YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በመቐለ ከተማ ሦስት ወጣቶች ሞተው ተገኙ!

በመቀለ ከተማ በአይደር ክፍለ ከተማ አዲሓ ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር አንዲት ሴትና ሁለት ወንድ ጓደኛሞች በአንድ ቤት ውስጥ ሞተው ተገኙ።ወጣቶቹ ሞተው የተገኙት በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ መሆኑን በከተማዋ የሚገኘው የአይደር ክፍለ ከተማ ፖሊስ ለቢቢሲ ገልጿል።ህይወታቸው አልፎ የተገኙት ሦስቱ ወጣቶች ርዕሶም ገብረእግዚአብሔር፣ ግርማይ ኃብተሚካኤል እና መርሃዊት ሐድጉ የተባሉት ጓደኛሞች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን እድሜያቸው ደግሞ በ20ዎች ውስጥ እንደሆነ ተነግሯል።ሦስቱም ወጣቶች ባለፈው ቅዳሜ መስከረም ሁለት ቀን በጋራ ሲጫወቱ አምሽተው ወደ ቤታቸው እንደገቡ የተገለጸ ሲሆን፤ በማግስቱ እሁድ ከሰዓት ግን በአንደኛው ሟች ቤት ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ታውቋል።

በአይደር ክፍለ ከተማ የወንጀል ምርመራ ክፍል ባልደረባ የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ገብረማርያም የማነ እንዳሉት የወጣቶቹ ሞት መንስዔ ለማወቅ ፖሊስ መርመራ እያካሄደ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጸዋል።ጨምረውም እስካሁን ባገኘው መረጃ ፖሊስ ለወጣቶቹ ሞት መንስዔ ተብሎ የሚጠረጠር ፍንጭ ያገኘ ቢሆንም፤ በአይደር ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ ተደርጎ ውጤት እስኪመጣለት ድረስ እየጠበቀ መሆኑንም መርማሪው ጨምረው ተናግረዋል።የሟች ርዕሶም ገብረእግዚአብሔር ወንድም የሆነው ገብረ መድኅን ገብረእግዚአብሔር ለቢቢሲ እንደተናገረው ወጣቶቹ ተኝተውበት በነበረው ክፍል ውስጥ የነበረው ጄነሬተር ለሞታቸው መንስኤ ሊሆን እንደሚችል አመልክቷል።

ገብረመድኅን እንደሚለው ከሆነ ቅዳሜ ዕለት ወጣቶቹ በሚኖሩበት አካባቢ መብራት ጠፍቶ ስለነበር ጄኔሬተሩ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ቢሆንም ማታ ግን ተለኩሶ ስለመቆየቱ መረጃ እንደሌለው ተናግሯል።ህይወታቸው አልፎ የተገኙት ሦስቱ ወጣቶች አስከሬን ወደ አይደር ሆስፒታል ሲወሰዱ ከህልፈታቸው በፊት ከአፋቸው አረፋ ይደፍቁ እንደነበርም ጨምሮ ተናግሯል።የሶስቱ ወጣቶች ድንገተኛ ሞት ዜና በርካታ የመቀለ ከተማ ነዋሪዎችን ያስደነገጠ ሲሆን፤ ለሞታቸው ሰበብ የሆነውን ምክንያት ለማወቅ የህክምናና የፖሊስ የመርመራ ውጤት እየተጠበቀ ነው።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የ”ሰላም”ፈራሚዎቹ ልኡካን ኋይት ሀውስ ደርሰዋል!

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች( ዩኤኢ)፣ በእስራኤልና በባህሬን የሰላም ስምምነት የሚሳተፉት የሉእካን ቡድን አባላት አሜሪካ ኋይት ሃውስ ገብተዋል፡፡የዩኤኢ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሸክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አልናህያን፣ የባህሬኑ አቻቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላቲፍ አል ዛያኒና የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይገኛሉ፡፡ሉእካኑ ኋይት ኃውስ ሲደርሱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተቀብለዋቸዋል፡፡በኋይት ሀውስ አንድ ሺ አሜሪካውያን፣ የአለም አቀፍና የአረብ ታዋቂ ሰዎች በኋይት ሃውስ ተገኝተዋል፡፡የአረብ ሀገራቱና የእስራኤል ግንኙነት እንዲታደስ እያመቻቸች ያለችው አሜሪካ ስትሆን ባለፈው ወር ዩኤኢና እስራል ታሪካዊ የተባለ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ድንበሮች ላይ ዳግም ባገረሸ ግጭት በትንሹ አራት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

የአካባቢው ነዋሪዎች አንዳሉት ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት ከሞቱት ሰዎች ባሻገር የመኖርያ መንደሮች በእሳት ወድመዋል። የግጭቱ መነሻ በአሌ ልዩ ወረዳ ቀርቀርቴ ቀበሌ ውስጥ በቡድን የተሰባሰቡ ሰዎች የአንድ ሰው ሕይወት አጥፍተዋል የሚል መረጃ ከተሰራጨ በኋላ መሆኑን፤ በዚህም ምክንያት በሁለቱም ወገን በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን አንድ እማኝ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። የቀርቀርቴ ቀበሌ ነዋሪ መሆናቸውን የገለፁት የዓይን ምስክሩ እንደሚሉት ቢያንስ የአራት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።በኮንሶ ዞን የካራ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሣሁን ገረመው በወረዳው አርካይዴና ገላቡ በተባሉት ቀበሌዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሁለት ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠዋል። የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየው ባውዴም ግጭቱ ዳግም መቀስቀሱን በማረጋገጥ፤ በአሁኑ ወቅትም የፀጥታ ኃይል በመንደሮቹ በመግባት ለማረጋጋት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 700 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 10,024 የላብራቶሪ ምርመራ 700 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ13 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1035 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 655 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 25,988 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 65,486 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዩኤኢ እና ባህሬን ከእስራኤል ጋር ታሪካዊውን የሰላም ስምምነት በዋይት ሀውስ ተፈራረሙ!

በፍልስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት እና እስራኤል መካከል እ.ኤ.አ. በ 1993 የኦስሎ ስምምነት ከተፈረመ ከ 26 ዓመታት በላይ ከዘለቀ ቖይታ በኋላ ዛሬ በዋይት ሃውስ በእስራኤል እና በአረብ ሀገራት መካከል የመጀመሪያው የሰላም ስምምነት ተፈርሟል፡፡በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ እስራኤል ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ከባህሬን ጋር ስምምነት እንድትደርስ አሜሪካ የማደራደሩን ስራ አከናውናለች፡፡የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና የባህሬን መንግሥት በፊርማው ሥነ-ስርዓት ላይ በቅደም ተከተል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና አብዱል ላቲፍ ቢን ራሺድ አል ዛያኒ የተወከሉ ሲሆኑ እስራኤል ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተወክላለች፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በአሜሪካ 99 ሺህ ዶላር የተያዘበት ኢትዮጵያዊ ገንዘቡ ሊወረስ ይችላል ተባለ!

ባለፈው ሳምንት ለጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ሳያሳውቅ ወደ 99 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ከአሜሪካ ሊያስወጣ ሲል የተያዘበት ኢትዮጵያዊ ገንዘቡ ሊወረስ እንደሚችል ተገለጸ።ቢቢሲ በአሜሪካ የአገር ውስጥ ደኅንነት መስሪያ ቤት ስር ከሚገኘው የጉምሩክና የድንበር መቆጣጠሪያ ክፍል ባገኘው መረጃ መሰረት ከኢትዮጵያዊው ላይ የተያዘው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በመንግሥት ሊወረስ ይችላል ተብሏል።

የዛሬ ሳምንት ረቡዕ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ ከነበረው መንገደኛ ላይ ዋሽንግተን በሚገኘው ደለስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ተቆጣጣሪዎች የተያዘው ገንዘብ 99 ሺህ ዶላር የሚጠጋ እንደሆነ ተነግሯል።

ቢቢሲ እንዳረጋገጠው ከግለሰቡ ላይ የተያዘው የገንዘብ መጠን 98,762 ዶላር ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ከ3.6 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል።የጉምሩክ መስሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሠራተኛ ስቲቭ ሳፕ ለቢቢሲ በሰጡት የጽሁፍ ምላሽ ላይ እንዳመለከቱት፣ ግለሰቡ ይዞት የነበረው ዶላር የተያዘበት ተጓዦች የያዙትን የገንዘብ መጠን እንዲያሳውቁ የሚጠይቀውን የአገሪቱን ሕግ በመተለላፍ ነው።በተጨማሪም ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ግለሰቡ በዚሁ ሳቢያ ያልታሰረ ሲሆን የወንጀል ክስ ስላልተመሰረተበትም ማንነቱ እንደማይገለጽ ለማወቅ ተችሏል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተጠቆመ!

በተለያዩ ሃገራት ከሚያገለግሉትና ለሥልጠና ከመጡት የኢትዮጵያ አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች የተወሰኑት በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ታማኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል።በቫይረሱ መያዛቸው የተነገራቸው አምባሳደሮች ቁጥር ይሄን ያህል ነው ማለት እንደማይቻል የጠቀሱት ምንጮቹ፣ የተነገራቸው በየግል በመሆኑ ድምሩን ማስቀመጥ እንደማይቻል አመልክተዋል። ቀደም ሲል ሲጠቀስ የነበረው ቁጥር ግን 12 እንደነበር ነው የጠቆሙት፤ ቆየት ብለው የወጡ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ደግሞ 21 አድርሰውታል::ሁኔታውን ለስልጠና ከመሰባሰባቸው ጋር ማገናኘት እንደማይቻል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች አክለው ጠቅሰዋል።ከየትኛውም የሕብረተሰብ ክፍል ናሙና ሲወሰድ እንደሚሆነው ሁሉ ከአምባሳደሮቹም መካከል የተወሰኑት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ነው ያሉት።ከተለያየ የዓለም ክፍል መጥተው ለተሰባሰቡ ሰዎች ምርመራ ሲደረግ በቫይረሱ የተያዙ መገኘታቸው የሚጠበቅ መሆኑንም ነው ያመለከቱት።አምባሳደሮቹ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በቢሾፍቱ ከተማ ኩሪፍቱ መዝናኛ በተካሄደው ስልጠና ለመሳተፍ መሆኑንም የቪኦኤ ዘገባ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
Audio
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በገንዘብ ለውጡ ሂደት ላይ ሊፈፀሙ የሚችሉ የመጭበርበር ሙከራዎችን ለመቆጣጠር ከዛሬ ጀምሮ የፖሊስ አባላትን ማሰማራቱን ለሸገር ተናገሯል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የፋይናንስ ደንበኞች ጥበቃ መመሪያ አወጣ!

መመሪያው የፋይናንስ ተጠቃሚዎችን ካልተገባ ችግር የሚጠብቅ ነው ይላል። መመሪያው እንደሚለው የደንበኞች እምነት በፋይናንስ አካታችነት፣ ጤናማ የገንዘብ እንቅስቃሴ፣ የዘርፉን እድገት ለማጎልበት፣ እንዲሁም የፋይናንስ ስርአቱ በስነምግባር የተረጋጋ እንዲሁም በፈጠራ እና ብቃት የታገዘ እንዱሆን አስፈላጉ በመሆኑ መመሪያው ሊወጣ ግድ ሆናል፡፡በፋይናንስ ዘርፍ የመረዳት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ ማንኛውም ዜጋ አገልግሎ ላይ መታለል እነዳያጋጥመው ከፍተኛ ሃላፊነት ለሁሉም የፋይናንስ ተቋመት ይሰጣል አዲሱ መመሪያ፡፡በከፍተኛ የለውጥ ጉዞ ላይ የሚገኘው ብሄራዊ ባንክ ባለፉት ሁለት አመታት 47 መመሪያዎችን ያወጣ ሲሆን አብዛኞቹ አዳዲስ መሆናቸውን የባንኩ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ፓርላማው ለመጪው ዓርብ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ!

ከሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለዓመታዊ እረፍት የተበተነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለመጪው ዓርብ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ።ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የሕዝብ ተመራጮቹ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተዋል፡፡ የተጠራው አስቸኳይ ስብሰባም ምክር ቤቱ የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ስብሰባውን በሚያካሂድበት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዳራሽ እንደሚሆን ይጠቁማል።ሪፖርተር ያነጋገራቸው የምክር ቤቱ ምንጮች ለአስቸኳይ ስብሰባው ከሚቀርቡ አጀንዳዎች መካከል፣ እስካሁን እንደሚታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሚያቀርቡትን የካቢኔ አባላት ሹመት መርምሮ ማፅደቅ እንደሆነ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ ከሚያቀርቧቸው ተሿሚዎች መካከል ሦስቱ በምክር ቤቱ ሳይሾሙ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጧቸው የሹመት ደብዳቤ ብቻ ቢሮ ተረክበው እያገለገሉ የሚገኙት ባለሥልጣናት ናቸው።ከእነዚህም መካከል ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባነት ተነስተው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሹመት ደብዳቤ የተሰጣቸው ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ይገኙበታል።በተመሳሳይ ወቅት ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትርነት ተነስተው የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሹመት ደብዳቤ የተሰጣቸው አቶ ሳሙኤል ሁርካቶና የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ለማ መገርሳ በመተካት የተሾሙት ቀንአ ያደታ (ዶ/ር) ናቸው።

[ሪፖርተር]
@YeneTube @FikerAssefa
በሳውዲ እስር ቤቶች የሚገኙ ስደተኞች ሁኔታ አሳሳቢ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የስደትድርጅት ገለፀ።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ከጀኔቫ ትናንት ባወጣው ዘገባ በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት የታሰሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሰብዓዊ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱን አሳስቧል።
በቅርቡ በተሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል የሰዎች መጨናነቅ ፣ለሰዎች የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ዕቃዎች እጥረት እና የጤና እና የንፅህና አጠባበቅ ሁኔታዎችን እንዲሁም የእርዳታ ልመናዎች ድርጅቱ መመልከቱን ጠቅሷል።ስደተኞች በተለይም ለእስር የተዳረጉት ከሚያጋጥማቸው መድልዎ ፣ የውጭ ዜጎች ጥላቻ ፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የጉልበት ብዝበዛ አደጋ በተጨማሪ ከጎርጎሪያኑ 2020 መጀመሪያ ጀምሮ በድንገት ለተከሰተው የኮቪድ -19 በሽታ ተጋላጭነታቸውም ጨምሯል ሲል አይ ኦ ኤም ገልጿል።

ስለሆነም ሀገራት ምንም ይሁን ምን በሁሉም ለህዝብ የጤና በሚሰጡ ምላሾች ስደተኞችን ማካተታቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡በእንደዚህ ያሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የስደተኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ የአስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲያገኙ ድርጅቱ ተማፅኗል፡፡ይህ ድጋፍ ከመጡበት ሀገር የሚደረግን ዘላቂ የመልሶ ማቋቋምንና በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው የመመለስ አማራጮችን እንደሚያጠቃልል አመልክቷል።ከዚህ በተጨማሪ ስደተኞችን በግዳጅ መመለስና በኮቪድ-19 ሰበብ በአንድ አካባቢ ማጎር እንዲገታ ዓለም አቀፉ የስደት ድርጅትና እና የተባበሩት መንግስታት የስደት ትስስር ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህ ይልቅ ለህፃናት፣ ለቤተሰብ አባላትና ተጋላጭ ለሆኑ ስደተኞች ቅድሚያ በመስጠት ማህበረሰብን መሠረት ያደረጉ አማራጮችን እንዲጠቀሙ መክረዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ከታጣቂ ሀይሎች ጥቃት እራሳቸውን ለመጠበቅ በሚል በጫካ ውስጥ ተሸሽገው የነበሩ ከ300 በላይ ዜጎች ወደ ቄያቸው ተመለሱ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በታጣቂ ሀይሎች ከተሰነዘረው ጥቃት ሸሽተው በጫካ ውስጥ ተደብቀው የነበሩ 12 የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ከ 310 በላይ ንፁሀን ዜጎች በፌደራልና በክልል የፀጥታ ሀይሎች በተሰራ ኦፕሬሽን ወደ ቄያቸው መመለሳቸው ተገለፀ፡፡በቅርቡ ጳጉሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ኤርታል ቀበሌ ላይ በታጣቂ ሀይሎች በተሰነዘረ ጥቃት የአካባቢው ሰላማዊ ሰዎችን እና በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች ወደ ጫካ ተበታትነው እንደነበረ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ነጋ ጃራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ እንዳሉት 12 የጤና ባለሙያዎች እና የልማት ጣቢያ ሰራተኞች በወቅቱ ከተፈጠረው ጥቃት በመሸሽ በጫካ ውስጥ እራሳቸውን ደብቀው መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡ሆኖም በፌደራልና በክልል የፀጥታ ሀይሎች በተሰራ ኦፕሬሽን በህይወት ተገኝተው ወደ ቀበሌያቸው እንዲመለሱና ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲመሩ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡ከዚህ ባሻገር 300 የሚሆን ንፁሀን የማህበረሰብ ክፍሎች በተመሳሳይ ከጥቃቱ ሸሽተው በቀበሌው በቅርብ እርቀት ወደሚገኝ ጫካ እራሳቸውን የሸሸጉ መሆኑን ገልፀዋል ም/ል ኮሚሽነር ነጋ።እነዚህንም ዜጎች ወደ ቄያቸው መመለስ መቻላቸውን እና ሰላማዊ ህይወታቸውን እንዲመሩ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡ታጣቂዎቹን የመደምሰስ ስራው በመካሄድ ላይ ነው ያሉት ኮሚሽነር ነጋ በጫካ እራሳቸውን የደበቁ ንፁሀን ዜጎችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ነግረውናል፡፡

ሙሉ በሙሉ የኦፕሬሽን ስራው እንደተጠናቀቀ በተደራጀ መልኩ ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ የተፈጠረውን ተመሳሳይ ጥቃት ለመቀልበስ የፌደራልና የክልል የፀጥታ ሀይሎች ገብተው የተቀናጀ የወንጀል መከላከል ስራ ተጀምሯል ብለዋል፡፡ሙሉ የኦፕሬሽን ስራው እንደተጠናቀቀ መረጃው ለህዝብ ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡ በመተከል ዞን ቡለን እና ወንበራ ወረዳ ላይ የፀጥታ ችግር ከመከሰቱ በፊት በጉባ ወረዳም እነዚህ የታጠቁ ሀይሎች ገብተው በንፁሀን ዜጎች ላይ ጥቃት መሰንዘር የጀምረው እንደነበር ይታወቃል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች የተያዘ የመጀመሪያ ኢንደስትሪ ፓርክ ግንባታ ተጀመረ!

ከ30 አመት በፊት ተገንብቶ የነበረውን የሀዋሳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ከ 3 አመታት በፊት የገዙት 3 ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች በፋብሪካ ግቢው ውስጥ የአልባሳት ኢንደስትሪ ፓርክ ግንባታ በይፋ አስጀምረዋል፡፡ይህም በኢትዮጵያውያን የተያዘ የመጀመሪያው ፓርክ የሚደርገው ሲሆን፡፡ በአልባሳት ዘርፍ የሚገኝ የመጀመሪያው የግል ኢንደስትሪ ፓርክ ይሆናል፡፡የፓርኩ ስራ 14 ባለ 11ሺ ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ሼዶች የሚኖሩት ሲሆን፡፡በፓርኩ እነደ ጋፕ የመሰሉ ታዋቂ አለም አቀፍ የልብስ ብራንዶች እንደሚገቡ ይጠበቃል ሲሉ የሀዋሳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እና ኢንደስትሪ ፓርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና አንደኛው ባለድርሻ አቶ አህመድ አብደሩፍ ተናግረዋል፡፡የፓርኩ ኢንቨስትመንት አንድ ቢሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ድጋፍ እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡ግንባታውን ሲኖማ ኢንጂነሪንግ የተባለ የቻይና መንግስት የግንባታ ድርጅት እያከናወነው ሲሆን በቀጣይ አንድ አመት ግዜ ውስጥ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ሲኖማ በኢትዮጵያ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታን እንዲሁም የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ማስፋፊያን ጨምሮ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እውን ያደረገ ነው፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ለጃዋር መሐመድ የሳተላይት መሳሪያ በመግጠም የተከሰሱት አቶ ሚሻ አደም ዛሬ በነበራቸው ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ። አቶ ሚሻ ትላንት በዋስትና ከእስር መፈታታቸው ቢነገርም፤ ጠበቆቻቸው ግን በድጋሚ መታሰራቸውን መስማታቸውን ዛሬ ለችሎት ገልጸዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
ዓለም አቀፍ የኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር 29 ሚሊዮን ደርሷል!

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ29 ሚሊዮን በላይ ማለፉንና 935ሺ ሰዎች መሞታቸውን የጆን ሆፕ ኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመለክታል፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 20 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ማገገም ችለዋል፡፡በቻይና እስካሁን 85ሺ ሰዎች በኮሮና ምክንያት የተጠቁ ሲሆን 4743 ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን ይፋ አድርጋለች፡፡ የቫይረሱ መነሻ ከሆነችው ቻይና በላይ በአሜሪካ፣ በህንድና በሩሲያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተጠቅተዋል፡፡በህንድ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ5 ሚሊዮን በላይ የደረሰ ሲሆን በአሜሪካ ደግሞ 6.6 ሚሊዮን ሰዎች ተጠቅተዋል፡፡እስካሁን 195ሺ በላይ አሜሪካውን በኮሮና ቫይረስ አጥተዋል፣ ይህም ከሌሎች ሀገራት አንጻር ከፍተኛ የሞት መጠን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ግብርና እና ለአርሶ አደሮች ድጋፍ የሚውል የ80 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ማጽደቁን አስታወቀ።ባንኩ በድረ ገጹ ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳስታወቀው፣ እርዳታው የኢትዮጵያን ግብርና ምርት ለማሰደግ እና በእፕነስተኛ ማሳ ለሚተዳደሩ ለአርሶ አደሮች የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚውል ነው።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ላይ የተከፈተው መዝገብ ላይ ለመበየን ቀጠሮ ሰጠ!

በዋስትና እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው በኋላ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች በድጋሜ ታስረው ከሀጫሉ ግድያ በኋላ አመፅ አስነስተዋል በሚል ሌላ የምርመራ መዝገብ የተከፈተባቸው በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ለመስከረም 7/2013 ዓ/ም ለብይን ተቀጠሩ።

ከሕዳር 12/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአሥራት ሚዲያ ላይ በተሰሩ ዘገባዎችና ፕሮግራሞች ምክንያት ኦሮሚያ ውስጥ አመፅ ተነስቶ በሰው ሕይወት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ደርሷል በሚል ተጠርጥረዋል ተብለው በቀጠሮ ከተመላለሱ በኋላ የዋስትና መብታቸው ሲከበር፣ ከእስር ቤት እንደወጡ እንደገና መታሰራቸው ይታወሳል። የአሥራት ጋዜጠኞች በድጋሜ የተከፈተባቸውን መዝገብ ከቀደመው ጉዳይ የተለየ አይደለም ብለው በመከራከራቸው ፍርድ ቤቱ የፖሊስና የፍርድ ቤቱን መዝገብ መርምሮ በድጋሜ የተከፈተባቸው መዝገብ ከቀደመው የተለየ ስለመሆን አለመሆኑ ለመበየን ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ ነበር። የቀደሙት የፖሊስና የፍርድ ቤት መዝገቦች ከቀጠሮው ቀደም ብለው በድጋሜ ከተከፈተባቸው መዝገብ ጋር እንዲያያዙ አራዳ መጀመርያ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ መዝገቦቹን ያያያዘው ዛሬ ጠዋት መሆኑን ተናግሯል።

በዚህም ምክንያት ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት እንዳልቻለ ተገልፆአል። ፍርድ ቤቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ሌላ መዝገብ የተከፈተባቸው ባለፈው ዋስትና ባገኙበት ተመሳሳይ ጉዳይ ነው ወይንስ አይደለም የሚለውን ለመበየን ለመስከረም 7/2013 ዓ/ም ከሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል።

[Asrat Media House]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ለጃዋር መሐመድ የሳተላይት መሳሪያ በመግጠም የተከሰሱት አቶ ሚሻ አደም ዛሬ በነበራቸው ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ። አቶ ሚሻ ትላንት በዋስትና ከእስር መፈታታቸው ቢነገርም፤ ጠበቆቻቸው ግን በድጋሚ መታሰራቸውን መስማታቸውን ዛሬ ለችሎት ገልጸዋል። [Ethiopia Insider] @YeneTube @FikerAssefa
ዋስትና ተፈቅዶላቸው የነበሩት አቶ ሚሻ አደም በድጋሚ ታስረዋል ተባለ!

በትላንትናው ዕለት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለአቶ ሚሻ አደም የመፈቻ ትዕዛዝ ጽፎላቸው እንደነበር አንድ የቤተሰብ አባል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል። እኚሁ የቤተሰብ አባል የመፈቻ ትዕዛዙን ይዘው ተከሳሹ ወደ ታሰሩበት አዲስ አበባ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢያመሩም በጥበቃ ላይ በተሰማሩ ፖሊሶች መለቀቃቸው እንደተነገራቸው አብራርተዋል።ዘግይቶም አቶ ሚሻ ከእስር ከወጡ በኋላ በኦሮሚያ ፖሊስ እንደተወሰዱ መስማታቸውን አክለዋል።የተከሳሹ ጠበቆችም ተመሳሳይ መረጃ እንደደረሳቸው ዛሬ ለችሎት አቤት ብለዋል።

የአቶ ሚሻን የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል ክስ የሚመለከተው 20ኛ ወንጀል፤ በአቶ ሚሻ ላይ የሚመሰክሩ ምስክሮች ማንነት እንዳይገለጽ አቃቤ ህግ ላቀረበው አቤቱታ፤ የተከሳሽ ጠበቆች የሚሰጡትን አስተያየት ለማድመጥ ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፤ አቤቱታውን ቅድሚያ ሰጥቶ ተመልክቷል።ጉዳዩን በጽህፈት ቤት የተመለከተው ችሎቱ፤ “ተከሳሹ ተለቅቋል ተብሎ ቢገለጽም ለኦሮሚያ ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል” መባሉን ከግራ ቀኙ ክርክር መረዳቱን ገልጿል። በዚህም ላይ በመመስረት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የኦሮሚያ ፖሊስ በፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳዩን እንዲያስረዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ከ300 በላይ ሰዎች በንጹሀን ዜጎች ግድያ ተጠርጥረው ተያዙ።

ከሰሞኑ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን በንፁን ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ የነበሩ ከ304 የሚደርሱ የፀረ-ሰላም ሀይሎች መታሰራቸውን የቡኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ነጋ ጃራ እንደገለፁት በመተከል ዞን ገብተው ጥቃት ሲሰነዝሩ የነበሩ ታጣቂ ሀይሎችን የመደምሰስና የመምታት ኦፕሬሽን በፌደራልና በክልሉ የፀጥታ ሀይሎች እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በዚህም እስካሁን የመደምሰስ እርምጃ የተወሰደባቸው ታጣቂ ሀይሎች እንዳሉ ሆነው ወደ 304 የሚደርሱ የጥቃቱ ተዋንያንን በቁጥጥር ስር ማድረግ ተችሏል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ያዋልናቸው እነዚህ ግለሰቦች በዞኑ ጥቃት ሲያደርሱ የነበሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ኮሚሽነር ነጋ በአሁኑ ሰዓት በእስር ቤት ሆነው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ መሆኑን አንስተዋል፡፡ከዚህ ባሻገር በመተከል ዞን የተሰመማራው የፀጥታ ሀይል ታጣቂዎቹ ለወንጀሉ ይጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡የፀጥታ ሀይሉ 33 የተለያዩ ጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን 100 የክላሽ ጥይቶችም ይዟል ብለዋል፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም 293 የብሬን ጥይቶች እና ለወንጀል ተግባር ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተጨማሪ 3 ኤግዚቢቶች በቁጥጥር ስር አድርገናል በማለት ገልፀዋል፡፡በዞኑ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ታጣቂ ሀይሎች እየወሰዱ ያሉት ጥቃት ንፁሀንን ያነጣጠረ ነው ያሉት ኮሚሽነር ነጋ ብሔርን ያነጣጠረ ተደርጎ የሚነዛው የሀሰት መረጃ በመሆኑ ይህንን የሚያሰራጩ ሀይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል፡፡

በመተከል በሁሉም ወረዳዎች የተሰማራው የፌደራልና የክልል የፀጥታ ሀይል ታጣቂዎቹን የመምታትና የመደምሰስ ተግባሩን አንደቀጠለ መሆኑን ሀላፊው አረጋግጠዋል፡፡በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች እና በፀጥታ ሀይላችን የተደመሰሱ ታጣቂዎችን የተመለከተ ኦፕሬሽኑ ገና ያልተጠናቀቀ በመሆኑ እርሱ ሲጠናቀቅ በተደራጀ መልኩ ትክክለኛውን መረጃ ለህዝብ እናሳውቃለን ብለዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በሳኡዲ አረቢያ ጂዳ ከተማ በተለያዩ ችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 247 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ዛሬ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

@YeneTube @FikerAssefa