YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠ/ሚ ዐቢይ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሰብኣዊ እርዳታ ተደራሽነት ዙሪያ እንዲሁም በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳይ መወያየታቸውን ከተባበሩት መንግሥታት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢ ሕገ መንግሥታዊ አንቀጾች ከክልሎች ሕገ መንግሥት ውስጥ እንዲሻሩ ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጥያቄ ቀረበ!

በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ ህዳጣን ብሔረሰቦችን ‹‹መብት የሚጥሱና ከፌዴራሉ ሕገ መንግሥት ጋር የሚቃረኑ›› የተባሉ በስምንት ክልሎች ሕገ መንግሥቶች ውስጥ የሚገኙ አንቀጽና ንዑስ አንቀጾች እንዲሻሩ፣ ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጥያቄ ቀረበ፡፡

ጥያቄ የተነሳባቸው በሶማሌ፣ በአፋር፣ በሐረሪ፣ በሲዳማ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብና በጋምቤላ ክልሎች ሕገ መንግሥቶች ውስጥ የሚገኙ አንቀጾችና ንዑስ አንቀጾች ናቸው፡፡ በተጨማሪም ከሱማሌ፣ ከደቡብና ከጋምቤላ ክልሎች ውጪ ያሉት ሌሎች የተጠቀሱ ክልሎች ሕገ መንግሥት መግቢያም አቤቱታ ቀርቦበታል፡፡

ጥያቄውን ያቀረበው የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች የተሰኘ አገር በቀል የሲቪል ማኅበር፣ በአቤቱታው ላይ የተጠቀሱ የሕገ መንግሥቶቹ ክፍሎች በክልሎቹ ውስጥ የሚኖሩ ህዳጣን ማኅበረሰቦችን የፖለቲካ ተሳትፎ መብቶች የሚገድቡ ስለመሆናቸው በጥር ወር ለጉባዔው ባስገባው የ15 ገጽ ማመልከቻ አብራርቷል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ : http://bit.ly/34mLaig

@YeneTube @FikerAssefa
የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራው እንደሚመለስ ተገለፀ።

በስንዴ ዋጋ መጨመር ምክንያት አቅርቦቱ ቀንሶ የነበረው የሸገር ዳቦ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ወደ አቅርቦት ስራው እንደሚመለስ ተገልጿል።ፋብሪካው ወደ ስራ እንዲመለስ በእያንዳንዱ ዳቦ ላይ የከተማ መስተዳድሩ 1 ብር ከ 14 ሳንቲም ድጎማ ማድረጉን የተገለፀ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ በአመት 613 ሚሊየን ብር ድጎማ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ናቸው የገለፁት።

ከዚህ ሳምንት ጀምሮም በ 2ብር ከ 10 ሳንቲም መከፋፈሉን እንደሚቀጥል ተገልጿል።

መንግስት ካደረገው ድጎማ በተጨማሪ የተወሰነ የዋጋ ማሻሻያ በማስፈለጉ ከዚህ በፊት ይቀርብበት ከነበረው የዋጋ መጠን ጭማሪ ተደርጎ ወደ ማከፋፈል ሂደቱ እንደሚገባ ተገልጿል።ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ምርት ሂደቱ በመግባት በቀን ከ700 እስከ 800 ሺህ ዳቦ በማምረት በአዲስ አበባ እና ዙሪያው ባሉት ከ400 በላይ ሱቆቹ ምርቱን ያከፋፍላል ተብሏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ከሰኔ 15 ክስተት ጋር ተያይዞ ከሕዳር 23/2012 ዓ.ም ጀምሮ ጉዳያቸው በፍርድ ሂደት ሲታይ የቆዩ ተጠርጣሪዎች ጥፋተኛ በተባሉ 31 ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ጥፋተኛ በተባሉ 31 ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ችሎቱ በእያንዳንዳቸው ተከሳሾች ላይ ከእድሜ ልክ እስከ 15 ዓመት ጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ ነው ያስተላለፈው፡፡

ከቅጣት ውሳኔው በፊት በተከሳሾች የቀረበውን የቅጣት ማቅለያ ተቀብሎ የመረመረው ችሎቱ ለአራት ተከሳሾች አምስት ማቅለያዎችን፣ ለ20 ተከሳሾች አራት ማቅለያዎችን፣ ለአራት ተከሳሾች ሦስት ማቅለያዎችን እና ጉዳያቸው በሌሉበት ሲታይ የቆዩ ሦስት ተከሳሾችን ደግሞ አንድ ማቅለያ ተቀብሏል፡፡

ማኅበራዊ አገልግሎት፣ የቤተሰብ ኀላፊነት፣ ሕመም፣ ወንጀሉን ከመፈጸማቸው በፊት የነበራቸው ለሀገር የተከፈለ ዋጋ እና ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መኾኑ በቅጣት ማቅለያነት ታይቷል፡፡

ችሎቱ ጉዳያቸው በሌሉበት ሲታይ የቆየውን የሻምበል መማር ጌትነት፣ በላይሰው ሰፊነው እና ልቅናው ይሁኔ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በሌሎች 28 ተከሳሾች ላይ ደግሞ ከ15 ዓመት እስከ 18 ዓመት ጽኑ እስራት አስተላልፏል፡፡18 ተከሳሾች በ16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት፣ ሁለት ተከሳሾች በ15 ዓመት ጽኑ እስራት፣ ሁለት ተከሳሾች 16 ዓመት፣ አራት ተከሳሾች በ18 ዓመት እና ሁለት ተከሳሾች በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

Via AMC
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን ለሩሲያ የባሕር ኃይል መደብ መገንቢያ ወደ መፍቀዱ በማዘንበሏ ግብፅ ተከፍታለች ተባለ፡፡

የሱዳን ገዢ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ጄኔራል ሐምዳን ዳግሎ ሩሲያ በሱዳን የባሕር ኃይል መደብ ብትመሰርት ምንም ችግር የለብንም ማለታቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር አስታውሷል፡፡ዳግሎ በቅርቡ በሩሲያ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

ጄኔራሉ ስለ ሩሲያ የባሕር ኃይል መደብ ጉዳይ ያደረጉት ንግግር የግብፅ ባለሥልጣናትን አስደንግጧቸዋል ተብሏል፡፡

ግብፅ የሩሲያ ባሕር ኃይል መደብ በሱዳን መቋቋሙን ለቀይ ባሕር ቀጠና ደህንነት ሥጋት አድርጋ እንደምትቆጥረው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡በዚህም የተነሳ የግብፅ ሹሞች የሱዳኑን ወታደራዊ መንግስት ምክትል መሪ ጄኔራል ሐምዳን ዳግሎን ማብራሪያ መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡

Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) በአንድ ባንክ ውስጥ በርከት ያለ ሂሳብ የያዙ ግለሰቦችን ወይም ድርጅቶችን በማቀላቀል ወደ አንድ የባንክ ሂሳብ እንዲያወርዱ ባንኮችን አዘዘ!

በነበረው አሰራር አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት በተመሳሳይ ባንክ ለምሳሌ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ቅርንጫፎች ከአንድ በላይ ሂሳብ ሊከፍት ወይም ሊኖረው ይችል ነበር፡፡ ይህ ግለሰብ ወይም ድርጅት በተመሳሳይ ባንክ ውስጥ በርካታ ሂሳቦች እንዲኖሩት አድርጓል፤ በጠቅላላው በባንኮች የተከፈቱ ሂሳቦች እንዲበራከቱ ማድረጉን ባለሞያዎች ይገልፃሉ፡፡ ይህም ለቁጥጥር አመቺ አይሆንም ነው የሚሉት በፋይናንስ ደህንነት ላይ የሚሰሩ ባለሞያዎች፡፡በመሆኑም የተበታተኑ ሂሳቦች ወደ አንድ መውረዳቸው መልካም እንደሆነ ይጠቅሳሉ፡፡በኢብባ ውሳኔ መሰረት ባንኮች ደንበኞችን በመጥራት የተበራከቱ ሂሳቦቻቸውን ወደ መረጡት ግን አንድ ሂሳብ እንዲያቀላቅሉ የማድረግ ስራ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እያከናወኑ ነው፡፡ ካፒታልም በባንክ ቅርንጫፎች በመሄድ ይሄን አረጋግጫለሁ ብላለች ፡፡

በኢብባ መረጃ መሰረት በአገሪቱ ከ72.3 ሚሊየን በላይ የቁጠባ ሂሳቦች ይገኛሉ፡፡
የፋይናንስ ዘርፉን ከማዘመን እና ከስጋት የፀዳ ለማድረግ ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ የሆነው እና ደንበኛን ማወቅ የሚለው ስራ ላለፉት 6 ወራት ሲከናወን ቆይቶ ከሳምንት በፊት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ ባለፈው ነሃሴ ኢብባ ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት ባንኮች ደንበኞችን በመጥራት እንደ ፎቶ እና መታወቂያ የመሳሰሉ ሙሉ መረጃዎችን ከደንቦች ማህደር ጋር የማዋሃድ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በመመሪያው መሰረት በቂ መረጃ የሌላቸው እና በተጠቀሰው ጊዜ ማቅረብ ያልቻሉ ደንበኞችን ሂሳብ ባንኮች ለብሄራዊ ባንክ እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
#BACK_TO_SCHOOL_AFRICA_EXPO_2022

Less than a month to go until this Global Hybrid expo & it will take place onsite at the magnificent Abrehot Library as well as Virtually.

Few spots left so make sure you book your booth. Click here and REGISTER NOW: www.backtoschoolafrica.com

If you are one of these, come join us:
Schools, Colleges & Universities, School Management Solution Providers, Software developers, App developers & Coders, Start-ups & TECH Entrepreneurs, Education Consultants, STEM Education Incubators, Digital Service Providers, Education Material Producers & Suppliers, Digital Libraries, NGOs & related.

For more info: +251 974 0820 36/37
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በይዲድያ አርት ሚኒስትሪ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው "ፈገግ ቢል " የተሠኘው ኘሮግራም በቅርብ ቀን!!!!

በቅርብ ቀን ይጠብቁ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፓሊስ በአዲስ አበባ ጅምላ እስር እያካሄደ ነው ሲል ማምሻውን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ፓርቲው መንግሥት ምንሊክ አደባባይን ይፋዊ የአድዋ ድል መታሰቢያ ቦታ እንዲያደርግ፣ በካራማራ ድል በዓል አከባበር ላይ የታሠሩ 34 የፓርቲው አባላት እና ከቤታቸው እየታፈሱ ያሉ በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችን እንዲፈታ፣ የፍትህ ሥርዓቱን የፖለቲካ መጠቀሚያ ከማድረግ እና ሕዝብን ሆን ብሎ ከመተናኮል እንዲቆጠብ እና ሕዝብ ለሚያነሳው የኑሮ ውድነት ችግር መልስ እንዲሰጥ ጠይቋል። መንግሥት ይህን ካላሟላ ግን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት እንደሚገደድ ፓርቲው አስጠንቅቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በቡድን እና በተናጠል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ 21 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በቡድን ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ 21 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ። የልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ከክትትል ክፍሉ ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት በ3 ቡድን የተደራጁ 16 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል።

በተመሳሳይ በተናጠል የመኪና ስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 5 ግለሰቦችንም በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ያሬድ አለማየሁ በከተማዋ በተለያየ ጊዜ ተሽከርካሪዎች ተሰርቀው አካላቸው ተበታትኖ ለሽያጭ መቅረባቸው እንደተደረሰበት ገልፀዋል።

በዚህም በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ የተሰረቁ ተሽከርካሪዎችን ማስመለስ መቻሉንም ዋና ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል።

በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በተደረገ ሰፊ ምርመራ እና ክትትል 9 ተሽከርካሪዎች መሰረቃቸውን በማረጋገጥና ከያሉበት በማስመለስ ተጠርጣሪዎች በ10 መዝገቦች ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሆነ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የተሽከርካሪ ባለንብረቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆይ ባይደን ሀገራቸው ከራሺያ ነዳጅ ከዛሬ ጀምሮ ማስገባት እንደምታቆም አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኤርትራውያን ዳያስፖራዎች ኤሎን መስክ ለሀገራቸው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያደርስላቸው እየተማፀኑ ይገኛሉ።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ በኤርትራ የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት ከ1% አያልፍም። ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ኤርትራውያን ዳያስፖራዎች የአለም ባለፀጋው ሰው ስታርሊንክ ሳተላይትን በመጠቀም ለዩከሬናዊያን እንዲጠቀሙበት እንደፈቀደው ሁሉ ለኤርትራውያንም እንዲፈቅድላቸው እየተማፀኑት ሚገኙት።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
👍1
Forwarded from YeneTube
📌 ጥራት ያላቸው ኦሪጅናል የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከ T-max ኤሌክትሮኒክስ
ምርቶችቻችንን ለማየት ሊንኩን ይጠቀሙ:
👉 https://tttttt.me/tmaxelct

📌 አድራሻ: መርካቶ ይርጋ ሃይሌ ህንፃ ምድር ላይ ሱቅ ቁጥር፡ ጂ-96
ብዛት ለማዘዝ ይደውሉ
🤳 09 33 11 11 11 / 09 74 55 55 55
በሶማሌ ከልል 11 ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለአስቸኳይ ዕርዳታ መጋለጡን የሶማሌ ክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ቢሮ አስታወቀ።

በድርቁ ከአንድ ሚሊዮን በላይ እንስሳት መሞታቸውም ተገልጿል።የሶማሌ ክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዲፈታህ መሓመድ አብዲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በሶማሌ ክልል በ2013 ዓ.ም ሚያዚያና ግንቦት ወራት መጣል የነበረበት ዝናብ ባለመጣሉና በዘንድሮውም ዓመት በጥቅምትና በህዳር ወራት መደበኛ ዝናብ ባለመዝነቡ በክልሉ 11ድ ዞኖች ድርቅ ተከስቷል።

በሁሉም የክልሉ ዞኖች በተከሰተው ድርቅ ከሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአስቸኳይ ዕርዳታ ሲጋለጡ፤ ከአንድ ሚሊዮን በላይ እንስሳት ደግሞ መሞታቸውን ገልጸዋል።በቀጣዮቹ መጋቢትና ሚያዚያ ወራት የሚጠበቀው ዝናብ ካልተገኘ ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሻቅብ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት አጋርተዋል።
የድርቁ ሁኔታም እየከፋ ከሄደ ክልሉ ካለው ስምንት ሚሊዮን የእንስሳት ሃብት አብዛኛውን ሊያጣ እንደሚችልም ተናግረዋል።

ሙሉውን ለማንበብ:
https://www.press.et/ama/?p=68235

@YeneTube @FikerAssefa
የሸገር ዳቦ በ2ብር ከ 10 ሳንቲም ለገበያ መቅረብ ሊጀምር ነው!

ስራ አቋርጦ የነበረው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራው የሚገባ ሲሆን ወደስራ ሲገባ የዋጋ ማሻሻያ በማድረግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።የሸገር ዳቦ በስንዴ ዋጋ መጨመር እና በፋብሪካው ዓመታዊ የማሽንች ጥገና ስራ እንዳቆመ በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል መኤሶ ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩ ሲሆን የሸገር ዳቦ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ወደ አቅርቦት ስራው እንደሚመለስ ገልፀዋል።

ፋብሪካው ወደ ስራ እንዲመለስ በእያንዳንዱ ዳቦ ላይ የከተማ መስተዳድሩ 1 ብር ከ 14 ሳንቲም ድጎማ ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ 613 ሚሊየን ብር ድጎማ በዓመት እንደሚያደርግ አብራርተዋል።መንግስት ካደረገው ድጎማ በተጨማሪ የተወሰነ የዋጋ ማሻሻያ በማስፈለጉ ከዚህ በፊት ይቀርብበት ከነበረው የዋጋ መጠን ጭማሪ ተደርጎ ወደ ማከፋፈል ሂደቱ እንደሚገባ ተገልጿል።

ከዚህ ሳምንት ጀምሮም በ2ብር ከ 10 ሳንቲም መከፋፈሉ ይጀምራል።ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ምርት ሂደቱ በመግባት በቀን ከ700 እስከ 800 ሺህ ዳቦ በማምረት በአዲስ አበባ እና ዙሪያው ባሉት ከ400 በላይ ሱቆቹ ምርቱን ያከፋፍላል ተብሏል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት በስፋት ተዘግቦ የነበረው "40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ሊገዛ ነው" ዜና ትክክል እንዳልሆነ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል!

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ንግድ ቢሮዎች ጋር በመሆን ሰኞ እለት በሰጠው መግለጫ40 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ግን የ40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዥ ስምምነት አለመፈጸሙን አስታውቆ ጉዳዩ በጅምር ላይ ያለና ጥናት እየተካሄደበት መሆኑን ገልጿል፡፡

Via Reporter newspaper
@Yenetube @Fikerassefa
“የ2014 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና መስጫ ቀን አልተቆረጠም”--- የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በተያዘዉ የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች “የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከግንቦት 22 - 25/ 2014 ዓ.ም ይሰጣል” የሚል መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ የገኛል። መረጃዉ በተማሪዎች ዘንድ ግርታን እየፈጠረ እንደሆነም ተመልክተናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሆኑትን አቶ ቤከማ ስለሺ አናግሯል።

እርሳቸዉም “የ2014 /ፈተና/ መቼ እንደሚሰጥ አልታወቀም። ቀኑ አልተቆረጠም፤ ስለ ፈተናዉ ቀንም የተባለ ነገር የለም” ብለዋል። በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ያለዉ (ፈተናዉ ከግንቦት 22 - 25/ 2014 ዓ.ም ይሰጣል) የሚለዉ መረጃም በተቋሙ እዉቅና እንደሌለዉ ነግረዉናል።

“ፈተና የሚሰጥበት ቀን ሲቆረጥና ሲታወቅ በሚዲያዎች መግለጫ ይሰጣል” ብዋል አቶ ቤከማ ስለሺ።

Via EthiopiaCheck
@YeneTube @FikerAssefa
ግሎኬር ፋርማ ማኑፋክቸሪንግ የተሰኘው የህንድ ኩባንያ መድኃኒት ማምረት ጀመረ!

ግሎኬር ፋርማ ማኑፋክቸሪንግ የተሰኘው የህንድ ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ባስገነባው ፍብሪካው መድኃኒት ማምረት ጀምሯል።በመድሀኒት ማምረትና ማዘጋጀት ስራ ላይ የተሰማራው ይህ ኩባንያ ግንባታውንና ቅድመ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ምርት ጀምሯል።

በምርት ማስጀመሪያና በፋብሪካ ምረቃ ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ፤ የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

የፋብሪካው የመጀመሪያው ምእራፍ 5 ሚሊዮን ዶላር የፈጀ ሲሆን በቀጣይ እስከ 2.5 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚጠይቁ የፋብሪካው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ምእራፍ ግንባታዎች ይከናወናሉ ተብሏል።ፋብሪካው በአጠቃላይ 36 አይነት መድሀኒቶችን እንደሚያመርት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa