በእሳት አደጋ የአንድ ቤተሰብ ልጆች የሆኑ ወንድም እና እህት ህይወታቸዉ አለፈ!
በትላንትናዉ እለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ከሀያ ደቂቃ ላይ አራብሳ ኮንደሚኒየም ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የስድስት አመት እድሜ ያለው ህጻን ህይወቱ ሲያልፍ እድሜዋ 10 አመት የሆነች የሟች እህት በጭስ የመታፈን አደጋ ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ገብታ ነበር፡፡ሆኖም በተደረገላት የህክምና ድጋፍ መትረፍ ሳትችል ህይወቷ አልፏል፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አራብሳ ኮንደሚኒየም ብሎክ ሰላሳ አራት 2ኛ ፎቅ ላይ አደጋው መድረሱን ገልፀዋል።አደጋው ሲደርስ በጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ የምትኖር የ18 አመት እድሜ ያላት የቤት ውስጥ ሰራተኛ ከ5ኛ ፎቅ ላይ ዘላ ራሷን ለማዳን ባደረገችዉ ሙከራ ከባድ ጉዳት እንደረሰባት ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
በእሳት አደጋዉ 50 ሺህ ብር የተገመተ ንብረት ሲወድም የእሳት አደጋ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ተዛምቶ ከዚህ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ እሳቱን መቆጣጠር ችለዋል። በኮንዶሚኒየም ቤቶች አልፎ አልፎም ቢሆን አደጋ እያጋጠመ በመሆኑና የአደጋዉ ምክንያትም በአብዛኛዉ ኤሌክትሪክ በመሆኑ በኤሌክትሪክ አጠቃቀም ወቅት ተገቢዉ ጥንቃቄ እንዲረግና የኤሌክትሪክ መስመሮቻችን በባለሞያ ማስፈተሽ እንደሚያስፈልግ አቶ ንጋቱ አሳስበዋል፡፡የትላንትናዉ የእሳት አደጋ በኤሌክትሪክ ምክንያት የተነሳ እንደሆነ ገልፀዋል።
የኮንደሚኒየም ቤቶች የአደጋ ጊዜ ማምለጫ ደረጃዎችም ሊታሰብበት የሚገባው ጉዳይ እንደሆነም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በ196 ሚሊየን ብር ወጪ ዘመናዊውን ዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ የክፍለ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሰሩት ለማስቻል 150 ማተሚያ ማሽኖችን ገዝቶ ለክፍለ ከተሞች ማከፋፈሉን ለዋዜማ ተናግሯል፡፡ ከዚህ ቀደም ዘመናዊ መታወቂያው በኤጀንሲው በኩል ብቻ የሚሰጥ የነበረ ሲሆን መታወቂያውን ለማግኘት ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ መጠበቅ ያስፈልግ ነበር።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢንዶኔዥያ ሱማትራ አቅራቢያ በ6.2 በሬክተር ስኬል በተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ 2 ሰዎች ሞቱ!
በኢንዶኔዥያ ዛሬ በተከሰተ በከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ 2 ሰዎች ሲሞቱ 20 ሰዎች ላይ አካላዊ ጉዳት አስከትሏል።ከኮረብታ ቡኪቲንግጊ ከተማ 66 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኙ ህንፃዎችን አፈራርሷል።እንደ ሀገሪቱ ባለሥልጣናቱ ገለጻ የመሬት መንሸራተት መከሰቱንና በጎረቤት ማሌዢያ እና ሲንጋፖርም ተፅዕኖዎች ማሳደሩን ተናግረዋል።

“በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ለመመለስ እየተሠራ ነው” - አምባሳደር ሌንጮ ባቲ
በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በአጭር ጊዜ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር በቅርበት እየተሠራ መሆኑን በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሌንጮ ባቲ፣ በተለያየ ምክንያት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ገብተው ለእስር እና ለእንግልት የተዳረጉ ኢትዮጵያውያንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ጋር በቅርበት እየሠራ ነው ብለዋል።
ከሳዑዲ የሚመለሱ ዜጎችን በተመለከተ ከተመለሱ በኋላ ችግር ላይ እንዳይወድቁ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከክልሎች ጋር ወደ ሥራ መግባቱንም ተናግረዋል።
Via EBC

ሩሲያ በፈፀመችው ጥቃት በዋና ከተማዋ በኪየቭ የሟቾች ቁጥር 137 ሲደርስ 316 ወታደሮች እና ሲቪሎች መቁሰላቸውም ታውቋል፡፡
የዩክሬን ታጣቂ ሃይሎች በ3 DPR ሰፈሮች ላይ ከባድ መሳሪያ መተኮሳቸው የተነገረ ሲሆን በዚህም 2 ሰዎች ሲሞቱ 12 ያክሉ ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ የDPR አካባቢ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የዩክሬን ሃይሎች በሮስቶቭ ክልል ሚሎሮቮ የሚገኘውን ወታደራዊ አየር ማረፊያ ቶቺካ በተሰኘው ሚሳኤል መምታታቸውን ያልተረጋገጠ ዘገባዎች አመላክተዋል ሲል RT ኒውስ ዘግቧል፡፡
የዩክሬን ሃይሎች ከኪየቭ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለውን ቁልፍ ድልድይ ማፈንዳታቸውንም ዘገባው አክሏል፡፡
በሁሉም የኪየቭ አካባቢዎችም በአንድ ሌሊት በርካታ ፍንዳታዎች ተዘግበዋል።
አውሮፕላንም ከህንጻ ጋር መጋጨቱና የቪታሊ ከንቲባን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡
ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በቼርኖቤል በዋና ከተማዋ በኪየቭ እንደሚቆዩ አስታውቀዋል፡፡
ከ100,000 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ ማስታወቁን የሩሲያው አርቲ የዜና ወኪል ዘግቧል።
Via Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa

👍1
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዐቢይ ጾምን በማስመልከት ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ!
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የዐቢይ ጾም መግባትን አስመልክተው ዛሬ የካቲት 18/2014 ዓ.ም ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አሁን ላይ ልባችን እንደሚመስክርብን ያለንበት ጊዜ ጥል ያየለበት ጭካኔ ስር የሰደደብት እንደሆነ አይካድም በዚህ ምክንያት የብዙ ልጆቻችን ሕይወት ተቀጠፎአል ተመስቃቅሏል ጥላቻ ቦታ ካገኝ ውጤቱ ክዚህ ሌላ ሊሆን አይችልምና ይህን ሁሉ አስከትሎብናል።
በዙም ወርኃ ጾም ንሥሐ መግባት አልበን ስንል የከረምነበትን የጥላቻ ሕሊና ከስር መሰረቱ ነቅለን በመጣል ፤ፍቅርንና ሰላምን በመሻት ወደ እግዚአብሔር መቀረብ አለብን ሲሉ ቅዱስ ፓትርያርኩ ተናግረዋል።
በመዋዕለ ጾሙ ስለሐገርና ሰለ ቤተክርስቲያናን አንድነት፤ ስለህዝባችን ዘላቂ ፍቅርና ስምምነት አጥብቀን እንድንጸልይ እንዲሁም በግጭትና በድርቁ ለትጎዱ ወገኖቻችን ካለን በማካፈል ምዕመኑ የችግሩ ተካፋይ እንዲሆን ቤተክርስቲያን መለዕክቷን አስተላልፋለች።
[Asham]

በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ጀርመን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር እንዲመካከሩ ኤምባሲው አሳሰበ!
በጀርመን በርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዩክሬን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ለኤምባሲው እንዲያሳውቁ አሳሰበ፡፡
ኤምባሲው በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እና ችግር እንደሚረዳና ኢትዮጵያውያን ከመንቀሣቀሣቸው በፊት ለደኅንነታቸው ሲባል በማንኛውም ጊዜ በ+491767269094 የሞባይል ስልክ ቁጥር እና በ berlin.embassy@mfa.gov.et ኢሜይል አድራሻ በመጠቀም ኤምባሲውን እንዲያገኙ እና እንዲመካከሩ አሳስቧል፡፡

በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው እንዲገቡ በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳይገጥማቸው ክትትል እያደረገ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።በዚህም በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው መግባት እንዲችሉ ከፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተነጋግሮ ማስፈቀዱን አስታውቋል።
በመሆኑም በታቸለ ፍጥነት በዩኩሬን የሚኖሩ እና ወደ ድንበር ጉዞ በማድረግ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ግዛት በመግባት በተቻለ ፍጥነት ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓዙ አሳስቧል።

የሩሲያ ጦር ወደ ዩክሬን መዲና ከዬቭ መግባቱን የዩክሬን ባለስልጣናት ገለፁ!
የሩሲያ ኃይሎች የዩክሬንን ዋና ከተማ ኪዬቭን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የዩክሬን መከላከያ ኃይል ማንኛውም ዜጋ እንዲዋጋ በትዊተር ገጹ ጥሪ አቅርቧል።
የወታደሮቹ አዛዥ መግለጫ በዚህ ውጊያ "የእድሜ ገደቦች የሉም" ብሏል- ይህም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችም ትግሉን እንዲቀላቀሉ ሊፈቀድ እንደሚችል ያሳያል ተብሏል።
ነገር ገን የመከላከያ ሚኒስትሩ አሌክሲ ሬዝኒኮቭ ባወጡት አዲስ መግለጫ የዕድሜ ገደብ የለውም ሲባል ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ የዕድሜ ባለጸጎችን እንደሆነም ጠቁሟል። በዚህ መግለጫ ላይ ዕድሜያቸው ያልደረሰ ታዳጊዎችን አይጠቅስም።
"ከዩክሬን ጦር ኃይሎች ጦር አዛዥ ጋር በመስማማት ከ60 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች በአርበኞች ሰራዊት እንዲሳተፉ ወስነናል። ይህ ጥሪ በአካልም ሆነ በሞራል ዝግጁ የሆኑትንና ጠላትን ለማሸነፍ የተነሳሱትን ሁሉ የዕድሜ ባለጸጎች ይመለከታል" በማለት የመከላከያ ሚኒስትሩ አስፍረዋል።
Via BBC

ፕሬዝዳንት ፑቲን ተደራዳሪ ልዑካንን ወደ ቤላሩስ ለመላክ መዘጋጀታቸው ተሰማ!
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጦርነቱ ጉዳይ ከዩክሬን ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸው ተሰማ፡፡ፑቲን ከዩክሬን ተወካዮች ጋር የሚደራደር ልዑክ ወደ ቤላሩስ ሚኒስክ ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ልዑኩ የመከላከያ፣ የውጭ ጉዳይ እና ከፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት (ክሬምሊን) የተውጣጡ አካላትን ሊያካትት እንደሚችልም ነው የተነገረው፡፡ሩሲያ ለድርድር የምትቀመጠው የዩክሬን ጦር ትጥቅ ሲያወርድ ብቻ መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሰርጌይ ላቭሮቭ በኩል አስታውቃለች፡፡
[Alain]

በአዲስ አበባ ያለሀኪም ማዘዣ የሚሸጡ መድኃኒቶች መበራከታቸዉ ተሰማ!
በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በአዲስ አበባ በሚገኙ የመድሃኒት ተቋማት ላይ በተደረገ ቁጥጥር መድሃኒትን በኮንትሮባንድ በማስገባት፣በደህነነትና ፈዋሽነት ላይ ችግር የሚያመጡ እንዲሁም ያለ ሃኪም ትእዛዝ መድሃኒቶችን ሲሸጡ በተገኙ 53 መድሃኒት ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡
እርምጃ ከተወሰደባቸዉ መካከል 39 የሚሆኑት መድሃኒት ቤቶች የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸዉ ሲሆን 19ኙ ደግሞ እንዲታሸጉ መደረጋቸውን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አምደየሱስ አድነው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ያለ ሃኪም ትእዛዝ የሚሸጡ መድሃኒቶች መበራከታቸውን የገለጹ ሲሆን መድሃኒት የተላመዱ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስፋፉ ማድረጉን ገልጸዋል፡፤ይህ ሁኔታም በዚሁ ከቀጠለ የበሽታዎችን ስርጭት ለመቆጣጠር አዳጋች እንደሚያደርገውና የዜጎችን የጤና ሁኔታ ስጋት ላይ እንደሚጥል አክለዋል፡፡
በሌላ በኩል ፍቃድ አውጪ አካላት በስፍራው አለመገኘታቸው እና ለሌላ ሰው እውቅና በመስጠት መድሃኒቶችን በዚህ መልኩ እንዲሸጡ ማድረጋቸው ችግሩንም እንዳባባሰው አቶ አምደየሱስ አድነው አክለዋል፡፡ እነዚህንና ሌሎች ምክኒያቶችን መነሻ በማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባደረገው የቁጥጥር ስራ የተለያዩ የአስተዳደር እና ሌሎች እርምጃዎችን ወስዷል፡፡
Via Bisrat FM

በጎንደር ከተማ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ በጫነ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የሁለት ፖሊስ አባላት ህይወት ማለፉን ፖሊስ አሳወቀ፡፡
የፍንዳታው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ያሳወቀው ፖሊስ፥ ፍንዳታው ከቦምብ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረም ገልጿል፡፡የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ከጭልጋ መስመር ህገወጥ ጥይት የጫነ የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ በአዘዞ የፍተሻ ኬላ አምስተኛ ዋና ፓሊስ ጣቢያ በፖሊስ አበላት እየተፈተሸ ባለበት ወቅት ነው ፍንዳታው የደረሰው።
በፍንዳታው ሁለት የፖሊስ አባላት ህይወታቸው ማለፉን የተናገሩት ኮማንደሩ፥ ሰባቱ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።በጣቢያው የነበሩ ሁለት ሲቪል ሰዎችም የፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፥ ወደ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
Via FBC

መንግስት የነዳጅ ዋጋ እስከ መጋቢት 30 ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን አስታወቀ!
መንግስት የነዳጅ ዋጋ ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።ውሳኔው ከቀላል ጥቁር ናፍጣ፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ከአይሮኘላን ነዳጅ በስተቀር በሌሎች የነዳጅ ዓይነቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑም ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው።
ይህም የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።በዓለም ገበያ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑን የጠቆመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መንግስት የነዳጅ ምርት ከገዛበት ውድ ዋጋ በግማሽ ለህብረተሰቡ በሽያጭ እያስተላለፈ ይገኛል ብሏል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ምርቱን በከፍተኛ ቁጠባ የመጠቀም እንዲሁም የብዙሃን ትራንስፖርትን የመጠቀም ልምድ ሊያዳብርና በነዳጅ ምርቶች ግብይት ላይ የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ከፀጥታ አካላትጋር በትብብር ሊሠራ እንደሚገባ ለኢቲቪ በላከው መግለጫ አሳስቧል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዩናይትድ ኪንግደም ታንክ ኮንቮይ ወደ ሩሲያ ድንበር ወደምትገኘው የኔቶ ሀገር አቀና
የእንግሊዝ ጦር ኮንቮይ ወደ ባልቲክ ሀገር ኢስቶኒያ ገብቷል። (ስካይ ኒውስ)

የሰሜን ኮሪያው መሪ 2022 የግሪጎሪያን የዘመን መቁጠሪያን በአያታቸው የልደት ቀን ተኩ!
ሀገሪቱ የግሪጎሪያን አቆጣጠርን ከቀን አቆጣጠር ስርዓቷ ያወጣች ሲሆን፤ አሁን ያለንበትን የፈረንጆቹን 2022 ዓመትንም ሰርዛለች።በዚህም መሰረት ሰሜን ኮሪያውያን በ2022 ምትክ “ጁች 111” የሚል የቀን አቆጣጠር መጠቀም መጀመራቸውም ነው የተነገረው።
አዲሱ የሰሜን ኮሪያ “ጁች” የዘመን መቁጠሪያ የሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያ መሪ በሆኑት ኪም ኢል ሱንግ የልደት ቀን የሚጀመር ሲሆን፤ የዘመን መቁጠሪያው የመጀመሪያ ዓመትም የፈረንጆቹ 1992 ነው ተብሏል።

የሱማሊያ ጦር ሠራዊት ትናንት 29 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገድያለሁ ማለቱን ዥንዋ ዜና ምንጭ ዘግቧል። ታጣቂዎቹ የተገደሉት ከሞቃዲሾ በስተደቡብ ባንድ የመንግሥት ኃይሎች ወታደራዊ ጦር ሠፈር ላይ ድንገተኛ ጥቃት በሰነዘሩበት ወቅት ነው። አልሸባብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሞቃዲሾ እንዲሁም በደቡባዊ እና ማዕከላዊ ሱማሊያ በመንግሥት ተቋማት እና በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ጦር ሠፈሮች ላይ የሚፈጽማቸውን ተደጋጋሚ ጥቃቶች አጠናክሮ ቀጥሏል።
[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ዜሌንስኪ ከአገር እንዲወጡ በአሜሪካ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ!
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ ከአሜሪካ የቀረበላቸውን የድጋፍ ጥያቄ ሳይቀበሉት መቅረታቸው ተዘገበ።
ፕሬዝዳንቱ "ውጊያው ያለው እዚህ ነው። የምፈልገው የጦር መሳሪያ እንጂ የማምለጫ መንገድ አይደለም" ማለታቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ጉዳዩን የሚያውቁ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል።
ዋሽንግተን ፖስት የአሜሪካና የዩክሬን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ለመርዳት ተዘጋጅታ ነበር።
ፕሬዝዳንቱ የሩሲያን ወረራ ተከትሎ በወሰዱት አቋም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ሲወደሱ ቆይተዋል።የቀድሞው ኮሜዲያንና ተዋናይ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ባደረጉት ንግግር “ጥቃት ስትፈጽሙብን ፈት ለፊት እንጋፈጣችኋለን እንጂ አንሸሽም” በማለት አገራቸውን ከወረራው ለመከላከል ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
[BBC]

ሕወሓት በታች አርማጭሆ አካባቢ ሰዎችን ወደ ሱዳን እያስወጣ መሆኑ ተገለጸ!
ሕወሓት በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ቀበሌ ለሚገኙ ድንበር ጠባቂ የፀጥታ አካላት ገንዘብ በመክፈል ሠዎችን ለሥልጠና ወደ ሱዳን መላኩ ተሰማ፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የሕወሓት ቡድን፣ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ቀበሌ ለሚገኙ ለቀበሌ፣ ለፌደራል ፖሊስና ለጉምሩክ ድንበር ጠባቂ የፀጥታ አካላት በአንድ ሰው ከ120 ሺሕ ብር በላይ ገንዘብ በመክፈል፣ ከአንድ ሳምንት በፊት ከ60 በላይ ሠዎችን ለሥልጠና ወደ ሱዳን ማስወጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ጠቁመዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ሕወሓት ከአንድ ሳምንት በፊት ሠዎችን በ‹ሲኖትራክ› ጭኖና በታጣቂዎቹ አሳጅቦ ወደ ሱዳን ያስወጣ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ የወጡት እነዚህ ሠዎች ሱዳን ከሚገኘው “ሳምሪ” ከተባለው የሕወሓት ቡድን ጋር ሳይቀላቀሉ እንዳልቀሩ ተጠቁሟል፡፡
Via Addis Maleda

በወልድያ በደረሰ የእሳት አደጋ የአባት ፣ የእናት እና የህጻን ልጅ ህይወት አለፈ፡፡
በከተማዋ በ06 ቀበሌ በተለምዶ ጎማጣ ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር አካባቢ የካቲት 18 ለ19/2014 ዓ.ም ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ የአባት፣ እናት እና ህጻን ልጃቸውን ጨምሮ ለሞት ሲዳርግ ፥ ሦስት ሰዎች ደግሞ በቃጠሎው አደጋ ደርሶባቸዋል።ሦስቱ ቁስለኞች በወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።ፖሊስ የእሳት አደጋው መንስኤ እና በንብረት ላይ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት በማጣራት ላይ እንደሆነ ከከተማው ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።