የአሜሪካ ኮንግረስ የትራንስፖርት ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ ለደረሰው የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ የአሜሪካ መንግስት ተቆጣጣሪ አካል ግድፈት፣ የአውሮፕላን ዲዛይን ችግር እንዲሁም የቦይንግ ኩባንያ አውሮፕላኑ ችግር እንዳለበት እያወቀ እርምጃ አለመውሰዱ ያስከተለው መሆኑን ዛሬ አስታውቀዋል።
የኮሚቴው አጥኚ ቡድን ቦይንግ MCAS ስለተባለው ሶፍትዌር በተደጋጋሚ መረጃዎችን ከአሜሪካው የበረራ መቆጣጠርያ መምሪያ እና ከአየር መንገዶች እንደደበቀ ይፋ አርጓል። የ246 ገፅ ሪፖርቱ ከዚህ በፊት በተለያዩ ሚድያዎች ሲፃፍ የነበረውን የፓይለቶች ግድፈት ለአደጋው መንስኤ ሊሆን ይችላል የሚለውን ግምት እንደ ምክንያት አላቀረበም።
[Elias Meseret & AP]
@YeneTube @FikerAssefa

ኢጋድ በአዲስ አበባ የካንሰር ህክምና ማዕከልን ሊያቋቁም ነው!
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ድርጅት (ኢጋድ) በአዲስ አበባ ቀጣናዊ የካንሰር ህክምና ማዕከልን ሊያቋቁም መሆኑን አስታወቀ፡፡ድርጅቱ የአደጋ መከላከል ማስተባበሪያ ተቋምን በኬንያ ናይሮቢ እንደሚከፍትም ገልጿል፡፡በራሽያ ሞስኮ ጉብኝት ያደረጉት የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የማዕከላቱን ግንባታ በማስመልከት ከሚመለከታቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ውይይቱ ፍሬያማ እንደነበርም በማህበረሰብ የትስስር ገጾቻቸው አስታውቀዋል፡፡
[Al ain]

👆👆
ከምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ የተሰጠ
መግለጫ!
በምዕራብ ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የፀጥታ ችግሮችን የማስተካከል እና የቀጠናውን ሰላም የማስጠበቅ ተግባር የሚወጣው የምዕራብ ዕዝ ፣ በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር ከተሰጡት ቀጠናዎች መካከል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አንዱ ነው፡፡ ከሰሞኑም በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ውስጥ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር የማረጋጋት እና የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራዎች በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ በቡለን ወረዳ ኤጳራ ቀበሌ ውስጥ ሞጂ እና ኮሼቦንጂ በሚባሉ መንደሮች የአካባቢውን ሰላም በማደፍረስ በህዝቦች መሃል የእርስ በርስ ግጭቶችን ቀስቅሶ አካባቢውን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ ያለሙ ኃይሎች ነሃሴ 29 እና 30 ምሽት ላይ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡
የድርጊቱን መፈፀም ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው እንዲሰማራ የክልሉ መንግስት በጠየቀው መሰረት ጳጉሜ 1 ቀን 2012 ዓ/ም ወደ ቦታው የተንቀሳቀሰው ሰራዊታችን ፣ በኤጳራ ቀበሌ ውስጥ አሰሳ በማድረግ በአጥፊዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ወስዷል፡፡በቡድኑ ታግተው የነበሩ 27 ንፁሃን ዜጎችንም ማስለቀቅ የቻለ ሲሆን ፣ አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ሰራዊታችን የስምሪት ቀጣናውን በማስፋት በቡለን ፣ በወንበራ ፤ በጉባ፤ በዲባጢ ፤ በዳንጉር እና በማንዱራ ወረዳዎች የድርጊቱ ፈፃሚዎችን የመቆጣጠር እና አካባቢውን የማረጋጋት ስራ በስፋት በመስራት ላይ ነው፡፡
በየደረጃው ከሚገኙ የክልሉ የመስተዳድር አካላት ፣ የፀጥታ ሃይሎች እና ከህብረተሰቡ ጋር በጥምረት በተሰሩ ስራዎችም አሁን ላይ አካባቢው ወደ ተረጋጋ ሁኔታ በመመለስ ላይ ነው፡፡ሰራዊታችን መስዕዋትነት በመክፈል ጭምር አካባቢውን እና ክልሉን ለማተራመስ ባለሙ ሃይሎች የተቀሰቀሰውን ግጭት አስቁሟል፡፡
እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ግን በአንዳንድ ድረ-ገፆች እና ሚዲያዎች ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት እየተሰራጩ ያሉት የሰራዊታችንን መልካም ስም የሚያጎድፉ ፣ እውነታን ያላገናዘቡ እና ግጭትን የሚያባብሱ ዘገባዎች ተገቢነት የሌላቸው በመሆናቸው ፣ ይህን የሚያደርጉ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡ሰራዊታችን በህዝባችን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ፈፅሞ በቸልተኝነት እንደማይመለከት ማስገንዘብም እንወዳለን፡፡በዚሁ ቀጣና የተለያዩ ግጭቶችን በመቀስቀስ የሃገራችንን ሰላም ለማደፍረስ እና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችንን የግንባታ ሂደት ለማስተጓጎል የሚጥሩ የሀገር ውስጥም ይሁን የውጭ የፀረ-ሰላም ሃይሎችን ለመቆጣጠር ዕዛችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡
በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ በተፈፀሙት ጥቃቶች ህይወታቸውን ባጡት የህብረተሰባችን ክፍሎች ፣ የምዕራብ ዕዝ የተሰማውን ልባዊ ሃዘን እየገለፀ ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የዞን እና የወረዳ የመስተዳድር አካላትን ጨምሮ የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች እና ህብረተሰቡ ለአካባቢው ሰላም ላበረከታችሁት አስተዋፅኦ የምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ያለውን አክብሮት ይገልፃል፡፡
የምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
6/01/2013 ዓ.ም ነቀምቴ

የጤና ሚኒስቴር ትምህርት ለመጀመር የሚስችል ሁኔታ መኖሩን ሲያረጋግጥልን ትምህርት እንጀምራለን፡- የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.)
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገምግሞ ትምህርት ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን የጤና ሚኒስቴር ማረጋግጫ ሲሰጥና መንግስት ውሳኔ ሲያሳልፍ ትምህርት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ከትምህርት ገበታ ውጪ ያሉ ህፃናት በከፍትኛ ሁኔታ እየተጎዱ በመሆኑ ለእነሱ ቅድሚያ እንደሚሰጥም ነው ያብራሩት፡፡ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ለ6 ወር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህፃናት ከዚያ በፊት ለሁለት አመታት ያክል ይዘውት የነበረውን እውቀት ሊያሳጣቸው ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት ለህፃናት ቅድሚያ ለመስጠት እቅድ ተይዟል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየውም ህፃናት በኮሮና ቫይረስ የመያዝና የማስተላለፍ ባህሪያቸው ከሌሎቹ የቀነሰ በመሆኑ ድርጅቱ የሚያስቀምጣቸውን የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ሙሉ ለሙሉ በመተግበር ትምህርት ለመጀመር ጥረት ይደረጋል፡፡በትምህርት አከፋፈት ዙሪያ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታበተስፋፋባቸው እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ትምህርት በ3 ፈረቃ ለመጀመር እቅድ ተይዟል፡፡ከትላልቅ ከተሞች እርቀው የሚገኙና የቫይረሱ ስርጭት ስጋት በሌለባቸው አካባቢዎችም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንግዶችን በመተግብር ትምህርት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
[MoE]

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ተከብሮ ይውላል! - አባ ገዳዎች
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ተከብሮ እንደሚውል አባገዳዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።በዚህም የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 በአዲስ አበባ ፣ የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ደግሞ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም በቢሾፍቱ እንደሚከበር አባገዳዎቹ ገልጸዋል፡፡አባ ገዳዎቹ የኢሬቻ በዓል በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በሚታደሙበት ሲከበር መቆየቱን አስታውሰው ÷ የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ግን የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ከግምት ባስገባ መልኩ እንደሚከበርም ነው የገለጹት።በኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥር በሽታውን ለመከላከል እና የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት ምክር መሰረት የሚወሰን መሆኑ ተገልጿል።አባገዳዎቹ አያይዘውም የገዳ ስርዓት ባለቤት የሆነው የኦሮሞ ህዝብም ይህንን ከግምት በማስገባት በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ ማቅረባቸውን ከኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያኘነው መረጃ ያመላክታል።
[FBC]

በአፋር ክልል አብአላ ከተማ ከፖሊስ በተኮኮሰ ጥይት 3 ሰዎች ሲሞቱ ከ10 በላይ መቁሰላቸውን አንድ የአይን አማኝ ተናገሩ::
የአካባቢው ነዋሪ ወጣቶች ለመስቀል ዳመራ ዝግጅት አንጨት ለቅመው ወደከተማዋ ሲገቡ የክልሉ ልዩ ኃይል በከፈተው ተኩስ 3 ሰዎች ሲሞቱ ከ 10 በላይ ቆስለው 40 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው መቀሌ ከተማ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአይን አማኙ ለDW ተናግረዋል::በአሁኑ ሰዓት የመከላከያ ሰራዊት ገብቶ አያረጋጋው ቢሆንም አስከ ቀኑ 8 ሰዓት ረብሻዎች አንደነበሩ ለማወቅ ትችሏል።
በጉዳዩ ተጭማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ወደክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ስልክ ቢደወልም ስልካቸው ሊሰራ አልቻለም::በአሁኑ ሰዓት የአገር ሽማግሌዎች ነገሩን ለማብረድ አየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ታውቋል።
[DW]

በአዲስ አበባ ከባድ ተሽከርከሪዎችን ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽት 2፡00 ሰዓት ወደ ከተማዋ ማስገባትና ማንቀሳቀስ ከ5 መቶ እስከ 6 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው ከዚህ ቀደም የከባድ ተሽከርካሪዎችን የሰዓት ገደብ አንስቶ የነበረ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽት 2፡00 ሰዓት ከባድ ተሽከርከሪዎች በከተማዋ ማንቀሳቀስ እንደማይቻል ማሻሻያ አድርጓል።በተጨማሪም በሥራ መውጫ ሰዓታት ላይ የሚታየውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ ለመቀነስ የከባድ ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ መወሰን የሚያስችለውን መመሪያ ተግባራዊ ማድረጉ አስፈልጓልም ነው የተባለው፡፡በዚሁም መሰረት የመጫን አቅማቸው ከ2.5 ቶንና ከዚያ በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎች እንደጥፋቱ ክብደትና ድግግሞሽ ከብር 5 መቶ እስከ 6 ሺህ እንዲሁም በተደራቢነት ከ1 እስከ 3 ወር የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እንደሚያግድ መመሪያው ያትታል።
የቢሮው ኮምንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ እንዳሉት የመንቀሳቀሻ ፈቃድ ሳያወጡ በተከለከለው ሰዓት ከባድ ተሽከርካሪን ወደ ከተማዋ ማስገባትና በከተማዋ ውስጥ ማንቀሳቀስ እንዲሁም በዋና መንገድ ላይ ጭነት መጫንና ማውረድ ተግባር የፈፀመ ለመጀመሪያ ጊዜ ብር 1 ሺህ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ብር 2 ሺህ እንዲሁም ከሁለት ጊዜ በላይ ድርጊቱን ከፈፀመ 3 ሺህ ብር ተቀጥቶ የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ ለአንድ ወር እንዲታገድ በመመሪያው ተቀምጧል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ጊዜ ያለፈበት የመንቀሳቀሻ ፈቃድ ይዞ ወደ ከተማዋ ማስገባት ወይም በከተማዋ ውስጥ ማንቀሳቀስ ለመጀመሪያ ጊዜ ብር 500 እና ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ብር 1 ሺህ፤ ድርጊቱ ለሶስተኛ ጊዜ ከተፈፀመ ብር 4 ሺህ ተቀጥቶ የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ ለ2 ወር ይታገዳልም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የተሰረዘ ወይም የተደለዘ ወይም አስመስሎ የተሰራ የመንቀሳቀሻ ፈቃድ ይዞ መገኘትና መጠቀም እንዲሁም የመንቀሳቀሻ ፈቃዱን ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት ብር 6 ሺህ እንደሚያስቀጣ ነው አቶ አረጋዊ የተናገሩት።በመሆኑም የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የተከለከለውን ሰዓት ታሳቢ በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅንና አደጋን ለመቀነስ ትብብር እንድታደርጉ ቢሮው ጠይቋል፡፡
[Ethio FM]

የጃፓን መንግሥት በተፈጠሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን የሚውል ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አደረገ።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ጃፓን በኢትዮጵያ የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ያደረገችውን የ30.24 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጓል፡፡የአደጋ ስጋትና ስራ አመራ ኮሚሽ፤ የጃፓን ኤምባሲ እንዲሁም የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ በጋራ ባኬዱት የቨርችዋል ውይይት ይፋ የተደረገው ድጋፉ ወቅቱን የጠበቀ መሆኑም ተነስቷል፡፡በጎርፍ፣ በአንበጣ መንጋ፣ በድርቅና በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት እንደሚኖርም ተነግሯል፡፡በዚህም በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በደቡብና በትግራይ ክልሎች የሚገኙ ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተደራሽ የሚሆኑ ሲሆን ድጋፉ በአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን አማካኝነት እንደሚሰራጭ ነው የተገለጸው፡፡
ምንጭ፡- ኢዜአ

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ከነገ ጀምሮ የሚተገበር የአሰራር ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።
ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ጥሬ ገንዘብን ሥርዓት ለማስያዝ ሲባል መንግስት የተለያዩ የማሻሻያ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ይህንኑ ተከትሎ ህገወጥነትን ለመከላከል እና ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን ሲባል ከነገ መስከረም 07 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ኤጀንሲው ባደረገው የአሰራር ማሻሻያ መሰረት የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኤጀንሲው የሚመጡ ተገልጋዮች የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው መፈጸም ያለበት፡-
👉 በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት፡፡
👉 በብድር ውል ጊዜ የብድሩ ገንዘብ ባንክ ከሚገኝ የአበዳሪ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ተበዳሪ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት፡፡በመሆኑም የሽያጩ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ ክፍያው ከላይ በተገለጸው አግባብ የተፈጸመ ስለመሆኑ የሚገልጽና በባንኩ ማህተም የተደገፈ የሂሳብ ማስተላለፊያ (Bank Transfer Slip) የሰነድ ማስረጃ መቅረብ ያለበት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በተጨማሪም ህገወጥነትን ለመከላከል ሲባል ሌሎች የአሰራር ማሻሻያዎች እስኪደረጉ ድረስ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ኤጀንሲው ላልተወሰነ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
[የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ]

በኢትዮጵያ ከ1,300 በላይ የጤና ባለሙያዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ከ1 ሺህ 300 በላይ የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ሚኒስቴሩ በነገው ዕለት የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሕሙማን ደህንነት ቀንን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴሩ የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ ሰማን እንዳሉት ኮሮናቫይረስን በመከላከል ሥራ ግንባር ቀደም የሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ላይ መጠነ ሰፊ ችግር አስከትሏል።በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 1 ነጥበ 3 ሚሊዮን የሚሆኑት የጤናው ሴክተር ሠራተኞች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
“በኢትዮጵያም ኮቪድ-19 ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 1 ሺህ 311 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 700 የሚሆኑት ደግሞ አገግመው ወጥተዋል፤ ቀሪዎቹ በህክምና ተቋማት ይገኛሉ” ብለዋል አቶ ያዕቆብ።ሁለት የሕክምና ባለሙያዎችም ለሞት መዳረጋቸውን ነው ያስታወሱት።ነገ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቱ የሚከበረው የሕሙማን ቀንም ቫይረሱ የተገኘባቸው ወገኖቻቸውን ሌት ተቀን እያገለገሉ ላሉ ባለሙያዎችና አጋሮቻቸው ክብርና ምስጋናን በመስጠት እንደሚከበር ተናግረዋል።በዓሉ የጤና ባለሙያዎች በሥራ ላይ የሚገጥማቸውን ችግር በመፍታትና በማገዝ እንዲሁም ራሳቸውን ከበሽታ ጠብቀው ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ በሚያደርጉ ፕሮግራሞች የሚከበር መሆኑንም ነው አቶ ያዕቆብ ያመለከቱት።የጤና ባለሙያዎች ደህንነት እንዲጠበቅ የሚያስችል ሳይንሳዊ የሆኑ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው የሚመለከታቸው አካልት እንዲወያዩበት የሚደረግበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
[ENA]

በንጹኃን ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ኃላፊነቱን እንዲወስዱ የአማራ መማክርት ጉባኤ ጠየቀ።
በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸሙ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዲቆሙ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምሁራን መማክርት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ። ጉባኤው በተለይም በአማራ፣ አገውና ሌሎች ሕዝቦች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም የሚጠይቅ መግለጫ አውጥቷል።የፌዴራል መንግሥትና የተለያዩ ክልል መንግሥታት ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚኖሩ የአማራ፣ አገውና ሌሎች ሕዝቦች ላይ እየደረሰ ያለውን ማንነትን መሠረት ያደረገ የተቀናጀ ተደጋጋሚ ጥቃት ከመደረሱ በፊት ቀድመው የመከላከል ግዴታቸውን አለመወጣታቸው እንዳሳዘነውና ድርጊቱ በማንኛውም ምክንያት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የምሁራን መማክርት ጉባኤው ገለፀ፡፡
ለዚህ ዓይነቱ ጥቃት መፈጸም የፌዴራል መንግሥትና የሚመለከታቸው የክልል መንግሥታት ኃላፊነቱን ሊወስዱ እንደሚገባም የመማክርት ጉባኤው ጠይቋል፡፡"ለዚህ ዓይነቱ ተዳጋጋሚ አሰቃቂ ብሔር ተኮር ጥቃት ተጋላጭ የመሆናቸው መሠረታዊ ምክንያትም በሚኖሩባችው አካባቢዎች የግለሰብ እና የቡድን መብታቸው አለመከበር፣ ተገቢው የፖለቲካ ውክልናና አዳረጃጀት እንዲኖራችው አለመደረጉ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል" ሲል መማክርቱ አስተውቋል፡፡ ሰሞኑን ቤኔሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ላይ የተፈጸመው አሳዛኝ ክስተት ለዚህ አንዱ ማሳያ መሆኑንም አብነት ጠቅሷል፡፡
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ለዚህ ዓይነቱ አሳዛኝ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት በተደጋጋሚ ሰለባ መሆናቸውን መማክርቱ አስታወሶ፤ ይህ ዓይነቱ ጥቃት በአማራ ላይም ሆነ በሌሎች ሕዝቦች ላይ በድጋሜ እንዳይፈጸም እና በማንኛውም አካባቢ ሰብዓዊ መብቶቻችው እና ክብራቸው ተጠብቆ መኖር የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለዜጎች መሠረታዊ መብቶች መከበር የሚታገሉ የፖለቲካ ኃይሎች እና የሲቪክ አደረጃጀቶቸ በዚህ አጀንዳ ላይ ቅድሚያ ሰጥተውና አበክረው በመሥራት ተገቢውን ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲያስገኙ መማክርቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
"የፌዴራል መንግሥቱ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች ማንነትን መሠረት ላደረገ ጥቃት እንዳይገለጡ እና መሠረታዊ የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህላዊ መብቶቻቸው ተክብረው መኖር ይችሉ ዘንድ ልዩ ጥበቃ የሚሰጥ የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት እና ተቋማትን በመዘርጋት አስተማማኝ እና ሁለንተናዊ የደኅንነት ዋስትና በማረጋገጥ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል" ሲል መማክርቱ አሳስቧል፡፡ለተጎጅዎች ባሉበት እንዲቋቋሙ መንግሥት እና ሌሎች አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲደርጉላቸውም መማክርቱ ጠይቋል፡፡
[AMMA]

አቶ ልደቱ አያሌው ጠበቆቻቸውን አሰናበቱ!
የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት የወከሏቸውን ጠበቆች አሰናበቱ።አቶ ልደቱ እርምጃውን የወሰዱት ከዚህ በኋላ በከተማው ፍርድ ቤት የህግ ክርክር ማድረግ ባለመፈለጋቸው እንደሆነ ዛሬ ረቡዕ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል። ከዚህ በኋላ የሚካሄደውን ክርክር “ትርጉም የሌለው” ሲሉ የጠሩት አቶ ልደቱ፤ “ህግ የፖለቲካ መሳሪያ በሆነበት ሁኔታ በህግ ክርክር መብትን ማስከበር ስለማይቻል ከአሁን በኋላ ግዴታዬን ለመወጣት ቀጠሮ ሲሰጠኝ በችሎት ፊት ከመገኘት ባለፈ የህግ ክርክር የማድረግ ፍላጎት የለኝም” ሲሉ በፓርቲያቸው በኩል ባሰራጩት ደብዳቤያቸው አስፍረዋል።
[ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 738 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 8,355 የላብራቶሪ ምርመራ 738 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ10 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1045 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 677 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 26,665 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 66,224 ደርሷል፡፡

በሊባኖስ ይኖሩ የነበሩ 94 ኢትዮጵያውያን ትናንት መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ወደ አገር ቤት ተሸኝተዋል፡፡
ትናንት የተሸኙትም ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ አገር ቤት ይገባሉ፡፡ ኢትዮጵያውያኑ በሊባኖስ እስር ቤቶች የነበሩ፣ ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ፣ በቤሩት ወደብ ፍንዳታ መጠለያ ያጡና ችግር ላይ የነበሩ፤ እንዲሁም በአሰሪዎች በደልና የመብት ጥሰቶች፣ የአካልና የስነ-ልቦና ጉዳት የደረሰባቸው እና መጠለያና ምግብ ያጡ የነበሩ ናቸው፡፡
ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን፣ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበርን እንዲሁም ሌሎች ድጋፍ የሚያደርጉ በጎ አድራጎት ድርጅቶችንና ግለሰቦችንም በማስተባበር መጠለያዎችን፤ የአውሮፕላን ቲኬት ወጭዎችን እና ሌሎች የተለያዩ ድጋፎችና እገዛዎች እንዲደረጉላቸው ተደርጎ የጉዞ ሰነዶቻቸው፤ የመውጫ ቪዛና መሰል ጉዳዮችን በማጠናቀቅ፤ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
በተመሳሳይ ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ማታ 27 ወደ አገር ቤት የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ይሸኛሉ፡፡
[በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ]

የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ ያለአግባብ ከታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉ የነበሩ 68 አሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ ተወሰደ።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን የስምሪት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ለአሐዱ እንደተናገሩት የትራንስፖርት ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች 120 አሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ መወሰዱን የተናገሩ ሲሆን 68ቱ ያለ አግባብ ከታሪፍ በላይ ዋጋ ሲያስከፍሉ የተገኙ ናቸው።
[አሐዱ ሬዲዮ]

ደቡብ አፍሪካ ወደ ኮሮና ቫይረስ ማንቂያ ደረጃ አንድ ተሸጋገረች!
አምስት ደረጃዎች ያሉትን የኮሮና ቫይረስ የማንቂያ ደረጃዎች (Alert Levels) ተግባራዊ ስታደርግ የቆየችው ደቡብ አፍሪካ የቫይረሱን ስርጭት መቀነስ ምክንያት በማድረግ እ.ኤ.አ ከመጪው ሴፕቴምበር 20 ቀን 2020 ጀምሮ ወደ ማንቂያ ደረጃ አንድ መሸጋገሯን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖሳ ትናንት ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ።በደቡብ አፍሪ እስካሁን በበሽታው ከ650 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ፣ ከእነዚህም 15 ሺህ ያህሉ ህይወታቸው እንዳለፈ፣ 89 በመቶ ያህሉ እንዳገገሙናና በወረርሺኙ ምክንያት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ መከሰቱን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ የበሽታውን ስርጭት በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ውጤት ተገኝቷል፣ ከእንግዲህ ትልቁ ተግዳሮት ሁለተኛ ዙር የበሽታው ስርጭት (Second Wave) እንዳይከሰት ለማድረግ የአደጋ ጊዜ አዋጁ እስከ ኦክቶበር አጋማሽ ድረስ እንዲቀጥል መወሰኑንም ተናግረዋል።
በዓለም-አቀፍ በረራዎች የተጣለው ገደብ እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 1 ቀን 2020 ጀምሮ ደረጃ በደረጃ ዝቅ እንዲል እንደሚደረግ፣ ከፍተኛ የቫይረሱ ስርጭት ካለባቸው ሀገራት የሚደረጉ በረራዎች ታግደው እንደሚቆዩ፣ ሦስት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች ማለትም ኦ አር ታምቦ፣ ኪንግ ሻካ እና ኬፕታውን ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች ብቻ ዓለም-አቀፍ በረራን ማስተናገድ እንደሚችሉ፣መንገደኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በ72 ሰዓታት ውስጥ የተደረገ የኮቪድ 19 ነጻ የምርመራ ውጤት ማቅረብ እንደሚያስፈልጋቸው፣ የበሽታው ምልክት የሚታይባቸው ተጓዦች በማቆያ እንዲቀመጡ አስታውቀዋል።እንዲሁም የዓለም-አቀፍ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው እንደሚከፈትና ቱሪስቶች ወደ ደቡብ አፍሪካ መግባት እንደሚፈቀድላቸው፣በውጪ ሀገራት የሚገኙ የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲዎች ቪዛ መስጠት እንደሚጀምሩ አመልክተዋል።
[በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ]

የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል ጋር ያለውን ቁርሾ የሚፈታበት ወቅት ከምንጊዜውም በላይ አሁን መሆኑን ዓለም አቀፉ ቀውስ አጥኚ ቡድን አሳሰበ።
የትግራይ ክልል ጳግሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው ምርጫ ገዢው ግንባር ሕወሓት 152 ወንበሮችን በማግኘት ማሸነፉን የምርጫ ኮሚሽኑ መግለጹ ይታወሳል፡፡ይህን ተከትሎ አስተያየታቸውን ለሮይተርስ የሰጡት የዓለም አቀፉ ቀውስ አጥኚ ቡድን የኢትዮጵያ ተወካይ ዊሊያም ዳቪሰን ማዕከላዊ መንግስቱና የትግራይ ክልል በአስቸኳይ ችግሮቻቸውን ተነጋግረው ሊፈቱ ይገባል ብለዋል፡፡ሕወሓት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ብርቱ ተቺ መሆኑን ያስታወሱት ዳቪሰን የፌደራል መንግስት ከክልሉ ጋር ያለውን ቁርሾ የሚፈታበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል፡፡ከወር በፊት በተመሳሳይ ይኽው የቀውስ አጥኚ ቡድን ሁለቱ አካላት አለመግባባቶቻቸውን በቶሎ እንዲያርቁ ማሳሰቡ አይዘነጋም፡፡ይህ የመፍትሔ ሀሳብ በቡድኑ በኩል ይቅረብ እንጂ የፌደራል መንግስቱ በሪፐብሊካን ጋርድ፤ ክልሉ ደግሞ በልዩ ሀይልና ሚሊሻዎች ታጅበው የሚያደርጉት ወታደራዊ ትዕይንት የእልባቱን ጊዜ እንዳያርቀው ተሰግቷል፡፡