YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጣልያን ገጠራማ ቦታ በግብርና ስራ ትተዳደር የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ አጊቱ ጉደታ መሞቷን በጣልያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታወቀ።

በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዳስታወቀው በአጊቱ ጉደታ ድንገተኛ ሞት ማዘኑን ገልጿል።

ኤምባሲው የግድያ ሁኔታው በቶሎ ተጣርቶ እንዲገለፅና ወንጀለኛ ተለይቶ ለፍትህ እንዲቀርብ ከጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።

አጊቱ ጉደታ በጣሊያን ገጠራማ ስፍራ መሬት ገዝታ ፍየል እያረባች፤ አይብ በማምረት ትተዳደር እንደነበረ ሪፐብሊካ የተባለ የጣልያንኛ ጋዜጣ በሰራው ዘገባ አስፍሯል።

Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኖ የፀሐይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

የ12ቱ ትናንሽ የፀሐይ ሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ፓይሌት ፕሮጀክት አንድ አካል የሆነውና ከሐረር ከተማ 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚኖ ከተማ የተገነባው የሶላር ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡የግንባታ ስራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የሚኖ ፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 225 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን የግንባታ፣ ፍተሻና የሙከራ ስራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረጉት ቆይታ የህወሃት ጉዳይ በቦርዱ እየታየ መሆኑን ተናግረዋል።

በቆይታቸው "በአመፅ ድርጊት፣ የሃይል እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ የሚሉትን ጉዳዮች ቦርዱ መርምሮ፣ ህጎች አገናዝቦ በህወኃት ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ ይኖራል፣ ገና በመታየት ላይ ነው፣ እንደጨረስን ውሳኔውን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡" ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የፋይናንስ ጤናማነት አመላካቾችን/ FSI በመጠቀም በየሩብ አመቱ ለIMF ማቅረብ ልትጀምር ነው።

ባለፈው ሰኔ አጋማሽ እና ሃምሌ መጀመሪያ የ IMF ባለሞያዎች ለብሄራዊ ባንክ የባንኮች ተቆጣጣሪ ክፍል የቅድመ ዝግጅት እና ስልጠና መሰረት ማእከላዊ ባንኩ የባንኮችን የሂሳብ ጤናማነት ይበልጥ መረዳት እና መመዝገብ በሚያስችለው ደረጃ አቅም የፈጠረ ሲሆን።ይህንኑ መሰረት ያደረገ የጤናማነት ሪፖርት በየሩብ አመቱ እያዘጋጀ ለውስጥ ስራ እና ትንተና ከመጠቀም አልፎ ለ IMF የስታቲክስ ክፍል እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ ወር አንስቶ እንደሚያቀርብ ታውቋል።ከዛም ባለፈ ሪፖርቱ በስታቲክስ ክፍሉ ድረ ገፅ ላይ የሚወጣ ሲሆን ይህም ቀደም ሲል መረጃቸው ከሚለቀቀው 143 አገራት በተጨማሪ ኢትዮጵያን የሚያካትት ይሆናል።በትግበራው ከልማት ባንክ ውጭ ያሉት ሁሉም ባንኮች የሚካተቱበት ይሆናል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
የጸረ ኮሌራ ክትባት በጉጂ ዞን ተጀመረ!

የጸረ ኮሌራ ክትባት በጉጂ ዞን አባያ ወረዳ በኢትዮጵያ የማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትውት ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ በተገኘበት ተጀምሯል።ኮሌራ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች መከሰቱን ዳይሬክተሩ ገልጿል፡፡

በዚህም 15,623 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ 275 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ባሳለፍነው አመት ደግሞ በድምሩ በአራት ክልሎች እና 26 ወረዳዎች ላይ በሽታው ተከስቷል፡፡ በዚህም 17,956 ሰዎች ተይዘው 319 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ኢንሰቲትዩቱ ይፋ አድርጓል።

እስካሁን ክትባቱ በኦሮሚያ አምስት ወረዳዎች፣ በደቡብ አምስት ወረዳዎች፣ በሱማሌ ሶስት ወረዳዎች፣በአፋር ሁለት ወረዳዎች እንዲሁም በአዲስ አበባ በተመረጡ ቦታዎች ላይ በ2012 በተደረገ ክትባት በመጀመሪያ ዙር ብቻ 613,572 ሰዎች የኮሌራ ክትባትን ሲያገኙ በሁለተኛ ዙር ክትባት ደግሞ ለ285,354 ሰዎች በምዕራብ ሃረርጌ ዞን አምስት ወረዳዎች ክትባቱን መስጠት እንደተቻለ ተናግሯል።

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዳሴ ግድብ ድርድር በመጭው ዕሁድ እንዲቀጥል አፍሪካ ኅብረት ለሦስቱ ሀገራት ጥሪ ማድረጉን የግብጽ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡ የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲም ትናንት በሰጡት መግለጫ ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡ ድርድሩ ላንድ ወር የተቋረጠው፣ ሱዳን የአፍሪካ ኅብረት ባለሙያዎች በድርድሩ ጠንካራ ሚና ይሰጣቸው፤ የድርድሩ አካሄድም ይቀየር የሚል ቅድመ ሁኔታ ካሰቀመጠች በኋላ ነበር፡፡ ዐርብ በሚገባው አዲሱ የፈረንጆች ዐመት ዲሞክራቲክ ኮንጎ የአፍሪካ ኅብረትን የወቅቱ ሊቀመንበርነት ቦታ ከደቡብ አፍሪካ ትረከባለች፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረው አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ መስጠት ተጀመረ።

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በትግራይ ክልል ከነበረው ሆኔታ ጋር በተያያዘ አዲስ የነዋሪነት ምዝገባ እና የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎቶች ላልተወሰነ ቆመዋል ማለቱ ይታወሳል።

ከታህሳስ 20፣ 2013ዓ/ም ጀምሮ ግን እገዳው ተነስቶ አገልግሎቱ መጀመሩን የኤጀንሲዉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዮናስ አለማየሁ መናገራቸውን ሸገር ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ጭንብል የማድረግ ግዴታ ተጣለ!

በደቡብ ክልል የኮሮና ስጋትን ለመከላከል የክልሉ ነዋሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው አስታውቀዋል።ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ማምሻውን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የክልሉ ህዝብ ኮሮናን በመከላከል በኩል እያሳየ ያለው ከልክ ያለፈ ቸልተኝነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸው ቀደም ሲል የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ይደረግ የነበረው ጥንቃቄ አሁን ላይ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡የበሽታው ባህሪ እየተቀየረና የሚያደርሰው ጉዳት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ "ጥንቃቄያችንን የምናጠናክርበት እንጂ የምንዘናጋበት አይደለም" ብለዋል።

የበሽታው ሥርጭት እየጨመረና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከመድረሱ ጋር ተያይዞ የክልሉ ህዝብ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።ተገልጋዩ ህብረተሰብ ወደ ማንኛውም የመንግስትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሲሄድ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የመጠቀም ግዴታ እንዳለበትም አስታውቀዋል።የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በበኩላቸው በክልሉ የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት አሳሰቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸዋል።

እስካሁን በክልሉ ከ150 ሺህ በላይ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል ከ4 ሺህ 300 በላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው አመልክተው፤ 46 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን አውስተዋል።በተለይ የመተንፈሻ መሳሪያዎች እጥረት እያጋጠመ በመሆኑ አሁን ያለንበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ብለዋል።የ"መካኒካል ቬንትሌተር" አቅርቦትም በቂ አለመሆኑን ያነሱት አቶ አቅናው አስከፊ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታየው መዘናጋት እንዲቆም መልዕክት ማስተላፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለአዲግራት ዩንቨርስቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተምሪዎች!!

በ2012 የትምህርት ዘመን ተመራቂ የነበራችሁ የአዲግራት ዩንቨርስቲ ተማሪዎች አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በመታደስ ላይ በመሆኑ ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ የምትመረቁት በመቐለ ዩንቨርስቲ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በመሆኑም ተማሪዎች ታህሳስ 30 እና ጥር 1 ዓ.ም በመቐለ ዩንቨርስቲ ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ተብላቿል።

@YeneTube @FikerAssefa
በግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን መጋዘኖች ውስጥ ተከማችቶ የሚገኘው ምጥን ማዳበሪያ መፍትሔ እንዲሰጠው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ አሳሰበ።

ከሰባት አመት በፊት 466 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የአፈር ማዳበሪያ አገልግሎት ሳይሰጥ በመጋዘን ተከማችቶ እንደሚገኝ በምክር ቤቱ የግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል።

ትናንት የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን መነሻ በማድረግ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከተጠሪ ተቋማት ጋር ዛሬ ውይይት ያደረገው ቋሚ ኮሚቴው በመጋዘኖች ተከማችቶ የሚገኘው የአፈር ማዳበሪያ አፋጣኝ መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስቧል።

የአፈር ማዳበሪያው የብድር ወለድና የመጋዘን ኪራይ እየተከፈለበት ለሰባት ዓመት አገልግሎት ሳይሰጥ በመቆየቱ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት እያስከተለ በመሆኑ በፍጥነት እልባት ሊሰጠው ይገባል ብሏል ቋሚ ኮሚቴው።

በውይይቱ በአሁኑ ወቅት የግብርና ልማት ስራ ላይ የሚታየው ውጤታማነት በእንስሳት ሃብት ልማትም እንዲደገም ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከሶስት ዓመት በፊት የቆላ ዝንብን ለመከላከል እንዲቻል ሁለት ድሮኖች ወደ አገር ውስጥ የገቡ ቢሆንም እስካሁን ስራ አልጀመሩም፤ ይሕ ደግሞ ሊስተካከል የሚገባው ጉዳይ ነው ብሏል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
ግብጽ የኢትዮጵያን አምባሳደር ለማብራሪያ መጥራቷን ገለጸች!

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡት መጥራቱን አህራም ዘግቧል።አምባሳደሩ የተጠሩት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ግብፅን በተመለከተ አስተያየት በመስጠታቸው ነው ተብሏል።አህራም አምባሳደር ዲና የግብጽን ውስጣዊ ጉዳይ በመጥቀስ ሰሞኑን ማብራሪያ ሰጥተዋል ብሏል።ይሁንና ቃል አቀባይ ዲና ከሰሞኑ በሰጧቸው መግለጫቸው ግብጽ የሚልን ቃል ከመጥቀስ ተቆጥበው ነበረ።ቃል አቀባዪ በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንደነበሩ ይታወቃል።

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል እና የወረርሽኙን መስፋፋት ለመግታት 'ሴቭ ዘ ችልድረን' የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት 505 ታብሌቶችን ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ አድረጓል፡፡
@Yenetube @FikerAssefa
በተያዘው ዓመት በመስኖ እየለማ ያለው የስንዴ ምርት ከውጭ አገር የሚገባውን በ50 በመቶ ያህል እንዳሚያስቀር የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ።

@Yenetube @Fikerassefa
የፀረ-ኮሌራ ክትባት ዘመቻ በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ መጀመሩን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይፋ አድረጓል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የፀሐይ ሪል እስቴት ላይ የሀራጅ ማስታወቂያ ያወጣው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ጉዳዩን ለ3 ወር እንዳራዘመው ተሰማ፡፡

ባንኩ በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የፀሐይ ሪል እስቴት አፓርትመንት ከዚህ ቀደም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ እንዲሸጡ ሀራጅ አውጥቶባቸው ነበር፡፡ሆኖም ግን የፀሐይ ሪል እስቴት የቤት ባለቤቶች ማህበር ከባንኩ ጋር መነጋገሩን ተሰምቷል፡፡በዚህ መሰረት ባንኩ ጉዳዩን ለ3 ወር እናዳራዘመው ማህበሩ ተናግሯል፡፡

የፀሐይ ሪል እስቴት የቤት ባለቤቶች ማህበር ይህን ማስተማመኛ ሰነድ ከባንኩ እንዳላገኙ ታውቋል፡፡የቡና ባንክ የሀራጅ ሽያጩን ለተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን በተመለከተ ሸገር የባንኩን የስራ ሀላፊዎች ለማግኘት ሞክሮ እንዳልተሳካለት ገልጿል፡፡በCMC አካባቢ የሀራጅ ሽያጭ የወጣባቸው አፓርትመንቶች 13 መሆናቸው ይታወቃል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
ወጋገን ባንክ ከታክስ በፊት ከ1 ቢሊየን በላይ ብር ትርፍ ማሰመዝገቡን አስታወቀ።

ባንኩ ዓመታዊ የባለአክስዮኖች ጉባኤን በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል።ባንኩ በበጀት አመቱ ከታክስ በፊት 1.1 ቢሊዮን ብር ማግኘቱን የገለጸ ሲሆን የተገኘው ትርፍ ከዓምናው ተመሳሳይ በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር 342 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው አስታውቋል።በባንኩ ደንበኞች የተከፈቱ የቁጠባ ሂሳቦች ብዛትም የ38 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 1.8 ሚሊዮን መድርሱን የባንኩ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ተፈራ ሞላ ተናግረዋል።

ባንኩ ለተለያዩ የብድር ዘርፎች ለደንበኞቹ የሰጠው አጠቃላይ የብድር መጠንም በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ 23.7 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር የ44 በመቶ ጭማሪ አስመዝግቧል።በበጀት አመቱ በባንኩ የተከፈለ ካፒታል 2.9 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ካፒታሉም ወደ ብር 5.1 ቢሊዮን አድጓል።እንደዚሁም የባንኩ አጣቃላይ ሀብት 38.2 ቢሊዮን ብር መድረሱን ባንኩ አስታውቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በዘንድሮ የገና በዓል በላሊበላ 1.5 ሚሊየን ሰዎችን ይታደማሉ ተባለ!

በየዓመቱ ታህሳስ 29 የሚከበረውን የክርስቶስ ልደትን በዓል ለማክበር 1.5 ሚሊየን የሚሆኑ የበዓሉ ታዳሚዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ አህዛዊ ግምቱን ያስቀመጠዉ በላሊበላ ከተማ ባሉ 10 የመግቢያ በሮች የሚገቡትን እንግዶች ከአሁን ቀደም በተደረገ ቆጠራ አማካይ በመዉሰድ እንደሆነ የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ መርጌታ መልካሙ አለሙ በተለይም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮውን ገናን በላሊበላ ለማክበር አስተዳደሩ የኮሮናን ቫይረስ ጥንቃቄ ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን የሰላምና እና የጸጥታ ሁኔታ ከግምት አስገብቶ በርካታ የጸጥታ አካላት ፤ሚኒሻዎች፤ በከተማዋ የሚገኙ እና የተመዘገቡ አስጎብኝዎች እንዲያስተባብሩ መደረጉን ተሰምቷል፡፡

በበዓሉ ከስርቆትና ሌሎች ወንጀሎች ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን በአስቸካይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል በዞን እና በወረዳ ደረጃ ግዚያዊ ችሎት መቋቋሙንምመርጌታ መልካሙ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በጊዜያዊነት የሚያገለግሉ አስር ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤቶች የተዘጋጁ ሲሆን በበዓሉ ማግስት የከተማዋም ወጣቶች ከተማዋን ለማጽዳት እቅድ መያዙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል አስቸኳይ እርዳታ ለሚሹ ወገኖች እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ገልጸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በደቡብ ክልል የኮሮና ስጋትን ለመከላከል የክልሉ ነዋሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው አስታውቀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ተመድና የአፍሪካ ሕብረት በዳርፉር ያሰማሩት የሰላም አስከባሪ ኃይል ተልዕኮ ተጠናቀቀ!

የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪካ ሕብረት ተልዕኮ በመጠናቀቁ በዳርፉር ተቃውሞ ተቀስቅሷል፡፡ በሱዳን ዳርፉር ግጭት እ.ኤ.አ. ከ2003 ጀምሮ 300 ሺ ሰዎች እንደተገደሉ ይታመናል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa