በልደታ ክ/ከተማ ተሠርቀው የተከማቹ በርካታ የመኪና እቃዎችን ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የአብነት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገለፀ፡፡
የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመኪና ዕቃ ስርቆት ወንጀልን ለመከላከል የክትትልና ኦፕሬሽን ቡድን አዋቅሮ ወደ ተግባር በመግባት ህብረተሰቡ የራሱን ንብረት በራሱ ገንዘብ እንዲገዛ የሚገደድበትን ህገ ወጥ ድርጊት ለማስቀረት እየሠራ መሆኑን አሰታውቋል፡፡በዚህ እንቅስቃሴም በክፍለ ከተማው ወረዳ 4 በተለምዶ ሱማሌ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባባቢ ከተለያዩ ክ/ከተሞች የተሠረቁ የመኪና እቃዎችን ከህብረተሰቡ በደረሠ ጥቆማና ተጨማሪ ጥናትን መሠረት በማድረግ መስከረም 6 ቀን 2013ዓ.ም በ4 ቤቶች ላይ በተካሄደ ብርበራ ተሰርቀው የተከማቹ በርካታ የመኪና ዕቃዎች ሊያዙ መቻላቸውን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ስዩም አስፍሃ ገልፀዋል፡፡
የአብነት አካባባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ዋና ሳጅን ታመነ መገርሳ በበኩላቸው በብርበራው ወቅት የመኪና ስፖኪዮ ፣ ፍሬቻ ፣ የነዳጅ ታንከር (ሰልባቲዮ) ክዳን እና ሌሎች የመኪና እቃዎች ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር ተይዘው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡አሽከርካሪዎች ተሽከርካሪያቸውን ሲያቆሙ ከእይታቸው አልያም ከጥበቃ ባልራቀ ሁኔታ ቢሆን እንደሚመረጥ እና ፖሊስም የሚያደርገው ክትትል እና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ስዩም በተለያዩ ክ/ከተሞች በተለያየ ጊዜ የመኪና ዕቃ የተሠረቀባቸው ግለሰቦች ወደ ፖሊስ መምሪያው በመምጣት ንብረታቸው ስለመኖሩ አረጋግጠው እና ለይተው መውሰድ የሚችሉ መሆኑን ማሳሰባቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
@YeneTube @FikerAssefa

አቶ ልደቱ አያሌው በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ በፍርድ ቤት ተወሰነላቸው!
የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተፈትተው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ከሰዓት ትዕዛዝ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን የሰጠው ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 12 ከሰዓት በነበረው የችሎት ውሎው ነው። ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ የተከሰሱበትን ጉዳይ ለመመልከት ለመስከረም 20 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የዛሬውን የችሎት ውሎ የተከታተሉት የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ተናግረዋል።
[ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ በእንግሊዝ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች ላይ ደጋፊዎችን ከመስከረም 21 ጀምሮ ወደ ስታዲየም የማስገባቱ እቅድ ወድቅ መደረጉ ተገለጸ።
ይህ የሆነበት ምክንያት በዩናይድ ኪንግደም እና በተቀሩበት የአውሮፓ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ መሆኑን የጠቅላይ ሚንስትሩ ካቢኔ አባል የሆኑት ማይክል ጎብ ተናግረዋል።ከዚህ ቀደም የነበረው እቅድ እስከ 1ሺህ የሚደርሱ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ገብተው ክለባቸውን እንዲደግፉ መፍቀድ ነበር።በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከሼፊልድ ዩናይትድ መስከረም 23 በሚያደርጉት ጨዋታ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየሞች ይገባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።ካለፈው መጋቢት ወር ወዲህ በእንግሊዝ የእግር ኳስ ውድድሮች በዝግ ስታዲየም ሲካሄዱ ቆይተዋል።በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት ስፓርታዊ ውድድሮች በዝግ ስታዲየም እንዲደረጉ መወሰኑ በክለቦች ላይ ከፍተኛ የፋይንስ ቀውስ አስክትሏል።
የባህል፣ ሚዲያ እና ስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ጁሊያን ናይት “ታዳሚዎች ወደ ስታዲየሞች የሚመለሱበትን ብልህ የሆኑ አሰራሮች ካልዘረጋን የስፖርት እና ባህላዊ መሠረተ ልማቶቻችን ተንኮታኩተው ይቀራሉ” ብለዋል።ከ100 በላይ የስፖርታዊ ውድድሮች አመራሮች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ካጋጠማቸው ኪሳራ ለማገገም ለጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል።ስፖርት ኢንግላንድ የተሰኘው የመንግሥት አካል 200 ሚሊዮን ፓውንድ ለአስቸኳይ ወጪ መሸፈኛ በሚል ለስፖርት ክለቦች ድጋፍ አቅርቧል። ይሁን እንጂ ይህ ገንዘብ ክለቦች ያጋጠማቸውን ኪሳራ ለመሸፈን በቂ አይደለም ተብሏል።
[BBC]

በሊባኖስ በድጋሚ ሌላ ፍንዳታ ተከሰተ!
በሊባኖስ በሂዝቦላህ የመሳሪያ መጋዘን ውስጥ ፍንዳታ ተከሰተ።በሊባኖስ በሚገኘው የሂዝቦላህ የመሳሪያ መጋዘን ዛሬ ማክሰኞ በቴክኒካዊ ስህተት ምክንያት ፍንዳታ መከሰቱን የሀገሪቱ ደህንነት ምንጭ አስታወቀ፡፡የሂዝቦላህ ጠንካራ ይዞታ በሆነው በደቡባዊ ሊባኖስ የተከሰተው ፍንዳታ አካባቢውን ያናወጠ ሲሆን በስፍራው ከፍተኛ ጭስ እየጨሰ ነው፡፡ፍንዳታው የተከሰተው ከወደብ ከተማዋ ከሲዶን ከፍ ብላ በምትገኘው በአይን ቃና ደቡባዊ መንደር ነው፡፡ፍንዳታው ስላደረሰው ጉዳት እስካሁን የወጣ መረጃ አልተገኘም፡፡
አንድ የሊባኖስ የሂዝቦላህ ባለስልጣን ፍንዳታ መኖሩን አረጋግጠው ነገር ግን ተጨማሪ ዝርዝሮችን ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡የሂዝቦላህ ቡድን አባላት ጋዜጠኞች ወደ አካባቢው እንዳይደርሱ በማገድ የፀጥታ ስራ ማከናወን ጀምረዋል፡፡በአከባቢው አል ጃዲድ ጣቢያ የተላለፈው የቪዲዮ ቀረፃ በህንፃዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ያሳያል፡፡የአሁኑ ፍንዳታ የተከሰተው በቤይሩት ወደብ በአሞኒየም ናይትሬት ክምችት ከፍተኛ ፍንዳታ ከተከሰተ ከሰባት ሳምንታት በኋላ ነው፡፡ በቤይሩቱ ፍንዳታ 200 ገደማ ሰዎች ሲሞቱ 6,500 ያህል ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል
[Alain]

👍1
53 ሕገ ወጥ ሽጉጦችና 3860 የሽጉጥ ጥይቶች በወረጃርሶ ወረዳ በቁጥጥር ስር ዋሉ!
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ 53 ሕገወጥ ሽጉጦችና 3860 የሽጉጥ ጥይቶች ባለፈው እሁድ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እያሉ በጎሃ ቀሬ ከተማ ኬላ ላይ መያዛቸውን የወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር አበባየሁ ገረመው በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩት ግለሰቦችና ሹፌር ያመለጡ በመሆናቸው እነሱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር አበባየሁ ገልጸዋል፡፡

የህጻን ጾታ ለማወቅ የሚስቱን ሆድ የቀደደው ህንዳዊ በፖሊስ ተያዘ!
በሰሜናዊ ህንድ የሚገኝ አንድ ሰው የህጻን ጾታ ለማወቅ የሚስቱን ሆድ በማጭድ ቀዶ ህጻኑ እንዲሞትና ሚስቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንድትጎዳ ካደረገ በኋላ በፖሊስ መያዙን ፖሊስና ዘመዶቿ ተናግረዋል፡፡ጉዳት የደረሰባት ሚስት በህንድ ዋና ከተማ ዴልሂ በሚገኝ ሆስፒታል ከፍተኛ እንክብካቤ እየተደረገላት መሆኑን በሰሜናዊ ኡታራ ፕራደሽ ግዛት ውስጥ ያለ ፖሊስ አስታውቋል፡፡የሚስትዮዋ ወንድም እንደተናገረው ጥቃቱ የተፈጸመው ባል የህጻን ጾታ ለማወቅ በመፈለጉ ነው ብሏል፡፡ ጥንዶቹ ከዚህ በፊት አምስት ልጆች ያፈሩ ናቸው፡፡
“በማጭድ በማጥቃት ሆዷን ቀዷል፤ ይህን ያደረገው ያልተወለደውን ህጻን ጾታ ለማወቅ መሆኑን እንደተናገረ“ የሚስት ወንድም የሆነው ጎሉ ሲንህ ለሮይተርስ ተናግሯል፡፡ፖሊስ እንደገለጸው ህፃኑ ሞቶ የተወለደ ሲሆን ይህን የፈጸመው ባል በፖሊስ ተይዞ እስር ቤት ይገኛል፡፡በህንድ ሴት ልጆች ብዙ ጊዜ እንደጫና የሚቆጠሩና በጋብቻ ጊዜ ቤተሰብ ለጥሎች የሚከፍል ሲሆን ወንዶች በአንጻሩ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንዲሁም የቤተሰብን መልካም ስም የሚያስጠሩና ሀብት የሚወርሱ ናቸው፡፡በህንድ የጽንስ ማስወረድ በህግ የተከለከለ ሲሆን የወንድ ልጆች ምርጫ መኖሩ የሴቶች ቁጥር እንዲቀንስ አድጓል፡፡

251 ኢትዮጵያዊያን ዜጎቻችን ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓም ከሳኡዲ አረቢያ ጄዳ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
ኢትዮጵያዊያኑ በሳኡዲ አረቢያ በሚገኙ እስር ቤቶች እና በተለያየ ችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።ኢትዮጵያውያኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ ሲደርሱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሚመለከታው መስሪያ ቤቶቸ የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።ባሳለፍነው ሳምንትም በሳኡዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ በተለያዩ ችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 274 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ መመለሳቸው ይታወሳል።
[FBC]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 713 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6,813 የላብራቶሪ ምርመራ 713 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ19 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1127 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 357 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 28,991 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 70,422 ደርሷል፡፡

Forwarded from Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
#ዘ_አልኬሚስት
#የስሜት_ትኩሳት
የፓውሎ ኮኤልሆ ሁለቱ ድንቅ መጽሐፍት!!
ከ150 ሚሊዮን ኮፒዎች በላይ በመሸጥ ጊነስ ቡክ ላይ ለመስፈር የበቃ፣ ከ80 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የተተረጎመ፣ 115 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን የተቀዳጀ የምንጊዜም ምርጥ መጽሐፍ የሆነው ዘ-አልኬሚስት# አማርኛው_እነሆ_ለ5ተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል!!!
“ድንቅ፣ ተዓምራዊ እና ሕይወትን የሚቀይር መጽሐፍ ነው... ባነበብኩት ቁጥር ከማስደመም ቦዝኖ አያውቅም... የሚያስገርም መጽሐፍ”
#ኒዪል_ፓትሪክ_ሃሪስ (ተዋናይ)
#የስሜት_ትኩሳት
ዘ-አልኬሚስትን ከወደዱት ደግሞ ይህን የስሜት ትኩሳትም ይወዱታል!!!
የ ”ኒው ውመን ማጋዚን” ሪቪው ባለ አራት ኮከብ ተሸላሚ መጽሐፍ ነው።
በድፍረት የተመዘዘ የዘመናችን ብዕር ውጤት . . . የራሱ የሆነ እንግዳ፣ ግን ደግሞ ውብ ኬሚስትሪ አለው።
#ዘ_ኦብዘርቨር
ጸሐፊው በተለመደው የሚያባብል ብዕሩ.... ያልተለመደውን ርዕስ አሽሞንሙኖታል።
#ግላስኮ_ኢቭኒንግ_ታይምስ
#አሁን_ሁለቱም_መጽሐፍት
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ፡፡
ሁለቱንም ያንብቧቸው እጅግ ይወዷቸዋል!!!
ይቀላቀሉን http://tttttt.me/teklutilahun

#መከረኞች
#እምዩ
ዘመን የማይሽራቸው መጽሐፍት በገበያ ላይ!!
#መከረኞች በአንድ ፊቱ የህብረተሰብ ታሪክ፣ በሌላ ፊቱ ፍልስፍና፣ በሶስተኛ መልኩ የጥበብ ስራ፣ ከዚህም ውጪ በብዙ አንጻር ሊተረጎም የሚችል ‹‹ዘላለማዊ›› ተብለው ከሚጠሩ ስነ-ፅሁፎች የሚመደብ፡፡
#እምዩ #የእናት_ፍቅርና_መስዋዕትነት ከባድ ፈተና ውስጥ የሚገባበት… እጅግ መሳጭ ታሪክ የያዘ ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር መጽሐፍ!!!
#የመጽሐፍ_ቅርስ_ካስፈለገዎት
#መከረኞችና_እምዩ_መጽሐፍት_አሉልዎት፡፡
በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል፡፡
ይቀላቀሉን 👉 http://tttttt.me/teklutilahun

Forwarded from YeneTube
🌻ከNat Computers አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ የወጣ ታላቅ ቅናሽ 🌻
🔅Gaming Laptops🔅
✅Omen X #41500birr
✅ DELL G5 i7 gaming #41500br
✅ Lenovo legion R720 #41500br
✅ Dell inspiron 7567 i7 #41500birr
እና ሌሎችም
🌻🌻ቅናሹን ለመጠቀም 🌻🌻
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል
ስልክ
+251911522626
+251953120011
+251947885430
Inbox @Natyendex
🔶 ለበለጠ መረጃ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAELbSrbiTDHFnicnnA
አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ እስታር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ከangla burger ፊለፊት

Forwarded from HEY Online Market
iPhone 11 (128GB)
New Packd
Storage: 128GB
Color: Grey , Red, white
📌Dual SIM card
Price:38,500
Contact us
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
091069510 @RoViii
New Packd
Storage: 128GB
Color: Grey , Red, white
📌Dual SIM card
Price:38,500
Contact us
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
091069510 @RoViii
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 14 አዉሮፕላኖችን ዳግም ለመንገደኞች በረራ ዝግጁ አደረገ!
በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽ ከተከሰተ በኋላ ከህዝብ ማመላሻነት ወደ ዕቃ ጫኝነት ከተቀየሩት 25 አውሮፕላኖች መካከል 14ቱ ዳግም ለመንገደኞች ዝግጁ መሆናቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ።አብዛኞቹ የዓለማችን አገራት የአየር ክልላቸውን በመዝጋታቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድም የህዝብ ማመላሻ የነበሩትን አውሮፕላኖች ወደ ካርጎ አገልግሎት ማዋሉ የሚታወስ ሲሆን በአሁን ወቅት ደግሞ አገራቱ የአየር ክልላቸውን በመክፈታቸው አውሮፕላቹን ከካርጎ ዳግም ወደ ሕዝብ ማመላሻነት እየተቀየሩ መሆናቸውን ኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።
[Addis Maleda]

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም በኖርዌይ ኦስሎ ተገኝተው ያሸነፉትን የዓለም "የ2020 ብሪጅ ሜከር" ሽልማት ተረከቡ።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
3 ወር ይፈጅ የነበረው የፓስፖርት ዕድሳት በ12 ቀናት ይጠናቀቃል ተባለ፡፡
ከቀናት በፊት የተጀመረው የበ'Online’ ዕድሳት እንደ ቀደሙት ጊዜያቶች ተገልጋዮች በግንባር መምጣትን ሳይጠበቅባቸው 3 ወር መጠበቅም ሳይኖርባቸው በ12 ቀናት ፓስፖርታቸውን ማሳደስ ይችላሉ ሲሉ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል ማረጋገጫ ሰጥተዋል።በአውሮፓና በአፍሪካ በተለይም ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ይህንኑ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ እሩቅ እንዳልሆነ ዋና ዳይሬተሩ ተናግረዋል ።በሀገር ውስጥ ያሉ ዜጎችም በ'Online’ ፓስፖርት የሚያሳድሱበት ቴክኖሎጂ ዘጠና በመቶ ስራው መጠናቀቁንም የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አሳውቋል።
[Sheger FM]

በተያዘው 2013 በጀት ዓመት ከቱሪዝም ዘርፍ ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
ከ400 በላይ የመስህብ ሀብቶችና መዳረሻ ቦታዎችን ለቱሪዝም ገበያ ክፍት ለማድረግ መወጠኑንም አስታውቋል፡፡
በዚህ ዓመት ከ240 ሺህ በላይ የውጭ ሀገርና 14 ሚሊዮን የሚጠጋ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ወደ ክልሉ የመዳረሻ ስፍራዎች ይጎርፋሉ ተብሎ ተጠብቋል፡፡ በዚህም ከውጭና ሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
[AMMA]

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተስተጓጉሎ የነበረው የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የቅርስ ክብካቤ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊገባ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ከዘጠኝ መቶ ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ክብካቤ ለማድረግ ከአንድ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ መንግስት ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በመተባበር የቅርስ አድን ፕሮጀክት ተነድፎ ወደ ስራ ተግብቷል፡፡የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ጥበቃ ፕሮጄክትን በሁለት ክፍሎች ለማከናወን ታቅዶ ወደስራ መገባቱ ይታወቃል፡፡የመጀሪያውና ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር የተጀመረው ቅርሶቹን የመመርምር ሂደት፣ በምርመራው የተገኘውን ውጤት ተከትሎም አስፈላጊውን ክብካቤ ለማድረግ የአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ እንደተያዘለት አይዘነጋም፡፡
ይሁንና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ጥናትና ተግባራዊ የማድረግ እንቅስቃሴ በኮቪድ 19 ምክንያት በታቀደው ፍጥነት ማካሄድ እንዳልተቻለ ይታወቃል፡፡
ወረርሽኙ ሙሉ በሙሉ ባይወገድ የዚህ ፕሮጀክት ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? ወረርሽኙ እንዳለ ሆኖ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ምን ታስቧል በሚል በኢትዮጵያና ፈረንሳይ የቅርስ አድን ትብብር ፕሮጀክት የኢትዮጵያ አስተባባሪው ዶክተር መንግስቱ ጎበዜን ተጠይቀዋል፡፡ዶክተር መንግስቱ ቫይረሱ ባለበት ቢቀጥል እንኳን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱ አይቀርም ሲሉ መለሰዋል፡፡
[አሐዱ ሬዲዮ]

የጊንጪ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ!
ላርሰን ኤንድ ቱርቦ በተባለ የህንድ ኩባንያ የተገነባው የጊንጪ ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ፡፡የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ገ/እግዝአብሔር እንዳስታወቁት የማከፋፈያ ጣቢያው መጠናቀቅ በጊንጭና በዙሪያው የሚገኙ ከተሞችን የኃይል መቆራረጥ ከማስቀረቱም በተጨማሪ ወደ ፊት አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል፡፡የማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል የሚያገኘው ከገፈርሳ - ጌዲዮን ከተዘረጋው ባለ 230 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ሲሆን ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች ተተክለውለታል፡፡ጣቢያው ሁለት ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ገቢ እና 10 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡በ2008 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪው 67 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ነው፡፡
[EEPCo]