ዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ የዓለም የኩላሊት ቀን ታስቦ ይውላል!
👉አጫጭር መረጃዎች ኩላሊትን በተመለከተ
~የኩላሊት አማካይ ክብደት የሞባይል ስልክ ያሃ ሲሆን ከ114 እስከ-170 ግራም ድረስ ይመዝናል።ምንም እንኳን ኩላሊቱ በአማካይ የሰውነት ክብደት 0.5% ብቻ ቢይዝም ከጉበት በመቀጠል ከሌሎች የአካል ክፍሎች የበለጠ ደም ይቀበላል፤ወይም በመጠን የኮምፒውተር ማውዝ ያክላሉ።
~በአለም ከሚኖረው ህዝብ 10በመቶ የሚሆነው በከባድ የኩላሊት በሽታ የተጠቃ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ተመጣጣኝ ህክምና ባለማግኘት በየዓመቱ ህይወታቸውን ያጣሉ።
~እ.ኤ.አ በ1990 በዓለም አቀፍ ደረጃ የኩላሊት በሽታ 27ኛው ገዳይ በሽታ የነበረ ሲሆን በ2010 ማብቂያ ግን ወደ 18ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።
~አብዛኛው የሰው ልጅ የተወለደው ከ2 ኩላሊት ጋር ነው። ነገር ግን ካሉት ኩላሊት አንዱ ቢወጣ ሰውነቱ የኩላሊት ስራን የሚያጣው 25% ብቻ ነው። በከፍተኛ የደም ግፊት (hypertrophy) ምክንያት የቀረው ኩላሊት ሰውነቱን ማቆየቱን ይቀጥላል።
~በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በህይወት ለመቆየት የኩላሊት እጥበት(ዳያሊስስ) ወይም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ያደርጋሉ።ነገር ግን ይህ ቁጥር ህክምና ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች 10% ብቻ ይወክላል።
~ኩላሊት በቀን ወደ 170 ሊትር ደም ያጣራል።ከመጠን በላይ ኢቡፕሮፌን እና አስፕሪን ኩላሊትን ሊጎዱ ይችላሉ።
~ኩላሊት ሰውነታችን ውስጥ የሆርሞን ምርት፣ የንጥረ ነገሮች ምርትና ምጣኔ፣ የሰውነት ፈሳሽን ምጣኔ እና ሌሎች በርካታ ተግባራትን ያከናውናል።
~በአለም የተመዘገበው ትልቁ የኩላሊት ጠጠር 1.1 ኪሎ ግራም ይመዝናል።
[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa

በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ!
በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ሲካሄድ የቆየው የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፡- በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ካምፖች በፈታኝ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡
የዜጎቹን ማንነት፤ ያሉበትንሁኔታና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ለማጠናቀር ወደ ስፍራው አቅንቶ የነበረው ልዑክ መመለሱን ያወሱት ቃል አቀባዩ፤ ዜጎቹን መመለስ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡ለተልዕኮው ስኬትም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሚመራ 16 ተቋማትን ያካተተ ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡
በተያያዘም ዩክሬንና ሩሲያ በመካከላቸው የተፋፋመው ግጭትና ውጊያ በማቆም ዓለም ጎራ ለይቶ እንዲዋጋ ከሚያነሳሱ ትንኮሳዎች እንዲቆጠቡ ኢትዮጵያ ጥሪ ማቅረቧን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል፡፡በሁለቱ ሀገራት መካከል የተካረረው ሁኔታ ዓለምን በጎራ ወደ ውጊያ እንዳያስገባ ተንኳሽ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ችግሩ የንግግር መፍትሄ እንዲበጅለት ኢትዮጵያ ፅኑ አቋም አላት ብለዋል አምባሳደር ዲና።ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያንፀባረቀችው ድምፅ አልባ ውሳኔም የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት ባለበት ትልቅ ትሩፋት ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ!
የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት ባለበት ትልቅ ትሩፋት ነው ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።አምባሳደር ዲና በዛሬው እለት ሳምንታዊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ ማብራሪያ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይን በተመለክተ ተቋማዊ አለመሆኑ ችግር አይፈጥርም ወይ በሚል ለቀረበው ጥያቄ በዋናነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ሰላም ነው ሲሉ ተናግረዋል።እንዲሁም በጋራ ጉዳዮች ላይ መደጋጋፍ በተለያዩ መድረኮች ላይ ተደጋግፎ መታየቱ ነው ዋናው ነው ሲሉ አክለዋል።
ይሄ ሰላም ከተፈጠረ ገና 3 ዓመት ነው በዚህ መሃል የተሻለ አፈጻጸም እንዳይታይ ያደረጉ እንቅፋቶች አሉ ግን ደግሞ በአጠቃላይ ሲታይ የሰጠው ትሩፋት ትልቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።በሀገራቱ መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት ተቋርጦ የቆየው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዳግም እንዲጀመር ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንደሆኑ ይታወሳል።
[ዳጉ ጆርናል]

አረብ ኤሚሬት ለኢትዮጵያ የሚሆን የ85 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች!
ድጋፉ ለአንገብጋቢ ሰብዓዊ ፍላጎቶች ምላሽ ለመስጠት የሚውል ነው ተብሏል
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ለኢትዮጵያ የሚሆን የ85 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች፡፡ድጋፉ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታዎች አስተባባሪ ተቋማት በኩል ለተጠቃሚዎች የሚደርስ ነው ተብሏል፡፡ከዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ ከዓለም የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማህበራት፣ ከዩኒሴፍ እና ሌሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ተቋማት ጋር እንደሚሰራም ነው የተገለጸው፡፡
ዩኤኢ ድጋን እንደምታደርግ ያስታወቀችው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታዋ ሼክ ሻክቦት ቢን ናህያን አል ናህያን፣ የተመድ የሰብዓዊ እና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ እንዲሁም በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በተገኙበት በተካሄደ የበይነ መረብ ስብሰባ ነው፡፡ግሪፊትስ ለድጋፉ ዩኤኢን አመስግነዋል፡፡አምባሳደር ታዬ ስለ ድጋፉ ያሉት ነገር እንዳለ አላስታወቁም፡፡
Via Alain

የሮማን አብራሞቪች ቼልሲ እግር ኳስ ክለብን የመሸጥ እቅድ ችግር ላይ ወድቋል ተባለ
እገዳው አብራሞቪች ቼልሲን ለመሸጥ በያዙት ውጥን ላይ ችግር መፍጠሩ ነው የተነገረው
የእንግሊዝ መንግስት መንግስት የቼልሲ እግር ኳስ ክለብ ባለቤት ሮማን አብራሞቪችን ጨምሮ በሰባት ሩሲያውያን ቱጃሮች ላይ አዲስ የሃብትና የጉዞ እገዳ መጣሉን አስታወቀ።
በቦሪስ ጆንሰን ጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚመራው የእንግሊዝ መንግስት የክለቡ ባለቤት ከእንግሊዛውያን ባለሃብቶች ጋር ምንም ዐይነት ግብይቶችንም ሆነ የቢዝነስ ስምምነቶችን ማድረግ እንደማይችሉ አታውቋል።
ሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች የቼልሲ እግር ኳስ ክለብን ለመሸጥ መወሰናቸው አስታወቁ ይህም ማለት አብራሞቪች እንዳሰቡት ሁሉ ቼልሲን ለመሸጥ አይችሉም ማለት ነው።
በአንድ ወቅት የአብራሞቪች የንግድ ሸሪክ የነበሩት ኦሌግ ዴሪፓስካ ተመሳሳይ እጣ ፋንታ ከገጠማቸው ቱጃሮች መካከል ናቸው።
የሩሲያ የነዳጅ ኩባንያ ሮዝኔፍት ኃላፊ ኢጎር ሼሺን ጨምሮ ሌሎች የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ሰዎች ናቸው የተባሉ አራት ሰዎች የእገዳው ሰለባ ናቸውም ተብሏል፡፡ እገዳው በቀጣዩ ሳምንት ተግባራዊ እንደሚደረግም ነው የተገለጸው።
ለፑቲን ደጋፊዎች የሚሆን ምቹ ሁኔታ እንደማይኖርም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን የተናገሩት።
እገዳው ለዩክሬናውያን ያለንን ድጋፍ የሚያሳይ ነውም ብለዋል ጆንሰን። የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ በሩሲያ እንዳይደረግ ተወሰነ በዩክሬናውያን ደም እጃቸው አለበት በሚል ቱጃሮቹን የከሰሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ በበኩላቸው አንገታቸውን ሊደፉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በድምሩ 15 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገደማ የሚገመት የ7ቱ ቱጃሮች ሃብት ነው እገዳ የተጣለበት።
Via :- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa

ባልደራስ 46 የፓርቲው አባላት እና የአዲስ አበባ እስረኞች ከተማ ዳር ወደሚገኘው አባ ሳሙኤል እስር ቤት መወሰዳቸውን አስታወቀ!
በአድዋ እና ካራማራ ሳቢያ የተከሰሱት 34 የባልደራስ እስረኞችን ጨምሮ 46 የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ በምሳ ሰዓት ታስረው ከሚገኙበት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከተማ ዳር ወደሚገኘው አባ ሳሙኤል መዘዋወራቸውን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አስታወቀ፡፡
ይህ ፍፁም ያልተጠበቀ እና ህገ ወጥ እርምጃ ነው ያለው ፓርቲው፣ እስካሁን ባለው አሰራር ተጠርጣሪዎች መደበኛ የክስ ፋይል እስካልተከፈተባቸው ድረስ ወደ አባ ሳሙኤል እንደማይሄዱ ገልጿል፡፡ “ተጠርጣሪዎች የምርመራ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ጊዮርጊስ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ወይም በየወረዳው ባሉ የፖሊስ ጣቢያ እስር ቤቶች ነው፡፡ እርምጃው መንግሥት በህገወጥ እና በጉልበት አካሄዱ እየገፋበት እንደሆነ ያመላክታል፡፡” ሲልም ባልደራስ ገልጿል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የፓርቲው አባላት እና ሌሎች የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተጠርጥረው በተያዙበት ጉዳይ ዛሬ ማለዳ አራዳ ጊዮርጊስ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ3 የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ መቅረባቸውን አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ፣ “ተጠርጣሪዎቹ በአድዋና በካራማራ ክብረ-በዓላት ላይ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት፣ ህዝብ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽ በማድረግ፣ የመንግሥት ባለስልጣናትን በመሳደብና በማዋረድ ተግባር ላይ ሲሰማሩ አግኝቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም፣ የተከለከለ ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በመንግሥት ላይ አመጽ ለማነሳሳት ሞክረዋል፡፡ ስለሆነም፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እንድናደርግባቸው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ” ብሏል፡፡
የተከሳሾቹ ጠበቆች ባቀረቡት ክርክር፣ “ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የለውም፤ ጉዳዩም መታየት ካለበት የወንጀል ተግባሩ ተፈፀመ በተባለበት በልደታ ክፈለ ከተማ አጥቢያ ፍርድ ቤት ነው፣ በአንድ የወንጀል ጉዳይ ሁለት የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ልደታ እና አራዳ ክፍለ ከተማ ሊከፈት አይገባም፣ ፖሊስ 48 ሰዓት ካለፈ በኋላ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ውቅድ ሊሆን ይገባል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተዛወሩት እስረኞችን ለመበቀል፣ ሆን ብሎ ለማንገላታትና በረዥም ጊዜ ቀጠሮ ያለአግባብ ለማጉላላት ነው።” ማለታቸው ተገልጿል፡፡
ጠበቆቹ አክለውም ተከሳሾቹ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እያሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበው የ3 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ከተሰጣቸው በኋላ፣ ፖሊስ በዕለቱ ለይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ ቢያቀርብም፣ ችሎቱ የፖሊስን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በ3 ቀን ውስጥ አጣርቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ በተሰጠበት ሁኔታ፣ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የምርመራ ሥራውን ሰርቶ ማቅረብ ሲገባው፣ ይህንን ወደ ጎን በመተው ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አዲስ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ማስከፈቱ ተጠርጣሪዎቹን ለመበቀል አላማ እንደሆነ መረዳት ይቻላል” ብለዋል፡፡
በተጨማሪም፣ ፖሊስ በቀን የካቲት 23 የአድዋ በዓል እና የካራማራ የድል በዓል ላይ ሁከትና ብጥብጥ ተፈፀመ ቢልም፣ በእለቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰጠው መግለጫ በዓሉ በሰላም ተጠናቋል የሚል መግለጫ አውጥቶ እያለ፣ መስተዳድሩ የማያውቀው ሁከትና ብጥብጥ እንደተፈፀመ ተደርጎ በፖሊስ የቀረበው ክርክር ውድቅ እንዲደረግ ተጠይቋል፡፡
እንዲሁም፣ ፖሊስ ባቀረበው አቤቱታ የድል በዓላቱ በሚከበርበት ጊዜ የባለሥልጣናት ሥም ተነስቶ የስድብ እና ማዋረድ እንደተፈፀመ ቢያቀርብም፣ ጉዳዩ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚቀርብ ሆኖ ሳለ፣ ባለሥልጣናቱ ቀርበው ምርመራ እንዲጣራላቸው አቤቱታ ወይም ማመልከቻ ለፖሊስ ባላቀረቡበት ሁኔታ፣ ፖሊሰ በራሱ ተነሳሽነት ሊያጣራው የሚችለው ባለመሆኑና ጊዜ ቀጠሮ የሚያስጠይቅ ባለመሆኑ የፖሊስ አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ ተጠይቋል፡፡
በተጨማሪም፣ የተከለከለ ሰንደቅ አላማ ይዘው ወጥተዋል በሚል ያቀረበውን በተመለከተም፣ በአዋጅ ቁጥር 654/2001 መሠረት ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ እንኳን፣ በገንዘብ አማራጭ የሚያስቀጣ ቀላል ጉዳይ በመሆኑ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህጉ አላማና ግብ ያፈነገጠ በመሆኑ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባም ሲሉ ጠበቆቹ ተከራክረዋል፡፡
ፖሊስ አሰባስባችኋል ያላቸው የሰነድ፣ የሰው እና የስልክ ማስረጃዎች ቀጠሮ ለማሰጠት በቂ አይደሉም፡፡ የማያውቋቸው ምስክሮች እና አባሪዎች ሊያሸሹብኝ ይችላሉ ያለውን ሥማቸው ተጠቅሶ ያላወቅናቸው ስለሆነ ተገቢነት ያለው አይደለም ብለው ጠበቆች መከራከራቸውን ባልደራስ ገልጿል፡፡ፍርድ ቤቱም በጠበቆች ክርክር ላይ ፖሊስ መልስ እንዲሰጥ ካደረገ በኋላ ትዕዛዝ ለመስጠት ለመጋቢት 5 ቀን 2014 በ8፡00 ሰዓት ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡
[Addis Maleda]

ብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔውን ነገ ይጀምራል!
ገዢው ፓርቲ ብልፅግና ጠቅላላ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ ያካሂዳል።ጉባኤውን አስመልክቶ የፓርቲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ግኑኝነት ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ መግለጫ ሰጥተዋል።ዶክተር ቢቂላ የብልጽግና አንደኛ ጉባኤ ባለፉት ሶስት አመታት ፓርቲው በሁሉም መስክ የተጎናጸፋቸውን ድሎች ይገመግማል ብለዋል።
የገጠሙትን ችግሮች እና ተግዳሮቶች በጥልቀት ገምግሞ ለማረም ታሪካዊ ውሳኔ ያሳልፋልም ብለዋል።ጉባኤው በጸጥታ ሁኔታ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመክርም ገልጸዋል።
በዚህም ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያመጡ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ነው ያሉት።የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ነገ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ይጀምራል።በጉባኤው 1 ሺህ 600 የፓርቲው አባላት በድምፅ የሚሳተፉ ሲሆን፥ 400 ከተለያየ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ከውጭ ሀገራት የተጋበዙ እንግዶች ያለ ድምፅ ይሳተፋሉ።
ጉባኤው የፓርቲው አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት የሚጎናጸፉበት፣ ፓርቲው በአደረጃጀት እና አሰራር ራሱን የሚያጠናክርበት እንዲሁም ፓርቲውን ሊያሻግሩ እና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ሊያረጋግጡ የሚችሉ ጠንካራ የፓርቲ አመራሮች የሚመረጡበትም ይሆናል ብለዋል።
Via FBC

#BACK_TO_SCHOOL_AFRICA_EXPO_2022
ጥቂት ሳምንታት የቀሩት አለም አቀፍ የትምህርት ኤክስፖ በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ ላይ ይካሄዳል።
ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?
ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ
ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች፣ የት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣ የሶፍትዌር ገንቢዎች፣ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች፣ አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች ፣ የትምህርት ኢንኩቤተሮች፣ የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች፣ የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች፣ ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው።
ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ!
www.backtoschoolafrica.com
ለበለጠ መረጃ +251 974 0820 36/37

ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች የራሳቸውንና የሠራተኞችን የሀብት ምዝገባ አጠናቀው እንዲያሳውቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ!
ሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ከዓመታት በፊት በፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ተግባራዊ የተደረገውን አሠራር በመቀየር፣ በቀጣይ ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች በበላይነት እንዲቆጣጠሩትና እሰከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ የራሳቸውንና የሠራተኞችን ሀብት ምዝገባ አጠናቀው ለኮሚሽኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡
ከዚህ ቀደም በመንግሥት ተቋማት የተሰየሙ የሥነ ምግባር መኮንኖች፣ በኮሚሽኑ አስተባባሪነት ሲያከናውኑት የነበረውን የሀብት ምዝገባ፣ ከቀናት በፊት በዋና ኮሚሽነሩ በተጻፈ ደብዳቤ እስከ ታችኛው የመንግሥት ዕርከን ድረስ የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎችንና ሠራተኞችን ሀብት ምዝገባ አጠናቀው ሪፖርት እንዲያቀርቡ፣ ከየካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ማሳሰቢያ መሰጠቱን፣ በኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዘገባ ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይነህ ተናግረዋል፡፡
Via Reporter

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከመጋቢት 5 ቀን ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራውን ይጀምራል ተባለ!
በአሸባሪው ቡድን ውድመት ደርሶበት የነበረው የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከመጋቢት 5 ቀን ጀምሮ ከ3 ሺህ 600 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ሥራውን እንደሚቀጥል ገለጸ።የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሱልጣን መሀመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ከሽብር ቡድኑ ውድመት በኋላ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል።
በዚህም ተማሪዎች መጋቢት 5 እና 6 ቀን ማለትም የፊታችን ሰኞና ማክሰኞ ወደ ግቢያቸው መምጣት ይችላሉ ብለዋል።ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ የቅበላ መርሃ-ግብሩ የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት የሆኑ ከ3 ሺህ 600 በላይ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ዶክተር ሱልጣን ተናግረዋል።

በጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ላይ በ15 ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰረት ፍርድ ቤት አዘዘ!
ላለፉት 90 ቀናት በእስር ላይ በሚገኘው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ላይ የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰርት የገላን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ። የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተባለው ጊዜ ክስ እስኪመሰርት ድረስም፤ ጋዜጠኛው በፊንፊኔ ዙሪያ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ከተማ በሚገኘው ዳለቲ ማረሚያ ቤት እንዲቆይ ፍርድ ቤቱ አዝዟል።
የገላን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሁለቱን ትዕዛዞች ያስተላለፈው፤ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጋዜጠኛው ላይ ሲያከናውን የነበረውን ምርመራ ማጠናቀቁን ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 1፤ 2014 ለተሰየመው ችሎት መግለጹን ተከትሎ ነው። የኦሮሚያ ፖሊስ በዛሬው የችሎት ውሎ የጋዜጠኛውን የምርመራ መዝገብ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ማስተላለፉን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል።
የኦሮሚያ ፖሊስ በዛሬው ችሎቱ “ምርመራዬን ጨርሻለሁ” ከማለት ባለፈ በተፈቀደለት 14 የምርመራ ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ለችሎቱ አለማሰማቱን የጋዜጠኛው ጠበቃ አቶ ገመቹ ጉተማ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ምርመራውን ማጠናቀቁን ለችሎቱ ከገለጸ በኋላ፤ የጋዜጠኛው ጠበቃ በደንበኛቸው ላይ የተከፈተው የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ እንዲዘጋ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸውን አስረድተዋል።
Via Ethiopian Insider

ለትግራይ ችግር ተቃዋሚዎች ህወሃትን ከሰሱ!
እየቀጠለ ባለው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ያለው ህዝብ ለከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር መጋለጡ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ። ፓርቲዎቹ መፍትሔ ባለማበጀት እና ተጨማሪ ችግር በመፍጠር ትግራይን እያስተዳደረ ያለው በህወሓት የሚመራው ክልላዊ መንግስት ወቅሰዋል። በትግራይ ያለው ረሀብ፣ የማሕበራዊ አገልግሎቶች እጦት እና ሌሎች ችግሮች በአጭር ግዜ መፍትሔ ካላገኙ በቅርቡ አስከፊ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል የገለፁት በትግራይ የሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎች፥ ዓለም ያለው ሁኔታ በትክክል ተገንዝቦ የትግራይ ህዝብ ችግር የሚያሳጥር ጫና ይፍጠር ብለዋል።
[DW]

አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication

📌 ጥራት ያላቸው ኦሪጅናል የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከ T-max ኤሌክትሮኒክስ
ምርቶችቻችንን ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ:
👉 https://tttttt.me/tmaxelct
📌 አድራሻ: መርካቶ ይርጋ ሃይሌ ህንፃ ምድር ላይ ሱቅ ቁጥር፡ ጂ-96
ብዛት ለማዘዝ ይደውሉ
🤳 09 33 11 11 11 / 09 74 55 55 55

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አይኤስ የመሪውን አልቁራይሺ መሞት አምኖ፤ ተተኪ መሪ ሾመ!
ኢስላሚክ ስቴት ወይም በእንግሊዝኛ የምህጻር ቃል አይኤስ (IS) የተሰኘው ጽንፈኛ ቡድን የመሪውን የአቡ ኢብራሒም አልቁራይሺን መገደል አመነ፡፡በድረ ገጽ በተለቀቀ አንድ የድምጽ መልእክት አቡ አልሐሰን ሐሸሚ አልቁራይሺ አዲሱ መሪ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህ እጩ መሪ ትክክለኛ ስሙና ማንነቱን ግን ይፋ አልተደረገም፡፡በዚህ የድምጽ መልእክት እስከዛሬ ቡድኑን ሲመራ የነበረው አቡ ኢብራሒም አልቁራይሺ የት፣ በማንና እንዴት እንደተገደለ ያለው ነገርም የለም፡፡አሜሪካ እንደምትለው ግን አልቁራይሺን ለመያዝ ልዩ ዘመቻ በተደረገበት ወቅት ከበባ ላይ መሆኑን ሲረዳ ራሱንና ቤተሰቡን በቦምብ አጥፍቷል፡፡ይህም የሆነው፣ እንደ አሜሪካ መረጃ፣ በየካቲት 3 በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ከተደበቀበት ሥፍራ ነው፡፡
[BBC]

የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ማስፋፊያ ተነሽዎች ካሳ ሳይከፈላቸው ቤታቸውን አፍርሱ ተባሉ!
የኦሮሚያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ማስፋፊያ ተነሽ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ካሳ ወይም ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ቤታቸውን በሦስት ቀን ውስጥ እንዲያፈርሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ዋዜማ ከተነሽዎች ሰምቻለሁ ብላለች፡፡
አዲስ አበባ ፍላሚንጎ አካባቢ እስከ ግሪክ ትምህርት ቤት ድረስ ባለው አካባቢ ለሚገነባው የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ማስፋፊያ ቦታውን እንዲለቁ ትዕዛዝ የተሰጣቸው መካከል 15 የግለሰብ ቤቶች የሚገኙ ሲሆን፣ የቀበሌ ቤቶችም ተነሽ ናቸው ተብሏል፡፡
ዋዜማ የተመለከተችው በየካቲት 30/2014 ዓ.ም ለተነሽዎች የተሰጠ የቤት ማፍረሻ የመጨረሻ ማስጠንቀቂ ትዕዛዝ “ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በደረሰዎት በተከታታይ ሦስት ቀናት ውስጥ ቦታውን ነጻ እንድታደርጉ እያሳሰብን፣ ይህ ሳይሆን ቢገኝ ግን ለሚወሰደው እርምጃ ጽሕፈት ቤታችን ኃላፊነቱን እንደማይወስድ እናሳውቃለን” ይላል፡፡
የመጨረሻ ማስጠንቀቂ ደብዳቤውን ለተነሽዎች የጻፈው የቂርቆስ ከፍል ከተማ ወረዳ 01 የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ነው፡፡
ሙሉ ዘገባው: https://bit.ly/3HYfFJ7