የብላክ ፓንተር ፊልም መሪ ተዋናይ ቻድዊክ ቦስማን ከዚህ አለም በ43 አመቱ ተለይቷል።
" ሊገለፅ በማይችል ጥልቅ ሀዘን ሆነን ቻድዊክ ቦስማን ማረፉን ልናረጋግጥላቹ እንወዳለን " ይላል ከቤተሰቦቹ ወገን የተለለቀውና ወደ እሱ አካውንት የተለጠፈው የቲዊተር መልእክት ።
ቻድዊክ ቦስማን ደረጃ አራት በደረሰ በኮሎን ካንሰር ህመም ለአመት ያክል ሲሰቃይ ነበር ።ትናንት ለሊት ሒወቱ ማለፉን ተከትሎ በርካታ ወዳጆቹ አድናቂዎቹ ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው ።
ዲሞክራት ፖርቲን ወክለው በመጪው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሚወዳደሩት ጆ ባይደን የተሰማቸውን ሀዘን በቲወተር ገፃቸው በኩል ይሄን አስፍረዋል;
" የቻድዊክ የስራው አቅምና ጉልበት በፊልም ላይ ካየነው በላይ ነው ። በተወነበቸው ፊልሞች ከብላክ ፓንተር አንስቶ እስከ ጃኪ ሮቢንሰን ሰዎች ያለሙትን መስራት አንደሚቻሉ አስተምሯል። አኔና ሚስቴ ለወዳጆቹ መፅናናትን እንመኛለን " ብለዋል
ቦስማን ማርቭል፣ጌት ኦን አፕ፣ተርጉድ ማርሻል፣ጃኪ ሮቢንሰንና ብላክ ፓንተር ከተወነባቸው ፊልሞች መሀል ይጠቀሳሉ።
Via:- ፊደል ፓስት
@Yenetube @Fikerassefa

የኮሮናቫይረስ መነሻ የሆነችው የቻይናዋ ውሃን ከተማ በመጪው ማክሰኞ ሙሉ ለሙሉ ት/ቤት ልትከፍት ነው ።
ሬዊተርስ የከተማዋ ባለስልጣናት ትናንት አርብ ያወጡትን መግለጫ ጠቅሶ እንደፃፈው የኮሮናቫይረስ መነሻ የሆነችው የቻይናዋ ውሃን ከተማ በመጪው ማክሰኞ 1.4 ሚልየን ተማሪ የሚማሩባቸው 2,842 ት/ቤቶቿን ሙሉ ለሙሉ የምትከፍት ስትሆን ተማሪዎች ማስክ ማድረግን እና በዛ ብሎ መሰብሰብን እንዳያከናወኑ በጥብቅ አሳስባለች።
Via:- Fidel Post

በሶማሌ ክልል የኮሮና ስርጭትን ለመከላከል ከ1 ሺህ በላይ የህግ ታራሚዎች ተለቀቁ
የሶማሌ ክልል የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሲል 1 ሺህ 200 ታራሚዎች መልቀቁን አስታወቀ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እንዲሁም በኢትዮ-ሶማሌና በኢትዮ-ሶማሌ ላንድ ድንበር ኮሮናቫይረስን ለመከላከል እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝቷል።
ቦርዱ ከሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ መሐመድና ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ሪፖርት የቀረበበት ሰፊ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።
ቦርዱ ማረሚያ ቤቶችን፣ የቶጎ ጫሌ ደረቅ ወደ ብና የጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ የለይቶ ማቆያዎችን መመልከቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ አመልክቷል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት የሶማሌ ክልል ጠረፍ አካባቢ ያለና አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል አርብቶ አደር በመሆኑ ለወረርሽኙ ተጋላጭነት እንዳለው ገልጸዋል።
Via:- ENA

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከ7 ሺህ በላይ ተማሪዎቹን አስመረቀ!
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታው እና በክረምት መርሀግብር ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 7 ሺህ 520 ተማሪዎቹን በዛሬው እለት አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው በኮቪድ-19 ወረረሽኝ ምክንያት በበይነመረብ በሚተፈላለፍ የቀጥታ ስርጭት ነው ተማሪዎቹን ያስመረቀው።ከተመራቂ ተማሪዎች መካከልም 2 ሺህ 345 ሴቶች ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ አምስቱ የሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ናቸው።
[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa

ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 780 ተማሪዎች አስመረቀ!
ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 780 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ ተማሪዎቹ ከአንደኛ ዲግሪ እስከ ፒ ኤች ዲ ድረስ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠኑ ሲሆን የምረቃ ስነ ስርአቱም በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተካሂዷል፡፡
[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 780 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ ተማሪዎቹ ከአንደኛ ዲግሪ እስከ ፒ ኤች ዲ ድረስ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠኑ ሲሆን የምረቃ ስነ ስርአቱም በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተካሂዷል፡፡
[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የህዳሴ ግድብ ድርድር መስከረም 4 ይቀጥላል!
የኢትዮጵያ ውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮች የግድቡ ድርድር መስከረም 4፣2013 እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮች የግድቡ ድርድር መስከረም 4፣2013 እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው በ5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ አዲስ የምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሹመትን አፅድቋል።በዚህም መሠረት ወ/ሮ አዲስዓለም በዛብህ የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ፣ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የቀረቡትን ወ/ሮ ሚስራ አብደላን ደግሞ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሹሟል።
ተሿሚዎቹም በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።በተጨማሪም ወ/ሮ ፎዚያ በክሪ በሕግ፣ አስተዳደር፣ የሴቶች ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት ከምክር ቤቱ አባላት የቀረበውን ሹመትም በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን ደግሞ በምክር ቤቱ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት በመሾም ስብሰባውን አጠናቅቋል።
[ኢዜአ]
@YeneTube @Fiker

ብሔራዊ ሙዚየም በኮሮና ምክንያት 150 ሺ ጎብኚዎችን አጥቷል!
ኮሮና ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ የጉብኝት አገልግሎቱ በመቋረጡ በአምስት ወራት ውስጥ 150 ሺ ጎብኚዎችን ማጣቱን ብሔራዊ ሙዚየም አስታወቀ። በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የብሔራዊ ሙዚየም ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም አማረ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የኮሮና በሽታ ወደኢትዮጵያ ከገባ ከመጋቢት 15 ቀን 2012 ጀምሮ የብሔራዊ ሙዚያም ለጥንቃቄ ሲባል ለጎብኚዎች ዝግ ሆኖ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት ባለፉት አምስት ወራት ሙዚየሙን ሊጎበኙ ለሚችሉ 150ሺህ ሰዎች አገልግሎት መስጠት አልተቻለም።
ቀደም ባለው ጊዜ ባለው ልምድ መሰረት ብሔራዊ ሙዚየምን በየቀኑ የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ አንድ ሺ ይደርሳል። በተለይ በክረምት ወቅት ከትምህርት ቤቶች እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙዚየሙን ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር አመልክተው፣ የውጭ ሃገራት ጎብኚዎችም በብዛት ወደኢትዮጵያ እንደሚመጡ የሚጠበቅበት ወቅት እንደነበር አስታውቀዋል።ሙዚየሙ በኮሮና በሽታ ምክንያት ሲዘጋ አገልግሎቱን ማግኘት ካልቻሉ 150 ሺህ ሰዎች መካከል 45ሺህ የሚሆኑት ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ጎብኝዎች እንደሚሆኑ ይገመታል ያሉት አቶ ኤፍሬም፤ ጎብኚዎቹ በመቅረታቸው የባህል እቃዎች እና አልባሳት አቅራቢዎችን ገቢ ክፉኛ እንደጎዳው ተናግረዋል።
[EPA]

የአዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል የፊታችን ጳጉሜን 5 ስራ ይጀምራል!
በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የተገነባው የኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል የፊታችን ጳጉሜን 5 ስራ እንደሚጀምር ተገለፀ።የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ጋር በመሆን ሆስፒታሉን ጎብኝተዋል።ሆስፒታሉ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስር በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት በአለም ምግብ ፕሮግራምና በአለም ጤና ድርጅት ድጋፍ የተገነባ ነው።

በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ምግብና ቁሳቁስ ተሰበሰበ!
በአፋር ክልል ጎርፍ ጉዳት ላደረሰባቸው ወገኖች ከ80ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ልዩ ልዩ ምግብና ቁሳቁስ በድጋፍ መሰብሰቡን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ።ከአማራ ደቡብ ወሎ ዞን እና ኦሮሚያ አዳማ ከተማ ትናንት የተለያየ ምግብ እና አልባሳት ድጋፍ ተደርጓል።በዚህ ወቅት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን እንደተናገሩት፣ በክልሉ በተከሰተው ጎርፍ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ ኢትዮጵያዊያን ከጎናቸው በመቆም አብሮነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።
ክልሉ ከተለያዩ አጋሮች ያገኘው ድጋፍና ያለውን ክምችት በመጠቀም ዘርፉ የሚመራበትን የአሠራር ሥርዓት ተከትሎ ለተጎጂ ወገኖች የዕለት ደራሽ ምግብና ምግብ-ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን በአግባቡ እያደረሰ ነው ብለዋል።ሆኖም ባለፈው ሳምንትም በክልሉ በመካከለኛው አዋሽ ስር በሚገኙ ወረዳዎች ጎርፍ በመከሰቱ የተጎጂዎቹ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።እስካሁን በክልሉ ከ17 ሺህ ኩንታል በላይ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን ጨምሮ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመጡ አካላት የተሰበሰበው ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት አቶ መሐመድ አስታውቀዋል።በክልሉ መንግሥት እና ተጎጂዎች ስም ሁሉንም ኢትዮጵየዊያን ላሳዩት አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሶማሊያ የድጋፍ ተልዕኮ (UNSOM) እስከ ቀጣዩ ዓመት መጨረሻ ባለበት እንዲቀጥል ወሰነ!
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ ያለው ድጋፍ ሰጪ ተልዕኮ (UNSOM) እስከ ቀጣዩ ዓመት መጨረሻ ወርሃ ነሃሴ ድረስ እንዲቀጥል ወሰነ፡፡የሶማሊያ መንግስትንና እና የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር (AMISOM) ን እየደገፈ ያለፉትን 8 ዓመታት በሞቃዲሾ ያሳለፈው ተልዕኮው እስከ ቀጣዩ ዓመት ነሃሴ 30 ድረስ ባለበት እንዲቀጥል ነው ምክር ቤቱ የወሰነው፡፡UNSOM እ.ኤ.አ ከ2013 ጀምሮ በተለያዩ የጸጥታና ደህንነት፣የፖለቲካ፣ የሰብዓዊ እና ሌሎችም ድጋፎች ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡
[አል ዐይን]

ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዲሱን የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በዛሬው ይፋ አደረገ።
የፌዴራል ፖሊስን የደንብ ልብስን በአዲስ መቀየር ያስፈለገበት ምክንያት ልብሱ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ላይ በመቆየቱ መሆኑን የደንብ ልብሱን ይፋ ያደረጉት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ገልጸዋል።ከዚህ በተጨማሪም በቀድሞው የደንብ ልብስ ተጠቅመው የተለያዩ ወንጀሎች ሲፈፀሙ የነበሩ አካላት በመበራከታቸው መሆኑንም እንደምክንያት አስቀምጠዋል።
[አሐዱ ሬዲዮ]
Photo: EBC

በጉለሌ ክፍለከተማ ከመሬት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ መስሪያ ቤቱ የሄዱ ተገልጋዮችን ጉዳይ እናስፈጽማለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ ከተዘረጋው ሰንሰለት በተጨማሪ ደላሎችም ይገኙበታል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ከተገልጋዮቹ ጋር በመሆን ባደረገው ተከታታይ ክትትል በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት እንዲከፈላቸው የጠየቁትን ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ህብረተሰቡም በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚችለውን አገልግሎት ገንዘብ በመቀበል በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት አካላትን በማጋለጥ ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በኩል ለህዝብ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል።
[Addis Ababa Mayor Office]

ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ | ነፍስ ይማር
ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ባደረበት ድንገተኛ ህመም ዛሬ አርፏል። ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ በድንገት የታመመ ሲሆን ባለፈው ማክሰኞ ከአይደር ሆስፒታል በአስቸኳይ ወደ ጥንቁር እንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህክምና የተላከ ሲሆን ዛሬ አመሻሹን ማረፉን ከቤተሰቡ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ለሞት ያበቃው የደም ካንሰር ነው የተባለ ሲሆን ለቀናት የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ነበር።
ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ እስከለ እለተሞቱ ድረስ በድመፂ ወያነ ቴሌቪዥን እየሰራ የነበረ ሲሆን ቀደም ሲል ለበርካታ አመታት በአዲስ አበባ ፋና ሬዲዮና ፋና ቴሌቭዥን ሰርቷል።
ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ባለትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር።
ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ አውሎ ሚዲያ ፍሬ ከናፍር ፕሮግራም ላይም በተደጋጋሚ ተሳትፏል።
ምንጭ:- አውሎ ሚዲያ
በጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለወዳጆቹ ለቤተሰቡና ለሙያ አጋሮቹ መፅናናትን ይመኛል።
@Yenetube @Fikerasseda

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡
በዚሁ መሰረት፦
1. ወይዘሮ አልፍያ ዩሱፍ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ
2. አቶ ኤፍሬም ግዛው በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
3. አቶ መለሰ አለሙ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
[Addis Ababa City PS]