YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን አካውንት ለግዜው ያግዳል የተባለው ወሬ ሐሰት መሆኑን ባንኩ አስታወቀ።

ባንኩ “መረጃ አሟሉ አልኩ እንጂ የባንክ ሂሳብ አግዳለሁ አላልኩም” ፤ ማለቱን ለሸገር ነግሯል።ዛሬ የደንበኞችን መረጃ የመሰብሰቢያ ቀን የመጨረሻ ነው የተባለውም ሐሰት ነው ሲል ባንኩ ይናገራል።

የባንኩ የኮምዩንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ያብስራ ከበደ ባንኩ የደንበኞችን መረጃ ለመሰብሰብ አገልግሎቱን ለጊዜው ገደበ እንጂ አለማገዱን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲ.ኤምና የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን መገደብ ያስፈለገው የብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የግል ባንኮች የላከውን መመሪያ ለመተግበር በመገደዱ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ደንበኞች ለጊዜው በኤቲኤም እና በሞባይል ባንኪንግ የገንዘብ ማስተላለፍና ማውጣት አገልግሎት ባያገኙም ወደ ቅርንጫፍ መጥተው ሀብታቸውንና ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ መታወቅ አለበት ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞችን መረጃ ለመፈለግ የመጨረሻው ቀን ዛሬ አርብ ነው የተባለውም ትክክል እንዳልሆነ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ደንበኞች በየቅርንጫፉ መጉላላት ፣ መሰለፍ እና ጊዜያችሁን ማባከን የለባችሁም ባመቻችሁ ጊዜ ባንኩ የሚጠይቀውን መረጃ መስጠት ትችላላችሁ ፤ ተብላችኋል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አና ሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር የኦፕቲካል ፋይበር ኪራይ ሥምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር አንዋር ሶውሳ ናቸው፡፡

ሥምምነቱ በመጀመሪያ ምዕራፍ 4097 ኪ.ሜ፣ በሁለተኛው ምዕራፍ 2078 ኪ.ሜ እንዲሁም በሶስተኛው ምዕራፍ 2904 ኪ.ሜ የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ኪራይን ያጠቃልላል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በመጀመሪያው ምዕራፍ የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ኪራይ በዓመት እስከ 140 ሚሊዮን ብር ገቢ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እስከ 15 ሺህ ኪ.ሜ የሚሸፍን የኦፕቲከል ፋይበር መስመር ባለቤት ሲሆን ኢትዮ-ቴሌኮም 8745 ኪ.ሜ በኪራይ እንዲሁም ደግሞ ተቋሙ ለውስጥ የመረጃ ልውውጥ እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የአፋር እና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች ላይ የተደረገ ምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆነ!

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና በአማራ ክልሎች ተስፋፍቶ በቆየው ጦርነት የተከሰቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ ከመስከረም ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለአራት ወራት ያክል ያደረገውን ምርመራ ባለ 110 ገፅ ሪፖርት መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል፡፡ ኢሰመኮ በዚህ ሪፖርቱ በጦርነቱ ተሳታፊ በሆኑ አካላት በተለያየ ደረጃ የተፈጸሙ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚዘረዝር ሲሆን፣ ፍትሕን ለማረጋገጥ እንዲሁም የተጎዱ ሰዎችና አካባቢዎችን መልሶ ለመጠገን እና ለማቋቋም የሁሉንም ወገኖች እና ተቋማት ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግም ገልጿል።

ኢሰመኮ ከዚህ ቀደም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት (UNOHCHR) ጋር በጣምራ ካደረጉትና በትግራይ ክልል ላይ ካተኮረው ሪፖርት ቀጣይ በሆነው በዚህ ሪፖርት፤ በተለይ ከሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የትግራይ ኃይሎች በአፋርና በአማራ ክልሎች በከፈቱት ወታደራዊ ጥቃት በርካታ ቦታዎችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ከነፆታዊ እንድምታቸው መርምሯል፡፡

ሙሉ ሪፖርት: https://ehrc.org/am/%e1%8a%a0%e1%8d%8b%e1%88%ad-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8a%a0%e1%88%9b%e1%88%ab-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8e%e1%89%bd%e1%8d%a1-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8a%a0/

@YeneTube @FikerAssefa
ፌስቡክ በሩሲያ ወረራ ዙሪያ ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮችን ሊፈቅድ ነዉ!

የፌስቡክ እና ኢንስታግራም የወላጅ ኩባንያ የሆነው ሜታ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችዉ ወረራ በኋላ በአመጽ ንግግር ላይ ያለዉን ፖሊሲውን ለጊዜው በማቃለሉ "ሞት ለወራሪዋ ሩሲያ " ይሁን የሚሉ ልጥፎችን ማድረግ እንደሚቻል ይፈቅዳል፡፡ነገር ግን በሰላማዊ ሰዎች ላይ እንዲህ ዓይነቱ ዛቻ እንደማያካትት አስታዉቋል።

የዚህ ፖሊሲ ውሳኔ ይፋ እንደተደረገ ወዲያውኑ ውዝግብ አስነስቷል፡፡እንደ አልጃዚራ ዘገባ ከሆነ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ የፌስቡክ ባለቤትን ከአክራሪነት እንቅስቃሴ እንዲገደብ ጠይቋል፡፡ኤምባሲው በሰጠው መግለጫ "በሩሲያውያን ላይ የጥላቻ እና የጥላቻ ስሜትን ወደማነሳሳት የሚያመራው የሜታ ጨካኝ እና የወንጀል ፖሊሲ አስጸያፊ ነው" ብሏል። "የኩባንያው ድርጊት በአገራችን ላይ የታወጀ የመረጃ ጦርነት ሌላ ማስረጃ ነው፡፡"ሲል ኤምባሲዉ አክሏል፡፡

ኩባንያዉ እንዲህ ዓይነት አግላይ እርምጃ ሲወስድ የመጀመሪያዉ አይደለም እ.ኤ.አ. በጁላይ 2021 የኢራን ልዕለ መሪ አያቶላህ ሩሖላህ ኾሜይኒ በመጥቀስ “ሞት ለኾሜይኒ” የሚሉ ልጥፎችን በጊዜው ፈቅዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
በመጪዎቹ 4 ዓመታት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ እንዲኖረው እየተሰራ መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ተናገረ፡፡

በሙከራ ደረጃ ዜጎችን የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ለማድረግ የምዝገባ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ከብሔርና ከሃይማኖት በስተቀር የዓይን አሻራ ሳይቀር ማንኛውንም የመታወቂያውን ባለቤት ማንነት ይይዛል የተባለው ብሔራዊ መታወቂያ የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀሎችን ለመከላከል እንደሚያግዝ ሸገር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ከ10 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ሊኖረው ይገባል ተብሎ እየተሰራበት ያለው ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የጣትና የዓይን አሻራን ጨምሮ የመታወቂያው ባለቤቱን ሙሉ አድራሻና ሙሉ መረጃውን የሚይዝ ይሆናል ተብሏል፡፡

እንዲህ ያለው ብሔራዊ መታወቂያ ዜጎች ከሚጠቀሙባቸው እንደ ቀበሌ መታወቂያ ፣ ፓስፖርትና ሌሎችም መታወቂያዎች በተጨማሪ ሁሉም ዜጋ በግዴታ ሊኖረው የሚገባ እንደሆነም ሰምተናል፡፡

በኢትዮጵያ እያንዳንዱ ዜጋ በቴክኖሎጂ የበለፀገ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እንዲይዝ መደረጉ ግለሰቦች በተለያየ ስምና መታወቂያ የሚፈፅሙትን ማጭበርበር ለመከላከል ያግዛል ተብሎ በፅኑ ታምኖበታል፡፡

ለብሔራዊ መታወቂያው የአሰራር ሥርዓትን የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅም የተሰናዳ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው ብሔራዊ የመታወቂያ ፕሮግራም ጉዳዩ ከሚያገባቸው ጋር በመመካከር ረቂቅ አዋጁን የተሻለ ለማዳበር እየተሰራሁ ነው ብሏል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ መረጃቸውን በማስተካከል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡

ባንኩ ዛሬ በሰጠው ማብራሪያ÷ ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ መረጃቸውን በማስተካከል አገልግሎት ማግኘት እንድሚችሉ አስታውቆ በዛሬው ቀን በቅርንጫፎች የተፈጠረው መጨናነቅ አላስፈላጊ መሆኑንም ገልጿል፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አ.ኤ.አ በ27/08/2021 ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ የደንበኞችን መረጃ የማደራጀትና የማጥራት ስራ ላለፉት 6 ወራት በመሥራት ላይ መሆኑን አስታውሷል፡፡

በዚህም መሠረት÷ እስካሁን በርካታ ደንበኞች መረጃቸውን በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወቅታዊ ማድረጋቻውን አስታውቋል፡፡ሆኖም እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ በተለያዩ ምክንያቶች መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ ያልቻሉ ደንበኞች÷ የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አግልግሎቶች ብቻ ማለትም (የሞባይል ባንኪንግ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ እንዲሁም የኤቲኤም እና የፖስ አገልግሎት) እንደሚቋረጥባቸው ገልፆ÷ በማንኛውም ጊዜ ግን ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች በመምጣት መረጃቸውን ሲያስተካክሉ ወዲያውኑ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉም አስታውቋል፡፡በተጨማሪም በተለያዩ የማህበራዊ ትሥሥር ገጾች እና የመረጃ ምንጮች መረጃ ያላስተካከሉ ደንበኞች ሂሳብ ይዘጋል በሚል የሚናፈሰው ወሬ በፍጹም ትክክል አለመሆኑን ባንኩ አረጋግጧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
8 ነፍሰጡር እናቶች በሕክምና ማጣት ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችኮሚሽን በሪፖርቱ ገለጸ፡፡

በአማራ ክልል መቄት ወረዳ ሸሆድ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በደረሰበት ዘረፋ እና ውድመት ምክንያት አገልግሎት መስጠት በማቆሙ በወረዳው 8 ነፍሰጡር እናቶች በሕክምና ማጣት ሕይወታቸው ማለፉን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት በአጠቃላይ 749 ያህል ዜጎች መሞታቸውን ገልጿል፡፡
አሸባሪው የህውሃት ቡድን በክልሉ በጤና እና በትምህርት ተቋማት ላይ በደረሰው ዝርፊያ፤ ውድመት እና ቃጠሎ የአካባቢው ነዋሪዎች የጤና እና ትምህርት አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ ያደረገ ሲሆን፣ ነፍሰጡር እናቶች በሕክምና እጦት ሕይወታቸው አልፏል ሲል በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

የሕክምና ተቋማት በመውደማቸው እና በመዘረፋቸው በቂ ሕክምና ለማግኘት ሳይችሉ ሕይወታቸው ያለፈ ሕፃናትም አሉ ተብሏል።

በአማራ እና በአፋር ክልሎች የአሸባሪው የህውሀት ሀይሎች ባደረጉት የቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት በ100ዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ተጎጂዎች የደረሰባቸው ወሲባዊ ጥቓት በማህበረሰቡ ከታወቀ ሊደርስባቸው የሚችለውን መድሎ እና መገለል በመፍራት ብዙውን ጊዜ ጉዳታቸውን ለመናገር የማፈልጉ በመሆናቸው የጥቃቱ ስፋት በሪፖርቱ ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ ነው ሲል በዛሬው እለት ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

Via Fidel Post
@Yenetube @Fikerassefa
ባለ5 ሊትር ዘይት በ472 ብር እንዲሁም ባለ 20 ሊትሩን በ1818 ብር ለህብረተሰቡ እየተሰራጨ ነው ተባለ!

ባለ5 ሊትር ዘይት በ472 ብር እንዲሁም ባለ 20 ሊትሩን በ1818 ብር ለህብረተሰቡ እያሰራጨ መሆኑን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት አሰታወቀ።ባለ5 ሊትር ፌቤላ ዘይት በ472 ብር እንዲሁም ባለ 20 ሊትር ዘይት በ1818 ብር እየተከፋፈለ መሆኑን የክፍለ ከተማው ህብረት ስራ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጓዱ ጥጋቡ ሃላፊ አቶ ጓዱ ጥጋቡ ገልጸዋል።በዚህ ዙር 52ሺ ሊትር ዘይት ተቀብለው እያሰራጩ መሆኑን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#BACK_TO_SCHOOL_AFRICA_EXPO_2022

ጥቂት ሳምንታት የቀሩት አለም አቀፍ የትምህርት ኤክስፖ በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ ላይ ይካሄዳል።
ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?

ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ

ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች፣ የት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣ የሶፍትዌር ገንቢዎች፣ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች፣ አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች ፣ የትምህርት ኢንኩቤተሮች፣ የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች፣ የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች፣ ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው።

ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ!
www.backtoschoolafrica.com

ለበለጠ መረጃ +251 974 0820 36/37
ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ!

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ እና ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ።ፑቲን፤ ገንዘብ ሳይከፈላቸው ለሩሲያ መዋጋት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ ካሉ በኋላ፤ “እነዚህን ሰዎች ወደ ጦር ግንባር በመላክ ማድረግ የሚፈልጉትን መተባበር አለብን” ብለዋል።የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተነስተው በዶንባስ ግዛት ከሩሲያ ጦር ጎን መሰለፍ የሚፈልጉ 16 ሺህ ሰዎች አሉ ሲሉ ለፑቲን መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም የሶሪያ ወታደሮች በሩሲያ መንግሥት እየተከፋላቸው በዩክሬን ሊዋጉ ይችላሉ የሚል መረጃ በስፋት ሲሰራጭ ነበር።ባሻር አል-አሳድ ሕዝባዊ ተቃውሞ በተነሳባቸው ወቅት ከሩሲያ መንግሥት ጠንካራ ድጋፋ አግኝተው በሥልጣናቸው ላይ አሁንም ይገኛሉ።ፑቲን ለፀጥታ ምክር ቤታቸው ምዕራባውያን “በግልጽ ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመተላለፍ ተዋጊዎችን ለዩክሬን እየቀጠሩ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ስጋዊ እረፍትን ተከትሎ የሽኝትና አስክሬናቸውን የማሳረፍ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ይካሄዳል

የሽኝቱና የቀብር ስነ-ስርዓቱ በሰላም እንዲከናወን የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

በመስቀል አደባባይ የፓትርያኩ አስከሬን ሽኝት የሚካሄድና የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ/ም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚፈፀም ሲሆን፡-
ነገ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-

*ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ
-ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ
-ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት
-ከፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል መብራት
-ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር
-ከጦር ኃይሎች ፣ በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት
ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከቀኑ 12:30 ጀምሮ ዝግጅቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በእለቱ የብፁእነታቸው አስከሬን ከመስቀል አደባባይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ (ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን) በሚንቀሳቀስበት ወቅት ከመስቀል አደባባይ ፣ በብሔራዊ ቤተ መንግስት፣ ውጭ ጉዳይ ፣ አራት ኪሎ ፣ ቅድስት ማርያም የሚወስደው መንገድ፣

መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ/ም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ስነ-ስርዓት የሚፈፀም በመሆኑ የቀብር ስነ-ስርዓቱ እስከሚፈፀም ወደ ቅድስት ማርያም ፣ አራት ኪሎ እና ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሰጡት አማራጭ መንገዶችን እንድትጠቀሙ ግብረ ኃይሉ እያስታወቀ ለጋራ ደህንነት ሲባል በሽኝቱ እና በቀብር ስነ-ስርአቶች ወቅት ፍተሻ መኖሩን የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ተገንዝበው ለፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
አሶሴትድ ፕሬስ እስር ላይ ያሉ ዘጋቢዎቹ እንዲለቀቁለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በድጋሚ ጠይቋል።

አሚር ከሦስት ወራት በላይ እስር ላይ ቢቆይም የወንጀል ክስ እንዳልተመሠረተበት የገለጠው ድርጅቱ፣ አሚር የታሠረው በጋዜጠኛነት ሥራው ብቻ ነው ብሏል። ፖሊስ አሚርን ያሰረው ወደ ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ከሌሎች ባልደረቦቹ ጋር ተጉዞ፣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽ እና አመራሮቹን እና ታጣቂዎችን በማናገር ያሰባሰበውን መረጃ ኢትዮጵያ ጠል ወደሆኑ አገሮች ልኳል በሚል ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
📌 ጥራት ያላቸው ኦሪጅናል የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከ T-max ኤሌክትሮኒክስ
ምርቶችቻችንን ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ:
👉 https://tttttt.me/tmaxelct

📌 አድራሻ: መርካቶ ይርጋ ሃይሌ ህንፃ ምድር ላይ ሱቅ ቁጥር፡ ጂ-96
ብዛት ለማዘዝ ይደውሉ
🤳 09 33 11 11 11 / 09 74 55 55 55
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተለያዩ ለሴት እና ለወንድ እንዲሁም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን የሚያገኙበት ድረ-ገጽ 👇
shein.com SHEIN.COM shein.com

ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን (SHEIN.COM)

Contact @kiru04
☎️ 0931607806

Join 👇👇👇
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡

በሽኝት መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፣ ብፁዓን አባቶች እና የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እጅግ አሰቃቂና ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ መንግስት ገለፀ!

ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ እጅግ አሰቃቂ እና ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ መንግስት ገለፀ።
 
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ እጅግ አሰቃቂ እና ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ድርጊት መፈጸሙን አንስቷል።
 
በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተንቀሳቃሽ ምስል ሲዘዋወር በቆየው እጅግ አሰቃቂ ድርጊት ንፁሃን ዜጎች በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ሲደረግ መታየቱ በመግለጫው ተመላክቷል።
 
ይህ ድርጊት ከኢትዮጵያዊነት ባህል፣ እሴትና ከማንኛውም የሰብዓዊነት እሳቤ ያፈነገጠና እጅግ አሰቃቂ ወንጀል ነው ያለው አገልግሎቱ፥ ይህ እኩይ ድርጊት መጠፋፋትን ያፈጥን ካልሆነ በቀር ሰላምንም ሆነ ፍትህን እውን ሊያደርግ እንደማይችልም አስገንዝቧል።

በመሆኑም ድርጊቱ ሊኮነንና ሊወገዝ ይገባል፤መነሻቸውም ሆነ ማንነታቸው ምንም ይሁን ምን መንግስት ይህን አይነት ፍፁም ከሰብዓዊነት የራቀና ጭካኔ የተሞላበትን ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።
 
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ህገወጥነት ለመቆጣጠርና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከልም ከክልሉና ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
 
የንፁሃን ዜጎችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላትን መንግስት ከዚህ በኋላ አይታገስም ያለው መግለጫው÷እነዚህ በወንጀል ስራ ላይ የተሰማሩና የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላት ከወዲሁ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም በጥብቅ አሳስቧል።
 
@YeneTube @FikerAssefa
የሕንድ ጦር በስህተት ወደ ፓኪስታን ሚሳየል መተኮሱን አመነ፡፡

የሕንድ የመከላከያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚሳየሉ በስህተት በመተኮሴ አዝኛለሁ ማለቱን ዴይሊ ሞኒተር ፅፏል፡፡ቀደም ሲል የፓኪስታን ጦር ወደ አገሪቱ የተወነጨፈውን ተምዘግዛጊ በሚመለከት ሕንድን ማብራሪያ ለመጠየቅ እንዳላረፈደ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ሕንድ እና ፓኪስታን ግንኙነታቸው በቋፍ ላይ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡አነስተኛዎቹን ቁርቋሶዎች ሳይጨምር ሁለቱ አገሮች በመካከላቸው ቢያንስ 3 ታላላቅ ጦርነቶችን ማድጋቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡በተለይም በካሽሚር ግዛት ጉዳይ ስሜተ ስሱዎች ናቸው ይባላል፡፡

Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa