YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሀገር ልጅ፣ የማር እጅ’ በሚል የድጋፍ ጥሪ በቀጣይ ሳምንት ኅዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ለትግራይ ሕዝብ ድጋፍ ማሰባሰብ ሊካሄድ ነው።

ጥበብብ ለሀገር በሚል በተዋቀረ የአርቲስቶች ኮሚቴ አዘጋጅነት የሚካሄደው ድጋፍ ማሰባሰብ መርሐ ግብር በመላ ሀገሪቱ የሚከናወን መሆኑ ታውቋል።በመርሐ ግብሩ ላይ አንጋፋ እና ወጣት አርቲስቶች የሚሳተፉ መሆኑንም ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።ሕግ የማስከበር እርምጃ እየተወሰደ ባለበት የትግራይ ክልል ለሕዝቡ የምግብ፣ አልባሳት እና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለመሰብሰብ መታቀዱም ተገልጿል።በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ ትልልቅ የግል እና የመንግሥት ተቋማት፣ ከአትሌቶች እና ከፋብሪካዎች ድጋፍ ለማሰባሰብ መታሰቡ ተጠቁሟል።

[አሐዱ ሬዲዮ 94.3]
@YeneTube @FikerAssefa
በአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቆመ!

በመሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እየፈጸመ በመሸሽ ላይ የሚገኘው የሕወሓት ህገወጥ ቡድን በአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተጠቆመ።

የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው የአክሱም ከተማ የተገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ በ526 ሚሊዮን 860 ሺህ 200 ብር ወጪ የተገነባ መሆኑን፣ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለአገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ሰፊ እንደነበር ተገልጿል።

የአየር ማረፊያው መጎዳት የአክሱም ሐውልትን ከጉዳት ለመታደግ የሚደረገውን የጥገና ስራ እንደሚያስተጓጉልና በርካታ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቁሟል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት 15 ቀናት ውስጥ ከ93 በላይ ሰዎችን የህወሀት እና ኦነግ ሸኔ የጥፋት ተልዕኮ ይዘው ሲንቀሳቀሱ በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ጦርነቱን አዲስ አበባ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሳለን ብሎ ሀገር የመናድ ጦርነት የለኮሰው ወንበዴው፣ አሸባሪውና የማፊያዎች ስብስብ የሆነው የህወሀት ጁንታ ቡድን ከዕለት ዕለት ወታደራዊ ሽንፈትና ክሽፈት እየተከናነበ ይገኛል ብሏል።ጽንፈኛው ቡድን በከፈተው በዚህ ባልተጠበቀ ጥቃት እንደመከላከያ ሰራዊታችን ሁሉ በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ22 በላይ የልማት አውታሮችን ከየትኛውም ጥቃት ሲጠብቁ አመታትን ባስቆጠሩ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ አባላት መኖሪያ ካምፖች ላይ ጥቃት በማድረስ በርካታ አባላት ላይ የግድያና የአፈና ወንጀል መፈጸሙን የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጄይላን አብዲ ተናግረዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት በከፍተኛ ቁጭትና ወኔ በመነሳሳት በመሃል ሀገር ያለውን የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ለማድረግ ቀን ከሌት በትጋት ሙያዊ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።

ይህ የጥፋት ቡድን አባላትና ተላላኪዎቻቸው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፣ በቦሌና በየክልሉ በሚገኙ ኤርፖርቶች፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በሀይል ሰብስቴሽኖች፣ በውሃ ግድቦች፣ በነዳጅ ዲፖዎች፣ በፋብሪካዎች፣ በድልድዮች፣ በስደተኛ ካምፖች፣ በሳተላይት ጣቢያዎች፣ በማዕድን ማውጫዎች፣ በቤተመንግስትና በክልል ም/ቤቶች፣ በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች፣ በልማት ድርጅቶች፣ በዋና ዋና የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች፣ በምድር ባቡር ፕሮጀክቶች፣ በቢሮዎችና መኖሪያ ካምፖች፣ በፌዴራል ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች እንዲሁም ሌሎች የልማት አውታሮችና ጠረፍና የጠረፍ ከተሞች ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉትን ጥቃቶች አስቀድሞ ለማክሸፍ ጥብቅ ክትትልና ቋሚ ጥበቃ በማድረግ ላይ ይገኛሉም ብሏል፡፡

ከዚህም ባለፈ በግዳጅ የነበሩት የፌዴራል ፖሊስ አባላት የከሃዲው ህወሀት ቡድንን ጥቃት በመከላከል በአንዳንድ ግንባሮች ከጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሆን በግንባር እየተፋለሙ ይገኛሉም ተብሏል።

ሌሎች ደግሞ በሰሜን ቀጠና፣ በምዕራብ ቀጠና በኦሮሚያ ወለጋ ዞኖች፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና መተከል ዞን እና አካባቢው፣ በደቡብ ቀጠና በሚዛን ቴፒ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በወላይታ ሶዶ እና ኮንሶ፣ ከነገሌ ቦረና እስከ ሞያሌ፣ በምስራቅ ቀጠና ከአዋሽ እስከ ጋላፊ እንዲሁም በሁሉም የሀገራችን ድንበሮች ከክልሎች የፀጥታ ሀይልና በየቦታው ካለው የመከላከያ ሰራዊታችን ጋር ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠርና የህዝብን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ የህግ የበላይነት እንዲከበር ሌት ተቀን በትጋት እየሰሩ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ከተለያዩ ክልሎች ፖሊስ በዚህ ወንጀል የጠረጠራቸውን ከ93 በላይ የህወሀት ቡድን አባላትና የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላትን በህግ ቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሆነ ተገልጿል።

በተደረገ ብርበራ፣ ፍተሻና አሰሳ እንዲሁም በህብረተሰቡ ጥቆማ፡- 30 የመከላከያና የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ 47 የተለያዩ ጠመንጃዎች፣ 43 የተለያዩ ሽጉጦች፣ 1 ሺህ 376 የተለያዩ ጥይቶች ፣ 7 ቦምቦች፣ 2 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 102 ድምፅ አልባ መሳሪያ፣ 8 የእጅ ራዲዮ መገናኛ፣ ለእኩይ ተግባራቸው ማስፈፀሚያ የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ የቴሌኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎች፣ 534 ሺህ 870 የኢትዮጵያ ብር እና የተለያዩ ተሸከርካሪዎች መያዝ ተችሏል፡፡

ይህ የተገኘው ውጤት ሰላም ወዳዱ የሀገሪቱ ዜጋ እና በየክልሉ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ከፖሊስ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በመስራታቸው የተገኘ ስኬት በመሆኑ ይህንኑ ትብብሩን አጠናክሮ በመቀጠል ለሰላምና ደህንነታችን መረጋገጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት እያሳሰብን በቀጣይ ለሚደረጉ የህግ ማስከበር ተግባራት የተለመደውን ድጋፍና ትብብራችሁን እንጠይቃለን ብሏል፡፡አጠራጣሪ ነገሮች ሲኖሩ መረጃ ለመስጠት በስልክ ቁጥሮች፦
987፣ 816 እንዲሁም በ0115-51 80 00 ደውላችሁ አሳውቁኝ ተብላችኋል።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ ላለመሳተፍ ወሰነች!

ሱዳን ሚኒስትሮች በህዳሴው ግድብ ላይ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንደማትሳተፍ ገልጻለች፤ የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ሚና ድርድሩን እንዲያመቻቹም እንዲሆን ጠይቃለች፡፡የሱዳን መስኖና የውሃ ሃብት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ካርቱም በፊት በነበረው አካሄድ በሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እንደማትሳተፍ ወስናለች፡፡ሱዳን ከዚህ አቋም ላይ የደረሰችው የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል እንደ አመቻች ሆነው እንዲያገለግሉ ትፈልጋለች፤ለዚህ ያቀበቸው ምክንያት ያለፉት የድርድር ዙሮች ጥቅም የሌላቸው ሆነው በማግኘቷ መሆኑን ገልጻለች፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 473 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፣ 209 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 589 የላቦራቶሪ ምርመራ 473 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ሺህ 352 ደርሷል።በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት ከበሽታው ያገገሙ 209 ሰዎች ጨምሮ በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 65 ሺህ 534 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 636 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬለ ማስጠንቀቂያ አለመስጠቱን ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ አረጋግጠዋል ሲል ራሱ ዶይቼ ቬለ ዘገበ።

ዋና ዳይሬክተሩ በዶይቼ ቬለ ዘገባዎች ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አሉት ያሏቸውን ቅሬታዎች ግን በዝርዝር አስረድተዋል።ባለሥልጣኑ የሬውተርስ የአዲስ አበባ ዘጋቢን ፈቃድ ሰረዘ፤ ለዶይቼ ቬለ እና ለቢቢሲ ራዲዮ ጣቢያዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ የሚል መረጃ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተሰራጭቶ ነበር። መረጃው የተሰራጨው የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ለሸገር ራዲዮ ጣቢያ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ መሠረት በማድረግ ነው።

"ለዶይቼ ቬለ የሰጠንው ማስጠንቀቀያ የለም። ምን አልባት ቢሯችን ጠርተን ያደረግንው ምክክር እንደዚያ ተደርጎ ተገልጾ ከነበረ ስህተት ነው። የጽሁፍም ሆነ የቃል ማስጠንቀቂያ የሚባል ነገር ግን ለዶይቼ ቬለ የሰጠንው የለም" ያሉት ዶክተር ጌታቸው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በዘገባዎች ላይ ቅሬታዎች እንዳሉት አስረድተዋል።"ወደ አንድ ወገን ማጋደላችሁ ይኼ ነው ሊባል የሚችል አይደለም። በብዙ ቅሬታ አቅራቢዎች ጭምር የተደገፈ ነው።እኛም ደግሞ በሙያዊ ትንታኔ ያንን አይተን ያንን ቅሬታችንን የምናቀርብ ይሆናል። በዚህ አይነት ከቀጠለ ሌሎቹን ተጠያቂ እንዳደረግንው ሁሉ ዶይቼ ቬለ በዚያ መልኩ አይጠየቅም ማለት አይቻልም" ሲሉ ተቋማቸው ያለውን ቅሬታ ዶክተር ጌታቸው አስረድተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ በሚል የተጠረጠሩ 93 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ።

የህወሓት ቡድን በትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ጥቃት እንዳይፈፀም ጠበቅ ያለ ጥበቃ እየደረገ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተናገሯል።በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ በኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫዎችና ሰብስቴሽኖች፣ በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ጥበቃው መጠናከሩን ኮሚሽኑ በመግለጫው ተነግሯል።በቦሌና በየክልሉ በሚገኙ ኤርፖርቶች፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በውሃ ግድቦች፣ በነዳጅ ዲፖዎች፣ ፋብሪካዎችና ድልድዮችም ፣በስደተኛ ካምፖች፣ በሳተላይት ጣቢያዎች ፣ በማዕድን ማውጫዎች እንዲሁም በሌሎች ተቋማትና ፕሮጀክቶች ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉትን ጥቃቶች አስቀድሞ ለማክሸፍ ጥብቅ ክትትልና ቋሚ ጥበቃ እየተደረገ መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ከዚሁ ከፍተኛ ጥበቃና ቁጥጥር ጋር በተያያዘ በወንጀል የጠረጠሩ 93 የህወሃትና የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።በተደረገ ፍተሻና አሰሳ እንዲሁም በህብረተሰቡ ጥቆማም 30 የመከላከያና የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ 47 የተለያዩ ጠመንጃዎች፣ 43 የተለያዩ ሽጉጦች፣ 1 ሺ 376 የተለያዩ ጥይቶች ፣ 7 ቦምቦች፣ 2 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 102 ድምፅ አልባ መሳሪያዎች መያዛቸውን ሰምተናል።በተጨማሪም 8 የእጅ ራዲዮ መገናኛ፣ የተለያዩ የቴሌኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎች፣ 534,870 ብር እና የተለያዩ ተሸከርካሪዎች መያዛቸው ተነግሯል።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ፍቅር...

👉ለመላው የቴዎድሮስ ካስሁን(ቴዲ አፍሮ) አድናቂዎች "ወደ ፍቅር" የተሰኘው ማህበራችን በየ 3 ወር ልዩነት የደም ልገሳ መርሀ ግብር እንዳለው ይታወቃል ስለሆነም በመጪው እሁድ #ህዳር_13 #በብሔራዊ_የደም_ባንክ አገልግሎት ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው ቅጥር ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ 03:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራማችን ይጀምራል ስለሆነም መላው #የቴዲ_አፍሮ ወዳጆች በዚህ ቀን ህይወት ለማዳን ተጋብዛችኋል።

👉ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉት ስልክ ቁጥሮች መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
0947646445/0913668491

💚💛ፍቅር ያሸንፋል!!!
በትግራይ የተከፈቱ የትኛውም የባንክ አካውንቶች ለጊዜው መንቀሳቀስ አንዳይችሉ ብሔራዊ ባንክ አዟል!

አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ አንደዘገበው በትግራይ የተከፈቱ የትኛውም የባንክ አካውንቶች ለጊዜው መንቀሳቀስ አንዳይችሉ ብሔራዊ ባንክ አዟል።በዚህም መሰረት ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ገንዘብ ማውጣት አይችሉም።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በከተማ ደረጃ 49 ኪ.ሜ ርዝመት ያላቸው 5 አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት በይፋ አሰጀምሯል።

የፕሮጀክቶቹ ማስጀመሪያ ላይ፣ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና አፈጉባኤ ወ/ሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ እንዲሁም የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የካቢኔ አባላት ተገኝተዋል።ዛሬ ከተጀመሩት ፕሮጀክቶች መካከል 4ቱ በኮዬ ፈጬ እና ቱሉዲምቱ የጋራ መኖሪያ ውስጥ የሚገነባ ሲሆን ሌላው ከሲኤምሲ ወደ ጎሮ የሚወስድ የመንገድ ፕሮጀክት ነው።የመንገድ ፕሮጀክቶቹ በ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ 49 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ እና ከ15 እስከ 40 ሜትር የጎን ስፋት ያላቸው መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሞገስ ጥበቡ ገልጸዋል።ፕሮጀክቶቹ በአንድ ዓመት ከ7 ወር እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው ሥራ እንደሚጀምሩ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአንድ ሳምንት ብቻ 51 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ከዚህ ውስጥ ከ31 ሚየን ብር በላይ የሚገመተው ወደ ሀገር ሲገባ ሲሆን ከ20 ሚሊየን  ብር በላይ የሚሆነው ደግሞ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር ነው ተብሏል፡፡በቁጥጥር ስር የዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የቁም እንስሳት፣ የምግብ ምርቶች፣ ጌጣጌጥ፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እና አደንዛዥ ዕፅ ይገኙበታል፡፡በከፍተኛ መጠን ከተያዙ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ በሞያሌ ቅርንጫፍ ስር በሚገኙ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ነጌሌ ቦረና፣ ቡሌሆራ መስመር አድንዛዥ ዕፅ፣ በሀዋሳ ቅርንጫፍ ስር በሚገኙ ጢጢቻ፣ ጪጩ፣ ኮንሶ፣አዳባ፣ ዲላ መስመር ዘጠኝ ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ስጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ ናቸው፡፡

እንዲሁም በሞያሌ ቅርንጫፍ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ የምግብ ምርቶች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ እንዲሁም በድሬደዋ ቅርንጫፍ ሀረር፤ ድሬደዋ፣ ለጋር፣ ቢዮቆቤና ደወሌ መስመር ከ3 ሚሊየን ብር በላይ  የሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡እንዲሁም በባህርዳር ቅርንጫፍ ሰራቫ፣ ሻውራ፣ መተማ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች 30 የብሬይን ጥይት፣ 166 የክላሽ ጥይት፣ 2 ሺህ 771 የአሜሪካን ዶለር በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን ከገቢዎች ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከነገ የሚጀምር ከከባድ ተሽከርካሪዎች የከተማ ውስጥ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የሰዓት ገደብ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ የሰዓት ገደቡን ያሳለፈው በአስተዳደሩ እየተከሰተ ካለው የትራፊክ መጨናነቅና በዚህም ሳቢያ እየተፈጠረ ያለውን የመንገዶች መዘጋትና መጉላላት ለመቀነስና ለማስቀረት አስቦ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

ገደቡ ከነገ ጀምሮ ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስን ያግዳል ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ይሁን በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የፈቀደው ከምሽት 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና!!

የመከላከያ ሠራዊት ከአዲግራት ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ ከተማን ተቆጣጥሯል። የመከላከያ ሠራዊቱ የዘመቻው የመጨረሻ ግብ የሆነችውን መቀሌን ለመያዝ እየገሠገሠ ነው።

[የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ]
@YeneTube @FikerAssefa
“መቀሌን በታንክ ለመክበብ ከሚያስችል ውጊያ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን”-መከላከያ

በተለያዩ ግንባሮች ከህወሓት ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት ጋር እየተዋጋ ወደ መቀሌ እየገሰገሰ ያለው የመከላከያ ሰራዊት በራያ ግምባር ከከተማዋ በ70 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

ትናንት ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ በራያ ግንባር የሚደረገው ዘመቻ ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል ያሉት የግንባሩ የሚዲያ አስተባባሪ ኮሎኔል ደጀኔ ጸጋዬ የተራራ ውጊያዎችን ጨርሰን ቁልቁል ከምንወርድበት የውጊያ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

“ከእንግዲህ ያለው ውጊያ የታንክ ነው” ያሉት አስተባባሪው ሰራዊቱ “መቀሌን በታንክ ለመክበብ” ከሚያስችል ውጊያ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ጊዜው “መቀሌ ያለው ህዝባችን ከከባድ መሳሪያ ጥቃት ራሱን እንዲታደግ ጥሪ የሚተላለፍበት ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

እንደ አስተባባሪው ገለጻ ከሆነ “ከዚያ በኋላ ምህረት የለም”፡፡

ህብረተሰቡም በውስጡ የተደበቀውን ኃይል “የግድ ማራቅ፣ ውጣልኝ አታስጨርሰኝ” ማለት ይጠበቅበታል፡፡

“ሰራዊቱ እስካሁን ተዋጊውን የህወሓት ኃይል በመለየት እና የህዝቡን ደህንነት በመጠበቅ በጥንቃቄ ላይ የተመሰረተ ማጥቃት ነበር ሲያካሂድ የነበረው“ ያሉት ኮሎኔል ደጀኔ በመቀሌ ግን እንደዛ ሊሆን እንደማይችል አስታውቀዋል፡፡

[EBC & Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አካባቢ ዲቪዥን የሠፈራ ጣቢያ ለጥፋት አላማ ሊውል የነበረ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አካባቢ ዲቪዥን የሠፈራ ጣቢያ ለጥፋት አላማ ሊውል የነበረ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን በሰሜን እዝ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጄኔራል ሙሏለም አድማሱ አስታወቁ።
በቁጥጥር ስር የዋሉ የጦር መሳሪያዎች፦
-207 ክላሽ፣
-9 ሺህ 80 ጥይት፣
- 26 አርባ ጎራሽ፣
- 18 አስር ጎራሽ፣
- የተለያዩ ሽጉጦች ማካሮፍ 26፣
- ስታር 5፣
- fort five 4፣
- Breta 1፣ Map 2 እንዲሁም 108 የተለያዩ የቦምብ አይነቶች ናቸው። ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ የህወሀት የቀድሞ ታጋዮች እና ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች እንዲሠፍሩ ሲደረግበት በቆየው የመኖሪያ ጣቢያ በተደረገ ኦፕሬሽን ያለምንም የተኩስ ልውውጥ በልዩ ወታደራዊ ጥበብ መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴር ጄነራሉ ገልፀዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአድዋ ተምቤን መሥመር ማይቅናጥል በተባለውና ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው የሐውዜን ተምቤን መገንጥያ መንገድ የገጠመውን የህወሓት ኃይል ድል አድርጓል።በዚሁ መገንጠያ ላይ የሠራዊቱን ግሥጋሴ ለመግታት በኮሎኔል ጸጋዬ ማርክስና በኮሎኔል ሸሪፎ የሚመራው የጽንፈኛው ቡድን አንድ ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።የመከላከያ ዘመቻ ዋና መመሪያ ማምሻውን እንዳስታወቀው የመከላከያ ሠራዊታችን ክፍለ ጦሩን ሙሉ በሙሉ ከደመሰሰ በኋላ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 433 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4,495 የላብራቶሪ ምርመራ 433 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,647 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 157 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 65,691 አድርሶታል፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 105,785 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የተጀመረው ሕግን የማስከበር እርምጃ ሁለተኛ ምእራፍ መጠናቀቁ እና የ'ጁንታው' አባላት በቀጣይ 72 ሰዓታት ውስጥ እጃቸው በሰላም እንዲሰጡ ጥሪ መቅረቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

ጠ/ሚር አብይ በትግራይ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው የህግ ማስከበር ዘመቻ ሁለተኛው ምዕራፍ መጠናቀቁን አስመልክተው የሰጡት መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa