YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
https://youtu.be/sG0S6CNbmvw

Check out and subscribe to our youtube channel to get recommendations on amazing movies and tvshows.

የፊልሞች እና የቲቪ ምርጫዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይመልከቱ እና ሰብስክራይብ ያድርጉ።


https://youtu.be/5O1i0ZvTYMgb
🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
https://youtu.be/G-fzeN_xbRk
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
በየኔ ትዩብ ላይ ማስታወቂያችንን ዐይቶ ተመዝግቦ አሁን ላይ በአሜሪካ ትምህርት የጀመረ ተማሪ ምስክርነት በላይ ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ!

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication

ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy
🇬🇧 የስራ ጉዞ ወደ #UK 🇬🇧

👉 የሚሰራበት አገር - UK
👉 የስራው አይነት - Vegetables and fruits picker
👉 የስራ ቀናት - 5 - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - ከ8 - 10 hr/day
40/60 working hrs per week
👉 ደሞዝ - £8.91 per hr + bonuses for OT
👉 ፆታ - ወንድ እና ሴት
👉 ዕድሜ - 20 እስከ 45
👉 OT - ይቻላል
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ 2 ወር

Accommodation is provided by the employer (~£55 per week)

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo

#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 20 ሰው ብቻ::

Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com
http://Sabinaadvisor.com
https://tttttt.me/sabinaadvisor
👍1
ሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት በዩክሬን ፈጸመች!

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በሀገሪቱ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ሩሲያ በዩክሬን መሠረተ ልማቶች እና በድንበር ጠባቂዎች ላይ የሚሳኤል ጥቃት አድርሳለች፡፡የዩክሬን ወታደራዊ ሀይል የሩስያ ሀይሎች በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ላይ ጠንካራ ጥቃት እንደጀመሩ መግለጫ አውጥቷል።

ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ አቅራቢያ በሚገኘው ቦሪስፒል አውሮፕላን ማረፊያ እና በሌሎች በርካታ አየር ማረፊያዎች ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟን መግለጫው ገልጿል።የዩክሬን አየር ሃይል በሩሲያ የሚሰነዘረውን የአየር ጥቃት እየመከተ እንደሆነም አስታዉቋል፡፡በዋና ከተማዋ ኬየቭ የፍንዳታ ድምጽ እየተሰማ ይገኛል፡፡

የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የዩክሬን ወታደራዊ መሠረተ ልማትን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መሆኑን ገልጿል፡፡ፕሬዚደንት ፑቲን በምስራቃዊ ዩክሬን "ወታደራዊ ዘመቻ" እንደሚካሄድ ባወጁበት ቅጽበት ከሰባት ዓመታት በላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ዋጋ ከ100 ዶላር በላይ ከፍ ብሏል።

የዩክሬይን ባለስልጣናትን በመጥቀስ በርካታ ዘገባዎች እንዳመላከቱት በቤላሩስ የሚገኙ ወታደሮች የሩስያን ጥቃት እየተቀላቀሉ መሆናቸዉን ጽፈዋል፡፡በዩክሬን ሰሜናዊ ድንበር ላይ የምትገኘው ቤላሩስ የረጅም ጊዜ የሩሲያ ወዳጅ ሀገር ስትሆን ከሞስኮ ጎን መሰለፏ እየተገለጸ ይገኛል፡፡

ዳጉ ጆርናል
@YeneTube @FikerAssefa
ኦነግ ሸኔ በጉጂ ዞን አራት ወረዳዎችን እንደተቆጣጠረ ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን ከሚገኙ 18 ወረዳዎች ውስጥ አራቱ በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ሥር መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡በዞኑ ከሚገኙት ውስጥ የዋደራ ወረዳ ገጠራማ ቀበሌዎች፣ ጎሮ ዶላ፣ ጉሜ አልደሎ፣ ሰባ ቦሮ ወረዳዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት በተፈረጀው የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ኃይል ቁጥጥር ሥር እንደሚገኙ ነዋሪዎቹ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የአዶላ ወዩ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ነጌሳ ጉራቻ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በአዶላ ሬዴ ወረዳ አቡሎ ሩኬሳ፣ አቡሎ ኡዶቱ፣ ሒርቦራ በርኮ (ዘንባባ) የገጠር ቀበሌዎች ላይ የኦነግ ሸኔ እንቅስቃሴ አይሏል፡፡በዞኑ 2009 ዓ.ም. ከተመሠረተችው ጉሚ ኤደሎና ከነጌሌ ከተማ ውጪ የሚገኙ ገጠራማ ቦታዎች ለደኅንነት አሥጊ መሆናቸውን አቶ ነጌሳ አስረድተዋል፡፡

ታጣቂ ቡድኑ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ግድያ፣ ዘረፋና ዕገታ የሚያደርጉ መሆናቸውን የገለጹት የከተማው ነዋሪ፣ ታጣቂዎቹ ዕገታ ሲያደርጉ የሚጠይቁት ገንዘብ የቤተሰቡን አቅም አጥንተው መሆኑን አስረድተዋል፡፡በአዶላ ሬዴና በአካባቢዋ ማለትም አብሎ ሩኬሳና አቡሎ ኡዶቷ አካባቢዎች የመንግሥት መዋቅር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት በኦነግ ሸኔ ላይ ዕርምጃ እየወሰደ መሆኑን የገለጹት ነዋሪው፣ ዕርምጃው አጥጋቢ አለመሆኑን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ የመከላከያ ኃይል፣ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ ልዩ ኃይል በዕርምጃው እየተሳተፉ ቢሆንም፣ ለኦፕሬሽን የሚካሄዱበት ሥፍራና የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ያሉበት ቦታ የተለያዩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ዘገባው የሪፖርተር ነው ተጨማሪ ለማንበብ : http://bit.ly/3IjuqHp

@YeneTube @FikerAssefa
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን እንዲያቆም ተማጸኑ!

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን እንዲያቆም ተማጽነዋል።"በሰብኣዊነት ስም ይህን ጦርነት አቁሙ" ሲሉ ነው የፀጥታው ምክር ቤት በዩክሬን ላይ ካካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ መልዕክት ያስተላለፉት።

@YeneTube @FikerAssefa
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የከተማችን ዜጎች ለ 10 ወራት የሚቆይ የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግላቸው መሆኑን ተሰማ!

በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነታቸው ያደረጉ 350ሺህ የሚጠጉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ወርሃዊ ድጋፍ ሊደረግላቸው መሆኑ ከሃላፊው ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደዳስታወቀው በኮሮና ቫይረስ መከሰት ምክንያት በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ 350 ሺህ ያህል ዜጎች ድጋፍ ሊያደርግ እንደሆነ ተነግሯል።

ድጋፉ ለሚቀጥሉት አስር ወራት የሚቆይ ሲሆን በየወሩ የአንድ ሺህ ብር ድጋፍ ያገኛሉ ብሏል፡፡የምግብ ዋስትና ጽ/ ቤት የህብረተሰብ ተሳትፎ እና አደረጃጀት የቡድን መሪ አቶ ብርሀኑ ረዳ እንደተናገሩት ለዚህ መርሀ ግብር ማስፈጸሚያ የሚሆን 1 ቢሊየን 51ሚሊየን ብር ከአለም ባንክ በኩል መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

በ350ሺህ ዜጎች ተጠቃሚ ካደርጋል በተባለለት በዚህ መርሃ ግብር እስከ አሁን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ደረጃ 290ሺህ ያህል ዜጎች ተለይተዋል ብለዋል፡፡ቀሪዎቹን 60 ሺህ የመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ዜጎች የመለየቱ ስራ ደግሞ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ አቶ ብርሀኑ ተናግረዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የግድቡ ግንባታ እንዲቆም ኢትዮጲያ አልተፈራረመችም ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ!

የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲቆም ኢትዮጲያ የተፈራረመችው ምንም ነገር የለም ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።አምባሳደር ዲና በዛሬው እለት ሳምንታዊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ ማብራሪያ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

የግድቡ ግንባታ እስከቀጠለ ድረስ የማመንጨት ሂደት ላይ ይደርሳል ሲሉ ተናግረዋል። እ.ኤ.አ በ2015 በሱዳን መዲና ካርቱም ላይ የተፈረመው የሶስትዮሽ ስምምነት የግድቡ ግንባታ እንዲቆም የተደረሰበት አይደለም ሲሉ አስታውሰዋል።

አሁን ላይ የህግና የቴክኒክ ጉዳይ ላይ እየተሰራ ይገኛል ድርድሩ እንዲቆም ኢትዮጵያ አላደረገች፤ በኢትዮጵያ በኩል ያለው አቋም በቀሩት ልዩነቶች ላይ መወያያት ነው ሲሉ ገልፀዋል።የተገደበው ውሃ የግድቡን ተርባይን ሲመታ ወደ ታች ይወርዳል፤ እንዲሁም ቀደም ሲል በትነት ይባክን የነበረው በመገደቡ ጥቅሙ ለጋራችን ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

የታላቁ የኢትዮጲያ የህዳሴ ግድብ በተለይ ለሱዳን የተለየ ጥቅም አለው፤ ግብፅ እና ሱዳን በርካሽ ዋጋ ኃይል መጠቀም ይችላሉ ሲሉ አክለዋል።የሚያዋጣን በናይል ወንዝ ላይ አብረን ማደግ ነው መናቆሩ አይጠቅም በተፋሰሱ በጋራ መጠቀም እንችላለን ወዳጆቻችን ይህንኑ እንዲያስተላልፉ ነው የምንፈልገው ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
ራሺያ በዩክሬን ላይ የቀጥታ ጦርነት መክፈቷ ከተሰማ በኋላ ለደህንነታቸው የሰጉ የኪየቭ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እየሸሹ ይገኛሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
በልደታ ክ/ከተማ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 4 አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 4 አመራሮችና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ፓሊስ መምሪያና በማህበርሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ከአዲሱ የአመራር ምደባ በፊት የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ፋይናንስ አስተዳደር ፑል ጽ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም በፑሉ የግዥ ቡድን መሪና የግዥ ባለሙያ መሆናቸው ተገልጿል።

አስተዳደሩ የደረሰበትን በየጊዜው ለህዝቡ እንደሚያሳውቅ እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሰራርንም በቁርጠኝነት እንደሚታገል መግለፁን ከልደታ ክ/ከ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
የሩሲያን ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ ኪዬቭ ከሞስኮ ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በይፋ ማቋረጧን አስታወቀች።

ይህ የተገለጸው የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎደሚየር ዜሌኒስኪ በሰጡት መግለጫ ነው።

ፕሬዝደንቱ በዚህ መግለጫቸው ፍላጎት ያላቸውን የዩክሬን ዜጎች በሙሉ መንግሥታቸው እንደሚያስታጥቅ ተናግረዋል።

ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ፍጥጫ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ለሲቪል ዜጎቿ መሠረታዊ ወታደራዊ ስልጠና ስትሰጥ ቆይታለች።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ኔቶ ዛሬ ሐሙስ ካደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ ዩክሬን እና ሩሲያ በሚዋሰኑበት ምሥራቃዊ ግዛት የምድር፣ የባህር እና የአየር ኃይሉን ለማጠናከር መወሰኑን አስታወቀ።

የኔቶ አምባሳደሮች ባወጡት መግለጫ "በጥምረቱ ምሥራቃዊ ክፍል ተጨማሪ የምድር፣ የአየር እና የባህር መከላከያ ኃይል ልናሰማራ ነው" ብለዋል። የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ የንስ ስቶልተንበርግ በምሥራቃዊ አውሮፓ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን የመከላከያ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኑን ለጋዜጠኞች አረጋግጠዋል።

የድርጅቱ አባላት የሆኑት የምስራቅ አዉሮጳ ሐገራት ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ፣ ሉቱኒያ እና ፖላንድ የሰሜን የግዛት አንድነት፣ የፖለቲካ ነጻነት ወይም ጸጥታ አደጋ ውስጥ ሲወድቅ ሌላ ስብስባ እንዲጠራ ጠይቀዋል። ለግጭቱ ቅርበት ካላቸው አገራት አንዷ የሆነችው ሉቱኒያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጋለች።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በቼርኖቤል ኒውክሌር ጣቢያ አቅራቢያ ጦርነት መቀስቀሱን ተናገሩ!

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት በትዊተር ገጻቸው ላይ “የሩሲያ ወረራ ሃይሎች የቼርኖቤል የኒውክሌር ሃይል ማመንጫ ጣቢያን ለመያዝ እየሞከሩ ነው” ሲሉ ለጥፈዋል።

ዘለንስኪ ወታደሮቹ ተቋሙን እየተከላከሉ መሆናቸውን እና የተጠረጠረውን ጥቃት ለስዊድን ጠ/ሚ እንዳሳወቁ ተናግሯል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም “ይህ በመላው አውሮፓ ላይ የታወጀ የጦርነት ነው” ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል የገላን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በተራራ ኔትዎርክ የበይነ መረብ ብዙኀን መገናኛ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ላይ ዛሬ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንደፈቀደ ተራራ ኔትዎርክ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ዘግቧል።

የዛሬው ችሎት ቀጠሮ የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመስማት ቢሆንም፣ ፖሊስ ግን የተጠርጣሪውን ስልክ እና ኮምፒውተሮች ለመበርበር ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለቱ ነው የጠየቀው ጊዜ የተፈቀደለት። የጋዜጠኛው ጠበቃ የፖሊስ የሽብር ክስ በሕጉ መሠረት ወደ ክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዛወር እንዳለበት ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጓል።

Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የሩሲያ ወታደሮች ወደ ዋና ከተማ ኪዬቭ ተቃርበዋል ተባለ!

የሩሲያ አየር ወለዶች ከዩክሬን መዲና ኪዬቭ በ30 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ይገኛሉ።ከረፋድ ጀምሮ የሩሲያ አየር ወለዶች የዩክሬንን አንቶኖቭ ጦር ካምፕን በቁጥጥራቸው ስር አስገብተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የዩክሬን ብሔራዊ ዘብ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ መጀመሩን አስታውቋል።በምድር፣ በአየርና በባሕር ሐሙስ ጠዋት በዩክሬን ላይ ጥቃት የከፈተችው ሩሲያ ከፍተኛ ውግዘት እየገጠማት ቢሆንም ዘመቻዋን ቀጥላለች።

የሩሲያ ጦር በተለያዩ አቅጣጫዎች ጥቃት የከፈተ ሲሆን ብረተ ለበስ ሜካናይዝድ ጦር ፈጣን ግስጋሴ እያደረገ ነው።በዚህም ከደቡብ አቅጣጫ በቤላሩስ ድንበር በኩል እንዲሁም በሰሜን ከክሬሚያ አቅጣጫ ወደ ዩክሬን አምርቷል።በኪዬቭ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ፖል አደምስ ሩሲያ በቀጣይ ምን ልታደርግ እንደምትችል ግልጽ አይደለም ብሏል።

ምናልባት የአየር ኃይሉን ጦር ካምፕ የተቆጣጠሩት አየር ወለዶች ባሉበት ሆነው ሜካናይዝድ ጦሩን ሊጠብቁ እንደሚችሉ አመልክቷል።አልያም አየር ወለዶቹ የያዙትን የአየር ኃይል ካምፕ በኪዬቭ ላይ የአየር ጥቃት ለመክፈት ይጠቀሙበት ይሆናል ብሏል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የራሺያ ጦር የቼርኖቢል የኒውክሊዬር ሃይል ማመንጫ መቆጣጠሩን የዩክሬይን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

[RT]
@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
የሻረግ_ቅመማ_ቅመም
#YesharegSpices

የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ሲፈልጉ የሻረግ ቅመማ ቅመም ብለው ይጠይቁ

🔔 አዲስ አበባ በሚገኙ ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል

☎️ +251 911 66 47 75
+251 911 87 28 27

🔴 የሻረግ ቅመማ ቅመም
ምርጥ ጣዕም❗️
https://youtu.be/sG0S6CNbmvw

Check out and subscribe to our youtube channel to get recommendations on amazing movies and tvshows.

የፊልሞች እና የቲቪ ምርጫዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይመልከቱ እና ሰብስክራይብ ያድርጉ።


https://youtu.be/5O1i0ZvTYMgb
ለ 12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ውጤት በመለቀቁ እያልን !
ወደ ውጭ ሀገሮች ሄዳችሁ Scholarship መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ ወደ 👇👇👇👇
👉🇨🇦 ካናዳ
👉🇺🇸 አሜሪካ
👉🇦🇺 አውስትራሊያ
👉🇪🇺 አውሮፓ
👉🇬🇧 እንግሊዝ
ሌሎችም ሀገሮች ላይም apply ማድረግ ለምትፈልጉ ምዝገባ የጀመርን መሆኑን እየገለጽን
ለመመዝገብ 📞☎️

@Sabinavisa
@Sabinavisa2
0936363639
0936363680