YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
የዋሪት የውሀ ማጣሪያ ከ15% ልዩ ቅናሽ ጋር

ሰብስቤ www.sebsibie.com በመግባት መገበየት ይችላሉ።

ሰብስቤ ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

ከ3,200 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

📞 0953707070

Dedicated online shopping platform
Forwarded from YeneTube
🖼 ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለሙሽሮች እና ለተመራቂዎች ለየት ያለ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ?
#join
👇👇👇👇
@giftsoflovee
@giftsoflovee
👆👆👆👆
📱+251914839754
📱+251936871620
#ኣድራሻችን፡ 4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ
በደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት 91 ነጥብ 3 በመቶ ተማሪዎች ወደ ወደ 9ኛ ክፍል ተዛወሩ!

የደቡብ ክልል ትምህርት የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ማድረጉን የቢሮው ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ አስታወቁ።

በዚህም በሲዳማና በደቡብ ክልል ለፈተና ከተቀመጡ 352 ሺህ 806 ተማሪዎች ውስጥ ወደ 322 ሺህ 136 የሚሆኑት ወደ 9ኛ ክፍል መዛወራቸውን ተናግረዋል።

በዚህም 91 ነጥብ 3 በመቶ ማለፋቸውን አመላክተዋል፡፡

በማረም ወቅት መልስ መስጫ ወረቀት በትክክል ያለማጥቆር፣ የስም ስህተትና የመለያ ኮድ ስህትት የታዩ ችግሮች መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

ይህን ችግር እንግሊዝ ሀገር ካለው DRS ከሚባል ሶፍት ዌር ኩባንያ ጋር በመነጋገር መፈታቱንና በቀጣይ ይህ ችግር እንዳይገጥም ተማሪዎች መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል፡፡

በአጠቃለይ የማለፊያ ነጥቡ ኮቪድን ታሳቢ በማድረግ ለወንድ 41፣ ለሴት 40 እና ማየት ለተሳናቸው 39 ሆኑ ተወስኗል ብለዋል።

በተያያዘም የ9ኛ ክፍል ቅበላ በሁሉም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የካቲት 1 እና 2 ቀን ሲሆን ትምህርት የካቲት 3 ቀ 2013 ዓ.ም መሆኑንና ተማሪዎችም በተገለጸው ጊዜ አስፈላጊ ቁሳቁስ በማዘጋጀት ትምህርት ቤት እንዲገኙም ጥሪ ማቅረባቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ስቴቨን ኦማሞ ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሯ የዓለም የምግብ ድርጅት ኢትዮጵያ ቀውስ ባጋጠማት ወቅት ሁሉ ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጎን በመቆም ላደረጉት የረጅም ዘመናት ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የህግ ማስከበር ሂደቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል ላጋጠሙ የሰብዓዊና የመሰረተ ልማት ቀውሶች አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት እየተካሄደ ስላለው አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ የማቋቋም ሂደት ገለጻ አድርገዋል።

የዓለም ምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ስቴቨን ኦማሞ በበኩላቸው የዓለም ምግብ ድርጅት እንደሁልጊዜውም ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጎን በመቆም የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን በተቀላጠፈ መንገድ ለማሳለጥ ከብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አማራር ኮሚሽን ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
አያት አደባባይ አካባቢ በሱቆች ላይ የተነሳው እሳት ወደ ሌሎች ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ትላንት ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ አያት አደባባይ አካባቢ በሱቆች ላይ የተነሳው እሳት ወደ ሌሎች ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ ።

በሱቆች ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ በተደረገው ፈጣን ከፍተኛ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል ብሏል ከተማ አስተዳደሩ ።

የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች ሱቆች እንዳይዛመት የእሳት እና አደጋ መከላከል ሰራተኞች ፣የአካባቢው ማህበረሰብ እና የጸጥታ አካላት ላደረጉት ርብርብ የከተማ አስተዳደሩ ምስጋና ይገባችኋል ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሸማቾች ጥበቃ እና ውድድር ባለስልጣን ሸማቾችን ያሳስታሉ በሚል 3 ማስታወቂያዎችን አገደ።

ባለስልጣኑ ከአዋጁ ጋር የሚጻረሩ የንግድ እቃዎችና የአገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ገልጿል።

በግማሽ ዓመት አፈፃፀም የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለ ስልጣን ባወጣው ሪፖርት መሰረት ከአዋጅ ቁጥር 813/2006 ጋር የማይጣጣሙ የንግድ ዕቃዎችና የአገልግሎት ማስታወቂያዎችን 48 ጊዜ በመከታተል እና ከአዋጁ ጋር የሚፃረሩ የንግድ ማስታወቂያዎች ላይም በግማሾቹ ላይ የማስታወቂያ እግድ ሲወጣ ቀሪዎቹ ላይ ይዘታቸው እየተጣራ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ላይ ሲተላለፉ የነበሩ ከሴራሚክ ሽያጭ፣ የቀለም ሽያጭ፣ ከዲኮደር ሽያጭ፣ ከታሸገ ዉሃ ማስታወቂያ እና ለትራንፖርት አገልግሎት ከሚዉሉ ታክሲዎች ከቀረጥ ነፃ አቅርቦት ጋር በተገናኘ የሚተላለፉ የንግድ ማስታወቂያዎች ግልፀኝነት የጎደላቸዉና ሸማቹን ሊያሳስቱ ይችላሉ በማለት 3ቱ ሲታገዱ የ 2 ማስታወቅያዎች ይዘት እየተጣራ ይገኛልም ተብሏል በሪፖርቱ፡፡

በተጨማሪም የ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓላትን ምክንያት በማድረግ በ14 የሴትና የወንድ ልብስና ጫማ መሸጫ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ፈርኒቸር መሸጫ የንግድ መደብሮች ስለዋጋ ቅናሽ የተለጠፉ የውጭ ማስታወቂያዎች ላይ ክትትል በማድረግ በ 10 የንግድ መደብሮች የተለጠፉ የንግድ ማስታወቂያዎች ግልፀኝነት የጎደላቸው እና አሳሳች ናቸው ተብለዋል፡፡

በዚህም በአዋጁ አንቀፅ 7 እና 8 መሠረት ማስታወቂያዎችን እንዲያስተካክሉ ከመደረጉም በላይ ተመሳሳይ ድርጊት ለወደፊቱ እንዳይፈፅሙ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡

በተያያዘም የህትመት ሚዲያ ላይ አሳሳች ማስታወቂያዎችን ከመከታተል አንፃርም የተለያዩ የህትመት ሚዲያ ላይ እየተሰራጩ የሚገኙ የንግድ ማስታወቂያዎች ይዘት ትክክለኛ ስለመሆኑ ምርመራ እንዲጀመር ተደርጓልም ተብሏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ለአዲሱ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ መሰጠቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ የስደተኞች ጉዳይ እንዲሁም ከሰብዓዊ ድጋፍ አሰጣጥ ጋር በተገናኘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከአትላንቲክ ካውንስል ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በውይይቱም ይነሱ ለነበሩት በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሰጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡በተለይም በምዕራባዊያኑ በኩል ይነሱ ለነበሩት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡ከሞላ ጎደል በትግራይ ክልል ያለው እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት እየተመለሰ እንደሚገኝ ለሰብዓዊ ድጋፍም ክፍት መሆኑን ማስረዳታቸውን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ለተገደሉ ንፁሃን መንግሥት ማዘኑን ገለፀ፡፡

‹‹የአንድ ንፁህ ሰው ሞት በራሱ ብዙ ነው›› ሲል መግለጫ ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ሆኖም በሕግ ማስከበር ዘመቻው በፌደራሉ መንግሥት በኩል በንፁሃን ላይ የደረሰ ጉልህ ጉዳት አለመኖሩንም ያነሳል፡፡ምክንያት ያለው ደግሞ የመከላከያ ሰራዊቱ ሙያዊ ስልቱን ተጠቅሞና ጥንቃቄ በተሞላበት እቅድ ስለተመራ ነው የሚል ነው፡፡የመረጃ ማጣሪያው በትግራይ ሕግ የማስከበር ወቅት በንፁሃን ላይ የተፈጸሙ ግድያዎችን በተመለከተ በዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጩት መረጃዎች በመረጃ ያልተደገፉና ያልተረጋገጡ ናቸው ሲልም አጣጥሏቸዋል፡፡ የመገናኛ ብዙኃን መረጃዎቹ ከፖለቲካ ፍላጎት የመነጩ ስለመሆናቸውም ተከራክሯል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በመቐለ ከተማ ትምህርት የካቲት 1 እንደሚጀመር ተገለጸ!

በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና በኮሮና ምክንያት በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ከፊታችን የካቲት 1 ቀን 203 ዓ.ም አንስቶ እንደሚጀመር የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ።

የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በመጀመሪያ በኮሮና ምክንያት በኋላም በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ትምህርት ተቋርጦ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት የከተማዋ ሰለምና ጸጥታ የተረጋጋ በመሆኑና የኮሮኖ መከላከያ ጥንቃቄን ተግባራዊ በማድረግ በሁሉም ደረጃ ባሉ የትምህርት ክፍሎች ከየካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም አንስቶ ትምህርት መስጠት ይጀመራል።

ወላጆች ልጆቻቸውን ከተጠቀሰው እለት ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩም አቶ አታከልቲ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅት በመቀሌ ከተማ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደባኛ ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም ከንቲባው አስታውቀዋል።

Via EPA
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን 18.2 ቢሊዮን ብር ወጪ 738.19 ኪ.ሜ ርዝማኔው ያላቸውን 8 መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችለውን ስምምነት ከተለያዩ ስራ ተቋራጮች ጋር ተፈራርሟል።

በአጠቃላይ ባለስልጣን መስሪያቤቱባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በ43.3 ቢሊየን ብር ወጪ 21 መንገድ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ከተለያዩ የሐገር ውስጥና ከውጭ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶች ጋር ተፈራርሟል።

ከመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል ወደ ጎረቤት ሐገር ከሚያስተሳስሩ ፕሮጀክቶች; አንደስላሴ-ራማ ገረሁ ሰናይ ከኤርትራ፣ ዱርቤቴ -ቁንዝላ-መተማ ከሱዳን አንዲሁም ነጌሌ ቦረና-መልካሱፍቱ ከኬንያ አና ከሶማሊያ ይገኙበታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ36 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው በወረዳው በዱሴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ዛሬ ከረፋዱ አምስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ላይ ነው።ከወረዳው ዱሴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ወደ ጨለንቆ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 – 73876 አአ የሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ በመገልበጡ አደጋው መድረሱ ተገልጿል።በአደጋው በተሽከርካሪው ላይ ተጭነው የነበሩ የ36 ሰዎች ህይወት ወድያው አልፏል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በደደር፣ ጨለንቆና ድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው ድልጮራ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን ለየቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ መሆኑን አሳውቋል።የአደጋው መንስዔ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ፖሊስ መምሪያው ለኢዜአ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል፡፡

ም/ቤቱ ነገ በጠቅላይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባው የ6ኛ አመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን መርምሮ በማጽደቅ ይጀምራል፡፡ ም/ቤቱ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም እንዲሁም ለሴቶች ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ነው የሚጠበቀው፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዳንስኬ ባንክ ኤ.ስ መካከል ለብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የሜቲዎሮሎጂ ምልከታ መሰረተ ልማት እና የትንበያ አቅም ግንባታ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ የሚያፀድቅ ሲሆን የምርጫ ጉዳዮች በፍርድ ቤት የሚስተናገዱበት የሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ረቂቅ ደንብንም መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጄፍ ቤዞስ ከአማዞን ሥራ አስፈጻሚነት እንደሚለቅ አስታወቀ።

የአማዞን መሥራችና ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ከኩባንያው ሥራ አስፈጻሚነት እንደሚለቅ ያስታወቀ ሲሆን በቀጣይ የበላይ ጠባቂ ሆኖ በዋና ዋና የአማዞን ጉዳዮች ብቻ መሳተፍ ብቻ እንደሚፈልግ ገልጿል።

'የአማዞን ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ መሥራት ፋታ የለውም። ጊዜና ጉልበትን ያሟጥጣል። እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት ላይ መሆን ሌሎች ነገሮች ላይ ለማተኮር ጊዜ አይሰጥም' ይላል ቤዞስ በይፋ በጻፈው የመልቀቂያ ደብዳቤ።

ቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ አሁን ትኩረት ሊያደርግበት የፈለጋቸው የሥራ ዘርፎች በህዋ ትራንስፖርት ላይ የሚያተኩረው ብሉ ኦሪጂን እንዲሁም ዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ህትመት እና ሌሎች የግል ፍላጎቶቹ ላይ ነው።

የአማዞን የበይነ መረብ ገበያን የጀመረው በ1994 ሲሆን ያን ጊዜ መጽሐፍ በበይነ መረብ የሚሸጥ ትንሽ ድርጅት ሆኖ ነበር አማዞን የተመሰረተው። አሁን አማዞን በመላው ዓለም 1.3 ሚሊዮን ሰራተኞች አሉት።

በ2020 ዓ/ም ብቻ የአማዞን ጠቅላላ ሽያጭ 386 ቢሊዮን ዶላር አልፏል። ይህም የሆነው በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት የበይነ መረብ ገበያው ስለደራ ነው። ጄፍ ቤዞስ በፎርብስ የሀብት ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰለት ሀብቱ 192 ቢሊዯን ዶላር ደርሷል።

Via - BBC
@Yenetube @FikerAsssefa
የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ባለው ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ዛሬ እንደሚወያይ ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የተመድ ሰብዓዊ ሁኔታዎች ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ በክልሉ ስላለው ሰብዓዊ ሁኔታ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ጉዳዩ ለሦስተኛ ጊዜ ውይይት እንዲደረግበት ሃሳብ ካቀረቡት የምክር ቤቱ አባል ሀገራት መካከል፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ኖርዌይ ይገኙበታል፡፡ ጉዳዩ እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ “ሌሎች ጉዳዮች” በሚል ርዕስ ስር የተያዘ ሲሆን፣ በውይይቱ ማብቂያ መግለጫ ይወጣል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ለብልጽግና ፓርቲ ድጋፍ ለማሳየት የተለያዩ ሰልፎች መካሄዳቸው ይታወቃል። እነዚህን ሰልፎች ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) “ፓርቲያችን ያለአግባብ ተወንጅሏል፣ ይህም ፓርቲዎች የፈረሙትን የጋራ የስነምግባር ደንብ የጣሰ ነው” ሲል አቤቱታውን ለቦርዱ አቅርቧል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ከአቤቱታው በተጨማሪ በእለቱ የተደረጉ የተለያዩ ሰልፎችን በሚዲያ ክትትል ክፍሉ አማካኝነት ክትትል በማድረግ በአሜሪካ ድምጽ፣ በዋልታ፣ በፋና፣ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ እንዲሁም በነዚሁ ሚዲያዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በቀጥታ የተላለፉ መልእክቶችን በማየት
- ሠልፎቹ በዋልታ ቴሌቪዥን እና በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ በቀጥታ መተላለፋቸውን እንዲሁም የመንግስት አመራር አካላት፣ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች መሳተፋቸውን ተረድቷል።
- ከሚዲያዎቹ በቀጥታ ከመተላለፉም በተጨማሪ የተለያዩ የመንግስት አመራር አባላት በሰልፎቹ ላይ ያደረጓቸውን ንግግሮች ተመልክቷል።
- በሰልፎቹ የተለያዩ መፈክሮች፣ በተወሰኑ የመንግስት የዞን፣ የከተማ አስተዳድር አመራር አካላት እና ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊዎች ንግግሮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ እና የምርጫ ምልክቶቻቸውን የመረጡ ፓርቲዎች በአሉታዊ መልኩ መነሳታቸውን ተገንዝቧል።

እነዚህ ሰልፎቹ ላይ የተነሱ ንግግሮች እና መፈክሮች በህጋዊነት ተመዝግበው፣ በፖለቲካ ፓርቲነት የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችን ማለትም አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በአመፃ ተግባር በመሳተፍ ከምርጫ ቦርድ ከተሰረዘው ጁንታ በማለት ከሚጠሩ ህወሃት ፓርቲ ጋር አንድ በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው ብሎ በመፈረጅ እና ህገወጥ ናቸው በማለት የምርጫ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር ህግ 1162/2011 ላይ ያሉ ድንጋጌዎችን ጥሰዋል።

ቦርዱ ሰልፎቹ ላይ የተንጸባረቁት ንግግሮች እና መፈክሮች በአዋጁ አንቀጽ 132 ንኡስ 2(ሀ) ላይ የተጠቀሰውን ስም የሚያጠፋ ንግግርን ክልከላ ድንጋጌ አንዲሁም በዚሁ ህግ አንቀጽ 143 (2) ላይ የተጠቀሰውን ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዳያሰራጩ ስጋት እና ፍርሀት የመፍጠር የስነምግባር ጥሰት ፈጽሞ አግኝቶታል። ከዚህም በተጨማሪ ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ገዥው ፓርቲ በጋራ ተስማምተው በፈረሙት የቃልኪዳን ሰነድ አንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ የተጠቀሰውን “የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በየትኛውም ጉዳይ ላይ ሊኖር የሚችል የዓላማ፣ የሃሳብ ወይም የዘር ልዩነትን፣ ወይም ሌላ ምክንያት መሰረት በማድረግ የሌሎች ፓርቲዎችን መብቶች የሚፃረሩ ወይም የሚያጣብቡ ድርጊቶችን ከመፈፀም የመቆጠብ ግዴታ አለባቸው” የሚለውን አንቀጽ የሚጥስ ተግባር ነው።

ይህ ተግባር በተለይ ቦርዱ የመጨረሻ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ የምርጫ ተግባራት በይፋ መፈጸም ከጀመረ በኋላ በምንገኝበት የምርጫ ወቅት መከሰቱ በምርጫ ውድድር ላይ ፓርቲዎች በእኩልነት የመወዳደር መብታቸውን ችግር ላይ የሚጥል በመሆኑ ቦርዱን በእጅጉ አሳስቦታል። በመሆኑም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው ያሉ የገዥው ፓርቲ አመራሮች እና በየአስተዳደር እርከኑ ያሉ የመንግስት ሃላፊዎች በተመሳሳይ ተግባራት ከመሳተፍ እንዲቆጠቡ ያሳውቃል።

ለወደፊትም በተመሳሳይ በምርጫ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር ህግ 1162/2011 እና ተያያዥ መመሪያዎች መሰረት የፓርቲዎች የቅስቀሳ የንግግር እና ሌሎች ለህዝብ የሚያሰራጯቸውን መልእክቶች ላይ ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን እስከእጩ መሰረዝ የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ያሳውቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
በአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት ሊፈፅሙ የነበሩ 15 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከውጭ የሽብር ቡድን አባላት ተልእኮ በመቀበል አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት በመፈጸም በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ እንዲሁም የአፍሪካና የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን የአዲስ አበባን በጎ ገጽታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ የነበሩት ቡድኖችን የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት 15 የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙኀን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣አሸባሪዎች ለጥቃት ሊጠቀሙባቸው ያዘጋጇቸው ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎች እና ለፍንዳታ ሥራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶች እና የተለያዩ ሰነዶች ተገኝተዋል።

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከኅዳር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከሌሎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ መረጃ ተቋማት ጋር በመሆን ጥብቅ ክትትል እና የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የታቀደውን የሽብር ጥቃት ማክሸፍ ችሏል።

የሽብር ጥቃቱን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት መካከል የቡድኑን አባላት ሲመራ የነበረው የ35 ዓመቱ ዓሊ አህመድ አርዳይቶ ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመር ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

ለዓሊ አህመድ አርዳይቶ ለሽብር ጥቃቱ ማቀነባበሪያነት እንዲውል በዐሥር ሺዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር እንደተላከለት ከተሰበሰቡ መረጃዎች ማረጋገጥ እንደተቻለ ተጠቁሟል።

ከዚህ ግለሰብ ጋር ግንኙነት የነበረው እና የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በህቡዕ ሲያሴር የቆየው መሐሙድ አብዱልቃኒ የተባለ ሌላ ተጠርጣሪም ከቀናት በኋላ በቁጥጥር ሥር በዋለበት ወቅት በመኖሪያ ቤቱ የጦር መሣሪያዎች፣ ለፍንዳት ስራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቄሳቀሶች እና ሰነዶች መያዛቸውን አስታውቋል።

ሌላ ተመሳሳይ ተልእኮ የተሰጠው ቡድን በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ተመሳሳይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተጠቅሷል።

የሽብር ቡድኑ መሪ ከውጭ አመራር የሚሰጠው ኑሮውን በስዊዲን ያደረገው አህመድ እስማኤል የተባለ ግለሰብ ነው።

የሽብር ጥቃት ዕቅድ በማውጣት እና ከሽብር ቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኤምባሲ የደህንነት መረጃዎች እንዲሰበሰቡ አቅጣጫ ሲሰጥ ቆይቷል።

ከአውሮፓ፣ አፍሪካ እና እስያ የመረጃና ደህንነት ተቋማት ጋር የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ እና ብርቱ ክትትል በማድረግ አህመድ እስማኤል በስዊዲን ሀገር በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
የዋሪት የውሀ ማጣሪያ ከ15% ልዩ ቅናሽ ጋር

ሰብስቤ www.sebsibie.com በመግባት መገበየት ይችላሉ።

ሰብስቤ ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ

ከ3,200 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com

📞 0953707070

Dedicated online shopping platform
Forwarded from YeneTube
🖼 ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለሙሽሮች እና ለተመራቂዎች ለየት ያለ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ?
#join
👇👇👇👇
@giftsoflovee
@giftsoflovee
👆👆👆👆
📱+251914839754
📱+251936871620
#ኣድራሻችን፡ 4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ
ወደ መቀሌ ተልኮ መደረሻው ሳይታወቅ የቆየው 1.3 ቢሊየን አዲሱ ብር ተገኘ!

አሁን በምርጫ ቦርድ ተዘርዞ ህልውናው እንዲከስም የተደረገው ቀድሞ የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እና በማዕከላዊው መንግስት መካከል ጦርነት የተቀሰቀሰ ዕለት ጥቅምት 24 ቀን 2013 አ.ም ምሽት ወደ ትግራይ መቀሌ በአሮጌው ብር እንዲቀየር በብሄራዊ ባንክ በአውሮፕላን የተላከው አዲሱ 1.3 ቢሊየን ብር መዳረሻው መታወቁን ዋዜማ ራዲዮ ሰምታለች።

ከምንጫችን እንደሰማነው በአሮጌው ብር እንዲቀየር የተላከው 1.3 ቢሊየን ብር መቀሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ክፍል ውስጥ ታሽጎ ነው የተገኘው።

ህወሀት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ፈፅሟል በተባለበትና ግጭቱ ወደለየለት ጦርነት በተሸጋገረበት በዚያ ዕለት አሮጌውን የብር ኖት እንዲተካ የተላከው ብር መዳረሻ አልታወቀም ነበር።

በወቅቱም መንግስት ገንዘቡን በትግራይ ክልል ላሉ የተለያዩ ባንኮች አከፋፍያለሁ ብሎ በብሄራዊው የቴሌቭዥን ጣብያ ማስነገሩ ይታወሳል። ማይጨው ፣ አደዋ ፣ሽሬ እንዳስላሴ እና አዲግራት ላሉ የተለያዩ ንግድ ባንኮች ብሩ ተከፋፍሏል ተብሎም ነበር። ሆኖም በወቅቱ በክልሉ ከነበረው ሁኔታ አንጻርና እንደተባለውም ብሩ በክልሉ ላሉ የባንክ ቅርንጫፎች እንዳልተከፋፈለ ዋዜማ ራዲዮ ከታማኝ ምንጮቿ አረጋግጣ መዘገቧ ይታወሳል።

የ1.3 ቢሊየን አዲሱን ብር እጣ ፈንታም የፌዴራል መንግስት የመቀሌ ከተማን ከተቆጣጠረም በሁዋላ በመቀሌ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ አዲስ ስራ እንኪጀምር አላወቀም ነበር ብለውናል ምንጫችን። ሆኖም ከሳምንታት ወዲህ በመቀሌ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫ እንደገና ስራ ሲጀምር ነው የቅርንጫፉ ሰራተኞች ብሩን በአንድ ክፍል ታሽጎ ያገኙት። ገንዘቡ ሲገኝም የመጠን ቅናሽ እንዳልነበረው ከምንጫችን መረዳት ችለናል።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በክልሎች ብርን ለማሰራጨት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎችን በማእከልነት እንደሚጠቀም ይታወቃል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ለ53 ቢሊየን ብር ኪሣራ ተዳርጓል!

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ሕገወጥ ተግባራትና በአመራር ዝርክርክነት ለ53 ቢሊየን ብር ኪሣራ መዳረጉ ተገለፀ። ኮርፖሬሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ኦዲት አለመደረጉም ተጠቆመ።በኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የከተማ ልማት መምህርና በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዙሪያ ጥናት ያደረገው ቡድን አስተባባሪ ዶክተር ቱሉ ቶላ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ሲካሄድ ቆይቷል።በዚህ ጊዜ ውስጥም ኦዲት ተደርጎ አያውቅም።

ግንባታው ከፍተኛ የሀገሪቱ ሀብት የፈሰሰበት ቢሆንም በሕግና በሥራት የሚመራ አልነበረም የሚሉት ዶክተር ቶላ፤ በዚህ የተነሳ ለከፍተኛ የአሠራር ብልሹነትና የገንዘብ ዕዳ መዳረጉን አመልክተዋል።ቡድኑ ባደረገው የማጣራት ሂደት ለግለሰቦች የተላለፈበት መንገድ ያልታወቀ፣ መረጃ ያላቀረቡ፣ ዝግ የሆኑ፣ ባዶ ቤቶችና መሰል ችግሮች መለየታቸውን ጠቁመው፣ በከተማዋ ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት እያለ ለ11 ዓመታት ዝግ ሆነው የቆዩ ቤቶች እንደነበሩም ጠቁመዋል። ከዚህም ባሻገር 21 ሺህ የሚሆኑ ቤቶች በማን እንደተያዙ ምን አይነት መረጃ ያልቀረበባቸው እንደነበሩም አስታውቀዋል።ቤቶቹ በዚህ መልኩ እንዲባክኑና ለሙስና እንዲዳረጉ የተደረገው ሆን ተብሎ ነው የሚሉት ዶክተር ቱሉ፣ ለዚህም ቤቶቹ መረጃ እንዳይኖራቸው ማድረግ አንዱ የሌብነት ስልት እንደነበረ ጠቁመዋል።

በዚህም መሰረት 85 ከመቶ የሚሆኑ ቤቶች ምንም አይነት የቤት መግለጫ የሌላቸው እንደሆኑ አመልክተዋል።በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከህብረተሰቡ የሚሰሙ ሮሮዎች የቆዩ መሆናቸውን የሚናገሩት ዶክተር ቱሉ፣ ሆኖም በዚህ ደረጃ ችግሩ ሥር የሰደደ ስለመሆኑ ግንዛቤ አልነበረንም።ጥናት በምናደርግበት ወቅትም ሀገሪቷ በምን አይነት ውስብስብ ችግር ውስጥ እንደነበረች ማየት ችለናል ብለዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa