የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የፓርቲውን ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋ አደረጉ፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐብይ አህመድ የፓርቲውን ማንፌስቶ እና የመወዳደሪያ ምልክት ዛሬ በይፋ ማስተዋወቃቸውን ከብልጽግና ፓርቲ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
Photo: EPA
@YeneTube @FikerAssefa

በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን በአባ ወረዳ በ48 ሚሊዮን ብር ወጪ አዲስ ባለ 132/33 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሊገነባ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሰብስቴሽንና ትራንስሚሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ገዛኽኝ እንደገለፁት 1998 ዓ.ም. ተገንብቶ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የአባ ባለ 132/33 ኪ.ቮ. ማከፋፈያ ጣቢያ በ2012 ዓ.ም. በደረሰበት የመሬት መሸራተት የተነሳ አገልግሎት አቋርጧል፡፡በመሆኑም ችግር የገጠመውን ማከፋፈያ ጣቢያ በአዲስ ባለ132/33 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለመተካት መወሰኑን ተናግረዋል፡፡አካባቢው ኃይል እንዳያጣ አደጋው በደረሰበት ወቅት ተቀሳቃሽ (የሞባይል) የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በጊዜያዊነት መተከሉን ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል፡፡
ተንቀሳቀሽ ማከፋፈያ ጣቢያው ባሉት 3 ባለ 33 ኪ.ቮ. ወጪ መስመሮች ለዳወሮ እና ለኮንታ ዞኖች ኃይል እየሰጠ ይገኛል።የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የሚገኝበት ቦታ የኦሞ ሸለቆ ውስጥ የሚገኝበት በመሆኑ ተደጋጋሚ የመሬት መሸራተት የሚከሰትበት አስቸጋሪ ቦታ ነው ፡፡
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም በተደረገው የአፈር ጥናት ከነባሩ ማከፋፈያ ጣቢያ በ18 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ልዩ ስሙ ቦሪቃ በሚባል አለታማ ቦታ ላይ አዲስ ማከፋፈያ ለመገንባት የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ዳሬክተሩ አብራርተዋል፡፡የግንባታ ሥራው በተቋሙ የራስ ኃይል በሁለት ዓመት ያልቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡አባ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ከአዲስ አበባ በ451 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
[EEPCo]

በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የሶስት ሰው ህይወት አለፈ፡፡
በአዲስ ትናንት እና ከትናንስ በስቲያ በተለያዩ ቦታዎች በተከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎች የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገልጿል።
የመጀመርያው የሞት አደጋ የተከሰተው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት የ29 አመት ሴት ልጅ ወንዝ ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል፡፡
ሌላው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ሁለት ወጣት ወንዶች ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሂወታቸው ማለፉን የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በተያያዘ ዜና በከተማዋ በደረሱ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች በሁለት ሰዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ መድረሱን ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል፡፡
በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት በመኖርያ ቤት እና በሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ ሁለት ወጣቶች በአደጋው ከባድ ቁስለት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡
በዚሁ አደጋ ምክንያትም ሁለት ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት የወደመ ሲሆን 12 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
[Ethio FM]

ስለ ፀጥታ እና ደህንነት ምክክር እየተደረገ ነው!
ተጎራባች ክልሎች በሰላም እና ፀጥታ እንዲሁም ደህንነት ላይ ያተኮረ ውይይትና ምክክር በድሬደዋ ከተማ እያካሄዱ ሲሆን በዚህ ጉባዔ ላይ የአፋር፣ የሶማሌ፣ የኦሮሚያ፣ የሃረሪ ክልሎች እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኃይሎች በአሁናዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ምክክር እያደረጉ ነው ተብሏል።
በጉባዔዉ ላይ የተገኙት የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮምሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ “በቀጣናው አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን፣ አልሸባብንና ሌሎች ፀረ-ሰላም ሃይሎችን ከመቆጣጠር አንፃር፣ ህገ-ወጥ የመሳሪያና የሰዎች ዝውውር እንዲሁም ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ኃይሉ ያለው ዝግጁነት ይዳሰሳል” ብለዋል፡፡
እንዲሁም አጠቃላይ ከአዳማ እስከ ጅግጅጋ – ጅቡቲ ያለውን እንቅስቃሴ ሰላማዊ ከማድረግ አንፃር እየተከናወኑ ያሉ የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን በተመለከተ ውይይት እንደሚደረግም ነው የተገለጸው፡፡ በውይይቱ ላይ የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያና የክልሎች ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቪል ባለስልጣናት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
[@AddisZeybe]

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት ግርማ ሞገስ ለገሰ ትላንት እሑድ የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው አልፏል።
የኢዜማ አባላት እና አመራሮች ይህን ዜና ስንሰማ ከፍተኛ ሐዘን ተሰምቶናል ብለዋል።
ኢዜማ በአባሉ ላይ የተፈፀመውን የግድያ ወንጀል በፅኑ ያወገዘ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሰብስቦ እንደጨረሰ ዝርዝር ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።
ፓርቲው ለግርማ ሞገስ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና የትግል አጋሮች ልባዊ መጽናናትን ተመኝቷል።
@Yenetube @Fikerassefa

ለሱዳናዊያን የዳቦ ጥያቄ አዲስ ባይሆንም ሱዳናዊያን ተማሪዎች የዳቦ ጥያቄ ይዘው አደባባይ ወጥተዋል፡፡
በሺህዎች የሚቆጠሩ ሱዳናዊያን ተማሪዎች የዳቦ ጥያቄ ይዘው አደባባይ መውጣታቸው ተነግሯል፡፡
ተማሪዎቹ ከሰሞኑ በሀገሪቱ ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ የኑሮ ውድነት ጫናውን መቋቋም እንዳልቻሉ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ አሰምተዋል።
በቀይ ባህር አካባቢ እና በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል የሚኖሩ ነዋሪዎችም ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ ምሬታቸው ማሰማት ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አማካኝነት የተጀመረው የዳቦ ጥያቄ አሁን ላይ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ተማሪዎች ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡
ተማሪዎቹ ባሁኑ ሰአት ዋና ዋና መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሞአቸው እያሰሙ ይገኛሉ ሲል ኦል አፍሪካን ዶት ኮም ዘግቧል።
የአካባቢው አስተዳዳሪዎችም ከተማሪ ተወካይ ጋር በጉዳዩ ዙርያ መነጋገራቸው ተሰምቷል፡፡
በሱዳን የዋሊ ግዛት አስተዳዳሪ አብድላህ ሻንጋራይ እንደተናገሩት መንግስት የተማሪዎችን መብት ያከብራል ተማሪዎችም የሀገሪቱን ህግ ማክበር አለባቸው ብለዋል፡፡
አስተዳዳሪው አክለው እንደተናገሩትም በሰላማዊ መንገድ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይችላሉ ይህ ደግሞ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸው ሊከበርም ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሱዳን ዳርፉር ከሰሞኑ ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር ተያይዞ 100 ሺህ የሚጠጉ ሱዳናዊያን ቤታቸው ጥለው ተሰደዋል፡፡
እንደዚሁም 250 የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ ከዚሁ ግጭት ጋር በተያያዘ ህይወታቸው አልፋል፡፡
ከፈረንጆቹ 2007 አንስቶ በሱዳን በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩት ግጭቶች 400 ሺህ ዜጎች ህይወታቸው ሲያልፍ ሶስት ሚሊየን ሱዳናዊን ደግሞ ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ የመንግስታቱ ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡
Via:- Ethio FM

የትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ዘመቻው ከስፍራው ላይ ተኩኖ እንደተዘገበው ሁሉ የሰብዓዊ መብት አያያዝ እና ሰብዓዊ እርዳታዉም በስፍራዉ በመሆን ሊዘገብ እንደሚገባ ኢዜማ አሳሰበ፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ወንደሰን አንዱአለም የሰብአዊ መብት አያያዝ ሂደትን በትግራይ ክልል ለመዘገብ ጠይቆ የተከለከለ ሚዲያም ሆነም ጋዜጠኛ የለም ብለዋል፡፡በትግራይ ክልል የነበረዉን የህግ ማስከበር ሂደት ተከትሎ በርካታ መገናኛ ብዙሀን የተመረጡ ጋዜጠኞችን ወደ ስፍራዉ በመላክ የነበረዉን ሂደት ከስፍራዉ እንዲዘግቡ ማድረጋቸዉ አይዘነጋም፡፡በክልሉ የሰበአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ ዜጎች ድጋፉን እያገኙ ያሉት ከመቀሌ ነዋሪ ነዉ ሲሉ የኢዜማ ሊቀመንብር አቶ የሺዋስ አሰፋ ተናግረዋል፡፡
[አሐዱ ራዲዮ 94.3]

በትግራይ ክልል እየደረሰ ያለውን ፆታዊ ጥቃት ለመከላከል በክልሉ ያለው ጾታዊ ጥቃት መከላከልና ምላሽ አሰጣጥ ግብረሀይል መልሶ ወደ ስራ መግባቱን የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ገለጸ!
በትግራይ ክልል በህግ ማስከበሩ ዘመቻ በርካታ ሴቶችና ህጻናት ከመኖሪያ ቄያቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል፡፤ ለተፈናቃዮች ሰብዐዊ ድጋፍ ከማድረስ ባለፈ ጾታዊ ጥቃት እንዳይደርስባቸው መከላከል የመንግስት ሀላፊነት ነው፡፤በክልሉ ተፈናቅለው ያሉ ሴቶችና ህጻናት የጾታዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን የሚያመልክት መረጃ እየወጣ ነው፡፡ አሀዱም ከዚህ በኋላ ጥቃት እንዳይደርስ ከለላ ከመስጠትና ከፍትህ አካላት ጋር ተናቦ ከመስራት አኳያ በሚኒስቴሩ ምን እየተሰራ ነው ሲል ጠይቋል፡፡
የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙና አህመድ እንደገለጹት ጾታዊ ጥቃትን ከመከላከል አኳያ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡የመከላከሉ ተግባር በአንድ ተቋም ብቻ የሚሰራ እንዳልሆነ ገልጸው በክልሉ ያለው ጾታዊ ጥቃት መከላከልና ምላሽ አሰጣጥ ግብረሀይል ወደ ስራ እንዲገባ ስለመደረጉ ተናግረዋል፡፡ ጥቃት እንዳይፈጸም ከለላ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው የህክምና ተቋማት ማደራጀት ላይ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል፡፡
አሐዱ ራዲዮ 94.3

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ከ60 በላይ ቀበሌዎች የአስተዳደር እና የፀጥታ መዋቅሮች እንደአዲስ መዋቀራቸው ተገለፀ።
የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተዋቀረው የተቀናጀ ግብረሃይል የፖለቲካና ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለፁት፣ ግብረሃይሉ ስራ በጀመረበት ወቅት በአካባቢው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር እንደነበር አስታውሰው፣እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።የመተከል ችግር የተለያዩ የውስጥና የውጭ ሃይሎች የተሳተፉበት ነበር ያሉት አቶ ተስፋዬ፣ በውስጥ በየደረጃው ያለው የመንግሥት እና የፀጥታ መዋቅር የተሳተፈበት መሆኑ ችግሩን ውስብስብ እና አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቁመዋል።ከዚህ አንጻር መሳሪያ ጭምር ለጥፋት ሃይሎች የሚያቀብሉ የፀጥታ አካላት እንደነበሩ ማረጋገጥ መቻሉንም ጠቁመዋል።ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታትና የዞኑን ሰላም ለመመለስ ከተወሰዱ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ የችግሩ አካል የሆኑ አመራሮችና የፀጥታ አካላትን የመለየትና ተገቢውን እርምጃ የመውሰድ ስራ አንዱ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተስፋዬ፤ ህብረተሰቡን የሚመስል የአስተዳደር እና የፀጥታ መዋቅር እንዲኖር ለማድረግ ሰፊ ስራ ተሰርቷልም ብለዋል።
[EPA]

ናይጄሪያዊቷ የዓለም ንግድ ድርጅት መሪ ሆነው ተመረጡ
ናይጄሪያዊቷ ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዊዓላ (ዶ/ር) የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመረጡ፡፡
ኢዊዓላ ዓለም አቀፉን ተቋም እንዲመሩ የተመረጡት ድርጅቱ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ነው፡፡
የቀድሞዋ የናይጄሪያ የፋይናንስ ሚኒስትር ከመጪው መጋቢት 1 (እ.አ.አ) ጀምሮ ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት ይመራሉ ተብሏል፡፡
ይህም ኢዊዓላ ተቋሙን ለመምራት የቻሉ የመጀመሪያዋ ሴት እና የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ያደርጋቸዋል፡፡
ድርጅቱን ለመምራት የቻሉ 7ኛዋ ሰውም ናቸው፡፡
በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ለደረሱ ምጣኔ ሃብታዊ ቀውሶች ምላሽ ለመስጠት ከአባል ሃገራቱ ጋር ተቀናጅቶ መስራት ተቀዳሚ የቤት ስራቸው እንደሚሆንም ሹመታቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል፡፡
via:- Alain

ከሰሞኑ በግለሰብ መጋዘን በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘው 2 ሚሊየን ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ሸማች ማህበራት እየተሰራጨ ነው።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ ጎን በአንድ ግለሰብ መጋዘን ውስጥ በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 2 ሚሊየን ጀሪካን የፓልም የምግብ ዘይት በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉ የሚታወስ ነው።
ይህ በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የሸማች ማህበራት አማካኝነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ በወሰነው መሠረት በዛሬው ዕለት የማሰራጨት ስራ ተጀምሯል ።
የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ ይህ በህገወጥ የተያዘው ዘይት መሰራጨት በከተማዋ የሚስተዋለውን የዘይት እጥረት ያቃልላል ብለዋል ።
በቀጣይም በክፍለ ከተማው መሰል የፍጆታ እቃዎችን በመጋዘን የሚያከማቹ ግለሰቦችንና ተቋማትን ለመቆጣጠር የተደራጀው ልዩ ግብረሀይል መንግስት በድጎማ የሚያስገባቸውን መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በህገወጥ መንገድ በማከማቸት እና የአቅርቦት እጥረት በመፍጠር የንግድ ስርዓቱን ለማዛባት በሚንቀሳቀሱ አካላት የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል ።
ህብረተሰቡ በየትኛውም አካባቢ የፍጆታ ሸቀጦችን የሚያከማቹ አካላትን እና ግለሰቦችን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲሰጥ ወ/ሮ ነጻነት ጥሪ አቅርበዋል።
Via:- AACPS
@Yentube @Fikerassefa

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በአንዳንድ የምዕራብ ኦሮሚያ አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ሲያስጀምሩ ፤ ተገንብተው የተጠናቀቁትን ደግሞ መርቀው ከፍተዋል።
በኢትዮጵያ ቀደም ሲል በተለይ ምርጫ በሚካሄድበት ዓመት እንዲህ በስፋት የግንባታ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ እና የተገነቡትን ማስመረቅ የተለመደ ነበር።
በምርጫ 2007 በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የበርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት ዓመት ነበር። ከክልል አስተዳዳሪዎች ጀምሮ እስከ ታችኛው የአስተዳደር መዋቅሮች በያሉበት ተመሳሳይ ተግባራት ሲከወኑ ነበር።
በወቅቱ በሀገሪቱ የተለያዩ አቅጣጫዎች ለመገንባት የታቀዱ ሀገር አቋራጭ የባቡር መስመር ግንባታን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ታቅደው ነበር። በእርግጥ ነው በትላልቅ ከተሞች ለመገንባት ከታቀዱ የኢንዱስትሪ መንደሮች ውስጥ አብዛኞቹ ተገንብተው ሥራ መጀመራቸው ሲገለጽ ቆይቷል።
በዚያው ልክ የባቡር መስመርን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶች በወቅቱ የመሠረት ድንጋይ ከተቀመጠ በኋላ አሁንም ድረስ ግንባታቸው ያልተጀመረ እንዳሉ ይታወቃል። በሌላ በኩል ደግሞ ግንባታቸው ቢጀመርም በወቅቱ ያልተጠናቀቁ አልያም ግንባታቸው የተቋረጠ እንዳለም ይሰማል።
መንግሥት በምርጫ ዋዜማ ከወትሮ በተለየ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን መንቀሳቀሱን ከምርጫ ጋር የሚያገናኙ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ መቼም ይሁን የሕዝቡን የመሠረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ የሚሠራ ሥራ ተቀባይነት አለው ብለው የሚከራከሩ ሰዎች አሉ።
ለመሆኑ ምርጫ ሊደረግ በታቀደበት ዓመት በኢትዮጵያ በየአካባቢው የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እርስዎ እንዴት ያዩታል? ሃሳብዎን ያጋሩን፤ በኮሜንት ተወያዩበት
⤵️

ለመሆኑ ዓለም አቀፉን ተቋም እንዲመሩ የተመረጡት ኢዊዓላ ማን ናቸው?
የ67 ዓመቷ ኢዊዓላ እ.አ.አ በ1954 ነው ያኔ ሃገራቸው ናይጄሪያ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችበት ጊዜ የተወለዱት፡፡
የመጀመሪያና የሁተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሃገራቸው ከተማሩ በኋላም በ1973 ወደ አሜሪካ አቅንተው ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡
የዶክትሬት ዲግሪያቸውንም በ1981 ከማሳቹሴትስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ በልማታዊ ኢኮኖሚክስ አግኝተዋል፡፡
ኢዊዓላ ለ25 ዓመታት ያህል የዓለም ባንክን በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡ በባንኩ የስልጣን እርከን ሁለተኛ ሰው እስከመሆን ደርሰውም ነበረ፡፡
የናይጄሪያ የፋይናንስ ሚኒስትር በመሆንም በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ሃገራቸውን አገልግለዋል፡፡
ይህ የሆነው በኦሊሴጉን ኦባሳንጆ እና በጉድላክ ጆናታን የፕሬዝዳንትነት ዘመን ነው፡፡
ይህም በሁለት የተለያዩ ፕሬዝዳንቶች የስልጣን ዘመን ሃገራቸውን በፋይናንስ ሚኒስትርነት ያገለገሉ የመጀመሪያዋ ናይጄሪያዊ ያደርጋቸዋል፡፡
Via:- Alain

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ከልል መተከል ዞን ፓዊ ወረዳ 1200 ሚሊሺያዎች ሥልጠና ላይ መሆናቸውን ዞኑ አስታወቀ። በመጀመሪያው ዙር 1292 ሚሊሺያዎች ሠልጥነዋል።ሥልጠናው "በመተከል ዞን የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ" የሚደረገው ጥረት አካል ነው።በመተከል ዞን፣ ወምበራ፣ ቡለን፣ ድባጢ፣ ማንዱራ እና ጉባ ወረዳዎች አስተዳዳሪዎች እና የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ የ44 ሹማምንት ሹም ሽር መካሔዱን ዞኑ ከሁለት ቀናት በፊት አስታውቋል።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባል የሆኑት አቶ አብርሃ ደስታ የክልሉን ግዝያዊ መስተዳድርን ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ እንደሚደግፉ ተናግረዋል።
ምክንያት ብለው ያስቀመጡት ደግሞ መንግስት አልባ ከመሆን የግዝያዊ መንግስትን መኖር መሻሉ ነው። ምክንያቱም መንግስት ካለ መብራት፣ ስልክ፣ ባንክ ወዘተ ይኖራሉ ብለዋል። ህዝብ በደል ሲደርስበት የሚጮህበት አካል ማስፈለጉም አንዱ ምክንያት ነው ብለዋል። የግዝያዊ መስተዳድሩ አካል የሆንኩት በፖለቲካዊ ምርጫዬ አይደለም ያሉ ሲሆን፤ የፌደራል መንግስትን አቋም ደግፌ ወይም ህወሓትን ተቃውሜ አይደለምም ብለዋል። የግዝያዊ መስተዳድሩ አካል የሆኑት በሰብአዊነት መሆኑን ገልፀዋል፤ ቢያንስ የአንድን ትግራዋይ ህይወት ማዳን እችላለሁ ብዬ ነውም ብለዋል።እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡት ደግሞ ከትግራይ መሬት አንድ ካሬ ሜትር ብትወሰድ ግን ስልጣኔን በገዛ ፍቃዴ እለቃለሁ በሚል አቋማቸው ነው። መልቀቅ ብቻ አይደለም፤ የፌደራል መንግስትን ባደባባይ እቃወማለሁም፣ መቃወም ብቻ አይደለም፤ መሬቴን ለማስመለስ እታገላለሁ ብለዋል። ደግነቱ የትግራይ ክልል ግዝያዊ አስተዳደር ካቢኔ አቋምም ይሄ ነው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 733 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ15 ሰዎች ሕይወት ደግሞ አልፋል!
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 1 የላቦራቶሪ ምርመራ 733 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ካለባቸው 18 ሺህ 668ሰዎች መካከል 307 ሰዎች በጽኑ ሕመም ላይ ይገኛሉ።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 147 ሺህ 825 ደርሷል፡፡
በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት ከበሽታው ያገገሙትን 204 ሰዎች ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 128 ሺህ 946 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ15 ሰዎች ሕይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 209 ደርሷል።በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ2 ሚሊዮን 051 ሺህ 853 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጓል።

አስደሳች ዜና ለስኮላር ሽፕ ዝግጅት ፈላጊዎች
ወቅቱ የስኮላርሽ ጊዜ ስለሆነ ተማሪዎች ይህንን አጋጣሚ ይጠቀሙ።
ወደ መደበኛ ትምህርታችሁ ከመመለሳችሁ በፊት ጊዚያችሁን ተጠቀሙበት
ለ High School | Collage | University ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ
IELTS | TOFEl | SAT | GRE ማስተማር ጀምረናል።
ወደ #አሜሪካ ፣ #ካናዳ ፣ #እንግሊዝ ፣ #አውስትራልያ ፣ #አውሮፓ፣ #ቻይና
አድራሻ
Mexico:+251919913021
Hayahullet:+251919913022
Piassa:+251919913023/24
Admission Open Now
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
T.me/SCHOOLOFAMERICAN