የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መንግሥት ሁሉንም የቤት ሰራተኞች ቀጣሪ ኤጀንሲዎችን ሊዘጋ ነው፡፡
የቤት ሰራተኞች አስመጪ ኤጀንሲዎቹ በመጋቢት ወር ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጉ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡በአገሪቱ 250 የቤት ሰራተኛ አስቀጣሪ ኤጀንሲዎች እንዳሉ መረጃው አስታውሷል፡፡አብዛኞቹም በሕገ-ወጥ መንገድ በቱሪስት ቪዛ ወደ አገሪቱ የቤት ሰራተኞችን የሚያስገቡ ናቸው ተብሏል፡፡ነባሮቹ የግል ኤጀንሲዎች በመጋቢት ወር ሙሉ በሙሉ ሲዘጉ ለዚሁ ዓላማ የተቋቋሙ 58 የመንግሥት ማዕከላት የቤት ሰራተኞችን ቅጥር እና አስተዳደር እንደሚያቀላጥፉ ተነግሯል፡በመንግሥት ስታትስቲካዊ አሃዝ መሰረት በኢሚሬትስ ከሚኖሩ ሰዎች ከ88 በመቶ በላይ የውጭ አገራት ዜጎች ናቸው፡፡
[ሚድል ኢስት ሞኒተር/ሸገር]
@YeneTube @FikerAssefa

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትግራይ ክልል 18.3 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እህል ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብረሃም በላይ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ አስረክበዋል።ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ድጋፉ በጁንታው እኩይ ተግባር ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ የትግራይ ወገኖች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ያለመ ነው።የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ዲሞክራሲ ህይወቱን የሰዋ ህዝብ በመሆኑ በነሱ የደረሰው ጉዳት የኛም ጉዳት ነው፤ በቀጣይ ክልሉን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆን የድጋፍ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ባለሙዎች በትግራይ ክልል በቀጣይ ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ ጊዜያዊ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር መክረዋል።ለናሙናነት በተካሄዱ የመስክ ምልከታዎች እንደተረጋገጠው በክልሉ የሚገኙ የትምህርት መሠረተ-ልማትና ግብዓቶች በህወሃት የጥፋት ቡድን ጉዳት እንደደረሰባቸውና እንደተዘረፉ ለመመልከት መቻሉን ሚንስቴር መስሪያቤቱ በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።የመማር-ማስተማር ሥራው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ነበረበት እንዲመለስ የክልሉ መንግሥትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ አረጋግጠዋል።

አቶ በላይነህ ክንዴ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ-ራንች ጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ800 ኩንታል ዱቄት ድጋፍ ማድረጋቸውን በቻግኒ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
በከታማዋ በጊዜያዊነት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ጀምበሩ ደሴ እንደገለፁት ባለሃብቱ በላይነህ ክንዴ ያደረጉት ድጋፍ ለተፈናቃዮች ጊዚያዊ እፎይታ የሚሰጥ እና ለወገን ደራሽነታቸውን ያሳዩበት ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በቻግኒ ከተማ ራንች በተባለው ጊዜያዊ መጠለያ ከ40 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ አብመድ ዘግቧል።

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎችን ጥር 20 እና 21 በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኹሓ ካምፓስ ተቀብሎ እንደሚያስተምር አስታወቀ።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ የመማር ማስተማር ሂደትን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ “በትግራይ ክልል እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ተቋርጦ የነበረው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኹሓ ካምፓስ ይጀመራል” ብለዋል።ዩኒቨርሲቲው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተደረገ ውይይት ተመራቂ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆች የደህንነት ስጋት ሳይገባቸው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተመራቂዎቹ መገኘት እንዳለባቸው በመግለጽ ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣይም ሌሎች ተመራቂ ላልሆኑ ተማሪዎች ጥሪ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው የሚያስተምር መሆኑንም ነው የገለጹት።የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና የመሰረተ ልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ሰለሞን አብርሃም፤ መንግስት በትግራይ ክልል ባካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ሂደት ተስተጓጉሎ እንደነበር አስታውሰዋል።በዋናነት በአክሱም እና በአዲግራት ዩኒቨርሰቲ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማስቀጠል እንዳልተቻለም አንስተዋል።የመቀሌ እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቃቸውን ፕሬዚዳንቱ አስታውሰዋል።በአክሱም እና አዲግራት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እንዲቀጥል የማመቻቸት ስራ መስራቱን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በትግራይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በጤናው ዘርፍ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል የጤና ባለሞያዎች ቡድን መላኩን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ!
በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በጤናው ዘርፍ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል የተለያዩ የጤና ባለሞያዎች ቡድን ወደ ክልሉ መላኩን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ ኤጀንሲዎች እና የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ከሰብአዊ ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል ድጋፍ እና መልሶ ማቋቋም ላይ በስፋት እየሠራ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በትግራይ በተጎዱ አካባቢዎች ያለው የኅብረተሰብ ጤና እና ደህንነት ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ መንግሥት በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ድንገተኛ ምላሽ እየሰጠ እና ወሳኝ የጤና አገልግሎቶችን ለማድረስ ካለፉት በርካታ ሳምንታት ወዲህ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
በክልሉ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻልም የተለያዩ የጤና ባለሞያዎች ቡድን መላኩንም ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡
እስካሁንም ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶች እና የሕክምና ግብዓቶችን በክልሉ ለሚገኙ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ማእከላት ተልከው ለሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛሉም ብሏል፡፡
ጤና ተቋማት የሚሰጡት መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማስቀጠል ከሕክምና አቅርቦቶች እና መድኃኒቶች በተጨማሪ አምቡላንሶችን ጨምሮ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም በሚኒስቴሩ መግለጫ ተመልክቷል፡፡
በማኅበረሰቡ ውስጥ የበሽታ ቅኝት እና የተንቀሳቃሽ ክሊኒከ አገልግሎቶችም በአንዳንድ አካባቢዎች ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር እየተሰጠ እንደሚገኝ የገለጸው የጤና ሚኒስቴር፣ እየሰጠ ያለውን የጤና አገልግሎት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡
Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa

ለትግራይ ክልል 71 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና ግብዐቶች ተልከዋል!
በትግራይ ክልል ለደረሰው አስቸኳይ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እስካሁን ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና ግብዐቶችን በክልሉ ለሚገኙ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ማዕከላት በመላክ ለሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
ለደረሰው አስቸኳይ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ ለመስጠትም የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች የያዘ ቡድን ወደ ትግራይ መላኩን ጠቅሷል።
ሚኒስቴሩ፣ ተጠሪ ኤጀንሲዎቹ እና የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ከሰብዓዊና ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል ድጋፍ እና መልሶ ማቋቋም ላይ በስፋት እየሰሩ እንደሚገኙም በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አመልክቷል።
“በተጎዱ አካባቢዎች ያለው የህብረተሰብ ጤና እና ደህንነት ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ሲሆን መንግስት በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች የድንገተኛ ምላሽ እየሰጠና ወገኖች ወሳኝ የጤና አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ ላለፉት በርካታ ሳምንታት እየሰራ ይገኛል” ሲል ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

ፌስቡክ የትራምፕን አካውንት ለማገድ ያሳለፈውን ውሳኔ ለተቆጣጣሪ ቦርድ አቀረበ!
ፌስቡክ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አካውንትን ላልተወሰነ ጊዜ ለማገድ ያሳለፈውን ውሳኔ ገለልተኛ ለሆነው የተቆጣጣሪ ቦርዱ መምራቱን አስታውቋል፡፡ ይዘትን በተመለከተ የካምፓኒውን ውሳኔ ሊሽር የሚችለው በቅርቡ የተመሰረተው ቦርድ ወሳኔውን እስኪመረምረው ድረስ የትራምፕ አካውንት እንደታገደ ይቆያል ተብሏል፡፡ የትራምፕ አካውንት የታገደው ደጋፊዎቻቸውን በማስተባበር በካፒቶል ችግር ፈጥረዋል የሚል ውግዘት ከደረሰባቸው በኋላ ነው፡፡የፌስቡክ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኃላፊ ኒክ ክሌግ በበኩላቸው “በእኛ ጉዳይ ላይ በጣም እምነት አለኝ” ብለዋል ፡፡ “ያንን ውሳኔ የወሰንንበትን ሁኔታ የሚመለከት እና አሁን ያሉትን ፖሊሲዎቻችንን የሚመለከት ማንኛውም ምክንያታዊ ሰው እንደሚስማማ በጣም እርግጠኛ ነኝ” ብለዋል፡፡
✍Al-ain

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን የሚያስተባብር ምክትል ርዕሰ መምህር በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲኖር የሚያስችል የአደረጃጀት መመሪያ እየተዘጋጀ ነው::
Via :- ትምህርት ሚንስትር
@Yenetube @FikerAssefa
Via :- ትምህርት ሚንስትር
@Yenetube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን በተቀሰቀሰ የኩፍኝ ወረርሽኝ የሁለት ሕጻናት ሕይወት ሲያልፍ ሌሎች ከ80ያ በላይ የሚሆኑት መታመማቸውን የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተቋም አመለከተ።
ተቋሙ እንዳስታወቀው የኩፍኝ ወረርሽኙ ከባለፈው ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ የተቀሰቀሰው በዞኑ ካራትና ሰገን ዙሪያ ወረዳዎች ውስጥ ነው።በወረዳዎች በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ 81 ሕጻናት በወረርሽኙ ተይዘው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ነው የተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር አቶ እንዳሻው ሽብሩ ዛሬ ለዶቼ ቬለ (DW) የገለጹት። በወረርሽኙ ከተያዙት መካከል በካራት ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበሩ ሁለት ህጻናት ህይወታቸው ማለፉን ምክትል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።ወረርሽኙ በወረዳዎቹ ሊከሰት የቻለው ከወራት በፊት በክልል ደረጃ የተከናወነው መደበኛ የሕጻናት ክትባት ዘመቻ በስፍራው በሚታየው የጸጥታ ችግር የተነሳ ሳይካሄድ በመቅረቱ መሆኑን አቶ እንዳሻው አመልክተዋል።በአሁኑ ወቅት የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ ከኮንሶ ዞን ጤና መምሪያና ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በተውጣጣ የባለሙያዎች ግብረ ሀይል አማካኝነት ክትባት የመስጠት ሥራ መጀመሩንም ገልጸዋል።ለአንድ ሳምንት በሚካሄደው የመከተብ ሥራ ከ24 ሺህ በላይ ሕጻናት ይከተባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምክትል ዳይሬክተሩን የጠቀሰው የዶይቼ ቨሌ ዘገባ ያመለክታል።

ፍርድ ቤቱ እነ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ የ18 ተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ!
ነገር ግን ዐቃቤ ሕግ ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ማመልከቻ አቅርቧል።
የማመልከቻው ይዘት በእነ ጃዋር የክስ መዝገብ አምስት ክሶች በተለይም ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ጋር በተያያዘ አዋጁን ጠቅሶ ዋናው ክስ ላይ የጠቀሰውን የክስ ጭብጥ ፍርድ ቤቱ እንዲያሻሽል ትእዛዝ ቢሰጥም ማሻሻል እንደማይችል የተለያዩ ምክንያቶች ጠቅሶ ማመልከቻ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
ችሎቱም የተወሰነ ጊዜ ወስዶ የዐቃቤ ሕግን ማመልከቻ መርምሯል። በመሆኑም ከጦር መሣሪያ አዋጅ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የሰጠው ትእዛዝ አሳማኝ መሆኑን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ ከጦር መሣሪያ ጋር ተያየዝ በተከሳሾች ላይ ያቀረበውን ክስ የማያሻሽል መሆኑን በመገንዘብ እንዲቋረጥ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ይህንንም ተከትሎ ፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃል እንዲሰጡ ተከሳሾችን ጠይቋል፤ ነገር ግን የተከሳሽ ጠበቆች ተሻሽሏል የተባለውን ክስ በአግባቡ ለመረዳት ጊዜ ስለሚያስፈልግ እና ከደንበኞች ጋር ለመመካከር ስለሚያስፈልግ አሁን ባለንበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ያስቸግራል፤ ስለዚህ አጭር ቀጠሮ ይሰጠኝ በማለት አመልክተዋል።
ተከሳሾችም በዛሬው ቀጠሮ የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ዝግጁ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።
ይህንን ግምት ውስጥ ያስገባው ችሎቱ ተከሳኞች ጠበቆች ከጠቀሱት ወሳኝ በሚባለው የእምነት ክህደት ቃል መስጠት ጋር በተያያዘ በቂ ዝግጅት አድርገው እንዲመጡ ለመጪው ረቡዕ ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
[ዳጉ ጆርናል]

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰላም እና ብሔራዊ መግባባት ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጠ!
በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለሰላም እና ብሔራዊ መግባባት መሠረት ናቸው ባሏቸው ጉዳዮች ያደረጉትን ውይይት አስመልክተው ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጫ ሰጥተዋል።በተያዘው ዓመት የሚደረገው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲያልፍ ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ሂደትም ሆነ ከምርጫ በኋላ ሁሉም ፓርቲዎች እና ባለድርሻ አካላት ሊያደረጉ የሚገቡ ጉዳዮችን የሚዳስስ ውይይት ከጥር 02-04 ቀን 2013 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ባደረጉት ውይይት የጋራ መግባባት ላይ የደረሱባቸውን ነጥቦች በዝርዝር አቅርበዋል።
በቀረበው መግለጫ ከምርጫው በፊት እና በኋላ ሀገራዊ ሰላም እንዲጠበቅ ይበጃሉ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት መወያየታቸውን አስገንዝበዋል።በሀገራዊ ሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ፣ የሰብአዊ መብት መከበር ጉዳይ ፣ የመንግስት ሓላፊነት እና ተጠያቂነት ላይ የጋራ መግባባት መደረሱ ተገልጿል፡፡በተጨማሪም የብሔረሰብ የማንነት ጥያቄ እና የምርጫ ክልል ተያያዥነት፣ በምርጫው ውጤት ሊነሡ ስለሚችሉ ጉዳዮች እና ተጠያቂነት፣ የፀጥታ አካላት ገለልተኝነት፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ገለልተኝነት ‹የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና የተቋማት ገለልተኝነትም መግባባት ከተደረሰባቸው መካከል መሆናቸውን ከሠላም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የሚዲያ ተቋማት ገለልተኝነት፣ ምርጫው ፍትሐዊ እና ተአማኒ እንዲሆን የፖለቲካ ምኅዳሩን ስለማስፋት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ የታሪክ እና ትርክት ጉዳይ፣ ብሔራዊ ዕርቅ በሚሉ ጉዳዮች ውይይት እንዳካሄዱባቸው እና የጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱባቸው በመግለጫ አትተዋል።

የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ!
የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ የሱዳን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ ዶሚኒክ ራብ በካርቱም ቆይታቸው በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበርና በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ፣ከሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት አባላትና ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክና ከካቢኔ አባሎቻቸው ጋር ፣ ውይይት ማድረጋቸውን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ዛሬ አመሻሽ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ይወያያሉ፡፡
[Al-ain]

(January 24 ) የፊታችን እሁድ በመዲናች አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ የመኪና ውድድር ይካሄዳል።
ከጠዋቱ አንድ ሰዐት ጀምሮ የሚካሄደውን የመኪና ውድድር አስመልክቶ ሜክሲኮ ቶታል አካባቢ ለገሀር እንዲሁም ብሄራዊ አካባቢ መንገዶች ዝግ እንደሚሆኑ አዘጋጅ ክፍሉ ጠቁሞናል።
የውድድሩ አዘጋጅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሞተር ስፖርት አሶሴሽን ነው።
@Yenetube @Fikerassefa
ከጠዋቱ አንድ ሰዐት ጀምሮ የሚካሄደውን የመኪና ውድድር አስመልክቶ ሜክሲኮ ቶታል አካባቢ ለገሀር እንዲሁም ብሄራዊ አካባቢ መንገዶች ዝግ እንደሚሆኑ አዘጋጅ ክፍሉ ጠቁሞናል።
የውድድሩ አዘጋጅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሞተር ስፖርት አሶሴሽን ነው።
@Yenetube @Fikerassefa
ጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ስድስት ወራት ከዕቅድ በላይ ኃይል ማመንጨት ችሏል ተባለ!
የጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በግማሽ ዓመቱ 958 ጌጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ለማመንጨት አቅዶ 1028 ነጥብ 5 ጌጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ማመንጨቱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ሐብታሙ ገረመው አስታወቁ፡፡ጣቢያው ያመነጨው ከዕቅዱ የ7 በመቶ ብልጫ እንዳለው ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል።ከጊቤ 3 እና ከበለስ ቀጥሎ ትልቁ የኃይል ማመንጫ የሆነው የጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ 420 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ሲኖረው የሀገሪቱን የኃይል ፍላጎት ከማሟላት አንፃር የጎላ ሚና በመጫዎት ላይ የሚገኝ ጣቢያ ነው፡፡
ከሰው ኃይል ልማት አኳያም ለዘጠኝ አዲስ መሐንዲሶች እና ለአራት ቴክኒሺያኖች ለሁለት ወራት ያህል የስራ ላይ ስልጠና መሰጠቱን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡የጣቢያው የጥገና ክፍል ተወካይ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ተስፋ በበኩላቸው ከኦፕሬሽን ተግባራት ጎን ለጎን ጣቢው ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል የጥገና ሥራዎች ሲከናወኑ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ዘይት እያፈሰሰ የኃይል ማመንጨቱን ስራ ያስተጓጉል የነበረውን የውሃ መቀበያ ዋና አሸንዳ እና የመቆጣጠሪያ ክፍል የአየር ማቀዝቀዣ በጥገና ክፍሉ ባለሙያዎች ተጠግኖ ወደ ስራ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡በ2002 ዓ.ም ተመርቆ በይፋ ስራ የጀመረው የጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሶስት ትራንስፎርመሮችን የያዘ ባለ 400 ኪ.ቮ ስዊች ያርድ አለው፡፡
[EEPco]

የበሪሳ ጋዜጣ መስራች ፕሮፌሰር ማህዲ ሀሚድ ሙዴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
ፕሮፌሰር ማህዲ ሀሚድ በ1960ዎቹ በብቸኝነት በአፋን ኦሮሞ ሲዘጋጅ የነበረውን በሪሳ ጋዜጣን ካቋቋሙት እና በአርታኢነት ካገለገሉ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ነበሩ፡፡በሪሳ በጊዜው በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የአፋን ኦሮሞ የግል ጋዜጣ የነበረ ሲሆን በደርግ መንግስት ከተወረሰ በኋላም ብቸኛው በቋንቋው የሚታተም ጋዜጣ ነበር፡፡
የሂሳብና የፊዚክስ መምህሩ ፕሮፌሰር ማህዲ ሀሚድ ሙዴ የአፋን ኦሮሞ መዝገበ ቃላት፣ የበሪሳ ግጥሞች፣ የበሪሳ ደብዳቤዎችን እና ሌሎች መፅሀፍትን ለንባብ አብቅተዋል፡፡ፕሮፌሰሩ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ የተወለዱ ሲሆን ኑሯቸውን ውጭ ሃገር አድርገው ቆይተዋል፡፡ባደረባቸው የልብ ህመም የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቢቆዩም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
Via FBC

የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጎንደር ገብተዋል!
የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ የብሪታኒያ ተራድኦ ድርጅት በሰሜኑ የኢትዮጵያ አካባቢ እያቀረበ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ ጎበኙ፡፡ሚኒስትሩ በጎንደር በመገኘት የብሪታኒያ ተራድኦ ድርጅት ለዓለማቀፉ የምግብ ፕሮግራም እና በተመድ የሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ ያደረገውን የ10 ሚሊየን ፓውንድ የሰብዓዊ ድጋፍ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ሚኒስትሩ ሰብዓዊ ድጋፉ በተፈለገው ቦታ ተደራሽ እንዲሆን ይሰራል ስለማለታቸውም ከኤፍቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ 11 ሰራተኞቹን ከስራ ማሰናበቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለፀ!
አገልግሎቱ ባለፉት ስድስት ወራት ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ በ68 ሰራተኞችና በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ የስራ መሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።በዚህም መሰረት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው 22 ፣ የደመወዝ ቅጣት የተጣለባቸው 35 ፣ ከስራ የተሰናበቱ 11 ሲሆኑ ፤ በዲሲፕሊን ኮሚቴ በመጣራት ሂደት ላይ የሚገኙ 39 ሰራተኞች ይገኙበታል ብሏል፡፡
በቅንነትና በታማኝነት ደንበኞችን ለማገልገል ሌት ተቀን የሚተጉ በርካታ የተቋሙ ሠራተኞች እንዳሉ ሁሉ ጥቂት የስነ ምግባር ችግር የሚስተዋልባቸው ደንበኞችን የሚያማርሩ ሲያጋጥሙ ፤ ህብረተሰቡ ተባባሪ ከመሆን መቆጠብ ይኖርበታል ተብሏል። እንዲሁም ቅሬታና ጥቆማ ሲኖር ፤ ተቋሙ በዘረጋቸው አሰራሮች በመጠቀም ጥቆማ ይደረግ ዘንድ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥሪ አቅርቧል።
[Bisrat FM]

እውቁ ጋዜጠኛ ላሪ ኪንግ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፈ!
አሜሪካዊው የቴሌቪዥንና ሬድዮ ፕሮግራም አቅራቢ በ87 አመቱ በቫይረሱ ህይወቱ አልፏል።ለስድስት አስርት ዓመታት በቆየው የስራ ዘመኑ በአሜሪካ በሚዲያ ከፍተኛ እውቅና ካላቸው ባለሙያዎች መካካል አንዱ ነው።እንደ ሲኤንኤን መረጃ ከሆነ በስራ ዘመኑ ከ30ሺ በላይ ቃለመጠይቆችን ሰርቷል።ከነዚህ መካከል ያሲር አራፋት፣ማንዴላን እና ፑቲንን ጨምሮ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ከሪቻርድ ኒክሰን ጀምሮ የቅርብ ጓደኛው እስከ ሆኑት ትራምፕ ድረስ ሁሉንም ቃለ መጠይቅ አድርጓል።
ላሪ ኪንግ ከሲኤንኤን በ2012 ከለቀቀ በኃላ ከሜክሲካዊው ቢሊየነር ካርሎስ ስሊም ጋር ኦራ የተሰኘ ቴሌቪዥን ጣቢያ መስርቷል።ስምንት ጊዜ ጋብቻ መስርቶ የፈታ ሲሆን የመጨረሻ ወይንም ስምንተኝ ትዳሩ በ2019 በፍቺ ተደምድሟል።አምስት ልጆች አሉት።ኪንግ በልብ፣በሳምባ ካንሰርና በስትሮክ በተለያዩ ጊዜያት ታሞ ነበር።ላሪ ኪንግ ላይቭ የተሰኘው ፕሮግራሙ ለ25 ዓመታት ሲያቀርብ በየምሽቱ 1.5 ሚሊየን ሰዎች ይከታተሉት ነበር።
✍ዳጉ ጆርናል

ክቡር ገና በመጪው ምርጫ ኢዜማን ወክለው ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በዕጩ ተወዳዳሪነት ሊቀርቡ ነው!
የቀድሞው የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ ክቡር ገና፤ በመጪው ምርጫ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን ወክለው በአዲስ አበባ ምክር ቤት ለመወዳደር በዕጩነት ቀረቡ። በኢዜማ የመሪነት እና የምክትል መሪነት ስልጣን ያላቸው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አንዷለም አራጌ፤ ለተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመመረጥ ከሌሎች የፓርቲው እጩዎች ጋር በነገው ዕለት ይፎካከራሉ።
ኢዜማ፤ ፓርቲውን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤትም ሆነ ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ዕጩዎችን የሚያስመርጠው፤ በየምርጫ ወረዳዎቹ ባሉ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት በሚሰጥ ድምጽ ነው። ፓርቲው አሉኝ ከሚላቸው 435 የምርጫ ወረዳዎች ውስጥ በ329ቱ የዕጩዎች ምርጫ አካሄዶ ማጠናቀቁን አስታውቋል። በዛሬ እና በነገው ዕለት ደግሞ በ71 የምርጫ ወረዳዎች የዕጩዎች ምርጫ ለማካሄድ ቀነ ቀጠሮ ይዟል።
[Ethiopia Insider]