YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ጀርመን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር እንዲመካከሩ ኤምባሲው አሳሰበ!

በጀርመን በርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዩክሬን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ለኤምባሲው እንዲያሳውቁ አሳሰበ፡፡

ኤምባሲው በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እና ችግር እንደሚረዳና ኢትዮጵያውያን ከመንቀሣቀሣቸው በፊት ለደኅንነታቸው ሲባል በማንኛውም ጊዜ በ+491767269094 የሞባይል ስልክ ቁጥር እና በ berlin.embassy@mfa.gov.et ኢሜይል አድራሻ በመጠቀም ኤምባሲውን እንዲያገኙ እና እንዲመካከሩ አሳስቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው እንዲገቡ በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳይገጥማቸው ክትትል እያደረገ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።በዚህም በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው መግባት እንዲችሉ ከፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተነጋግሮ ማስፈቀዱን አስታውቋል።

በመሆኑም በታቸለ ፍጥነት በዩኩሬን የሚኖሩ እና ወደ ድንበር ጉዞ በማድረግ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ግዛት በመግባት በተቻለ ፍጥነት ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓዙ አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሩሲያ ጦር ወደ ዩክሬን መዲና ከዬቭ መግባቱን የዩክሬን ባለስልጣናት ገለፁ!

የሩሲያ ኃይሎች የዩክሬንን ዋና ከተማ ኪዬቭን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የዩክሬን መከላከያ ኃይል ማንኛውም ዜጋ እንዲዋጋ በትዊተር ገጹ ጥሪ አቅርቧል።

የወታደሮቹ አዛዥ መግለጫ በዚህ ውጊያ "የእድሜ ገደቦች የሉም" ብሏል- ይህም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችም ትግሉን እንዲቀላቀሉ ሊፈቀድ እንደሚችል ያሳያል ተብሏል።

ነገር ገን የመከላከያ ሚኒስትሩ አሌክሲ ሬዝኒኮቭ ባወጡት አዲስ መግለጫ የዕድሜ ገደብ የለውም ሲባል ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ የዕድሜ ባለጸጎችን እንደሆነም ጠቁሟል። በዚህ መግለጫ ላይ ዕድሜያቸው ያልደረሰ ታዳጊዎችን አይጠቅስም።

"ከዩክሬን ጦር ኃይሎች ጦር አዛዥ ጋር በመስማማት ከ60 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች በአርበኞች ሰራዊት እንዲሳተፉ ወስነናል። ይህ ጥሪ በአካልም ሆነ በሞራል ዝግጁ የሆኑትንና ጠላትን ለማሸነፍ የተነሳሱትን ሁሉ የዕድሜ ባለጸጎች ይመለከታል" በማለት የመከላከያ ሚኒስትሩ አስፍረዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝዳንት ፑቲን ተደራዳሪ ልዑካንን ወደ ቤላሩስ ለመላክ መዘጋጀታቸው ተሰማ!

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጦርነቱ ጉዳይ ከዩክሬን ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸው ተሰማ፡፡ፑቲን ከዩክሬን ተወካዮች ጋር የሚደራደር ልዑክ ወደ ቤላሩስ ሚኒስክ ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ልዑኩ የመከላከያ፣ የውጭ ጉዳይ እና ከፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት (ክሬምሊን) የተውጣጡ አካላትን ሊያካትት እንደሚችልም ነው የተነገረው፡፡ሩሲያ ለድርድር የምትቀመጠው የዩክሬን ጦር ትጥቅ ሲያወርድ ብቻ መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሰርጌይ ላቭሮቭ በኩል አስታውቃለች፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ያለሀኪም ማዘዣ የሚሸጡ መድኃኒቶች መበራከታቸዉ ተሰማ!

በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በአዲስ አበባ በሚገኙ የመድሃኒት ተቋማት ላይ በተደረገ ቁጥጥር መድሃኒትን በኮንትሮባንድ በማስገባት፣በደህነነትና ፈዋሽነት ላይ ችግር የሚያመጡ እንዲሁም ያለ ሃኪም ትእዛዝ መድሃኒቶችን ሲሸጡ በተገኙ 53 መድሃኒት ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡

እርምጃ ከተወሰደባቸዉ መካከል 39 የሚሆኑት መድሃኒት ቤቶች የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸዉ ሲሆን 19ኙ ደግሞ እንዲታሸጉ መደረጋቸውን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አምደየሱስ አድነው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ያለ ሃኪም ትእዛዝ የሚሸጡ መድሃኒቶች መበራከታቸውን የገለጹ ሲሆን መድሃኒት የተላመዱ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስፋፉ ማድረጉን ገልጸዋል፡፤ይህ ሁኔታም በዚሁ ከቀጠለ የበሽታዎችን ስርጭት ለመቆጣጠር አዳጋች እንደሚያደርገውና የዜጎችን የጤና ሁኔታ ስጋት ላይ እንደሚጥል አክለዋል፡፡

በሌላ በኩል ፍቃድ አውጪ አካላት በስፍራው አለመገኘታቸው እና ለሌላ ሰው እውቅና በመስጠት መድሃኒቶችን በዚህ መልኩ እንዲሸጡ ማድረጋቸው ችግሩንም እንዳባባሰው አቶ አምደየሱስ አድነው አክለዋል፡፡ እነዚህንና ሌሎች ምክኒያቶችን መነሻ በማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባደረገው የቁጥጥር ስራ የተለያዩ የአስተዳደር እና ሌሎች እርምጃዎችን ወስዷል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
በጎንደር ከተማ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ በጫነ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የሁለት ፖሊስ አባላት ህይወት ማለፉን ፖሊስ አሳወቀ፡፡

የፍንዳታው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ያሳወቀው ፖሊስ፥ ፍንዳታው ከቦምብ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረም ገልጿል፡፡የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ከጭልጋ መስመር ህገወጥ ጥይት የጫነ የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ በአዘዞ የፍተሻ ኬላ አምስተኛ ዋና ፓሊስ ጣቢያ በፖሊስ አበላት እየተፈተሸ ባለበት ወቅት ነው ፍንዳታው የደረሰው።

በፍንዳታው ሁለት የፖሊስ አባላት ህይወታቸው ማለፉን የተናገሩት ኮማንደሩ፥ ሰባቱ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።በጣቢያው የነበሩ ሁለት ሲቪል ሰዎችም የፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፥ ወደ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት የነዳጅ ዋጋ እስከ መጋቢት 30 ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን አስታወቀ!

መንግስት የነዳጅ ዋጋ ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።ውሳኔው ከቀላል ጥቁር ናፍጣ፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ከአይሮኘላን ነዳጅ በስተቀር በሌሎች የነዳጅ ዓይነቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑም ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው።

ይህም የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።በዓለም ገበያ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑን የጠቆመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መንግስት የነዳጅ ምርት ከገዛበት ውድ ዋጋ በግማሽ ለህብረተሰቡ በሽያጭ እያስተላለፈ ይገኛል ብሏል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ምርቱን በከፍተኛ ቁጠባ የመጠቀም እንዲሁም የብዙሃን ትራንስፖርትን የመጠቀም ልምድ ሊያዳብርና በነዳጅ ምርቶች ግብይት ላይ የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ከፀጥታ አካላትጋር በትብብር ሊሠራ እንደሚገባ ለኢቲቪ በላከው መግለጫ አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዩናይትድ ኪንግደም ታንክ ኮንቮይ ወደ ሩሲያ ድንበር ወደምትገኘው የኔቶ ሀገር አቀና

የእንግሊዝ ጦር ኮንቮይ ወደ ባልቲክ ሀገር ኢስቶኒያ ገብቷል። (ስካይ ኒውስ)
የሰሜን ኮሪያው መሪ 2022 የግሪጎሪያን የዘመን መቁጠሪያን በአያታቸው የልደት ቀን ተኩ!

ሀገሪቱ የግሪጎሪያን አቆጣጠርን ከቀን አቆጣጠር ስርዓቷ ያወጣች ሲሆን፤ አሁን ያለንበትን የፈረንጆቹን 2022 ዓመትንም ሰርዛለች።በዚህም መሰረት ሰሜን ኮሪያውያን በ2022 ምትክ “ጁች 111” የሚል የቀን አቆጣጠር መጠቀም መጀመራቸውም ነው የተነገረው።

አዲሱ የሰሜን ኮሪያ “ጁች” የዘመን መቁጠሪያ የሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያ መሪ በሆኑት ኪም ኢል ሱንግ የልደት ቀን የሚጀመር ሲሆን፤ የዘመን መቁጠሪያው የመጀመሪያ ዓመትም የፈረንጆቹ 1992 ነው ተብሏል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የሱማሊያ ጦር ሠራዊት ትናንት 29 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገድያለሁ ማለቱን ዥንዋ ዜና ምንጭ ዘግቧል። ታጣቂዎቹ የተገደሉት ከሞቃዲሾ በስተደቡብ ባንድ የመንግሥት ኃይሎች ወታደራዊ ጦር ሠፈር ላይ ድንገተኛ ጥቃት በሰነዘሩበት ወቅት ነው። አልሸባብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሞቃዲሾ እንዲሁም በደቡባዊ እና ማዕከላዊ ሱማሊያ በመንግሥት ተቋማት እና በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ጦር ሠፈሮች ላይ የሚፈጽማቸውን ተደጋጋሚ ጥቃቶች አጠናክሮ ቀጥሏል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ዜሌንስኪ ከአገር እንዲወጡ በአሜሪካ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ!

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ ከአሜሪካ የቀረበላቸውን የድጋፍ ጥያቄ ሳይቀበሉት መቅረታቸው ተዘገበ።

ፕሬዝዳንቱ "ውጊያው ያለው እዚህ ነው። የምፈልገው የጦር መሳሪያ እንጂ የማምለጫ መንገድ አይደለም" ማለታቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ጉዳዩን የሚያውቁ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል።

ዋሽንግተን ፖስት የአሜሪካና የዩክሬን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ለመርዳት ተዘጋጅታ ነበር።

ፕሬዝዳንቱ የሩሲያን ወረራ ተከትሎ በወሰዱት አቋም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ሲወደሱ ቆይተዋል።የቀድሞው ኮሜዲያንና ተዋናይ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ባደረጉት ንግግር “ጥቃት ስትፈጽሙብን ፈት ለፊት እንጋፈጣችኋለን እንጂ አንሸሽም” በማለት አገራቸውን ከወረራው ለመከላከል ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ሕወሓት በታች አርማጭሆ አካባቢ ሰዎችን ወደ ሱዳን እያስወጣ መሆኑ ተገለጸ!

ሕወሓት በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ቀበሌ ለሚገኙ ድንበር ጠባቂ የፀጥታ አካላት ገንዘብ በመክፈል ሠዎችን ለሥልጠና ወደ ሱዳን መላኩ ተሰማ፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የሕወሓት ቡድን፣ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ቀበሌ ለሚገኙ ለቀበሌ፣ ለፌደራል ፖሊስና ለጉምሩክ ድንበር ጠባቂ የፀጥታ አካላት በአንድ ሰው ከ120 ሺሕ ብር በላይ ገንዘብ በመክፈል፣ ከአንድ ሳምንት በፊት ከ60 በላይ ሠዎችን ለሥልጠና ወደ ሱዳን ማስወጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ጠቁመዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ሕወሓት ከአንድ ሳምንት በፊት ሠዎችን በ‹ሲኖትራክ› ጭኖና በታጣቂዎቹ አሳጅቦ ወደ ሱዳን ያስወጣ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ የወጡት እነዚህ ሠዎች ሱዳን ከሚገኘው “ሳምሪ” ከተባለው የሕወሓት ቡድን ጋር ሳይቀላቀሉ እንዳልቀሩ ተጠቁሟል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በወልድያ በደረሰ የእሳት አደጋ የአባት ፣ የእናት እና የህጻን ልጅ ህይወት አለፈ፡፡

በከተማዋ በ06 ቀበሌ በተለምዶ ጎማጣ ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር አካባቢ የካቲት 18 ለ19/2014 ዓ.ም ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ የአባት፣ እናት እና ህጻን ልጃቸውን ጨምሮ ለሞት ሲዳርግ ፥ ሦስት ሰዎች ደግሞ በቃጠሎው አደጋ ደርሶባቸዋል።ሦስቱ ቁስለኞች በወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።ፖሊስ የእሳት አደጋው መንስኤ እና በንብረት ላይ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት በማጣራት ላይ እንደሆነ ከከተማው ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሩሲያ ኃይሎች የዩክሬን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ገቡ!

የሩስያ ኃይሎች የዩክሬን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ወደሆነችው ካርኪቭ መግባታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገለፁ።የካርኪቭ ግዛት አስተዳደር ኃላፊ ኦሌግ ሲኔጉቦቭ የሩሲያ ቀላል ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ወደ "ከተማዋ ገብተዋል" ብለዋል።

ከመግለጫው በፊት፣ አንዳንድ የሩሲያ ወታደራዊ መኪኖች በሰሜናዊ ምስራቅ ከተማ ጎዳናዎች ላይ ሲዞሩ የሚያሳይ ምስል ታይቷል።

ሲኔጉቦቭ የሩሲያ ወታደሮች መሃል ከተማ ውስጥ እንዳሉ በመግለጽ ነዋሪዎቹ ከተማቸውን ለቀው እንዳይወጡ አሳስበዋል።"ከመጠለያዎችን አትውጡ! የዩክሬን ጦር ኃይሎች ጠላትን እያስወገዱ ነው። ሲቪሎች ወደ ጎዳና እንዳይወጡ ተጠይቀዋል." ብለዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የዩክሬን ተወካዮች ከራሺያ አቻቸው ጋር በቤላሩስ ድንበር በምትገኘው ፕሪፕያት ወንዝ አቅራቢያ ለመደራደር መስማማታቸውን ራፕትሊ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔውን ከመጋቢት 2 እስከ 4 ያካሂዳል!

የብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔውን ከመጋቢት 2 እስከ 4ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚያካሄድ አስታወቀ።የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ፓርቲው "ከፈተና ወደ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 2 እስከ 4ቀን 2014 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ከተማ ያካሂዳል።

በጉባዔው 1600 አባላት በድምጽ፣ 400 ሰዎች ያለ ድምጽ፣ 41 የውጭ አገራት እህት ፓርቲዎች እንዲሁም የአገር ውስጥ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ አቶ አደም ገልጸዋል።ህዝብ የሰጠውን አደራ በብቃት ለመወጣት የሚያስችል አቅጣጫ ፓርቲው በጉባዔው እንደሚያስቀምጥም አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ማዕቀቦችን ተከትሎ የሩሲያ መገበበያ ገንዘብ ከአሜሪካ ዶላር በ30 በመቶ ቀነሰ!

የሩሲያ መገበያያ ገንዘብ
ምዕራባውያኑ ሩሲያ ላይ የጣሉትን ማዕቀቦችን ተከትሎ የሩሲያው መገበያያ ገንዘብ ሩብል ከአሜሪካ ዶላር አንጻር 30 በመቶ ዋጋው መቀነሱ ተገለጸ።የምዕራቡ ዓለም አገራት አንዳንድ የሩሲያ ባንኮች ስዊፍት የተሰኘውን ዓለማ አቀፍ የገንዘብ ማዘዋወሪያ ስርዓት እንዳይጠቀሙ ማገዳቸውን ተከትሎ ነው የሩሲያው ሩብል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ደረጃ ዋጋው የወረደው።እሁድ ዕለት የሩሲያው ማዕከላዊ ባንክ ከዚህም በኋላ የአገሪቱ ባንኮች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል በመጠቆም ዜጎች እንዲረጋጉ አሳስቧል።

የዩክሬን ቀውስን ተከትሎ ያልተጣራ አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋው ከ100 ዶላሮች በላይ ሆኗል።የአውሮፓ ሕብረት እና አሜሪካ እንዲሁም አጋሮቻቸው በርካታ የሚባሉ የሩሲያ ባንኮችን ከስዊፍት ያገዱ ሲሆን ይህ እርምጃ ከዩክሬን ወረራ በኋላ እስከዛሬ ከታዩ ማዕቀቦች ከባዱ እንደሆነ እየተነገረ ነው።የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ እገዳ የሚጣልበት ሲሆን ይህ ደግሞ አገሪቱ በሌሎች አገራት ያላትን ንብረት ማንቀሳቀስ እንዳትችል ያደርጋታል።ይህ እርምጃ ሩሲያን ከተቀረው ዓለም የንግድና ገንዘብ ነክ እንቅስቃሴዎች ማግለል እንደሆነ አገራቱ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሁለት መምህራንን አግተው 190 ሺህ ብር ከቤተሰቦቻቸው የተቀበሉት አጋቾች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!

ሁለት መምህራንን አግተው 190 ሺህ ብር ከቤተሰቦቻቸው በመቀበል ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የመተማ ወረዳ ፖሊስ ኮሚዩኒኬሽን አሳወቀ።

የወረዳው ፖሊስ ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ኢ/ር ጌታቸው ባየ እንደገለፁት፤ ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ኩመር አዉላላ ቀበሌ መምህርት ጠጀ ገዛኸኝ እና መምህርት ትርንጎ አንባቸውን የተባሉ ኹለት የኩመር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የካቲት 9/ 2014 ከምሸቱ 5፡30 ከመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው እያለ 5 አጋቾች አግተው በመውሰድ ቤተሰቦቻቸውን ገንዘብ ይጠይቃሉ።

አጋቾቹ ለቤተሰቦቻቸው በመደወል የጠየቁት ገንዘብ 900 ሺህ ብር ሲሆን፤ ይህን ካላደረጉ በህይወት እንደማያገኟቸዉ ያስጠነቅቃሉ ቤተሰብ በበኩሉ ምንም የገቢ ምንጭ እንደሌላቸውና ከህብረተሰቡ ለምነዉ እንደሚያመጡ ነገረዉ ከብዙ ልመናና መደራደር በኃላ 190 ሺህ ብር ለአጋቾቹ በመስጠት ታጋቾቹን ያስለቅቃሉ።

ይህ መረጃ የደረሰው የወረዳዉ የፀጥታ አካል ከሌሎች የማህበረሰብ አካላት ጋር በመቀናጀት የካቲት 20 ቀን 2014 ከጠዋቱ 3:20 ላይ በተደረገ ጠንካራ ክትትል ማለደ አቡሃይ እና ሰለሞን አሸተ የተባሉትን ኹለት አጋቾች ከተቀበሉት 108 ሺህ 450 (አንድ መቶ ስምንት ሸህ አራት መቶ ሃምሳ ብር) ጋር ገንዳውሃ ኬላ ላይ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ ኮሚዩኒኬሽንን ጠቅሶ አዲስ ማለዳ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አለም ለጦርነቱ መፍትሄ ያመጣ ይሆናል ብሎ እየጠበቀ ለሚገኘው የዛሬው ድርድር የዩክሬን ተወካዮች በሄሊኮፕተር ቤላሩስ ፣ ጎሜል ደርሰዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ አፍሪካ መንግስት በዩክሬን ወረራ የተነሳ ለሁለት መከፈሉ ተሰማ!

የደቡብ አፍሪካ የዜና ማሰራጫዎች እንደዘገቡት በፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና በውጪ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ናሌዲ ፓንዶር መካከል የሩስያ ጦር ወደ ዩክሬን መግባቱን በተመለከተ ከፍተኛ ልዩነቶች በመካከላቸዉ መፈጠሩን ዘግበዋል፡፡የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ ፓንዶር ሩሲያ ከዩክሬን እንድትወጣ የሚጠይቅ መግለጫ ካወጡ በኋላ የፕሬዝዳንት ራማፎሳን ቁጣ ከፍ አድርጎታል፡፡

የደቡብ አፍሪካ መንግስት ከጦርነቱ ጎን እንደማይቆም አጥብቆ መናገሩን ስማቸው ያልጠቀሱ የውስጥ አዋቂዎችን ጠቅሶ ኒዉስ 24 ዘግቧል።የዜና ድህረ ገጹ አክሎ እንደገለጸው ገዢዉ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ አለም አቀፍ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ በሚደረገው ስብሰባ ሚኒስትሯን እንደሚተች ይጠበቃል፡፡

ሰንዴይ ታይምስ እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ ሩሲያ ከዩክሬን እንድትወጣ በጠንካራ ቃል በተነገረው መግለጫ ደስተኛ አይደሉም ሲሉ የቅርብ ምንጮች ዘግበዋል።ፕሬዚዳንቱ መግለጫውን ከመውጣቱ በፊት አላዩትም እናም አልተስማሙበትም።

ከሩሲያ ጋር ጠላት መሆን አለብን የሚል አጀንዳ ያላቸው የአለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ክፍል ውስጥ ያሉ ሰዎች እንዳሉ ሰንዴይ ታይምስ ስማቸው ያልተጠቀሰ ምንጭ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡የሚኒስትሯ ቃል አቀባይ ሉንጋ ንጌንገሌሌ ለጋዜጣው እንደተናገሩት ፕሬዚዳንቱ በመግለጫው ደስተኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa