YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በመዲናዋ ከፈረንጆቹ 2014 በፊት ተመርተው አገልግሎ እየሰጡ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛውን ለጤና ጎጂ የሆኑ ብናኝ ወደ ከባቢ አየር እንደሚለቁ ጥናት አመለከተ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በትራንስፖረቱ ዘርፍ የሚታየዉን የብክለት መጠን ምን ያክል እንደሆነ ለማወቅ እንዲረዳ በመሳሪያ የታገዘ መረጃ በመሰብሰብ ጥናት መካሄዱን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ከሲ40 ከተሞች የአመራሮች ቡድን ለአየር ንብረት ለውጥ (c40 cities climate leadership group) ጋር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጥናቱን አካሂዷል።

በዚህም በከተማዋ ከትራንስፖርት ዘርፍ የሚለቀቀዉን በካይ ጭስ በመሳሪያ የተደገፈ የሙቀት አማቂ ገዞችን ልቀት እና የአየር ጥራት ልኬት በማድረግ የከተማዋን የአየር ብክለት መጠን ያለበትን ደረጃ ለማወቅ እንደ መነሻ ጥናት እንደሚያለግል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ከተለያዩ የመኪና አይነቶች፣ከሚጠቀሙት የነዳጅ አይነትና ከተመረቱበት ለምሳሌ ከፈረንጆቹ ከ1992 በፊት እና ከ2014 ወዲህ የተመረቱ ላይ ከመኪና ጭስ ማዉጫ በቀጥታ ልኬት ተወስዷል።

በተወሰደዉ የልኬት መረጃ መሰረትም ከ2014 በፊት የተመረቱ መኪናዎች ከ72-74 ማይክሮ ግራም ፐር ሜትር ኪዩብ (µg/m3) በካይና ለጤና ጎጂ የሆኑ ብናኝ (PM2.5) ወደ ከባቢ አየር እንደሚለቁ እና እ.ኤ.አ ከ2014 ዓ.ም ወዲህ የተመረቱ መኪናዎች ደግሞ 45 ነጥብ 75 µg/m3) ማይክሮ ግራም ፐር ሜትር ኪዩብ በካይና ለጤና ጎጂ የሆኑ ብናኝ ወደ ከባቢ አየር እንደሚለቁ የመነሻ ጥናቱ ዉጤት እንሚያሳይ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም ከተለያዩ የመኪና አይነቶች በተወሰደ አማቂ ጋዝ ልኬት መሰረት ከባድ መኪናዎች እስከ 45 ነጥብ 75 ቶን ካርቦን ዳይኪክሳድ በአመት ወደከባቢ አየር እንደሚለቁ እንዲሁም የመጓጓዣ መኪናዎች ደግሞ ከ10-30 ቶን ካርቦን ዳይኪክሳድ በአመት ወደ ከባቢ አየር እንደሚለቁ በንፅፅር ለማወቅ መቻሉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የከባቢ አየር ጥራትን በተመለከተ ደግሞ ከታክሲ እና ከአዉቶቢስ ፌርማታዎች ላይ በተንቀሳቃሽ የአየር ጥራት መለኪያ መሳሪያ በተወሰደ ልኬት መሰረት በካይና ለጤና ጎጂ የሆኑ ብናኝ (PM2.5) ከ26-38.5 µg/m3) የሚለቁ ሲሆን ይህም የአለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠዉ ስታንዳርድ ማለትም ከ10 ማይክሮ ግራም ፐር ሜትር ኪዩብ (µg/m3 ) ጋር ሲነፃፀር ለጤና ጎጂ በሚባል ደረጃ እንዳለ እና የትራንስፖርቱን ዘርፍ በማዘመን ብክለትን የመቀነስ እርምጃ መወሰድ እንደሚገባዉ መነሻ ጥናቱ ዉጤት አሳይቷል ተብሏል፡፡

ጥናቱ በትራንስፖርቱ ዘርፍ በሚፈጠረዉ ብክለት የሚያደርሰዉን የጤና ጉዳት እንዲሁም በኢኮኖሚ ላይ የሚፈጥረዉን ተጽእኖ በማዎቅ ወደ እርምጃ ለመግባት እና መመሪያዎችን እና ፖሊሲዎችን ለማዉጣት እንደሚረዳ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት የአየር ንብረት ለዉጥ የሜይንስትሪሚንግ ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ፋንቱ ክፍሌ ገልጻዋል፡፡

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
ብልጽግና ብቁ መሪዎችን ለማፍራት እንደሚተጋ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ

የብልጽግና ጉዟችን ለሀገራችን ትርጉም ያለው ለውጥ ከማሳካት በዘለለ ብቁ መሪዎችን ለማፍራት እንደሚተጋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡

እንደ ንስር የሩቁን የሚመለከቱ፤ ከዋናው ዓላማቸው ሳይዛነፉ ግባቸውን የሚመቱ፤ በትጋት አሻራቸውን አኑረው የሚያልፉ ጽኑ መሪዎች ብሩህ ነጋችንን ይተልማሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒትሩ፣ ከነጠላ ጉዳይ ይልቅ ምሉዕ እይታን የሚያስቀድሙና ከችግር በላይ ከፍ ብለው መፍትሄ የሚያፈልቁ ዜጎች ውድ የሀገር ሀብቶች መሆናውንም ጠቁመዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፡፡

እንቅፋትና ጋሬጣውን አልፈው፣ መውደቅና መነሳቱን ተቋቁመው ድል የሚያስመዝግቡ ብርቱ ወጣቶች የኢትዮጵያ የመጪው ዘመኗ መሀንዲሶች ናቸው፤ እነሱን ይዛ ሀገራችን የማይቀለበስ የስኬት ጫፍ ትደርሳለችም ብለዋል።

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
ጃፓንን ለረዥም ጊዜ የመሩት ሺንዞ አቤ በጤና እክል ምክንያት ስልጣን ሊለቁ ነው

ጃፓንን ለስምንት ተከታታይ ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ሺንዞ አቤ በጤና እክል ምክንያት ስልጣናቸውን ሊለቁ መሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሰበር ዜና ዘግበዋል።

ኒዮርክ ታይም የጃፓንን ዜና ወኪሎች ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ሺንዞ አቤ ጃፓንን በጤና ምክንያት ስክልጣናቸውን እስከለቀቁበት ድረስ ለስምንት ተከታታይ ዓመታት መርተዋታል።

የ65 ዓመቱ ሺንዞ አቤ ብዙ ሰው በተደጋጋሚ በሚለቅበት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ለስምንት ዓመታት በመቆየት የመጀመሪያው ናቸው ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስልጣን ዘመናቸው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ሱናሚና የኒውክለር አደጋ ጃፓንን አጋጥሟት የነበረ ቢሆንም ከአደጋው እንድታገግምና ኢኮኖሚዋ እንዲነቃቃ ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጋቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

አቤ ከዚህ በተጨማሪ የጃፓን መከላከያ ሐይል በማጠናከር እና ወታደራዊ በጀት በማሳደግ አድናቆት አትርፈዋል።

ገዥው ሊብራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የጠቅላይ ሚኒስትር ምርጫ እስኪሚደረግ ድረስ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥራውን ተክቶ እንደሚሠራ ተጠቁሟል፡፡

የሺንዞ አቤ የስልጣን ማብቂያ ጊዜ መስከረም 2021 እንደነበረም ዘገባው አስታውሷል፡፡

Via:- EPA
@Yenetube @Fikerassefa
ፍርድ ቤቱ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል በተጠረጠሩት ከበደ ገመቹ እና አብዲ ዓለማየሁ ላይ አቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰርት የ15 ቀን ጊዜ ሰጠ።

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ ምርመራዬን አጠናቅቂያለሁ ብሎ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ አስረክቧል።

በችሎቱ አንደኛው ተጠርጣሪ አብዲ ዓለማየሁ አርቲስት ሃጫሉ በተገደለበት ወቅት በቦታው አልነበርኩም ያለ ቢሆንም ሌላኛው ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚ በበኩሉ አርቲስቱ ሲገደል ከበደ ገመቹ እና አብዲ ዓለማየሁ አብረውት እንደነበሩ አስረድቷል።

በዚሁም መሰረት ፍርድ ቤቱ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ መመስረቻ የ15 ቀን ጊዜ ሰጥቷል።

በሌላ በኩል የአስራት ሚዲያ ባለሙያዎች ላየ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት የአዲስ አበባ አስረኞች አስተዳደር ሀላፊ ቀርቦ በተጠርጣሪዎቹ የጤና ሁኔታ እና የእስር አያያዝ ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በዚህም የኮቪድ-19 ምርመራ እንደተደረገላቸው እና ነፃ መሆናቸውን አስታውቋል።

ይሁንና ተጠርጣሪዎቹ በፅዳት እጥረት ለጤና ችግር እየተጋለጥን ነው ማለታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ ከዐስር ሲፈቱ በጤናቸው ላይ እክል አጋጥሞ ጠባሳ ይዘው መውጣት የለባቸውም፣ ፖሊስ ትእዛዝ እስከሚሰጠው ድረስ መጠበቅ የለበትም፣ ደህንነታቸው እና ጤንነታቸው በተጠበቀ ቦታ ሊቆዩ ይገባል ሲል ትእዛዝ ሰጥቷል።

ፖሊስም ምርመራውን አጠናቆ እንዲመጣም ተጨማሪ ሰባት ቀን ፈቅዷል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
በእንግሊዝ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ለተፈጠረው ችግር በቂ ጥበቃ ባለመደረጉ ይቅርታ በመጠየቅ የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።

@Yenetube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት እና በከተማዋ ይስተዋላል ያለውን "ሕገ ወጥ የመሬት ወረራ" በተመለከተ አደረግሁት ያለውን ምርመራ ውጤት ይፋ ለማድረግ ዛሬ በራስ ሆቴል ሊሰጥ የነበረውን መግለጫ ከለከለ። ፖሊስ እንዳለው መግለጫው የተከለከለው ፓርቲው ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘውን የፈቃድ ደብዳቤ አላደረሰኝም በማለቱ ነው።

ኢዜማ በበኩሉ "ጥያቄውን ሕጋዊ በሆነ መልኩ አቅርቤያለሁ። ነገር ግን ክልከላው ከመግለጫው ይዘት ጋር የተያያዘ ነው" ብሏል። ፓርቲው "ይህም ልንገነባው ከምናስበው የዴሞክራሲ ባህል በተቃራኒ የሚቆም ድርጊት ነው" ብሎታል።ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በራስ ሆቴል በርከት ያሉ የመገናኛ ብዙሃን ለዘገባ የተገኙ ቢሆንም ፖሊሶች ክልከላ አድርገዋል። ዶይቼ ቬለ እንደዘገበው የፓርቲው መሪዎችና የከተማው ፖሊሶች በር ላይ ሰፊ ውይይት ቢያደርጉም መግለጫው እንደታሰበው ሳይሰጥ ቀርቷል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በይፋ ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡

ለሰባት ዓመት ከስምንት ወራ ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ሺንዞ አቤ ከሥልጣናቸው የለቀቁት ጤናቸው መታወኩን ተከትሎ ነው፡፡ አቤ እድሜአቸው 65 ሲሆን ዛሬ በሰጡት መግለጫ በህመም ጫና የተነሣ የመንግሥት ሥራ እንዲበደል አልፈልግም ነው ያሉት፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዩኤኢ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለመምህራኖቿ የኮሮና ምርመራ እያደረገች ነው።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶች ከመመለሳቸው አስቀድማ የግል ትምህርት ቤት መምህራንን እየመረመረች ነው፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በእናርጅ እናውጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ!

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እናውጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ።አደጋው የደረሰው ከደብረ ወርቅ ከተማ ወደ መጣያ ደጅ አጋምና ቀበሌ የሚጓዝ ባጃጅ ከደብረ ታቦር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ ሃገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ስማቸው አደጋው ከረፋዱ 5 ሰዓት አካባቢ ደጅ አጋምና ቀበሌ ኪዳነ ምህረት ልዩ ቦታው ከሻም ወንዝ አካባቢ መድረሱን ተናግረዋል፡፡በአደጋው የባጃጅ ሾፌሩን ጨምሮ የሶስት ሰዎች ወዲያውኑ ሲያልፍ ሁለቱ ሰዎች ባልና ሚስት መሆናቸውን ኮማንደር ስማቸው ገልጸዋል።ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ሴት በደብረ ወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል ብለዋል።ኮማንደር ስማቸው የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የወላይታ ዞን ከኃላፊነታቸው በተነሱት አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ምትክ አዲስ አስተዳዳሪ ተሾመለት።

ገዢው የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ የወላይታ ዞን ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሔደው ስብሰባ አቶ እንድርያስ ጌታ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።የደቡብ ክልል የመንግሥት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትም እንድርያስ ጌታ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው በወላይታ ዞን ምክር ቤት መሾማቸውን በፌስቡክ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል።አቶ ዳጋቶ ከሥልጣናቸው የተነሱት ከአንድ ሳምንት ገደማ በፊት መሆኑን ለአስተዳዳሪው ቅርበት ያላቸው የሶዶ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል።

የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ እንዳለው አዲሱ ተሿሚ እንድርያስ ጌታ (ዶ/ር) የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ነበሩ።ከኃላፊነታቸው የተነሱት ዳጋቶ ኩምቤ ባለፈው ነሐሴ 3 ቀን 2012 ዓ.ም .በሶዶ ከተማ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ከፍተኛ የዞኑ ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ናቸው። እስሩ በወቅቱ ከፍተኛ ተቃውሞ የቀሰቀሰ ሲሆን እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል።አቶ ዳጋቶ እና አብረዋቸው የታሰሩ የወላይታ ልሒቃን ከቀናት በኋላ በዋስ የተፈቱ ሲሆን ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ። የወላይታ ዞን የራሱን ክልል ለማቆም በሚያደርገው ግፊት ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጋር ብርቱ መቃቃር ውስጥ ገብቷል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት የፖለቲካ አመለካከትን ለመደፍጠጥ የሚያደርገውን ጥረት እንዲያቆም አብን አሳሰበ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተፈፀመው «የዘር ማጥፋት ወንጀል» እንደሆነ ገልጿል።ንቅናቄው በጥፋቱ የተሳተፉ፣ ሕዝቡን ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ የመንግስት አመራሮችም በጉድለታቸው ልክ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን የመልሶ ማቋቋም ስራ እንዲሰራ ጥሪ ማቅረቡን አስታውሷል።ጥቃቱ መፈፀም ከጀመረበት ዕለት አንስቶ የነቃ ክትትል በማድረግ በርካታ ወገናዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ እንደቆየም ንቅናቄው ገልጿል፡፡

እንዲሁም ጥቃቱ ወደተፈፀመባቸው ቦታዎች በጊዜው በመንቀሳቀስ ዝርዝር ማስረጃዎችን ሰብስቦ እና አጠናቅሮ በልዩ ሁኔታ በጉዳዩ ዙሪያ ለሚሰሩ የአማራ ማኅበራት እና ተቋማት ማስተላለፉን በመግለጫው አሳውቋል፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርኔጋ ወረዳ ነሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተፈፀሙ ዘር-ተኮር ጥቃቶች ከአስራ አምስት(15) በላይ አማራዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን አረጋግጫለሁ በአካባቢም አሁም የጸጥታ ስጋት እንዳለም ለማወቅ ችያለሁ ነው የሚለው፡፡የሕግ የበላይነትን በፅኑ እናስከብራለን በሚል በኦሮሚያ መንግስት እና የፌዴራል መንግስት የተገቡት ቃላት እንዲተገበሩም ጠይቋል፡፡

መንግስት ይሄን ታቅዶ እየተፈፀመ ያለ የዘር ማጥፋት እና ማፅዳት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲያስቆም አብን ጠይቋል፡፡በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ከነበረው ጥቃት ጋር በተያያዘ ከታሰሩት ግለሰቦች መካከል የተወሰኑትን ጉዳይ ስንመለከት ወንጀልን በሰበብነት ተጠቅሞ የፖለቲካ አመለካከትን ለመደፍጠጥ ወይም ለጥፋተኞች የፖለቲካ ሚዛን መጠበቂያነት የማዋል ዝንባሌ እንዳለ ለመገንዘብ ችያለሁም ብሏል።በመንግስት በኩል ይህ ጉዳይ በአስቸኳይ ተጣርቶ ተገቢው እርምት እንዲሰጥ ንቅናቄው አሳስቧል። ያለምንም ተጨባጭ ጥፋት በእስር ላይ የሚገኙት የአስራት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱም አብን በመግለጫው አመልክቷል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና መደበኛ ባልሆነ መርሀ ግብር ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 520 ተማሪዎች በመጪው ቅዳሜ እንደሚያስመርቅ አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዘውዱ እምሩ (ዶክተር) የምረቃ ሥነ ስርዓቱ ጥቂት ተማሪዎችን ፊት ለፊትና አብዛኛዎቹን ባሉበት በተለያዩ አማራጮች በቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሮች ታግዞ እንደሚያስመርቅ ተናግረዋል።

[AMMA]
@YeneTube @FikerAssefa
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው የተቋረጠውን ኃይል ለመቀጠል ርብርብ እየተደረገ ነው!

በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደር በወንዝ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ የባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በጎርፍ በመውደቁ ምክንያት ከትናንት እኩለ ቀን ጀምሮ የተቋረጠውን ኃይል ለመቀጠል ርብርብ እየተደረገ ነው።የአካባቢው መስመር ከኮተቤ ከሚወጣ መስመር ጋር በጊዜያዊነት በማገናኘት እስከ ማምሻው ድረስ ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

[EEPCo]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲሱ ዓመት ለ10 የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ ሊሰጥ ነው!

በአዲሱ ዓመት ለአስር የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ እንደሚሰጥ ብሮድካስት ባለስልጣን አስታወቀ።መንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ኢንዱስትሪውን አትራፊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑም ተገልጿል።የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ለኢዜአ እንደገለጹት በቀጣዩ ዓመት በኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ፈቃድ ይሰጣል።ፈቃዱን ከሚያገኙት መካከል በጨረታ ያሸነፉ ሶስት ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ይገኙበታል።እንዲሁም ማስረጃዎችን አሟልተው የቀረቡ የሳተላይት ጣቢያ ፈቃድ ፈላጊዎች ወዲያውኑ ይስተናገዳሉ።ፈቃዱ የሚሰጠው ፍላጎትን በማመጣጠንና ያለውን ምጥን የሆነውን የአየር ሞገድ ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

[Walta & ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
በሰኔ 16ቱ ሽብር ወንጀል የተከሰሱ አምስት ግለሰቦች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው!

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ድጋፍ መስቀል አደባባይ ላይ በተጠራው ሰልፍ ላይ ቦምብ በመወርወር የሰው ሕይወት በመቅጠፍ እና ንብረት በማጥፋት ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱት አምስት ግለሰቦች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው።የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈባቸው ጌጡ ግርማ፣ ብርሃኑ ጃፋር፣ ጥላሁን ጌታቸው፣ ባሕሩ ቶላ እና ደሳለኝ ተስፋዬ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው።

አምስቱም ግለሰቦች በጋራ ስምምነት በወቅቱ በመስቀል አደባባይ ቦምብ በመወርወር የሁለት ሰዎች ሕይወት እንዲጠፋ እና ሌሎች ሰዎች ላይ ደግሞ አካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ማድረግን ጨምሮ ሌሎች ዝርዝር ወንጀሎችን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በዋና ድርጊት ፈጻሚነት እና ተባባሪነት ከሷቸዋል።ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሰምቶ ተከሳሾችም የመከላከያ ምስክር አቅርበዋል፤ የሁለቱን ወገን ክርክር የመረመረው የከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት በዛሬው ዕለት ሁሉም ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።የቅጣት ውሳኔ ለመስጠትም ለጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ከክረምቱ ጋር ተያይዞ ግድቦች የሞሉ በመሆኑ የማስተንፈስ ሥራ እየተሠራ መሆኑን የተፋሰሶች ባለስልጣን አሳሰበ።

ባለስልጣኑ ከዚህ ጋር ተያይዞ በ11 ግድቦች አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች እንዲነሱና ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል።የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዳነች ያሬድ የማስተንፈስ ሥራው በቆቃ፣ ግልገል ጊቤ፣ ተከዜ፣ ጣና በለስ በተለይም ፎገራና ደንቢያ፣ ግልግል ጊቤ 3፣ መልካ ዋከና፣ ፊንጫ፣ አመርቲነሸ፣ ከሰም፣ መካከለኛው አዋሽ፣ ተንዳሆ፣ ታችኛው አዋሽ እና የገናሌ ዳዋ ግድቦች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።ዋና ዳይሬክተሯ ከእነዚህ መካከለሰ ፊንጫ እና አመርቲነሸ ሥጋት እነደሌለባቸውም ነው የተናገሩት፡፡በአንጻሩ ከሰም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያሻው መናገራቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢዜማ ዛሬ በፖሊስ የተከለከለበትን መግለጫ በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ያሰፈረው👇👇

እውነታውን በማድበስበስ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ወረራን እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላን በተመለከተ የሚደርሱትን ጥቆማዎች በመቀበል ጉዳዮን የሚመረምር ከብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የተወጣጣ ኮሚቴ አቋቁሞ ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል። የጥናቱን ውጤት ለሕዝብ እና ለመገናኛ ብዙኃን ይፋ ለማድረግ ዛሬ አርብ ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ተዘጋጅቶ ነበር።ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲዘጋጅ ከዚህ ቀደም ጋዜጣዊ መግለጫ ስንሰጥ እንደምናደርገው ሁሉ ጋዜጣዊ መግለጫው ለሚደረግበት ራስ ሆቴል እንዲሁም በደብዳቤ ቁጥር ኢዜማ/695/12 ለኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር አስቀድመን አሳውቀናል።

ፓርቲያችን ሊሰጥ የነበረውን መግለጫ ለመከታተል እና ለሕዝብ ለማድረስ የተጠሩ ጋዜጠኞች ከተባሉት ሰዓት ቀድመው በአዳራሹ ውስጥ የተገኙ ሲሆን ብዙዎቹም የቀረጻ መሣሪዎቻቸውን አሰናድተው የመግለጫውን መሰጠት በመጠባበቅ ላይ እያሉ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባል መሆናቸውን የገለፁ የፖሊስ አባላት መግለጫው መሰጠት እንደማይቻል በማሳወቅ ጋዜጠኞቹ አዳራሹን ለቀው እንዲወጡ አድርገዋል። ፖሊሶቹ ጋዜጣዊ መግለጫውን ለማስቆም የሰጡት ምክንያት ጋዜጣዊ መግለጫው እንዲካሄድ ትዕዛዝ አልተሰጠንም የሚል ነበር።

ተጨማሪ ለማንበብ👇👇👇
https://telegra.ph/-08-28-657
አሜሪካ ለኢትዮጵያ ልትሰጠው የነበረውን 130 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ እንዳገደች ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት ዘግቧል፡፡ የታገደው ለጸጥታ፣ ጸረ ሽብር እና ወታደራዊ ሥልጠና የታሰበው ዕርዳታ ሲሆኑ፣ እገዳው ምግብ፣ ጤና እና ሰብዓዊ ዕርዳታን አይመለከትም፡፡ ስለ ዕርዳታው መታገድ የፖምፒዮ መስሪያ ቤት ትናንት ለሕግ መምሪያው ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ማይክ ፖምፒዮ ዕርዳታውን ያገዱት፣ ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ድርድር አቋሟ ላይ ጫና ለመፍጠር ዘገባው ገልጧል፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በህገወጥ የቴሌኮም ማጭበርበር ድርጊት የተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች ከነመሳሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎች በኢትዮ ቴሌኮም ሳተላይት ኔትወርክ በኩል ማለፍ ሲገባቸው ፤ህገወጥ የቴሎኮም መሳሪያዎችን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ወደ አገር ውስጥ በማስገባትና ዓለምአቀፍ ጥሪዎችን በመጥለፍ በራሳቸው መሰመሮች ለደንበኞች እያቀረቡ ህገወጥ ድርጊት ሲፈጽሙ እንደነበር የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አመልከቷል፡፡

ለዚህ ህገወጥ ተግባር ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 11 ጌትዌይ (ሲምቦክስ)፣ 26 ቲፕሊንክ፣ 1339 ሲም ካርዶች፣ 20 ፍላሽ ዲሰክ፣ 11 ላፕቶፕ እና ሌሎች ህገወጥ የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

ህገወጥ ድርጊቱ ኢትዮ ቴሌኮምን በአመት እስከ 137 ሚልዮን ብር እንደሚያሳጣው ጠቁሟል፡፡ሕገወጥ የቴሌኮም መሣሪያዎችን በመጠቀም አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 11 ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ለመያዝ በአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራንዮ፣ንፋስ ስልክ ላፍቶ እንዲሁም ልደታ፣ቦሌ እና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች በፌዴራልና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች አማካኝነት ኦፕሬሽኖች መካሄዳቸውንና በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን መግለጫው ጠቅሷል፡፡

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የድሮኖች ምዝገባ ሊጀመር ነው!

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሰው አልባ አይሮፕላን (ድሮን) አጠቃቀም ረቂቅ-መመሪያ ማዘጋጀቱን ገለጸ።በሃገሪቱ የሚገኙ ድሮኖችን በሙሉ ለመመዝገብ ዝግጅት ማድረጉንም ገልጿል።

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa