YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከመተከል ተፈናቃዮች የተመለመሉ ሚሊሻዎች እንዲደራጁ መወሰኑን አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ!

ከመተከል ከተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተመለመሉ ሚሊሻዎችን በማደራጀት ማኅበረሰቡን በዘላቂነት ከጥቃት መከላከል የሚያስችል አደረጃጀት እንዲፈጠር መወሰኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።አቶ ደመቀ ይህን ያሉት ከመተከል የተፈናቀሉ እና በቻግኒ ራንች በተባለ መጠለያ ጣቢያ ከተጠለሉ ተጎጂዎች ጋር ውይይት ባደረጉት ወቅት ነው። የአካባቢውን ሰላም በማረጋገጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ እና ከማኅበረሰቡ ጋር እርቅ የማካሄድ ሥራ እንደሚሠራም መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

"የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ደህንነት አስመልክቶ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ የሀሰት እንደ ሆነ ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ ለማሳሰብ እንወዳለን" በማለት የጠ/ሚር ፅ/ቤት ከደቂቃዎች በፊት አስታውቋል።

ፅ/ቤቱ መግለጫውን ያወጣው በማህበራዊ ሚድያ ላይ ጠ/ሚሩ ጉዳት እንዳጋጠማቸው እና ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር እንደሄዱ የሚገልፅ ፅሁፍ መውጣቱን ተከትሎ ነው።

ኢትዮጵያ ቼክ ባለፈው አንድ ሰአት ውስጥ ከተጨማሪ ሁለት ምንጮች ማረጋገጥ እንደቻለው የተሰራጨው መረጃው ፍፁም ውሸት ነው፣ ጠ/ሚሩም መደበኛ ስራቸው ላይ ይገኛሉ። ይህን መረጃ በመጀመርያ ያሰራጨ ግለሰብም ፅሁፎቹን አሁን አጥፍቷል።

የህብረተሰቡን ሰላም እና መረጋጋት የሚያውኩ እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ባለማጋራት ሀላፊነታችንን እንወጣ።

Via PMOEthiopia & @EthiopiaCheck
@YeneTube @FikerAssefa
አል ቡርሃን ከዩኤኢ ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ!

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ከተባሩት አረብ ኤሚሬቶች ምክትል ፕሬዝዳንት፣ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዢ ሼክ መሃመድ ቢን ረሺድ አል መክቱም ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ፡፡ውይይቱ የተደረገው ቡርሃን ደውለው ሲሆን በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች እንዲሁም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ መክረዋል፡፡አል መክቱም በውይይቱ ዩኤኢ ለሱዳን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ብልጽግና ጠንካራ ድጋፍ እንዳላት አስረግጠው ተናግረዋል፡፡በአዲሱ አመራር ስር ወንድምና እህት ባሏቸው ሱዳናውያን የተያዙ ቀዳሚ ሃገራዊ ውጥኖች እንዲሳኩ ያላቸውን መልካም ምኞትም ገልጸዋል እንደ ሃገሪቱ የዜና አገልግሎት (ዋም) ዘገባ፡፡አል ቡርሃን በበኩላቸው በኤመራቲ መንግስት ስለሚደረግላቸው ድጋፍ በህዝባቸው ስም አመስግነዋል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በቅርቡ እጃቸውን የሰጡት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴር ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ ወደ አዲስ አበባ ገቡ!

የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የነበሩ እና በጡረታ በክብር ተሰናብተው የጁንታውን ታጣቂ ኃይል ሲመሩ እና ሲያዋጉ ቆይተው በቅርቡ እጃቸውን የሰጡት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴር ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ አዲስ አበባ ገብተዋል።መኮንኖቹ በጡረታ ከተገለሉ በኋላ ጁንታውን በመቀላቀል የጦርነት ዝግጅት ሲያደርጉ ነበር ተብሏል።የአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ ላይ የሕወሓት ጁንታ ጥቃት በፈጸመበት ወቅትም ዋና አስተባባሪ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ታንዛንያ አቀኑ!

ፕሬዚደንቷ በታንዛንያ ቆይታቸው የናይል ቤዚን ኮሚሽንን ለማቋቋም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከፕሬዚደንት ጆሴፍ ማጉፉሊ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል ታንዛንያ የአባይ ውሃን በጋራ መጠቀም የሚያስችለውን Cooperative Framework Agreement (CFA) ስምምነትን ቀድማ የፈረመች ሀገር መሆኗ ይታወሳል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች በነበረው ሕግ የማስከበር ሒደት ምክንያት፣ ባልታጠቁና ሰላማዊ በሆኑ ሰዎች ላይ የተፈጸመው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ጉዳይ ከፍተኛ ሥጋት እንዳሳደረበት ገለጸ፡፡

በእነዚህ የመብት ጥሰቶች ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ቀዳሚ ሰለባዎች ስለመሆናቸውም ለማወቅ እንደቻለ ጠቁሟል፡፡ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎችም በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚንቀሳቀሱ የትግራይ ተወላጆች እስር፣ እንግልትና አድልኦ እየደረሰባቸው ስለመሆኑም ኢሰመጉ በርካታ አቤቱታዎች እንደደረሱትም አክሏል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ምርመራ አድርገው ቫይረሱ እንዳለባቸው ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ ህክምናቸውን እየተከታተሉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ አሁን ላይ ቀላል ምልክት እያሳዩ መሆናቸውን ገልጸው እንደማገግም “ብሩህ ተስፋ አለኝ”ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከሜክሲኮ ብሔራዊ ቤተ መንግስት ሆነው ሁሉንም ብሔራዊ ስራዎች እንደሚያከናውኑ ያስታወቁ ሲሆን ከቭላድሚር ፑቲን ጋር በኮሮና ክትባት ዙሪያ የሚያተኩር ውይይት እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡

የሜክሲኮ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ኦልጋ ሳንቼዝ እርሳቸውን ወክለው የዕለት ሥራዎችን የማሳወቅ ስራውን እንደሚያከናውኑም ነው ሲኤንኤን የዘገበው፡፡ በሜክሲኮ ከ 149 ሺ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት ሲዳረጉ ከ1 ሚሊዮን 752 ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል ተብሏል፡፡

Via:- Alian
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሞያዎች ማህበር፣ስለ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ አሟሟት፣የጠራ መረጃ እንዲወጣ አሳሰበ፡፡

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ሲያስተዳድረው በቆየው ትግራይ ቴሌቪዥን፣በጋዜጠኝነት ይሰራ የነበረው ዳዊት ከበደ አርአያ እና ጓደኛው፣ባለፈው ረቡዕ ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም፣መቀለ ውስጥ በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን፣ከስፍራው የወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ይሁንና እስካሁን ስለ-ጋዜጠኛው እና ጓደኛው አሟሟት በዝርዝር የወጣ መረጃ የለም፡፡

ይህንኑ ተከትሎም፣የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሞያዎች ማህበር፣ስለ ጉዳዩ በሚመለከተው አካል በኩል፣የተብራራ መረጃ ለህዝብ በይፋ እንዲገለፅ ጠይቋል፡፡የማህበሩ ፀሀፊ ጋዜጠኛ ሲሳይ ሳህሉ ለብስራት ሬድዮ ሲናገሩ፣ማህበራቸው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው እንዳለ ገልፀው፣ክልሉን ከሚያስተዳድሩት ባለስልጣናትም ሆነ ከሌላ ከማንኛው ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል በኩል፣ስለ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ አርአያ አሟሟት የሚያስረዳ ትክክለኛ መረጃ መውጣት አለበት ብለዋል፡፡ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ አርአያ፣በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በትግራይ ቴሌቪዥን ለበርካታ ዓመታት ያገለገለ ባለሞያ ነው፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
ኦብነግ አዲስ ሊቀመንበር ሾመ!

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አዲስ ሊቀመንበር መሾሙን የአል ዐይን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ለረጅም ጊዜ በሊቀመንበርነት ያገለገሉት አብዲራህማን መሀዲን አሁን ላይ በአዲስ ሊቀመንበር መተካታቸው ተሰምቷል፡፡በዚህም መሰረት ራይሌ ሀሙድ አዲሱ የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው ተሸመዋል፡፡ቀደም ሲል የኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አለመግባባት ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ከ10 በላይ የሚሆኑ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነት ተነስተዋል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ክልል የኦነግ አባላት ናችሁ በሚል እና ህወሀትን ትረዳላችሁ በሚል የታሰሩ ዜጎች በአፋጣኝ እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ።

ኮሚሽኑ በጋምቤላ ክልል የእስረኞች አያያዝ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ሊሻሻል እንደሚገባም አሳስቧል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 22 ቀን 2013 የሚቆይ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት ለልጃ ገረዶች መስጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በዚህም በአዲስ አበባ ከ49 ሺህ በላይ ልጃ ገረዶች በትምህርት ቤቶች እና በጤና ተቋማት የሚሰጠውን ክትባት ያገኛሉ ተብሏል።

በኢትዮጵያ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሁሉተኛ ደረጃ የሚገኝ ህመም ሲሆን በየዓመቱ ከ7 ሺህ በላይ ሴቶች የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር እንደሚታይባቸው የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዩሐንስ ጫና ገልፀዋል።

ከእነዚህም ውስጥ 5 ሺህ የሚሆኑት በበሽታው ምክንያት ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተጠቁሟል።

በሽታውን አስከፊ ያደረገው 80 በመቶ የሚሆነው ከ10 እስከ 20 ዓመት ድረስ ምልክት ሳያሳይ ቆይቶ የሚከሰት በመሆኑ ነው ሲሉ ሃላፊው ተናግረዋል።

በሽታው ሂውማን ፓፒሎማ በተሰኘ ቫይረስ የሚመጣ ሲሆን ዋነኛ መተላለፊያው የግብረ ስጋ ግንኙነት ነው።ክትባቱን የሚወስዱት 14 ዓመት የሞላቸው ልጃ ገረድ ሴቶች ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የደረሰው የቴሌኮም ውድመት ጥገና በአጭር ጊዜ እንደማይጠናቀቅ ተገለጸ!

በመሬት ላይ የተዘረጉ የፋይበር ገመዶች (OPGW) ላይ ‹‹ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አጋጥሟል›› ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ በቴሌ መስመር፣ ምሰሶና ማማ ላይ የደረሱት ጥፋቶችን ጨምሮ ያጋጠመው ጉዳት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ያጋጠመውን ችግር ለመቅረፍ ከተለያዩ አካባቢዎች ዕቃዎችን በማምጣት የመተካት፣ በተወሰኑ አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት የማስጀመሩ ሥራ ቀን ከሌት እየተከናወነ መሆኑን ወ/ሪት ፍሬሕይወት ተናግረዋል፡፡

ዘገባው የሪፖርተር ነው፣ ተጨማሪ ለማንበብ: https://bit.ly/2MnQGru

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የብር ኖት ቅያሪ

መቐለን ጨምሮ በትግራይ ክልል የብር ኖት ቅያሬን ከጀመሩ 14 ቀናት ባለፋቸው የክልሉ ከተሞች ሲሰጥ የነበረው ቅያሬ እንዲቋረጥ ተወሰነ፡፡

ብሔራዊ ባንክ ለአሐዱ ቴሌቪዥን በላከው መግለጫ በክልሉ በነበረው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ተቋርጦ የነበረው የብር ኖት ቅያሬ ከታኅሣሥ 21 ጀምሮ ለ14 ቀናት እንዲከወን ከዚህ ቀደም መወሰኑን አስታውሷል፡፡
ሆኖም በአተገባበሩ ላይ ብዥታ ተፈሯል ያለው ብሔራዊ ባንኩ 14 ቀኑ የሚሰላው በአንድ ከተማ ላይ አንድ ባንክ ቀድሞ ሥራ ከሚጀምርበት ቀን አንስቶ ነው ብሏል፡፡

ለምሳሌ በክልሉ አንድ ከተማ ላይ ቀድሞ ሥራ የጀመረው ባንክ ጥር 17 ከሆነ 14 ቀናቱ መሰላት የሚጀምሩት ከጥር 17 ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህም ዘግይተው ሥራ በሚጀምሩት የባንክ ቅርንጫፎች ላይ ተጨማሪ ቀን መስጠት ሳያስፈልግ ቅድሚያ በጀመረው ቅርንጫፍ የጊዜ ገደብ ብቻ እንዲያጠናቅቁ ይገደዳሉ ማለት ነው፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@Yenetube @Fikerassefa
👍1
የኢትዮጵያ ወታደሮች በኢትዮ-ሱዳን ድንበር በኩል የከባድ መሳሪያ ተኩስ ከፍተው ነበር ተባለ።

ሱዳን ትሪቡን ወታደራዊ ምንጮቼ ያላቸውን ጠቅሶ እሁድ ከኢትዮጵያ ወታደሮች በኩል በድንበር ላይ ቅኝት እያደረገ በነበረ የሱዳን ጦር ላይ ከባድ መሳሪያ መተኮሱን ዘግቧል። ሆኖም የተጎዳ አለመኖሩንም ነግረውኛል ብሏል።የዘገባው ባለቤት ሁለቱም አገራት ወደ ጦርነት መግባት እንደማይፈልጉ እየገለፁ ነው ካለ በኋላ፤ ሆኖም ሱዳን በድንበሩ ጉዳይ ከኢትዮጵያ በኩል እየቀረበ ያለን የድርድር ጥያቄ አልተቀበለችም ሲል ጽፏል።ምክንያቱ ደግሞ የካርቱም መንግሥት በቅርቡ የተቆጣጠረውን መሬት የእኔ ሉኣላዊ ግዛት ነው የሚል እምነት ያሳደረ በመሆኑ ነው ብሏል።

የሱዳን መንግሥት ከኅዳር ጀምሮ በ10 ሺሕዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን በድንበር አቅራቢያ ማስፈሩንም ሱዳን ትሪቡን አክሏል።ዘገባው ጨምሮም የሱዳን ወታደሮች ድንበር ጥሰው ወደ አትዮጵያ በመግባት በኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች ሰብል የተሸፈንን መሬት መያዛቸውን ነው የገለፀው።የአገሪቱ ባለሥልጣናት የቀድሞው የሱዳን መንግሥት ለኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች ሰጥቷቸው እንጂ መሬቱ የሱዳን ነው የሚል እምነት ማሳደራቸውም ይሰማል።አሐዱ ቴሌቪዥን እሁድ ተፈጽሟል ስለተባለው ተኩስና ወቅታዊ የድንበሩ ጉዳይ ለመጠየቅ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው ሬድዋን ሁሴን እና ቃል አቀባዩ ዲና ሙፍቲ የስልክ ጥሪን ቢያደርግም ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም ብሏል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
በሱማሌ ክልል ለግብርና ኢንቨስትመንት በሚል ተወስደው ከልማት ባንክ ብድር ተወስዶባቸው ባለመልማታቸው በእዳ ማካካሻ የተያዙ መሬቶችን ወደ ስራ ለማስመለስ ንግግር እየተደረገ ነው።

የሶማሌ ክልል የመስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱራህማን ኢድ ለካፒታል እንደተናገሩት ከለውጥ በፊት በአንዳንድ ክልሎች ተደርጎ የነበረው በመሬት ብድር በመውሰድ በህገወጥ የመበልፀግ ባህሪ በሱማሌ ክልልም በተወሰነ መልኩ ተከስቶ ነበር።መሬት እና ብድር ወስደው ተገቢውን ልማት ባላከናወኑት ለእዳ ማካካሻነት ልማት ባንኩ የተቆጣጠራቸውን ለም መሬቶች ተመልሰው ወደ ስራ የሚገቡበትን መንገድ ለመፈለግ በክልሉ ፕሬዝደንት መሪነት የተቋቋመ ኮሚቴ ከባንኩ ሃላፊዎች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የቢሮ ሃላፊው ተናግረዋል።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል የሚገኘው ነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ፣ ግጦሽ እና ሰደድ እሳት እንደወደመ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና እና አርብቶ አደር ቋሚ ኮሚቴ ማረጋገጡን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡የኦነግ ሸኔ ሕገወጥ ታጣቂዎች በፓርኩ ለረጅም ጊዜያት መሽገዋል፡፡የጋሞ ዞንም ሸማቂዎቹን ከፓርኩ ማስወጣት እንዳልቻለ ለኮሚቴው ገልጧል፡፡ኮሚቴው የታጣቂዎችን ጥቃት በመፍራት ኮሚቴው የፓርኩን አብዛኛውን ክፍል መጎብኘት ሳይችል ቀርቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የዶክተር ጥላሁን ገሰሰ አዲስ አልበም በቅርቡ ለአድማጭ እንደሚቀርብ ተገለጸ።

የአርቲስት ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ አዲስ የሙዚቃ አልበም ለአድማጭ በቅርቡ እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡ለአድማጭ የሚቀርበው አልበም ጥላሁን ገሰሰ በህይወት እያለ የሰራቸው ነገር ግን ለአድማጭ ያልቀረቡ ስራዎች ናቸው ተብሏል፡፡የአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ባለቤት ወ/ሮ ሮማን በዙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳረጋገጡት ከዚህ በፊት ለአድማጭ ያልቀረቡ እና ያልታተሙ ስራዎች በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል ብለዋል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘም አልበሙ ምን ያህል ሙዚቃዎች እንዳካተተ እና የአልበሙ ይዘት በቅርቡ ለህዝቡ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል ወ/ሮ ሮማን፡፡

አሁን ላይ ካሳታሚ ድርጅቶች እና የአልበሙን ስራ ከሚከታተሉ ሰዎች ጋር በአልበሙ ዙርያ ምክክር እያደረግን እንገኛለንም ብለዋል፡፡አዲስ በሚታተመው የአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ አልበም በመድረክ የተጫወታቸው ነገር ግን ህዝቡ የማያውቃቸው ስራዎች እንዳሉበትም ነው የተነገረው፡፡አልበሙን ያቀናበረው አበጋዝ ክብረወርቅ ሽኦታ መሆኑንም ወይዘሮ ሮማን ተናግረዋል።የአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ አድናቂዎች በተለያዩ ጊዜያቶች የአልበሙ ሂደት ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡በመጨረሻም የአልበሙ መታተም እውን የሆነ መስሏል፡፡

Via Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
የ8ኛው ጉዞ አድዋ ተጓዦች በትግራይ ችግር ውስጥ ላሉ ወገኖች የሚውል ከ2 ሺህ ኩንታል በላይ የዕለት ደራሽ እርዳታ ማሰባሰባቸውን የጉዞው አስተባበሪ አቶ ያሬድ ሹመቴ ገልጿል።

ከ2 ወር በፊት የእርዳታ ማሰባሰብ በአዲስ አበባ መጀመሩን የገለፀው አቶ ያሬድ እስካሁን ባለው ሂደት ከ2 ሺህ ኩንታል በላይ እርዳታ አሰባስበው 200 ኩንታል የሚሆነውን ደግሞ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን ተናግረዋል።120 ተጓዦችን ያካተተው የጉዞ አድዋ 8ኛው የተጓዦች ቡድን 125ኛውን የዓድዋ በዓል ታሳቢ በማድረግ ጎዞውን ከአንድ ሳምንት በፊት ከአዲስ አበባ ወደ አድዋ መጀመሩ ይታወቃል።

ቡድኑ አንድነትንና ኢትዮጵያዊ መተሳሰብን በተግባር ለማሳየት ዘንድሮ በጉዞው በሚያገኟቸው ከተሞች በትግራይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ እንደሚሰሩም ተገልጿል።በቀጣይም በሚደርሱባቸው ከተሞች ማለትም በደብረ ብረሃን፣ ሸዋሮቢት፣ ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴና ወልድያ ከተሞች ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር እርዳታ የማሰባሰቡ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው አቶ ያሬድ ያስታወቀው።

የሚሰበሰበው ዕርዳታ በገንዘብ ሳይሆን በዓይነት ብቻ መሆኑን የገለፀው አቶ ያሬድ ልገሳ የሚያደርግ ማንኛውም አካል የሚያስፈልጉ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ጨምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ቢሰጣቸው ለተረጂዎች ለማድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጿል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት በደረሰ የእሳት አደጋ፤ የዘጠኝ አመት ህፃን ልጅ ህይወት አለፈ!

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ገደማ በአንድ ህንፃ ላይ በሚገኝ የዕቃ
ግምጃ ቤት ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረት የጠፋ ሲሆን በአደጋው የአንዲት የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ የሆነ የዘጠኝ አመት ህፃን ልጅ ህይወት ማለፉ ታውቋል።

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ፖሊስ የምርመራ ስራ ጀምሯል፡፡ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ እና የእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች ላደረጉት ጥረት ዩኒቨርሲቲው ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

[ብስራት ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የኤርትራ ተዋናዮች መኖር እንዳሳሰባቸው ተሰናባቹ የአሜሪካ አባሳደር ገለጹ!

በትግራይ ክልል የኤርትራ ተዋናዮች መታየት በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው እና በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አባሳደር ማይክል ራይኖር ገለጹ።አምባሳደሩ በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ግፍ የተሞላባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና የአስገድዶ መድፈር እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ ሊቆሙ እንደሚገባ እና በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቀዋል።

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa