YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢህአፓ የትግራይ ክልል በወታደራዊ ዕዝ እንዲተዳደር ጠየቀ!

ፓርቲው በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባወጣው የአቋም መግለጫ ህወሓት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋሚ አደጋ እንዳይሆን ለማረጋገጥ፤ እንዲሁም ሁኔታዎች እስኪረጋጉና የአሸባሪው ቡድን ወኪሎች እስኪለዩ ድረስ ትግራይ ክልል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በወታደራዊ ዕዝ ማስተዳደር ይገባል ብሏል፡፡

ኢህአፓ ከዚህ ባሻገርም ምርኮኞች፣ የታሰሩ የህወሓት ደጋፊወች እና አባላት ህግን በተከተለና የሰብዓዊ መብትን በተላበሰ ሂደት ጉዳያቸው እየታየ የተቀላጠፈ ሕጋዊ ውሳኔ እንዲያገኙም ጠይቋል፡፡ከሕግ ውጪ በበቀል ተነሳስቶ በማንም ግለሰብ ላይ በደል እንዳይደርስ ጥረት ማድረግ እንደሚያሻም ፓርቲው አስታውቋል፡፡

በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች የተፈናቀሉትን ወገኖቻችንን በአስቸኳይ መልሶ ማቋቋም፣ እንዲሁም በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ለሚጀመረው የእርሻ ጊዜ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግና ድጋፍ መስጠት እንደሚገባም ፓርቲው ጠቁሟል፡፡

ከ45 ዓመታት በላይ ህወሓትን የታገልኩ ፓርቲ ነኝ ያለው ፓርቲው፤ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ሕዝብዊ ግንኙነቱ ወደ ነበረበት እንዲመለስ የሚያስችል መዋቅራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ ኢኮኖሚያዊ ይዘት ያለው ግብረኃይል በመመስረት ተጨባጭና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ያስፈልጋሉ ብሏል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
ለ6 ወራት ተዘግቶ የነበረው የኢትዮ-ሱዳን መንገድ ከነገ ጀምሮ ሊከፈት መሆኑ ተገለጸ!

የመተማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብቴ አዲሱ ለአል ዐይን አማርኛ እንደተናገሩት ሐምሌ 17፣2013ዓ.ም የመተማ-ጋላባት መንገድ በሱዳን በኩል ተዘግቶ ነበር፡፡ የሱዳን መንግስት መንገዱን የዘጋው አንድ ወታደራዊ አመራር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ተገድሎብኛል ብሎ በማሰቡ መሆኑን አቶ ሀብቴ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ማምሻውን ኤርትራ ገብተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስመራ ሲደርሱም የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በጉብኝታቸው ከኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በሌላ ዙር ጉዞ ሐሙስ ዕለት ለጉብኝት ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተዘገበ።

አንድ የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ፌልትማን ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመወያየት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለውን ግጭት ለማብቃት ግፊት ያደርጋሉ ተብሏል።አንድ ዓመት ያስቆጠረውን ደም አፋሻሽ ጦርነት ለማስቆም በሚደረገው ጥረት እንዲያግዙ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተሰየሙት ጄፍሪ ፌልትማን ባለፉት ወራት በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያና ወደ አካባቢው አገራት መመላለሳቸው ይታወሳል።

ሐሙስ ታኅሣሥ 28/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ የሚገቡት ፌልትማን "የሰላም ንግግርን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር" እንደሚወያዩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ከፍተኛ ኃላፊው መናገራቸው ተዘግቧል።ጦርነቱ በተባባሰበትና የህወሓት ኃይሎች ግስጋሴ በተጠናከረበት ጊዜ ቱርክንና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስን ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳንና ግብፅ በተደጋጋሚ የተመላለሱት ጄፍሪ ፌልትማን መንግሥትና አማጺያኑ ለንግግር እንዲቀመጡ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ወደ አዲስ አበባ በተደጋጋሚ የተመላላሱት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ባሻገር ከህወሓት ተወካዮች ጋር ኬንያ ውስጥ መነጋገራቸውን ከዚህ ቀደም ገልጸው ነበር።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ኦሮሚያ ከአንድ ሺህህ 800 በላይ የሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን የምዕራብ ዕዝ ኦሮሚያ ልዩ ኃይል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ጋሊ ከማል ገለፁ።

ረዳት ኮሚሽነር ጋሊ ለኢትዮጵያ ፕሬስ እንደገለጹት፤ በምዕራብ ኦሮሚያ ላይ በተለያየ ጊዜ በታቀደ መልኩ በተካሄደ ዘመቻ በአንድ ሺህ 836 በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎች ላይ እርምጃ ተወስዷል።

ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሺህ 643 የጠላት ታጣቂዎች መገደላቸው፣ 106 የሚሆኑት ደግሞ እጅ የሰጡ መሆናቸውና 87 የሚደርሱ የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎች ደግሞ መያዛቸውን ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የዲጂታል መታወቂያ ህትመትና ስርጭት በክፍለ ከተማ ደረጃ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራ መሆኑ ተነገረ!

የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ እንደገለጸው፣ የአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በማዕከል ደረጃ በማህተም ለሁሉም ክፍል ከተማ ሲያሰራጭ የነበረውን አሰራር ቀይሮ ህትመቱ በከተማ ባሉ በሁሉም ክፍለከተሞች ደረጃ ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቱ አንድ ነዋሪ አንድ የነዋሪነት መታወቂያ ብቻ እንዲኖረዉ ማድረግ እንደሚያስችል አስታውቋል::

ይህ ስርዓት ለነዋሪዎች የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ላይ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑንም ኤጀንሲው አስታውቋል::

ኤጀንሲው አገልግሎቱን ወደ ስራ ከማስገባቱ አስቀድሞ ለሁሉም ክፍለ ከተማ የነዋሪዎች አገልግሎት ባለሙያዎች ስልጠናን መስጠቱንም አስታውቋል::

ህትመትና ስርጭት ወደ ክ/ከተማ መውረዱ ተገልጋዩ ህብረተሰብ የመታወቂያ ህትመት ለመውሰድ የሚፈጅበትን ጊዜ እና ገንዘብ እንደሚያስቀርም ተጠቁሟል::

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በ2014 ዓመት መታወቂያቸውን ማደስ ሲኖርባቸው ያላደሱ ነዋሪዎች አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ተፈቀደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት የከተማውን የአገልግሎት ሁኔታ ለማሻሻል ሲባል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት መታወቂያቸውን ማደስ ሲኖርባቸው ያላደሱ ነዋሪዎች በመታወቂያቸው አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ መደረጉን በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በተለይ ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

የነዋሪነት አገልገሎት፣መሸኛ፣መታወቂያ ማደስ ፣በጠፋ ምትክ መውሰድ አገልግሎት በመቆሙ የተነሳ ተገልጋዮች ቅሬታ ማቅረባቸውን ተከትሎ ፍቃዱ ሊሰጥ መቻሉን አንስተዋል፡፡

ከተከለከሉ የአገልግሎት አይነቶች ውጪ በ2014 ዓ.ም መታወቂያቸውን ማደስ ሲኖርባቸው ያላደሱ ነዋሪዎች ከታህሳስ 21 ቀን2014ዓ.ም ጀምሮ በነዋሪነት ቅፅ ላይ መኖራቸው ተመሳክሮ እና በቅፅ 02 የግል መረጃቸውን አለመቀየራቸው ተረጋግጦ በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ተፈቅዷል፡፡በዚህም መሰረት የልደት፣የጋብቻ ፣የሞት እና መሰል የምስክር ወረቀት አገልገሎትን ነዋሪዎች ማግኘት ይችላሉ፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል የተከሰተው ድርቅ ዜጎችን ለሞት እየዳረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አብዱልቃድር ረሺድ በድርቁ ምክንያት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ለአሐዱ አረጋግጠዋል፡፡በጥቅምት መዝነብ የነበረበት ዝናብ ባለመዝነቡ በክልሉ የሚገኙ 9 ዞኖች ለድርቅ ተጋልጠው የነበረ ሲሆን አሁን ድርቁ ወደ 10ኛው ዞን መሸጋገሩን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በተለይም በክልሉ 4 ዞኖች በዳዋ ፣ አፍዴራ፣ ሸበሌ እና ቆራሔ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት 1 መቶ 46 ሺሕ 8 መቶ 6 እንስሳት መሞታቸውን ገልፀዋል፡፡

በድርቁ የሚሞቱ እንስሳት ቁጥር በቅርብ ቀናት ሊጨምር እንደሚችል ስጋት መኖሩንም ጠቅሰው ፤ በድርቁ የተነሳም በክልሉ የሚገኙ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ሕዝብ ለችግር መጋለጡን አስረድተዋል፡፡በሚያዚያ የሚጠበቅ ዝናብ እንዳለ የገለፁ ሲሆን ዝናብ ካልዘነበ ድርቁ ከዚህም በላይ የከፋ እንደሚሆንና በርካታ ዜጎችን ሊያሳጣ እንደሚችል ስጋት መኖሩን ተናግረዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ በአሸባሪው ህወሃት ተጨፍጭፈው በተለያየ ቦታ የተቀበረውን ከ200 በላይ አስክሬን በማውጣት በአንድ ስፍራ ላይ የመቅበር መርሃግብር ሊካሄድ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተናገሩ።

የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪው አቶ የአለም ፋንታሁን የህወሃት ታጣቂዎች በዞኑ ዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር መጨረሻ ከ200 በላይ ሰዎችን ጨፍጭፎ ከአካባቢው መሸሹን አስታውሰዋል፡፡አስተዳዳሪው የአካባቢው ማህበረሰብ ቤቱ የቀብር ስፍራ ሆኖበታል፤ በየደጃፉ ላይ አስክሬን ተቀብሮበታል፡፡ይህንን ከየቤቱና ከየደጃፉ በመልቀም ወደ አንድ ቦታ ለማምጣት ታስቧል ሲሉ አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው አቶ የአለም በአሁኑ ሰዓት አርሶ አደሩ አዝወረውን እየሰበሰበ ሳለ ድንገት አስክሬን ያገኛል፤ ህጻናት ደግሞ እንጨት ሲለቅሙ እንዲሁ አስክሬን ያገኛሉ ብለዋል፡፡በወቅቱ ወራሪው ይዞት የመጣው 9 ክፍለ ጦር በመሆኑ ከዚህ ውስጥ አብዛኛው በመገደሉ የአስክሬኑ ቁጥር ከፍ ያለ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ይህንን ብዛት ያለውን በየቦታው ያለውን አስከሬን በማሰባሰብ በአንድ ቦታ እንዲያርፍ የሚደረገውም የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ከመጡት ዲያስፖራዎች ጋር መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር ተያያዝ በቁጥጥር ከዋሉት ውስጥ ይቅርታ የጠየቁ በርካታ ሰዎች እንዲለቀቁ ተደርጓል- መንግስት

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር ተያያዞ በቁጥጥር ከዋሉት ውስጥ ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ የጠየቁ በርካታ ሰዎች እንዲለቀቁ መደረጉን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ ከተለያዩ የሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ የተጠረጠሩ ሰዎችን የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ይታወሳል፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሠ ቱሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በጸጥታ አካላት ተጠርጥረው ከታሰሩት ውስጥ የጥፋት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆነና መንግስት ከጥፋታቸው ተገቢውን ትምህርት ወስደዋል መንግስት ጉዳዩን በሆደ ሰፊነት አይቶ የለያቸው በርካታ ሰዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ አድርጓል ብለዋል፡፡

የቀሩትም እንደ ሁኔታው የጥፋት ደረጃቸው እየታየ ቀጠይ የሚለቀቁ እንደሚሆን ገልጸው፤ቁልፍ የችግሩ ተዋንያን የሆኑት ደግሞ ጉዳያቸው ተጣርቶ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

የመንግስት ዓላማ አስተማማኝ፣ ዘላቂ ሠላም አስፍኖ የህግ የበላይነት እንዲረጋጋጥ ማስቻል ነው ያሉት ዶክተር ለገሠ፤ ይህንን የሚገዳዳር ማናቸውን እንቅስቃሴዎች ከህግ ተጠያቂነት አያመልጥም ሲሉም ገልፀዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በሌላ ዙር ጉዞ ሐሙስ ዕለት ለጉብኝት ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተዘገበ። አንድ የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ፌልትማን ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመወያየት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለውን ግጭት ለማብቃት ግፊት ያደርጋሉ ተብሏል።አንድ ዓመት ያስቆጠረውን…
#Update

ነገ አዲስ አበባ ይመጣሉ ተብሎ የሚጠበቁት በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ከሃላፊነታቸው ሊለቁ ነው ተባለ፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ተደጋጋሚ ጉዞዎችን ያደረጉት ፌልትማን ከዘጠኝ ወራት የስልጣን ቆይታ በኋላ እንደሚለቁ ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በነገው እለት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ቢባልም ዛሬ ስልጣን እንደሚለቁ ይፋ ተደርጓል፡፡ሮይተርስ ይህንን ይበል እንጅ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየት አልሰጠም ተብሏል፡፡ጄፍሪ ፌልትማን በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመምከር ግብፅ፣ ዩኤኢ እና ቱርክ መጓዛቸው የሚታወስ ሲሆን እርሳቸውን ይተኳቸዋል ተብለው የሚጠበቁት ደግሞ በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደርነት ጊዜያቸውን የጨረሱት ዲፕሎማት ናቸው፡፡

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
ጠ/ሚር ዐቢይ እና ሚኒስትሮች የታላቁ ኅዳሴ ግድብን የግንባታ ሂደት ጎበኙ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የታላቁ ኅዳሴ ግድብን የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡በጉብኝት መርኃ ግብሩ የተለያዩ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ሚኒስትሮች መሳተፋቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡የሁሉም ሚኒስቴሮች የ100 ቀናት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በኅዳሴ ግድብ መገኛ በሆነችው ጉባ እየተካሄደ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ሰዓት እላፊ ላይ የመወሰን ሥልጣን ለከተማ አስተዳደሮች ተሰጠ!

የአማራ ክልል ምክር ቤት የሰዓት እላፊ ገደብን የማንሳትም ሆነ የማሻሻል መብትን ለከተማ አስተዳደሮች ሰጠ።እስከዛሬ ከምሽቱ 4፡00 እስከ ንጋቱ 11፡30 መንቀሳቀስ እንደማይቻል ውሳኔ ተላልፎ ሲተገበር ቆይቷል።ይሁን እንጂ አሁን ያለውን ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት በዛሬው እለት የሰዓት እላፊ ገደቡን በተመለከተ አስተዳደር ምክር ቤቱ ውይይት አድርጎ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡\በዚህም ከአሁን ቀደም ተጥሎ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ሙሉ ኃላፊነት ለከተማ አስተዳድሮች በመስጠት የፀጥታ ሁኔታውን እየገመገሙ በራሳቸው ሰዓት እላፊ ገደቡን የማንሳትም ሆነ የማስቀጠል ሙሉ ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር የተሰጣቸው መሆኑን ይፋ አድርጓል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

@YeneTube @FikerAssefa
ተማሪ ሐይማኖት በዳዳን በስለት የገደለው ወጣት በ21 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ!

የ4 ኛ አመት ህክምና ተማሪ የነበረችውን ሀይማኖት በዳዳን በመግደል ወንጀል ጥፋተኛ የተባለው ደግነት ወርቁ በዕርከን 36 መሰረት በ21 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በፍርድ ቤት ተወስኗል።የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1 ኛ የከባድ ግድያና የውንብድና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሽ ደግነት ወርቁ በግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ/ ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት አካባቢ የ4ኛ አመት ህክምና ተማሪ የነበረችው ሀይማኖት በዳዳ በጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፋርማሲ ላብራቶሪ ክፍል ስትገባ ተከሳሹ ተከትሎ በመግባትና የክፍሉን በር ከውስጥ በመቆለፍ ያለሽን አምጪ ብሎ በማስፈራራት ቦርሳዋን አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ላፕቶፕ ኮምፒዩተር በመቀማትና አይፎን ሞባይል ስልኳን ፖተርን አልከፍትም ስትለው መሬት ላይ ገፍትሮ በመወርወር በደረቷና አንገቷን በስለት ቢላ በአሰቃቂ መልኩ ጥቃት በማድረስ ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጎል ሲል ዓቃቢህግ በ1996 ዓ/ም የወጣውን የወንጀል ህግ 671 ንዑስ ቁጥር 2 ስር ያለውን ድንጋጌ በመተላለፍ በከባድ ውንብድና ወንጀል ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

በጊዜ ቀጠሮ ምርመራ ወቅት ወንጀሉን መፈጸሙን አስረድቶ የነበረው ተከሳሽ ደግነት ወርቁ ክሱ ከደረሰው በኋላ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ማለቱን ተከትሎ ከሳሽ ዓቃቢ ህግ ወንጀሉን ለመፈጸሙ የሚያስረዱ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ ማሰማቱ ይታወሳል።ማስረጃውን የመረመረው ፍርድ ቤቱ እንዲከላከል በሰጠው ብይን ላይ መከላከያ ማስረጃ የለኝም ሲል ምላሽ መስጠቱን ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱም በቀረበው ማስረጃ የግድያ ወንጀሉን መፈጸሙን ተረጋግጧል ሲል በጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ/ም የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎበት ነበር።

ተከሳሹ የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ካለው እንዲያቀርብ የተጠየቀ ሲሆን ማቅለያ ማቅረብ እንደማይፈልግ መግለጹን ተከትሎ አስቦበት የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርብ በተሰጠው ዕድል ለሶስት ጊዜ በእረጅም ተለዋጭ ቀጠሮ በአርባምንጭ አካባቢ የኤች አይቪ ባህላዊ መድሐኒት የፈጠራ ዕውቅና ማስረጃ እንዳለው እና የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለው ማስረጃ አቅርቧል።

በተጨማሪም በአርባምንጭ ዩንቨርስቲ በአትክልተኛነት መስራቱን ማስረጃ አቅርቦ ነበር።

ከሳሽ ዓቃቢህግም ጭካኔ በተሞላው መልኩ ወንጀሉን መፈጸሙን ተከትሎ ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ በመውጣት በዕድሜ ልክ ዕስራት ይቀጣልኝ ሲል የቅጣት ማክበጃ አስተተያየት በጥቅምት 16 ቀን 2014ዓ/ም ማቅረቡ ይታወሳል።

ይሁንና ፍርድ ቤት በድጋሚ ለቅጣት ውሳኔ ለዛሬ በሰጠው ቀጠሮ በተሟላ ዳኛ ተሰይሞ ዓቃቢህግ በዕድሜ ልክ ዕስራት ይቀጣልኝ ሲል ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ውድቅ አድርጎታል።

የተከሳሹን የባህላዊ መድሐኒት ፈጠራ ውጤት ማስረጃና የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለበት የቀረበ የቅጣት ማቅለያን በመያዝ በዕርከን 36 መሰረት በ21 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ሰቷል።ለአራት አመት ከመራጭነት መብትና ከህዝባዊ መብቱ እንዲታገድ ትዛዝ ተሰቷል።ይግባኝ መብት መሆኑም ተገልጿል።ከውሳኔው በኋላ የሟች ሀይማኖት ወላጅ አባትና እናት እንዲሁም ሌሎች ቤተሰቦች በፍርድ ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ እያለቀሱ ተስተውሏል።

Via Tarik Adugna
@YeneTube @FikerAssefa
የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የስራ ዘመኑ እንዲራዘም ጥያቄ አቀረበ!

የስራ ዘመኑ በዚህ ዓመት የሚጠናቀቀው የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን፤ የስራ ጊዜው ለተጨማሪ ሶስት ዓመታት እንዲራዘም ለሰላም ሚኒስቴር ጥያቄ አቀረበ። ኮሚሽኑ የስራ ዘመኑ እንዲራዘም ጥያቄ ያቀረበው፤ እያከናወናቸው ያላቸውን ጥናቶች “በጊዜ አጠናቅቆ መጨረስ ባለመቻሉ” መሆኑን የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወል ሁሴን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ከአስተዳደር ወሰኖች፣ ራስን በራስ ከማስተዳደር እና ከማንነት ጋር የተያያዙ ግጭቶችንና መንስኤዎቻቸውን በመተንተን የመፍትሔ ሃሳቦችን ለሚመለከታቸው አካላት እንዲያቀርብ በየካቲት 2011 የተቋቋመው ይህ ኮሚሽን፤ የስራ ዘመኑ ሶስት ዓመት እንደሚሆን በአዋጅ ተደንግጓል። ሆኖም የኮሚሽኑ የስራ ዘመን “እንደ ሁኔታው” ታይቶ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊራዘም እንደሚችል በአዋጁ ላይ ተቀምጧል።

በማቋቋሚያ አዋጁ መሰረት የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የነበረ ቢሆንም፤ ከሶስት ወራት በፊት የጸደቀው የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ግን ይህን በመቀየሩ የስራ ዘመን የማራዘም ጥያቄው የቀረበውም ይህንኑ ተከትሎ መሆኑን አቶ አወል ገልጸዋል። በአዲሱ አዋጁ መሰረት የኮሚሽኑን ተጠሪነት የተላለፈው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሰላም ሚኒስቴር ነው።

Via Ethiopian Insider
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግስት የልማት ድርጅቶች በአላትን አስታከው የተለያዩ ስጦታዎችን በማበርከት ሀብት እንዳያባክኑ ተከለከሉ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ለየመንግስት የልማት ድርጅቶች በፃፈው ደብዳቤ ነው ክልከላውን ያሳወቀው፡፡ክልከላው ሃብትን በቁጠባ መጠቀምን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ለልማት ድርጅቶች ከተፃፈላቻ ደብዳቤ ሸገር ተመልክቷል፡፡የልማት ድርጅቶች በአላትን እያስታከኩ አጋሮቻችን በሚል ለግለሰቦች እና ለተለያዩ ተቋማት ስጦታ የማበርከት ልማዳቸውን እንዲያቆሙ የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቃል፡፡

በኮሮና በጦርነት እና በተለያዩ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጫና ውስጥ መሆኑን የጠቀሰው የገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ ጫናውን ተቋቁሞ ልማቱን ለማስቀጠል እንዲህ ያሉ ሀብት የሚባክንባቸው ልማዶችን ከማስቆም ጀምሮ የለተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈልጓል ብሏል፡፡

እንደየ ተቋማቱ ቢለያይም በተለያዩ የበዓላት ጊዜ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከስጦታ ካርድ ጋር ውስኪና ወይንን ጨምሮ የተለያዩ ስጦታዎችን ለግለሰቦችና ለተቋማት በስጦታ የማበርከት ልማድ እንደነበራቸው ተሰምቷል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የ2014 በጀትን ለመደገፍ ከውጪ ምንጮች ይገኛል ተብሎ የታሰበው ገንዘብ በዚህ ዓመት ላይገኝ ስለሚችል በጀትን ከብክነት በፀዳ መልኩ እና በቁጠባ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ለመንግስት ተቋማት ማሳሰቢያ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

[Sheger]
@YeneTube @FikerAssefa