እውቁ የአሜሪካ ሳምንታዊ መጽሔት “ታይም”፤ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የጥበብ ሰዎችን አቤል ተስፋዬን (ዘ ዊኬንድ) እና ጁሊ ምህረቱን በዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪነት መረጠ።
https://time.com/collection/100-most-influential-people-2020/
@YeneTube @FikerAssefa

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200ሺ በላይ ሆነ!
በመላው አሜሪካ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ200ሺ በላይ ደርሷል፡፡በአሜሪካ ዊስኮንሲን ገዥ የሆኑት ቶኒ ኢቨርስ በትናንትናው እለት አስቸኳይ የህብረተሰብ ጤና ያወጁ ሲሆን ከባለፈው ህዳር ጀምሮ የነበረው አስገዳጅ የፌስማስክ ማድረግ ህግም ተራዝሟል፡፡ የሰዎች የአካል ግንኙነት በግዛቷ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ማድረጉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ኢቨርስ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሲመለሱ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የፌስማስክን በአግባቡ እንዲጠቀሙ መክረዋል፡፡ በተለይ በኮሌጆች የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መጨመሩን የግዛቱ አስተዳዳሪ ተናግረዋል፡፡
[Alain]

በቀጣዮቹ ቀናት በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል!
ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ፡-
• በመነን ት/ቤት፣ ሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሃኒዓለም፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ እና አካባቢዎቻቸው፤
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ፡-
• በግብፅ ኤንባሲ፣ በስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ፣በየካቲት ሆስፒታል፣ በቅድስተማርያም ቤተ-ክርስትያን ጀርባ፣ በእሪ በከንቱ፣ በፒያሳ፣ በቀይ ባህር ኮንደሚኒየም፣ በተፈሪ መኮንን ጀርባ፣ በአፍንጮ በር፣ በናይጄሪያ ኤንባሲ፣ በችሎት ጉቶ ሜዳ እና አካባቢዎቻቸው፤
እንዲሁም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ፡-
• በወሰን ግሮሰሪ፣ በወንድይራድ ት/ቤት ጀርባ፣ በባድሜ ሰፈር፣ በሰንጋ ተራ፣ በቴዎድሮስ አደባባይ፣ በንግድ ማተሚያ ቤት፣ በኤክስትሪም ሆቴል፣ በተክለሀይማኖት ሆስፒታል እና አካባቢዎቻቸው፤
በተጨማሪም ዓርብ መስከረም 15 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ፡-
• በወሰን ግሮሰሪ፣ በወንድይራድ ት/ቤት ጀርባ፣ በባድሜ ሰፈር፣ በቦሌ መድሃኒዓለም ቤተ-ክርስትያን፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ፣ በገርጂ ኮንደሚኒየም፣ በኢፔሪያል ሆቴል፣ በገርጂ ጤና ጣብያ፣ በዳችያ ቀለም፣ በገርጂ አንበሳ ጋራዥ እና አካባቢዎቻቸው፤
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በጎሮ፣በፍሊንተስቶን ሆምስ፣ በሰሚት ለስላሳ፣ በሰሚት ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስትያን፣ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ፣ በሰሚት ፍርድ ቤት እና አካባቢዎቻቸው፤
በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ ተብላችኋል፡፡
[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]

አቶ ልደቱ አያሌው በ100 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢወስንም ፖሊስ ሊፈታቸው እንዳልቻለ ተገለጸ።
ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ መገደሉን ተከትሎ ሁከት በማስነሳት እና በሌሎች ጉዳዮች ተጠርጥረው በአስር ላይ የነበሩት አቶ ልደቱ በትናንትናው ዕለት ምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል።
የአቶ ልደቱ ጠበቃ አቶ አብዱል ጀባር ሁሴን እንዳሉት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ብሩ የተከፈለ ቢሆንም ዛሬ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ብናመራም የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አልተከበረም ብለዋል።
የምርምራ ቡድኑ አቶ ልደቱ እንዲፈቱ ባስተላለፈው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ላይ ምንም ማለት አንችልም መባላቸውን ጠበቃው ተናግረዋል።በመሆኑም የፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን እንዲያስከብር ለፍርድ ቤት አቤቱታ እናስገባለን ሲሉም ተናግረዋል።
Via Ethio FM

በኢትዮጵያ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ምክንያት ለጉዳት መዳረጋቸውን ኮሚሽኑ አስታወቀ!
በኢትዮጵያ ባለፉት ወራት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያት በተለያዩ ክልሎች ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለጉዳት የተዳረጉ ሲሆን ከ313 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።ለተፈናቀሉ ዜጎችም የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገ እንደሚገኝ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዳመና ዳሮታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።በቀጣይም በተለያዩ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል እና ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት የተፋሰስ ልማት ባለስልጣን አሳስቧል።መግለጫውን በጋራ የሰጡት የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እና የተፋሰስ ልማት ባለስልጣን ናቸው።
(ኢቢሲ)

ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሲጀመሩ አስፈላጊው የኮቪድ 19 መከላከያ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢፊዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ።
በትናንትናው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ስፖርታዊ እንቅስቀሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዱቤ ጅሎ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል ፡፡በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሲባል ስፖርታዊ ስልጠናዎች፣ ውድድሮች በአጠቃላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ መደረጉ ይታወቃል፡፡የኢፊዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መፈቀዳቸውን አስመለክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ወደ ነበረበት ለመመለስ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እና የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት በማድረግ የኢፊዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በአዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ለሚመለከተው አካል ፍቃድ እንዲሰጥ መቅረቡን ገልጸዋል።በዚህም ፕሮቶኮሉን መነሻ በማድረግ እና የጤና ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ምክረ ሀሳብ መሰረት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ ተወስኗል ብለዋል ፡፡
ነገር ግን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሲጀመሩ አስፈላጊው የኮቪድ -19 መከላከያ መንገዶች እና ጥንቃቄዎች ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡በተለይም ስልጠናዎች እና ውድድሮች ከመጀመራቸው በፊት ከማዘውተሪያ ዝግጅት ፣ የሰው ሀይል ቁጥር እና ሌሎች አስፈላጊ የመከላከያ ግብዓቶች መሟላታቸው ሊረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡የሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት ስፖርቱን ሲያስጀምሩ በኮሚሽኑ እና በጤና ሚኒስቴር የወጣውን መመሪያ በየደረጃው ስራ ላይ እንዲውል ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው መጠቆማቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ይህን የሚከታተልም የብሔራዊ ኮሚቴ ፣የጤና እና የፀጥታ ኮሚቴ ተቋቁሞ አስፈላጊው ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡በተዋረድም በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮችም ኮሚቴዎች ተቋቁመው ክትትል እና ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡መመሪያውን ተላልፎ የሚገኝ አካል ላይም አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስበዋል፡፡ከዚህ ባሻገር ኮሚሽኑ ስፖርቱን በአሠራር እና በአደረጃጀት ለማስተካከል እና ውጤታማ ለማድረግ ሀገር አቀፍ የስፖርት ሪፎርሙን መሠረት በማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰራ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
[FBC]

የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ የቀድሞ የወላይታ ዞን አመራሮች የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ 20 ተጠርጣሪዎች በወላይታ ሶዶ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በተሰየመ ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ።
ፍርድ ቤቱ፤ በስር ፍርድ ቤት ለተጠርጣሪዎች ተፈቅዶ በነበረው ዋስትና ላይ ፖሊስ የመልስ መልስ ይዞ እንዲቀርብ ለመጪው ሳምንት ማክሰኞ መስከረም 19፤ 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃ ተመስገን ዋጃና ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ተናግረዋል።
Via:- Ethiopia Insider
@YeneTube @Fikerassefa

መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግና ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንዲሳተፉ ተወሰነ!
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግና ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንዲሳተፉ መወሰኑ ተገለፀ።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክሉት እንዲያሳውቅ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ የ2011 የፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እንዲሳተፍ ሲወስን የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንዲሳተፍ መወሰኑን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በመቋረጣቸው ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እና በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳትፍ ክለብ እንደማይኖር ተወስኖ እንደነበረ የሚታወስ ነው።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ 6ኛው አገራዊ ምርጫን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ!
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ተገሰ ጫፎ ትላንት ም/ቤቱ ያሳለፈውን ውሳኔ በተመለከተ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡አፈ ጉባኤው በመግለጫቸው በ2012 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው 6ኛው አገራዊ ምርጫ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት መራዘሙን ጠቁመው በተያዘው ዓመት አገራዊ ምርጫ ለማከላሄድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክር ቤቱ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ አገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውሰው፡፡ምርጫ ቦርድና የሚመለከታቸው አካላት ዝግጅት ማድረግ መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡
የአስቸኳ አዋጁ ጊዜ ገደብ ያለቀ በመሆኑ መንግስትና ሌሎች ተቋት የሚመሩባቸው የህግ ማዕቀፎች በመተግበር የትምህርት ስርአቱ፤ የትራንስፖርት አገልግሎቶች፤ ሆቴሎችን እና የቱሪዝም አገልግሎቶቸው እንዲሁም ስብሰባዎችን እንዴት መምራት እንደሚቻል የህግ ማዕቀፎችን በማስቀመጥ ስራቸውን በተገቢው መንገድ መከናወን እንዳለባቸው ጤና ሚኒስቴር በስራ አስፈፃሚው አካል የተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት ማስፈፀም እንዳለበት አሳሰበዋል፡፡
አያይዘውም ህብረተሰቡ ከጤና ሚኒስቴር የሚሰጡትን መመሪዎችና የግንዛቤ ስራዎችን በመረዳት ዜጎች ራሳቸውን ከኮሮና መሽታ በመከላከል አገራዊ ምርጫን ለማካሄድ መዘጋጀት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡አፈ ጉባኤ አቶ ተገሰ ጫፎ አክለውም ከትምህርት ተቋማት ጋር በተያያዘ በየደረጃው ያለው አመራርና ህብረተሰቡ እንዲሁም ተማሪዎችን ጭምር በወያየትና በማሳተፍ በቂ ግንዛቤ በመያዝ አስፈላጊ የትምህርት፤ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን፤የመማሪያ ክፍሎችን በማመቻቸት የትምህርት ስርአቱን ማስጀመር እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡
HoPR

''የመስቀልና የእሬቻ በዓላት ሲከበሩ ከሚፈቀዱ ስነ ስርዓቶች ውጪ የሆኑ እንቅስቃሴዎች የተከለከሉ ናቸው'' ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመስቀልና ለእሬቻ በዓላትን ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።የፖሊስ አባላት ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በዓላቱ በሰላም እንዲከበሩ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ገልጸዋል።ኮሚሽኑ በቂ የጸጥታ አባላትን እንደመደበና አስፈላጊ ሎጅስቲክ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።በዓላቱ ሲከበሩ ከሚፈቀዱ ስነ ስርዓቶች ውጪ የተለየ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል አመልክተዋል።
የእርስ በርስ ግጭትን የሚፈጥሩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ሰላምን ለማደፍረስ በሚጥሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ነው ኮሚሽነር ጌቱ የገለጹት።በህግ ከተፈቀደ ሰንደቅ ዓላማና አርማ ውጪ ሌሎችን በመያዝ ወደ በዓላቱ ስፍራ መምጣት የተከለከለ መሆኑንም ተናግረዋል።ፈቃድ ከተሰጠው አካል ውጪ ርችት መተኮስ እንደማይቻል ገልጸው፤ ይሄን ሲፈጽሙ በተገኙት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አመልክተዋል።
አንዳንድ አካላት በርችት መተኮስ ሽፋን ሰላምን ለማደፍረስ የሚጥሩ አካላት ሊኖሩ ስለሚችሉ አስፈላጊው ክትትልና ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል።በዓላቱን የሚያስተጓጉሉ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ሁሉም አካላት ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በዓላቱ በውስን ተሳታፊዎች እንደሚከበሩ አውስተው፤ በመስቀል በዓል እንዲሳተፉ ባጅ ከተዘጋጀላቸው ተሳታፊዎች ውጪ ሌላ ሰው መምጣት እንደማይችል ገልጸዋል።የእምነቱ ተከታይ ይሄንን በመገንዘብ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንደሚገባው ተናግረዋል።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዓላቱ በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ ከጸጥታ አካላት ጋር ከመቼውም ጊዜ በተሻለ መልኩ በጋራ እየሰራ መሆኑን ነው ኮሚሽነር ጌቱ የገለጹት።
የበዓላቱ ተሳታፊዎች የተለየ እንቅስቃሴ ካጋጠማቸው በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት እንዲሁም በ011-111-01-11 እና በ991 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ማሳወቅ እንደሚችሉም ገልጸዋል።የደመራ በዓልን አስመልክቶ የሚዘጉ መንገዶችን ለህብረተሰቡ ነገ በዝርዝር እንደሚገለጽ ተናግረዋል። ኮሚሽነር ጌቱ የመስቀልና እሬቻ በዓላት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የደስታ እንዲሆን ተመኝተዋል።የመስቀል በዓል ዋዜማ የደመራና የመስቀል በዓል መስከረም 16 እና 17 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሁም የእሬቻ በዓል በአዲስ አበባ መስከረም 23 ቀን 2013 ዓ.ም ይከበራሉ።
[ኢዜአ]

በትግራይ የግእዝ ቋንቋ በመደበኛ ትምህርት መርሀግብር ሊሰጥ ነው!
በትግራይ ክልል የግእዝ ቋንቋን በመደበኛ የትምህርት መርሀ ግብር ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ቋንቋዎች አካዳሚና ትምህርት ቢሮ አስታወቁ።የትግራይ ቋንቋዎች አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዳንኤል ተክሉ ለኢዜአ እንደገለፁት በሀገሪቱ በግእዝ ቋንቋ የታተሙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ጥንታዊ የብራናና የመጽሀፍት ህትመቶች አሉ።“አዲሱ ትውልድ ፅሁፎችን በማንበብ የሀገሩን ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ታሪክና ማንነት ጠንቅቆ እንዲያውቅ ለማበረታታት የቋንቋውን ትምህርት መስጠት አስፈልጓል” ብለዋል።በተያዘው 2013 አመት በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምሀርቱን ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል።
ከትግርኛ፣ ኩናምኛና ሳሆኛ ቋንቋዎች ቀጥሎ ግዕዝ አራተኛ ቋንቋ ሆኖ በክልሉ በሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።ቢሮው የመማር ማስተማር ስራውን እንዲጀምር በክልሉ ምክር ቤት በአዋጅ መጽደቁንም አስታውቀዋል።የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ባህታ ወልደሚካኤል በበኩላቸው የግዕዝ ቋንቋ ትምህርትን በክልሉ በሚገኙ ከ2 ሺህ በላይ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስጀመር የመምህራንና የመማሪያ መፃፍት ዝግጅት እየተደረገ ነው።ከስድስት ወራት በኋላ ትምሀርቱን ለመጀመር እቅድ መያዙን አመላክተዋል።
[ENA]

በሆስፒታል የሚገኘው አርቲስት አሊ ቢራ "እየተሻለኝ ነው" አለ!
የ73 ዓመቱ አርቲስት አሊ ቢራ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።"በፊት ላይ በጣም አሞኝ ነበር። አሁን ተሽሎኛል። አሁን ያለሁበት ሆስፒታል ጥሩ ክትትል እያደረጉልኝ ስለሆነ ፈጣሪ ይመስገን እየተሻለኝ ነው" ብሏል አሊ ቢራ።አሊ ቢራ በአሁኑ ወቅት የውስጥ ደዌ ህክምና እየተደረገለት ሲሆን ከዚህ ቀደምም የልብ እና የስኳር በሽታዎች ታማሚ መሆኑን ይናገራል።"አንዳንድ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስለ እኔ ሐሰተኛ ወሬ በማሰራጨት ሰዎችን እያስደነገጡ መሆኑን ሰምቻለሁ" የሚለው አርቲስት አሊ ቢራ፤ ሰዎች የመረጃዎችን እውነትነት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብሏል።
ከአሊ ጎን የነበረችው የአሊ ባለቤት ሊሊን ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያሰራጩት ሐሰተኛ ወሬ እጅጉን እንዳበሳጫት ለቢቢሲ ተናግራለች። ሰዎች ከዚህ መሰል ተግባራቸው እንዲቆጠቡም ጠይቃለች።አሊ ቢራን ሆስፒታል ድረስ በመሄድ ያነጋገረው የቢቢሲ ሪፖርተር "አሊ ምንም እንኳ ታሞ የሆስፒታል አልጋ ላይ ቢገኝም መልካም ስሜት እና ጤነኝነት ፊቱ ላይ ይነበባል" ብሏል።አሊ ቢራ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ስሜቱን እጅጉን ጎድቶት እንዸነበረ አልሸሸገም። "የዛ ልጅ ሞት እጅግ በጣም ጎድቶኛል . . . " ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ እምባ ቀድሞታል።የአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል የጤና ኮሌጅ የጤና ባለሙያዎች ጥሩ እንክብካቤ እና የሕክምና ድጋፍ እያደረጉለት እንደሆነ አሊ ቢራ ይናገራል።አሊ ቢራ ባለፉት 50 ዓመታት በኦሮሞ የሙዚቃ ስራዎች ውስጥ እንቁ ሆኖ ቆይቷል። ለቋንቋ የሙዚቃ እድገትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
[BBC]

በመተከል ዞን ለቀጣዮቹ 3 ወራት የሚቆይ የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ታዉጇል!
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች ከዛሬ ጀምሮ መተግበር ለጀመረው የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የክልሉ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል፡፡በመተከል ዞን በተለይም በቅርቡ የጸጥታ ችግር ተስተውሎባቸው የነበሩትን ጉባ፣ ወምበራ፣ ቡለንና ዳንጉር ወረዳዎች የጸጥታ ኮማንድ ፖስቱ በመከላከያ ሠራዊት የሚመራ ይሆናል፡፡
የጸጥታ ኮማንድ ፖስቱን በቀሪዎቹ የዞኑ ወረዳዎች ፓዌ፣ ማንዱራና ድባጤ ወረዳዎች የሚመሩት ደግሞ የወረዳዎቹ አስታዳዳሪዎች ናቸው፡፡በመሆኑም በመተከል ዞን ባለፉት የተለያዩ ጊዜያት የተስተዋሉ የጸጥታ መደፍረስ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እና ዘለቂ ሠላምን ለመገንባት እንዲሁም አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የክልሉ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል፡፡
[የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን]

ደንበኞች የጠፋ የሞባይል ስልካቸውን በፍጥነት ባለማዘጋታቸው በቁጥራቸው ሊፈጸም ከሚችል ወንጀል እንዲጠነቀቁ ኢትዮ ቴሌኮም አሳሰበ!
የሞባይል አገልግሎት ደንበኞች የሞባይል ስልካቸው ሲጠፋ ወዲያው ባለማዘጋታቸው ወንጀለኞች ለተለያዩ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሎች የሚጠቀሙበት መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።ሕገወጦች በደንበኞች በኩል የሚስተዋለውን ክፍተት በመጠቀምም የሚፈጸሙት የማጭበርበር ድርጊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚገኝ ተቋሙ አስታውቋል።ኢትዮ ቴሌኮም ለኢዜአ በላከው መግለጫ በ2012 ዓ.ም ብቻ በ130 ሺህ የስልክ መስመሮች የቴሌኮም ማጭበርበር ድርጊት በመፈጸሙ ለከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ኪሣራ እንደዳረገው አስታውቋል።ከዚህም በተጨማሪ ደንበኞች የስልክ መስመራቸውን (ሲምካርዳቸውን) ለሦስተኛ ወገን አሳልፈው በመስጠታቸውም ለእንግልትና የወንጀል ድርጊት ተጠያቂነት እየተዳረጉ መሆናቸውንም ጨምሮ ገልጿል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለሊባኖስ ፕሬዚዳንት ማይክል ኦን በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መብታቸው እንዲጠበቅ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
መልዕክቱን ቤይሩት የሚገኘው የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት ቆንሱል ጄኔራል አቶ ተመስገን ኡመር በሊባኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በአካል ተገኝተው ማስረከባቸው ነው የተገለጸው፡፡ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በመልዕክታቸው በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሰሩበት ደመወዝ እንዲከፈላቸው፣ መብታቸው እንዲጠበቅላቸው አሳስበዋል፡፡
እንዲሁም ከሊባኖስ ወደ አገር ቤት መመለስ የሚልጉ የመኖሪያ ፍቃድ፣ ፓስፖርት ወይም የጉዞ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች የመውጫ ቪዛ አስመልክቶ በሊባኖስ በኩል ውስብስብና ረጅም ጊዜ ስለሚወስድ የአሰጣጡ ሂደት ለተወሰነ ጊዜ ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል፡፡
እንዲሁም ኢትዮጵያውያኑ ከቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት የሚሰጣቸውን የጉዞ ሰነድ በመያዝ ኤርፖርት በሚገኘው ኢሚግሬሽን በኩል መውጫ እየተመታ ወደ አገር ቤት መመለስ እንዲችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡አቶ ተመስገን ኡመር ጉዳዩን አስመልክቶ ለሊባኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደርና የውጭ ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ ለሆኑ ከፍተኛ ባለስልጣን በዝርዝር አብራርተዋል፡፡
[ፋና]

የኢትዮጵያ መንግሥት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል አደገኛ አደንዛዥ ዕጾችን ሲያዘዋውሩ የያዛቸውን 58 ናይጀሪያዊያን እስረኞችን ለሀገራቸው እንዳስረከበ መስማቱን ሸገር ዘግቧል፡፡ ናይጀሪያዊያኑ እንደ ጥፋታቸው ቅጣት ተፈርዶባቸው እስር ላይ የነበሩ ናቸው፡፡ ወንጀለኞቹ ወደሀገራቸው የተላኩት በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ እንደሆነ በአዲስ አበባ የናይጀሪያ ኢምባሲ ተናግሯል፡፡ ሀገራቸው እንደደረሱም እስር ቤት ገብተዋል ተብሏል፡፡
[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 661 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፡፡
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,551 የላብራቶሪ ምርመራ 661 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 262 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 71,083 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,141 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 29,253 ደርሷል።

የዎላይታ ዞን አስተዳደር ባለፈው ወር በዞኑ በተከሰተው አለመረጋጋት ለተገዱ ቤተሰቦች በዛሬው ዕለት ድጋፍ አደረገ ::
ባለፈው በነሀሴ ወር ውስጥ በዎላይታ አካባቢ በተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰብና ለተጎዱ የዎላይታ ዞን አስተዳደር የገንዘብ ድጋፍ ደረጉ ተደርጓል።ድጋፍ በሚደረግበት መድረክ ላይ የሀይማኖት መሪዎች የሀገር ሽማግለዎችና የዞን አመራሮች ተገኝተው ተጎጂዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን አፅናንተዋል።ዛሬ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው በሁሉም አከባቢዎች በአለመረጋጋቱ ጉዳት የደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች፣ቀላልና መካከለኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በቀጣይነትም የዞኑ አስተዳደር በተለያየ መንገድ ድጋፍ የሚያደርግ እንደሆነና ሌሎች ድርጅቶችና ግለሰቦች ለተጎጂዎቹ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
[የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን]

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ትምህርት የማስጀምር ውሳኔ
(በዶይቼ ቨሌ)
ሰሞኑን 45 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮችን በማሳተፍ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጅማ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው የሦስት ቀናት ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ተጠናቋል። በውሳኔውም ለስድስት ወራት ተቋርጦ የቆየው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ትምህርት ዳግም እንዲጀመር መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለዶይቼ ቨሌ ተናግረዋል። በዚህም ለመማር ማስተማር ሂደቱ ዝግጁነት ያላቸው ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ተያዘው ወርሃ መስከረም መጨረሻ ዝግጁነታቸውን አጠናቀው ለተማሪዎች ጥሪ እንዲደረግ ውጥን ተይዟል።
በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የኮቪድ-19 ለይቶ ማቆያና ምርመራ ማዕከላት ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ለትምህርቱ ፈጥኖ መጀመር እንደ ስጋት ተነስቷል።በመሆኑም በአማራጭ ጉዳይ ላይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመምከር ለጊዜው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚገኙት 700 ሺህ ተማሪዎች ገደማ ቁጥራቸው ከ100 ሺህ የሚለቀውን ተመራቂዎች ቅድሚያ ሰጥቶ ወደ ትምህርት ገበታው እንዲመለሱ ነው የተወሰነው።በቀጣይነትም ከኮሮና ወረርሽኝ ሁኔታ ጋር በሚስማማ መልኩ ተለዋዋጭ እቅዶችን በመያዝ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ እንደሚሠራም ተገልጿል።
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ወጥነትን ሳይጠብቁ ቀድመው ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ በማድረግ ወደ መማር ማስተማር ሥራው እንዲገቡ ጉባኤው ወስኗል። ለተማሪዎች ጥሪ ከተደረገ በኋላ ከመጓጓዣ ሂደት ጀምሮ በየዩንቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ ወረርሽኙ እንዳይዛመት ከፍተኛ ዝግጅት መደረግ አለበትም ተብሏል። ከኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ባልተናነሰ አምና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ፈተና ሆኖ የከረመው የፀጥታ መደፍረስ እንዳያጋጥም ከአምና ልምድ መወሰዱን ጉባኤው የመከረበት ሲሆን፤ ጉዳዩ አሁን ለጊዜው ስጋት ባይሆንም መዘናጋት ሳይፈጠር ዩንቨርሲቲዎች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እንዲሠሩበት እቅድ መያዙ ተገልጿል።