጅ ሀዋሳ ካምፓስ እና ለራዳ ኮሌጅ ደብረ ብርሃን ካምፓስ መሆናቸውን ገልጿል።
ተቋማቱ ከፈፀሟቸው ጥሰቶች መካከል የእውቅና ፈቃድ ባልተገኘበት መርሐ ግብር መሰማራት፣ የመግቢያ መስፈርት የማያሟሉ ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማር፣ ያለባለስልጣኑ ፈቃድ የማስተማሪያ ቦታ ለውጥ ማድረግ እና እውቅና ያልተገኘበት የደረጃ ስያሜን መጠቀም ይገኙበታል።
በተቋማቱ ላይ የተወሰደው እርምጃም ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ እግድ የሚደርስ መሆኑን ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አዝናኝ ተከታታይ ኮሜዲ ድራማ
በዋሜን ኢንተር ቴመንት ዘወትር ሮብዕ 3:00 ላይ
ከወጣት እስከ አንጋፋ ተዋናይ የተሳተፉበት
ገብተው ይመልከቱት 🙏
https://youtu.be/JFZKCW5ga0Q
በዋሜን ኢንተር ቴመንት ዘወትር ሮብዕ 3:00 ላይ
ከወጣት እስከ አንጋፋ ተዋናይ የተሳተፉበት
ገብተው ይመልከቱት 🙏
https://youtu.be/JFZKCW5ga0Q
YouTube
ፍቅር አዳሽ አዲስ ተከታታይ ድራማ ክፍል 1 fikiri adashi 1
Unauthorized use, distribution, and re-upload of this content is strictly prohibited Copyright ©2021 sintayehu melaku
የሱማሌላንድ ራስ ገዝ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ለኦፊሴላዊ ጉብኝት ወደ አሜሪካ እንዳቀኑ የራስ ገዟ ውጭ ጉዴይ ሚንስቴር በትዊተር ገጹ አስታውቋል።
ፕሬዝዳንት ቢሂ በጉብኝታቸው ከአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ከሕግ አውጭ ምክር ቤቱ አባላት ጋር ይነጋገራሉ ተብሏል። ሱማሌላንድ በሐርጌሳ ወደቧ አሜሪካ ወታደራዊ ጦር ሠፈር ማቋቋም ከፈለገች ፍቃድ እንደምትሰጥ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የገለጠች ሲሆን፣ ፕሬዝዳንት ሙሴ በመጋቢት በአሜሪካ በሚያደርጉት ጉብኝት በጉዳዩ ላይ ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ በወቅቱ ተገልጦ ነበር።
[ዋዜማ ራዲዮ]
@Yenetube @Fikerassefa

በሱዳን የዳቦ ዋጋ በ40 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ የዳቦ አመጽ በመካሄድ ላይ ነው
በሱዳን የዳቦ ዋጋ መናሩን ተከትሎ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ተቀሰቀሰ፡፡
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ የተጀመረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት የዓለም ነዳጅ እና ምግብ ዋጋዎችን እንዲንር አድርጓል፡፡
በሱዳንም የዳቦ ዋጋ ከጦርነቱ በፊት ከነበረበት አሁን ላይ 50 የሱዳን ፓውንድ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም የአገሪቱን ዜጎች ለከፍተኛ ቁጣ ዳርጓል፡፡
በዚህም ምክንያት በሱዳን የዳቦ አመጽ በመካሄድ ላይ ሲሆን በሺህ የሚቆጠሩ ሱዳናዊያን ወደ አደባባይ ወጥተው ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው፡፡
ባሳለፍነው ጥቅምት በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ (ዶ/ር) ይመራ በነበረው መንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ስልጣን የተቆጣጠረው ወታደራዊ መንግስት ላይ ተጨማሪ ጫናን ይፈጥራል ተብሏል፡፡
መፈንቅለ መንግስቱን ለመቃወም ወደ አደባባይ የወጡት ሱዳናዊያን አሁን ደግሞ የዳቦ ዋጋ መናሩ ተጨማሪ ሱዳናዊያን ወደ አደባባይ ለተቃውሞ ወጥተዋል፡፡
የሱዳን የጸጥታ ሀይሎችም በአገሪቱ በርካታ ከተሞች ወደ አደባባይ የወጡ አመጸኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙን አልዓይን ከካርቱም ዘግቧል፡፡
ከዳቦ ዋጋ በተጨማሪም የነዳጅ ዋጋ በ50 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም በጀነራል አልቡርሃን ለሚመራው ወታደራዊ መንግስት ሌላኛው ፈተና ነውም ተብሏል፡፡
ተቃዋሚዎቹ ከዚህ በፊት ስልጣን በሀይል የተቆጣጠረው የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳድር እንዲመልስ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡
የዳቦ ዋጋ መናሩን ተከትሎ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ አንማርም ያሉ ተማሪዎችን ጨምሮ የባቡር መንገድ ሰራተኞችም የዳቦ አመጹን ተቀላቅለዋል፡፡
የሱዳን ጦር ስልጣን በሀይል መቆጣጠሩን ተከትሎ አሜሪካ ለሱዳን ልትሰጠው የነበረውን 700 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ማቆሟ ይታወሳል፡፡
በፈረንጆቹ 2019 በሱዳን የዳቦ ዋጋ ጨምሯል በሚል ተቃውሞ ተጀምሮ በስልጣን ላይ የነበሩት ፕሬዘዳንት ኦማል ሀሰን አልበሽርን ከስልጣን እንዲነሱ ዋነኛ ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም፡፡
Via:- Al ain

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ሌሊት ብሔርን መሠረት አድርጎ በተማሪዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት በበርካታ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ገለጹ።
ግጭቱን በቅርበት የተመለከቱ ተማሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት ችግሩ ከተፈጠረ ቀናት ያስቆጠረ ቢሆንም ትናንት ሌሊት ግን ወደ አካላዊ ግጭት ተሸጋግሯል። በተማሪዎቹ መካከል ወደ ብሄር ግጭት ያሸጋገረውን አጋጣሚ በተመለከተ አስተያየቱን ለዶይቼ ቬለ የሰጠው እና ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀው ተማሪ« ጥላቻን የሚሰብክ ወረቀት በጊቢው መበተኑን » ይገልጻል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር ዉባቸው ማሞ በበኩላቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ቅጥር ጊቢው በመግባት ተማሪዎችን ለፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃነት ተጠቅመዋል በማለት ይከሳሉ። ኢንጅነር ውባቸው አሁን ዩኒቨርሲቲው መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባሩ እንደቀጠለ መግለጻቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ያሏቸው ተማሪዎች እና ሌሎች አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን አስታውቀው ነበር።
[DW]