YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የቀድሞው የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ተቋም ዋና ዳይሬክተርነት ነበሩ።

Via Fortune Newspaper
@Yenetube @Fikerassefa
ፍርድ ቤት ተከሳሽ ሚሻ ጭሪን በዋስ ከለቀቀ በኋላ ፖሊስ ተከሳሹን እስር ቤት የማቆየት ምንም ዓይነት ስልጣን ስለማይኖረው እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ህግና ህገ መንግስቱን ጭምር በማክበር ፍ/ቤቱ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት በአስቸኳይ እንዲለቅ ታዟል ሲል ከፍተኛ ፍ/ ቤት ገለጸ።ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተሰጠው ትእዛዝ የማይፈጸም ከሆነ የሚመጣውን ሃላፊነት ለመውሰድ ጭምር ተከሳሹን ይዛቹ እንዲትቀርቡ በጥብቅ ታዟል ብለዋል።

[OMN]
@YeneTube @FikerAssefa
ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ አዲስ ባንክ እያቋቋሙ ነው!

በበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ቦርድ ሰብሳቢነት የሚቋቋመው ሆሳዕና ባንክ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣውን ደንብ እና መርሆዎች በመከተል በኹለት ቢሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል በምስረታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ። በዋነኝነት በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ የደቡብ ክልል ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን አነሳሽነት በምስረታ ላይ የሚገኘው ይህ ባንክ በአገራችን ያለውን ውስን የፋይናንስ ዘርፍ በማጠንከር ስራ ላይ የራሱን የሆነ አስተዋፅዎ እንደሚያበርክት ተገልጿል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
በያዝነው ሳምንት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ ተገለፀ!

በኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊጥል እንደሚችል የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት የልህቀት ማዕከል እጠነቀቀ፡፡ማዕከሉ እንደገለጸው በተለይም በመካከለኛው እና ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊጥል ይችላል፡፡በእነዚህ ሀገራት የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋዎችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ የልህቀት ማዕከሉ አስጠንቅቋል፡፡

የዝናብ ትንበያው ከዛሬ ጀምሮ በሚቀጠሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የሚጠበቅ ሲሆን በምዕራብ እና መካከለኛው ኢትዮጵያ ጥቂት ቦታዎች ከ 200 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ ዝናብ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በጎረቤት ሀገራት ደቡብ-ምዕራብ ሱዳን፣ከሰሜን-ምዕራብ እስከ ደቡብ-ምዕራብ ደቡብ ሱዳን፣በምዕራብ እና፣ሰሜን-ምስራቅ ሶማሊያ እንዲሁም በሰሜን-ምዕራብ ዩጋንዳ እና ምዕራብ ኬንያ ከ 50 እስከ 200 ሚሊ ሜትር የሆነ መካከለኛ ዝናብ ይኖራል፡፡በሰሜን፣በምስራቅ እና በደቡብ ኢትዮጵያ፣በማዕከላዊ ሱዳን፣በሰሜን ምዕራብ ኤርትራ፣በምዕራብ እና ማዕከላዊ ደቡብ ሱዳን፣በሰሜን እና በደቡብ ሶማሊያ፣በጅቡቲ የባህር ዳርቻዎች፣ በማዕከላዊ እና በምስራቅ ዩጋንዳ አንዳንድ አካባቢዎች ከ 50 ሚሊ ሜትር በታች የሆነ ቀላል ዝናብ ይኖራል ተብሏል፡፡

እንደ የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት የልህቀት ማዕከል ትንበያ ከሆነ አብዛኞቹ፣የደቡብ ምስራቅ እና ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች፤የታንዛኒያ፣ቡሩንዲ፣ሩዋንዳ ፣ደቡባዊ ኡጋንዳ ፣ከምስራቅ እስከ ሰሜን ምዕራብ ኬንያ፣ደቡብ ምስራቅ ደቡብ ሱዳን ፣ማዕከላዊ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣እና የኤርትራ ባህር ዳርቻዎች ደረቃማ የአየር ሁኔታ ያመዝናል፡፡በሌላ በኩል በማዕከሉ የሙቀት ትንበያ መሰረት በሰሜን-ምስራቅ ኢትዮጵያ አንዳንድ ክፍሎች ፤ሰሜን ሱዳን፣የኤርትራ ባህር ዳርቻዎች፣ በጅቡቲ እና የሶማሊያ ሰሜን ምዕራብ ጠረፍ ክፍሎች ከ 32 ℃ በላይ የሆነ ከፍተኛ ዕለታዊ አማካይ የሙቀት መጠን ይጠበቃል፡፡የደቡብ-ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች ከ 20 እስከ 32 የሆነ መካከለኛ የሙቀት መጠን ሲጠበቅ፤አብዛኞቹ ደቡባዊ እና ሰሜን ኢትዮጵያ ክፍሎች ገድሞ ከ20 በታች የሆነ የሙቀት መጠን ይኖራቸዋል ነው የተባለው፡፡

[ENA & ICPAC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማኑኤል ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ አማኑኤል ከተማ በደረስ የተራፊክ አደጋ የአንድሰው ህይወት ሲያልፍ በ9ኝ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡አደጋው መስከረም 5/2013 ዓመተ ምህረት ከጠዋቱ 1፡30አካባቢ በተለምዶ ጎጃም ዱር እየተባለ በሚጠራው ቦታ ታርጋ ቁጥር 25769 ኤፍ ኤስ አር ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻና ታርጋ ቁጥር 12086 አባዱላ የሆኑ ተሸከርካሪዎች ላይ በተፈጠረ ግጭት መድረሱን የገለፁት የማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኮማነደር አምሳል ሰውነት የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ገለፀዋል፡፡

[የወረዳው መ/ኮሙኒኬሽን]
@YeneTube @FikerAssefa
ዘመናዊው የቄራ ግንባታ በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ምክንያት ተስተጓጎለ!

የአዲስ አበባ የቄራዎች ድርጅት በሃና ማርያም አካባቢ ሊያከናውነው የነበረውን ዘመናዊ የቄራ ግንባታ በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ምክንያት ግንባታውን ለመጀመር መቸገሩን ገለጸ። ባጠናቀቅነው የ2012 በጀት ዓመት ግንባታው ለማጠናቀቅ የታቀደ ቢሆንም በሕገ- ወጥ መሬት ወረራ ምክንያት ግንባታው እስከአሁን አለመጀመሩን ድርጅቱ ለአዲስ ማለዳ አስታወቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ክንደያ ገብረህይወት ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትነታቸው ተነሱ! የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ክንደያ ገብረህይወት (ፕ/ር) ከሃላፊነት መነሳታቸውን አስታወቀ፡፡ፕሬዝዳንቱ ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ ለነበራቸው አበርክቶ ያመሰገኑት ሚኒስትሩ ሳሙዔል ኡርካቶ (ዶ/ር) ከነገ ጀምሮ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የተሰጣቸው ኃላፊነት መነሳቱን በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡…
ፕ/ር ክንደያ ገ/ሕይወት ከመቐለ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንትነት የተነሱት የስራ ዘመናቸውን በማጠናቀቃቸው መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚ/ር እንደሚከተለው አሳውቋል:

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት መቀሌ ዩኒቨርስቲን በፕሬዘዳንትነት ሲመሩ መቆየታቸው ይታወሳል።ሆኖም በተለመደው የዪኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ምልመላና ስምሪት መመሪያ መሠረት የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ በመሆኑ በክብር መሰናበታቸውን እንገልፃለን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ክንደያ በተሰጣቸው የኃላፊነት ጊዜና ከዚያም በላይ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ እያመሰገነ፣ ቀጣይ የሥራ ዘመናቸው ውጤታማ እንዲሆን ይመኛል፡፡

-የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ አቋርጦት የነበረውን ህክምና መስጠት ጀመረ!

የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለ3 ወር ያህል አቋርጦት የነበረውን ህክምና መስጠት እንደጀመረ አስታውቋል።ሆስፒታሉ ወረርሽኙን በመከላከል ረገድ ምርመራዎችን ማካሄድና ታካሚዎችን ከመንከባከብ ጋር ተያይዞ ወደ 25 ሺሀ የሚጠጉ ምርመራዎችን እንዳከናወነ ነው የገለፀው።ሆስፒታሉ 270 አልጋዎችን በማዘጋጀት ከኮሮና በሽታ ጋር ተያይዞ የተለየ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎች በመቀበል አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበርም ተጠቅሷል።ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከ900 ሰዎችን በመቀበል 640 ድነው መውጣታቸውና አሁን ላይ ደግሞ 150 ሰዎች በህክምና ላይ የሚገኙ እንደሆኑ ተጠቁሟል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አደረጉ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከክልል እና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።ውይይቱ በዋናነት በሀገራዊ መግባባት ላይ የተደረገውን ውይይት ምን እንደሚመስል መገምገም እና ቀጣይ በምን ሁኔታ ውይይቶች ይካሄዱ የሚለውን ለመወያየት ነው።አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደገለጹት የተደረጉ ውይይቶች በፓርቲዎች መካከል ፉክክር እንዲደረግ በር የከፈተ እና መቀራረብ የፈጠረ ነው ብለዋል።ታይተው የነበሩ ችግሮች እየተቀረፉ መምጣታቸውንም አንስተዋል።በሚቀጥለው ጊዜ ምን ይደረግ በሚለው ጉዳይ ላይም አራት ርእሰ ጉዳዮችን መርጠዋል።

እነዚህም

👉 ህገ መንግስት እና ህግ መንግስታዊነት ስር በኢትዮጵያ የቅራኔ ምንጭ ላይ ውይይት፣
👉 የፖለቲካ አደረጃጀቶች ምን መምሰል አለበት፣
👉 የፖለቲካ ፓርቲዎችን መሰባሰብ በሚመለከት እና
👉 ትክክለኛ ምርጫ ምን ማለት ነው በሚለው ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲደረጉ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምርጫው ስርዓቱ ምን ይሁን እንዲሁም በምን መልኩ ምርጫውን ማከናውን አለበት በሚሉ ጉዳይ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ይመክራሉ ተብሏል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በውጭ ሀገር የገንዘብ ምንዛሬ አገልግሎት የተጠረጠሩ ሱቆች ታሸጉ!

የኢትዮጵያ መንግስት አሁን በአገልግሎት ላይ የሚገኙትን የብር የገንዘብ አይነቶች እንዲሚቀይር በትላንትናው ዕለት ማስታወቁን ተከትሎ የ“ጥቁር ገበያ”ውን ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ ተጀመረ። በአዲስ አበባ ከባንክ ውጭ የሚደረጉ የውጭ ሀገር ገንዘብ ግብይቶችን በድብቅ ያከናውናሉ ከተባሉ ሱቆች መካከል የተወሰኑት ከትላንት ጀምሮ እንዲታሸጉ ተደርገዋል።የእርምጃው ሰለባ የሆኑት በይፋ ከሚታወቁባቸው አገልግሎቶች ባሻገር የውጭ ሀገር ገንዘቦች ምንዛሬን በተደራቢነት የሚሰጡ ሱቆች ናቸው።በኢትዮጵያ ሆቴል እና ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙት እነዚህ ሱቆች “ታሽጓል” የሚል ጽሁፍ እና ማህተም የሰፈረባቸው ወረቀቶች በየበሮቻቸው ላይ መለጠፍፋቸውን ዛሬ ረፋዱን በቦታው የተገኘው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ተመልክቷል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
ጋምቤላ በዐሥር ሺህዎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ተፈናቅለዋል!

ከ18ሺህ በላይ ሰዎች ጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ ውስጥ በጎርፍ መፈናቀላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ዐስታወቁ። የጎርፍ መጥለቅለቊ አደጋ የተከሰተበት ወረዳው ኢትዮጵያን ከሱዳን በሚያዋስን አካባቢ ነው፡፡ የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ ቤት ከተፈናቃዮች መካከል ወ/ሮ ኛዳክ ፓችን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰሞኑን እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በፈጠረው ጎርፍ ምክናያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከነቤተሰቦቻቸው በትምህርት ቤት አጥር ጊቢ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። መንግስት የአልባሳትና የምግብ አቅርቦት ባለማድረጉም ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ወ/ሮ ኛዳክ ተናግረዋል።

በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን የላሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋርዊች ቢየል በስልክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ሱዳንንና ኢትዮጵያን የሚያዋስነው ጂካዎ ወንዝ ሞልቶ በተፈጠረው ችግር ከ18ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ የሚኖሩትም በትምህርት ቤቶች እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡ እንስሳት እንደሞቱና የግጦሽ ሜዳዎችም በጎርፍ በመሸፈናቸው እንስሳቱም ለከፋ ረሀብ መጋለጣቸውን ዋና አስተዳዳሪው አመልክተዋል፡፡ አደጋው ከጳጉሜ ጀምሮ የተከሰተ ሲሆን ከክልል ርዳታ እንዲቀርብ ሪፖርት ቢደረግም ጉዳቱን መጥቶ ከመመልከት ውጪ እስካሁን ምንም እርዳታ እንዳልተገኘ ገልፀዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል አደጋ መከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያ አቶ ሰይፉ ወልዴ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ የአካባቢው ሰዎች አኗኗር ለእንደዚህ ዓይነት አደጋ እንደሚያጋልጥ አመልክተዋል። በመሆኑም ሰሞኑን በአካባቢው የጎርፍ መጥለቅለቅ መድረሱን አመልክተው የተጠቀሰው የርዳታ ፈላጊ ቁጥር ግን የተጋነነ እንደሆነ አመልክተዋል። ሆኖም ርዳታ ወደ አካባቢው ለመላክ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አመልክተዋል። በዘንድሮው ክረምት በተለያዩ አካባቢዎች የጣለው ከባድ ዝናብ በበርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጎርፍና ናዳ በመፍጠሩ በርካቶች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዳዲስ ሹመቶች ሰጡ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተለያዩ አዳዲስ ሹመቶችን እና የስራ ምደባ መስጠታቸው ተገለጸ፡፡የተጀመረውን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እና በተለያዩ ግዜያት የሚነሱ የህዝብ ቅሬታዎችን ለመመለስ የአመራር ሽግሽግና አዳዲስ የስራ ስምሪት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ዛሬ ለ8 አመራሮች ምደባ መሰጠቱን የከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት አስታውቋል፡፡

በዚሁም መሰረት፡-

1. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ - የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ተፈራ ሞላ - የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ጀማል ረዲ - የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. አቶ መኮንን አምባዬ - የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
5. አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ የህዝብ አደረጃጀት አማካሪ
6. አቶ ተተካ በቀለ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ አደረጃጀት አማካሪ
7. አቶ ጥላሁን ፍቃዱ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ ማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ
8. አቶ የትናየት ሙሉጌታ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ፅ/ቤት ኃላፊ

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተሿሚዎቹ የተሰጣቸው ሃላፊነት የህዝብ አገልጋይነት መሆኑን በመረዳት ህዝቡን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ እንዲሆኑ ማሳሰባቸውን ከፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa