YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቤንሻንጉል ጉምዝ በመተከል ዞን ያለው የጸጥታ ሁኔታ አንጻራዊ መሻሻሎች እየታዩበት መሆኑን የሠላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በአዲስ መልክ የተቋቋመው የፌዴራል ኮማንድ ፖስት ወደ ስራ መግባቱን ተከትሎ በመተከል ያለው የጸጥታ ሁኔታ ቀደም ሲል ከነበረው እየተሻሻለ መምጣቱን በሠላም ሚኒስቴር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ይትባረክ ተስፋዬ በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል።የመተከል ዞን የጸጥታ ስራ ለጊዜው በሀገር መከላከያ ሠራዊት እንዲተዳደር መደረጉም ተገልጿል።ከመተከል አካባቢ የተፈናቀሉት ነዋሪዎች በመተከል ዞን እና በአዊ ዞን ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በመተከል ዞን በ6 የመጠሊያ ማዕከላት 58 ሺህ ያህል ተፈናቃዮች መኖራቸውን ገልጸዋል ዳይሬክተሩ።በአዊ ዞን በጓንጓ ዙሪያ ወረዳ በ18 ቀበሌዎቸ ቁጥራቸው ወደ 14 ሺህ 586 ያህል ተፈናቃዮች ይገኛሉ ብለዋል አቶ ይትባረክ።በቻግኒ ከተማ ራንች የመጠሊያ ጣቢያ 16 ሺህ 204 ይገኛሉ ያሉ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎች በህብረተሰቡ ድጋፍ ከነዋሪዎች ጋር የሚኖሩትን ጨምሮ በአጠቃላይ በአዊ ዞን ወደ 47 ሺህ 400 ተፈናቃዮች ይገኛሉ ብለዋል።

ስንዴ፣ የስንዴ ዱቄት፣ በቆሎ፣ አልሚ ምግብ እና የቤት ቁሳቁስ ለተፈናቃዮች እየተከፋፈለ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።የሰብአዊ ድጋፉ በቂ ነው ባይባልም ከአደጋ ስጋት እና አመራር ኮሚሽን በጋር በመሆን ከስር ስር እያከፋፈልን ነው ብለዋል።በአካባቢው እየተደረገ ያለው ኦፕሬሽን ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀ በኋላ የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ ይሰራል ብለዋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት ከቀናት በፊት እራሱን በእሳት አቃጥሎ የገደለውን አካል ጉዳተኛ ጉዳይ በአንክሮ እንዲከታተል የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ፌደሬሽን አሳሰበ።

ፌዴራሽኑ እንዳስታወቀው ከቀናት በፊት ተማሪ አብርሃም ዱሬሳ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከዲላ ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት ቤት ያገኘ ሲሆን ህይወቱ እስካለፈችበት ቀን ድረስ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል አንዱ ነበር። የመውጫ ፈተናውን ማክሰኞ፣ ረቡዕ እና ሀሙስ በሰላም ተፈትኖ የመጨረሻው የፈተና ዕለት ማለትም አርብ የመፈተኛ ኮዱን ረስቶ ወደ ስድስት ኪሎ ግቢ መሄዱን ፌደሬሽኑ ገልጿል።

ካለ መፈተኛ ኮዱ መግባት ስለማይችል ወደ ቤቱ ሽሮ ሜዳ ተመልሶ የመፈተኛ ኮዱን ይዞ ሲመጣ የመፈተኛ ሰዓት አልፏል ይባላል።ፈተናው ከጠዋቱ 3፡30 የሚጀመር ሲሆን አብርሃም ግን አስር ደቂቃ ዘግይቶ 3፡40 ይደርሳል። ሱፐርቫይዘሩ መግባት እንደማይችል ሲነግረው ስላረፈደበት ምክንያት ሊያስረዳ ይሞክራል።

ተማሪ አብርሃም ዱሬሳም በተለያየ መንገድ ይማፀናል። አይነ_ስውር መሆኑን ታሳቢ አድርገው እንዲተባበሩት ቢለምንም ፈተናውን እንዲወስድ ግን እንዳልተፈቀደለት ተገልጿል።

ፈተናውን መፈተን ባለመቻሉ ሲያለቅስ ። ሲበሳጭ ይውላል። ምሽት ላይ ወደ ቤቱ በመግባትም ቤቱን ዘግቶ በራሱ ላይ ጋዝ አርከፍክፎ ከፍተኛ ቃጠሎ እንደደረሰበትና በኋላም ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ተወስዶ ህክምና ቢያገኝም ቃጠሎው ከፍተኛ ስለነበር ህይወቱ ማለፉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በመሆኑም በተማሪ አብርሃም ዱሬሳ ላይ የተፈጸመዉ ድርጊት ሰብአዊነት የጎደለዉ መሆኑን በመሆኑ መንግስት ክትትል አድርጎ እርምጃ እንዲወስድ ፌዴሬሽኑ ጠይቋል።በኢትዮጵያ ከ17 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአካል ጉዳተኞች እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ሪፖርትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ክስተት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሲመረምር መቆየቱን ገልጿል።

ሪፖርቱ ከሰኔ 22 አስከ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ባሉ ቀናት ውስጥ የተፈጠሩ ቀውሶችን አስመልክቶ ምርመራ ማካሄዱንም ገልጿል።

ሪፖርቱ 59 ገጽ የያዘ የምርመራ ሪፖርት ሲሆን ነገ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን በተገኙበት በአዲስ አበባ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ኮሚሽኑ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አጠቃላይ የሀብት መጠኑን በ56 በመቶ በማሳደግ 31.8 ቢሊዮን ብር ማድረሱንና በ2012 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 781 ሚሊዮን ብር እንዳተረፈ አስታወቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ «ዐብይ አህመድ በቀጣይ ምርጫ በድጋሜ ይመረጣል» ሲል ተንብዩዋል!

የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ ስለ ቀጣዩ የፈረንጆቹ አዲስ አመት (2021) ትንበያውን ዛሬ በድህረገፁ አውጥቷል፡፡

ካስቀመጣቸው ትንበያዎችም አንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) «በአዲሱ የፈረንጆቹ አመት የሚደረገውን ስድስተኛው ሀገረ አቀፍ ምርጫን ያሸንፋል፡፡ ነገር ግን ቀላል አይደለም» የሚል ነው፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክኒያት ምርጫው መደረግ ከነበረበት ጊዜ መገፋቱ ከህወሐት ጋር ቅራኔ ውስጥ እንዲገባ አድርጎት ነበር ይላል ትንበያው የተካተተበት ዘገባ፡፡

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ለነገ የጠራውን ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሰረዘ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡ጋዜጣዊ መግለጫው የተሰረዘው፣ ሆቴሉ ያለ ፖሊስ ፍቃድ አዳራሽ እንዳያከራይ ስለተከለከለ እና ፖሊስ ደሞ ፍቃድ ሰጭው የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ነው በማለቱ እንደሆነ ፓርቲው ገልጧል፡፡ ለጋዜጣዊ መግለጫ የማንም ፍቃድ እንደማያስፈልግ የጠቀሰው ፓርቲው፣ የፖሊስ ድርጊት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የሚያፍን ነው ብሏል፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫው የታሰበው፣ ምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ሰርዣለሁ ማለቱን በማስመልከት እንደነበርም ፓርቲው አመልክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ግብፅን በተመለከተ ኃላፊነት የጎደለው አስተያየት ሰጥተዋል ለሚለው የግብፅ ውንጀላ ምላሽ ሰጥተዋል።

“እኔ ቀጣናውን የሚረብሹ፤ ኢትዮጵያና ጎረቤቶቿን ማበጣበጥ የሚፈልጉ አካላት አሉ አልኩ እንጂ እከሌ ነው የሚል የሀገር ስም አልጠራሁም” ሲሉ ለአል ዐይን ኒውስ ተናግረዋል፡፡

“በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች አካባቢውን ማተራመስ በሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች ጭምር የተቀነባበሩ ናቸው ያሉት አምባሳደር ዲና እነዚህ አካላት በሱዳን ቢከሽፍባቸው በሌላ ቦታ ሊጀምሩ ይችላሉ” የሚል አስተያየት የሰጡ ቢሆንም ይህንን የሚያደርጉትን አካላት ወይም ሀገር ስም ግን አልጠቀሱም፡፡ “የኢትዮ-ሱዳንን ግንኙነት እንንከባከባለን ፤ ቁማር የሚጫወቱትን ማጋለጥ እንፈልጋለን ፤ ለነዚህ ሰዎች ዕድል አንሰጥም” ያሉት አምባሳደር ዲና “የአፍሪካ ቀንድና ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ እንዲተራመስ የሚፈልጉ አካላት አሉ ነው ያልነው ፣ ነገር ግን ሌባ እናት ልጇን ስለማታምን ይህንን የምናደርገው እኛ ነን ካሉ ምንም ማድረግ አንችልም” ብለዋል፡፡

Via Al-ain
@YeneTube @FikerAssefa
በዲላ ከተማ በሚገኘው ሰላም ሆስፒታል ዛሬ በተካሄደ ቀዶ ሕክምና ከአንዲት እናት 26 ኪሎግራም የሚመዝን ዕጢ የወጣላቸው መሆኑን የሆስፒታሉ ሐኪም አስታውቀዋል።

ቀዶ ሕክምና ያደረጉት የሆስፒታሉ ሐኪም ዶክተር ጌታቸው መርጊያ የ40 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እኚሁ እናት ሆዴ አብጧል ብለው ወደ ጤና ተቋሙ መምጣታቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።ምርመራ ሲካሄድም ከማሕጸን ተነስቶ ሁሉንም የሆዳቸውን አካባቢ የሸፈነ ዕጢ መሆኑ በመረጋገጡ ቀዶ ሕክምና እንደተደረገላቸው አስረድተዋል።
በቀዶ ሕክምና የወጣለቸው ዕጢ 26 ኪሎግራም የሚመዝን መሆኑን ዶክተር ጌታቸው አመልክተው መንስኤውን ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።ቀዶ ሕክምናው 30 ደቂቃ ብቻ መፍጀቱን የተናገሩት ሐኪሙ ከሕክምናው በኋላ እናቲቱ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ 888 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገለጸ!

የ‹‹ይቆጥቡ ይሸለሙ›› ፕሮግራም ከተጀመረበት ከ2004 ዓ.ም ወዲህ በየዓመቱ በአማካኝ ከ2 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት የባንኩን ጠቅላላ ሀብት 888 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የ‹‹ይቆጥቡ ይሸለሙ›› የ10ኛ ዙር የሽልማት መርሐ ግብር ላይ ለባለ ዕድለኛ ደንበኞቹ ሽልማታቸውን ባስረከቡበት ዕለት እንደገለጹት፤ ባንኩ ይህን ሽልማት ከመጀመሩ በፊት የነበረው ጠቅላላ ሀብት 74 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሲሆን፤ ሽልማቱን በጀመረ በአስር ዓመት ውስጥ 888 ቢሊዮን ብር መድረስ ችሏል ብለዋል።

እንዲሁም ከአስር ዓመት በፊት 2 ነጥብ 2 የነበረውን የቁጠባ ሂሳብ ብዛት ከ26 ሚሊዮን በላይ በማሳደግ 56 ቢሊዮን ብር የነበረውን ጠቅላላ የባንኩን ተቀማጭ ገንዘብ ወደ 670 ቢሊዮን ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።

ባንካችን የውጭና የሀገር ውስጥ ገንዘብ ለማሰባሰብ ከሚጠቀምባቸው ስልቶች መካከል አንዱ የ‹‹ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ›› እና ‹‹ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ›› ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ይህ ስልት ህብረተሰቡ የቁጠባ ባህሉን እንዲያሳድግ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል ለስድስት ዓመታት የሚቆይ ለመቀነስ ያግዛል የተባለለት ፕሮጀክት እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ። ለፕሮጀክቱ ማከናወኛ ከ745ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መያዙንና 200ሺህ ሰዎች ተጠቃሚ እንደሚያደረግ ኢፕድ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠት (Extradition) የሚደነግገው የተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አንቀጽ 44 ላይ ያላትን ተዓቅቦ አነሳች፡፡

ሀገሪቱ የኮንቬንሽኑን አንቀጽ 44 አስመልክቶ ተዓቅቦ (reservation) እንዳላት የኮንቬንሽኑ ምዕራፍ ሶስት ውስጥ የተመለከተውን የሙስና ወንጀልን ወንጀል አድርጎ መደንገግ እና ምዕራፍ አራት ዓለምአቀፍ ትብብርን አስመልክቶ እ.ኤ.አ ከ2010 አስከ 2015 ባለው ጊዜ የነበራትን አፈጻጸም ለገምጋሚ ሀገራት አቅርባ አስገምግማለች፡፡

ይህን የአፈጻጸም ግምገማ ተከትሎ ኢትዮጵያ እንድታስተካክል ተሰጥቷት ከነበሩ ምክረ ሀሳቦች አንዱ ከላይ በተጠቀሰው የኮንቬንሽኑ አንቀጽ ላይ ያላት ተዓቅቦ ነበር፡፡ በመሆኑም በዚህ ግምገማ መሠረት ሀገሪቱ አንቀጽ 44 ላይ የነበራትን ተዓቅቦ ያነሳች ሲሆን የፕሮቶኮሉን ድንጋጌዎች በሙሉ በማክበር ግዴታዎቿን እንደምትወጣ አረጋግጣለች፡፡

አንቀጽ 44 ላይ ያላት ተዓቅቦ መነሳቱን መቀመጫውን ኦስትሪያ ቪየና ላደረገው የተባበሩት መንግሥታት የአደገኛ ዕፅ እና ወንጀል መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት (UNODC) አስታውቃለች፡፡

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አባል ሀገር በመሆን በኮንቬንሽኑ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ለመተግበር በመስማማት በፊርማዋ አጽድቃ በህግ አውጭ ፓርላማዋ በአዋጅ ቁጥር 544/1999 ኮንቬንሽኑን በማጽደቅና የሀገሪቱ የህግ አካል በማድረግ ኮንቬንሽኑን ከሚተገብሩ ሀገራት መካከል እንደምትጠቀስ ከፌዴራል ስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የዲክኒል - ዳጉር መንገድን ከ43 ሚሊየን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ!

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የዲክኒል - ዳጉር መንገድን ከ43 ሚሊየን ዶላር በላይ የኮንትራት ዋጋ የዲዛይንና የግንባታ ስራ ለማከናወን ከጂቡቲ ወደቦች ኮሪደር ጋር ተፈራረመ፡፡የኮንትራት ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እና የጂቡቲ ወደቦች ኮሪደር ዋና ዳይሬክተር አብዲ ኢብራሂም ፋራህ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

የዲክኒል - ዳጉር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 80 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው ተብሏል፡፡35 ኪሎ ሜትሩ በአስፓልት ኮንክሪት ሲሸፈን ቀሪው 45 ኪሎ ሜትር ደግሞ የጠጠር መንገድ ጥገና መሆኑ ተገልጿል፡፡ከኢትዮ-ጂቡቲ ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ወደ ጂቡቲ ገባ ብሎ የሚጀምረው ይህ የመንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት የግንባታ ስራው በስምንት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ፡፡

(ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን)
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ላይ መግለጫ እየሰጠ ነው!

ከሰኔ 22/ 2012 የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተከስተዋል።40 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል፣ በሽዎች ተፈናቅለዋል።35 ሰዎች የተገደሉት በሁከቱ ላይ በተሳተፉ ሰዎች ነው የተገደሉት ሲል ኮሚሽኑ አስታውቋል።አጥቂዎች ሰዎች እና ቡድኖች የሰዎችን ቤት ሰብረው በመግባት አቃጥለዋል፣ ደብድበዋል፣ አርደዋል፣ እንዲሁም አስከሬኖችን በአደባባይ ላይ እንዲሆን በማድረግ ለሰዓታት እንዳይቀበር አድርገዋል ተብሏል።በህይወት እና ንብረታቸው ላይ ባጋጠመ ጥቃት ከ6000 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጠሩ ችግሮች የታዩ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ መገለጫ እየሰጠ ነው።

የሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተከሰተ ሁከት ጥቃቱ ያነጣጠረው በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ እንደሆነ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። በወቅቱ ጥቃት ሲደርስባቸው ለህግ አካላት ነዋሪዎች ቢያስታውቁም አወንታዊ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው እና የክልሉ መንግስት ችግሩን ለመቆጣጠር ዝግጁነት እንዳልነበረውም በመግለጫው ተጠቅሷል።

ከአማራ ብሔር ተወላጆች ባለፈም በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይም ጥቃት እንደተሰነዘረ ኮሚሽኑ በመግለጫው አካቷል።

አጠቃላይ በቀወሱ 123 ሰዎች ሲሞቱ በ500 ሰዎች ላይ ደግሞ አካላዊ ጉዳት አንደደረሰባቸው መግለጫው ያስረዳል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሊያጋጥም የሚችልበት አመላካች ነገሮችን በጥናታችን ለማግኘት ችለናል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር እርምጃ የታጠቁ ሃይሎች እጃቸውን እየሰጡ ነው ተባለ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር እርምጃ በርካታ የታጠቁ ሃይሎች እጃቸውን ለጸጥታ ሃይሉ እየሰጡ መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል አስታወቀ።የህግ ማስከበርና የፀጥታውን ዘርፍ በበላይነት የሚመሩት ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ የጥፋት ቡድኑ በመተከል ዞን በተለይም ቡለንና በቆጂ ወረዳዎች ዜጎችን በመግደል፣ ንብረት የመዝረፍና የማቃጠል አረመኔያዊ ተግባር መፈፀሙን አስታውሰዋል።የተጠናከረ ዘመቻ በማካሄድ በአካባቢው ህግ በማስከበር ሰላምን ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት በርካታ የታጠቁ ሃይሎች እጃቸውን እየሰጡ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ታጣቂ ቡድኑ ቀደም ሲል የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ስጋት አድሮባቸው መኖሪያቸውን ለቀው የነበሩ ዜጎችም ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን ሌተናል ጀኔራል አስራት ገልጸዋል።ግብረ ሃይሉ አካባቢውን ከተረከበ በኋላ በተለይ ስጋት ተፈጥሮባቸው የነበሩ አካባቢዎችን በማረጋጋት ወደ ተሻለ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል።በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪና የኮማንድ ፖስቱ የፖለቲካና ህዝባዊ ውይይቶች መሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በዜጎች ላይ ጥቃት የፈፀመውን ታጣቂ ቡድን የማደን ስራ መቀጠሉን ገልጸዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
አደገኛ ዕፅ የማዘዋወር ወንጀል የፈፀመው ናይጄሪያዊ በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ::

ናይጄሪያዊ ስምኦን እኬቾኩን በፈፀመው ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ ማዘዋወር ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን የእስራት እና የገንዘብ መቀጮ የፍርድ ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡ግለሰቡ ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ.ም መነሻውን ብራዚል ሳኦፖሎ በማድረግ ወደ ናይጄሪያ ሌጎስ ከተማ በአውሮፕላን ለመሄድ ለትራዚት
አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ባረፈበት ወቅት በተደረገ ፍተሻ ተጠርጥሮ የተያዘ መሆኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሆስፒታል በተደረገበት አካላዊ የራጅ ምርመራ እንዳይዘዋወር እና በጥቅም ላይ እንዳይውል የተከለከለውን 41 ጥቅል (992.29 ግራም) ኮኬይን የተባለ አደገኛ እፅ ውጦ መገኘቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም በፈፀመው መርዛማ ወይም የናርኮቲክና ሣይኮትሮፒክ እፆችን ማዘዋወር ወንጀል በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት መቅረቡ የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡ጉዳዩ የደረሰው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ግለሰቡን ጥፋተኛ ብሎታል፡፡የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኋላ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በ3 ዓመት ፅኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር እንዲቀጣ መወሰኑን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ማረሚያ ቤት ከሁለት ዓመታት በላይ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ተጠርጣሪዎች ተገኝተዋል ተባለ!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማረሚያ ቤት ባደረገው ጉብኝት ከሁለት ዓመታት በላይ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ተጠርጣሪዎችን አገኘ።

ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው ታይቶ በሶስት ቀናት ውስጥ እልባት እንዲሰጣቸውም ግብረ ሃይሉ አሳስቧል።

ግብረ ሃይሉ በማረሚያ ቤት ባደረገው ጉብኝት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በነበረ የፀጥታ ችግር በወንጀል ተጠርጥረው እስካሁን ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ተጠርጣሪዎችን አግኝቷል።

ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከሁለት ዓመት በላይ በማረሚያ ቤት መቆየታቸውንም አረጋግጧል።

በግብረ ኃይሉ የህግ ማስከበርና የፀጥታውን ዘርፍ በበላይነት የሚመሩት ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከሁለት ዓመታት በላይ መታሰራቸው ከህግ አግባብ ውጪ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ከፌደራል ዐቃቤ ህግ መርማሪ ቡድን ጋር ስራውን የሚመራ ኮሜቴ ተቋቁሞ በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ውስጥ ለማጠናቀቅ እያጣራ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በርካታ የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መማረካቻውን እና መደምሰሳቸው ተገለጸ!

በርካታ የ'ጁንታው' ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መማረካቻውን እና መደምሰሳቸውን የመከላከያ ኃይል ሥምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው አረጋገጡ።በውጭ የሚገኙ የጁንታው ሚዲያዎች የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ቢያናፍሱም የመከላከያ ኃይልና የፌዴራል ፖሊስ በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ በርካቶች መማረካቸውን ገልጸዋል።እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑትም ተደምስሰዋል ብለዋል።የተቀሩት በየእምነት ተቋማትና ገዳማት፣ ዋሻና ሸለቆዎች እራሳቸውን ደብቀው እንደሚገኙ መረጃ እንዳላቸው የገለፁት ጄኔራል ተስፋዬ፣ 'ጁንታው' የሞቱበትን ከፍተኛ አመራሮቹን ከሰብአዊ ርህረሄ ውጭ በሆነ መልኩ እንዳይታወቁ አንገታቸውን ቆርጦ ለየብቻ ስለሚቀብራቸው ለመለየት አዳጋች መሆኑን ተናግረዋል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
ምሥራቅ ጎጃም ደብረ ማርቆስ ከተማ ዉስጥ በልማዱ «ጉልት ገበያ» ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ በርካታ መደብሮችን አጋየ።

የደብረ ማርቆስ ፖሊስ እንዳስታወቀዉ እሳቱ 23 የኮንቴኔር (የብረት ሰንዱቅ) ሱቆችና በረንዳዎችን አጋይቷል።የከተማይቱ ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር አጃናዉ አዲስ ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት እሳቱ የተነሳበት ምክንያት ገና እየተጣራ ነዉ።ይሁንና በየሱቆቹ የነበሩ ተቀጣጣይ ሸቀጦች እሳቱን በፍጥነት በማዛመታቸዉ ባጭር ጊዜ ዉስጥ ያጠፋዉን ያክል ንብረት ለማጥፋት ሰበብ ሆኗል።ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ግድም የተነሳዉ ቃጠሎ በሰዉ ሕይወትና አካል ላይ ያደረሰዉ ጉዳት የለም።ቃጠሎዉ የከተማይቱን ሆስፒታል ጎድቷል የሚል ዘገባ ቢሰራጨም የፖሊስ አዛዡ «ከእዉነት የራቀ» ብለዉታል።ዶይቸ ቨለ እንደዘገበው ባለፈዉ ሳምንት በባሕር ዳር ከተማ “ጉዶ ባሕር” በተባለው አካባቢ 50 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለው ከ200 በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ማስታወቂያ❗️

የሚሸጥ መሬት

አድራሻ ደሴ
500+ ካሬ
አስፓልት ፊት ለፊት ያለ መሬት
ዋጋ 10,000,000ዋጋ ድርድር አለው
ፈላጊ በ +251904187518
+251955352406


ትክክለኛ ገዢ ብቻ ያናግረኝ @shebab41