በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን የመድኃኒት ዕጥረት ተከስቷል ተባለ!
በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን ዝቋላ ወረዳ ሥር በሚገኙ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች የመድኃኒት ዕጥረት መከሠቱን ከወረዳው የጤና ቢሮ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
በዝቋላ ወረዳ ሥር የሚገኙ የሕክምና ተቋማት የተለያዩ መድኃኒቶች ዕጥረት እንደገጠማቸውም የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ እስጢፋኖስ ወንዳዬ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
ኃላፊው እንደሚሉት ከሆነ፣ የዝቋላ ወረዳ ከነሐሴ 19/2013 ጀምሮ እስከ ኅዳር ወር ማገባደጃ 2014 ድረስ በጸጥታ ችግር ውስጥ ቆይቶ አሁን ላይ አንፃራዊ ሠላም በመምጠቱ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች መደበኛ ሥራቸውን ቢጀምሩም፣ የመድኃኒት ዕጥረት እንደገጠማቸው ነው ማወቅ የተቻለው።
[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መቐሌ እና አክሱምን ጨምሮ ከመላዉ ትግራይ ክልል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ተፈናቃዮች ወደ ቆቦ ከተማ እየገቡ መሆኑ ተነገረ!
ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች ከመላዉ የትግራይ ክልል ወደ ቆቦ ከተማ እየገቡ እንደሚገኝ የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ ይመር በተለይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
እንደ አቶ አለሙ ይመር ገለፃ ከትግራይ ክልል እየገቡ የሚገኙ ተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እየመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ከፌደራል መንግስት ጋር በመሆን አራት የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፖችን በማዘጋጀት ተፈናቃዮችን ለመቀበል እየሰሩ እንደሚገኝ አስታውቀዋል ።
ተፈናቃዮች ካለምንም ስጋት ወደ አማራ ክልል እየገቡ መሆኑንም ተናግረዉ የክልሉ መንግስትም ሆነ ህዝቡ ተፈናቃዮችን እየተቀበሉ እንደሚገኝ አቶ አለሙ ይመር ተናግረዋል። በተለይም ከአክሱም እና መቐለ ከተሞች ሴቶች እና አዛዉንቶች እንዲሁም ወጣቶች ጭምር ወደ ክልሉ እየገቡ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ወደ አማራ ክልል እየገባ ከሚገኘው ተፈናቃይ ቁጥር አንጻርም ከፍተኛ የሆነ ፍተሻ እና ቁጥጥር እየተደረገም እንደሚገኝ የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ ይመር ጨምረው ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
[ዳጉ ጆርናል]

የብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሽኝት መርሃ ግብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናወነ!
የቀድሞው የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የጸሎትና ሽኝት መርሃ ግብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናወነ።በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ከተለያዩ ገዳማትነ አድባራት የመጡ ካህናትና ምዕመናን መገኘታቸውን የቤተክርስቲያኒቷ የመገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ዘገባ ያመለክታል።
የጸሎት ሥነ ሥርዓቱ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና በገዳሙ ካህናትና ዲያቆናት መከናወኑ ተገልጿል።የብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ሥርዓተ ቀብር ነገ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓም በደብረ ብርሃን ከተማ በደብረ ብረሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚፈጸም ይሆናል።

5ኛው የኦዳ ሽልማት ስነስርዓት በአፋን ኦሮሞ የተሠሩ የኪነጥበብ ሥራዎችን በሙዚቃ፣ ፊልም እና ሥነ ጽሑፍ ዘውጎች ከ60 በላይ አርቲስቶችን በዕጩነት አቅርቦ በ20 ዘርፎች ሽልማትና እውቅና ሰጠ።
የ2013 5ኛው ዙር የኦዳ ተሸላሚ ከሆኑት፤ ከሴቶች መርጊቱ ወርቅነህ «ኦቦምቦሌቲ» በሚለው የቪዲዮ ክሊፕ ሙዚቃዋ፣ በዓመቱ ምርጥ የነጠላ ዜማ ዘርፍ ደግሞ «ደርቤ ላላ» በሚል ሙዚቃው ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ አሸናፊ ሆነዋል። በአመንሲሳ ኢፋ ዳይሬክተርነት የተዘጋጀው የድምጻዊ ገላና ጋሮምሳ «ወል-አጋራ» የሙዚቃ ክሊፕም በዓመቱ ከፍተኛ ተደማጭነት ያገኘ በሚል ተሸልሟል። የዓመቱ ምርጥ ቪዲዮ ክሊፕ ሽልማትን ደግሞ ሌንጮ ገመቹ «ሰግሊ» በሚል ሙዚቃው አሸንፎ ተሸላሚ ሆኗል።
በ2013 ዓ.ም. በአፋን ኦሮሞ የተሠሩ የአልበም ሥራዎች ሁለት ብቻ ሲሆኑ አርቲስት ሓጫሉ ሁንዴሳ «ማል መሊሳ» ለተሰኘው አልበሙ እንዲሁም ጅሬኛ ሽፈራው እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በፊልም ዘርፍ «ላፋፍ-ላፌ» የተሰኘው ሥራ የዓመቱ ምርጥ ሲባል በዚሁ ፊልም ከተወኑት አርቲስት አባቦ ወርቅነህ በምርጥ ሴት ተዋናይነት እንዲሁም አርቲስት ታምራት ከበደ ምርጥ ወንድ ተዋናይ በሚለው ዘርፍ ተሸልመዋል።
ቪዢን ኢንተርቴይመንት የዓመቱ ምርጥ ስቱዲዮ አሸናፊ ሲሆን፤ የዓመቱ ምርጥ ዳይሬክተር፣ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ፣ ምርጥ ጥምር ሙዚቃ እና በአጠቃላይ በ20 ዘርፎች እውቅና እና ሽልማቱ ተሰጥቷል። የሕይወት ዘመን ሽልማት ለሦስት አርቲስቶች የተሰጠ ሲሆን፤ በአፋን ኦሮሞ የኪነጥበብ ሥራዎች ጉልህ አሻራን አሳርፎ አምና ሕይወቱ ያለፈው ጋዜጠኛ እና የኪነጥበብ ሰው ኢብራሂም ሃጂ አሊ እውቅና ተሰጥቶታል።በተጨማሪም በአፋርኛ አርቲስት አሊዮ ያዮ እና በሲዳምኛ የክቡር ዶ/ር አርቲስት አዱኛ ዱቦ በኪነጥበብ ጉልህ አሻራን ያሳረፉ የሕይወት ዘመን ተሸላሚዎች ሆነዋል።
[DW]

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ የየካቲት ወር 2014ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ33.6 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
የምግብ ዋጋ ግሽበት የየካቲት ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ41.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በያዝነው ወር በአብዛኛው በእህሎች ዋጋ ጭማሪ የታየ ሲሆን በአንፃሩ የአትክልት ዋጋ ላይ ቅናሽ ታይቷል፡፡
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
የምግብ ዋጋ ግሽበት የየካቲት ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ41.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በያዝነው ወር በአብዛኛው በእህሎች ዋጋ ጭማሪ የታየ ሲሆን በአንፃሩ የአትክልት ዋጋ ላይ ቅናሽ ታይቷል፡፡
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በደላንታ ወረዳ በደረሰ እሳት አደጋ 52 ቤቶችና 1 መስጊድ ሙሉ ለሙሉ ወደሙ!
በደላንታ ወረዳ፤ 16 ቀበሌ ሰንበሌጥ ቆላ ልዮ ቦታው ሸንቦቆ ጉጥ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ትናንት የካቲት 29 ቀን 2014 ከቀኑ 5:30 ላይ በጥንቃቄ ጉድለት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ 52 ቤቶችና 1 መስጊድ ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ተገለፀ።
በመሆኑ አሁን ላይ እኒህ ጉዳት የደረሰባቸው ህብረተሰቦች የዕለት ምግብና ልብስ የሌላቸው በመሆኑ ሁላችንም ካለን በማካፍል ልንደርስላቸው ይገባል ሲል የወረዳው መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጠይቋል።

#BACK_TO_SCHOOL_AFRICA_EXPO_2022
Less than a month to go until this Global Hybrid expo & it will take place onsite at the magnificent Abrehot Library as well as Virtually.
Few spots left so make sure you book your booth. Click here and REGISTER NOW: www.backtoschoolafrica.com
If you are one of these, come join us:
Schools, Colleges & Universities, School Management Solution Providers, Software developers, App developers & Coders, Start-ups & TECH Entrepreneurs, Education Consultants, STEM Education Incubators, Digital Service Providers, Education Material Producers & Suppliers, Digital Libraries, NGOs & related.
For more info: +251 974 0820 36/37

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በይዲድያ አርት ሚኒስትሪ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው "ፈገግ ቢል " የተሠኘው ኘሮግራም በቅርብ ቀን!!!!
በቅርብ ቀን ይጠብቁ
በቅርብ ቀን ይጠብቁ
በ2011 ዓ.ም. በቻይና ሀገር ያላግባብ በአደንዛዥ እፅ ዝውውር ለተያዘችው ኢትዮጵያዊ ምክንያት የሆነችው ግለሰብ ተፈረደባት!
ናዝራዊት አበራ የተባለችውን ግለሰብ በታህሳስ ወር 2011 ዓ.ም. አደንዛዥ እፅ ወደ ቻይና እንድትወስድ ያደረገችው ስምረት ካሕሳይ የተባለች ተከሳሽ የ15 ዓመት እስራት እና የ100 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላለፈባት።
የፍትሕ ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ ቀርባ በሰጠችው ቃል መሰረት፣ “በዐቃቤ ህግ የተመሰረተብኝን ክስ ተረድቼዋለሁ፤ በተመሰረተብኝ ክስ ግን ጥፋተኛ አይደለሁም ምክንያቱም ለጓደኛዬ ለናዝራዊት አበራ የሰጠኋት የኮኬን ዕፅ ሳይሆን የፀጉር መታጠቢያ ሻምፖ ነው በዚህም ጥፋተኛ አይደለሁም” ስትል የእምነት ክህደት ቃሏን ሰጥታለች።
ይሁን እንጂ ዐቃቤ ህግ በተከሳሿ ላይ ስምንት የሰው እንዲሁም ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከኢሜግሬሽን ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጄንሲ የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቦ ጥፋተኛነቷን አሳይቷል ተብሏል። ተከሳሿም የሚቀጥለው ቀጠሮ ላይ ሳትገኝ ለጊዜው መሰወሯን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ተከሳሽ ስምረት ካህሳይ ልዩ ፍቃድ ሳይኖራት ህዳር 2011 ዓ.ም ወደ ሀገር ያስገባችውን 5 / አምስት / በሻምፖ እቃ የታሸገ ኮኬን ዕፅ ተበዳይ ናዝራዊት አበራ የተባለች ጓደኛዋን ወደ ቻይና ሀገር አብረን እንሂድ ብላ በማግባባት ቪዛ እና የአየር ትኬት ካስጨረሰች በኋላ ታህሳስ 11/2011 ዓ.ም ለናዝራዊት አበራ የሂውማን ሄር ማጠቢያ ነው ቻይና ውሰጅልኝ ብላ ከላከቻት በኋላ እርሷግን የአባቷን ሞት ምክንያት በማድረግ መቅረቷም ተገልጿል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ባስተላለፈበት የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ግለሰቦች እና ተቋማት ተከሳሿን ባገኙበት ወቅት ጥቆማ እንዲያደርጉ እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ ተከሳሿን አፈላልጎ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ በማዘዝ መዝገቡን ዘግቷል።

👍1
ዩክሬን ኃይሏን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮዎች ልታስወጣ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ላለው ውጊያ አቅሟን ለማጠናከር በአፍሪካ እና በአውሮፓ ፤ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ የሚገኙ ወታደሮቿን ፤ ትጥቅዋን እና ሄሊኮፕተሮችን ልታስወጣ ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የዩክሬን መገናኛ ብዙሃን እንዳስታቀው ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ያሉ የዩክሬን ወታደሮች እና መኮንኖች ወደ አገራቸው በመመለስ ከሩሲያ ጋር የገጠሙትን ጦርነት እንዲቀላቀሉ ትእዛዝ ሰጥተዋል ብሏል፡፡
ትልቁ የዩክሬናውያን ወታደራዊ ኃይል በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ሞኑጎ ውስጥ እያገለገሉ ሲሆን፤ሌሎች ዩክሬናውያን በማሊ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ቆጵሮስ እና ኮሶቮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ተልዕኮዎች ለመወጣት በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ይገኛሉ።ይሁን እንጂ የዩክሬን መንግስት ባቀረበው ጥሪ መሰረት ወታደሮቹ ትጥቃቸውን እና ሄሊኮፕተሮችን ይዘው ወደ ዩክሬን ሊመለሱ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
✍Ethio FM

የዩክሬን መንግስት ስንዴን ጨምሮ የምግብ አቅርቦቶች ለውጭ ገበያ እንዳይዉሉ እገዳ አስተላለፈ!
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በገባችበት ጦርነት ሳቢያ ሊከሰት የሚችለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመቋቋም ያግዛል በማለት የግብርና እና የአርብቶ አደር ውጤቶች ለውጭ ገበያ እንዳይዉሉ ወሰነች።ታይም የዜና ምንጭ እንደዘገበው በግብርና ምርቶች ለዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ተደራሽነት ከፍተኛ ሚና ያላት ዩክሬን በወቅታዊው ጦርነት ሳቢያ ምርቶች ለየትኛውም ሀገር እንዳይቀርቡ አሳስባለች።
ስንዴ፣ አጃ፣ ማሽላ፣ ስኳር፣ የቁም እንስሳትና ተዋፅኦዎቻቸውን ጨምሮ ለምግብነት የሚያገለግሉ በርካታ ምርቶችን ነው የዩክሬን የግብርና እና የምግብ ፖሊሲ ሚኒስቴር ያገደው።ይህ ውሳኔ ከዩክሬን ምርቶችን የሚያስገቡ የአውሮፓ፣ እስያ እና የአፍሪካ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል ተብሎ ተሰግቷል።
ስንዴ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከዓለም አምስተኛ ደረጃን የያዘችው ዩክሬን እ.ኤ.አ በ2019 ከ3 ቢልየን ዶላር በላይ በውጪ ንግድ ከስንዴ ማግኘት ችላለች። ግብፅ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ቱርክ እና ቱኒዝያ ደግሞ ዋነኛ የዩክሬን ስንዴ ደንበኞች ናቸው። ኢትዮጵያም ከዩክሬን ከፍተኛ የስንዴ ግዢ ከሚፈፅሙ ሀገራት አንዷ ስትሆን በ 2018 እአአ የ43 ሚልየን ዶላር ስንዴ ገዝታለች።
[@AddisZeybe]

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የተከሰተውን የዘይት አቅርቦትና ስርጭት ችግሮችን በአፋጣኝ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የንግድ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ አስታወቁ።
በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንዲቀርብ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡አቶ መስፍን አሰፋ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በከተማ ደረጃ የዘይት ምርት አቅርቦት ማነስና የዋጋ መጨመር መከሰቱን ጠቅሰው ነገር ግን የምርቱን አቅርቦትና ስርጭት ችግሮች ለመፍታት ከሀገር ውስጥ ዘይት አምራቾችና አቅራቢዎች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ነው።
ምርቱ ከዛሬ ጀምሮ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች በኩል ይሰራጫል። ፌቤላ የዘይት አምራች ድርጅት 3.1 ሚሊዮን ሊትር፤ሸሙ የዘይት አምራች ድርጅት 1.5 ሚሊዮን ሊትር፤የኢትዮጵያ ንግድ ስራ ኮርፖሬሽን 2 ሚሊዮን ሊትር ፓልም ዘይት በማቅረብ ስርጭት እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
የፌቤላ የዘይት ምርት 5 ሊትር ዋጋ 470 ብር፤ ሸሙ የዘይት ምርት 5 ሊትር ዋጋ 472 ብር እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ስራ ኮርፖሬሽን የዘይት ምርት 5 ሊትር ዋጋ 412 ብር መሆኑን ጠቁመው ከሰኞ ጀምሮ እስከዛሬ እሮብ ድረስ 674ሺ ሊትር ዘይት በህብረት ስራ ማህበራት በኩል እየተሰራጨ መሆኑን ጨምረው አስረድተዋል፡፡የሸገር ዳቦ ፍብሪካ በአዲስ መልክ ወደ ምርት የገባ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ የገንዘብ ድጎማ በማድረግ ምርቱ መጀመሩን ተጠቅሰዋል፡፡
[EPA]

የአፍሪቃ ቀንድ ሐገራትን በመታዉ ድርቅ ለረሐብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ መርጃ የሚያዉለዉ ገንዘብ አለማግኘቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።ድርጅቱ እንደሚለዉ ለጋሹ ዓለም ትኩረቱን ዩክሬን ጦርነት ላይ በማድረጉ ርዳታ ፈላጊዉ ሕዝብ ለከፋ ችግር እንዳይጋለጥ ያሰጋል።ድርጅቱ በተለይ ለሶማሊያ ችግረኞች መርጃ ከጠየቀዉ ገንዘብ እስካሁን ያገኘዉ 3 ከመቶ ብቻ ነዉ።
[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication

📌 ጥራት ያላቸው ኦሪጅናል የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከ T-max ኤሌክትሮኒክስ
ምርቶችቻችንን ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ:
👉 https://tttttt.me/tmaxelct
📌 አድራሻ: መርካቶ ይርጋ ሃይሌ ህንፃ ምድር ላይ ሱቅ ቁጥር፡ ጂ-96
ብዛት ለማዘዝ ይደውሉ
🤳 09 33 11 11 11 / 09 74 55 55 55
ምርቶችቻችንን ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ:
👉 https://tttttt.me/tmaxelct
📌 አድራሻ: መርካቶ ይርጋ ሃይሌ ህንፃ ምድር ላይ ሱቅ ቁጥር፡ ጂ-96
ብዛት ለማዘዝ ይደውሉ
🤳 09 33 11 11 11 / 09 74 55 55 55
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዩክሬን እና የሩሲያ የሰላም ተደራዳሪዎች ቱርክ ደረሱ!
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና የዩክሬኑ አቻቸው ድምትሮ ኩሌባ ለሰላም ንግግር ቱርክ ተገኝተዋል።
ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን በሚገኙበት ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቱርኳ አንታላይ ከተማ ዛሬ ንግግር ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቱርኩ ፕሬዝደንት ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚያደርጉት ውይይት፤ “ቋሚ ለሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት በር የሚከፍት ይሆናል ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ” ብለዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ወታደራዊ ወረራ ሁለት ሳምንት ሊሞላው የተቃረበ ቢሆንም እስካሁን የተደረጉ ንግግሮች ጦርነቱን ለማስቆም የሚያስችል ይህ ነው የሚባል ውጤት አላስገኙም።

39 በርሜል ነዳጅ በህገ ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ ከተማ ለማጓጓዝ የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ!
የንግድ ህጉን በመተላለፍ 39 በርሜል ነዳጅ በህገ ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ ከተማ ለማጓጓዝ የሞከሩ ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
የካቲት 27 ቀን 2014 ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ገርጂ ማርያም አካባቢ ከሚገኝ ኖክ ፈጣን ነዳጅ ማደያ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 A 10734 አ/አ በሆነ ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ 39 በርሜል ነዳጅ በመቅዳት ጭነው ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ ከተማ ሲያጓጉዙ የተገኙ ኹለት ግለሰቦችና ሁለት የማደያው ሰራተኞች ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ተይዘዋል፡፡
ፖሊስ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ በተወሰደ እርምጃ 50 በርሜል ተዘጋጅቶ ሰላሳ ዘጠኝ በርሜል ናፍጣ ተቀድቶ የተያዘ ሲሆን፤ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን እና የተያዘው ነዳጅ 7 ሺህ 800 ሊትር መሆኑን ተረግጧል፡፡
ግለሰቦቹ መመሪያ ቁጥር 12/2011 አንቀፅ 14 ንዑስ አንቀፅ 16 ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ምንም አይነት ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው ነዳጁን ለማጓጓዝ ሲሞክሩ መያዛቸውን ነው ፖሊስ ያስታወቀው።
ህገወጦቹ በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆ፤ መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሙ ጥቆማ የመስጠት ልምዱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ከአገር ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅማቸውን በማስቀደም የሚንቀሳቀሱ አካላት እና በህጋዊ የንግድ ፍቃድ ሽፋን ህገወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ከህገወጥ ተግባራቸው ሊታቀቡ እንዲሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።
@YeneTube