YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሩሲያና የዩክሬን ባለሥልጣናት የተጀመረውን ጦርነት ለማብቃት ያቀዱት ውይይት ዩክሬን ከቤላሩስ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር ላይ ተጀምሯል።

ውይይቱ በሁለቱ አገራት ባለሥልጣናት መካከል መጀመሩን የሚያመለክቱ ምስሎች እየወጡ ነው።ከስብሰባው ቀደም ብሎ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በአስቸኳይ ተኩስ እንዲቆምና የሩሲያ ወታደሮች ከግዛታቸው እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በሩሲያ በኩል ደግሞ በውይይቱ ሁለቱንም አገራት የሚጠቅም ስምምነት እንዲደረስ ፍላጎት እንዳለ ተገልጿል።አምስተኛ ቀኑን የያዘው የሩሲያ ወረራ ከሁለቱ አገራት አልፎ ምዕራባውያንን ከሩሲያ ጋር ፍጥጫ ውስጥ የከተተ ሲሆን፣ ሩሲያ የኑክሌር ኃይሏ በተጠንቀቅ እንዲቆም ማዘዟ ዓለምን ስጋት ውስጥ ከቷል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ተቃዋሚው የአፋር ሕዝብ ፓርቲ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በኃይል ከተቆጣጠሯቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ባስቸኳይ እና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲወጡ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ግፊት እንዲያደርግ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መግለጫ ጠይቋል። ፌደራል መንግሥቱ በአፋር ሕዝብ ላይ እየደረሰ ስላለው ሰቆቃ ዝምታን መርጧል ያለው ፓርቲው፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ በክልሉ ለተከሰተው አጣዳፊ ሰብዓዊ ቀውስ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲለግስ ጥሪ አድርጓል። የአፋር ክልል በርካታ አካባቢዎች በሕወሃት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር እያሉ፣ መንግሥት ከሕወሃት ጋር የተናጥል ድርድር የሚያደርግ ከሆነ ፓርቲው እንደማይቀበለውም መግለጫው አውስቷል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
የዐማራ ቅርስ ያሏቸው አካባቢዎችን ለድርድር ማቅረብ ተቀባይነት የለውም ሲሉ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ተቃወሙ።

የማኀበረሰብና የሚዲያ 24 ድርጅቶች ያወጡትን መግለጫ አስመልክቶ ተወካያቸው ኢንጂነር ሕዝቅኤል እስክንድር ለዶይቸ ቨለ፣ ወልቃይት፣ ራያና አካባቢው ከሕገ መንግሥት ዕውቅና ውጭ በህወሓት ተወስደው የነበሩ መሬቶች ሲሆኑ  ለድርድር ከቶውንም ሊቀርቡ አይችሉም ሲሉ ገልጸዋል።የትግራይ ክልልን በመወከል በውጭ የሚንቀሳቀሰው ኮሚቴ አባልና የቀድሞ ዲኘሎማት ዮሐንስ አብርሃ በበኩላቸው፣ የይገባኛል ጥያቄ የተነሳባቸው ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ከ30 በላይ የትግራይ ቀበሌዎች ዐማራ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል።የመንግሥት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሠ ቱሉ ጉዳዩን አስመልክቶ ዶይቸ ቨለ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ የተጠቀሱትን አካባቢዎች በተመለከተ መንግሥት የሚያካሄደው ድርድር እንደሌለ አስታውቀዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የሩሲያ እና የዩክሬን የመጀመሪያ ዙር ውይይት ተጠናቀቀ!

የሩሲያ ሠራዊት በዩክሬን ላይ ወረራ ከከፈተ ከአምስት ቀናት በኋላ የሁለቱ አገራት ባለሥልጣናት በጎረቤት ቤላሩስ ውስጥየ ጀመሩት ውይይት ተጠናቀቀ።ዩክሬን ውስጥ በሩሲያና በዩክሬን ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ እንደቀጠለ ባለበት ሁለቱ አገራት ለጦርነቱ መፍትሔ ለመፈለግ ነው ውይይት የፈለጉት።

የሁለቱ አገራት ተደራዳሪዎች የመጀመሪያ ቀን ውይይታቸውን አጠናቀው ሁለተኛውን ዙር ድርድር ከመጀመራቸው በፊት ለምክክር ወደ ዋና ከተሞቻቸው ተመልሰዋል።ቀጣይ ውይይት በመጪዎቹ ቀናት እንደሚቀጥል ሮይተርስ የዜና ወኪል የቤላሩስ የዜና ማሰራጫ የሆነውን ቤልታ ኒውስን ጠቅሶ ዘግቧል።

ዛሬ ሰኞ ከተደረገው የሁለቱ አገራት ባለሥልጣናት ውይይት ቀደምብሎ ለጦርነቱ ሰላማዊ መፍትሔ ይገኛል የሚለው ተስፋዝቅተኛ ነበር።ከውይይቱ ቀደም ብሎ ተኩስ አቁም እንዲደረግና የሩሲያ ወታደሮች ከግዛቷ ለቀው እንዲወጡ ዩክሬን የጠቀች ሲሆን፣ ሩሲያ ግን ፍላጎቷ ምን እንደሆነ በይፋ ያስቀመጠችው ነገር የለም። ነገር ግን የሩሲያ ተደራዳሪዎች በውይይቱ የሁለቱንም አገራት ጥቅም የሚያስከብር ስምምነት ላይ ለመድረስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ11 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ!

አግባብነት ባላቸው የትምህርት ክፍሎች ተመርመሮ፣ በየኮሌጆች አካዳሚክ ጉባዔዎች ተፈትሾ፣ አጥጋቢ በሆነ መልኩ በባለሙያ ተገመግሞ በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ እና ይሁንታ አግኝቶ የቀረበለትን የሙሉ ፕሮፌሰርነት መረጃ የተመለከተው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ
1. ዶ/ር ቁምላቸው የሺጥላ
2. ዶ/ር ሽመልስ አሰፋ
3. ዶ/ር መንግስቱ ለገሰ
4. ዶ/ር ጉታ ዘነበ
5. ዶ/ር ፋሲል አሰፋ
6. ዶ/ር ጥልዬ ፈይሳ
7. ዶ/ር ብሩክ ላምቢሶ
8. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
9. ዶ/ር ዘበነ ክፍሌ
10. ዶ/ር ተረፈ ደገፋ እና
11. ዶ/ር ንጉሴ ደዬሳን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፅድቋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሚሰጣቸው ምሑራን በመማር ማስተማሩ፣ በጥናትና ምርምር፣ በዩኒቨርስቲ ውስጥ አገልግሎት እንዲሁም በማህበረሰብ አቀፍና ሙያዊ አገልግሎት በዩኒቨርስቲው ሴኔት ሌጅስሌሽን መሰረት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ለተወጡ እና ለዓለም የዕውቀት ስርዓት መዳበር ስኬታማ አበርክቶ ላደረጉ መምህራን እና ተመራማሪዎች መሆኑንም ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የባሕልና ቱሪዝም ሚንስቴር የዘንድሮው የታላቁ አድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ በአድዋ ድልድይ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ እንደሚከበር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ሚንስቴሩ በዓሉን በአድዋ ድልድይ የሚያከብረው ከኦሮሚያ ክልል እና ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር በመተባበር እና "አድዋ ለኢትዮጵያ ኅብረት፣ ለአፍሪካዊያን የነጻነት ጮራ" በሚል መሪ ቃል እንደሆነ ገልጧል። የአድዋ ድል በዓል ላለፉት በርካታ ዓመታት ሲከበር የኖረው ግን በፒያዛ የአጼ ምንሊክ ሐውልት በሚገኝበት አደባባይ እንደሆነ ይታወቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
አፍሪካዊያን በዩክሬን ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተነገረ፡፡

ዩክሬን ውስጥ የሚገኙ የውጭ ሃገር ዜግነት ያላቸው ዜጎች ወደ ጎረቤት ሀገራት ድንበር አቋርጠው መውጣት የተፈቀደላቸው ሲሆን አፍሪካዊያን ይህ እድል ተነፍጓቸዋል ተብሏል፡፡በዩክሬን የሚገኙ አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮች ወደ ፖላንድ ያቀኑ ሲሆን አፍሪካዊያን ግን እዛው ዩክሬን እንዲቆዩ ተገደዋል፤በዚህ የተነሳም ዜጎቹ ጎዳና ማደሪያቸው አድርገዋል ሲል አልጀዚራ አስነብቧል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የናይጄርያ መንግስት የአፍሪካዊያን መብት ሊከበር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡አፍሪካዊያን ችግር ባለባቸው ሀገራት መብታቸው እየተነፈገ እና ለችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ ይህ አይነት አስተሳሰብ መለወጥ አለበት ሲሉ የናይጄርያው ፕሬዝዳንት ማማዱ ቡሀሪ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ዩክሬንን ለቀው ወደ ፖላንድ የገቡ ዜጎች ቁጥር 286ሺህ ሲሆን ወደ ሃንጋሪ የገቡ ዜጎች ቁጥር ደግሞ 87ሺህ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ወደ ሞልዶቫ እና ሮማኒያ ያቀኑ ዜጎች ቁጥር ደግሞ 56ሺህ ይጠጋሉ ሲል አልጀዚራ አስነብቧል፡፡

Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የቤት ዕጣ የወጣላቸው ሰዎች በወቅቱ ባለመረከባችን የ500 ሺሕ ብር ጉዳት ደርሶብናል አሉ!

በአዲስ አበባ ለሚኩራ ክፍለ ከተማወረዳ አራት ቦሌ በሻሌ በሚባለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንደር፣ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ የወጣላቸው ሠዎች፣ ቤቶቹን በወቅቱ ባለመረከባቸው ከ500 ሺሕ ብር በላይ ጉዳት እንደደረሠባቸው ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡

ዕጣ የወጣልን የካቲት 27/2011 ሲሆን፣ በመጭው የካቲት 27/2014 ሦስት ዓመት ይሞላናል የሚሉት ሥሜ አይጠቀስ ያሉ ግለሰብ፣ ቤቱን በወቅቱ ባለመረከባችን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አንድ ሰውበወር አምስት ሺሕ ብር የቤት ከራይ እንኳ ከፍሏል ተብሎ ቢታሠብ፣ ከ180 ሺሕ ብር ያላነሰ ወጭ ለቤት ኪራይ አውጥተናል ነው ያሉት፡፡

Via Addis Malede
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡባዊ ዩክሬን የምትገኘው የኬርሶን ከተማ በሩሲያ ጦር ተከባለች!

በደቡባዊ ዩክሬን የምትገኘው የኬርሶን ክልላዊ ማእከል በሩሲያ ወታደሮች መከቧን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የሩስያ ወታደሮች ዛሬ ማለዳ ላይ በሞስኮ ቁጥጥር ስር በምትገኘው ክሬሚያ አቅራቢያ በምትገኘው የኬርሶል ከተማ ላይ የምድር ጥቃት መጀመራቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል።

የከተማይቱ ከንቲባ ኢጎር ኮላይካዬቭ "የሩሲያ ጦር በኬርሶን መግቢያዎች ላይ የፍተሻ ኬላዎችን እያዘጋጀ ነው" በማለት በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። አክለውም ኬርሶን ምንጊዜም የዩክሬን ናት የዩክሬንም ሆና ትቆያለች" ብለዋል።

"ከተማዋ በሩሲያ ጦር ተከባለች። በሁሉም አቅጣጫ በኩል በርካታ የሩሲያ ወታደሮች እና የጦር መሳሪያዎች አሉ። የሩሲያ ኃይሎች በመውጫዎቹ ላይ የፍተሻ ኬላዎችን አዘጋጅተዋል" በማለት በኬርሶን መቀመጫውን ያደረገው አሌና ፓኒና በብሔራዊ ብሮድካስቲንግ ጣቢያው ዩክሬን 24 ላይ ተናግሯል።

ጋዜጠኛው አክሎም በኬርሶን አሁንም መብራት፣ውሃ እና ማሞቂያ እንዳለ ገልጾ ነገር ግን ምግቡ በከተማዋ ዳርቻ በሚገኙ መጋዘኖች ውስጥ የተከማቸ በመሆኑ 300 ሺህ ለሚሆነው የከተማዋ ነዋሪ ምግብ በማምጣት ረገድ ተግዳሮቶች እንዳሉ ገልጿል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳናውያን ወታደራዊ መንግስታቸውን በመቃዎም አሁንም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡

ባለፈው አመት የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን በካርቱም ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግስት ፊት ለፊት ባደረጉት ሰልፍ አንድ ሱዳናዊ ተቃዋሚ በጥይት ተመትቶ መሞቱን የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ጄኔራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን ባለፈው አመት ጥቅምት 25 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ካደረጉ በኋላ በተደረጉ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፎች የሞቱ ሰዎች ቁጥር 84 መድረሱን ገለልተኛ የህክምና ባለሙያዎች ቡድን አስታውቋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰባዊ መብት ባለሙያ የሆኑት አዳማ ዲንግ ወደ ሱዳን በሄዱበት ወቅት የሱዳን ባለሥልጣናት በተቃዋሚዎች ላይ የሚወስዷቸው እርምጃዎች እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በተመሳሳይ የሱዳን ተቃዋሚዎች ጉዳይ እንደሚያሳስበው የገለፀ ሲሆን ሁከቱ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ተጨማሪ መዘዞች ሊመጡ እንደሚችሉ ያለውን ስጋት ገልጿል፡፡

የሱዳን የቅርብ ጊዜ መፈንቅለ መንግሥቱ ሰፊ ዓለም አቀፍ ውግዘት እያጋጠመው ሲሆን ሀገሪቱ ያላት ዲፕሎማሲየዊ ግንኙነት እንዲቀዛቀዝ ምክንያት መሆኑን አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስታውቋል፡፡

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
ማሳሰብያ

በኦንላይን ቅሬታ ያቀረባችሁ የብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ያቀረባችሁት ቅሬታ መልስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡-
www.neaea.gov.et:8080 በመግባት የምታገኙ መሆኑን እንገልፃለን።

ቅሬታችሁን በአካል ያቀረባችሁ ቅሬታ አቅራቢዎች ምላሹ በስልክ ተደውሎ የሚነገራችሁ ይሆናል፡፡

ምላሽ ያልተሰልጣችሁ ቅሬታ አቅራቢዎች ለአገልግሎቱ የቀረቡት ቅሬታዎች እጅግ በጣም ብዙ ስለሆኑ በትእግስት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን፡፡
126ኛ የአድዋ ድል በዓል በነገው ዕለት “አድዋ ለኢትጵያዊያን ህብረት፤ ለአፍሪካ የነጻነት ጮራ!” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል!

126ኛ የአድዋ ድል በዓል በነገው ዕለት “አድዋ ለኢትጵያዊያን ህብረት፤ ለአፍሪካ የነጻነት ጮራ!” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡ የዘንድሮውን የአድዋ ድል በዓል እንደሁል ጊዜው በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ አስታውቋል።

የአከባበሩም ሁኔታ እንደተለመደው የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስተ የሥራ ሃላፊዎች፣ አባት አርበኞች እና መላው የከተማዋ ነዋሪ በሚገኝበት በእግር ጉዞና በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች ከሚኒሊክ አደባባይ እስከ አድዋ ድልድይ ይከናወናል ተብሏል፡፡

በዚሁ መሰረት በማለዳ በሚኒሊክ አደባባይ በሚደረገው የመክፈቻ ዝግጅት ተጀምሮ ወደ ሌላኛው ታሪካዊ ቦታ ወደ አድዋ ድልድይ በእግር ጉዘ የሚቀጥል ይሆናል መባሉን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡ በመጨረሻም አድዋ ድልድይ ጋር በሚደረጉ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚጠናቀቅ የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሩሲያ በኪዬቭ ዒላማዎችን ልትመታ እንደሆነ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

የሩሲያ ሠራዊት በዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ የሚገኙ ዒላማዎችን ለመምታት እየተዘጋጀ መሆኑን የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ለከተማዋ ነዋሪዎች ማስጠንቀቂያ አወጣ።ዛሬ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ የሩሲያ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ባወጡት መግለጫ ኃይሎቻቸው “ዒላማቸውን ለይተው ለመምታት” ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የዚህ ጥቃት ዋነኛ ዒላማ እንደሚሆኑ የተነገረላቸው ደግሞ “ኪዬቭ ውስጥ የሚገኙት የዩክሬን የደኅንነት አገልግሎት እና ዋነኛው የመረጃ ጥቃት ማዕከል” መሆናቸውንም መግለጫው አመልክቷል።መግለጫው ጨምሮም “ብሔረተኞች አማካይነት በሩሲያ ላይ ትንኮሳ የሚፈጽሙ” ያላቸውን የዩክሬን ዜጎችን ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፣ እንዲሁም ኢላማ በሆኑት ተቋማት አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችም ከቤታቸው እንዲርቁ አሳስቧል።

የሩሲያ ባለሥልጣንት ይህንን ጥቃት ለመፈጸም የተዘጋጁት ከዩክሬን በኩል “በሩሲያ ላይ የሚፈጸሙ የመረጃ ጥቃቶችን ለመከላከል ነው” ብለዋል።የሩሲያ ሠራዊት መጠነ ሰፊ ጥቃት ጥቃት በዋና ከተማዋ ኪዬቭ ላይ ሊያካሂድ እንደሚችል የተነገረ ሲሆን፣ አስከ 60 ኪሎሜትር የሚረዝም ርቀትን የሚሸፍን በብረት ለበሽ የሽከርካሪዎች የታገዘ ሠራዊትን ወደ ከተማዋ መንቀሳቀሱ ተዘግቧል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
አፋር ክልል ረሃብ ለመሰለ ሁኔታ መጋለጡን የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ተናገረ።

ፓርቲው ሕወሓት ከአፋር ክልል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸካይ እንዲወጣ የዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቋል። የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የክልሉ አምስት ወረዳዎች አሁን ድረስ በሕወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ይገኛሉ ብሏል። 350 ሺህ ሕዝብ ተፈናቅሎ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ እንደሚገኝም የክልሉ መንግሥት ተናግራል። የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ከአፋር ወደ መቀሌ የሚወስዱ መንገዶች በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ሆነው በመቆረጣቸው የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሮ ሰዎች በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑን ገልጿል። ትናንት ከባድ የሚባል ውጊያ እንደነበርም ድርጅቱ ተነግሯል። ከሕወሓት ጋር እየተዋጋ ያለው የክልሉ ሕዝብ፣ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ ነው ያለው የክልሉ መንግሥት ከመከላከያ ከድሮን ጥቃቶች በቀር የምድር ጦር በጦርነቱ እየተሳተፈ አለመሆኑን ገልጿል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግማሽ ዓመቱ 4.1ሚሊዮን ደንበኞችን አጓጓዘ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም በገንዘብ ሚኒስቴርና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በሂልተን ሆቴል በዛሬው ዕለት በተገመገመበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ ኢሳያስ ወልደ ማሪያም እንደገለፁት አየር መንገዱ ከመሰል ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ድርጅቶች አንጻር በተለያዩ መመዘኛዎች ሲታይ የላቀ ዕድገት አሳይቷል፤ ትርፋማነቱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ቀጥሏል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ በአሁኑ ጊዜ በርካታ የአየር መንገዶች በአስቸጋሪ ወቅት ላይ ቢሆኑም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ባሳየው ትርፋማነት፣ በወጪ ቅነሳ ረገድ ውጤት ማስመዝገቡና በተለይ በዕቃ ማጓጓዝ አገልግሎት ያሳየው አመርቂ አፈፃፀም የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
የሻረግ_ቅመማ_ቅመም
#YesharegSpices

የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ሲፈልጉ የሻረግ ቅመማ ቅመም ብለው ይጠይቁ

🔔 አዲስ አበባ በሚገኙ ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል

☎️ +251 911 66 47 75
+251 911 87 28 27

🔴 የሻረግ ቅመማ ቅመም
ምርጥ ጣዕም❗️
https://youtu.be/sG0S6CNbmvw

Check out and subscribe to our youtube channel to get recommendations on amazing movies and tvshows.

የፊልሞች እና የቲቪ ምርጫዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይመልከቱ እና ሰብስክራይብ ያድርጉ።


https://youtu.be/5O1i0ZvTYMgb
ለ 12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ውጤት በመለቀቁ እያልን !
ወደ ውጭ ሀገሮች ሄዳችሁ Scholarship መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ ወደ 👇👇👇👇
👉🇨🇦 ካናዳ
👉🇺🇸 አሜሪካ
👉🇦🇺 አውስትራሊያ
👉🇪🇺 አውሮፓ
👉🇬🇧 እንግሊዝ
ሌሎችም ሀገሮች ላይም apply ማድረግ ለምትፈልጉ ምዝገባ የጀመርን መሆኑን እየገለጽን
ለመመዝገብ 📞☎️

@Sabinavisa
@Sabinavisa2
0936363639
0936363680
እንኳን ለ126ኛው የአድዋ ድል በአል አደረሰን!

Photo: Fana
@YeneTube @FikerAssefa