YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የድምጽ ብክለትን ለመቆጣጠር የምሽት የቁጥጥር ሥራ ሊጀመር ነው!

በተለያዩ ሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ፣በመንገድ ላይ፣ በልብስ መሸጫ (ቡቲክ) እና በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚስተዋለውን የድምጽ ብክለት ለመቆጣጠር ከዚህ በፊት ይተገበር ያልነበረው የምሽት የቁጥጥር ስራ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ለመጀመር ማቀዱን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ለአዲሰ ማለዳ አስታወቀ።የቁጥጥር ስራው ቅዳሜ እና እሁድን በመጨመር ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተግባዊ እንደሚሆንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር ወረዳ ሚስቱን የገደለው ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተፈረደበት።

የዞኑ ኮሙንኬሽን እንዳስታወቀው ድርጊቱ ፈፃሚ አቶ በሀሩ ወንድም አገኝ ጉባሞ በጉራጌ ዞን እኖር ኤነረ ወረዳ የባረዋ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ለባለቤቱ እንደሚገድላት በተደጋጋሚ እየዛተባት ነበር።በእለተ ሀሙስ በቀን 24/07/2012 በግምት ከንጋቱ 12:00 ሟች አፀደ ዘመድአገኝ በባለቤቷ እንደዛተባትም በአሰቃቂ ሁኔታ በዱላ ጭንቅላቷንና ማጅራቷን ደብድቦ ከገደላት በኋላ ወንዝ ላይ ጥሏት መሄዱ ተገልጿል።ይህንን አሰቃቂ ድርጊት የሚገልፅ የምርመራ መዝገብ የደረሰው የጉራጌ ዞን ዐቃቤ ህግ መምሪያ የልዩ ልዩ የወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ የምርመራ መዝገቡ በአግባቡ በመመርመር በተከሳሹ ግለሰብ ላይ የኢ ፌ ዲ ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539 (1)(ሀ )ላይ የከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ክስ መስርቶበታል።

ክሱ የደረሰው የወልቂጤ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ በቀን 02/13/2012 ዓም በዋለው ችሎት የተከሳሹ ድርጊት እጅግ አደገኛና ነውረኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ አስገብቷል።በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ከዚህ ቀደም በ1999 ዓም በሀዋሳ ከተማ የቀድሞ ባለቤቱ በተመሳሳይ ሁኔታ ገድሎ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ከሁለት አመት በፊት በይቅርታ ተለቆ መውጣቱን በቅጣት ማክበጃነት ይዟል።በመሆኑም ሰው መግደል ልማድ አድርጎ የያዘ በመሆኑ: ከዚህ በኋላ እስራት ያስተምረዋል ተብሎ ስለማይታሰብና የኢ ፌ ዲ ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 117 መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ የሚያሟላ በመሆኑ በአጠቃላይ ሌላው የህብረተሰብ ክፍል ሊያስተምር ይችላል ያለውን የሞት ቅጣት ውሳኔ ወስኖበታል ተብሏል።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መርሃ-ግብሮች ያስተማራቸውን ከ 1000 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

በ1999 ዓ.ም የተመሰረተውና የሁለተኛ ትውልድ ዩኒቨርስቲ የሆነው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መርሃግብሮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 79 ተማሪዎችን ዛሬው ዕለት ለ12 ኛ ጊዜ ባካሄደው የምረቃ ስነስርዓት አስመርቋል። የምረቃ-ስነስርዓቱም በኮቪድ-19 ወረረሽኝ ምክንያት በበይነ-መረብ በሚተፈላለፍ የቀጥታ ስርጭት ተካሂዷል፡፡ዩኒቨርሲቲው በድህረ ምረቃና በቅድመ ምረቃ በመደበኛ፣ በሳምንቱ መጨረሻ እና በክረምት መርሀግብር በማሰልጠን በዛሬው ዕለት ካስመርቃቸው 1 ሺህ 79 ዕጩ ምሩቃን 493ቱ ሴቶች ሲሆኑ ከኒዚህም ውስጥ 51ዱ በተለያዩ የትህርት መስኮች በድህረ ምረቃ ዕጩ ምሩቃን ናቸው፡፡

[የወላይታ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት]
@YeneTube @FikerAssefa
በወልቃይት እና ራያ አካባቢ ደርሷል የተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ሊካሔድበት ነው!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በወልቃይት እና ራያ አካባቢ በሕወሓት እየደረሰ ነው የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊመረምር መሆኑን ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መከሰቱን ምክንያት በማድረግ 6ኛው አገራዊ ምርጫ መራዘሙን ተከትሎ በገዥው ፓርቲ ብልጽግና እና በህወሓት መካከል የተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ትግራይ ክልል ምርጫውን በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ጫፍ ደርሷል ይሄኑ መነሻ በማድረግ በአማራ ክልልና በትግራይ ክልል አዋሳኝ በወልቃይትና በራያ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች ህወሓት የግድ ትምርጣላችሁ በማለት ለእስር፣ድብደባ እና ለአፈና ተዳርገናል ሲሉ አቤቱታቸውን አቅርበዋል።

ተጨማሪ👇👇👇
https://telegra.ph/-09-08-449
የትግራይ ክልል ምርጫውን ለመታዘብ የጠየቀ አንድ ተቋምን ማገዱ ተገለጠ!

«ሰብ ሕድሪ ሲቪል ማሕበረሰብ ትግራይ» የተባለ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀስ ነፃ ተቋም በትግራይ ምርጫ ለመታዘብ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ እንደተደረገበት ገለፀ፡፡

ሰብ ሕድሪ ሲቪል ማሕበረሰብ ትግራይ ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው ተቋሙ «ታሪካዊ» ባለው የትግራይ ምርጫ በታዛቢነት ለመሳተፍ 300 ገደማ አባላቱን ለታዛቢነት አዘጋጅቶ ነበር። ቢሆንም የትግራይ ምርጫ ኮምሽን ከሦስተኛ ወገን በቀረበለት ቅሬታ ከታዛቢነት እንዳገደው ዐስታውቋል፡፡ሰብ ሕድሪ ሲቪል ማሕበረሰብ ትግራይ በትግራይ ምርጫ ኮምሽን የተላለፈውን የእግድ ውሳኔ «ተገቢነት የሌለው» ብሎታል፡፡

የትግራይ ምርጫ ኮምሽን በበኩሉ ሲቪል ተቋሙ በምርጫው ከሚወዳደር ፓርቲ ቅሬታ ስለቀረበበት ነገ ይካኼዳል በተባለው ምርጫ ተሳታፊ እንዳይኾን መወሰኑን ገልጧል፡፡ሰብ ሕድሪ ሲቪል ማሕበረሰብ ትግራይ ሰኔ 2010 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን፤ በትግራይ «ዴሞክራታይዜሽን» እና ክብሮች ዙርያ የሚሠራ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ይኽ በእንዲህ እንዳለ፦ የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ለ61 የሀገር ውስጥ ተቋማት ምርጫውን እንዲታዘቡ ፍቃድ መስጠቱን ዐስታውቋል፡፡

በትናንትናው እለት አራት ጋዜጠኞችን ጨምሮ የትግራይ ክልል ምርጫን ለመከታተል ወደ መቀሌ በአየር ሊጓዙ የነበሩ ዐሥራ ኹለት ሰዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንደታገዱ ተነግሯል። ከታገዱት መካከል የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች እንደሚገኙበትም ተዘግቧል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ብሄራዊ ባንክ ለ15 ተከታታይ አመታት ያልተንቀሳቀሱ ሂሳቦችን ወደ መንግስት እንዲገባ የሚያደርገውን የብሄራዊ ባንክ የባንክ ስራ አዎጅ ማስፈጸሚያ መመሪያ አወጣ!

በመመሪያው መሰረት ከ12 አመት በፊት የወጣውን የባንክ ስራ አዋጅ አንቀፅ 52 ማስፈፀሚያ የሚሆነው መመሪያ በባንኮች ለተከታታይ 15 አመት ያልተንቀሳቀሱ ከ5 ብር ጀምሮ ያሉ ሂሳቦች ወደ ብሄራዊ ባንክ መግባት አለባቸው፡፡ሆኖም ብሄራዊ ባንክ ቢደረግለትም ባለንብረቱ ወይም ህጋዊ ወራሽ ከመጣ ብሄራዊ ባንክ በማንኛውም ጊዜ ወለድን ሳይጨምር ገንዘቡን ይመልሳል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
የትምህርት ቤት ክፍያ ላይ አላስፈላጊ ጭማሪ ያሚደረጉ ትምህርት ቤቶች ላይ እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ትምህርት ሚኒስቴር አስጠነቀቀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከተማሪ ወላጆች የሚመጡ ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን መሰረት በማድረግ ነው እርምጃ እንደሚወሰድ ይፋ ያደረገው፡፡የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዎስ ከቀጣይ አመት ትምህርት ጋር በተያያዘ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ሚኒስትር ዴኤታው የግል ትምህርት ቤቶች ቀድመው ሲሰሩበት ከነበረው የአከፋፈል ስርዓት ውጪ ምንም አይነት ጭማሪ ማድረግ እንማይችሉ አስስበዋል፡፡

ቀድመው ከሚሰሩበት አሰራር ውጭ ተጨማሪ ክፍያ በሚያስከፍሉ ትምህርት ቤቶች ላይ ትምህርት ቤቶቹን እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችልም ትምህር ሚኒስቴር አስጠንቅቋል፡፡በቀጣይ ትምህርት ሲከፈት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ትምህርት ቤቶች በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪ ብቻ ለማስተማር የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

‹‹የግል ትምህርት ቤቶች ይህንን ለማድረግ አይቸገሩም ወይ?›› ተብለው ከጋዜጠኞች ጥያቄ የተነሳላቸው ሚኒስትር ዴኤታው ሚሊየን ማቲዮስ ቀጣዩ የትምህርት ስርዓት ወደ አዲስ አሰራር የሚሸጋገርበት በመሆኑ ራሳቸውን ለዚህ ዝግጁ ማድረግ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት፡፡የመንግስት ትምህርት ቤቶችም ተመራጭ እንዲሆኑ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ተብራርቷል::ትምህርት ሲጀመር የሚኖረው የትምህርት አሰጣጥ ሂደትም በአንድ ከፍል የሚማሩ የተማሪዎችን ቁጥር የሚወስን ይሆናል፡፡

[MoE]
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ባንክ ለ4 የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት አዲስ ዳይሬክተር ሾመ!

የዓለም ባንክ አቶ ኬት ሃንሰንን የኬንያ፣ ርዋንዳ፣ ሶማሊያ እና ኡጋንዳ ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ፡፡ልማትን የተመለከቱ የ30 ዓመታት ልምድ ያላቸው ሃንሰን የ13 ቢሊዬን ዶላር ዋጋ ያላቸው እና በ4ቱ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የተሚተገበሩ 100 ፕሮጄክቶችን ይመራሉ ተብሏል፡፡ትኩረታቸው በኮሮና ወረርሽኝ ላይ አድርገው ሃገራቱ የጀመሩትን የዘላቂ ልማት ጉዞ እንደሚደግፉም ነው የተገለጸው፡፡ከአሁን ቀደም አፍሪካን ጨምሮ ደቡብ አሜሪካን በመሳሰሉ የተለያዩ ክፍለ አህጉራት በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት ሃንሰን የባንኩ የሰብዓዊ ልማቶች ምክትል ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉም ሲሆን ዋና ስራ አስፈጻሚውን ያማክሩም እንደነበር የህይወትና የስራ ልምድ ማስረጃዎቻቸው ያሳያሉ፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመተከል ዞን ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ ለቢቢሲ እንደገለጹት "ፀረ ሠላም" ያሏቸው ኃይሎች በወንበራ ወረዳ መልካ በምትባል ቀበሌ ሠላማዊ ሰዎችን በማገት፣ የጦር መሣሪያዎችን በመቀማትና በአካባቢው ማኅበረሰብ ንብረት ላይ ዘረፋ ፈጽመዋል ብለዋል።በትላንትናው ዕለትም [ሰኞ] በቡለን ወረዳ ኤጳር በምትባል ቀበሌ እነዚሁ ኃይሎች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የአፈናና የግድያ ወንጀል ከመፈጸማቸው በተጨማሪ የተለያዩ ጉዳቶችን ማድረሳቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ በአካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን ጠይቆ እንደተረዳው በተለያዩ ጊዜያት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በሚፈጸመው ጥቃት የተነሳ የዕለት ከዕለት ተግባራቸውን በስጋት ውስጥ ሆነው እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል።በሚፈጸሙት ጥቃቶችም በሰው ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ በመሆኑ እንቅስቃሴያቸው መገደቡንና ክስተቱም ሁሉም በነጻነት እንዳይንቀሳቀስ በማድረጉ በአካባቢዎቹ ባለው ሥራ ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የወረዳው የመንግሥት ሠራተኛ ተናግረዋል።

ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከአካባቢው ነዋሪዎች በተጨማሪ የጤናና ግብርና ባለሙያዎችን ለማፈን ከመሞከራቸውም በላይ በመንግሥት መዋቅር ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከሩ መሆኑን ጠቅሰው ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ወደ ሌላ ወረዳ መሸሻቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት ተከትሎ በወጣው መረጃ መሰረት የአካባቢው ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ ልዩ ኃይል በጋራ በመሆን ወደ ወረዳዎቹ በመግባት ጥቃቱን ለማስቆምና ፈጻሚዎቹን ለመቆጣጠር በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ በወረዳዎቹ እንደሚሉት ጉዳት እያስከተለ ያለው ጥቃት የሚፈጸመው ስሙን ለጊዜው መጥቀስ ባልፈለጉት "የተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድን አባላት" መሆኑንና በቁጥጥር ስር እያዋሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ እስካሁን የታገቱ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር በተመለከከተ "በቁጥር ደረጃ በዝርዝር አልተለየም" ያሉት ኮማንደር ነጋ፤ መረጃው ተሰባሰቦ ሲያልቅ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ በክልሉ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች እየተፈጸመ ካለው ጥቃት ጋር በተያያዘ "ፀረ ሠላም" ያሏቸው ኃይሎች ከውጪ አገር ጭምር ድጋፍ እንደሚደረግላቸው መረጃ መገኘቱን ጠቅሰው "ወጣቶችን ለመመልመል እንደሚንቀሳቀሱም" ጨምረው ተናግረዋል።ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከቀናት በፊል መልካን በሚባል ቀበሌ 30 ሰዎችን አፍነው የነበረ ሲሆን አሁን እነሱን መልቀቃቸውን አመልክተው፤ የያዟቸውን ሰዎች ቡድኑን እንዲቀላቀሉ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በተለያዩ ጊዜያት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ማንነታቸው ያልተገጹ ቡድኖች በነዋሪዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው ባሻገር በተደጋጋሚ ሰዎችን እያገቱ እንደሚወስዱ ሲዘገብ ቆይቷል።ይህንንም ለማስቆም የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ከአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለመቆጣጠርና ድርጊቱን ለማስቆም እየጣሩ መሆኑ ተገልጿል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በሶሪያ እስር ቤቶች የነበሩ 3 ኢትዮጵያውን እና በሊባኖስ እስር ቤት የነበረች አንዲት ኢትዮጵያዊት ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል!

3 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ በሶሪያ አቋርጠው ወደ ሌሎች አገራት ለመሻገር ሲሞክሩ ተይዘው በሶሪያ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ ዜጎቻችንን ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ በቤይሩት ከሚገኘው የሶሪያ ኤምባሲ ጋር በመቀናጀት የኮሮናቫይረስ PCR ምርመራ አድርገው ዛሬ ጷጉሜ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል፡፡ሌሎች 2 በሶሪያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በመጭው ሳምንት ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ፡፡ቀደም ሲል በተመሳሳይ 12 ኢትዮጵያውያን (ከአንድ ህጻን ጋር) ከሶሪያ እስር ቤቶች ተለቀው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም በሊባኖስ እስር ቤት የነበረች አንዲት ኢትዮጵያዊትም ወደ አገር ቤት ተመልሳለች፡፡

[Ethiopian Counsulate in Beirut]
@YeneTube @FikerAssefa
ጥረት ኮርፖሬት ሥያሜውንና የመለያ ምልክቱን ሊቀይር ነው!

በቀድሞው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) እና በአሁኑ አማራ ብልጽግና ስር የሚተዳደረው የልማት ድርጅት ጥረት ኮርፖሬት መለያ ስያሜውንና የመለያ ምልክቱን ለመቀየር በኮርፖሬቱ ቦርድ ወሳኔ ማስተላለፉንና ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡ጥረት ኮርፖሬት ሥያሜውንና የመለያ ምልክቱን ሊቀይር ነውበቀድሞው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) እና በአሁኑ አማራ ብልጽግና ስር የሚተዳደረው የልማት ድርጅት ጥረት ኮርፖሬት መለያ ስያሜውንና የመለያ ምልክቱን ለመቀየር በኮርፖሬቱ ቦርድ ወሳኔ ማስተላለፉንና ወደ ስራ መግባቱን አስታወቋል፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ነገ በትግራይ ይደረጋል ለተባለው ምርጫ 2672 ድምፅ መስጫ ጣብያዎች መዘጋጀታቸው የትግራይ ምርጫ ኮምሽን ዐስታወቀ፡፡

በነገው ድምፅ የመስጠት ስነ ስርዓት 2 ነጥብ 7 ሚልዮን ህዝብ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡በመቐለ የተለያዩ አካባቢዎች የድምፅ መስጫ ጣብያዎች በየአካባቢው ምርጫ አስፈፃሚዎችና ወጣቶች እየተዘጋጁ ነው፡፡ በከተማዋ የፀጥታ ሐይሎች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉም ይገኛሉ፡፡ከዛሬ ምሽት ጀምሮም የብስክሌቶች፣ የሞተር ሳይክሎች፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጆች) እንቅስቃሴ በጊዜያዊነት መከልከሉ የትግራይ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡ነገ ጳጉሜ 4 ቀን፣ 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማታ 12 ሰዓት መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ፡ ተብሎ ይጠበቃል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1136 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 14,815 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 1136 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

307 ሰዎች ሲያገግሙ 16 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

እስካሁን በአጠቃላይ 60,784 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 22,677 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ949 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ከማለዳው 12 ሰአት የጀመረው የድምፅ አሰጣጥ ስነ ስርዓት በፎቶ።

[አዲስ ስታንዳርድ]
@YeneTube @FikerAssefa
ዓለም ተስፋ የጣለበት የኦክስፎርድ የኮሮና ክትባት ምርምር እንዲቆም ተደረገ!

የመጨረሻ የክሊኒካል ሙከራ ላይ የነበረውና ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የቆየው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ከመድሃኒት አምራቹ አስትራዜኔካ ኩባንያ ጋር እያበለጸጉት የነበረው የኮሮና ክትባት ምርምር እንዲቆም ተደረገ።ምርምሩ ለጊዜው ባለበት ይቁም የተባለበት ምክንያት የክትባት ቅንጣቱን የወሰዱ በጎ ፍቃደኛ ተሳታፊዎች ሕመም ስላጋጠማቸው ነው።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሐሰተኛ የብር ኖቶች እንዳይጭበረበሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ፖሊስ አሳሰበ!

ህብረተሰቡ ባዕድ ነገር ተቀላቅሎባቸው ከሚሸጡ ምግብና መጠጦች እንዳይታለል ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም ገልጿል።ኮሚሽኑ የዘመን መለወጫ በዓል በዓሉ ከወንጀል የጸዳና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ዝግጅት አድርጓል።ህብረተሰቡ ከወንጀል ድርጊቶች ራሱን እንዲጠበቅ መልዕክት እያስተላለፈ ነው።በተለይም በበዓላት ወቅት የሚፈጸም ወንጀል ቀድሞ ለመከላከልና መቆጣጠር ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እንዳደረገ አስታውቋል።በኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት የሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት የከተማ ነዋሪዎች ግብይት በሚፈጸምበት ወቅት በሐሰተኛ የብር ኖቶች እንዳይጭበርበር ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።

ህብረተሰቡ በገበያ ቦታዎች ላይ የሀሰተኛ የብር ኖቶች ዝውውር ከተመለከተ ለፖሊስ በፍጥነት እንዲጠቆምም አስገንዝበዋል።በበዓል ሰሞን ከሚፈጸሙ ወንጀሎች መካከል ምግብና መጠጥ ላይ ባዕድ ነገር መቀላቀል በዚህና ሌሎች በግብይት ወቅት ከሚፈጸሙ ማጭበርበር እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።ህብረተሰቡ በድርጊቱ የተሰማሩ አካላትን በመጠቆም ትብብር እንዲያደርግ ዋና ኢንስፔክተር ቶማስ አመልክተዋል።የከተማውን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር ህብረተሰቡን ያሳተፈ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።በመዝናኛ ቦታዎች የሚፈጠሩ ጸቦችን በየመንገዱ የሚደረጉ ዝርፊያና ቅሚያዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

በበዓል ወቅት የሚጨምረውን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ አደጋ በሚበዛባቸው ቦታዎች የትራፊክ ፖሊሶች መሰማራታቸው ዋና ኢንስፔክተር ቶማስ ገልጸዋል።አሽከርካሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ባላቸው ጉጉት በፍጥነት ሲያሽከረክሩ ለአደጋ እንዳይጋለጡ በጥንቃቄና በተረጋጋ መንገድ ማሽከርከር እንዳለባቸው አሳስበዋል።የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል በመዝናኛ ቦታዎች፣ በትራንስፖርት አገልግሎትና ሌሎች ሕዝብ በሚበዛባቸው ስፍራዎች ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።የመዲናዋ ነዋሪዎች ጥቆማ ሲኖራቸው በ011-111-01-11 እና በ991 ነጻ የስልክ መስመር እንዲሁም ለትራፊክ አደጋ 6727 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ማሳወቅ እንደሚችሉም ገልጸዋል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa